cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ሰበር ዜና ETHIOPIA

አላማችን መረጃን በአግባቡ በጥራት በፍጥነት ማድረስ ነው፡፡ @Ethioseberzina

نمایش بیشتر
Advertising posts
203مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ነዳጅ‼️ አማራ ክልል ወደ ገጸምድር እየፈሰሰ ባለው ነዳጅ ላይ ጥናት እያካሄደ ነው። 👉እየፈሰሰ ያለው ነዳጅ ፔትሮሊዮም መሆኑን ተረጋግጧል። የአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ከከርሰ ምድር ወጥቶ ወደ ገጸምድር እየፈሰሰ ባለው የተፈጥሮ ነዳጅ ላይ ጥናት እያካሄደ እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡ በክልሉ ካሉ ዩንቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር በዞኑ የጥናት ቡድን ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ፣ የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ የጥናት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ደረጀ አሰፋ ተናግረዋል፡፡ ቡድኑ በደቡብ ወሎ ዞን በተለይም ወረኢሉ ወረዳ ላይ ትኩረቱን እንዳደረገ እና ጥናቱ የተሻለ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ እስካሁን በተደረገው ጥናት ከከርሰ ምድር ወደ ገጸምድር እየፈሰሰ ያለው ነዳጅ ፔትሮሊዮም መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ተጨማሪ ግኝቶችን አስመልክቶ ጥናቱ እንዳበቃ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ የተቋቋመው የጥናት ቡድን የመተማ እና የአባይ ዝቅተኛ ቦታዎቸ ላይም ተመሳሳይ ሥራ በመስራት ለመንግሥት ሀሳብ የሚያቀርብ መሆኑን አክለዋል፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ በኢትዮጵያ የፔትሮሊዮም ነዳጅ ሊገኝባቸው ይችላል ተብሎ ከሚገመቱ አምስት ቦታዎች ውስጥ አምስቱ የሚገኙት በአማራ ክልል ነው፡፡ እነሱም የመተማ አካባቢ እና የአባይ ዝቅተኛ ቦታዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በሶማሌ ክልል ኦጋዴን ሰባት ትሪሊዮን ኪዩቢክ ቤዚን ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ማዕድን ሚኒስቴር ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡ በኦጋዴን ቤዚን ያለውን ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት ክምችትና የኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት መጠናቁም የሚታወስ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው በተባለለት በዚህ ጥናት ከዚህ ቀደም ከሁለት እስከ ሶስት ትሪሊየን ኪዩቢክ ጫማ እንደሆነ ሲገመት የነበረው የኦጋዴን ቤዚን የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት በሁለትና ሶስት እጥፍ የጨመረ ሆኖ መገኘቱ ተነግሯል፡፡ (በሳሙኤል ታዴ፣አዲስ ማለዳ) ህዳር 29/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ሆነ የፌደራል መንግስቱ ኃላፊዎች በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የሕዝብ ተመራጮች ለመረጣቸው ህዝብ ድምፅ ሆነው አስፈላጊውን ማስተካከያ እንዲደረግ ጫና ካልፈጠሩ እና  ሁኔታውን የማያረጋጉ ከሆነ፣  ሂደቱ ወደ አላስፈላጊ ብጥብጥና አለመረጋጋት ከተሸጋገሩ የመጀመሪያ ተጠያቂዎች መሆናቸውን አበክረው ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ህዳር 29/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
Natnael Mekonnen: የአዲስ አበባን ሕዝብ መብትና ፍላጎት በጉልበት ለመጨፍለቅ የሚደረገው እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ይቁም! ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ /ኢዜማ/ የተሰጠ መግለጫ፤ ባለፈው ዓመት ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቂሊንጦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጀምሮ እስከ ትናንትናው ህዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በበርካታ የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ፣ የክልል መለያ አርማና መዝሙርን መነሻ በማድረግ አላስፈላጊ ውጥረትና ግጭት እንዲቀሰቀስ እና የትምህርት ሂደቱ እንዲስተጓጎል ተደርጓል፤ ሁኔታውም እየተባባሰ ሊሄድ እንደሚችል የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶችም አሉ። ሰንደቅ ዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር የሀገርን ትርጉም የሰነቁ ትዕምሮቶች ናቸው። ጀግኖች አባቶቻችን ቀኝ ገዢ ወራሪዎችን የተፋለሙት የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ አንግበው፤ ብሔራዊ መዝሙሯንም በሕብረት እየዘመሩ ስለመሆኑ ታረክ በደማቁ መዝግቦታል። አትሌቶቻችን ድል ባደረጉባቸው የዓለም አደባባዮች ሁሉ በድል ከፍ አድርገው ያውለበለቡት የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ ነው። በስሜት እንባቸውን አፍስሰው የዘመሩትም ብሔራዊ መዝሙራችንን ነው። በአሸባሪዎች የተከፈተብንን ጦርነት የመከትነውም በሀገራችን ሰንደቅዓላማ ስር ተሰባስበን ነው። ይህ ሁሉ የሚያመለክተው ሰንደቅዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር የሀገር መገለጫ ክቡር ጌጦች መሆናቸውን ነው። ከዚህ መሠረታዊ ግንዛቤ፣ መርህ እና ሕጋዊ አሠራር ባፈነገጠ መልኩ ካለፈው ዓመት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚደረገው ሕገወጥ የሆነ የአንድን ክልል መዝሙር እና መለያ አርማ ከሀገር ሰንደቅ ዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር እኩል ወይም በላይ ተማሪዎች ላይ ለመጫን መሞከር ግጭትና ሁከትን ወደ ከተማዋ ማስረግ መታሰቡን ማሳያ ነው፡፡  ኢዜማን ግርታ የፈጠረበት ጉዳይ በከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡ የአዲስ አበባ አስተዳደር እና የፌደራል መንግስት ሀላፊዎች በጉዳዩ ላይ ያላቸው አረዳድ ትክክለኛ ባለመሆኑ መሬት ላይ እየፈጠሩት ያለውን ችግር ልብ ብለን ስናየው ችግር ካልተፈጠረ በሥልጣን ላይ መቆየት የማይችሉ እስከሚመስል የተደረሰበት ሁኔታ ነው። አንድን አመለካካት ብቻ በበላይነት ለመጫን  የተቀረፀው  ሕገ መንግስት እንኳን በሁኔታው ላይ  ከሚሰጠው  አረዳድ ውጭ በአዲስ አበባ ከተማና በኦሮሚያ ክልል መሀከል ያለውን የግንኙነት መስመርና የአሰራር መርህ የጣሰ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከተለያዩ ምንጮች ያሰባሰባቸው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ሕገወጥ ተግባር በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በተከታታይ ተስተውሏል። ለአብነትም፤  አርብ ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቂሊንጦ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ረቡዕ ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ብሔራዊ አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ረቡዕ ግንቦት 17 ቀን 2014 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ገላን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ረቡዕ ሰኔ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በሚያዝያ 23 የአጸደ ህጻናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ሐሙስ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፈለገ ዮርዳኖስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ማክሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጠመንጃ ያዥ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤   ሐሙስ ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ አምባ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  አርብ ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ድል በትግል እና አዲስ ተስፋ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፤  ማክሰኞ ህዳር 27/2015 ዓ.ም ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ሙሉ ብርሃን (አዲስ ብረሃን) ትምህርት ቤት፤  ማክሰኞ ህዳር 27/2015 ዓ.ም ጉለሌ ክ/ከተማ ቀጨኔ ደብረሰላም ትምህርት ቤት፤  ማክሰኞ ህዳር 27/2015 ዓ.