cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA

Addis Ababa, Ethiopia https://twitter.com/tikvahethiopia?s=09 @tikvahethedu @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استزبان مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
Advertising posts
906مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

" በፀጥታ አጠባበቁ ላይ ችግሮች እንደነበሩ መካድ አይቻልም " - ፖሊስ የጃፓን ፖሊስ ባለፈው ዓርብ በደቡባዊቷ ናራ ከተማ የቀድሞው የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ግድያ በተፈጸመበት ወቅት የፀጥታ ጥበቃ ክፍተቶች እንደነበሩ ገልጿጻ። የናራ ፖሊስ አዛዥ ቶሞአኪ ኦኒዙካ ፤ " በፀጥታ አጠባበቁ ላይ ችግሮች እንደነበሩ መካድ አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል። ተፈጥረዋል ያሏቸውን ክፍተቶች የት ላይ እንደሆኑ ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል። በሺንዞ አቤ ላይ ግድያውን በመፈጸም የተጠረጠረው የ41 ዓመቱ ቴሱያ ያማጋሚ አንድ በስም ያልተጠቀሰ ተቋም ላይ ቂም ይዞ ነበር ሲል ፖሊስ ይፋ አድርጓል። የጃፓን የመገናኛ ብዙኃን ፤ ለምርመራው ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገቡት ከሆነ ተጠርጣሪው ወላጅ እናቱን የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ከከተተ አንድ የሃይማኖት ቡድን ጋር ሺንዞ አቤ ግንኙነት አላቸው ብሎ ያምናል። ፖሊስ በተጠርጣሪውና በክስተቱ ላይ ጥልቅ ምርመራ እያካሄደ ይገኛል። መረጃው የቢቢሲ ነው። @tikvahethiopia
نمایش همه...
#Update ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ከእስር ተፈቷል። ዛሬ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ማዘዙ ይታወሳል። ይኸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተከብሮ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ከእስር መፈታቱን ጠበቃው ታደለ ገብረመድህን አረጋግጠዋል፡፡ @tikvahethiopia
نمایش همه...
#Update ኮድ 2 ሠሌዳ ! በአዲስ አበባ ከሚንቀሳቀሱ አ.አ ሠሌዳ መካከል የኮድ 2 ሠሌዳ አቅርቦት ከትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር በውክልና የወሰደው የፐፕሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በግብዓት እጥረት ምክንያት ለወራት አቅርቦቱ መቋረጡ ይታወቃል፡፡ የገጠመውን የአቅርቦት ችግር በመቅረፍ የምርት ስራው ስለተጀመረ ኮድ 2 አዲስ ሠሌዳ ፈላጊዎች ከ14/10/2014 ዓ/ም ጀምሮ ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት በ11 ቅ/ጽ ቤቶች በመኖሪያ አድራሻቸው አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ መሆኑንበአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በዛሬው ዕለት አሳውቋል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
በምዕራብ ጎጃም ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰወች ህይወት አለፈ። ትላንት በቀን 12/10/2014 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 AA 92926 የሆነ ላንድ ክሮዘር መኪና ከፍኖተ ሰላም ወደ ደብረማርቆስ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ እያለ ከፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር ከከተማው ወጣ ብሎ በተለምዶ " ገወቻው " አካባቢ በእግሩ ሲጓዝ የነበረን ሰው ገጭቶ የተገጨው ሰው ህይወቱ ወዲያውኑ አልፏል። ግጭቱን ያደረሰው ተሽከርካሪው መብራቱን በማጥፋት በፍጥነት ወደ ደብረ ማርቆስ አቅጣጫ ሲሄድ በጃቢ ጠህናን ወረዳ አርሴማ እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ ወጣ ብሎ ከሚገኝ አካባቢ በመገልበጡ መኪና ውስጥ የነበረ 1 ግለሰብ ህይወቱ ወዲያው አልፏል። 2 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ተሽከርካሪው በከፍተኛ ፍጥነት ሲጓዝ እንደነበር ተገልጿል። መረጃው ከምዕራብ ጎጃም ፖሊስ የተገኘ ነው። @tikvahethiopia
نمایش همه...
