cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ከመጽሐፍት መንደር💠

አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨 🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥 ለማንኛውም አስተያየት @manbabemuluyadergal_bot

نمایش بیشتر
Advertising posts
3 634مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+177 روز
+7530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ቀርቶታል                            #ክፍል_17 ራሴን አረጋጋሁ እና ኢክሩ ልታናደኝ ፈልጋ እንጂ እንደዚህ የምታደርግ ልጅ እንዳልሆነች ብዙ ምክንያቶችን እየሰጠሁ ራሴን አሳመንኩት። እንደዉም እኔ እወድሻለሁ ስላት አይኗን ወደ ሰማይ እየሰቀለች "ፈዉዛኔ የኔ ድመት አንተ ትወደኛለህ። እኔ ላንተ ያለኝ ፍቅር ግን ካንተ በጣኣኣኣም ይልቃል።" ያለችዉን አስታወስኩ። ኢክሩ በሁለት ወር ዉስጥ ይሄን ፍቅሯን ከልቧ አስወጥታ ከነገስኩበት የልቧ ዙፋን ላይ ሌላ ሰዉ እንደማታስቀምጥ ለራሴ ነገርኩት። "ምንም ችግር የለዉም። መብትሽ ነዉ!" ብዬ መለስኩላት። አልተናደድኩልሽም እንደማለት ነበር ያሰብኩት። እኔ ፍቅረኛ ይዤ ከሆነ ጠየቀችኝ እንዳልያዝኩ ነገርኳት። . ወደ ማታ ላይ ብሩኬን አግኝቼ የተፈጠረዉን ነገር ነገርኩት። ኢክሩ ፍቅረኛ ይዛ ከሆነም ሁለቱን ለመነጣጠል ስል የፍቅር ግንኙነት ከሷ ጋር ልጀምር እንደምችል ነገርኩት። ማንም እንደኔ ሊያስብላት አይችልም ብዬ አምናለሁ። ቢያንስ ከኔ ጋር ከሆነች ዝሙት ላይ አትወድቅም። ሌላ ወንድ ኢኩ ላይ ስሜቱን ሲያስታግስ መመልከት አልፈልግም። ኢኩ ንግስት ሆና ባል ስታነግስ ነዉ መመልከት የምሻዉ። አንገቴን አቀርቅሬ "ብሩኬ ኢኩ የእዉነት የፍቅር ግንኙነት ጀምራ ከሆነ እኔ ኢኩን እና ልጁን ለማጣላት ከሷ ጋር የፍቅር ግንኙነት እስከመቀጠል ድረስ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ።" አልኩት ብሩኬ እንደመቆጣት እያለ "በቃ ተዋት የራሷን ህይወት ትኑርበት!!" አለኝ ሳግ እየተናነቀኝ "ብሩኬ እኔ እኮ እንድታገባ እንጂ ከማንም ጋር እንድትንዘላዘል አይደለም የተዉኳት!!" አልኩት። "በቃ ተዋት አይመለከትህም!!" አለኝ አሁንም ቆጣ እንዳለ ነዉ። ብሩኬ ይሄን አቋሜን ስላልደገፈልኝ ተበሳጨሁ። ከዚህ በኋላ የምወስዳቸዉን እርምጃዎች እሱን ሳላማክር ለመዉሰድ ወሰንኩ። . ፊርደዉስ ክረምቱን በተደጋጋሚ እየደወለች እንድንገናኝ ትጠይቀኛለች። እኔ ግን ዉርርዷን ልትፈፅምብኝ እንደሆነ ስለማስብ ላገኛት ፈቃደኛ አልሆን አልኳት። እዉነት ለመናገር በኔና በሷ መካከል ሀይማኖት እና ማህበራዊ ስርዓታችን ልቅ መሳሳምን ባያወግዝ ኖሮ እኔ ነበርኩ ከንፈሯ እንደ ኢክሩ እስኪያብጥ የምስማት!! ግን ሰዉ እንደመሆኔ እንደ እንስሳ ማሰብ የለብኝም። ስጋዬ ይፈልጋል አልዋሽም!! ግን ፈጣሪዬን ማስቆጣት አልፈልግም። እሱን ካስቆጣሁ አንዷን ፊርደዉስን አግኝቼ ጌታዬን ላጣ እችላለሁ። እሱን ባስደስት ግን ጌታዬ የፊርደዉስ አይነት ሴቶች ካዝና በእጁ ነዉ። አንድ ቀን ሀሙስ እለት ፊርደዉስ ደዉላ የጓደኛቸዉን ልደት ስለሚያከብሩ እንድገኝ ጠየቀችኝ። ሙስሊም ስለሆንኩ ልደት እንደማላከብር ነገርኳት። "ኧረ ፈዉዛኔ ይሄን ያህልማ አታካብደዉ!!" አለችኝ። በሷ ቤት አክርሬባት ሞታለች። "ፊርደዉስ እኔ ሙዴ እንደዚህ ነዉ!! እንደየሙዳችን ብንሆን ይሻላል ከምንከራከር!" አልኳት "እሺ በጣም ጥሩ!! በርዝደይ ፓርቲዉ ላይ እኔም አልገኝም። ካንተ ጋር መገናኘት እፈልጋለሁ።" አለችኝ። ተስማምተን ቀጠሮ ያዝን። . ፊርደዉስ ስትስቅ ጉንጮቿ በጣም ይሰረጉዳሉ። በጣም ታምራለች። ሳር ቤት አካባቢ ተገናኘን። መኪና ይዛ ነበር የመጣችዉ። ገቢና ገብቼ ከዚህ በፊት ገብቼበት ወደማላዉቀዉ መናፈሻ ይዛኝ ሄደች። ቦታዉ በጣም ቆንጆ ነዉ። መኪናዋን ቦታ አስይዛ ካቆመችዉ በኋላ ከመኪናዉ ወርደን ዉቡ የሳር መናፈሻ ላይ የተቀመጡት ወንበሮች ላይ ተቀመጥን። "ፈዉዛኔ እኔ ማንንም ወንድ እንዳንተ ተለማምጬ አላዉቅም። ይህን ሁሉ የማደርገዉ እንድስምህ ስለተወራረድኩ ብቻ መስሎህ ከሆነ ተሳስተሀል! አንተ የራስህ አቋም አለህ። እንቢ ማለት መቻልን አስተምረኸኛል። እኔ ደግሞ አላማ አለኝ። ይሄን አላማዬን ለማሳካት ካንተ የተሻለ አማካሪ የማገኝ አይመስለኝም።" አለችና በረዥሙ ተነፈሰች ፊርደዉስ የኮምፒዩተር እዉቀቷ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ከነገረችኝ እቅዶቿ ተረዳሁ። ያለማቋረጥ ለአንድ ሰዓት እቅዷን ነገረችኝ። አሁን ፊርደዉስን በጣም አከበርኳት። በምችለዉ ሁሉ ላግዛትም ቃል ገባሁላት። . የኢድ አል አድሀ ማለትም የሀጅ ስነ ስርዓት እንዳለቀ ያለዉ የኢድ በዓል ደረሰ። ሁልጊዜም እንደማደርገዉ በስም ቅደም ተከተል ሰዎች ጋር እየደወልኩ እንኳን አደረሳችሁ እያልኩ በኢ ተርታ ያሉት ጋር ደርሼ ኢክራም ጋር ደወልኩ። የዛሬን አያድርገዉና ሌላ ጊዜ መጀመሪያ እሷ ጋር ደዉዬ ነበር ቀሪዎቹ ጋር በስም ቅደም ተከተላቸዉ የምደዉለዉ። አነሳችዉ "ኢኩዬ እንኳን አደረሰሽ!!" አልኳት። "እ ንኳን አብሮ አደረሰን!" አለችኝ እየተንጠባረረች "በዓል እንዴት ነዉ?" አልኳት "ጥሩ ነዉ አለችኝ" በአጭሩ። በመልሷ በጣም ተበሳጨሁ በስርዓቱ ተሰናበትኳትና ስልኩን ዘጋሁት። እኔ የስነ አእምሮ ተማሪ ነኝ ኢክራምን እንዲህ ያንጠባረራት ጉዳይ እንዳለ ተገለፀልኝ። አዎ ኢክራም ፍቅረኛ ይዛለች። ካንተ ሌላ ላፈር ስትለኝ የነበረችዉ ኢኩ በሁለት ወር ዉስጥ ሌላ ሰዉ ለምዳለች። ሰዉዬዉ ማን እንደሆነ ማወቅ ፈለግኩ። ኢክራምን በቅርብ ርቀት መሰለል ይኖርብኛል። ትኩረቴን ሙሉ ኢክራም ላይ አደረግኩ። አሁን ስላለችበት ሁኔታ በአምስት ቀናት ዉስጥ ሙሉ መረጃ ሰበሰብኩ። አዎን የኢክራም ህይወት ባልገመትኳቸዉ መንገዶች ሁላ ሳይቀር ተለዉጧል። ማመን የማልችላቸዉን መረጃዎች አገኘሁ።...    