cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ፍኖተ ተዓውን መረጃ ቻናል

ፍኖተ ተዓውን የተአውን ልማትና መረዳጃ ልሳን ሲሆን የተመረጡ ጠቃሚ መረጃወችን ለአባላት በማካፈል የርስ በርስ ቅርርብንና ትብብርን ማሳደግና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ማሳለጥ አላማው ነው።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
218مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo from Muhammed Anwar
نمایش همه...
የሺዓና የአህሉሱና የዓሹራ ውሎ ✍ አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ ሙሀረም 12/ 1436 ዓ.ሒ ተፃፈ የዓሹራ ቀን፤ የፊዓአውንን ትእቢትና አምባገነነንነት ያከተመበትና ለሌሎችም መቀጣጫ የሆነበት፣ ነብዩላህ ሙሳም የተደሰቱበት ለአህሉሱና ታላቅ ትርጉም ያለው የድል ብስራት ቀን ነው። አህሉሱና ይህንን ቀን በአል አያደርጉትም። የተለየ ድግስም ሆነ አለባበስ የላቸውም። ሆኖም መልእክተኛው ﷺ በደነገጉት መሰረት ይፆሙታል፣ መልካም ተግባራትን ይፈፅሙበታል፣ ከአላህ ልዩ ምንዳን በመከጀልም በዒባዳ ያሳልፉታል። ሺዓዎች ግን ስለ ዓሹራ ቀን ሲያስቡ ሚታወሳቸው የታላቁ ሰሀቢይ የአሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ልጅ ሁሰይን የተገደሉበት ቀን መሆኑ ብቻ ነው። ሺዓዎች በዚህ ቀን ሀዘናቸውን ለመግለፅ እራሳቸውን የሚጎዱ ብዙ ነገሮችን በስፋት ይፈፅማሉ። ጭንቅላትንና ሌሎች አካሎቻቸውን በስለት መብጣትና ማድማት (ተጥቢር)፣ ፊታቸውን መደብደብ (ለጥም፣) እራስን በሰንሰለት መግረፍና ማንገላታት፣ በእንብርክክ መሄድ፣ ብዙዎችም ዘንድ ጥቁር መልበስና የለቅሶ ሙሾ ማውረድ ብሎም በራስ ላይ ኩነኔን መጥራት የተለመዱ የአሹራ ትእይንቶቻቸው ናቸው። በእጅጉ ይገርማል፤ ለኛ ለአህሉሱና ደስታን ሲያላብሰን፣ ተስፋን አሰንቆ ድልን ሲያበስረን፤ ለወንጀላችን ማርታን ለማግኘት ሩጫ ውስጥ ሲከተን፤ ለሺአዎች ግና፤ የሀዘን የዋይታ፣ የውድቀት የሽንፈት ማስታወሻ፣ የተስፋ ማጨለሚያ ነው!! ሁሰይን የነብዩ ﷺ የልጅ ልጅ በኢስላማዊ እውቀት ከመጠቁ ታላላቅ ሰሀቦች አንዱ ናቸው። በኢባዳ ብርቱ የተወዳጇ የመልእክተኛው ﷺ ልጅ የፋጢማ ረዲየላሁ አንሀ ልጅ ናቸው። ሆኖም... ቀሪውን በዚህ ሊንክ ያንብቡ http://clearfaith.blogspot.com/2015/10/blog-post.html?m=1
نمایش همه...
