cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

🦋እራስን ፍለጋ🦋🦋67

ቢራቢሮዎች ነን ኑ አብረን እንብረር ።ለራሳችን የሚያስፈልገንን እየወሰድን ትውልድን እንቃኝ ወጣትነታችንን ሳንቆጭበት በደስታ እናሳልፍ ኑ ለትውልድ አብረን እንስራ ይቀላቀሉን 👇👇👇 @erasnflega77 ይጫኑት ያገኙናል ሌላ ስንከተል ከራሳችን ጋር እንዳንተላለፍ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 036
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+37 عوز
-1230 عوز
آرشیو پست ها
https://t.me/quizearnbot/quiz?startapp=58274695172595421 Do quizzes to earn US dollars, easily earn 1 US dollars in 1 minute, and anyone who logs in to our website will get 10 US dollars.ሰው በዚህ ቀላል ጥያቄዎች ሀብታም እየሆነ ለምሳሌ ውሻ መብረር ይችላል? ትሪያንግል ስንት ጎን አለው ምናምነ ነው ጥያቄው እና ገብታችሁ ስሩ።
نمایش همه...
https://t.me/quizearnbot/quiz?startapp=58274695172595421 Do quizzes to earn US dollars, easily earn 1 US dollars in 1 minute, and anyone who logs in to our website will get 10 US dollars. በጣም ቀላል ጥያቄዎችን በመመለስ 200$ያግኙ
نمایش همه...
እስቲ እመኑኝ እና ተቀላቀሉ ሁሌም ምርጥ ምርጡን ለእናንተ
نمایش همه...
https://t.me/tapswap_mirror_bot?start=r_6082440291 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift በባለፈው bitcoin ያልሰራችሁ ሁለተኛው እድል ተገኝቷል ይሄንን ተጭናችሁ በመግባት ከ100;000ብር በላይ ያግኙ binance በአቋራጭ በሉት
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የምወዳችሁ ይሄ ዩቲዮብ 1000ሊሞላ 1subscribe ይቀረዋል birhantube1358 ብላችሁ ገብታችሁ subscribe like share አድርጉልኝ
نمایش همه...
Repost from N/a
Photo unavailableShow in Telegram
የምወዳችሁ ይሄ ዩቲዮብ 1000ሊሞላ 1subscribe ይቀረዋል birhantube1358 ብላችሁ ገብታችሁ subscribe like share አድርጉልኝ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
Eid mubarek My bestiea!!!!!🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🫣🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋🌻🌻🌻🌻🌻🌻
نمایش همه...
የሙዚቃው ፈርጥ ዘፋኙ የአሁኑ ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል
نمایش همه...
ምንም ብር ሳይኖረኝ ያልተገደበ ኢንተርኔት(unlimited package)(free internet)#internet #u... https://youtube.com/watch?v=2mQ41j5barE&si=f4Oen9EU-tlhXyhq
نمایش همه...
የሞተ ቢናገር . ስንኖር ያልተረዳን ስንሞት አለቀሰ በቁም ያልጎበኘን ለቀብር ደረሰ በአንቋሸሸን መዳፍ ፅድቅን ተቆናጀን በእኔ ያርገው ለቅሶ ከአፈር ተወዳጀን አብረን ካልተቀበርን የሚለው ጎረፈ ከሀውልታችን ግርጌ ስማችን ተፃፈ ሊሾን አለበሱን ቆመው በእየተራ ሞትን ያጣጣለ በእኛ መሞት ፈራ . ፍትሀት እግዚኦታ ላኩ ለነፍሳችን ይማረኒ ብለው ለሰራን ጌታችን እሪታ እና ዋይታው ቆመ በሰዓታት የመጣን መቻል ነው! በማፅናኛ ቃላት ታሪክ ሆነን ቀረን የቀናት ትዝታ በሰው የታሰረ በአምላክ ተፈታ . በኪሩቤል አሰፋ ገጣሚው @erasnflega @erasnflega
نمایش همه...
#በድጋሜ⚠️ ውድ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ አድርጉ። በሀገራችን ያለውን ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ጫናን ለመቋቋምና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ብዙ ሳይደክሙ በርካታ ገንዘብ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት በርካታ የሀገራችን ልጆች ደክመው በላባቸው ያገኙትን ፤ ከቤተሰብም ለስራ በሚል የተቀበሉትን ብር በኦንላይን አጭበርባሪ ዘራፊዎች በየዕለቱ እየተበሉ ይገኛል። ከዚህ ቀደም መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኦንላይን ከሚደረጉ የማጭበርበር ስራዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ የአደራ ማሳሰቢያ መላክችን ይታወሳል። አሁንም ሰዎች በመቶ ሺህ የሚቆጠር ብራቸውን እየተበሉ ይገኛል። እባካችሁን በ " ዋትአፕም " ይሁን በ " ቴሌግራም " አድራሻችሁን አግኝተው የሚያናግሯችሁን የማታውቋቸውን ሰዎች መልዕክት አትመልሱ። " በተለያየ ኦንላይን ስራ ፣ በፎሬክስ ትሬዲንግ እና በሌሎችም በትንሽ እና በማያደክም ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን ፤ ይሄን ይሄን ስራ ስሩ በዚህ አካውንት ገንዘብ አስገቡና እኛም መልሰን ትርፉን እናስገባለን " የሚሉ አጭበርባሪዎች ተንሰራፍተዋልና ተጠንቀቁ። በነገው ዕለት ከዚህ ጋር በተያያዘ ስላጋጠመ ክስተት እናጋራችኃል። ለአሁኑ ግን ምናልባት " ይሄን ስራ ስሩና ትርፋማ ትሆናላችሁ ፤ ገንዘብ ላኩና ትርፉን እንልካለን " በሚል እያባበሉ ገንዘብ እድትልኩ የሚጠይቋችሁን ሰዎች ከማናገር ተቆጠቡ፤ ምንም ገንዘብም አትላኩላቸው። @tikvahethiopia
نمایش همه...
ሀገራችን ኢትዮጵያ የመቻቻል የመከባበር የአብሮነት ሀገር ማሳያ መሆኗን የምናውቀው በዚህ ነው ዛሬ ታላቁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፆም እና የሙስሊም እምነት ተከታዮች ረመዳን ፆም ገብቷል የግቢያችን ተማሪዎች ፆሙ የሰላም ይሁንላችሁ እያለ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን @erasnflega @erasnflega
نمایش همه...
ትራማዶልን ተገቢ ባልሆነ መንገድ መጠቀም ለድንገተኛ ሞት ያጋልጣል #Ethiopia | ትራማዶልን ከሐኪም ፈቃድ ውጪ በአንድ ጊዜ አብዝቶ መውሰድ ከድንገተኛ ሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና ዕክሎች እንደሚያጋልጥ ተጠቆመ፡፡ ትራማዶል የተሰኘው ጊዜያዊ የህመም ማስታገሻ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እየተዘወተረ እና ሱስ እየሆነ የወጣቶችን ጤና እያመሳቀለ መሆኑን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር መስፍን በኃይሉ ገልጸዋል፡፡ በአብዛኛው ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች በትራማዶል ሱስ እንደሚጠመዱ ጠቅሰው÷ ያለ በቂ ምክንያት እና ተዘውትሮ ሲወሰድ ወደ ሱስነት እንደሚሸጋገር አስረድተዋል፡፡ የትራማዶል ሱስ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ ያለ አደገኛ የሥነ-አዕምሮ ችግር ነው ያሉት ባለሙያው÷ ከድንገተኛ ሞት እስከ ቀጣይነት ያላቸው የጤና እክሎች እንደሚያስከትል አስረድተዋል፡፡ በአንድ ጊዜ በብዛት ከተወሰደም ለሞት ይዳርጋል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ በተጨማሪም የአንጎል ንዝረት፣ የኩላሊት መድከም (መባባስ)፣ ለጡንቻ መቅለጥ እና ለከፋ የሥነ-ልቦና ችግር እንደሚዳርግ አንስተዋል፡፡ አንዳንድ ወጣቶች ኪኒኑን በመውሰድ ሱሳቸውን ማብረድ ሲሳናቸው በመርፌ መውሰድ እንደሚጀምሩ አመላክተው÷ ይህ ሁኔታም ለስትሮክ እንደሚያጋልጥ ጠቁመዋል፡፡ 🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋 @erasnflega🦋🦋🦋 @erasnflega🦋🦋🦋🦋
نمایش همه...
