cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አዲስ ነገር መረጃ

አዲስ ነገር መረጃዎች መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇 @Addisnegermereja_bot

نمایش بیشتر
Advertising posts
76 269مشترکین
-4024 ساعت
-427 روز
-56130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የቡርኪናፋሶ ጦር በ223 ሰዎች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰዱን የሰብዓዊ መብት ድርጅት አስታወቀ በተያዘው አመት ከ220 በላይ ንፁሀን ዜጎች፣ ቢያንስ 56 ህፃናት በቡርኪናፋሶ ጦር በአንድ ቀን ተጨፍጭፈዋል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል። በሰራዊቱ ላይ የተፈፀመው ጥቃት ለመበቀል ጦረ በሶሮ መንደር 179 ሰዎች ሲገድል 44 ሌሎች  ሰዎች ደግሞ በአቅራቢያው በሚገኘው ኖንዲን መንደር ውስጥ መገደላቸውን የመብት ተሟጋች ቡድሙ ያደረገው ምርመራ አረጋግጧል።የጅምላ ግድያው "በሀገሪቱ ከአስር አመታት ወዲህ ከተከሰቱት እጅግ የከፋ የጦር ሰራዊት ጥቃት" ሲል ገልጿል። የቡርኪናፋሶ ባለስልጣናት በሪፖርቱ ላይ አስተያየት እስካሁን አልሰጡም። ባለፈው ወር የህዝብ አቃቤ ህግ አሊ ቤንጃሚን ኩሊባሊ ከጅምላ ግድያው ጀርባ ያለውን ቡድን ለመለየት ምስክሮች እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። በወቅቱ የሟቾችን ቁጥር 170 አድርሶታል። ከጥቃቱ የተረፉ መንደርተኞች ለሂውማን ራይትስ ዎች እንደተናገሩት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንዳለፉ  ከ30 ደቂቃ በኋላ ወታደራዊ ኃይሉ ወደ ኖንዲን መንደር መውረዱን ተናግረዋል። ወታደሮቹ ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ ነዋሪዎችን ከቤታቸው እያባረሩ ወንጀሉን ፈፅመዋል ሲሉ ተደምጠዋል። በመቀጠል 5 ኪሜ ርቀት ላይ ወደምትገኘው ሶሮ መንደር ደርሰው ከአንድ ሰአት በኋላ በመንደሩ ሰዎች ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ከጥቃቱ  የተረፉት እማኞች ገልጸዋል። በሁለቱም መንደሮች ወታደሮቹ ለመደበቅ ወይም ለማምለጥ በሞከሩ ሰዎች ላይ መተኮሳቸውን እማኞቹ አክለዋል። የጅምላ ግድያው በወታደሮች የተወሰደው በታጣቂ ቡድን ለተፈፀመባቸው ጥቃት የበቀል እርምጃ ነው ተብሎ ታምኖበታል። የመንደሩ ነዋሪዎች የታጠቁ ተዋጊዎችን ይረዱ ነበር በሚል ተከሰዋል። በሰሜናዊ ያትንጋ ግዛት አቅራቢያ በሚገኝ የጦር ካምፕ ላይ ታጣቂ ቡድኖች ጥቃት ሰንዝረዋል።የሂዩማን ራይትስ ዎች ዋና ዳይሬክተር ቲራና ሃሰን እንዳሉት በኖንዲን እና በሶሮ መንደር የተፈፀመው እልቂት የቡርኪናፋሶ ወታደሮች በፀረ-ሽምቅ ዘመቻቸው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈፀሙት የቅርብ ጊዜ የጅምላ ግድያ ነው ሲሉ ተደምጠዋል። @Addis_News
نمایش همه...