ብዙ ሰዎች ኢክሩ በፍፁም ጥፋተኛ እንዳልሆነች ነዉ የሚያስቡት። "ሳይቸግርህ ጭረሀት" "አንተ ነህ የተዉካት!!" ምናምን ይሉኛል። መተዉ ምን ማለት ነዉ? እኔ እኮ ኢክሩን በጊዜዉ ለማግባት ስለማልችል እንድታገባ ብዬ ነበር የተለየኋት። አደራ ያልኩት እኮ ፈጣሪዬን ነበር። እኔ እሷን የመናፈቅ እሳቴን አፍኜ ይብቃን ስላት ለሷ የወደፊት ህይወት ማማር እየተሰዋሁ እንደነበር ለምን አይገባቸዉም? ተዋት ይላሉ እንዴ? አቅሜን አዉቄ ለፈጣሪ አሳልፌ በሰጠሁ ገፋት ይላሉ እንዴ? አስመሳይ ሁላ!! ለነገሩ የነሱ ወሬ ለኔ ምንም ነዉ። ያመንኩበትን ነገር እንጂ አላደርግም! ስሜት ያወረዉ ትዉልድ የሚታይ ድርጊት እንጂ የታፈነ ስሜት አይገባዉም። ኢክራም እንደተሰዋሁላት እንዲገባት ከፎቅ ላይ ራሴን መፈጥፈጥ አይጠበቅብኝም። ማንም ሳያዉቅ በልቤ እንደታፈንኩ እኖራለሁ። በኔ ዝምታ ዉስጥ ብዙ ትርጉም ነበር። እሷን በመተዌ ያሳለፍኩትን ስቃይ እኔ ነኝ የማዉቀዉ። እስከዛሬ ጠረኗ የማይረሳኝ ሰዉ እኮ ነኝ!! ከሷ በኋላ ማንንም ያላየሁ!! አዎ የሱመያን የድምፅ መስረቅረቅ አድንቄያለሁ ፣ የፊርደዉስን ዉበት አሞግሻለሁ ግን አንዳቸዉንም ከምላሴ አሳልፌ ልቤ ዉስጥ አላስገባሁም። በሁሉም ሴቶች ዉስጥ የምትታየኝ ኢኩዬ ነበረች። ሁሌም ቃሌን አስታዉሳለሁ። ስንለያይ ለራሴ የገባሁትን ቃል!! የማግባት የስነ ልቦና እና የገንዘብ አቅም ሲኖረኝ መጀመሪያ ኢኩዬን ፈልጌ ካላገባች ላገባት ለራሴ የገባሁትን ቃል!! ተዋት ይላሉ እንዴ? ለሷ አልጋዉን አደላድዬ እኔ መሬት ላይ በተኛሁ ገፋት ይላሉ እንዴ? ወረኛ ሁላ!! ሲጀመር እነሱ የመዉደድን ልክ የወደዱትን የራስ ከማድረግ አሻግረዉ መመልከት አልቻሉም። እኔ ዉዴታዬ በዝቶ ለኢክሩ ባል ተመኘሁላት!! ኢክሩ ንግስት እንድትሆን ከነክብሯ እንድትለየኝ አደረግኩ። ጌታዬን አስደስቻለሁ እሷ የፈለገችዉን ትበል ግድ የለም። እንደኔ ያሰበላት፣ ወደፊትም የሚያስብላት ሰዉ ግን የሚኖር አይመስለኝም። Like በማድረግ ቀጣዩን ክፍል ይጠብቁን ነጠብጣብ ፍፃሜው ቀርቧል እስከዛ Like share
نمایش همه...
👍 2 1
♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞                           #ክፍል_16 ኢክሩ እኔ ጋር አትደዉልም ግን ብሩኬ ጋር ትደዉላለች። እሱም ይደዉልላታል። አንድ ቀን እነ ብሩኬ ቤት ሆነን ብሩኬ ኢኩን ችላ ሳይል እንዲያማክራት አደራ አልኩት። እሱም አደራዉን ተቀበለ። ኢክራም ወደ ትዳር ህይወት እንድትገባ ብዬ እንደተዉኳት ያዉቃል። ስለዚህ ከማንም ጋር እንዳትንዘላዘል መምከር አያቅተዉም ብዬ አስባለሁ። . በቀጣዩ ሳምንት ልጆቹን ለመተዋወቅ ወደ ተቀጣጠርንበት ከስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ በር ፊት ለፊት ወዳለዉ መናፈሻ ሄድኩ።ከአንድ ዛፍ ስር ያለ ወንበር ላይ የተቀመጠች ቀይ ሴት እጇን አዉለበለበችልኝ። እኔ ሁለት ሴቶች እንደሚጠብቁኝ ነበር የተነገረኝ። "ፈዉዛን ዌልካም!!" አለችኝ ከመቀመጫዋ ተነስታ እንድቀመጥ እየጋበዘችኝ። "ሁለት ሰዉ እንደሚጠብቀኝ ነበር የተነገረኝ!!" አልኳት። "አዎ ነዉ ግን ዛሬ ለምናወራዉ ነገር የሜሮን መኖር አስፈላጊ ስላልሆነ ነዉ ብቻዬን የመጣሁት!!" አለችኝ። "ባይዘዌይ ፊርደዉስ እባላለሁ!!" አለች የአክብሮት ፈገግታ እያሳየችኝ። አየኋት በጣም ቆንጆ ናት! በጣም!! ከኢክሩ ሌላ ቆንጆ ነበር እንዴ? የእዉነት በጣም ዉብ ናት። የለበሰችዉ ቀሚስ ሰፋ ያለ ነዉ። አይጨንቅም!! በጣም ልብሱን አሳምራዋለች። "እና እንደዚህ ዉብ ሆነሽ ፊርደዉስ ካላሉ ምን ብለዉ ስም ሊያወጡልሽ ነበር?" አልኳት እየሳቅኩ ፊርደዉስ ሳቋን ለቀቀችዉ!! ጉንጯ ላይ ስርጉድ አለ። ወይኔ በቃ ይህቺ ልጅ ልቤን ልታሰረጉደዉ ነዉ። ፊርደዉስ ከጀነት በጣም ያማረዉ ጀነት ነዉ። ጀነት እንደሆቴል ባለ4 ባለ5 ኮከብ እንደምንለዉ ይለያያል። ሰው እንደስራዉ ምርጡ ላይ ይገባል። ስሟ እና ዉበቷ በጣም የተስማማ ነዉ። ፊርደዉስ ስቃ ስትጨርስ"ፈዉዛን መንገድ ላይ ነበር ያየሁህ! ከዛም ከሰዎች ስላንተ አንዳንድ መረጃዎችን አገኘሁ!!" አለችኝ። ፈገግ አለችና እጇን እየዘረጋችልኝ ያዘዉ አለችኝ። ይሄ ነገር ወዴት ወዴት እየሄደ እንደሆነ ግራ ገባኝ። "ይቅርታ ሴት አልጨብጥም!!" አልኳት "ለምን?" አለችኝ የእዉነት የእስልምና እምነት ተከታይ አልመስልህ አለችኝ። ሙስሊም ሆና ይህን አለማወቋ አሳዘነኝ። "ቁርዓን ላይ ማን ማንን መንካት እንደተፈቀደልሽ ተፅፏል አንብቢዉ!!" አልኳት። "እሺ ለዛሬ ብቻ ጨብጠኝ!!"አለችኝ በአይኖቿ እየተለማመጠችኝ። አለንጋ ጣቶቿን ፊቴ ድረስ አስጠጋቻቸዉ። የአይኗን እንቅስቃሴ በሚገባ አጤንኩት ይዞር ይዞርና ወደ ግራ እየሰረቀ ያያል። የስነ አእምሮ ተማሪ እንደመሆኔ በግራ በኩል የሚያየን ሰዉ እንዳለ ገመትኩ። ዞር ስል አንዲት ሴት የስልኳን ካሜራ አነጣጥራ እየቀረፀችን ነዉ። . ያላየሁ መስዬ "ፊርደዉስ ሪያሊቲ ሾዉ ለመስራት አስበሽ ነዉ እንዴ የጠራሽኝ?" አልኳት ወዲያዉ እንደባነንኩ ስለገባት ጓደኛዋ መቅረፅ እንድታቆም በእጇ ምልክት ሰጠቻት። . "ፈዉዛን በጣም ይቅርታ!! በቃ እዉነቱን እነግርሀለሁ!"አለችኝ የመሸነፍ ስሜት እየታየባት እኔ የሰዉነቷን እንቅስቃሴ እና የምትመርጣቸዉን ቃላት በማዳመጥ የምታወራዉ እዉነት መሆን እና አለመሆኑን ለማጤን ተዘጋጀሁ። "ፈዉዛን እኔ የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ተማሪ ነኝ። እኛ ባች ዉስጥ "አይ ዊል ዱ ኢት" የሚባል ሙድ አለ።አንድ ቀን ጓደኛሞች አንድ ላይ ሆነን የኛ ጓደኛ ልትጨብጥህ ስትል ሴት አልጨብጥም ስትላት አየሁ። እና እኔ "አይ ዊል ዱ ኢት" አልኩ። እኔ አንተን በግድ እንድትጨብጠኝ ላደርግህ ከነሱ ጋር ተወራረድኩ።"አለችኝ። "ዉርርዱን ባትፈፅሚ ምን ይከተልሻል?" አልኳት በጣም አሳዘነችኝ! "ለኔ ዉርደት ነዉማንንም የሚያንበረክክ ዉበት አለኝ!! ጓደኞቼ መቀለጃ ነዉ የሚያደርጉኝ የምፈራቸዉ እነዚህን ነዉ ሲቀጥል ሁሉንም ሸራተን እራት ለመጋበዝ እገደዳለሁ።" አለችኝ። ሁለት ነገሮች አስገረሙኝ በዉበቷ እርግጠኛ መሆኗ እና ሀንዳዉት ኮፒ ማድረጊያ ያጡ በሞሉባት ሀገር ለቀልድ ሸራተን ራት የሚገባበዙ ተማሪዎች መኖራቸዉ። ደግሞ እኮ እራት መጋበዙ ለሷ ቀላል ነዉ። ያስፈራት ሙድ መያዣ መሆኑ ነዉ። "ልትጨብጪኝ ብቻ ነዉ የፈለግሽዉ?" አልኳት ድርድሩ ለመጨባበጥ ብቻ የተደረገ አለመሆኑን ከመቀጮዉ ስለተረዳሁ። እንደማፈር እያለች"አይደለም ከንፈርህን መሳም ነዉ ዉርርዱ አለችኝ።" ከወንበሬ እየተነሳሁ "እንዳታስቢዉ!!" አልኳት። ፊቷ በእልህ እየቀላ "ፈዉዛን ታደርገዋለህ!!"አለችኝ። በተቀመጠችበት ትቻት ሄድኩ።. ሰዓታት ምንም የሰዉ ልጅ ለዉጥ ቢፈጥርም ባይፈጥርም ከመቁጠር አይወገዱም። ተኝተንም እንዋል በስራ ተጠመድን ቀን ይነጉዳል።