የየካቲት 12 ሰማዕታት #Ethiopia | በዛሬው ቀን በግፍ ለተጨፈጨፉ ከ30 ሺህ በላይ ንፁህ ኢትዮጵያዊያን በአምስቱ የፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ዘመን ከተፈጸሙት ግፎች አንዱ የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጸመው በታሪክ ይጠቀሳል። አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የተባሉ ሁለት ወጣቶች በግራዚያኒ ላይ ቦምብ ጥለው ካቆሰሉት በኋላ አዲስ አበባ የቂም በትር አረፈባት፡፡ በተናደዱ የፋሽስት ወታደሮች በሺ የሚቆጠር ወገኖች ደም ሜዳ ፈሰሰ። ለመናገር የሚሰቀጥጥ ግፍ ተፈፀመ። በአዲስ አበባ ከተማ ለሦስት ቀናት በዘለቀው ጭፍጨፋ ብቻ 30 ሺ ኢትዮጵያውያን ሰማዕት ሆኑ። እነሆ ለዚህ ታላቅ መሰዋዕትነት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎና በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሐውልቶች እንዲቆሙ ተደረገ። የዘመናችን የጥበብ ፈርጥ እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) አያቶቻችን የከፈሉልንን ዋጋ እንዲህ ገልፃዋለች። "የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካጥንት ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር ትናገር ሃገሬ እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ..." *** ስለ የካቲት 12 ቀን እልቂት ጳውሎስ ኞኞ የኢትዮጵያና የኢጣሊያ ጦርነት በተሰኘ መፅሐፉ እንዲህ ያስነብበናል ...የኔፕልስ ልዕልት በመወለዷ ግራዚያኒ የደስታ መግለጫ ገንዘብ እሰጣለሁ ብሎ ከዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከድሮው ቤተመንግስት ድሆች እንዲሰበሰቡ አዘዘ:: ከድሆቹም በስተቀር ታላላቅ የኢጣሊያ ሹማምንት የሜትሮፓሊታን ጳጳስ አቡነ ኪርልና ሌሎችም መኳንንት ነበሩ:: ለእያንዳንዱ ድሃም ሁለት ማርትሬዛ ብር እንዲሰጥ ተወስኖ ነበር:: እኩለ ቀን ገደማ ላይ 3000 የሚሆኑ ድሆች ከቤተ መንግስቱ ገቡ:: ጓደኛማቾቹ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በዓሉ ከሚደረግበት ቦታ ቀደም ብለው ደርሰዋል:: ሁለቱም በኪሶቻቸው ቦንብ ይዘዋል:: ማርሻል ግራዚያኒ ለተሰበሰበው የአዲስ አበባ ሕዝብ ንግግር ሲያደርግ የያዙትን ቦንብ ወረወሩት:: ለ3ኛ ግዜ የተጣለው ቦንብ የፋሽስት ኢጣሊያ መኳንንት ካሉበት ቦታ ፈነዳ:: ግራዚያኒ በጀርባው ወደቀ:: በቀጠለው ጥቂት ደቂቃ ውስጥ ሌሎች ቦንቦች ተከታትለው ተጣሉ:: ከጥቂት ግዜ በኋላ (ያለማቋረጥ ለ3ሰዓት ከተካሄደው ተኩስ በኋላ) ባለ ጥቁር ሸሚዞች የኢጣሊያ ሾፌሮች የቅኝ ግዛት ወታደሮች በአዲስ አበባ ከተማ እየዞሩ ሕዝቡን ይፈጁት ጀመር:: የካቲት 12 ቀን የጀመረው እልቂት በ3 ቀን 30,000 ሰዎች በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከተገደሉ በኋላ ሌላው እየታፈሰ ወደ በረሃ እስር ቤቶች ተላከ... የተከፈለልንን አንረሳም! ክብር ለሰማዕታት! *** የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም #Ethiopia | የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን ... አገር ተቃጠለ! እሳተ ጎመራ ወረደ ከሰለ። ጭስ አመድ አዋራ ሰማዩን ሸፈነው ጥቁር ሰማይ ጥቁር! ሸፈነውጨለማ ሞት በእናት ቅድስት አገር በጀግናው ሕዝብ ላይ የጠላት ግፍ ቀንበር። ፋሽስት አስተጋባ ፋስ ተሰነዘረ ባካፋ መጆሻ ሕዝቡ ተወገረ።.... ክብር ለሰማዕታት! የተከፈለልንን አንረሳም! የሰው ጭንቅላት ኳስ።…… አባቶች ተረዱ እናቶች ታረዱ ቤት ንብረት ፈረሰ ከብቶቹ ተነዱ። ዓለም መና ቀረ * ገብረ ክርስቶስ ደስታ (መንገድ ስጡኝ ሰፊ _ የደም ቀን) ክብር ለሰማዕታት! የተከፈለልንን አንረሳም!
نمایش همه...
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ፍቅራችሁን አሳዪኝ ስለምታደርገለን እናመሰግናለን ክብረት ይስጥልኝ
نمایش همه...
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር . ያሳለፍነዉ ሁሉ አሁን ትዝታ እንጂ ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ ታወሪያለሽ አሉ . . (እኔ ግን ልንገርሽ) የሁለታችን ፍቅር ምን እንደሚመስል. . . እንዴት እንደነበር በሶስት ምስክር 1 አሁን በቀደም ለት የሆነ ቦታ ላይ ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ ፒያሳ አደባባይ ድንገት በቀደም ለት በዛ ቦታ ስሄድ ከሰባት ወር በፊት ስቀሽ የነበረዉ ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ መራመድ አቃተኝ የሚገርምሽ ነገር ያለፈ ነዉ ያልሺዉ ትዝታ ነዉ ያልሽዉ ፍቅርሽና ሳቅሽ ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ ይሰማል ልንገርሽ . (ታዲያ ለምንድን ነዉ) የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ (ይልቅ እኔን ስሚኝ) . ወደየትም ሳይሆን ወዴትም ተመለሽ የትም ሳትደርሺ ጊዜን እንዳቆምነዉ እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ ደቂቃ እንዳልሄደ አስረጂ ሊሆንሽ ምስክር ሊሆንሽ ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ አደባባይ መሀል ከቡና ጠረን ጋር እንደወንዝ የሚፈስ ሳቅሽን ትሰሚያለሽ . 2 ትዝ ይልሽ እንደሆን ካንቺ መኖሪያ ቤት (የመጣሁኝ ጊዜ) የመራራቅ ናፍቆት አስክሮን ቸኩለን ሰማያት ለመዝለቅ ከመሬት ላይ ወድቀን ፍቅር ስንሰራ ፍቅር ስንሰራ ፍቅር ስንሰራ ከሴት ወዝሽ ጋራ የጡትሽ ስር ሽቶ ሸሚዜ ላይ ቀርቶ ሸሚዜ ላይ ቀርቶ ምወደዉን ሸሚዝ ለመልበስ እርም አልኩኝ ለብሼዉ እንዳልሄድ ከበደኝ ጨነቀኝ ያንቺን ጠረን ማጠብ. . . ነፍስ የማጥፋት ያህል ሀጥያት መስሎ ታየኝ (የሚገርምሽ ነገር) እስከ ዛሬ ድረስ በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ . 3 ታስታዉሽ እንደሆን የሆነ ቅዳሜ የሆነ ዉብ ሆቴል ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ ይኼ እንኳን ትዝ ይላል እና. . . እኔና አንቺ ብቻ የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ ከዘጠኝ ወር ኋላ. . . እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ የሚገርምሽ ነገር ጻፊዉን ባላዉቅም #ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ ከዘጠኝ ወር ኋላ አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር (ምስክር ሊሆኑን) ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን ከወይንም. . . Two Ocean እኔ የጨለጥኩት አንቺ ያጋመስሽዉ እኛ ያስተረፍነዉ እስከዛሬ ድረስ ያተረፍነዉ ማዕድ. . . ጠርሙስና ጽዋዉ በክብር ተቀምጧል ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ (ታዲያ ምን ማለት ነዉ) . . . ፒያሳ አደባባይ የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ ከቡና ጠረን ጋ ከኔ መኖሪያ ቤት. . . የምወደዉ ሸሚዝ ላይ የሽቶ መአዛሽ ከሴት ላቦትሽ ጋር ደግሞም እዚያ ዉብ ሆቴል ስር ያስተረፍነዉ . . . ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ አንጀት ከሚበላ ከቆንጆ ጥቅስ ጋር ‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’ . ነበርን እስካሁን በመሆን እያየሽ ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ ከምወደዉ ሸሚዝ የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ (ታዲያ ለምንድን ነዉ) ያሳለፍነዉ ሁሉ #አሁን_ትዝታ_እንጂ..... #ዉስጡ_ህይወት_የለም ብለሽ ለመንደሩ ላገሩ ማዉራትሽ እዉነት ለምንድን ነዉ? . . . . . ©ኤፍሬም ስዩም(ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር)
نمایش همه...