👍 20
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ብድር እዳ እንዳለበትና የዕዳ ጫናዉን ለማቃለል የባንክ ወለዱ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን አስታወቀ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል የ9 ወራት የስራ አፈፃጸም ሪፖርት ባዳመጠበት ወቅት የተቋሙ የብድር ጫና በጣም ከፍተኛ መሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በሪፖርታቸው እንደገለፁት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ብድር እንዳለበት እና የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ አስረድተዋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ተቋሙ ካለበት የዕዳ ጫና ለመውጣት የታሪፍ ማሻሻያዎችን የውጭ የሃይል ሽያጭ አቅሞችን በማጠናከር እና የውስጥ ገቢን በመሳደግ ለዕዳ ቅነሳው ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ማሳሰብን ካፒታል ሰምቷል። Via:ካፒታል @Addis_News
نمایش همه...
👍 6
በርካታ የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግር ጥቆማዎች እየደረሱኝ ነው - የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በርካታ የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግር ጥቆማዎች እየደረሱት መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡ ባለስልጣኑ የጥቆማ መቀበያ ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ካደረገ በኃላ በርካታ ጥቆማዎች እየደረሱት መሆኑን የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለኢቢሲ ሳይበር ተናግረዋል፡፡ የሚመጡ ጥቆማዎችን ተገቢነት በማጣራት ጥፋተኞችን ለሕግ ለማቅረብ ከፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ የጥላቻ እና ሐሰተኛ ንግግሮች በአዋጁ መሰረት ከገንዘብ እስከ እስራት ቅጣት እንደሚያስከትሉ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ጠቁመዋል፡፡ ባለስልጣኑ የማህበራዊ የትስስር ገጽ አገልግሎት ሰጪዎች የኢትዮጵያን ሕግ እና ስርዓት አክብረው እንዲሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡ ህዝቡ ለሀገራዊ ሰላም እና ለህዝቦች አንድነት ፀር የሆኑ የሐሰተኛ እና የጥላቻ ንግግሮችን ሲመለከት በ9192 ነጻ የስልክ መስመር ጥቆማዎችን እንዲሰጥ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡ @Addis_News
نمایش همه...
👍 11
የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ የፀረሰላም ኃይሎችን በመደገፍና ጦር መሳሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። ክሱ የተመሰረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግስት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን በሚመለከተው ችሎት ነው። የፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በተከሳሽ ታዬ ደንደአ ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቧል። በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 251/ሐ እና አንቀጽ 257/ሰ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ እና የጦር መሳሪያ አዋጅን መተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦባቸዋል። በክሱ ላይ እንደተመላከተው÷ተከሳሹ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገርን፣ የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ማረጋገጥ ሲገባቸው ይህን ወደጎን በመተው ፀረሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ የፕሮፖጋንዳ መልዕክቶችን በማስተላለፍ በስማቸው በተከፈተ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ድጋፍ የሚገልጹ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ነበር የሚል ነው፡፡ እንዲሁም ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ አዋጁን በመተላለፍ በታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 5 ሰዓት ላይ በልደታ ክ/ከ ወረዳ 6 በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተደረገ ብርበራ አንድ ታጣፊ ክላሽን ኮቭ መሳሪያ ከ2 ክላሽ ካዝና እና ከ60 ጥይት ጋር ይዘው መገኘታቸው ተጠቅሶ ክስ ቀርቦባቸዋል። ተከሳሽ አቶ ታዬ ደንደአ በአራት ጠበቆቻቸው ተወክለው ችሎት ቀርበው የክስ ዝርዝሩ ተነቦላቸዋል። ክሱ ከተነበበ በኋላ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ ቀርቧል። የችሎት ዘገባው የፋና ነው። @Addis_News
نمایش همه...
👍 14🤔 4😐 1
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ በቤሩት የገጠመው አስገራሚ ነገር የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚበርባቸውን አየር ማረፊያዎችና የቱሪዝም መዳረሳዎችን ስም በአውሮፕላኖቹ ላይ ይፅፋል። ለምሳሌ ኪሊማንጃሮ፣ ቶሮንቶ፣ ጀኔቫ፣ ዳሎል፣ ሰሜን ተራሮች፣ አድዋ ፤ አልነጃሺ ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው (በፎቶው እንደሚታየው)። ዛሬ ታዲያ ወደ ቤሩት የበረረው አየር መንገዳችን የበረራ ቁጥር ET-AXK የውሮፕላን በቢሩት ራፊቅ አል ሃሪሪ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደረሰ። አውሮፕላኑ ወደ ኋለኛው ክፍሉ ላይ በአነስተኛ ፅሁፍ "Tel Aviv" የሚል ስም የተፃፈበት ነበር። የሰሞኑ የእስራኤል ሃማስ ጦርነት ያመጣው ዳፋ ለኛም ተርፎ ጉዳዩን በበጎ አልተመለከቱትም የቤሩት ባለስልጣናት። የአገሪቱ የሲቪል አቪየሽን ዳሬክቶሬት ጀየራሉ አየር መንገዱ ተመልሶ ከመነሳቱ በፊት ስሙ መፋቅ እንዳለበት ገልፆ ከዚህ በኋላ አየር ማረፊያውን ሲጠቀም ከእስራኤል ጋር የተያያዙ ምልክትና ፅሁፎች መጠቀም እንደሌለበት ተገልፆለታል ተብሏል፡፡ via - Ibcgroup tv @Addis_News
نمایش همه...
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተዘገበ ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል። ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል። በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።  እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ  ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም። Via Addis Maleda @Addis_News
نمایش همه...
👍 20
ጎማ የተገጠመለት ተንቀሳቃሽ የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ በ29 ሺ የአሜሪካን ዶላር ገደማ መሸጡ ተሰማ ጎማ የተበጀለት የአስክሬን ሳጥን በተሽከርካሪ መልክ መቅረቡን ተከትሎ በ28,750 የአሜሪካን ዶላር የተሸጠ ሲሆን ያልተለመደው የሳጥኑ ቅርፅ መኪና ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። እኤአ በ1965 ለእይታ ይቀርብ ከነበረው የቴሌቭዥን ተከታታይ ዘ ሙንስተር ትዕይንት ላይ ድራግ-ዩ-ላ የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ መነሳሻ ሆኖ እንደተሰራም ተሰምቷል።ይህ ያልተለመደ የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ የሳጥን-ፍሬም እና ስምንት የፋይበርግላስ ሳጥን በመጠቀም ስራ ላይ ውሏል። የሹፌሩ መቀመጫ የተበጀለት ሲሆን ለተመለከተው በሙሉ እውነተኛ አስክሬን የጫና እንዲመስል ሆኖ ተሰርቷል። የተሟላ ሰፊ የኋላ ጎማዎች በእሽቅድምድም ተንሸራታች ተደርገው የተሰሩ ሲሆን፣ ቀጥ ያሉ የጭስ ማውጫ ቱቦዎች እና የፋኖስ አይነት መልክ ያላቸው መብራት የተሞላው ይህ የሬሳ ሳጥን መኪና ከትክክለኛው ለመንገድ ብቁ ነው ከሚባለው ተሽከርካሪ ይልቅ ለፊልም የሚውል ንድፈ ሀሳብ ይመስላል። ነገር ግን ይህው የአስክሬን ሳጥን ተሽከርካሪ በኒውዮርክ ተመዝግቧል። በምዝገባውም በ1928 ፎርድ እና ትክክለኛ የሰሌዳ ቁጥር ተሰጥቶታል። የሹፌሩ ክፍል በሬሳ ሣጥኑ የኋላ ክፍል ላይ የሚገኝ ሲሆን አነስተኛ መቀመጫ በሰማያዊ ጨርቃ ተሸፍኗል። ቼቭሮሌት ቪ8 ሞተር በሻሲው ማእከሉ ወደ ኋላ ተቀምጧል። ባለአራት በርሜል ካርቡረተር፣ የኤደልብሮክ ማስገቢያ መያዣ እና ሪብብ ቫልቭ አሉት። የማርሽ ሳጥኑን በተመለከተ አውቶማቲክ ሲሆን በወርቅ ቀለም በተቀባ የጽጌረዳ ዘዬዎች ተቀርጿል። የነዳጅ ማጠራቀሚያው ወደ ተሸከርካሪው አፍንጫ አቅጣጫ ላይ ተቀምጧል ።