" ቤቲንግ እንዲታገድ እየሰራሁ ነው " - የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የስፖርት ውርርድ / ቤቲንግ እንዲታገድ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ከታዲጊዎች እና ወጣቶች ስብዕና ግንባታ እንዲሁም በተለያየ መንገድ ከሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውሶች አንጻር ዘርፉ ሊታገድ ይገባል በሚል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ ገልጿል። በተለያየ ጊዜ የተዘጋጁ የዳሰሳ ጥናቶች የስፖርት ውርርድ ለወጣቱና ለታዳጊው ዘርፈ ብዙ አደጋ የደቀነ መሆኑን ያመላከቱ ናቸው የተባለ ሲሆን ዘርፉ በተጨባጭ ችግር የሚፈጥር መሆኑን ተገምግሟል። ሚኒስቴሩ የስፖርት ውርርድ ' ቁማር ነው ' ብሎ እንቅስቃሴ መጀመሩን እና ቁማር የሚባለው ነገር ደግሞ በራሱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የሚያስከትል ጉዳይ መሆኑን ገልጿል። ቁማር ታዳጊዎችን ይሁን አዋቂ ሰዎችን ወዳልተፈለገ መንገድ ሊወስድ የሚችል ማህበራዊ ቀውስ እንደሆነና ማንኛውም ሰው ሰርቶ የመለወጥ እሳቤውን የሚያቀጭጭ፣ ቤተሰብን ጭምር ወደ መበተን ሊያደርስ የሚችል ጉዳይ መሆኑን አስገንዝቧል። ወጣቶች እና ታዲጊዎች ለቤቲንግ ውርርድ ሲሉ ያላቸውን ነገር በሙሉ እስከማውጣት እንደሚደርሱ የተጠቀሰ ሲሆን ወጣቶች ስራን ከመስራት ይልቅ በአቋራጭ መክበር እንዲያስቡ በማድረግ ምርት እና ምርታማነትን የሚቀንስ ተግባር ነው ብሏል። ሚኒስቴሩ ቤቲንግ እንዲታገድ ፍቃድ ለሚሰጡት የንግድ ሚኒስቴር እና የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ተቋማት አስፈላጊውን የግንዛቤ እና የማሳወቅ ስራ መሰራቱን ገልጾ እነዚህ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አለማድረጋቸው ለውሳኔው መዘግየት ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ገልጿል። #ኢብኮ @tikvahethiopia
نمایش همه...
#ሐማቅ_ትሬዲንግ የኤሌትሪክ ሃይል Mini Stablizer ፦ የኤሌትሪክ ሃይል መጨመርና መቀነስን ለመቆጣጠር ፤የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ለረጅም ጊዜ ለመጠቀም Power Factor መቆጣጠሪያ(Voltage Protector) ይጠቀሙ። ለድርጅቶችና ንግድ ተቋማት አስፈላጊ ለፍሪጅ፣ ቲቪ፣ Adaptorና ለተለያዩ ዕቃዎች የሚያገለግል ዋጋ 950 ብር Made in Japan ከሁለት አመት ዋስትና ጋር ☎️ 0912917632 ያሉበት ድረስ በነፃ እናደርሳለን አድራሻ አቢሲኒያ ፕላዛ
نمایش همه...
" ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን " - ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያው መሪ ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ጦርነት እጁን የሚያስገባ ማንኛውም አገር ላይ መብረቃዊ ጥቃት እንደሚፈጸምበት አስጠነቀቁ፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ አገራቸው ሩሲያ አቅምም ብቃትም አላት ብለዋል፡፡ ‹‹ማንም አገር አለኝ የማይለው የጦር መሣሪያ አለን፡፡…አስፈላጊ ከሆነ እንጠቀመዋለን›› ሲሉ ብዙዎችን ያሳሰበ ንግግር አድርገዋል፡፡ አንዳንድ ተንታኞች ፑቲን በዚህ ንግግራቸው ለመጠቆም የሞከሩት ባለስቲክ ሚሳኤልና የኑክሊየር መሣሪያን ነው በማለት ግምት ወስደዋል፡፡ ፑቲን ከዚህ በፊት በለጦር ሹማምንቶቻቸው የኑክሊየር መሣሪያ በተጠንቀቅ እንዲዘጋጅ ትዕዛዝ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ የፑቲን መራር ንግግር የተሰማው ምዕራባዊያን ለዩክሬን እጅግ ውስብስብና ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመስጠት በተጠመዱበት ወቅት ነው። በተለይም ባለፉት ቀናት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ኦስቲን በኪየቭ ጉብኝት አድርገው ነበር። በዚህ ጉብኝታቸው ለዩክሬን ወደ 700 ሚሊዮን ዶላር የተጠጋ እርዳታን ይፋ አድርገዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ የምዕራብ አገራት በጀርመን ተሰብስበው ለዩክሬን የሚደረገውን የጦር መሣሪያ እርዳታ እንዴት ከዚህም በላቀ መልኩ ማሳደግ ይቻላል በሚል ተወያይተው ነበር፡፡ በጦርነት ጣልቃ ያለመግባት ጥብቅ ፖሊሲን ትከተል የነበረችው ጀርመን ሳይቀር ያልተጠበቀ የፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ለዩክሬን 50 የአየር መቃወሚያ ታንኮችን እሰጣለሁ ብላለች፡፡ መረጃው የቢቢሲ ነው። @tikvahethiopia
نمایش همه...
