cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
پست‌های تبلیغاتی
262
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

"የአዕምሮ ለውጥ" <አዕምሮን እንደ ዛፍ ልናስበው እንችልለን ስሮቿ የነገሮችን መጨረሻ ማስተዋል፣ግንዷ ትዕግስት ፣ቅርንጫፎቿ ዕውቀት፣ቅጠሎቿ መልካም ስነ-ምግባር፣ ፍሮዎቿ ደግሞ ጥበብ እንደሆነች ዛፍ > (ኢማም ኢብኑል ቀይም ) የአዕምሮ ለውጥ በተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን የኛንም እግዛ ይፈልጋል:: አዕምሮ ልክ እንደ መሬት ነው::ገበሬው እኛ ነን ::ገበሬው መሬቱን ዝምብሎ ያገኘውን አይዘራበትም :: በመጀመሪያ መሬቱ ለዘሩ እንዲስማማ ያስተካክላዋል :: ያለሰልሰዋል ከዛም ምርጥ ዘሩን ይዘራል ::እኛም አዕምሯችን ለመልካም ዘር ዝግጁ ማድርግ እና መልካሙን እየመረጡ መዝራት ያስፈልጋል:: ገበሬው ዘሩን ከዘራ ቡሃላ ለፍሬ እስኪያበቃ ድረስ ይንከባከቧል :: እሱ ከዘራው ምርጥ ዘር ውጪ የበቀለውን አረም ይነቅልለታል ፣ እኛም ሚዲያዎች ፣ ይምንቀርባቸው ሰዎች ፣ ጏደኞቻችን ወዘተ ....እኛ ከዘራነው ውጪ ይዘሩብናል ፣ የተዘራብን ደግሞ ይበቅላል ::ልክ እንደ ገበሬው ከመልካሙ መሃከል አረሙን ማፅዳት ይኖርብናል :: ገበሬው ምርጥ ዘሩን ሲሰበስብ ከዘራው በብዙ እጥፍ እንደሚሰበስብ እኛም የዘራነውን ማንነት ፣ ህይወት ፣ ስኬት እንጎናፀፋለን:: ይህንን ለውጥ መቀበል ፣ማገዝ ያስፈልጋል :: ልክ እንደ ገበሬው ማደበሪያ አላህ ሱብሃነሁ ወተአላን በማወቅ ፣ ሆነ የተመረጡ መፅሐፍት ፣ስልጠናዎችን ፣ ኢስላማዊ ኦዲዎች ፣ቪዲዎችን በመመገብ ልናሰድገው ፣ ልንከባከበው እና ፍሬያማ እናድርገው ዘንድ ከኛም ብዙ ነገሮችን ማድረግ ያስፈልጋል :: ‎‌ؕ اِنَّ اللّٰهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوۡمٍ حَتّٰى يُغَيِّرُوۡا مَا بِاَنۡفُسِهِمۡ‌ؕ "አላህ በሰዎች ያለን ሁኔታ አይቀይርም ::በነፍሶቻቸው ውስጥ ያለን እስኪቀይሩ ድረስ"(እር-ረዐድ 11) join 👉 https://t.me/Darularkam ▶️ የነብያት ታሪክ ▶️ ኢስላማዊ ኣስተሳሰብ ▶️ የእውቀት ኣድማሳችንን ለማስፋት JOIN ያድርጉ
نمایش همه...
ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104

"ነገህን ዛሬ መጀመር ትችላለህ" ነገ ከዛሬ ጋር አብሮ አለ ::(ዐሊይ ኢብኑ አቢጧሊብ ) የሰው ልጅ የዛሬ ማንነቱ የትናንት ውጤቱ ነው። ትናንት ለዛሬ መነሻ ቢሆንም የትናንት እስረኞች መሆን የለብንም። ትናንት ላይመለስ ሄዷል። ፅሀይዋ ጠልቃለች። ስለዚህ የአሉታዊ ጥላው አንተ ላይ እንዲያጠላ አትፍቀድለት። ነገ አዲስ ቀን ነው። አዲስ ፀሀይ ይፈነጥቃል... እድሜህም በአንድ ቀን ጨምሯል::የምድራዊ ቆይታህም በአንድ ቀን ቀንሷል :: ስለዚህም ከዘሬ ጋር ኑር ::ማንም ወደ ሗላ ተመልሶ እንደ አዲስ መጀመር አይችልም ::ነገር ግን ዛሬን መነሻ እድርጎ አዲስ መድረሻ እና መዳረሻ መፍጠር ይችላል ::ትላንትን መለወጥ ባትችልም ዛሬ ግን በእጅህ ነው :: ዛሬን ለመለወጥ ተነሳ:: join 👉 https://t.me/Darularkam ▶️ የነብያት ታሪክ ▶️ ኢስላማዊ ኣስተሳሰብ ▶️ የእውቀት ኣድማሳችንን ለማስፋት JOIN ያድርጉ
نمایش همه...
ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104

"ተወኩል " አብዛኛው ሰው በአላህ መመካት ማላት ምን ማለት እንደሆነ ግክፅ ግንዛቤ የላቸውም:: ከፊሎች ምክንያት(ሰበቡን ) በማድረስ፣ ሀላፊነትን በመወጣት ብቻ ይብቃቀሉ ::እነዝህ ረዥሙን መንገድ ብቻቸውን ለመጏዝ ይገደዳሉ ::ሌሎች ደግሞ እጃቸውን አጣጥፈው ይቀመጡና የአላህን እርዳታ ይጠብቃሉ ::ሳያርሱ አዝመራን ፣ሳይጋግሩ መብላትን ፣ሳይታጠቡ መፅዳትን .....ይፈልጋሉ :: እነኚህ አጉል ተስፈኞች ናቸው:: እርግጥ ነው ለአላህ የሚሳነው የለም ::ያለእኛ ተሳትፎ የምንፈልገውን ነገር ሁሉ ሊያሟላልን ይችላል ::ነገር ግን የምድርን ስርኣት እንዲህ አይደለም ያስቀመጠው ::የኣደም ልጆች በሁለት ክንፍ እንዲበሩ ይፈልጋል ::አንደኛው ክንፍ በእርሱ ላይ መመካት ሲሆን ፣ሌላኛው ሰበቦችን ማድረስ ::የስኬት ምንጩ በአላህ መደገፍ ነው :: የስኬትን ረዥም ጉዞ ብቻህን አትችላውም ::በራስ ተብቃቅቶ መጏዝ ወንዝ አያሻግርም ::በግል ጥረት ዳር ለመድረስ የሚጥር ሁሉ ለግል ጥረታቸው ይታዋሉ :: ትልቁን ከፍታ ብቻቸውን ለመውጣት ይገደዳሉ :: ያ በአላህ የተመካው ግን በስንዝር ጥረት የክንድ ያህል ያራመዳል::ከጥረቱ በላይ ውጤት ያገኛል :: አስታውስ👉የተኛ ውሃ ይሸታል፤ የታሰረ ወፍ ይሞታል፤ የተጠፈነገ አንበሣ ይዋረዳል ። የሰው ልጅ በአንድ ቦታ ላይ ሆኖ ውጤት ማምጣት አይቻለውምና በአንድ ቦታ አትቀመጥ አደራህን አትሰልች አትታክት፣ ስልቹ ሰው ግዴታውን የመወጣት ብቃት የለውም፡፡ የሚታክት ሰው ክብሩን አይጠብቅም፡፡ ስለሆነም ታገስ፤ በርታ ፤ ጽነ፡፡ join 👉 https://t.me/Darularkam ▶️ የነብያት ታሪክ ▶️ ኢስላማዊ ኣስተሳሰብ ▶️ የእውቀት ኣድማሳችንን ለማስፋት JOIN ያድርጉ
نمایش همه...
ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104

"ማንነትን ፍለጋ" እኔ ማን ነኝ ብለህ እራስህን ጠይቀው ማንነትህን ጠንቅቀህ ስታውቅ ዋጋህን ታውቃለህ :: وَفِي أَنفُسِكُمْ ۚ أَفَلَا تُبْصِرُونَ ( 21 ) በነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?› ስለዚህ አንተ ውስጥ አስገራሚ ብቃትና የእውቀት ዝንባሌ አለ፤ ለመሆንና ልትችለው የተፈጠርክለትን ማንነት ! ችላ ብለህ ለአንተ ያልተሠጠውን ማንነት ሆኖ ለመገኘት እና ከሆንከው ማንነትህ ጋር የማይሄደውን ለማወቅና ለማድረግ መሞከር ማለቀቂያ የሌለው ጉዞ ይሆንብሃል፡፡ ስለዚህ በዛ በተሰጠህ ነገር ላይ ልፋ ስኬታማ ትሆናለህ፡፡ ሰው ከእንስሳ የሚለየው የተፈጠረበትን አላማ ፤ የሚኖርበትን ምክንያት፤ የሚጏዝበትን መነሻና መድረሻ በአግባቡ መረዳቱ ነው :: እንስሳዎች በአጠቃላይ ለሰው ልጅ አገልግሎት እያደሩ የሰው ልጅ ግን የተፈጠረበትን ዋና አላማ ከዘነጋ ከእንስሳ በታች ሆነ ማለት ነው :: እንስሳት አንተን በማገልገል አላማ ላይ ተፈጥረዋል ::ይህንን ተልእኳቸውንም በአግባቡ ተወጥተዋል :: አንተ ደግሞ የሁለት አለም ስኬትን ለመቆናጠጥ ተፈረሃል ::ወደ እዚች ምድር የመጣኸው ለምክንያት ነው፤ እናም አንተ የዚህች አላም ገፅ ውብ እና ሙሉ ይሆን ዘንድ እንደ አንዱ ጡብ ነህ :: አስታውስ አንተን መሆን የሚችል ምትክ የለህምና ህይወትን በአላማ እና በእቅድ በመምራት ልታሳካቸው ግድ ይላል :: ይህቺን ሀገር (ዱኒያን ) በከይር ስራ በማሳመር አኪራን ግዛበት ! ይህም ነው የሚማጥንህ :: አላህ በህይወት መቆየታችንን ለመልካም ስራ ጭማሪ ያድርግልን ህልፈታችንን ደግሞ ከመጥፎ ስራ መገላገያ ያድርግልን ኣሚን!!! join 👉 https://t.me/Darularkam ▶️ የነብያት ታሪክ ▶️ ኢስላማዊ ኣስተሳሰብ ▶️ የእውቀት ኣድማሳችንን ለማስፋት JOIN ያድርጉ
نمایش همه...
ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104

"በማይመለከተው ነገር የተጠመደ የሚመለከተው ነገር ያመልጠዋል (ነቢዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)" ትልቅ አገላለጽ ነው :: የአንድ አማኝ ጥሩ የእምነቱ ተከታይነት መገለጫው የማይመለከተውን ነገር መተው ነው ::በሚመለከተውና በሚጠቅመው ነገር ብቻ መጠመዱ ነው ::የሰው ልጅ በምድራዊ ቆይታው ሁለት ነገሮችን ይጋፈጣል :: አንድ የሚመለከተው፣ ለለውጡ የሚረዳው ፣ ለአላማው ስኬት ግብአት የሚሆነው ....ሲሆን ፣ ሌላው ደግሞ የማይመለከተው ፣ የማይጠቅው ፣ ካሳመረው የህይወት ግብ ተቃራኒ የሆነ ነው :: በአንድ የተወጠር ሌላኛው ያመልጠዋል :: ተዲያ አንተም ለእድገትህና ለጀመርከው ጉዞ አጋዥ በሚሆንህ ነገር ላይ ብቻ አትኩር ..... ያኔ በአላህ ፍቃድ ወደ ስኬት መድረስህ የእርግጠኝነት ጉዳይ ይሆናል:: join 👉 https://t.me/Darularkam ▶️ የነብያት ታሪክ ▶️ ኢስላማዊ ኣስተሳሰብ ▶️ የእውቀት ኣድማሳችንን ለማስፋት JOIN ያድርጉ
نمایش همه...
ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104

"ጊዜ" ህይወት እረቂቅ ምስጢር ናት። አላህ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህችን ምስጢራዊ ህይወት እድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት አደለን። ይህችንም ከረጢት በውስጧ እድል በተሰኙ ፈርጦች ተሞልታለች። ከረጢቷ እንዳትሰረቅ ያለ ጊዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጭ እንዳትሆን ፣ ሀላፊነቱን አላህ ለኛው ነው የሰጠን። ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜ ያልተጠቀምንባቸው የዕድል ፈርጦች ከጊዜው ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈው ይነጉዳሉ ። ስኬት በትጋትና በስራ የተለወጡ ዕድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደሉም። ድህነት የባከኑ ዕድሎችና ያልተጠቀምንበት ዕድሜ ውጤት ነው "ዛሬ ከቀረችው የህይወት ቆይታህ የመጀመሪያዋ ቀን ናት እና ተጠቀምበት " ሐሰን አልበስር join 👉 https://t.me/Darularkam ▶️ የነብያት ታሪክ ▶️ ኢስላማዊ ኣስተሳሰብ ▶️ የእውቀት ኣድማሳችንን ለማስፋት JOIN ያድርጉ
نمایش همه...
ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104

የነቢዩ__ሙሐመድ ﷺ የሕይወት__ታሪክ #ክፍል_ 11 አሁን ከዘረዘራችሁት ነገር ሁሉ አንዱን እንኳ ብትሉ ውሸታምነታችን ይታወቅብናል። ይሁን እንጂ ትንሽ ተቀባይነት ሊኖረው የምችለው ድግምተኛ (ሳሒር) ነው፤ ንግግሮቹም ድግምት ናቸው ብትሉ ነው። በድግምት አባትና ልጅን ፣ ባልና ምስትን፣ ወንዳማማቾችን ፣ ዘመድማማቾችን ይለያያል ብትሉ ይሻላል።» አላቸው። በዚሁ ተስማምተው ተለያዩ። ሰዎች ወደ ሐጅ ሲመጡ መንገድ ላይ በመቀጥ ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያስጠነቅቋቸው ጀመር። ማንኛውንም ሰው ስለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሳይነግሩትና ሳያስጠነቅቁት አያልፍም። ሰው ሁሉ ነቢዩን ሳያያቸውና ከሳቸውም ሳይሰማ ስለሳቸው መኖር አወቀ። የሐጅ ወቅት ሲገባ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ ሐጃጆች መሰብሰብያዎችና ማረፊያዎች እየሄዱ ወደ ኢስላም መጣራት ጀመሩ። እንዲህ ይሉዋቸውም ነበር፦ “እናንተ ሰዎች ሆይ! ላኢላህ ኢለላህ (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚገዙት ሌላ አምላክ የለም) በሉ፤ የምትፈልጉትን ታገኛላችሁና ፤ ትድናላችሁ።” አቡለሀብ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እየተከተላቸው ...ያስተባብላቸውና ያስቸግራቸው ነበር። ዐረቦች ከዚያ ዓመት ሐጅ ወደየ አገራቸው ሲመለሱ የነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጉዳይ አውቀው ነበር የተመለሱት። የሳቸው ነገር በዐረብ አገር ሁሉ ተስፋፋ። ዳዕዋን ለመዋጋት ቁረይሾች የተጠቀሙበት የተለያዩ ዘዴዎች ሐጅ አብቅቶ ቁረሾች ወደ-የቤታቸው ተመልሰው ከተረጋጉ በኋላ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ አላህ ጥሪ በማድረጋቸው የተፈጠረውን ችግር መፍትሔ ሊያገኙበት እንደሚገባ ወሰኑ። አሰቡ ፤ ተወያዩም። ከዚያም ይህን ዳዕዋ ለመዋጋትና ለማጥፋት የተለያዩ ዘዴዎችንና መንገዶችን መረጡ። ከነዚህም የሚከተሉት ይገኙበታል፦ 1/ በነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና በሙስሊሞች ላይ መሳለቅና ማሾፍ በማሾፍና በመሳለቅ ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና ሙስሊሞችን ማዋረድና ሥነ-ልቦናዊ ጥንካሬያቸውን ማዳከም ፈለጉ። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ድግምት የተደረገበት ሰው ነው፤ ገጣሚ ነው ፤ እብድ ነው፤ ሸይጧኖች የሚሰበሰቡበት ጠንቋይ ነው፤ ድግምተኛ ውሸታም ነው፤ ቀጣፊ ነው ይሏቸው ነበር። በሌሎች ስድቦችም ይሰድቧቸዋል። ይወነጅሏቸዋልም። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲሄዱና ሲመጡ ሲያዩዋቸው የቁጣና የጥላቻ አመለካከት ይመለከቷቸዋል። ይህን ነገር በመግለጽ አላህ (ሱ.