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 It is ma youtube channal subscribe በማድረግ አብርነታችሁን አሳዪኝ ስለፍቅራችሁ አመሰግናለሁ። 🦋🦋🦋🦋🦋🦋🦋
نمایش همه...
ተስፋ ማን ነህ? በዘላለም ታሪክ በጊዜ ርዝማኔ አንተ ተስፋ ሆይ ቆይ ማን ነህ? መኖርን ኖረህ ያስጀመርክ ኖሮ መሰንበትንም ያስተማርክ የፍጥረቱ የመፈጠር ዓላማ ቀማሪ የመኖርንም ትርጉም አስተማሪ የሕይወት ጉዞ ጥጉ፣ መድረሻ አንተ መሆን አለብህ ከንቱነትን ድል መንሻ በዓለም የመከሰትን ቅድመ ሁኔታ በጥበብህ አሟልተህ የሕይወት ጌታ አካላዊ መልኬን፣ ቁመናዬን ሕይወቴን ቀድመህ አይተህ በተስፋ ሻርክ የአለመኖር ወቅቴን በቅድመ ዕውቀትህ በመምራት ስሌት በወላጆቼ የዘር ሃረግ የትውልድ ታሪክ ሰንሰለት እኔን በዚህ ትውልድ መሃል በዚህ ጊዜ አይተህ ገና ሳልፈጠር እርምጃዬን ወስነህ ለይተህ የትናንትናዬ ፈጣሪ የዛሬዬ  ተጠሪ የነገ ሕይወት ዋስትና የሽምግልናዬ ጧሪ ከዚያም በኋላ ለሚኖር ሕይወት በዘላለም ጊዜ ዝርጋታ አንተ ነህ ተስፋ የነፍሴ እርካታ የልቤ ዕርጋታ እኮ አንተ ተስፋ ማን ነህ? በሰው ልጅ ታሪክ በዘላለም ርዝማኔ በሕይወት ምዕራፍ በእያንዳንዱ እርከን ሕይወትን የሚያስቀጥል የሌለበት እንከን ትናንት አስፈልጎ ዛሬ ላይ ማይተው እርሱ አካል ቢኖረው አጥርቶ ማየት ነው እኔ በእናቴ ማህፀን ሳለሁ እንደማንኛውም ሰው ለተፈጥሮ ሥርዓት እገዛለሁ ሕይወቴም ይቀጥል የነበረው ቢሆንም በእንግደ ልጅ በኩል የነገሮች ለሕይወት ያላቸው ዋጋ በሁሉ ጊዜ አይታይምና በእኩል ልክ ከተወለድኩ በኋላ የማህጸን ኑሮ ሲያበቃ የእንግደ ልጅም ለመኖሬ ያለው ዋጋ አበቃ አድጌ ስመላለስም በዚህች ዓለም የሁል ጊዜ ተስፋ የሁልጊዜ ዋስትና የለም ሁሉም በጊዜ እና በሁኔታ በሚወሰን ሥርዓት እስከሚችለው ይጥራል ዋስትና ባለው መልክ ነገን ለመሥራት ሁሉም ደካማ ነው ሕይወትን ለማስቀጠል ወቅትም ተለውጦ እንደሚያራግፍ ቅጠል ሁሉም ይለወጥ እና በሌላ ይተካል ለማከማቸት የተለፋበት ተከምሮም ያልቃል የተተካውም አይዘልቅ ለልሹ ሚጠፋ የሙጥኝ ካልነው ይዞን ሚጠፋ/አውጥቶ ሚተፋ አንተ ግን ተስፋ ሆይ፣ እኮ Man ነህ አውቄ ልከተልህ የተስፋውን ሥርዓት ልጠብቅ ዛሬን በሕይወት ልኑር ነገዬንም ላስጠብቅ አሳ ብለው ውሃ ካሉ ዛፍ ብለው መሬት ካሉ ጽንስ ብለው እናት ቢሉ እኔን ካሉ አንተን ይበሉ ተስፋ ማደርግህ ለጉዳይ አይደለም አንተ ሕይወቴ ሆነህ አንተን አለመጠበቅ የለም የመኖር ምክንያት በሕይወትም የመዝለቅ በጊዜ መግፋት ማይደበዝዝ መልኩን የማይለቅ ዕድሜ ሲጨምር፣ ጉብዝና ሲከዳ እርጅና ሲጫጫን ሕይወት እንደጠብታ ውሃ ሲቀዳ የዚያን ጊዜ ብቻ አይደለም ተስፋዬ የምትሆን አሁንም ተስፋ አደርግሃለሁ ሕይወቴ እንድትሆን ተስፋዬ በልቤ በደማቅ ተጽፋ ትኑር ተስፋዬ የእኔ ተስፋ ተስፋ ከልቤ አትጥፋ የሕይወት ምንጭ ሆይ አትንጠፋ @erasnflega
نمایش همه...