#AddisAbaba በመዲናችን አዲስ አበባ የ10 ዓመት ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታውቋል። የሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት በህፃኑ ስም ገንዘብ ሲያሰባስቡ ተገኝተው በቁጥጥር ስር የዋሉት 11 ግለሰቦች (9 ሴቶች እና 2 ወንዶች) ሲሆኑ አሁን ላይ ምርመራ እየተሰራ ነው ተብሏል። ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት በ3 ክፍለ/ከተሞች ስም የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነድ እንዲሁም የሃኪም ማስረጃዎችን ከሚለምኑባቸው 2 ሚኒባስ መኪኖች (ታርጋ ቁጥር 58456 እና 79169 ኮድ 3 ኦሮሚያ) ጋር በህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማና በፀጥታ ኃይሎች ክትትል ነው ተብሏል። አሁን ላይ በከተማዋ የተለያዩ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማዘጋጀትና ያልታመመ ሰውን ታሟል በማለት የሚመለከተው የህክምና ተቋም ማረጋገጫ ሳይሠጥ በህገ-ወጥ መንገድ የሚካሄዱ ልመናዎች በዝተወልና ህብረተሰቡ ከአጭበርባሪ ወንጀለኞች ራሱንና ንብረቱን ይጠብቅ ተብሏል። ከዙህ ቀደም (የካቲት ወር ላይ) በጭሮ ከተማ የ ' አጥንት ካንሰር ታማሚ ' በመምሰል በተሽከርካሪ ላይ እየተዘዋወረች ስትለምን የነበረችውን ወጣት በፖሊስ መያዟ ይታወሳል (ለማስታወስ ይኸው ሊንኩ t.me/tikvahethiopia/67710 ) እንዲህ ያሉ ድርጊቶች በእርግጥም ታመው እና አቅም አንሷቸው በህምመም ለሚሰቃዩ ወገኖቻን በሚደረገው ድጋፍ ላይ ተፅእኖ ያሳድራል፤ ሰዎች ድጋፋቸውን ለማድረግ እንዲጠራጠሩም ይሆናል፤ በዚህም ምክንያት በእኛ የ10 ብር እና 20 ብር ድጋፍ ተሰባብሶ ሊተርፉ የሚችሉ ወገኖቻችን እናጣቸዋለን። ምን ቢደረግ የተሻለ ነው ? ሃሳባችሁን አካፍሉ ፤ ተነጋገሩት👇 @tikvahethiopiaBOT
نمایش همه...
#Update #Tigray, #Mekelle 📍 ትላንትና በጉዞ ላይ እንደነበሩ የተነገረላቸው አስፈላጊ የሆኑ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶችን የጫኑት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ተሸከርካሪዎች የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ደርሰዋል። ሁሉም (50ውም) ተሸከርካሪዎች በሰላም ነው መቐለ የደረሱት። ምን ይዘዋል ? ➡️ 1,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ እና ጥራጥሬ ፤ ➡️ 700 ሜትሪክ ቶን የጤና ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና WASH (ውሃ፣ የአካባቢ እና የግል ንፅህና መጠበቂያ እቃዎች) + 115,000 ሊትር ነዳጅ ይዘው ነው መቐለ የደረሱት። የዓለም ምግብ ፕሮግራም መቐለ የደረሱትን እነዚህን ምግብ / አልሚ ምግቦች በዚህ ሳምንት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ማከፋፈል እንደሚጀምር አሳውቋል። በዚህም ድርጅቱ 43,000 አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች እንዲሁም ተጋላጭ ለሆኑ 24,000 እናቶች እና ህጻናት በተመጣጠነ ምግብ ለመድረስ ማቀዱን ገልጿል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
#PressRelease የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ጠቅላይ ምክር ቤት መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. 48ተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። በዚህ ስብሰባ ማጠናቀቂያ ም/ቤቱ ባለአስር ነጥብ የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
وارد شوید و به اطلاعات مفصل دسترسی پیدا کنید

ما این گنجینه ها را پس از تأیید هویت به شما نشان خواهیم داد. ما وعده می‌دهیم که سریع است!