ወ) በቁርአን እንዲህ ይላል፦ وَإِن يَكَادُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَيُزْلِقُونَكَ بِأَبْصَـٰرِهِمْ لَمَّا سَمِعُوا۟ ٱلذِّكْرَ وَيَقُولُونَ إِنَّهُۥلَمَجْنُونٌۭ ﴿٥١﴾ “እነሆ እነዚያም የካዱት ሰዎች ቁርአኑን በሰሙ ጊዜ በአይኖቻቸው ሊጥሉህ (ሊያጠፉህ) ይቃረባሉ፤ እርሱም በእርግጥ እብድ ነው ይላሉ።” (አል-ቀለም፥ 68፡ 51) ሲያዩ ያላግጥባቸው ነበር። አላህ እንዲህ ይላል፦ وَإِذَا رَءَاكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَـٰذَاٱلَّذِى يَذْكُرُ ءَالِهَتَكُمْ وَهُم بِذِكْرِ ٱلرَّحْمَـٰنِ هُمْ كَـٰفِرُونَ ﴿٣٦﴾ “እነዚያም የካዱት ሰዎች ባዩህ ኢዜ መሳለቂያ አድርገው እንጂ አይይዙህም፤ እነሱ በአልረሕማን መወሳት እነርሱ ከሐዲዎች ሲሆኑ ያ አማልክቶቻችሁን (በክፉ) የሚያነሳው ይህ ነውን? (ይላሉ)።” (አል-አንቢያእ፥ 21 ፡ 36 ደከም ያሉ ሶሓቦችን ሲያገኙዋቸው ደግሞ «የምድር ነገሥታት መጡ» እያሉ ይሳለቁባቸዋል። አላህ እንዲህ ይላል፦ وَكَذَ ٰلِكَ فَتَنَّا بَعْضَهُمبِبَعْضٍۢ لِّيَقُولُوٓا۟ أَهَـٰٓؤُلَآءِ مَنَّ ٱللَّهُ عَلَيْهِم مِّنۢ بَيْنِنَآ ۗ أَلَيْسَ ٱللَّهُ بِأَعْلَمَ بِٱلشَّـٰكِرِينَ﴿٥٣﴾ “እንደዚሁም «ከመካከላችን አላህ የለገሰላቸው እነዚህ ናቸውን» ይሉ ዘንድ ከፊላቸውን በከፊሉ ሞከርን፡፡ አላህ አመስጋኞቹን ዐዋቂ አይደለምን።” (አን-አንዓም፥ 6፡ 53) إِنَّ ٱلَّذِينَ أَجْرَمُوا۟كَانُوا۟ مِنَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ يَضْحَكُونَ ﴿٢٩﴾ وَإِذَا مَرُّوا۟ بِهِمْ يَتَغَامَزُونَ ﴿٣٠﴾ وَإِذَاٱنقَلَبُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَهْلِهِمُ ٱنقَلَبُوا۟ فَكِهِينَ ﴿٣١﴾ وَإِذَا رَأَوْهُمْ قَالُوٓا۟ إِنَّ هَـٰٓؤُلَآءِ لَضَآلُّونَ ﴿٣٢﴾ “እነዚያ ያምመፁት በነዚያ ባመኑት በእርግጥ ይስቁ ነበሩ። በነሱ ላይ ባለፉ ጊዜ ይጠቃቀሱ ነበር። ወደ ቤተሰቦቻቸውም በተመለሱ ጊዜ (በመሳለቃቸው) ተደሳቾች ሆነው ይመለሱ ነበር። ባዩዋቸው ጊዜ እነዚህ በርግጥ ተሳሳቾች ናቸው ይሉ ነበር።” (አል-ሙጠፍፊን፥ 83 ፡ 29-32) በመሳለቅና ማላገጥ፣ በነገር መውጋትና ሰዎችን ማስሳቅ ስላበዙ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተሰማቸው። ይህንን በማስመልከት አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦ وَلَقَدْنَعْلَمُ أَنَّكَ يَضِيقُ صَدْرُكَ بِمَا يَقُولُونَ ﴿٩٧﴾ «አንተም እነሱ በሚሉት ነገር ልብህ የምትጨነቅ መሆኑን በእርግጥ እናውቃለን።» (ሱረቱ አል-ሒጅር፥ 15:97) ከዚያም አላህ (ሱ.ወ) አረጋጋቸው። መጠበቡንና መጨነቁን የሚያስወግድላቸውን ነገር ገለጸላቸው። 2/ ሰዎች የነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዳዕዋ እንዳይሰሙ እንቅፋት መሆን ► ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ አላህ ጥሪ ለማድረግ ሲዘጋጁ ባዩዋቸው ቁጥር ህውከትና ረብሻ ለመፍጠር፣ ድምጽ ከፍ አድርጐ ለመንጫጫትና ሰዎችን ለማባረር እንዲሁም ለሚያደርጉት ጥሪ ማብራሪያ ለመስጠት ዕድል እንዳያገኙ ለማድረግ ወሰኑ። በዚህ ጉዳይ ላይ ለመረዳዳት እርስ በርሳቸው አደራ ተባባሉ። አላህ እንዲህ ይላል፦ وَقَالَ ٱلَّذِينَكَفَرُوا۟ لَا تَسْمَعُوا۟ لِهَـٰذَا ٱلْقُرْءَانِ وَٱلْغَوْا۟ فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَغْلِبُونَ ﴿٢٦﴾ “እነዚያም የካዱት፣ ይህንን ቁርአን አታዳምጡ፤ ታሸንፉም ዘንድ (ሲነበብ) በርሱ ውስጥ ተንጫጩ አሉ።” (ሱረቱ ፉሲለት፥ 26) ቁረይሾች መንጫጫቱንና ህውከት መፍጠሩን በከፋ ሁኔታ ቀጠሉበት። በዚህም ምክንያት ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቁረይሾች በሚሰበሰቡበት ቦታ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንበብ (መቅራት) የቻሉት አል-ነጅምን ብቻ ነበር። ይህ የሆነው ነቢዩ ከሆኑ በአምስተኛው ዓመታቸው በረመዷን ወር ነበር። ይቀጥላል.... join 👉 https://t.me/Darularkam ▶️ የነብያት ታሪክ ▶️ ኢስላማዊ ኣስተሳሰብ ▶️ የእውቀት ኣድማሳችንን ለማስፋት JOIN ያድርጉ
نمایش همه...
ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104

"መልካም ስራ የሚሰራ ሰው አይወድቅም:ቢወድቅም እንኳ አይሰበርም " (ሙሀመድ ኢብን አል -ሀነፊይ) መልካል ስራ ክመጥፎ አወዳደቅ ይከለከላል :: ይህ የሆነው በሰራኸው አንድ መልካም ሥራ፤ በገላገልከው ጭንቀት ፤ በተባበርከው ሰው ጉዳይ ፤ አሊያም ባስወገድከው ችግር ሳቢያ:: አሊይ ኢብን አቢ ጣሊብ እንዲህ ያላሉ :- ሁሉንም ድምፆች በሚሰማው ጌታ እምላለው!...ማንኛውም በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ደስታን የፈጠረ ግለሠብ አላህ ሱ.ወ ከዚህ ደስታ እዝነትን ይፈጥርለታል፤ ታዲያ መከራ በእርሱ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ይህች እዝነት እንደ ጎርፍ ዉሃ ወደ መከራው ትፈስበታለች፤ እናም ያልለመደች ግመል እንደምታስበረግግ ይህንን መከራ አስበርግጋ ታባርራቸዋለች:: የከይር ዛር ጀነትን ያፈራል ፤ በዱንያ ውስጥ የመልካም ሥራ ጠራራ ፀሐይን የተቋቋመ በአኬራ ኒዕማ ጥላ ስር ይውላል :: የመልካም ሥራ ተነሳሽነትህ የምር ሆኖ ለመተግበር ቆራጥ ብትሆን ረሱል ﷺ ቀብራቸው ውስጥ ሆነው እንዴት ይደሰቱብህ !!! join 👉 https://t.me/Darularkam ▶️ የነብያት ታሪክ ▶️ ኢስላማዊ ኣስተሳሰብ ▶️ የእውቀት ኣድማሳችንን ለማስፋት JOIN ያድርጉ
نمایش همه...
ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104

የነቢዩ__ሙሐመድ ﷺ የሕይወት__ታሪክ "ከባለፈው የቀጠለ.." ሰዎች ሲሰበሰቡ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦ «ከዚህ ተራራ ሥር በሸለቆው ውስጥ እናንተን ለመውረር የመጣ ፈረሰኛ ሠራዊት አለ ብላችሁ ታምኑኛላችሁን?» ሲሉ ጠየቁዋቸው። ‹፣አዎ! እናምንሃለን፣ ከአንተ እውነትን እንጂ ውሸትን ሰምተን አናውቅም። ሲሉ መለሱላቸው። “እኔ በርግጥ ከብርቱ ቅጣት ነው የማስጠነቅቃችሁ። የኔና የናንተ ምሳሌ ወራሪ ጠላትን እንዳየ ሰውና እሱን ቀድሞ በመሄድ ወገኖቹን እንዳያጠቃ በመፍራት ከፍታ ቦታ ላይ ወጥቶ «ያ ሰባሓህ) እያለ እንደሚጣራ ሰው ምሳሌ ነው።» አሉ። ከዚያም ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ፣ የሌለ መሆኑንና ሙሐመድ ደግሞ መልዕክተኛው እንደሆነ እንዲመሰክሩ ጥሪ አቀረቡላቸው። ይህንን ከመሰከሩ አዱንያን እንደሚቆጣጠሩዋትና በአኺራም ከአላህ ቅጣት ነፃ እንደሚሆኑ ነገሩዋቸው። ከዚያም እሳቸው ከአላህ ዘንድ ባመጡት ነገር ካላመኑና በሽርካቸው የሚገፉበት ከሆነ የአላህ ቅጣት እንደሚጣብቃቸው አስጠንቀቁዋቸው። መልዕክተኛ ቢሆኑም ከአላህ ቅጣት ሊያድኑዋቸው ምንም እንደማይችሉና ምንም ሊጠቅሙዋቸው እንደማይችሉ ነገሩዋቸው። በማስጠንቀቂያቸው ቁረይሾችን ባጠቃላይና ግለሰቦችንም በተለይ በስሞቻቸው እየጠሩ ምንም ሊጠቅሙዋቸው እንደማይችሉ ነገሩዋቸው። እንደሚከተለው ነበር፦ «እናንተ የቁረይሽ ሕዝቦች ሆይ! ነፍሶቻችሁን ከአላህ ግዙ፣ ነፍሶቻችሁን ከእሳት አድኑ፤ እኔ ሊጠቅማችሁም ሆነ ሊጐዳችሁ አልችልም፣ ከአላህ ቅጣት ምንም ልከላከልላችሁ አልችልም። «በኒ ከዕብ ቢን ሉእይ ሆይ! ነፍሶቻችሁን ከእሳት አድኑ፣ እኔ ሊጠቅማችሁም ሆነ ሊጐዳችሁ አልችልም። «በኒ ሙራ ሆይ! ነፍሶቻችሁን ከእሳት አድኑ፣ እኔ ሊጠቅማችሁም ሆነ ሊጐዳችሁ አልችልም። «በኒ ዐብድ ሸምስ ሆይ! ነፍሶቻችሁን ከእሳት አድኑ።» «በኒ ዐብድ መናፍ ሆይ! ነፍሶቻችሁን ከእሳት አድኑ፤ እኔ በርግጥ ሊጠቅማችሁም ሆነ ሊግጐዳችሁ አልችልም። «በኒ ሃሺም ሆይ! ነፍሶቻችሁ ከእሳት አድኑ። «በኒ ዐብዱል ሙጠሊብ ሆይ! ነፍሶቻችሁ ከእሳት ጠብቁ፤ እኔ በርግጥ ሊጠቅማችሁም ሆነ ሊጐዳችሁ አልችልምና ፤ ከአላህ ቅጣት ምንም ሊከላከልላችሁ አልችልም። ከገንዘቤ የፈለጋችሁትን ያህል ጠይቁኝ፤ ከአላህ ቅጣት ግን ምንም ሊጠብቅችሁ አልችልም። «ዐባስ ቢን ዐብዱል ሙጠሊብ ሆይ! ከአላህ ቅጣት ምንም ሊጠብቅህ አልችልም። «ሰፊያ ቢንት ዐብዱል ሙጠሊብ - የአላህ መልዕክተኛ አክስት ሆይ! ከአላህ ቅጣት ምንም ልጠብቅሽ አልችልም። «ፋጢማ ቢንት ሙሐመድን ረሱሊላህ ሆይ! የፈለግሽውን ነገር ጠይቂኝ ፤ ነፍስሽን ግን ከእሳት አድኚ፤ እኔ ከአላህ ቅጣት ምንም ልጠብቅሽ አልችልምና። ይሁን እንጂ ከኔ ያላችሁን ዝምድና በተገቢው እቀጥላለሁ። ማስጠንቀቂያቸውን ሲያጠቃልሉ ተሰብሳቢዎቹ ተበተኑ። አቡለሀብ ብቻ ክፉ ነገር ተናገራቸው እንጂ ሌሎቹ ሲሰሙት ነበር በወቅቱ ተቃውሞ ም ሆነ ድጋፍ ማድረጋቸው አልተዘገበም። አቡለሀብ ‹፣ለዚህ ነው የሰበሰብከን? ጥፋትና ኪሳራ ለአንተ ይሁን!» አላቸው። በአፀፋው አላህ (ሱ.