ይህችን ፅሁፍ ማንበብ እንዳትዘነጉ መምህርት ሊያ የ5ኛ ክፍል አስተማሪ ነች ሊያ ተማሪዎቿን አንድ በአንድ የምትከታተል ብርቱ መምህር ነች ከተማሪዎቿ አንዱ ኒክ ይባላል ኒክ አያወራም: ከተማሪዎች ጋር አይጫወትም: ልብሱ ዝብርቅርቅ ያለ ነው: ክፍል ውስጥ አይሳተፍም - መምህር ሊያ በኒክ ደስተኛ አይደለችም መምህር ሊያ የተማሪዎችን የቤት ሾል እና ፈተና ባረመች ጊዜ ሁሉ የኒክን ፈተና በትልቁ ኤክስ (X) የምታደርግ እና በብስጭት ስንፍናውን የምትፅፍ ሆነች - አልወደደችውም   በትምህርት ቤቱ ህግ ደግሞ የእያንዳንዱን ተማሪ የቀድሞ አመታት የውጤት ፋይሎችን ማየት ግዴታ ስለሆነ መምህርት ሊያም ይህንኑ ስታደርግ የሁሉንም ፋይል አይታ የኒክ መጨረሻ ላይ ቀረ አነበበችው : ተገረመች : ደነገጠች! የደነገጠችውም ሾለ ተማሪዎቹ ህይወት በሰርተፊኬቱ ጀርባ የሚፃፈውን አንብባ ነበር የኒክ የህይወት ታሪኩም እንዲህ ተብሎ ነበር የተፃፈው **** የአንደኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነው! ፀባዩም ሸጋ ነው: ንፁህ እና ብሩህ ተማሪ ነው" የሁለተኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ ጎበዝ ተማሪ ነው: ነገር ግን በዚህ አመት እናቱ በጠና ስለታመመች በውጤቱ ቀንሷል" የሶስተኛ ክፍል መምህሩ "ኒክ በእናቱ ሞት ተጎድቷል: አባቱም በሀዘን ተጎድቶ ትኩረት የሚሰጠው ሰው የለም" የአራተኛ ክፍል መምህሩ "አባቱን በሞት የተነጠቀው ኒክ በዚህ አመት ብሶበታል: ብቸኛ ነው: ከማንም ጋር አያወራም: ውጤቱም ወርዷል" *** 🎄እለቱ የገና ዋዜማ ነው: ተማሪዎች ለመህራኖቻቸው ስጦታ የሚሰጡበት እለት ነው - ሁሉም ተማሪዎች ለመምህርት ሊያ የሚያምሩ ስጦታዎችን እየሰጡ ነበር ኒክ በስተመጨረሻ መጣ - በእጁ ጌጣቸው የረገፈ አምባር እና ሊያልቅ ቂጡ ላይ የደረሰ ሽቶ ይዟል: የእናቱ የእጅ አምባር እና ሽቶ ነበር - ተማሪዎች ይህንን አይተው ሳቁ : መምህሯ ግን ተማሪዎቹን ፀጥ አሰኝታ አምባሩን አጠለቀችው : ሽቶውን ተቀባች : ኒክን አቀፈችው "ዛሬ እናቴን ትመስያለሽ : እናቴን እናቴን ትሸቻለሽ" አላት : ተማሪዎች ከሄዱ በኃላ ለሰአታት ብቻዋን አለቀሰች ** ከዚያች ቀን ጀምሮ መምህርት ሊያ ኒክን ጤንነቱን መከታተል , አብራው መዋል ጀመረች, ከዚያም ኒክ ከብቸኝነት ስሜት እየተላቀቀ ወደ ጤንነቱ ተመለስ ,ኒክ ጎበዘ: አመቱ መጨረሻ ላይ ጥሩ ውጤት አመጣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ "የመምህራን ምርጫ" ተብሎ ለመጠራት የበቃው ኒክ በትምህርቱ ጎበዝ: በፀባዩ ምስጉን እና በባህሪው ደግሞ ተግባቢ እና ደስተኛ ሆነ ብዙ አመታት አለፉ: በእነዚህ አመታቶች ሁሉ በገና እለት ዋዜማ መምህርት ሊያ የቤቷ በራፍ ላይ "በህይወቴ ሁሌም ምርጧ አስተማሪ ነሽ! ኒክ" የሚል ፅሁፍ ታገኛለች 👨‍🎓👨‍⚕ኒክ ተመረቀ: ዶክተር ሆነ: በስራው የታወቀ ሀኪም ሆነ 👸ከእለታት በአንዱ ቀን "መምህርት ሆይ! ጥሩ እጮኛ አገኘሁኝ! እናት እና አባት እንደሌለኝ ታውቂያለሽ:: ስለዚህ የሰርጌ ቀን ከጎኔ ቁሚልኝ! ኒክ" የሚል ደብዳቤ ደረሳት ** 🤵‍♂👸በሰርጉ ቀን የእናቱን አምባር አድርጋ እና ሽቶውን ተቀብታ ከጎኑ ቆመች : ዳረችው በሰርጉ መሃል እጁን ይዛ ወደ አዳራሹ ሲገቡ "መምህርት ሊያ ህይወቴን በተለየ መልኩ እንድረዳ እና እንድመለከት ስላደረግሽ አመሰግንሻለሁኝ" አላት መምህርት ሊያ እንዲህ አለች:- “ዶ/ር ኒክ! አንተ ነህ ሰዎችን እና ይህችን አለም የማይበትን መነጽር እንድቀይር ያደረግከኝ: አመሰግንሃለሁ 👉 ሰውን አሁን ባለው አቋም አትገምተው በተቻለህ መጠን ከመንቀፍህ በፊት የጀርባ ታሪኩን አጥንተህ ለሱም ላንተም መኖር ምክንያት ሁን ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ ✍ፀሐፊው @erasnflega @erasnflega @erasnflega
نمایش همه...
ወጣትነት ፋሽን ተከታይ ዘናጭ ተሽቀርቃሪ መሆን ማለት አይደለም! ወጣትነት ራስን በሱሶች ማጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት በምክንያታዊነት ሳይሆን በስሜታዊነት እየተነዱ ራስንና ሌላውን አደጋ ውስጥ መዝፈቅ ማለት አይደለም! ወጣትነት ብዙ ጃንቦ የጠጣ ጀግና ማን ነው መባባል ማለት አይደለም! ወጣትነት ብረት ገፍቶ ደረትን ማሳበጥ ማለት አይደለም! ወጣትነት ሺሻ ቤት ተቀምጦ ጭስ ማቡነን ማለት አይደለም! . . ወጣትነት በወሲብ ሱስ ከዚህም ከዚያችም ጋር በዝሙት ተወጥሮ መልከስከስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በጥላቻ እና በዘረኝነት ተሞልቶ መታወር፣ መደባደብ እና መነታረክ ማለት አይደለም! ወጣትነት ተመልሶ የማይመጣውን ተፈጥሮ የሰጠችንን ታላቅ ሃይል በማይረባው ነገር ጊዜን ማቃጠል ማለት አይደለም! ወጣትነት ግዜያዊ ስሜትን ብቻ እያዳመጡ እንደፈረስ ጋሪ መነዳት ብቻ አይደለም! ወጣትነት በሀሜት፣ በአሉባልታ፣ በወሬ ሱስ፣ በአቃቂር፣ በተንኳሽነት፣ በቧልት መሞላት ማለት አይደለም! . . ወጣትነት ይሄንንም ያንንም ይቺንም ያቺንም መጀንጀን መጀናጀን ማጀናጀን ማለት አይደለም! ወጣትነት በባዶ ጭንቅላት ምርጥ አልባሳትን ለብሶ እየተጀነኑ በባዶ ኩራት ተወጥሮ መሬትን ለመርገጥ እየተጸየፉ መራመድ ማለት አይደለም! ወጣትነት በግዴለሽነት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ ከነፈሰው ጋር መንፈስ ማለት አይደለም! ወጣትነት በራስ ወዳድነት መንፈስ መወጠር እና እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ማለት አይደለም! ወጣትነት በማይረባው በቀበሌኛው አመለካከት መታጠር ማለት አይደለም! ወጣትነት ቁንጫ የምታክል እውቀት በመያዝ ይቺ እውቀት ብቻ ትበቃኛለች እያሉ አጉል መመጻደቅ ማለት አይደለም... . . ወጣትነት ባህር ነው። ወጣትነት ውቂያኖስ ነው። ወጣትነት አድማሰ ሰፊነት ነው። ወጣትነት እውቀትን ለማስፋት የምንጋደልበት ሰአት ነው። ወጣትነት በማስተዋል ብርሃን መሞላት ነው። ወጣትነት ችግር ፈጣሪነት ሳይሆን ችግር ፈቺነት ነው። ወጣትነት በዘረኝነት ተሞልቶ አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ...ቅብርጥሶ እየተባባሉ ቡድን በመስራት ስለ ቀበሌኛ አስተሳሰብ መስበክ ሳይሆን ወጣትነት ስለ ኢትዮጵያዊነት ከተቻለም አለም አቀፋዊ እይታን ማስፋት ነው። . . ወጣትነት ፍቅርን እና አንድነትን መስበክ ነው። ወጣትነት በዝሙት ባህር መንቦራጨቅ ሳይሆን ስሜትን የመግዛት ጥበብ ማዳበር መቻል ነው። ወጣትነት ብርሃን ነው። ወጣትነት ተስፋ አለመቁረጥ ነው። ወጣትነት በቀናነት መሞላት ነው! ወጣትነት እስከመጨረሻው ጠብታ ህልምን ለማሳካት መፍጨርጨር ነው። ወጣትነት ማንበብ ነው ። ወጣትነት መጠየቅ ነው ። ወጣትነት ስለዓለም፣ ስለ ህይወት፣ ስለ ጥበብ፣ ስለ እውቀት ብዙ ለማወቅ መጠማት ነው ። ወጣትነት ለሌሎች መኖር ነው። ወጣትነት ለአገሬ ምን ልስራላት ብሎ ራስን መጠየቅ ነው። ወጣትነት ስለነገ ትልቅ ህልም እና እቅድ መሰነቅ ነው። ወጣትነት እሳት ነው። ወጣትነት ቤንዚል ነው። ወጣትነት ቅጠል ነው። ወጣትነት ጤዛ ነው። ወጣትነት ታክሲ ነው። ወጣትነት ምርጫ ነው። ወጣትነት በባህር ላይ ያለች ጀልባ መሆን ነው። ወጣትነት የመቶ ሜትር ሩጫ ያህል ነው። ወጣትነት ውስጥን ፈተናን ለማለፍ ማጀገን ነው። ወጣትነት ከፍርሃት፣ አልችልም እና አይሳካልኝም የሚለውን እስር በጣጥሶ ማለፍ ነው። ወጣትነት ለአንዳች ስኬት በኩራት እና በሞራል መራመድ ነው ...። . @erasnflega
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
#GeneneMekuria አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የሀገራችንን ስፖርታዊ ክንውኖችን በማቅረብ እንዲሁም ከስፖርታዊ ክንዋኔዎች በተጨማሪ በጠቅላላ እውቀቱና መረጃ አያያዙ በርካታ እውቀቶችን ያስጨበጠ ጋዜጠኛ ነበር። በተለያዩ የፅሁፍ ስራዎች ፣ የራዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ላይ ታሪኮችንና ወጎችን በማቅረብም በሚዲያው ላይ ከአርባ አመታት በላይ አገልግሏል። ለአብነት በቀድሞ ዛሚ ኤፍ ኤም፣ በኤፍ ኤም አዲስ ፣ በብስራት ኤፍ ኤም ፣ በአሻም ቴሌቪዥን ላይ የተለያዩ የታሪክና የስፖርት ዝግጅቶችን ባማረና ቀልብን በሚስብ አቀራረብ ሰርቷል። የሀገር ውስጥ ስፖርት ላይ ባለው አስተዋጽኦ ካፍ በ2009 ዓ.ም የ60 ዓመት ጎንደል ኦፍ ሜሪት ሽልማትም ሸልሞታል። ስድስት áŒ‹á‹œáŒ áŠžá‰˝ ብቻ ያገኙትን ሽልማት በመውሰድ ከምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው ነው።  መጋቢት 5/1957 ዓ.ም በይርጋለም የተወለደው ጋዜጠኛ ገነነ ፤ ስፖርትና ታሪክ አጣምሮ የሚወድ ፣ áˆˆáˆšáŠ“áŒˆáˆŤá‰¸á‹áˆ ወይም ለሚያቀርባቸው የጽሁፍ ስራዎች በቂ ማስረጃ እና ሰነድ ይዞ á‹¨áˆšá‰€áˆ­á‰Ľ በመሆኑ  " ተንቀሳቃሹ ቤተ መፅሐፍት " የሚል ስያሜንም አግኝቷል። ባደረበት ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቢቆይም ዛሬ ህይወቱ አልፏል። አንተ የሰው ምርጥ ነፍስህ በሰላም ትረፍ @eraanflega @erasnflega
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
አስፊቲ ቀልድ መስሎኝ ነበር ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ጋዜጠኛው ባደረበት ህመም በአሜሪካ ሀገር ህክምናውን ሲከታተል ቢቆይም ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል መቅረቱ ተነግሯል። ጋዜጠኛው ቀድሞ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኤፍ.ኤም አዲስ 97.1 ሬዲዮ ህይወቱ እስካለፈበት ሰዓት ድረስ ደግሞ የEBS ቴሌቪዥን መዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢ በመሆን ሰርቷል።
نمایش همه...
ከትላንት እይታ ልደቱን እንጂ ባለልደቱን ረሳነው   ምክንያቱም ባለልደቱ ልደቱ እንዲከበር የሚፈልገው በዚህ መንገድ አልነበረም ስንቶች እንሆን የተራቡትን አብልተን የተራቆቱትን አልብሰን የክርስቶስን ውልደት አስበን የዋልን?? ስንቶች እንሆን እና ግን ገና ዛሬ አይደለም ገና ታህሳስ አይደለም ገና ሁሌም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ትላንትናም ዛሬም እስከ ለዘለአለም ያው ነው። ለማንኛውም እንኳን አደረሰን
نمایش همه...
ከትላንት እይታ ልደቱን እንጂ ባለልደቱን ረሳነው ምክንያቱም ባለልደቱ ልደቱ እንዲከበር የሚፈልገው በዚህ መንገድ አልነበረም ስንቶች እንሆን የተራቡትን አብልተን የተራቆቱትን አልብሰን የክርስቶስን ውልደት አስበን የዋልን?? ስንቶች እንሆን ለማንኛውም እንኳን አደረሰን
نمایش همه...
ትንቢተ ኢሳይያስ 9 6፤ ሕፃን #ተወልዶልናልና፥ #ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ #አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም #ድንቅ መካር፥ #ኃያል አምላክ፥ #የዘላለም አባት፥ #የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። 7፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ #አለቅነቱ ይበዛል፥ #ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።   እንኳን ለጌታቾን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል አደረሳችሁ አደረሰን @erasnflega @erasnflega
نمایش همه...
What type am i The DO...ER THE THINKER THE CREATER THE HELPER THE PERSEVADER THE ORGANISOR WHO ARE U? @erasnflega @erasnflega
نمایش همه...