#መልካም_ዜና‼ በመዲና በእንግልት ላይ ለነበሩት ኢትዮጵያውያን ሁጃጆች የሳዑዲ መንግስት ደረጃውን ወደ ጠበቀ ሆቴል እንዲዘዋወሩ አደረገ! ለመጅሊሱ 241ሺህ ብር ከፍለው ለሐጅ ወደ መዲና የተጓዙ ኢትዮጵያውያን ሁጃጆች ያረፉበት ሆቴል መሰረታዊ የሚባለው የውሃ አቅርቦት የሌለው፣ ምግብ መመገቢያ ወንበር የሌለው ፣ምግቡ ጥራት የሌለው እጅግ አሳፋሪ ሆቴል የነበረ ሲሆን ኢትዮጵያውያን ሁጃጆች በሆቴሉ እየደረሰባቸው ያለውን እንግልት ስሞታ እና እሮሮ ሲያሰሙ ነበር:; በትላንትናው እለትም ይህን የሁጃጆች እሮሮ መረጃ ማጋራታችን የሚታወስ ሲሆን በሁጃጆቹ ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት እና ግፍ ለሳዑዲ መንግስት በደረሰው ጥቆማ መሰረት ከሳዑዲ የሐጅ ሚኒስተር ፣ከመዲና አሚር አስተዳደር ቢሮ እና ከመዲና መዘጋጃ ቤት የተውጣጣ የጋራ ኮሚቴ በሆቴሉ ያለውን ሁኔታ ከተመለከቱ ቡኃላ ለአረህማን እንግዶች ይህ አይገባም በማለት እጅግ ዘመናዊ ባሶችን በማስመጣት ኢትዮጵያውያን ሀጃጆች ካረፉበት ውሃ እንኳን በአግባቡ ከሌለው ሆቴል እንዲወጡ አድርገዋል:: የሳዑዲ መንግስት ለኢትዮጵያውያን ሁጃጆች እጅግ ክብር በተሞላበት መልኩ ዘመናዊ ባስ ትላንት ለሊት በማቅረብ ለመስጂደ ነበዊ እጅግ ቅርብ ወደ ሆነ መርከዚያ ደረጃውን ወደ ጠበቀ ባለኮከብ ሆቴል እንዲዘዋወወሩ አድርጓል:: መጅሊሱ ትርፍ ለማጋበስ ሲል እጅግ የወደቀ ማረፊያ ተከራይቶ ሁጃጆቹን ሲያንገላታ የነበረ ሲሆን ይህን የተከራዩትን የነበረውን ሆቴል የሳዑዲ መንግስት እንዲታሸግ አድርጓል:: አላህ የሁጃጆቹን ለቅሶ ሰምቶ በሳዑዲ መንግስት አማካኝነት ለመስጂደል ነበዊ አጠገብ ባሉ ሆቴል እንዲያርፉ የተደረገ ሲሆን ሆቴሉም የራሱ ዘመናዊ ሬስቶራንት ያለው፣ ለሁጃጆቹም በቀን ሶስት ጊዜ ምግብ በብፌ መልኩ በማቅረብ እንግዶችን የሚያስተናግድ ነው:: የሆቴሉን ክፍያ በተመለከተ ለጊዜው በሳዑዲ መንግስት የተሸፈነ ሲሆን መጅሊሱ ለኢሹራንስ ካስያዘው ብር ላይ ተቆራጭ እንደሚደረግ ታውቋል:: ሁጇጆቹ በመዲና ቆይታቸው በነዚህ ሆቴሎች የሚቆዩ ሲሆን ወደ መካ ሲሄዱም የተሻለ ማረፊያ መጅሊሱ ከዚህ ትምህርት ወስዶ ሊያዘጋጅላቸው ይገባል! አቡ ዳውድ ኡስማን
نمایش همه...
*በነገው የመርከዘ ሱና የሁፋዞች የምረቃ በአል ላይ ለመታደም ወደ ደማቋ መካነሰላም እያመሩ ካሉ ታላላቅ ኡስታዞችና መሻይኾች* 🫐🌿🌹💐🌾
نمایش همه...
🌷አስደሳች ዜና 🌷 በታላቁ የደባት ሸኽ ሃጂ ዐበደል ከሪም አህመድ እና በታላቁ ዳዒና ሸኽ ሸኽ ዙበይር ዐብዱል መጂድ(رحمهما الله تعالى) ልዩ ጥምረት የተመሰረተው እና በሀገር አቀፍ ድረጃ እውቅናን ያተረፉ በመቶ የሚቆጠሩ ሃፊዞችን ያፈራው አንጋፋው የሂፍዝ ማእከል መርከዝ አስሱና መካነ ሰላም በመጪው #እሁድ ሰኔ 19 /2014 አ.ል መላው የመካነ ሰላም እና አካባቢዋ ሙስሊም ህበረተሰብ እና ጥሪ የተደረገላቸው ታላላቅ ዑለማኦች በተገኙበት ከአርባ በላይ ሀፊዞችን በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል። ** በመሆኑም ማንኛውም የአካባቢ ተወላጅም ሆነ አጠቃላይ የኢስላም ጉዳይ የሚያገባው ሁሉ በዚህ ቁርኣንን ከፍ በምናደርግበት ታሪካዊ የምርቃትና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት የበኩለዎን ኢስላማዊ አሻራ እንዲያሳርፉ ተጋብዘዋል። ®[ኡስታዝ መሀመድ ሀሰን ]
نمایش همه...