cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

EBS TV

worldwide news🌍

نمایش بیشتر
Advertising posts
2 784مشترکین
-124 ساعت
-97 روز
-2130 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#አስቸኳይ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ ” - የታጋች እናት በሊቢያ ደላሎች የታገተው የሀዋሳው ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ እንገድለዋለን ” በማለት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደሰጡ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። የታጋቹ እናት ወ/ሮ ገነት ጥላሁን ይግለጡ በሰጡት ቃል፣ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ እባካችሁ ልጄን ታደጉኝ ” ሲሉ እያለቀሱ ጠይቀዋል። “ በሄደ በ17 ቀኑ ከሊቢያ ስልክ በጓደኛው አማካኝነት ተደወለልኝ። ስልኩን ሳነሳ ‘ሊቢያ ላይ ተይዟልና 950 ሺሕ ብር ተጠይቋል’ ብሎ ጓደኛው ነገረኝ ” ያሉት የታጋቹ እናት፣ “ ከዚያ ወዲያውኑ ደግሞ ሊቢያዎቹ እየገረፉት ምስል ላኩልኝ። አካውንትም ላኩልኝ ‘ገንዘብ ላኪ’ ብለው ” ሲሉ አስረድተዋል። አክለውም፣ “ እንደገና ለ3ኛ ጊዜ መደኃኒት ሰጥተውት እንደ እብድ እያደረገው ቪዲዮ ላኩልኝ። እንደገና ለ4ኛ ጊዜ ደግሞ ወደ ታች #ዘቅዝቀው #እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ከዚያ ‘ተሽጧል 1.7 ሚሊዮን ብር አምጭ’ ብለው ደወሉ። ቪዲዮ እያሳዩም ‘1.7 ሚሊዮን ብር ታመጫለሽ አታመጭም?’ አሉኝ ” ብለዋል። በዚህም “ እኔ የለኝም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉልበቴ ስለሆነ ለምኘ፣ እርዳታ አሰባስቤም እከፍላለሁ አልኳቸው። ለ5ኛ ጊዜ እንደገና #ፀጉሩን ላጭተው የሆነ #ውሻ አስመስለው ምስል ላኩልኝ። ከዚያ በኋላ በቃ ‘የጨመረሻ ቀን ብለው’ ደወሉ። ልጄም በጣም #እያለቀሰ ‘አስለቅቂኝ’ አለኝ። እነርሱም ‘ነገ #አርብ 1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን በፊት ለፊትሽ ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን ” አሉኝ ሲሉ አንብተዋል። አጋቾቹ ‘ብር ላኪ’ ሲሏቸው ባለማወቅ የመፍትሄ መንገድ መስሏቸው የላኩትን አካውንት በሕግ እንዳሳገዱ፣ በዚህም አጋቾቹ የወጣቱን ስቃይ እንዳበዙት፣ ከታገተ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው፣ ገንዘቡ እስኪሟላ ተጨማሪ ቀን መጠየቃቸውን የገለጹት እናት፤ “ ፌደራልም ሊቢያና ሱዳን ድንበር ላይ የሊቢያ መግቢያ ላይ ነው የታገተው ብለው ነገሩኝ ” ብለዋል። ወ/ሮ ገነት፣ ምርመራውን ይዞታል የተባሉ የፌደራል ፓሊስ አባል የአጋቹን አካል ቢደርሱበትም በሕግ በኩልም መፍትሄ እንዳላገኙ አስረድተዋል። ያላቸው አሁናዊ የምርመራ ሂደትን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው መርማሪው የፌደራል ፓሊስ ጉዳዩን በጽሞና ከሰሙ በኋላ “ መልስ መሰጠት የሚችለው እንደ ተቋም ስለሆነ በተቋሙ በኩል ኦፊሻል ደብዳቤ ይዘው በአካል መጥተው አመራሮችን ማነጋገር ይችላሉ ” ከማለት ውጪ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። ሆኖም ስለጉዳዩ በደብዳቤ ጠይቀን ምላሹን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል። እናት አጋቾቹ ከጠየቁት ውስጥ እስካሁን የተሰበሰበው ወደ 350 ሺሕ ብር ብቻ እንደሆነ አስረድተው “ ሀዘን ላይ ነኝ። በቅርቡ ልጄ ሞቶብኛል። አሁን ደግሞ ይሄ ደረሰልኝ ብዬ፣ አሁን እንደዚህ ሆነብኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ረድቶኝ ልጄን እንዲያስለቅቅልኝ በትህትና እጠይቃለሁ ” ሲሉ ተማጽነዋል። ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ የወ/ሮ ገነት ጥላሁን ይግለጡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000523577402 ሲሆን ሌሎችም የሂሳብ ቁጥሮች ከላይ ተያይዟል። በስልክ ልታገኟቸው የምትፈልጉ 0916848184፣ 0911720985 ደውሉላቸው። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" 11 ንፁሃን ነው የተገደሉት " - የዶዶላ ከተማ አስተዳደር በዶዶላ ባለፈው ሰኞ ዕለት ምሽት 3 ሰዓት ገደማ በተፈፀመ ጥቃት 11 ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን የከተማው አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል አረጋግጧል። የከተማው አስተዳደር ለሬድው ጣቢያው " በዕለቱ በድንገት በተፈፀመ ጥቃት 11 ሰዎች ሞተዋል። በጥይት ተመተው የተጎዱም አሉ። ከጥቃቱ ጀርባ በገደብ አሳሳ ፣ አዳባ፣ በክልል ደረጃም ታጥቆ የሚንቀሳቀሰው የሸኔ ቡድን አለ የሚል መላምት አለ ግን ምርመራ እየተካሄደ ነው " ብሏል። ይህ ሁሉ ሰው #ሲገደል የፀጥታ ኃይሉ ለምን በስፍራው አልደረሰም ? ለሚለው ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ ፤ " ጥቃቱ የተፈፀመው በደነባ ክ/ከተማ ደብረ ቅዱሳን ጻድቁ አቡነ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አቅራቢያ ነው። ይህ ሆን ብሎ የሃይማኖት አባትን እና ልጆቻቸውን የገደለው እርስ በእርስ ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ ነው ብለን እንገምታለን። በጣም ታስቦበት የተፈፀመ ግድያ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ንፁሃኑ ግድያው የተፈፀመባቸው በቤታቸው እያሉ #በጥይት ተተኩሶባቸው እንደሆነና መንግሥት ግድያውን እንደሚያወግዝ የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል። ለመሆኑ የጥቃቱ ፈፃሚዎች ተይዘዋል ? ለሚለው ጥያቄ ፥ የዶዶላ ከተማ አስተዳደር " ክትትል እየተደረገ ነው " የሚል ምላሽ ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥቷል። ይህ የአስተዳደሩ ምላሽም አንድም የተያዘ ሰው እንደሌለ የሚጠቁም ነው። በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ 2 የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪና የዓይን እማኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው ይታወሳል። ነዋሪው ፤ አንድ መሪጌታ ከእነባለቤቱ እና ከሁለቱ ልጆቹ ጋ፣ አንድ ዲያቆን ከእነባለቤቱና እህቱ ጋር መገደላቸውን ፤ የመርጌታው ሁለቱ ልጆቹ ሲገደሉ የ1 ዓመት ከ5 ወር ህፃን ብቻ መቅረቱን ገልጸው ነበር። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ዛሬ ከቀኑ 09:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉ መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል። በሲስተም ላይ በገጠመ ችግር ኃይል መቋረጡን ያስታወቀው ተቋሙ  ለጊዜው የችግሩን ምክንያት ለማወቅ ጥረት እየተደረገ ነው ብሏል። የተቋረጠውን ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ የተጀመረ መሆኑን የገለጸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፥ ችግሩን በመቅረፍ ዳግም ሲስተሙ ተመልሶ እስኪገናኝ ድረስ በትዕግስት ጠብቁ ሲል አስታውቋል። #NB: ተቋሙ ይህንን መረጃ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ከደቂቃዎች በፊት ያወጣው ሲሆን አሁን ላይ በአንዳንድ አከባቢዎች የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል መመለሱን ማረጋገጥ ችለናል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#እናት እናት ፓርቲ ፥ " መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶችንና ምእመናንን አሰቃቂ ግድያ በማስቆም ከደሙ ነጻ መሆኑን በአስቸኳይ ሊያረጋግጥ ይገባል " ብሏል። ይህን ያለው ከሰሞነኛው የዶዶላው ግድያ በኃላ ባወጣው መግለጫ ነው። " የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን ባለፋት ሶስት አስርት ዓመታት እጅግ በጣም አሰቃቂ ጥቃት ደርሶባቸዋል " ያለው ፓርቲው " በተለይም ባለፉት 5 ዓመታት በቤተክርስቲያኗ እና ምእመናኗ ላይ እየተፈጸመ የሚገኘው ግፍ እና አሰቃቂ ግድያዎች ክፉኛ ተጠናክረው ቀጥለዋል " ሲል ገልጿል። ፓርቲው ፥ በዶዶላ ከተማ ባለፈው ሰኞ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ  ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ መርጌታ፣ 2 ልጆቻቸው እና ባለቤታቸውን ጨምሮ ከ2 ወራት በፊት ሥርዓተ ጋብቻቸውን የፈጸሙ ሙሽሮች (አንድ ዲያቆን ከባለቤቱ እና ታላቅ እህቱ ጋር) በአጠቃላይ 7 ንጹሐን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ካህናትና ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ በታጣቂዎች መገደላቸውን አመልክቷል። በተጨማሪም በቀን ሥራ ይተዳደሩ የነበሩ 4 ንጹሐን ዜጎችም በታጣቂ ኃይሎች መገደላቸውን ገልጿል። ሌሎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 7 ሰዎችም በዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ጠቁሟል። ፓርቲው ፤ " ከዚህ ማብቂያ ካጣው አሰቃቂ ግድያ ጋር በተያያዘ መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አባቶችና ምእመናንን አሰቃቂ ግድያ በማስቆምና መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ከእነዚህ ንጹሐን ደም  ነጻ መሆኑን በአስቸኳይ ሊያረጋግጥ ይገባል " ብሏል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ ከቀኑ 09:46 ጀምሮ ከባህርዳርና አካባቢው በስተቀር በመላው ኢትዮጵያ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል መልሶ መገናኘት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል። አብዛኛው የአዲስ አበባ ክፍል እና የተቀሩት የሀገሪቱ ክፍሎች መልሰው ኃይል ማግኘት እንደቻሉ ተገልጿል። የተቀሩትን አካባቢዎች መልሶ ለማገናኘት ጥረቱ መቀጠሉ ተነግሯል። @tikvahwthiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣ እንመክራለን " - የአማራ ክልላዊ መንግሥት የአማራ ክልል መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ " ሲል #አስጠነቀቀ። የክልሉ መንግሥት ፥ በአሁን ሰዓት የወልቃይት  ጠገዴ ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ህዝብ ለረጅም ዓመታት በ " ህወሓት " በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረው የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት የተመለሰበት እንደሆነ ጠቁሟል። ህዝቡም እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል ነው ብሏል። " የፕሪቶሪያው የሠላም #ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም #በትምህርቱም_መስክ ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል " ሲል ገልጿል። ክልሉ ፤ እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማር መብታቸው እንዲከበር ግዴታውን መወጣቱን ገልጿል። የትምህርት ስርዓቱን ሰበብ በማድረግ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ እንዳወጣ ጠቁሟል። ይህም " ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም " ሲል ተችቷል። የአማራ ክልል መንግሥት ፥ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሀገራችንን እና ሁለቱን ክልሎች ወደ #ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር  እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላምና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን " ብሏል። ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.me/tikvahethiopia/86444 @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአማራ ክልል ይፋዊ ምላሽ ሰጠ። * " የዛቻና የጠብ አጫሪነት የሆነውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መግለጫ ተመልክተነዋል " - የአማራ ክልል የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ሀሙስ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል " ብሏል። የጊዚያዊ አስተዳደሩ የአማራ ክልል የትምህርት ስርዓትን በማጣቀስ " የተሳሳተ ካርታ ተሰርቷል " ሲል ያወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳችና  የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ ነው ሲል ገልጿል። #በትናንትናው እለት ደግሞ ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደልና በማሰቃየት ላይ ይገኛል ሲል የአማራ ክልል ከሷል። (ሙሉው መግለጫ ከላይ ተያይዟል) @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት አዲስ አበባ ከተማ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፍጹም መቆም የሚከለክሉ የትራፊክ ምልክቶች ተተክለዋል። በስራ መግቢያ እና ከስራ መውጪያ ሰዓትም በአካባቢው ላይ በመንገድ መዘጋጋት ህብረተሰቡ እንዳይጉላላ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል። በዚሁ መሰረት ፤ " ፍጹም መቆም የሚከለክሉ " ምልክት የተተከለባቸው ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አድዋ መታሰቢያ የሚወስድ ዋና መንገድ እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ አድዋ ሙዚዬም ዙሪያ እና ማዘጋጃ ዙሪያ ከዛሬ መጋቢት 19/2016 ጀምሮ ጥብቅ ቁጥጥር ይጀመራል ተብሏል። በአካባቢው በግዜያዊነት ለተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት የሚውል የአድዋ ሙዚዬም "ሰርፌስ ፓርኪንግ" አገልግሎት መስጠት ስለጀመረ አሽከርካሪዎች እንደ አማራጭ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪ ፦ - ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ - ከአራት ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ፣ አማራጭ መንገድ ከአራት ኪሎ-አባድር  - ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ - ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ራስ መኮንን ድልድይ - ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ - ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ - ከባሻወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ - ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዘበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል። በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ ለመቅረፍ ፤ አማራጭ #ማስተንፈሻ የሚሆን መንገድ በተለምዶ ከቀይባሕር ኮንደሚንየም ወደ ደጎል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ዛሬ ከሰዓት ለተሽከርካሪዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል። መረጃው የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ነው። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" እየመጣችሁ ላላስፈላጊ እንግልት እንዳትዳረጉ " - የቤቶች ልማት እና አስተዳደር የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ለጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግበው እየጠበቁ ያሉ ነዋሪዎች ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ #በቲክቶክ እየተለቀቀ ባለ የተሳሳተ መረጃ ምክንያት ወደ ቢሮ መጥተው እንዳይንገላቱ ጥሪ አቀረበ። ቢሮው ፥ " ' የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝግባችሁ እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ብቁ መሆን አለመሆናችሁን ባምቢስ በሚገኘው የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ 5ኛ ፎቅ መታችሁ እንድታዩ ' በሚል የተለቀቀው መረጃ የተሳሳተ ነው " ብሏል። ተመዝግበው እየተጠባበቁ የምትገኙ ነዋሪዎችም ላተፈለገ እንግልት እንዳይዳረጉ ጥሪ አቅርቧል። " ተመዝጋቢዎችም ሆነ ሌሎች ነዋሪዎች የተቋሙ ባልሆኑ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ሆነ ግለሰቦች በሚያናፍሱት ወሬ እንዳትታለሉ " ብሏል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
Repost from TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ እንዲታገድ ለካቢኔው ጥያቄ አቅርቢያለሁ " - የኢራቅ ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር የኢራቅ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ሂያም አል-ያስሪ ' ቲክቶክ ' የተሰኘው የአጫጭር ቪድዮ ማጋሪያ መተግበሪያ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ካቢኔ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናገሩ። " የኢራቅን የማህበራዊ ህይወት ትስስር እየሸረሸረው ነው " ያሉት ሚኒስትሯ የእግድ ጥያቄውን በቅርቡ ካቢኔው እንደሚያየውና እንደሚነጋገርበት ገልጸዋል። " መተግበሪያው ማህበረሰቡን የሚጠቅም የረባ ትምህርታዊ ጠቀሜታ የለውም ሙሉ በሙሉ መዝናኛ ላይ ያተኮረ ከምንም በላይ የኢራቅን ህዝብ ባህል፣ እሴት አጠቃላይ ትስስርን የሚሸረሽሩ ይዘቶች የሚሰራጩበት ነው " ብለዋል። የኢራቅ ፓርላማ እንዲህ ያለው መተግበሪያ እንዲታገድ ድጋፍና ትብብር ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
وارد شوید و به اطلاعات مفصل دسترسی پیدا کنید

ما این گنجینه ها را پس از تأیید هویت به شما نشان خواهیم داد. ما وعده می‌دهیم که سریع است!