ወ) የሚከተለውን አንቀጽ አወረደ፦ تَبَّتْ يَدَآ أَبِى لَهَبٍۢ وَتَبَّ ﴿١﴾ “የአቡ ለሀብ ሁለት እጆች ከሰሩ (ጠፉ፤እርሱ) ከሰረም።“ (ሱረቱ አል-መሰድ፥ 1) ባጣቃላይ ቁረይሾች ግን በዚህ ድንገተኛ ማስጠንቀቂያ ስለተደናገጡና ግራ ስለተጋቡ በዚህ ጉዳይ አቋማቸውን መለየት አልቻሉም። በወቅቱ ተቃዋሚም ደጋፊም አልሆኑም። ነገር ግን ወደየቤታቸው ተመልሰው ነፍሶቻቸው ተረጋግተው ከድንጋጤያቸው መለስ ብለው ሲረጋጉ ኩራትና ትምክህት ይሰማቸው ጀመር። ይህንን ጥሪና ማስጠንቀቂያ አቀለሉት፤ አሾፉበትም። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እነሱ በተሰበሰቡበት ለማለፍ ከሄዱ ያሾፉባቸው ጀመር። አላህ መልዕክተኛ አድርጐ የላከው ይህንን ሰው ነው? ይህ የአቡ ከብሻ ልጅ!? አላህ ከሰማይ ያናግረዋል!» ሌላም ሌላም እያሉ ይሳለቁባቸዋል። አቡከብሻ ማለት ከነቢዩ አያቶች አንዱ ነው- በእናታቸው በኩል። አቡከብሻ ከቁረይሽ ሃይማኖት በማፈንገጥ ነሷራ ሆኖ ነበር። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የቁረይሽን ሃይማኖት ሲቃወሙ ቁረይሾች ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለማነወር፣ ለመናቅና በነገር ለመውጋት ሲሉ ከአቡከብሻ በማመሳሰል የአቡከብሻ ልጅ አሉዋቸው። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዳዕዋውን ቀጠሉ። የአላህን ቁርአን እያነበቡላቸው በየክለቦቻቸውና በየስብሰባ ቦታዎቻቸው በግልፅ መጣራት ጀመሩ። መልዕክተኞች ሁሉ ወደ ተጣሩበት የአላህ ሃይማኖት መጣራታቸውን ገፉበት። فَقَالَ يَـٰقَوْمِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُۥٓ ...... ﴿٥٩﴾.﴾.....﴿ “....ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ ለናንተ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፤ .....” (ሱረቱ አል-አ’ዕራፍ፥ 59፣ 65፣ 71፣ 85) በነሱ ፊት አላህን መገዛት ጀመሩ። በገሃድ በቀን ሰዎች በተሰበሰቡበት በከዕባ ፊት ለፊት ይሰግዱ ነበር። ጥሪያቸው በተወሰነ ደረጃ ተቀባይነትን አገኘ። ጥቂት የማይባሉ ሰዎች አንድ በአንድና ተራ በተራ ወደ አላህ ሃይማኖት ገቡ። በሙስሊሞችና በቤታቸው ውስጥ ባልሰለሙት ቤተሰቦች መሀል መጠላላትና መራራቅ ተፈጠረ። #ክፍል_ 10 "ቁረይሾች ሑጃጆችን ከዳዕዋ ለማገድ ያደረጉት ውይይት" ► ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባደረጉት ጥሪ ምክንያት የተፈጠረው ሁኔታ ቁረይሾችን አስከፋቸው፣ አሳሰባቸውም። የሐጅ ወቅት ለመድረስ የተወሰኑ ቀናት ብቻ ስለቀሩ የሑጃጆች ጉዳይ አሳሰባቸው። ስለዚህም ወሊድ ቢን አል-ሙጊራ ዘንድ ተሰብስበው ተወያዩ። ወሊድ የዕድሜ ባለፀጋና በነሱ ዘንድ የተከበረ ሰው ነበር። ውይይቱ እንደሚከተለው ነበር፦ ► ወሊድ፦ “የቁረይሽ ሕዝቦች ሆይ! የሐጅ ወቅት ደረሰ፤ የዐረብ ልዑካኖች ይመጡባችኋል። ስለዚህ ሰው (ስለነቢዩ ﷺ ) አስቀድመው ሰምተዋል። ስለዚህ አንድ ዓይነት ሐሳብ ያዙ፣ እንዳትለያዩ ፣ ከፊላችሁ ከፊላችሁን እንዳያስዋሽ።” አላቸው። ► ቁረይሾች፦ «ማለት ያለብንን እስቲ አንተ ንገረን» አሉት። ► ወሊድ፦ « እስቲ እናንተ ንገሩኝና ልስማችሁ።» አላቸው። ► ቁረይሾች፦ «ጠንቋይ (ካህን) ነው እንበል።» ► ወሊድ፦ «ጠንቋይ አይደለም፤ ጠንቋዮችን አይተናቸዋል የነሱ ዓይነት ማጉረምረም የለበትም።» ► ቁረይሾች፦ «እብድ ነው እንበል።» ► ወሊድ፦ «እብድ አይደለም፤ እብደትን አይተናል፤ እናውቀዋለን፤ ሲናገር እንደ እብድ አይኮለተፍም አይተናነቀውም፤ ወስዋስም የለበትም።» ► ቁረይሾች፦ «ገጣሚ (የቅኔ ሰው) ነው እንበል።» ► ወሊድ፦ «ገጣሚ አይደለም፤ ግጥም ሁሉዋንም እናቃታለን፤ ሰሙንም ወርቁንም እናውቃለን።» ► ቁረይሾች፦ «ድግምተኛ (ሳሒር) ነው እንበል።» ► ወሊድ፦ «ድግምተኛም አይደለም፤ ድግምተኞችንና ድግምታቸውን አይተናል፤ እንደነሱ ቋጣሪም ተፊም አይደለም።» ► ቁረይሾች፦ «ታዲያ ምን እንበል።» ► ወሊድ፦ «ወላሂ ንግግሮቹ እጅግ ጥፍጥናና ውበት አላቸው፤ ሥሮቹ የጠለቁ ቅርንጫፎቹ ፍሬያማ ናቸው። ይቀጥላል.... join 👉 https://t.me/Darularkam ▶️ የነብያት ታሪክ ▶️ ኢስላማዊ ኣስተሳሰብ ▶️ የእውቀት ኣድማሳችንን ለማስፋት JOIN ያድርጉ
نمایش همه...
ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104

#የነቢዩ__ሙሐመድ ﷺ #የሕይወት__ታሪክ #ክፍል__9 የምእመናን ዒባዳና እና ተርቢያ የሱረቱ አል ሙደሲር መጀመሪያዎቹ አንቀጾች ከወረዱ በኋላ ወሕይ ተከታትሎ መውረዱን ቀጠለ። ከሱረቱ አል ሙደሲር መጀመሪያዎቹ አንቀጾች በኋላ መጀመሪያ የወረደች ሱረቱ አልፋቲሃ ነች ይባላል። ይህቺ ሱራ አላህን ማወደስን (ሐምድንና) መለመንን (ዱዓ) ያጠቃለለች እንዲሁም ከቁርአንና ከኢስላም የሚፈለጉትን ነገሮች ሁሉ ጠቅለል ባለ መልኩ ያካተተች ናት። ከዒባዳዎች ውስጥም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መጀመሪያ የታዘዙት በሶላት ነው-- ጧት ሁለት ረከዓ። ጂብሪል (ዐ.ሰ) ይህን ይዞት መጥቶ ዉዱእ እና ሶላት አስተማራቸው። ሙሉ ንጽሕና የሙእሚኖች መለያ ምልክት ነበር። «ዉዱእ» የሶላት መስፈርት (ሸርጥ) ነው። ፋቲሃ የሶላት መሠረት ናት። «ሐምድ» እና «ተስቢሕ» (ማመስገንና ማጥራት) የሶላት ውዳሴዎች ናቸው። ሶላት ሁልጊዜ ያከናውኗት የነበረ የምእመናን ዒባዳ ነበረች። ከእይታ ራቅ ወዳሉ ቦታዎች አንዳንዴም ወደ ሸላቆዎችና ተራሮች እየሄዱ ነበር የሚሰግዷት። በመጀመሪያዎቹ የኢስላም ቀናት (ዘመናት) ሌሎች ዒባዳዎች፤ ትእዛዞች (አዋሚር) እና ክልክሎች (ነዋህ) አይታወቁም ነበር። በዚያን ጊዜ ወሕይ ስለተውሒድ የተለያዩ አቅጣጫዎች ያብራራላቸው ነበር። ነፍሶቻቸውን እንዲያጠሩና ጥሩ ባሕሪ እንዲኖራቸው ያነሳሳቸው ነበር። ስለጀነትና ስለእሳት (ጀሃነም) ያብራራላቸው ነበር። ልብን የሚታሰፋና ሩሕን የምትመግብ ግሣጼና ምክርም ይሰጣቸው ነበር። ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶሓቦቻቸውን (ከሽርክ) ያጠሩዋቸው፣ መጽሐፍን (ቁርአንን) እና ጥበብን ያስተምሩዋቸው፣ ልቦቻቸውን እንዲያንጹ ፣ ባህሪያቸውን እንዲያሳምሩና እንዲያጠሩ፣ነፍሶቻቸውን ከመጥፎ ነገር እንዲጠብቁና ከሰዎች ጋር በሚሠሩት ነገር (በቢዝነዝ) እውነተኞች እንዲሆኑ ያደርጉዋቸውና በአጠቃላይ ከጨለማዎች (ዙሉማት) ወደ ብርሃን (ኑር) በማስወጣት ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመሩዋቸው ነበር። የአላህን ዲንና የአላህ የኢማን ገመድ በጥብቅ እንዲይዙ፣ በአላህ ትእዛዝ ላይ እንዲፀኑና እንዲዘወትሩ ያለማምዱዋቸውና ያሰለጥኑዋቸው ነበር። ሦስት ዓመታትን ያሳለፉት በዚህ ዓይነት ሁኔታ ጥሪያቸውን በግለሰቦች ላይ ብቻ በመወሰን ነበር። ቁረይሾች ዳዕዋውን ያወቁት ቢሆንም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በስብሰባ ቦታዎችና በክበቦች ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ወደ ኢስላም አልተጣሩም ነበር- ለሦስት ዓመታት። ከቁረይሾች አንዳንዶቹ አልፎ አልፎ ዳዕዋን የሚቃወሙና በምእመናን ላይ በደል የሚፈፅሙ ቢኖሩም ጠላትነታቸውና ድንበር ማለፋቸው ባጠቃላይ መልኩ አልነበረም። ምክንያቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሃይማኖታቸውን አልተጋፈጡም፣ አማልክቶቻቸውንም አልነኩባቸውም ነበርና ነው። 3/ የደእዋ ግልጽ መውጣት የቅርብ ዘመዶች ጥሪ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በግለሰባዊ ጥሪ ላይ ሦስት ዓመታትን ካሳለፉ፣ አድማጭ ጆሮዎችን ካገኙና ከቁረይሾች ውስጥና ከቁረይሾች ውጭ ደጋግና መልካም ሰዎችን ካፈሩ በኋላና ዳዕዋው ግልጽ እንዲወጣ መንገዶችና ሁኔታዎች ሲመቻቹ አላህ (ሱ.