እንደቀልድ አመት አለቀ ይባላል። ከኢክራም ጋር የፍቅር ግንኙነታችንን ካቋረጥን ከሶስት ወራት በላይ ተቆጠሩ። በወንድምነት የነበረንንም ትስስር ኢክሩ ካቆረፈደችዉ ሁለት ወር ሆነ። የዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት ትምህርቴን አጠናቅቄ ክረምቱን እየቦዘንኩ ነበር አንዳንዴ እዚህ ካፌ እየመጣሁ ከረሂማ ጋር እጫወታለሁ።አንዳንዴ ብሩኬ ጋር እየሄድኩ እደበራለሁ።በዛ ሰሞን ግን ለተለያዩ ተቋሞች የስነ ፅሁፍ ስራዎችን ድህረ ገፃቸዉ ላይ በመስራት ተጠምጄ ስለነበር ኢንተርኔት ላይ ተጥጄ እዉል ነበር። አንድ ቀን እንደተለመደዉ ኢንተርኔት ላይ ተጥጄ ከማላዉቀዉ ሰዉ መልዕክት ደረሰኝ። ልጁ ሰላምታ እንደተለዋወጥን "ፈዉዛኔ እኔ ሰፈር አካባቢ አዉቅሀለሁ። ከኢክሩ ጋርም ግንኙነት እንደነበራችሁ አዉቃለሁ። አሁን የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ናችሁ እንዴ?"የሚል መልዕክት ላከልኝ። ወዲያዉ "እኔና እሷ መገናኘት ካቆምን በጣም ቆይቷል። በመካከላችን ምንም አይነት ግንኙነት የለም።"አልኩት። ልጁ አመስግኖ ተሰናበተኝ።ትንሽ ቆይቼ አሰብኩና በመልሴ ተፀፀትኩ። ፍቅረኛዬ ናት ነበር ማለት የነበረብኝ።ኢክሩን ከዚህ በኋላ አግብታ እንጂ ከማንም ወንድ ጋር ስትንዘላዘል ማየት አልፈልግም። ልጁ ጥያቄ ደግሞ ከተዉካት ልዉሰዳት አይነት ነዉ። ማንም የጣለዉን ሲያነሱበት አይወድም። ሊያዉም እንድታገባ የምመኝላትን ሴት አብራዉ ስትንዘላዘል ማየት ያመኛል። ዉስጤ ሰላም አጣ።የኢክሩን የፌስቡክ ገፅ ለመጎብኘት ገባሁ አንፍሬንድ እንደተደረግኩ ነዉ።ላወራትና ከልጁ ላስጥላት ፈለግኩ። . ከኢክሩ ጋር ከሶስት ወራት በኋላ ድጋሚ ፌስቡክ ላይ አወራን።ስላለችበት ሁኔታ አንዳንድ ነገሮችን ጠየቅኳት።እንደድሮዉ በመካከላችን ሰላም አዉርደን በወንድምነት እንድንቀጥል ጠየቅኳት። መልዕክቱን የላኩላት በእንግሊዘኛ ስለነበር የፍቅር ግንኙነታችንን ድጋሚ መልሰን እንቀጥል ያልኳት መስሏት እንዲህ አለችኝ ፦"እኔ ስትፈልግ የምትጥለኝ ስትፈልግ የምታነሳኝ እቃ አይደለሁም።አሁን ከሌላ ሰዉ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምሬያለሁ።" ደነገጥኩ!እሞትልሀለሁ ስትለኝ የነበረችዉ ኢክሩ ናት በሁለት ወር ዉስጥ ከህይወቷ ማህደር ፍቃኝ ከሌላ ወንድ ጋር ፍቅቅሮሽ የጀመረችዉ?ወይስ ሲጀመርም አፈቀርን ሲሉ ሰምታ እንጂ ፍቅር ምን እንደሆነ እንኳ አታዉቅም? እንዴ እኔ እኮ ኢክሩ ግጥም ስለማትወድ ብዬ ግጥም መፃፍ ያቆምኩኝ ይኸዉ እስከአሁን ግጥም አልፃፍኩም።ቆሻሻ ላይ የተወለደ ፍቅር ንፅህና ሊኖረዉ እንደማይችል ግልፅ ነበር።ትዳር ላይ ያልተመሰረተ ግንኙነት ፍሬ ሊያፈራ አይችልም። ኢክሩ እንዴት እኔን ረስታ ሌላ ወንድ ጋር ለመሄድ ደፈረች?እኔ እኮ እንኳን ልረሳት በጣም ስትስቅ የሚሸበሸበዉ አፍንጫዋ አሁንም አይኔ ላይ አለ።ኢክሩ እኮ እየተኮላተፈች 'ደ' ስትል አሁንም ጆሮዬ ላይ ይደጋገማልነጠብጣብ ዛሬ ማታ 3 ሰአት ላይ ፍፃሜው ያገኛል
نمایش همه...
👍 5 2
🤔አንዳንዴ ዝም ትላለክ አንዳንዴ ደግሞ እንደ ሰዉ  በ ብዙ  ነገር ትገረማል ዞር ሲያደርግም ወደ እብደት ጎዳና ታመራ ጨርሶ  ወፈፍ እንዲያረግ ትመኛለ ምክንያቱም ድክም ሲል መርሳትን አብዝተ ትመኛለ እልሞችክን ግብክን ትረሳ እና ትሄዳለ መሄድ ብቻ ብቻ በማለፍያ ዉስጥ አትለፍ እንጂ ሁሉም ያልፋል በድጋሚ ፈገግ እንላለን ምን አልባት ዉድቀቶቻችን ያጠነክሩን እና አህድ እንላለን መልካም ይሆናል አንድ ቀን በፈጣሪ ደግሞ ደግሞ ተስፋ አይቆረጥም ባይ ነኝ። ብቻ በማለፍ ዉስጥ አንለፍ እንጂ ይሆናል ታሪኮቻችን መቼም አይደለዙም እልሞቻችን መቼም አይቀሩም ምን አልባት ብዙ ነጭ ወረቀቶችን አጋምሰን ይሆናል ግን ቦታ አይጠፋም ለነጋችን ግን መፃፎቻችን ምነዉ በነበር ቆም ሚፃፍእ ታሪክ ጠፋ ወይሥ እንጃ ብቻ ቃል የለኝም ተመሥገን🙏 በሕይወት ብዙ ነገር ጥለክ ታልፋል ሕይወትም ይቀጥላል…………………… ✍እብድዋ ብእረኛ
نمایش همه...
👍 1
ከመጽሐፉ፧ ➡️መሆን የሚገባው ከመሆን አይዘልም:: የነገ ዕጣፈንታህ ካንተ ቁጥጥር ውጭ ነው:: አታውቀውም:: ይህም ስለሆነ በኑሮህ ዓላማና ግብ አያስፈልግህም ማለት አይደለም:: ህልምና ምኞት አያሻህም ማለት አይደለም፨ የተሟላ ኑሮ ላንተ እርም ነው ማለት አይደለም፡፡ ✅ኑሮ - ላንተና ለቤተስብህ የተደላደለ ሆኖ ቢገኝ ትመርጣለህ። ቢሆንም ያማረና የሰመረ ኑሮ በምርጫ እንደማይገኝ ልታውቅ ይገባል፡፡ ብርቱ ጥረት፤ አታካች የህይወት ውጣ ውረድ ሳያጋጥምህ የተመኘኸውን የተደላደለ ኑሮ አታገኘውም። ትልቅ አሳቢ፤ ሩቅ አላሚ መሆን አለብህ። ✅ትልቅ አሳቢ ነው ትልቅ የሚሆነው፧፧ ዓላማና ግብ ያለው ነው የሚሳካለት። እንከን የሌለበት ትልቅ አሳብ አመንጭቶ በድርጊት ያረጋገጠ አዕምሮ እስከአሁን በምድራችን አልታየም። 🔵ነቢዩ ዳዊት “ሰው ራሱን የሚያውቀውን ያህል ነው ብሏል፡፡ ኢመርሶን “አለምን በበላይነት የሚመራ አሳብ መሆኑን የሚያምኑ እነርሱ ታላቆች ናቸው ሲል ተናግሯል፡፡ ⭐ሚልተን “አዕምሮ - ሰማያት የትም ሳይባዝን ገሃነምን መንግሥተ ሰማያትን ይችላል የሚል አሳብ ሰንዝሯል። ✅ሼክስፒር "ጥሩና መጥፎ የሚባል ነገር የለም በማለት በቅኔዎቹ ላይ አስፍሯል። ግን የእነዚህ ታላቅ አሳቦች  ማረጋገጫው ምንድነው? የእነዚህ ታላቅ አሳብ አመንጭዎች አሳብ ትክክለኛ መሆኑንስ እንዴት እናውቃለን? ጥያቄዎቹን ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ ቢሆንም መልሱ ሩቅ አይደለም። ስኬትን ሙሉ በሙሉ በእጅ አድርገው ኑሯቸውን በተድላና በደስታ ሊመሩ በቻሉ በየአካባቢያችን በሚገኙ ጥቂት ሰዎች ማረጋገጥ እንችላለን። ትልቅ ማሰብ ለተአምረ ስኬት መገኛ እንገነዘባለን። 室 መንገድ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱ አሳቦችና ምክሮች ከሰው ልጅ የህይወትና የኑሮ ልምድ ነጥረው የወጡ እውነቶች ናቸው። አሳቦቹና ምክሮቹ የአንድ ሰው መላ ምት አስተያየቶች አይደሉም∶: በህይወትና የተስተዋሉ እርግጠኛ በኑሮ አጋጣሚ ላይ እውነቶች ናቸው፡፡ በየትኛውም የአለም ክፍል፤ በማንኛውም የሰው ዝርያ፤ በማናቸውም እምነትና ቋንቋ ሳይገደብ የሚነበበው መፅሐፍ ✅️@Enmare1988 ✅️✅️@Enmare1988
نمایش همه...
♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞                           #ክፍል_15 በኋላ ላይ ሳጣራ ብሩክ የሻፈደባት ልጅ ስም ኢማን ነበር። በኋላ ላይ ከኔ የወሰደዉ ስልክ ትክክለኛ አለመሆኑን ሲያዉቅ ኢክራምን እንድትሰጠዉ ለመናት። ኢክራም መጀመሪያ ላይ እኔ ባለሁበት ሲጠይቃት አልሰጥህም አለችዉ። በኋላ ላይ ግን ሲያኮርፈኝ ጨነቀኝ ምናምን ብላ ስልኳን ሰጠችዉ። የመጀመሪያ ቀንም ያልሰጠችዉ እኔ ስለነበርኩና አቋሜን ስለምታዉቅ ላለመጠቆር ይመስለኛል። . አንድ ቀን ከሱመያ ጋር ቻት እያደረግን ሁዳ የምትባል ልጅ አዉቅ እንደሆነ ጠየቀችኝ። እኔ ማዉቃት ሁዳ ቤተ መፅሀፍ አብረን የምናነብ የነበረችዉን ቀጮዋን ሁዳ እንደሆነ ነገርኳት። እህቷ እንደሆነች ነገረችኝ። ገረመኝ በፍፁም አይመሳሰሉም። መልካቸዉም ድምፃቸዉም ፈፅሞ አይመሳሰልም ነበር።ሱመያ የሁዳ እህት መሆኗን ካወቅኩ በኋላ በመካከላችን ያለዉ ግንኙነት እየጠነከረ ሄደ። ብሩክ ሴት ማሯሯጥ ላይ በጣም በርትቷል። ከሪሀና ጋር በአንዴ ከነፉ ከሷ ጋር ሲደባበሩ ይኸዉ ኢማንን ለመጀንጀን ይሞክራል። ለነገሩ ኢማን ፊትም አልሰጠችዉም። አልሰማህኝ አለችው። እኔ የስነ አእምሮ እዉቀቴ ከፍ እያለ ሲመጣ ሰዎችን እንደድሮዉ በግርድፉ ማዳመጥ አቆምኩ። በንግግራቸዉ ዉስጥ ስሜታቸዉን እከታተላለሁ፣ በሰዉነት እንቅስቃሴያቸዉ ብቻ የደበቁትን እረዳለሁ። የተለየ የእይታ ምህዳር ፈጠሩልኝ። . ጊዜዉ የፈተና ወቅት የደረሰበት ስለነበር እና ሰፈር ስለነበርኩ ከሰፈራችን ቤተ መፅሀፍ አልጠፋም ነበር። የረዊና እህት እምነትም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ስለደረሰ አብራኝ ቤተ መፅሀፍ መዋል ጀመርን። እምነት በጣም ደስ የምትል ልጅ ናት። ብሩኬ ሊጀነጅናት ፈልጎ አይሆንም ብዬዋለሁ። የረዊና አደራ ስላለብኝ እና ብሩኬም በኔ ምክንያት ስለተዋወቃት አርፎ እንዲቀመጥ ነግሬዉ እሺ አለኝ። ጓደኝነት ለኔ ከአንድ ብቻ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ የሚታይ ነገር ነዉ። ረዊናም እንደ ብሩክ ጓደኛዬ ናትና አደራዋን መጠበቅ ይኖርብኛል። አደራዉ እምነትን ያልሆነ ነገርዉስጥ ከመግባት መታደግ ነዉ። አንድ ቀን አስራአንድ ሰዓት አካባቢ እኔናእምነት ቤተ መፅሀፍ እያነበብን ኢክሩ መጣች። ከኢክሩ ጋር አስተዋዉቄያቸዉ ስለነበር ምንም አላለችም። እንደዉም ከእምነት ጋር ጥሩ ወዳጅ ሆነዋል። እንዴት እንደሆነ ባላዉቅም ብሩኬ ቤተ መፅሀፍ መጥቶ ተቀላቀለን። እያጠናም አልነበረም። ሰዓቱ ሲገፋ ወደ ቤታችን ለመመለስ መንገድ ጀመርን። እምነትን እና ኢክራምን ሸኝተን እኛ ወደየቤታችን ለመመለስ ነበር ያሰብነዉ። መንገድ ላይ እየሄደን ኢክሩ እግሯ ትቦ ለመሸፈን የተደረጉ አርማታዎች መካከል ሾልኮ ገባ ለማዉጣት ስትሞክር በፍፁም እግሯ አልወጣም አላት የኢክራም እግር ትቦዉን ለመሸፈን በተረበረቡ አርማታዎች መካከል ሾልኮ ሲገባ እኔ ተንደርድሬ ያዝኳት።እግሯ ለመዉጣት ስላልቻለ ረጋ ብላ እንድታወጣዉ እና ሰዉም እየበዛ ስለነበር ከሰዉ እይታ ኢክሩን ለመሸፈን ኢክሩን ለቅቄ ከእምነት ጋር ጎን ለጎን ቆመን ለመከለል ሞከርን። እኔ እግሯን ጎትቼ ላወጣላት አልችልም። ምክንያቱም አርማታዉ እግሯን ሊቧጭራት ይችላል።ሁሉም ሰዉ ከመዉደቁ በላይ የሚያመዉ በሰዉ መታየቱ ነዉና እሷ ተረጋግታ እግሯን እስከምታወጣዉ ድረስ ከእይታ ልጋርዳት ፈለግኩ። በዚህ መካከል ብሩኬ ኢክራምን ደግፎ ይዟት ነበር።ሁላችንም የትናንት ጭንቀታችንን አልፎ ስናየዉ ደስ ይለናል።ኢኩዬም እግሯ ከትቦዉ ዉስጥ ከወጣ በኋላ እንዴት እንደነበረች እያሰበች እንድትስቅ ብዬ ፎቶ አነሳኋት።ትልቁ ስህተት የተፈጠረዉ እዚህ ጋር ነዉ። ፎቶ ያነሳኋት በእኔ ሳይሆን በእምነት ስልክ ነበር። አንድ አሮጊት "ተሰበረች?" አሉ ወደ ኢክራም እየመጡ። "የሚሰብር ነገር ይስበሮት!" አለ ብሩኬ በንዴት። አንዳንዴ ሰዎች የሚጠይቁትን ጥያቄ በአግባቡ አያዉቁም።የታመመ ሰዉ "ተሻለዉ ወይ" ተብሎ እንጂ "ሞተ ይሆን?" ተብሎ አይጠየቅም። ሴትየዋም ኢክሩን "እግሯ ከጉድጓዱ ወጣላት?" ብለዉ እንደመጠየቅ "ተሰበረች?" ብለዉ መጠየቃቸዉ አግባብ አልነበረም።ግን የዛን ቀን እኔ ስሜታዊ ያልሆንኩትን ያህል ብሩኬ እንደዛ መቆጣቱ ገርሞኛል። ለነገሩ እኔ ምክንያታዊ ክርክር እንጂ ቧልታዊ ምልልስ ሲጀመርም አልወድም። በስንት መከራ የኢክሩ እግር ከትቦዉ ዉስጥ ወጣ። አካባቢዉ ላይ ከነበረ ቤት ዉሀ ጠይቀን ኢክሩ ተጣጠበች። ዘንቦ ስለነበር ትንሽ ጭቃ ነክቷት ነበር። የዛን ቀን ብሩኬ ላደረገዉ ነገር ምስጋና ይገባዋል። በጣም ነበር ሲሯሯጥ የነበረዉ። . ከዛ ሁሉ ጭንቅ በኋላ የኢኩዬ እግር በሰላም ወጥቶ መንገድ እንደጀመርን እኔ ስትወጣ አይታዉ ዘና ትልበትና እናጠፋዋለን ብዬ አስቤ በእምነት ስልክ ያነሳኋትን ጉድጓዱ ዉስጥ እግሯ እያለ የሚያሳይ ፎቶ አሳየኋት። አይታዉ ፈገግ አለች!ልናጠፋዉ ስንል ግን እምነት በፍፁም አይሆንም አለች። ስልኳ የሚስጥር ቁጥር ስለሚጠይቅ ያለ እምነት ይሁንታ ማጥፋት አይቻልም። ነገሩ ከቁጥጥሬ ዉስጥ እንደወጣ ተረዳሁ።