ም የካ ክ/ከተማ ከፍተኛ 12 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤  ረቡዕ ህዳር 28/ 2015ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አዲስ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልልን አርማ ለመስቀል እና የክልሉን መዝሙር ለማስዘመር በተደረጉ ሕገወጥ ተግባራት ረብሻዎች፣ ግጭቶች እና የትምህርት ክፍለጊዜ መስተጓጎሎች ከመከሰታቸውም ባለፈ ድርጊቱን የተቃወሙ ተማሪዎች እና መምህራንም ታስረዋል፤ ተደብድበዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች አንድም በከተማው አስተዳደር ወይም በፌደራል መንግስቱ ሥር ያሉ ናቸው። የአዲስ አበባን መስተዳደር ም/ቤትን የመረጠው የአዲስ አበባ ሕዝብ እንጂ የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ አይደለም፤ የፌደራል መንግስቱም የተመረጠው፣ የአዲስ አበባን ሕዝብ ጨምሮ፣ በሁሉም ክልሎች በሚኖረው ሕዝብ በመሆኑ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ወይም በፌደራል መንግስት ሥር የሚገኙ ት/ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎችን የኦሮሚያ ክልል መዝሙር ዘምሩ፣ የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ አውለብልቡ ተብለው የሚታመሱበት ጉዳይ ፍጹም አግባብነት የለውም፡፡ እንደ ኢዜማ አረዳድ ይህ አካሄድ በየትኛውም መመዘኛ ሕጋዊ መሠረት የሌለው ሲሆን ከአዲስ አበባ ት/ት ቢሮም ሆነ ከሚመለከተው የመንግስት አካላት በጽሑፍ የሰፈረ መመሪያና ትዕዛዝ ወደ ት/ቤቶች መተላለፍ አለመተላለፉን ለአዲስ አበባ ሕዝብ በግልጽ እንዲያሳውቁ አበክረን እንጠይቃለን፡፡ የነገው አገር ተረካቢ ትውልድ በዘር ፖለቲካ ትርክት ተፅዕኖ ሥር ወድቆ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር መቆርቆሩን የሀገር ተስፋ መሆኑን ማሳያ ምልክት ነው። ታዳጊ ተማሪዎች የሀገር ትርጉም ገብቷቸው ለኢትዮጵያ ሲሟገቱላት፤ በዕድሜ ታላላቆቻቸው ደግሞ በሀገር ቋሚ ምልክቶች ላይ ሲቀልዱ መመልከት በእጅጉ ያሳፍራል። መጪው ትውልድ ሀገሩን የበለጠ እንዲወድ ማድረግ በሚገባቸው ትምህርት ቤቶች ከፋፋይ ትርክቶችን ማስተጋባት በሀገር ዕጣ ፈንታ ላይ መቀለድ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። ለትምህርት ከቤታቸው የወጡ ተማሪዎችን ለግጭት መጋበዝም ኢ-ሞራላዊነት መሆኑም አፅንዖት ሊሰጠው ይገባል። በዚህ አጋጣሚም ተማሪዎች ለግጭት የሚጋብዟቸውን ድርጊቶች በትዕግስት፣ በሰላማዊ እና ስርዓት ባለው መንገድ በማስተናገድ ራሳቸውን ከጉዳት እንዲጠብቁ መልዕክት ማስተላለፍ እንወዳለን። የፀጥታ አካላትም ተማሪዎችን ከጉዳት መጠበቅ እንጂ የሀይል አካሄድን በፍጹም መጠቀም እንደማይገባቸው እያሳሰብን የስርዓት ሳይሆን የህዝብ ጠባቂ መሆናቸውንም ለአፍታም ቢሆን እንዳይዘነጉት መልዕክታችንን እናስተላልፋለን። ምንም እንኳን መንግስታት በተቀያየሩ ቁጥር በሰንደቅ አላማችን መደብ ላይ በሚያርፈው አርማ ሙሉ ለሙሉ መግባባት ላይ ባይደረስም፤ ሕጋዊ ዕውቅና ያለውን የኢትዮጵያ ሰንደቅዓላማ እና ብሔራዊ መዝሙር ማጉደፍ ግን በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ሰሞኑን በአዲስ አበባ ት/ቤቶች በተነሱ ግጭቶች የተነሳ ጉዳት ለደረሰባቸው ተማሪዎችም ሆኑ ወላጆች የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለእስር የተዳረጉት ተማሪዎች እና መምህራን በአስቸኳይ እንዲፈቱ ይጠይቃል።
نمایش همه...
ፑቲን የሩስያና ዩክሬን ጦርነት ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተናገሩ። ሆኖም ፕሬዝዳንት ፑቲን ለሁለተኛ ጊዜ የወታደር ጥሪ እንደማይደረግ ተናግረዋል። ሞስኮ በዩክሬን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ተከታታይ ማፈግፈግ እያደረገች ነው ተብሏል። ህዳር 29/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
ዩንቨርስቲዎች‼️ በስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲጀመር መወሰኑ ተሠማ። ይህ የተገለጸው የሕ/ተ/ም/ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2014 በጀት ዓመት የኦዲት ባለድርሻ አካላትን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ሰኞ ኅዳር 26/2015 ዓ.ም በገመገመበት ወቅት ነው፡፡ የቋሚ ኮሚቴው የፐብሊክ ፋይናንስ ኦፊሰር አቶ ዘሪሁን አስፋው እንደተናገሩት፥ የመንግሥትን ሀብት በመመዝበር በተለዩ ስምንት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በፍትሕ ሚኒስቴር ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ጭብጦችን የመለየት ሥራ በመከናወን ላይ ነው። የወንጀል ምርመራ እንዲካሄድባቸው የተለዩት ዩኒቨርሲቲዎችም ቡሌ ሆራ፣ አርባ ምንጭ፣ ወልድያ፣ ሀዋሳ፣ መቱ፣ ደብረ ታቦር፣ ዲላ እና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል። (ሪፖርተር) ህዳር 28/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
መልካም ዜና መቀሌ‼️ መቀሌ ትናንት ጀምሮ የመብራት ሃይል አገልግሎት ተጀምሯል። የሽሬው መስመርም ጥገናው ተጠናቋል፣በቅርቡ አገልግሎት ይጀመራል። ህዳር 28/2015 ዓ.ም
نمایش همه...