ወ) በመልዕከተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ የሚከተሉትን የቁርአን አንቀጾችን አወረደ። وَأَنذِرْ عَشِيرَتَكَ ٱلْأَقْرَبِينَ ﴿٢١٤﴾ وَٱخْفِضْ جَنَاحَكَ لِمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ﴿٢١٥﴾ فَإِنْ عَصَوْكَ فَقُلْ إِنِّى بَرِىٓءٌۭ مِّمَّا تَعْمَلُونَ ﴿٢١٦﴾ “ቅርቦች ዘመዶችህንም አስጠንቅቅ፡፡ ከምእምናንም ለተከተሉህ ሰዎች ክንፍህን ዝቅ አድርግ፤ (ልዝብ ኹን)፡፡ «እንቢ» ቢሉህም «እኔ ከምትሠሩት ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡” (አል-ሹዐራእ፥ 214—216) ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቅርብ ዘመዶቻቸውን ማለት በኑ ሃሺምንና ከበኑ ሙጠሊብም የተወሰኑ ሰዎችን በመሰብሰብ አላህን አመስግነው የተውሒድን ምስክርነት ከሰጡ በኋላ የሚከተለውን ተናገሩ፦ «ቃኚ ወገኖቹን አይዋሽም። ወላሂ (በአላህ እምላለሁ) ሰውን በሙሉ ብዋሽ እንኳ እናንተን አልዋሽም። ሰውን በሙሉ ባታልል እንኳ እናንተን አላታልልም። ከሱ በስተቀር ሌላ አምላክ በሌላው አላህ እምላለሁ፤ እኔ በርግጥ ወደ እናንተ በተለይና ወደ ሰው ልጅ ባጠቃላይ የተላክሁ የአላህ መልዕክተኛ ነኝ። ወላሂ ልክ እንደምትተኙ በርግጥ ትሞታላችሁ ፣ ከእንቅልፍ እንደምትነቁ ደግሞ በርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፤ በሠራችሁትም ነገር በርግጥ ትታሰባላችሁ (ትገመገማላችሁ) ፤ በሠራችሁት መልካም ነገር መልካሙን በርግጥ ትመነዳላችሁ፤ በመጥፎም ነገር መጥፎውን በርግጥ ትመነዳላችሁ፤ እሷም የዘላለም ገነት ወይም የዘላለም እሳት ነች። ከአጐታቸው አቡለሀብ በስተቀር ሌሎች ሰዎች ለስለስ ያለ ንግግር ተናገሩ። አቡለሀብ ግን እንዲህ አለ፦ «ዐረቦች (ሊያጠቁት) ላይሰበሰቡለት እጁን ያዙት (ይዛችሁት ድርጊቱን አስተውት) ፤ አሳልፋችሁ ለጠላት ብትሰጡትም ውርደት ነው፤ ብትከላከሉለትም ደግሞ ትገደላላችሁ (ስለዚህ ከአሁኑ አስቁሙት)» አለ። አቡጣሊብ ግን፦ «ወላሂ በሕይወት እስካለን ድረስ እንከላከልለታለን» አሉ። ቀጠሉና፦ «(በጌታህ) የታዘዝከውን ቀጥልበት፤ ግፋበት ፤ ከአንተ መከላከልንና መመለስን አልተውም፤ ነገር ግን የዐብዱልሙጠሊብን ሃይማኖት ለመተው ልቤ አትፈቅድልኝም።» አሉ። በአስ-ሰፋ ተራራ ላይ በአስ-ሰፋ ተራራ ላይ በዚያው ጊዜ የሚከተለው የአላህ ቃል ወረደ፦ فَٱصْدَعْ بِمَا تُؤْمَرُ وَأَعْرِضْ عَنِ ٱلْمُشْرِكِينَ ﴿٩٤﴾ "የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለጽ፡፡ አጋሪዎችንም ተዋቸው፡” (ሱረቱ አል-ሒጅር፥ 94) ከዚህ በኋላ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአስ-ሰፋ ተራራ ጫፍ ላይ ወጥተው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ «ያ ሰባሓህ» አሉ። ሠራዊት ለማጥቃት ሲመጣ ወይም አንድ ከባድ አደጋ ሲከሰት ዐረቦች የሚጠቀሙበት የማስጠንቀቂያ ቃል ናት። ከዚያ ቁረይሾችን በየነገዳቸው መጣራት ጀመሩ። ያ በኒ ፊህር፣ (የፊህር ዘሮች ሆይ!) በኒ ዐደይ! በኒ እከሌ ሆይ! በኒ እከሌ ሆይ! በኒ ዐብደልመናፍ ሆይ! በኒ ዐብዱል ሙጠሊብ ሆይ! በማለት ተጣሩ። ጥሪውን ሲሰሙት «ማን ነው እንዲህ የሚጣራው?» በማለት ተጠያየቁ። «ሙሐመድ ነው» ተባባሉ። ሰዎች ሁሉ በመቻኮል ወደሳቸው ሄዱ። መሄድ ያልቻሉት እንኳ ነገሩን እንዲያጣሩላቸው መልዕክተኞችን ላኩ። ሰዎች ሲሰበሰቡ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦ «ከዚህ ተራራ ሥር በሸለቆው ውስጥ እናንተን ለመውረር የመጣ ፈረሰኛ ሠራዊት አለ ብላችሁ ታምኑኛላችሁን?» ሲሉ ጠየቁዋቸው። ‹፣አዎ! እናምንሃለን፣ ከአንተ እውነትን እንጂ ውሸትን ሰምተን አናውቅም። ሲሉ መለሱላቸው። ይቀጥላል.... join 👉 https://t.me/Darularkam ▶️ የነብያት ታሪክ ▶️ ኢስላማዊ ኣስተሳሰብ ▶️ የእውቀት ኣድማሳችንን ለማስፋት JOIN ያድርጉ
نمایش همه...
ዳሩል-አርቀም

<<ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ :በመልካም ስራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለሉ ሕዝቦች ይኑሩ ::..>> ቁርዓን 3:104