ኢክሩ በጣም እንዳዘነችብኝ ገብቶኛል።እኔ ግን ፎቶዉን ያነሳሁት የኢኩ ፊት ላይ ፈገግታ ለመፍጠር ነበር። እምነት ሁሉንም ነገር አበላሸችዉ። በነጋታዉ ከእምነት ጋር ቤተ መፅሀፍ ስንገናኝ ሰበብ ፈልጌ የስልኳን የሚስጥር ቁልፍ እንድትከፍትልኝ ጠየቅኳት። ከፈተችልኝ። ወዲያዉ በፍጥነት ትናንት ያነሳሁትን ፎቶ ከእምነት ስልክ ላይ አጠፋሁት። እምነት ስልኳን ስመልስላት ወዲያዉ ፎቶ ዉስጥ ገብታ ምስሉን ማጥፋቴን አይታ ሳቀች። "ፈዊ እንደምታጠፋዉ አዉቅ ነበር!!" አለችኝ እየሳቀች! "አሁን እንዴት ቀለል እንዳለኝ ብታዉቂ ከምር ጨንቆኝ ነበር!!" አልኳት ሳቋን መቆጣጠር እያቃታት "አይቅለልህ እንደምታጠፋዉ ስለገመትኩ ኮፒ አድርጌ ሌላ ቦታ ላይ አስቀምጨዋለሁ።ፒሲ ላይ ሳይቀር አለ።" አለችኝ። ሌላ ሰዉ ቢሆን እጣላዉ ነበር ግን እምነት ስለሆነች ምንም ማድረግ አልቻልኩም።ዉስጧ ምንም ክፋት ኖሮ አይደለም እንዲህ ያደረገችዉ። በቀጣይ ከኢኩ ጋር ቤተ መፅሀፍ መጥታ ስንገናኝ ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ዉጪ ሆኖ እንደሆነ ለማስረዳት ሞክሬ ስለፎቶዉ ይቅርታ ጠየቅኳት።ኢክራም ግን ከላዩ ይቅርታ ብታደርግልኝም በዉስጧ እንዳዘነችብኝ ያሳብቃል። ያደረግኩት ነገር በራሱ ትክክል አይደለም። ያደረግኩትን ነገር ትክክል የሚያደርገዉ ያደረግኩበት ምክንያት ነበር። ኢክሩ ፊት ላይ ፈገግታ መፍጠር።ግን ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ዉጪ ሆኖ ኢክሩ ፊት ላይ ፈገግታ ይፈጥራል ብዬ የሰራሁት ስራ በእምነት ምክንያት ኢክሩ ፊት ላይ ሀዘን ፈጠረ። አላማዬ ለመልካም የነበረ ቢሆንም ዉጤቱ መጥፎ ሆኖ ስላረፈዉ ይቅርታ ከመጠየቅ ዉጪ አማራጭ የለኝም። ይቅርታ የማያሽረዉ በሽታ የለም!! እምነቴ ነዉ! . ኢክራም ከነዚህ ቀናት በኋላ ከእኔ ጋር ያላት ግንኙነት እየቀዘቀዘ መጣ። የሚያገናኙንም ምክንያቶች ጠፉ። እኔም እሷ እየቀዘቀዘች ስትሄድ በጣሙን እየቀዘቀዝኩ መጣሁ። በዚህ መሀል አንድ የግቢ ጓደኛዬ ሁለት ቆንጅዬ የግቢ ተማሪዎች ሊተዋወቁኝ እንደሚፈልጉ ነገረኝ። በቁንጅናቸዉ ከግቢያቸዉ ተነጥለዉ የሚታወቁ ናቸዉ።እነሱ የአምስት ኪሎ ግቢ ተማሪዎች ሲሆኑ እኔ ደግሞ የስድስት ኪሎ ግቢ ተማሪ ነኝ። የቆንጆዎች መናኸሪያ የሆነዉ የአምስት ኪሎ ግቢ ዉስጥ በቁንጅና መታወቃቸዉ ምን ያህል ቆንጆ ቢሆኑ እንደሆነ ግልፅ ነዉ። ለጊዜዉ ስለማይመቸኝ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደማገኛቸዉ ነገርኩት። ነጠብጣብ ሊያልቅ 2 ክፍል ብቻ ይቀረዋል እስከዛ Like share
نمایش همه...
2👍 5
♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️    #ክፍል_15 "ኢክሩ መናገር የምትፈልጊዉ ነገር አለ?" አልኳት። ልቤ በጣም ይመታል። ትንሽ አየችኝና በአሉታ አንገቷን ነቀነቀችልኝ። በቆመችበት ትቻት ሄድኩ!! ንግግሬ በራሴ ጆሮ ላይ እየደጋገመ ያስተጋባል።"ለዝሙት ካልሆነ በቀር ወደ እኔ አትምጪ" የኢክራምን እኔን ለመመለስ የሚያስችሉ ሙከራዎች ሁሉ ለመክሸፍ የተጠቀምኳት ቃል ነበረች። እኔ ከኢክራም ጋር ስለያይ ምንም እንኳ ከዚህ በፊት አብረን የነበርን እንደመሆናችን መልካም የሆነ ወንድማዊ ግንኙነት እንዲኖረን እናድርግ ማለቴ እንጂ በደረስኩበት አትድረሺ ማለቴ አልነበረም። ኢክሩ ዉሳኔዬን ማክበሯን ፌስቡክ ላይ አንፍሬንድ ከማድረግ ጀመረችዉ። መንገድ ላይ ስታገኘኝ ባላየ ማለፍ ወይም ለሰላምታ ከብሩክ ጋር ስሆን ብሩክን ብቻ ጠርታ ሰላም ማለት ጀመረች። ነገሩ ምንም አልጥምህ ስላለኝ አግኝቼ ላናግራት ወሰንኩ።ኢክሩ በጣም ልቧ ተሰብሯል ፤አዝናብኛለች። ልትረዳዉ ያልቻለችዉ ትልቅ ሀቅ አለ።እኔ ዛሬ ማንንም አይቼ አይደለም ይብቃን ያልኳት።ግን እዉነቱን መቀበል ነበረብን። እዉነቱ ደግሞ ድርጊታችን ጌታችንን የሚያስቆጣ ከመሆኑም ጋር የኢክሩን እምቡጥ እድሜ የሚያባክን ነበር።ግን ከማንም በላይ የምወዳት ሴት እሷ ነበረች። ኢክራምን አግኝቼ በመካከላችን ያለዉ ግንኙነት የጠላት እየመሰለ እንደሆነ እና እንድናስ ተካክለዉ ነገርኳት። ኢክሩ በሂደት በመካከላችን ያለዉ ግንኙነት ሰላማዊ እንዲሆን የበኩሏን አደረገች። ሀሙስ ቀን ላይ ኢክሩ ስልክ ደወለችልኝ። "ወዬ ኢክሩ" አልኳት መደወሏ ገርሞኝ "ፈዊ ላገኝህ እፈልጋለሁ የማማክርህ ጉዳይ አለኝ።"አለችኝ። በሰዓቱ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ነበርኩ። ከፈለግኩ መምጣት እንደምትችል ነገረችኝ። በጣም ግራ ስለተጋባሁ ወደ ሰፈር ስመለስ ለመገናኘት ተቀጣጠርን። ከራሴ ጋር ከባድ ትግል ዉስጥ ነኝ። ኢክሩ ለምን ፈለገችኝ?ግራ ያጋባል።... 🖊ወደ ሰፈር ከመመለሴ በፊት አንድ የማላዉቀዉ ስልክ ተደወለልኝ። "አቤት!!"አልኩ ስልኩን አንስቼ!!አንዲት ሴት እንደ ሙዚቃ በሚሰረቀረቅ ዉብ ድምፅ"ፈዉዛን ነህ አይደል?"አለችኝ። ድምፁ አዲስ ስለሆነብኝ ግራ እየተጋባሁ "አዎ ነኝ ምን ልታዘዝ?"አልኩ። ልጅቷ ኢክራም የምትመራዉ ሀይማኖታዊ ማህበር ዉስጥ የስነ ፅሁፍ ዘርፍ ላይ እንደምትሰራ እና መፅሔት ለማዘጋጀት እየሞከሩ ስለሆነ እንዳግዛቸዉ ዘፈነችልኝ።