"ማንበብ የማይጠቅመው የማያነብን ብቻ ነው" የጊዜ🗓 እይታን ከሁለት መፅሀፎች ታዩ ዘንድ ወደድንና እነሆ አልን ጊዜ በሰመመን መፅሀፍ እይታ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ........ጊዜ🗓 ወደ ፊት አይገፈተርም፡፡ ጊዜ ለሠው ጭንቀትም ሆነ ደስታ ደንታ የለውም፡፡ የራሱን ስርአት ጠብቆ ነው የሚጓዘው ፧ ያለፈው ጊዜ አይመለስም ፧ የወደፊቱ ደግሞ እንደፈለጉት ፈጥኖ አይመጣም ፡፡ ሰው በጊዜ ቁጥጥ ስር ነው እንጂ ፥ ጊዜ 🗓በሰው ቁጥጥር ስር አይደለም፡፡🕐 ሰዓት ሰው ሠራሽ ነገር ነው ፧ ሞላውን በማዞር ካለበት ስአት🕡 ወይም ደቂቃ ማስቀደም ይቻላል፡፡ ቀንን ገፍቶ ማስመሸት ወይም ምሽትን ገፍቶ ማንጋት ግን የማይቻል ነው፡፡ አቤል ቢቸግረው እንዲ አይነት የጊዜ ምርምር ውስጥ ገባ፡፡🤔 ምንጭ ሰመመን መፅሀፍ ደራሲ ሲሣይ ንጉሴ ከገፅ 186 የተቀነጨበ ጊዜ🗓 በ የተቆለፈበት ቁልፍ ላይ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ገንዘብ 💶የጊዜ🗓 ምንዛሬ ነው። ጊዜ 🗓ያልተመነዘረ ገንዘብ💸 ነው። ህይወት እረቂቅ ምስጢር ናት። አምላክ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህችን ምስጢራዊ ህይወት እድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ🗓 ከረጢት አደለን። ይህችንም ከረጢት በውስጧ እድል በተሰኙ ፈርጦች ተሞልታለች። ከረጢቷ እንዳትሰረቅ ያለ ጊዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጭ እንዳትሆን ፣ሀላፊነቱን ፈጣሪ ለኛው ነው የሰጠን። በከረጢትዋ ውስጥ ያሉት ፈርጦች አንድ ባንድ፣አንዳንዴም ካንድ በላይ ባንዴ እያብለጨለጩ ከባለ ከረጢቱ እጅ ላይ ይወድቃሉ። 📆ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜ ያልተጠቀምንባቸው የድል ፈርጦች ከጊዜው ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈው ይነጉዳሉ። ስኬት በትጋትና በስራ የተለወጡ እድሎች እንጂ ሌላ ምንም አይደሉም። ድህነት የባከኑ እድሎችና ያልተጠቀምንበት እድሜ ውጤት ነው እንጂ ያርባ ቀን እድል አይደለም። ምንጭ የተቆለፈበት ቁልፍ ደራሲ ዶ/ር ምህረት ደበበ የሁለቱን የጊዜ🗓 እይታ አንድነት ሆነ ልዩነት ለ እናንተ በመተው @erasn flega😍😊😘😁 በአግባቡ የተጠቀምክበት ጊዜ ወርቅህ ነው ብለን አበቃን! @erasn flega @erasn flega @erasn flega@erasn flega
نمایش همه...
አዋቂ ሰዉ ሁለት ልብ አለዉ አንዱ ሲደማበት በሁለተኛዉ ይታገላል ቁጅና የለዉ ፊት ላይ አይደለም ቁጅና በዉስጣችን የሚገኝ የልብ ብርሃን ነዉ። እምነት እዉነትነቱን ከማረጋገጥ ባሻገር በልብ ዉስጥ የሚገኝ እዉቀት ነዉ።ኢምንቷ የደግነት ስራ ትልቁን ነገር ለማድረግ ከማሰብ በላይ ዋጋ አላት።እዉነት እርቃኑን በባዶዉ መራመድ ይችላል።ዉሸት ግን አምሮ እና ደምቆ መልበስን ይፈልጋል ደግነት መስጠት ከምትችለዉ በላይ መስጠት ሲሆን ኩሩ መሆን ማለት ደግሞ ከምትፈልገዉ በታች መዉሰድ ነዉ።ፍቅር የመለያያ ሰአቱ እስኪደርስ ደረስ የራሱ ጥልቀት አይረዳም።ልክ እደ አበባ ሁን ፊትህን ወደ ፀሀይ ብርሀን አዙር ።ሀዘን እና ደስታ የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸዉ።ሁለቱም አብረዉ ይመጣሉ ።ነገር ግን አንዱ ብቻዉን ከጎንህ ሲሆን ሌላኛዉ ከቤትህ እደተጋደመ አትርሳ። በአንድ ህይወት ዉስጥ ወደ ኋላ እየተመለሱ መደሰት መቻል ሁለቴ መኖር ማለት ነዉ። ፍቅር እና ደግነት የድክመት እና የተስፋ መቁረጥ ምልክቶች ሳይሆኑ የጥንካሬ እና የዉሳኔ ሰጭነት መገለጫ ናቸዉ ትላንትና ለዛሬ ትዝታ ነዉ ነገ ደግሞ ለዛሬ ህልም ነዉ። ልክ ወንዝ አና ባህር አንድ እደሆኑት ሁሉ ህይወት አና ሞትም አንድ ናቸዉ። ጓደኝነት የሁል ጊዜ ጣፈጭ ሀላፊነት እንጅ አጋጣሚ አይደለም......
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
😳ድንቁርና ሲጮህ አዋቂነት ዝም ይላል* አህያ ለነብር ሳር ሰማያዊ ቀለም እንዳለው ይነግረዋል ። ነብርም አይ አይደለም አረንጓዴ ነው ይላል። እንዲህ እንዲህ እያለ በመሃከላቸው ያለው ክርክር እየሞቀ ሄዶ መግባባት አቃታቸውና እንዲ ሸመግላቸው የጫካው ንጉስ ወደሆነው ወደ አንበሳ ይሄዳሉ። ከዚያም አንበሳ ጋር እንደደረሱ አህያ እየጮኸች ክቡርነትዎ 'እውነት አይደል! ሳር ሰማያዊ ቀለም አይደል ያለው?' ትለዋለች። አንበሳም በትክክል በማለት መለሰላት። አህያም አሁንም ወደ ፊት ጠጋ በማለት ነብር በእኔ ሃሳብ አይስማማም፤ እኔን ይቃረነኛል ስለዚህ አስቆጥቶኛልና እባክህ ይቀጣልኝ አለች።አንበሳም በጥሞና ከአዳመጠ በኋላ ለ5 አመት ነብር ምንም እንዳያወራና ዝም እንዲል በማለት ፍርዱን አሳለፈ።አህያም በፍርዱ ተደስቶ እየዘለለ 'ሳር ሰማያዊ ነው' በማለት አየጮኸ ሄደ። ነብርም ፍርዱን ተቀብሎ ሲያበቃ ክቡርነትዎ ሳር አረንጓዴ ሆኖ ሳለ ለምን ቀጣከኝ? አለ። አንበሳም እንደዚህ መለሰ ፦'በእርግጥ ሳር አረንጓዴ ነው።' ነብርም ታዲያ ለምን ቀጣሃኝ አለው? አንበሳም መለሰ ' ሳር አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ መሆኑ ጥያቄው ምንም አያደርግም። እኔ ይህን የወሰንኩት እንደ አንተ አይነት ንቁ አስተዋይና ብልህ የሆነ በማይረባ ነገር ከአህያ ጋር እየተከራከረ ጊዜውን እንዳያጠፋና ሌላ ጊዜ እንዲህ አይነት ነገር ወደ እኔ እንዳይመጣብኝ ነው አለው። በመቀጠልም እንዲህ አለው 'ብዙው ሰአት የሚጠፋው ከሞኝ ጋር በምታደርገው ክርክር ነው።'ሞኝ ስለ እውነት ወይም እውነታነት ሳይሆን የሚጨነቀው ስለ ድልና ስለ እምነቱ ነው። በመጨረሻም 'ድንቁርና ሲጮህ አዋቂነት ዝም ይላል!'አለው። ከአሸናፊ አዲሱ ፌስቡክ ገጽ ላይ የተወሰደ
نمایش همه...