አፍሪቃዊቷ ሞሮኮ በአስደማሚ የኳስ ጥበብ ስፔንን አሸነፈች! ስፔን እና ሞሮኮ በቀጠር የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ወደ ሩብ ፍጻሜ ለማለፍ ዛሬ ባደረጉት የጥሎ ማለፍ ግጥሚያ መደበኛው 90 ደቂቃም ሆነ ጭማሪው 30 ደቂቃ ያለምንም ግብ ተጠናቆ በፍጹም ቅጣት ምት ሞሮኮ በአውሮጳ ጠንካራውን የስፔን ቡድን 3 ለ0 ድል አድርጋለች። ድንቅ ሞሮኮ! የሞሮኮ ደጋፊዎች ድጋፍ እጅግ ደማቅ እና ብርቱ ነበር። በዚህ ውጤት መሠረትም ሞሮኮ ዘንድሮ አፍሪቃን ወክለው ለዓለም ዋንጫ ከቀረቡ አምስት ሃገራት መካከል ወደ ሩብ ፍጻሜ ያለፈች ብቸኛ ሀገር ሆናለች። ከጥቂት ሰአታት በኋላ ደግሞ ፖርቹጋል ከስዊትዘርላንድ ጋር ይጋጠማሉ። ከፖርቹጋል እና ስዊትዘርላንድ አሸናፊ ጋር በሩብ ፍጻሜው ሞሮኮ የፊታችን ቅዳሜ ትጋጠማለች። ያን ጨዋታም ካለፈች ወደ ግማሽ ፍጻሜው በመሻገር የመጀመሪያዋ አፍሪቃዊት ሀገር የመሆን ክብር ትቀዳጃለች ማለት ነው።  የስፔን አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ በጨዋታው ወቅት የሞሮኮ ተጨዋቾች ሰአት እያባከኑ ነው በሚል ሰአታቸውን ዕያሳዩ ሲበሳጩ ነበር። ድንቅ ሞሮኮ!
نمایش همه...
የመቀሌ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ተገናኘ! Good News በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ከዓመት በላይ ከብሔራዊ የኃይል ቋት ጋር ተቋርጦ የቆየው የመቀሌ ከተማ ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል (ግሪድ) ጋር ተገናኝቷል መገናኘቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር መስመሩ ከብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል ጋር የተገናኘው ከአላማጣ መሆኒ በተዘረጋው የባለ 230 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ከተጠናቀቀ በኋላ ነው ብለዋል። በመስመሩ ፍተሻና የጥገና ሥራ ላይ በሰሜን ምስራቅ ሪጅን አስተባባሪነት ከሁሉም ሪጅን የተውጣጡ የማከፋፈያ ጣቢያና ማስተላለፊያ መስመር የጥገና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።የመስመሩ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መጀመር በትግራይ ክልል ኤሌክትሪክ መልሶ ሥራ ለማስጀመር የተጀመረውን ሥራ የሚያፋጥነው ይሆናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሁመራ እስከ ሽሬ ድረስ የተዘረጋው የባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቋል።ይሁንና ለሽሬ ኃይል የሚሰጠው ከተከዜ እስከ አክሱም በተዘረጋው መስመር ስምንት ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማጋጠሙ ጥገናው ወደ ተከዜ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ መቀጠሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
نمایش همه...
በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ሠራተኞች ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው ተለቀቁ! በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ውስጥ ባለፈው ሳምንት በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች ከፍተኛ የማስለቀቂያ ገንዘብ ከፍለው ተለቀቁ።ከ30 በላይ የሚሆኑት የፋብሪካው ሠራተኞች ምዕራብ ሸዋ ዞን አደአ በርጋ ወረዳ ውስጥ ረቡዕ ኅዳር 21/2015 ዓ.ም. ንጋት ላይ ነበር በታጣቂዎች ታግተው የተወሰዱት።ምንጮች እንዳሉት በሠራተኞቹ ላይ እገታውን የፈጸመው መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀው እና ‘ሸኔ’ ብሎ የሚጠራው፣ በአካባቢው እንደሚንቀሳቀስ የሚነገረው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን አባላት ናቸው። የሲሚንቶ ፋብሪካው ሠራተኞች እገታን ተከትሎ የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ ተጠይቀው እስካሁን ያሉት ነገር የለም።የታጣቂ ቡድኑ አባላት ካገቷቸው በፋብሪካው አውቶብስ ተሳፍረው ሲጓዙ ከነበሩት ሠራተኞች መካከል የሥራ ድርሻቸው ጽዳት እና ጥበቃ የሆኑትን በመለየት ከለቀቁ በኋላ 17 ሰዎችን ይዞ አቆይቶ ነበር።የሠራተኞች እገታ ባጋጠመ ወቅት የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሁለት ኃላፊዎች 17 ያህል ሠራተኞች የት እንዳሉ እንደማያውቁ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ቢቢሲ ከምንጮቹ እንዳጣራው በታጣቂዎቹ ታግተው ለቀናት የቆዩት ሠራተኞች ከ300 ሺህ እስከ 500 ሺህ ብር የማስለቀቂያ ገንዘብ ከፍለው ባለፈው ቅዳሜ እና ዕሁድ ተለቀዋል።ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ነዋሪ እና የፋብሪካው ኃላፊዎች ሠራተኞቹ የሲሚንቶ ግብዓት ተቆፍሮ ወደሚወጣበት ስፍራ በድርጅቱ የሠራተኞች ማመላለሽ አውቶብስ እየተጓዙ ሳለ ነበር በታጣቂ ቡድኑ አባላት የታገቱት። ይህ ሠራተኞቹ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት የታገቱበት ፋብሪካ የሚገኘው ከአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ 90 ኪሎ ሜትር ያህል ርቆ ነው።እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን በስፋት በሚንቀሳቀስበት በዚህ አካባቢ ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት ያለ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደምም በዚህ አካባቢ ሰዎችን አግቶ ገንዘብ መጠየቅ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለ ጉዳይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገረዋል። Via BBC
نمایش همه...
" መንግስት በማንኛውም ሁኔታ የዜጎችን ሁለንተናዊ ደህንነት የመጠበቅ ሃለፊነቱን በአግባቡ ይወጣ " -  የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ም/ቤት የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በምዕራብ ኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞት፣ መፈናቀል እና ሰቆቃ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጾ መንግስት የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ጥሪውን ያቀርቧል።        ምክር ቤቱ በላከል መግለጫ ፤ ሰሞኑን በምዕራብ ኦሮሚያ ምሥራቅ ወለጋ በቀጠለው ግጭት በዜጎች ላይ  ጉዳት መድረሱን  ከአካባቢው በሚወጡ መረጃዎች መረዳቱን ገልጿል። በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ሞት፣ መፈናቀል እና ሰቆቃ በእጅጉ ያሳሰበው መሆኑን የገለፀው ምክር ቤቱ ፤ 1ኛ) መንግስት በማንኛውም ሁኔታ የዜጎችን ሁለንተናዊ ደህንነት የመጠበቅ ሃለፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ፤ 2ኛ) ብዥታን ለማስወገድ እና የተሳሳቱ መረጃዎችን ለማጥራት፤ በጉዳዩ ላይ ወቅታዊ፤ተጨባጭ እና ትክክለኛ መረጃ ለህዝብ እንዲደርስ እንዲያደርግ፤ 3ኛ) በአካባቢው ያለው ሁኔታ ተጣርቶ፤ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፤ 4ኛ) አፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታና ድጋፍ ለተጎጂዎች እንዲቀርብ ፤ እንዲሁም ፤ ለጉዳዩ ፤ ዘላቂ እና ሁለንተናዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ብሎም በየትኛውም የሀገሪቱ ማእዝናት የሚኖሩ ዜጎች ሁለንተናዊ ደህንነታቸው እንዲረጋገጥ የጀመረውን የሰላም ግንባታ ስራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል ያለውን ቁርጠኝነትና ዝግጁነት አረጋግጧል
نمایش همه...