(የልጅቷ ድምፅ ከመስረቅረቁ የተነሳ ተናገረች ማለት ስለሚከብደኝ ነዉ ዘፈነችልኝ ያልኩት) እኔም ወደ ሰፈር ስመለስ ላገኛቸዉ ለጁምዓ(አርብ) ተቀጣጠርን። ጁምዓ(አርብ) ዕለት ከደወለችልኝ ልጅ ጋር ሰፈር መስጂድ ዉስጥ በመካከላችን መጋረጃ ተጋርዶ በአካል አወራን። አልተያየንም!! አብረዋት ሁለት ልጆች ነበሩ። ወንድና ሴት ዉይይት ሲያስፈልግ ሁሌም እንዲህ ነዉ የሚደረገዉ መጋረጃ ተጋርዶ እንወያያለን። ይሄ የሚደረገዉ ሀራም(ክልክል) ፆታዊ መፈላለጎችን ለመታደግ ነዉ። ልጅቷ ስሟ ሱመያ ነዉ።ድምጿ በጣም ያምራል። በምችለዉ ሁሉ ላግዛት እና ስለስራዉ በስልክ እየተደዋወልን ለመነጋገር ተስማምተን ተለያየን። ሱመያ ገና ከዛዉ ቀን ጀምሮ ፌስቡክ ላይ ስለብዙ ነገሮች ታማክረኝ ጀመር።ምናለ ታይፕ ተደርገዉ የተላኩ ሚሴጆችን በፀሀፊዉ ድምፅ የሚያነብ ማሽን በኖረ! የሱመያን መልዕክቶች በሷ ድምፅ እሰማበት ነበር።የፈጣሪ ያለህ የሰዉ ድምፅ እንዲህ ይስረቀረቃል?የሷ በጣም ይለያል። . በነጋታዉ ቅዳሜ ኢክሩ ደዉላ የምንገናኝበትን ሰዓት ተነጋገርን።ሰዓቱ ሲደርስ መንገድ ላይ ተገናኝተን ወደዚህ ካፌ መጣን። ኢክሩ ጥቁር ሰማያዊ ጅልባብ ለብሳለች።ረሂማ መጥታ ከታዘዘችን በኋላ ኢክሩ አይኔን ትኩር ብላ እያየችኝ "ፈዉዛኔ ግን ምንም የአቋም ፅናት የለህም።"አለችኝ። እዉነቷን ነዉ አንድ ነገር ላይ ለረዥም ጊዜ በፅናት መቆም ይከብደኛል። አሁንም ከሷ ጋር በፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ለመቆየት ከጌታዬ ጋር የምጋፋበት ፅናት አጥቻለሁ። እየሳቅኩ "ኢክሩ ልክ ነሽ" አልኳት። አሁን ከኢክራም እየተረዳሁ ያለሁት ግን ከዚህ ቀደም በመካከላችን ያለዉን ግንኙነት የጠላት አናስመስለዉ ማለቴን እንደገና ወደፍቅር ህይወት እንመለስ ለማለት እንዳሰብኩ አድርጋ ነዉ የተረጎመችዉ። በፍቅር አብረዉት ከነበሩት ልጅ ጋር ወንድም ሆኖ መቀጠል ይከብዳል። ሱመያ እኔን ወንድም ብሎ መቀበል ከብዷታል። እንዴት አይክበዳት? ስንቱን አብረን አሳልፈናል እኮ!! ትዳር ተወድዶ ጉድ አደረገን። ማህበረሰባችን የትዳርን ዋጋ አስወድዶ የዝሙትን ዋጋ አርክሶንብን ተቸገርን!! ወሬ ለመቀየር ያህል"ሱመያ የምትባል ልጅ ከናንተ ጀመዓ(ህብረት) አናግራኝ ነበር።"አልኳት። እየሳቀች "እኔ ነኝ እንዲያናግሩህ የጠቆምኳቸዉ!!" አለችኝ። እኔም ሳቋ ተጋባብኝ!!ከዛ ደግሞ አሳዘነችኝ። ኢክሩ ነገረ ስራዋ ሁሉ ግራ ያጋባል። . ኢኩ ለሷ ጥላቻ እንዳለኝ መጠርጠር ሳትጀምር አትቀርም።በስልክ ስናወራ እየጮህክብኝ ነዉ ፣ተቆጣኸኝ ምናምን የሚሉ ሰበቦችን እየፈለገች ታኮርፋለች። የሚንቃትን ፈዉዛንን እና ኩርፊያዉን እራሷ በጠርጣሪዉ ጭንቅላቷ ትፈበርካለች። እኔ እንዴት ኢክሩን እጠላታለሁ?የማይመስል ነዉ። የዛን ቀን ጉዳያችንን እንደጨረስን ወደ ቤቷ ሸኝቼያት ተመለስኩ። ከዚህ ቀን በኋላ ከኢክራም ጋር በስልክም በአካልም ያለን ግንኙነት እየቀዘቀዘ መጣ። እኔ ፍቅረኛ የሚባለዉን ታፔላ ብታነሳልኝ ከጎኗ ሆኜ እንደወንድም ላማክራት ፈቃደኛ ነበርኩ። እሷ ግን የፈለገች አይመስለኝም። ከነሱመያ ጋር በቀጣይ ልንገናኝ ስንቀጣጠር ከመስጂድ ዉጪ ስለነበር ከብሩክ ጋር አብረን ሄድን። አንድ ሙሉ የቆንጆ ቡድን ከተቀጣጠርንበት ህንፃ ስር ቆሞ ጠበቀን። አራት ነበሩ።ሱመያ የትኛዋ እንደሆነች አላዉቅም። ወደኔ ቀረብ ሲሉ አንደኛዋ ቀደም እያለች ስትመራቸዉ እሷ መሆኗን ገመትኩ። ከአራቱ ዉስጥ አንደኛዋ በጣም ነበር የምታምረዉ!!በጣም!! ሲጀመር ሁሉም ቆንጆ ነበሩ። ሱመያ እንደሆነች የገመትኳት ልጅ ፈገግ ብላ አንድ ደብተር እየሰጠችኝ "ሁሉንም እዚህ ላይ ፅፈነዋል እየዉና አስተያየትህን ትሰጠናለህ!!" ብላ ሞዘቀች!! ሱመያ ነበረች። ድምጿ ሲስረቀረቅ ነበር የለየኋት። ብሩኬ እኔ ከሱመያ ጋር ሳወራ እሱ አብራት ያለችዉን ቆንጅዬ ልጅ እየተመለከተ ተቁነጠነጠ። ደብተሩን ተቀብያቸዉ ገና ዞር እንዳሉ ብሩኬ ደብተሩን ቀምቶኝ ሮጠ። ነገረ ስራዉ ሁሉ ስለገባኝ "ብሩኬ አይሆንም!!" እያልኩ ተከተልኩት። ደብተሩ ላይ ስልክ ቁጥሮችን ስላየ ነበር ነጥቆኝ የሮጠዉ። ብሩኬ ስልክ ቁጥሩን ስልኩ ላይ ለመመዝገብ አስፓልት ተሻግሮ ሮጠ። ተከተልኩት። ረዥም መንገድ ተሯሯጥን። እኔ በሀይማኖት ጉዳይ ምክንያት ሴቶች የሰጡኝን የግል መረጃ አሳልፌ መስጠት አልፈልግም። በሀይማኖት ጉዳይ ተገናኝቶ ፈጣሪን የሚያምፅ ነገር መፈብረክ ያስጠላል። አንዳንዶች ሀይማኖታዊ ህብረቶችን ሲቀላቀሉ ቁጥብ እና ቆንጆ የሆኑ ልጆችን ለማጥመድ ነዉ።ለነገሩ ሁሉም የሀሳቡን ያገኛል። ቆንጆ የፈለገዉ ቆንጆ ፣ የቆንጆዎች ካዝና ባለቤት የሆነዉን ፈጣሪዉን የፈለገ ደግሞ ፈጣሪዉን!! ለዛ ነዉ ከብሩኬ ጋር እንዲህ የተሯሯጥነዉ። አለማዊ ሽኩቻዉ ሰልችቷቸዉ መስጂድ የመጡትን ልጆች ወደማይፈልጉት ጉዳይ ዉስጥ እንዲገቡ መሳሪያ ላለመሆን!! ግን ብሩኬ ስልክ ቁጥሩ ያለበትን ገፅ ቀድዶ ወሰደዉ። በኋላ ላይ ሳጣራ ብሩክ የሻፈደባት ልጅ ስም ኢማን ነበር። በኋላ ላይ ከኔ የወሰደዉ ስልክ ትክክለኛ አለመሆኑን ሲያዉቅ ኢክራምን እንድትሰጠዉ ለመናት። ነጠብጣብ እኮ ሊያልቅ ነው አንብበው ከወደዱት Like Share
نمایش همه...