አልበርት አይንስታይን በክፍል ውስጥ ባለው ሰሌዳ ላይ የሚከተሉትን ስሌቶች እየጻፈ ለተማሪዎቹ እያሳየ ነበር፡- (9 X 1 = 9) . . . (9 X 2 = 18) . . . (9 X 3 = 27) . . . (9 X 4 = 36) . . . (9 X 5 = 45) . . . (9 X 6 = 54) . . . (9 X 7 = 63) . . . (9 X 8 = 72) . . . (9 X 9 = 81) . . . (9 X 10 = 91) ከእነዚህ የሂሳብ የድምር ስሌቶች ሁሉም ትክክል ሆነው ሳለ ለመጨረሻው የሰጠው መልስ 90 መሆን ሲገባው 91 በመሆኑ እንደተሳሳተ የተመለከቱ ተማሪዎቹ በጣም ሳቁበት፡፡ “ይህንን የመሰለ ሊቅ እንዴት ይሳሳታል” ነበር የሳቁ መነሻ፡፡ እሱም ሳቃቸውን እስከሚጨርሱ ጠበቀና፣ “የመጀመሪያዎቹን ዘጠኙን ጥያቄዎች በትክክል መመለሴን በማንሳት ማንም ተማሪ አላደነቀኝም፡፡ ነገር ግን አንዷን ስለተሳሳትኩኝ ብቻ ሁላችሁም ሳቃችሁብኝ፡፡ ይህች አለም እንዲህ ናት ጀግናው ለሰዎች ብዙ ጥሩ ነገሮችን ብታደርግ እንኳን ብታረግ እንኳን በአንድ ስህተት ብዙ ይሉካል ስለዚህ ሁሉንም ለማስደሰት መሞከር ትተህ እንተ የተመቸህን ሕይወት ኑር🔥 "SHARE"
نمایش همه...
#እነዚህን_3ቱን_ሁን! 📖 #ጠንካራ_ግን_ደግ_ሁን። አንዳንዱ ሰው ጠንካራ ሁን ሲባል ጭካኔን፣ ርህራሄ አልባነትን ይላበሳል። ለዚህች አጭር አለም የክፋት ገጸባህሪን ይጫወታል። ነጻ ሁን ግን ስነ ምግባር ያለው። አንዳንዱ ነጻ ሁን ሲባል ልቅ ይሆናል። ለሚያወራውም ይሁን ለሚያደርገው ሀላፊነት የማይሰማው አቦ ሰጥ አይነት። 📖 #ራስህን_ሁን_ሌላውንም_አክብር ራስህ ልትኮራበት የምትችለውን ነገር አድርግ ግን ከማንም ጋራ አትፎካከር። አንዳንዱ ራስህን ሁን ሲባል ከሌሎች ጋር በማያገናኘው ነገር ላይ ሳይቀር ግብ ግብ ይገጥማል። ራስህን ጠቃሚ በሆኑ ሰዎች መሃል አስገኝ ግን፤ ማንንም ለመናቅ ለራስህ አትፍቀድለት። አንዳንዱ ከጠቃሚ ሰዎች ጋር ሁን ሲባል ለአላማው የማይመቹ ሰዎችን ሁሉ በቸልታ በንቀት ይመለከታል። 📖 #ለራስህ_እውነተኛ_ሁን_ስብእናም_ይኑርህ ግን፤ ላገኘኸው ሁሉ ሚስጥርህን ተናገር ምንም ሚስጥር አይኑርህ ማለት አይደለም። መብትህን አታስጠብቅም አይደለም። አንዳንዱ እውነተኛ ሁን ሲባል ሚስጥሩን ላገኘው ይዘረግፋል ባዶ ቀፎ የሆነ ያህል እስኪሰማው ሁሉም ያውቀዋል። ለራስህ ስትል ተነስ ግን፤ ማንንም ጥለህ አጭበርብረህ አይሁን። አንዳንዱ ራስህን አንሳ ወድቀህ አትቅር ሲባል፣ ህይወትህን አስተካክል ሲሉት የሌሎችን አበላሽቶ ለሳቁ እንባ አስፈስሶ፣ ለመድረሱ አስቀርቶ በሌሎች መከፋት ላይ ይንጠላጠላል። ☑️ ሁን ግን እንዴት? ራስህን ጠይቅ! #በራስ_መተማመን መጽሐፍ 5ተኛ ዕትም #ራስን_መምራት 2ተኛ ዕትም ሁለቱም መጽሐፍት በገበያ ላይ ይገኛሉ 👇 ቴሌግራም- https://t.me/teklu_tilahun ፌስቡክ- https://www.facebook.com/booklandbook/
نمایش همه...
እኔና የካፌዋ አስተናጋጅ! ትናንት አንድ ካፌ ቁጭ ብዬ አንድ መጽሐፍ እያነበብኩኝ ሳለሁ ከአስተናጋጆቹ አንዷ ቀረብ ብላ “ምን ላምጣልህ” አለችኝ፡፡ ሃሳቤ በማነበው ነገር ተወስዶ ስለነበረ ለመልስ ዘግየት ስላልኩባት በትእግስት ከጠበቀችኝ በኋላ “ምን አይነት ሃሳብ እያነበብክ ቢሆን ነው እንደዚህ ትኩረትህን የሳበው?” አለችኝ፣ በፈገግታ፡፡ እኔም ለጥያቄዋ መልስ ከሰጠኋት በኋላ፣ “መጽሐፍ ታነቢያለሽ?” ብዬ ጠየኳት፡፡ የልጅቷ መልስ፡- “ሰዎች ከሚሰጡኝ “ቲፕ” የማገኘውን ገንዘብ በመለቃቀምና በማጠራቀም የየእለት ኑሮዬን ለማሸነፍ ከጠዋት እስከማታ ስለፋ ስለምውል ለማንበብም ጊዜ የለኝም” የሚል ነበር፡፡ ይህ መልሷ በወቅቱ አጠር ያለች ሃሳብ እንድለግሳት፣ ቤቷ ስትሄድ ደግሞ የምትሰራውን የቤት ስራን እንድሰጣት አነሳሳኝ፡፡ ይህቺ ሴት የዘነጋችው ነገር ቢኖር በየእለቱ የማንበብን ልማድ ብታዳብር፣ በምትለቅመው “ቲፕ” የየእለት ኑሮዋን ለማሸነፍ ከመታገልና ማለቂያ የሌለው ዑደት ውስጥ ከመቅረት አልፋ በምታነበው ሃሳብ ደግሞ የነገ ኑሮዋን የተሻለ የማድረግ አመራጩ እንዳላት ነው፡፡  ከዚህ በፊት አንብቤው ያነቃቃኝ አንድ ሃሳብ ትዝ አለኝና እሱን አሳብ በአጭሩ አጋራኋት፡- በቀን ውስጥ ካለን ጊዜ አንድ በመቶውን (1%) ብቻ ከዓላማችን አንጻር እድገት-ተኮር የሆኑ ጽሑፎችን ብናነብ በሌላ መልኩ ልናመጣ የማንችለውን ለውጥና እድገት እናመጣዋለን፡፡ ይህ ማለት በቀን ውስጥ ካሉን 1,440 ደቂቃዎች ውስጥ አንድ በመቶውን (1%) ማለትም 14.4 ደቂቃዎችን (15 ደቂቃ የማይሞላ) ጊዜያችንን ለንባብ መጠቀም ማለት ነው፡፡ ሰዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዓታትን በጥናት አሳልፈው በጥቂት ገጾች ውስጥ ያሰፈሩልንን እውቀት እኛ በቀን 15 ደቂቃዎችን ብቻ በማሳለፍ፣ በማንበብና ተግባራዊ በማድረግ ታላቅ የሆነ እድገት ውስጥ መግባት እንችላለን፡፡ አንድ ጥናት እንደሚነግረን በቀን ውስጥ በአማካኝ ከ60 ጊዜ በላይ ጊዜ ስልካችንን እናነሳለን፡፡ ይህ ልማድ በቀን ውስጥ ከ3 ሰዓታት በላይ ስልካችን ላይ የማሳለፍን ሁኔታ ይፈጥራል፡፡ ከዚህ አንጻር ሲታይ ለ15 ደቂቃዎች መጽሐፍን ማንሳት አስቸጋሪ አይደለም፣ የልማድ ጉዳይ ሆኖ ነው እንጂ! የልጅቷ መልስ ከዚህ ስሌት አንጻር ሲተረጎም፣ “ለማደግ ጊዜ የለኝም” የሚል ይሆናል፡፡ በየቀኑ የእለት ኑሮዋን ለመግፋት ሰዓታት በማሳለፍ የምትለቅመው “ቲፕ” አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በየቀኑ የወደፊት ኑሮዋን ለመለወጥ አስራ አምስት ደቂቃዎች በመውሰድ ሕይወት ለዋጭ እውቀት “የመለቃቀምን” ልማድ ብትጨምርበት ደግሞ እጅግ የተሻለ ነው፡፡ ካላት የማስተናገድ ሾል ሩጫ ሰረቅ በማድረግ የሰጠችኝን ትኩረቷን በመጠቀም ከላይ የዘረዘርኩትን  ሃሳብ ጠቆምኳትና እንዳጋጣሚ በቦርሳዬ ውስጥ የያዝኩትን በራሴው ከተጻፉት መጽሐፎች አንዱን ሰጠኋት፡፡ የመጨረሻ ጥያቄዋ እንዴት የንባብን ልማድ ላዳብር ነበረና የሚከተሉትን ለእኔ የጠቀሙኝን ልምምዶች አጋራኋት፡፡ 1.  