ጎልቶ እንዲታይ ለማድረግ በወርቅ ቀለም የተቀባ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ ሌሎች ጎልተው እንዲታዩ የሚገባቸው የተሽከርካሪው ክፍል አካል ሲሆን ለምሳሌ እንደ መቃብር ላይ ሀውልት ከፊት ለፊት ያለው የመቃብር ድንጋይ እና ግዙፍ የጭስ ማውጫዎች ለማመሳሰል ተሞክሯል።ልዩ የሆነው ተሽከርካሪ ኦዶሜትር የተገጠመለት ስላልሆነ አጠቃላይ የኪሎሜትር ርቀት አይታወቅም። በሰዓት በምን ዓይነት ፍጥነት እንደሚጓዝ ምንም አይነት መረጃ ማግኘት አልተቻለም። ነገር ግን ተሽከርካሪው የውድድር መኪና እንዳልሆነ ይታወቃል ተብሏል።የአስክሬን ሣጥን መኪናው ባለፈው ሳምንት በ28,750 ዶላር የተሸጠ ሲሆን፥ መኪናውን በተለያዩ ዝግጅቶች ጨረታ በማሸነፍ እና ልዩ ልዩ ምርቶችን በመሰብሰብ የሚታወቅ ድርጅት የግሉ አድርጎታል። @Addis_News
نمایش همه...
👍 21🤔 2
አሜሪካ ዩክሬንን ለመርዳት የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን በድብቅ መላኳ ተነገረ ዩክሬን ዩናይትድ ስቴትስ በድብቅ የሰጠችውን የረዥም ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በሩሲያ ወራሪ ሃይሎች ላይ መጠቀም መጀመሯን የአሜሪካ ባለስልጣናት አረጋግጠዋል። መሳሪያዎቹ በመጋቢት ወር በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የፀደቀው የ300 ሚሊዮን ዶላር የእርዳታ ጥቅል አካል ሲሆኑ በዚህ ወር ዩክሬን ደርሰዋል። በሩሲያ በተያዘችው የዩክሬን ግዛት ክሬሚያ ድራስ ኢላማዎችን ለመምታት ቢያንስ አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋ። ባይደን በተመሳሳይ አሁንም ለዩክሬን የ61 ቢሊዮን ዶላር የእርዳታ ፓኬጅ ፈርመዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ቀደም ለዩክሬን መካከለኛ ክልል የሚደርሱ የጦር ሃይል ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም አቅርባ ነበር። ነገርግን የበለጠ ኃይለኛ የጦር መሳሪያዎችን ለመላክ ፍቃደኛ ሳትሆን የቀረች ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በከፊል የአሜሪካን ወታደራዊ ዝግጁነት ለመጉዳት ያሳስባል በሚል ነበር። ሆኖም ባይደን በየካቲት ወር እስከ 300 ኪ.ሜ የሚተኮሱ የረዥም ርቀት የሚሳኤል ስርዓትን ለዩክሬን ለመላክ አረንጓዴ መብራትን በድብቅ መስጠታቸው ተነግሯል። የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ቬዳንት ፓቴል "ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳኤል መሳሪያብ በፕሬዝዳንቱ ቀጥተኛ መመሪያ እንደሰጠች አረጋግጠዋል። ከመሳሪያዎቹ ውስጥ ምን ያህሉ እንደተላከ ግልጽ ባይሆንም የዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ዋሽንግተን ተጨማሪ ለመላክ አቅዳለች ብለዋል። ረጅም ርቀት የሚጓዙ ሚሳኤሎች ባለፈው ሳምንት ለመጀመሪያ ጊዜ በክራይሚያ የሚገኘውን የሩሲያ አየር መንገድ ለመምታት ጥቅም ላይ መዋላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ስማቸው ያልገለጻቸውን የአሜሪካ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል። አዲሶቹ ሚሳኤሎች ማክሰኞ እለት በሞስኮ በተያዘችው የዩክሬን የወደብ ከተማ በርዲያንስክ ውስጥ በሩሲያ ወታደሮች ላይ በተሰነዘረ ጥቃትም ጥቅም ላይ ውለዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። በቅርብ ወራት ኪየቭ የጥይት ክምችቷ በመሟጠጡ እና ለሩሲያ ይህ ሁኔታ ቀጣይነት ያለው ትርፍ ስለሚያስገኝ በሚል ለምዕራቡ ዓለም የእርዳታ ጥሪዋን እያጠናከረች ትገኛለች። @Addis_News
نمایش همه...
👍 12
ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ሸገር ሲቲ አንድን አባት እኚህን አባት ከየት መጣህ ? ለምን መጣህ ? ማን ነህ ? ምንድን ነህ ? እያሉ እየተሳለቁባቸው፣ሲያስጨንቋቸው እና ሲደበድቧቸው የሚያሳይ ምስል ተቀርፆ ወጥቶ መነጋገሪያ ሆኖ መክረሙ ይታወሳል። ይህ የሆነው በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ለገጣፎ አቅራቢያ 44 ማዞሪያ ጅዳ ኩራ በተባለ ቦታ ሲሆን ከቀናት በፊት ተደብዳቢው አባትም ደብዳቢዎቹም ጅዳኩራ በተባለ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበረ ቢሆንም ድብደባ እና ወከባ የደረሰባቸው አባት(አቶ ብርሃኑ) ትናንት ከእስር ተፈተዋል። እኚህ አባት ላይ ወከባ እና ድብደባ ፈፅመውባቸው የነበሩ7 ወጣቶች በፍ/ቤት ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። @Addis_News
نمایش همه...
👍 76
በአርጀንቲና መንግስት ለትምህርት የሚያደርገዉን ድጎማ በማቋረጡ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነሳ በመላው አርጀንቲና የትምህርት ወጪ መቀነስን በመቃወም ታላቅ ሰልፎች ተካሂደዋል።የፕሬዚዳንት ጃቪየር ሚሌ አክራሪ የቁጠባ እርምጃዎች በህዝብ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የሚያስከትለውን ውጤት በመቃወም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አርጀንቲናዉያን ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች ከሀገሪቱ ኃያላን የሰራተኛ ማህበራት እና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመቀላቀል ተቃዉሞ አሰምተዋል። የቀኝ አክራሪው ፕሬዝደንት በታህሳስ ወር ስልጣን ከያዙ በኋላ በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ተከታታይ ተቃውሞዎች የተደረጉ ሲሆኑ የአሁኑ በተገኘዉ ህዝብ ብዛት ትልቁ ነዉ ተብሏል፡፡አስተባባሪዎች ዩንቨርስቲዎችን የመዝጋት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ያሉትን የበጀት ቅነሳን ለመቃወም ጥሪ አቅርበዋል። የቦነስ አይረስ ዩኒቨርሲቲ በዋና ከተማው ብቻ በተቃውሞው ላይ ከ500 ሺ በላይ ሰዎች መሣተፋቸውን ገልጿል።ሚሌ በምርጫ ዘመቻው ወቅት የህዝብ ወጪን ለመቀነስ እና የመንግስትን ከባድ የኢኮኖሚ ፈተናዎች ለመፍታት እየሰሩ ይገኛል፡፡ኢኮኖሚውን ለማስተካከል የተወሰኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን መዝጋት፣ የባህል ማዕከላትን ከጥቅም ውጪ ማድረግ፣ የመንግስት ሰራተኞችን ማሰናበት እና ድጎማዎችን ማቋረጠ ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል ናቸዉ፡፡ @Addis_News
نمایش همه...
👍 19