👍 5
እሺ እናንተስ እንዴት ነው የተገናኛችሁት #3 "እሺ ጆኒ እናንተስ" አሉ ለቀጣዩ ታሪክ እየጓጉ ሳባ ወደ ጆኒ ዞራ "አንተ ንገራቸው" አለች እየተሽኮረመመች።ጉሮሮውን ጠራርጎ ጀመረ። " አንድ የተባረከ ቅዳሜ አውቶቢስ ተራ ወደ መሳለሚያ በእግሬ እየተራመድኩ እያለ የሆነች ቆንጂዬ ሸፋፋ ከፊቴ እየመጣች እያለ አጠገቤ አብሮኝ በእኩል እርምጃ ሲራመድ የነበረ አንድ የማላውቀው ሰው ፈጠን ብሎ ሄደና የሆነ ነገር ብሏት አለፈ። ወዲያው ፊቷን ጭምድድ ስታደርገው እንዴት ደሜ እንደፈላ ብቻ ከመቅፅበት ሮጬ አንገቱን አንቄ "ምንድነው ያልካት" አልኩት "ምን አገባህ?" አለኝ ተገርሞ እሷም ስለሷ መሆኑን ስታውቅ ወዲያው እየሮጠች መጥታ ያዘቺኝ ጭራሽ ስትመጣ ደግሞ የልብ ልብ ተሰማኝ "አትናገርም?" ብዬ በቦክስ ፊቱን ስነርተው ወደቀ።ወዲያው አጠገቤ ደርሳ ሁለቱንም እጄን ያዘችው "እረፍ በቃ" አለችኝ በልምምጥ አይኔን እያየችው። የሰደባትም ሰውዬም የተመታበትን አፉን ይዞ ልብሱን እያራገፈ "ሂድ አንተም በቃ" አለችው። ፊቱን አዙሮ ሄደ። እኔ ግን ንዴቱ አለቀቀኝም። እሱ መሄዱን አይታ ዞር ስትል "ንገሪኝ ምንድነው ያለሽ" አልኳት "ተወው በቃ አመሰግናለሁ ግን" አለቺኝ። ወደሌላ አቅጣጫ እያየች። "ካልነገርሺኝ አለቅሽም" አልኳት። "እሺ በቃ" ቦርሳዋን የያዘችበትን ግራ እጇን እያሳየቺኝ "ቀለበት አለማድረጌን አየና እስካሁን ካላገባሽ ቆመሽ መቅረትሽ ነው አለኝ" አለች። አየኋት ከዛ እንደዚህ ካላት በኋላ ፊቷ እንዴት እንደነበረ ሳስታውስ ልቤ ስብር አለ። "ቆንጂዬ እኮ ነሽ እንዴት ነው ቆመሽ የምትቀሪው" አልኳት። "እኔንጃ" አለቺኝ ተስፋ መቁረጥ እየተነበበባት "እኔም ቆሜ መቅረት አልፍልግም" አልኳት ፈገግ አለች "ስለዚህ...?" አንጠልጥዬ ተውኩት "ስለዚህ?" አለች በደንብ ፈግጋ "ስለዚህ ቆመን ከምንቀር የሆነ ቦታ ሻይ እንጠጣ" አልኳት በደንብ ሳቀች "እንደዚህ በቀላሉ?" አለች "ቆመን ከምንቀር አይሻልም"አልኳት። ይኸው ነው አብረን ቀረን ማለት" ብሎ አበቃ።"ጀግና እኮ ነህ ጆኒ እስኪ ለጆኒ" አለ ናቲ ብርጭቆውን ከፍ አድርጎ። ቺርስ ✍nani
نمایش همه...
5👍 2
✔️ፍቀጂልኝ ፍቀጂልኝ ፀጉርሽ ተንጨብርሮ ባየው ጊዜ እንዳጥብሽ ፍቀጂልኝ ረጥቦም አይቆይ በፎጣ ላደራርቅልሽ ፍቀጂልኝ ፣ የደረቀው ፀጉርሽን ትንሽ ቦታ ከፍዬ እንድሰራሽ ፍቀጂልኝ ፣ በረደሽ አይደል? እንኪ ያፈላሁልሽን ቡና ጠጪልኝ ይጣፍጣል ብለሽ ሲጣፍጥሽ እንዳይ ፍቀጂልኝ ፣ ጠጥተሽ ፀጉርሽን ስትሰሪ የፀሃዬ ዮሐንስን "ሳቂልኝ" እንዳዜምልሽ ፍቀጂልኝ ሁለት ዘለላ ከሰራሁሽ በውሃላም የጥላሁን ገሰሰን "የቀይ ዳማን" እንድዘፍንልሽ ፍቀጂልኝ አዎ ፍቀጂልኝ ✔️ጠዋት ስትነሺ ሸሚዜን አርገሽ ሽንኩርት ስትከትፊ እንዳገኝሽ ፍቀጂልኝ ፣ ወገብሽ ላይ ተጠምጥሜ ደህና አደርሽልኝ እንድልሽ ፍቀጂልኝ ፣ ማታ የሰራሁሽን ፀጉርሽን ወደአንድ ጎን አድርጌ አንገትሽን እንድስም ፍቀጂልኝ ፣ ያልጨረሽውን ምግብ እንድጨርሰው ፍቀጂልኝ ፣ ✔️በትልቁ ስፒከራችን የዳዊት ፅጌን "ደሞ በዚ ላይ" ሚለውን እየሰማን ቁርሳችንን እንድንበላ ፍቀጂልኝ፣ ልክ "ደሞ በዚ ላይ ፀባይ" ሲል እንዳጎርስሽ ፍቀጂልኝ የበላሽበትን አፍሽን በጣቶቼ ጠርጌልሽ እንድስምሽ ፍቀጂልኝ ፣ ማቋረጥ ስለማልፈልግ የበለጠ ወገብሽን እንድይዝ አንገትሽን እንዳቀና ፍቀጂልኝ ፣ ግን ምን ልፍቀድልሽ? 👍ምለብሰውን ልብስ እንድትመርጪልኝ ልፍቀድልሽ ፣ እጆቼን ስትይዢ እንድዘረጋልሽ ልፍቀድልሽ ፣ ስራ ቦታዬ መጥተሽ እንድትስሚኝ ልፍቀድልሽ ስብሰባውን በውሃላ እንቀጥለዋለን ብዬ ወጥቼ ምሳ እንድንበላ ልፍቀድልሽ ምሽቱን ማመሽ ከሆነ እየነዳሽ መጥተሽ እዛው እንድናድር ልፍቀድልሽ ፣ ጓደኞቼ ሲደውሉልኝ እየተጫወትኩ ስትደውይ እና እንደናፈቅሽኝ ስትነግሪኝ ጥያቸው እንደምመጣ ልፍቀድልሽ እዚህ የፈረንሳዩ ፓሪስ ኤፍል ታወር ስር ቀለበት ሳደርግልሽ እንደፈቀድሽልኝ ሁሉ ጣቶችሽን ዘርግተሽ ፎቶ እንድትነሺ ልፍቀድልሽ። 🔸ቀሪ ዘመኔን ከአንድ ሰው ጋር ለመኖር ወሰንኩ ሁሉን ተውኩ ሁሉን ሸሸሁ አንቺን መረጥኩ እንዳትለቂኝ አለቅሽም አለም መፅሃፉን ከፈቀደላቸው ጥቂት ጥንዶች መሃል እነሆ የኛም ስም ይጨመር ዘንድ አፈቀርኩሽ! ልብወለድ አይደለም
نمایش همه...
👏 12👍 4
.              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️                #ክፍል_14 . ዩኒቨርሲቲን ተላምደነዉ እኔም ስነ አእምሮ(Psycology) ደርሶኝ በፍቅር እየተማርኩት ትንሽ እንደቆየሁ ብሩኬ ወደ ሸገር ተመለሰ። ሀገሩ አልተስማማኝም አልቀጥልም አለ። እኔ የእዉነት ደስ አለኝ። በጣም ናፍቆኝ ነበር። እዚሁ ቆይቶ ቀጣይ ዓመት የግል ኮሌጅ ለመማር ነዉ ያሰበዉ። ከሪም ጋርም በአካል ለመገናኘት በቁ!! ግን በመካከላቸዉ ትንሽ ክፍተት ተፈጥሯል። ከአርባምንጭ ከተመለሰ በኋላ ብሩክ በፍፁም የማዉቀዉ ብሩክ ሊሆንልኝ አልቻለም። ፀባዩ ተቀያይሯ ል። ለሱ እርድና ማለት ክለብ መዉጣት እና ሴት ማዉጣት ሆኗል። በተግባር አያደርገዉም በምላሱ ግን ሁሌም የሚያወራዉ እሱኑ ነዉ። እኔ የኢክራምን እና የእኔን ግንኙነት በተመለከተ ትልቅ ዉሳኔ ለመወሰን እያዉጠነጠንኩ ነዉ።... 🖊ካምፓስ ገብቼ ሁለተኛዉ የትምህርት ዘመን አጋማሽ ተጀምሯል። ብሩኬ ጊዜዉን ፊልም በማየት ያሳልፋል። እኔ የላላዉን ሀይማኖቴ ላይ የነበረኝን አቋም ለማስተካከል እየሞከርኩ ነዉ። ከኢክሩ ጋር ከሁለቱ ቀናት በኋላ ድጋሚ ተሳስመን አናዉቅም። አንነካካም!! እናወራለን!! ስለ ጋብቻ እናልምና እንለያያለን!! አለቀ። ቀኑ ሀሙስ ነበር። ከ6ኪሎ ካምፓስ ታክሲ ይዤ ወደ ፒያሳ ሄድኩ። ወደ መስጂደ ኑር!! ይሄ መስጂድ በተለምዶ በኒ መስጂድ ይባላል። መስጂዱ ዉስጥ ገብቼ ከመድረኩ የሚሰጠዉን ትምህርት መከታተል ጀመርኩ። የመስጂዱ ግርማ ሞገስ የሆኑት ሸህ ኡመር ኢድሪስ የቁርዓንን ትርጉም ይተነትናሉ። ከቁርዓኑ እየተተነተነ የነበረዉ አንቀፅ የዩሱፍ(ዮሴፍ) ምዕራፍ ነበር። ይህ ምዕራፍ የዩሱፍን ታሪክ በሰፊዉ ይተርካል። ዩሱፍ በወንድሞቹ የዉሀ ጉድጓድ ዉስጥ ከተጣለ በኋላ ነጋዴዎች አግኝተዉት ለአንድ የምስር(ግብፅ) ባለስልጣን ይሸጡታል። ይህ የገዛዉም ሰዉ ዩሱፍን ለሚስቱ በስጦታ መልክ ያበረክትላታል። ዩሱፍ በጣም ቆንጆ ከመሆኑ የተነሳ የባለስልጣኑ ሚስት ለነፍሷ ትመኘዋለች። ከዚህ ዉብ ፍጥረት ጋር አለሟን መቅጨት ያምራታል። ዩሱፍንም በሮቿን ሁሉ ዘጋግታ ለሱ እንደተዘጋጀችለት እና አብሯት የስጋ ጥሙን እንዲያረካ ትጋብዘዋለች። ዩሱፍ ግን ጥሪዉን ገፍቶ አልቀበልም ይላል። የባለስልጣኑ ሚስት እልህ ግን ዩሱፍን ከእርሷ ጋር ከመተኛት አሊያም ከመታሰር የሚያስመርጥበት ደረጃ ላይ ይደርሳል። . ሸይኹም(መምህሩም) ትኩረት ሰጥተዉ እየተነተኑት ያለዉ ቦታ ይሄ ነዉ። ዩሱፍ ከመታሰር እና ጌታዉን ከማመፅ ምርጫ ሲቀርብለት የተናገረዉን ንግግር ሸይኹ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ "ዩሱፍ ሴቲቱ የዚህ አይነት አጣብቂኝ ዉስጥ ስትከታቸዉ እንዲህ ብለዉ ጌታቸዉን ለመኑ 'ጌታዬ ሆይ በርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለኔ የተወደደ ነዉ። ተንኮላቸዉንም ከኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ እዘነበላለሁ ፣ ከስህተተኞችም እሆናለሁ።' አለ። አላህም ፀሎቱን ተቀበለዉና ታሰረ።" ከዚህ በላይ ማዳመጡ ከበደኝ ከኢክራም ጋር ያሳለፍኳቸዉ ሁለቱ ቀናት ትዝ አሉኝ።በጋብቻ ያልተሳሰርኳትን ኢክራምን ከንፈር የሳምኩባቸዉ ፣ የተከለከልኩትን የአካሏን ክፍሎች የነካሁባቸዉ ሁለት ቀናት!! እኔ ጌታዬን ለማመፅ እቅድ አዉጥቼ ተገበርኩ። ዩሱፍ ግን ማንም ሰዉ በሌለበት ሊያዉም ከባለስልጣን ሚስት የደረሰዉን የእንተኛ ጥያቄ ገፋዉ ፤ ጌታዉንም ላለማመፅ ሲል ታሰረ። ዛሬ ሁሉም ነገር ግልፅ ሆኖ ይታየኝ ጀመር። እኔ አሁን ገና የካምፓስ ተማሪ ነኝ። ኢክራምን ለማግባት የቁስም ሆነ የስነ ልቦና ዝግጅቱ የለኝም። የኢክራምን ዉድ የወጣትነት እድሜ እያባከንኩባት ነዉ፤ ጌታዬንም እያስቆጣሁት ነዉ። መጃጃሉ ይበቃል! ከኢክሩ ጋር እዉነቷን ተነጋግሮ መለያየት ይሻላል!! ግን የዛን ቀን ለራሴ አንድ ቃል ገባሁ። እኔ የስነ ልቦናም ሆነ የቁስ ዝግጅቴ ለጋብቻ ብቁ ሲሆን የፈለጉ አመታት ቢነጉዱ እንኳ ኢክራምን ፈልጌ ካላገባች እሷኑ ላገባ። አዎ በፍቅር የሰከርኩላትን ፣ ከማንም በላይ የማዝንላትን ኢኩዬን ለማግባት!! . ከስድስት ኪሎ ወደ ፒያሳ ተሳፍሬ ሄጄ የሰማሁት ነገር አቋሜን ለዉጦት ወደ ስድስት ኪሎ ተመለስኩ። አሁን ለኢክራም እንዴት ማስረዳት እንደምችል አሰብኩ። መጀመሪያ እኔ ከሷ ጋር ግንኙነቴን ለማቆም ምክንያት የሆኑኙን ሁለት ነገሮችን አሰብኩ። ጌታዬን እያስቆጣሁ መሆኑና ኢክሩ ከእኔ ጋር በመሆኗ ምክንያት አለማግባቷ ናቸዉ። ከኔ ጋር ፍቅር የሚሉትን እቃቃ ባትጀምር ኖሮ የማግባት እድሏ ሰፊ ነበር። የሷ ማግባት ደግሞ ለቤተሰቦቿም ጥቅም አለዉ። ኢክራምን በምክንያት ለማስረዳት ከሞከርኩ እኔዉ ራሴ ከዚህ በፊት ባስጠናኋት የቃላት ድርደራዎች ልትረታኝ ትችላለች። ስለዚህ አዲስ ስልት መጠቀም ነበረብኝ። ኢክራምን እንድትጠላኝ ቢያደርጋትም እንኳ ግንኙነታችንን ለማቋረጥ እንደሚረዳ አሰብኩ። አዎን ዉጤታማ መንገድ አቀድኩ!! ለበጎዉም ለመጥፎዉም የማቀድ በሽታ አለብኝ። . ኢክሩ ፌስቡክ ላይ ስትፅፍልኝም እንደድሮዉ ትኩረት ሰጥቼ አላወራት አልኩ። የሳምንቱ የትምህርት የመጨረሻ ቀን ጁምዓ (አርብ) ሲደርስ ከስድስት ኪሎ ዶርም ወደ ሰፈር ተመለስኩ። በነገራችን ላይ ከዶርም ወደ ቤት የምመለስበት ዋነኛዉ ምክንያት ቤተሰቦቼ ናፍቀዉኝ ሳይሆን ኢክራምን ለማግኘት ነበር። እሷ ሰሞኑን ብዙም በስልክም ስላልተገናኘን ናፍቄያት ነበር። ደዉላ የምንገናኝበትን ሰዓት ጠየቀችኝ ፤ነገርኳት። አሁን ልቤ ለአንድ አመት ያክል አብሬያት የነበረችዉን ልጅ ይብቃን ለማለት ያለዉን ጥንካሬ ሁሉ እየሰበሰበ ነዉ። በቃ ከእዉነታዉ ጋር መጋፈጥ አለብኝ!! . ሰዓቱ ሲደርስ ከኢክሩ ጋር ወደኛ ሰፈር የሚያስገባዉ መንገድ ጋር ተገናኘን። ኢክሩ ዛሬ ጅልባብ ለብሳ ነዉ የመጣችዉ። ጅልባብ ማለት ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱት ፊትንና እጅን ብቻ የሚያሳይ ልብስ ነዉ። የሰዉነታቸዉን ቅርፅ በፍፁም አያሳይም። ሰፊ ነዉ። ኢክሩን በጅልባብ ሳያት ደስ አለኝ። በጅልባብ ደግሞ በጣም ነዉ የምታምረዉ። ይሄ ፈገግታ ፣ ይሄ ዉበት ላይ ነዉ ጨክኜ ፣ ከፈገግታዋናዉበቷ ዘላቂ ደስታዋን እና የጌታዬን ክብር መርጬ በቃን ልላት የወሰንኩት። ልክ አጠገቤ እንደደረሰች እንደተለመደዉ ከአጠገቤ ቆማ "አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ" አለችኝ። የአላህ ሰላምና እዝነት ባንተ ላይ ይሁን ማለት ነዉ። "ወአለይኩሙሰላም ወራህመቱላህ" አልኳት። ባንቺም ላይ የአላህ ሰላም እና እዝነት ይሁን ማለት ነዉ። . ሰላም ተባብለን ከጨረስን በኋላ ወዲያዉ እዛዉ እንደቆምን ወደገደለዉ ለመግባት ፈለግኩ። ፊቴን አጨፈገግኩ እና ትንፋሼን ዉጬ "ኢክሩዬ ለረዥም ጊዜ አብረን ቆይተናል ግን ግንኙነታችን ወዳልሆነ መስመር እየወሰደን ነዉ። ባለፈዉ ያደረግነዉን ታስታዉሻለሽ አይደል?(መሳሳሙን ማለቴ ነበር) በዚህ ከቀጠልን ሌሎች ነገሮች ላይም ልንወድቅ እንችላለን። ስለዚህ ከዚህ በኋላ ለዝሙት ካልሆነ በቀር ወደ እኔ አትምጪ!!" አልኳት። ኢክሩ ፊቷ ተቀያየረ ፣ አይኗ በእንባ ተሞላ ፣ ወዲያዉ በዉሸት ፈገግታዋ እንባዋን ለማጨንገፍ ሞከረች። "ኢክሩ መናገር የምትፈልጊዉ ነገር አለ?" አልኳት። ልቤ በጣም ይመታል። ትንሽ አየችኝና በአሉታ አንገቷን ነቀነቀችልኝ። በቆመችበት ትቻት ሄድኩ!! ንግግሬ በራሴ ጆሮ ላይ እየደጋገመ ያስተጋባል። "ለዝሙት ካልሆነ በቀር ወደ እኔ አትምጪ" የኢክራምን እኔን ለመመለስ የሚያስችሉ ሙከራዎች ሁሉ ለመክሸፍ የተጠቀምኳት ቃል ነበረች። . ነጠብጣብ ትረካ ሊያልቅ ጥቂት ክፍል ብቻ ይቀራል ከወደዱት Like share
نمایش همه...
👍 9
ሁሌ ማታ አጠገቤ የማትጠፋ በሚያምር ድምጿ የምታንጎራጉርልኝ እየሳመች እየነከሰች የምታቀብጠኝ ብመታት ብቆጣት የማትቀየም የማትርቀኝ የኔ ፍቅር ...... : : ቢንቢ!😍
نمایش همه...
😁 19