የምታነቢውን የመጽሐፍ ርእስ ለማምጣት ከምትፈልጊው ለውጥ አንጻር ምረጪ፡፡ 2.  የማንበብን ልማድ በደንብ እስከምታዳብሪ ገጻተቸው አነስ ያሉ መጽሐፎች ላይ አተኩሪ፡፡ 3.  በቀን ውስጥ ለ15 ደቂቃዎች የምታነቢበትን ንቁ ሰዓት ለይተሽ መድቢ፡፡ 4.  በዚያን ጊዜ ሌሎች ማድረግ የምትፈልጊያቸው ነገሮች ብቅ ቢሉም፣ ሆን ብለሽ ከእነሱ ይልቅ ማንበብ ላይ አተኩ፡፡ 5.  ማንበብ ካስቸገረሽ የማንበብ ልማዱ ያላቸው የንባብ አጋሮችን በማዘጋጀት የጋራ ነገር በማንበብ ተበረታቱ፡፡ 6.  በቀን ውስጥ የማንበቢያ ክፍተቶችን ለይተሽ ተጠቀሚባቸው፡፡ የማንበቢያ ክፍተቶች ማለት፣ ሰውን ስትጠብቂ፣ በታክሲ ውስጥ ስትጓዢ፣ በስራ መካከል ያለ እረፍት፣ ከመተኛትሽ በፊት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ አንብቡ! እናንብብ! እንደግ! የወደፊታችንን እኛው እንወስን! ምንጭ:- ዶ/ር ኢዮብ ማሞ (ከቴሌግራም ቻናላቸው የተወሰደ)
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የእርዳታ ጥሪ የሚዲያ ተጠቃሚዎች የሆናቹ የሃገሬ ልጆች በሙሉ ሰላም ለናንተ ይሁን። ወጣት ተረፈ ታደሰ ካሳዬ የተባለ ወጣት በቤተክርስትያናችን በጸሎት ፣ በወንጌል ስርጭት እና በወጣቶች የሚያገለግል ሲሆን የአንድ ሚስት ባል እና የሁለት ልጆች አባት ነው። አሁን ላይ "የሀሞት ትቦ መጥበብ ወይም መዘጋት" በጠና ታሞ ቤተሰቡን ማስተዳደር እና አገልግሎቱንም ማገልገል አቅቶት በህመሙ ምክንያት እሰከ ቤተሰቡ እየተሰቃየ ይገኛል። ያሉበትም ሁኔታ በጣም ያሳዝናል። ሀኪሞች በአገር ውስጥ ህክምና ለመከታተል እንደማይችል እና ከሀገር ወጥቶ እንዲታከም ነግረውታል። ይሁን እንጂ ይህንን ከባድ ወጪ ለመሸፈን ለወንደማችን ህልም ሁኖበታል ስለሆነም ለወገን ደራሽ ወገን ነዉና የወንድማችን ሂወትን ለማትረፍ የኛ/የናንተ/ያንተ/ያንቺ እርዳታ ያስፈልገዋል። ስለዚህም ገንዘብ ያለዉ በገንዘብ ገንዘብ የሌለዉ ደግሞ በጸሎት ሞራል በመስጠት እንዲሁም ለብዙወች እንዲደርስ Like, comment & share በማድረግ ትብብራቹሁን እንድታሳዩ እንጠይቃለን ። " ... ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።" (1ኛ ተሰሎንቄ 5:15) 1000382765846 CBE 5116005978071 Dashin Terefe Tadesse Kassaye
نمایش همه...
ይህ የማይታመን ክስተት ነው እባካችሁ በሱስ ያለን እንንቃ ጫቴን ነካሽ ብሎ እናቱን ገደለ በተማም አሰፋ በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ምዕራብ ጎርጠንቹ ቀበሌ ልዩ ስሙ ወሽርሚኒ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መስከረም 29 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 ገደማ ‹‹ጫቴን ነካች›› ብሎ እናቱን የገደለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዉሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ፖሊስ ስለወንጀል ድርጊቱ ሲያብራራ ሟች በጓሮ የተከሉትን ጫት ሁሌም እየሰበሩ ይቅማሉ ቀሪውን ደግሞ ለነጋዴ ይሸጣሉ፡፡ በሽያጭ ያገኙትን ገንዘብ ደግሞ ለቤት አስቤዛ ያውሉታል፡፡ ተከሳሽ የጫቱን ኃላፊነት ለብቻው ጠቅልሎ በመያዝ እንዲያስተዳድር በማሰብና እናቱን ደግሞ ለማግለል እቅድ ያወጣል፡ ፡ ‹‹የተከልኩትን ጫት ከእንግዲህ እኔ ብቻዬ ነው የምጠቀመው›› በማለት ለእናቱ ከበድ ያለ ማስጠንቀቂያ ይሰጣታል፡፡ እናቱ በልጃቸው ዛቻ ተገርመው ልጄ ‹‹የጫት ማሳው ያአንተም የኔም ነው የሚሸጠውም የኔንና ያአንተን የቤተሰብ ወጭን ለመሸፈን ነው›› ብለው መልስ ይሰጡታል፡፡ በዚህ በእናቱ ሀሳብ ያልተስማማው ልጅ ከወላጅ እናቱ ጋር ጭቅጭቅ ይጀምራል፡ ፡ በመሀላቸው ሶስተኛ ወገን ሽማግሌ ገብቶ ያስታርቃቸዋል፡፡ ልጅ በእናቱ ላይ ቂም በመያዝ እናቲቱ ሀገር አማን ነው ብለው ቡና እያፈሉ እያለ ጭካኔ በተላበሰ መንገድ በድንጋይ ማጅራታቸወውን ደጋግሞ በመምታት ከፍተኛ ጉዳት ያደርስባቸዋል፡፡ እናቲቱም ጩኸት ያሰማሉ፡፡ ጩኸቱን የሰሙ የአካባቢው ማህበረሰብ ከቦታው ሲደርሱ ያዩትን ማመን ከበዳቸው እናትም በልጃቸው በደረሰባቸው ከፍተኛ ጉዳት ህወታቸው ያልፋል፡፡ ፖሊስ ከቦታው ደርሶ ተጠርጣሪውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ በሰውና በህክምና ማስረጃ አስደግፎ ከዓቃቤ ህግ ጋር በመሆን በሰው መግደል ወንጀል ክስ መስርቶ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦታል መረጃውን ያገኘው ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ነው፡፡ ምንጭ: ፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ @erasnflega🦋🦋🦋🦋🦋🦋
نمایش همه...