cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የቡራዩ ደ/ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ሰላም ሰንበት ት/ቤት

ይህ ገፅ የቡራዩ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ካቴድራል ፍኖተ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት መልዕክቶችን ዘመኑ በሚፈቅደው መንገድ እንዲተላለፍበት በህዝብ ግንኙነት ክፍል የሚመራ ይፈዋዊ ገጽ ነው። 📞+251944247165 ሀሳብ አስተያየት ካሎት @finoteselam27 inbox አድራሻችን ነው።

نمایش بیشتر
Advertising posts
1 188مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+37 روز
+2830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#ዓውደ_መጽሐፍት ------------------------------ #የመጽሐፉ ርዕስ -#ሕማማት #ደራሲ - #ዲን_ሄኖክ_ኃይሌ #የገጽ_ብዛት_528 ከመጽሐፉ የተወሰደ ➳➺ #ለንስኃ_የሚቀሰቅስ_ዶሮ ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሓ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር ... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሓ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሓ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን? የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?     በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሓ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው? ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሓ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡      "ሕማማት" ከተሰኘው ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ መጽሐፍ 2ኛው ምዕራፍ ላይ  የተወሰደ! ይህንን ድንቅ መጽሐፍ በተለይ ከፊታችን በሚመጣው የሰሙነ ሕማማት ወቅት መነበብ ያለበት ድንቅ መጽሐፍ ነው። ከወዲሁ እንድታነቡት እየጋበዝን መጽሐፈ በሰንበት ትምህርት ቤቱ የንዋያተ ቅዱሳት መሸጫ ሱቅ ያገኙታል። መልካም ንባብ! ---------------------- ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
#የእለቱ_መልእክት ------------------------- #ከኒቆዲሞስ_ምን_እንማር #ትግሃ_ሌሊት እንደ ሌሊት ለመንፈሳዊ ህሊና ለተመስጦ የሚመች ጊዜ የለም ፡፡ ቀን ለስጋ ሲራወጥ የነበረ አካልና መንፈስ ሌሊቱን ለነፍስ በምገዛት ስጋውን መጎሰም አለበት፡፡ ለዚህም ነው ቅድስት ቤተክርስቲያን ቀኑን በቅዳሴ ሌሊቱን ደግሞ በማኅሌት በሰዓታት በኪዳን እግዚአብሔርን ስታምሰግን የምታድረው፡፡ ቅዱስ ማር ይስሐቅ ሌሊትስ ጌታን ለማመስገን የተፈጠረ ድንቅ ጊዜ ነው ያለው፡፡ ጌታችንም ሐዋርያቱን ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ብሏቸዋል ማቴ 26፡፡ አሁንም ቤተክርስቲያን እንደ ኒቆዲሞስ በሌሊት ገስግሶ ለኪዳን ለማኅሌት ለጸሎት የሚመጣን ምዕመን ትፈልጋለች። ሰናይ ቀንን ተመኘን ----------------------------- ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
🥰 6🙏 3
በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የሸገር ከተማ እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መመሪያ ሰጪነት በዛሬው እለት በቡራዩ ክፍለ ከተማ ሥልጠና ተሰጥቷል። ሥልጠናው የተሰጠው ለቡራዩ፣ መልካ ኖኖ እና ገፈርሳ ጉጄ ክፍላ ከተሞች ቤተ ክህነት፣ አድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ማኅበራት እና ሰንበት ት/ቤት አመራሮች ሲሆን ሥልጠናውን የሰጡት ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በመጡ መምህርና የሸገር ሀገረ ስብከት አመራሮች እንደሆኑ ታውቆአል። የሥልጠናው ትኩረትም ትምህርተ ኖሎት፣ ሕግን ያማከለ አስተዳደር፣ የገንዘብና የንብረት አስተዳደር እና ስብከተ ወንጌል ናቸው። ዘገባው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ነው። | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም
نمایش همه...
#ኪነ_ጥበብ -ግጥም ---------------------------- #መምህር_ሆይ! መሆንህን አውቆ እውነተኛ ገሰገሰ ወዳንተ በሌሊት ሳይተኛ ቅዱስ ቃልህንም ሲሰማ ፈወሰው የታወረ ኅሊናውን አብርቶ አቀናው ጥያቄውን እንዲያቀርብ አበረታታኸው ስለ ዳግም ውልደትም አስተማርከው ‹‹እውነት እውነት እልሀለሁ›› ስትለው ዳግመኛ ያልተወለደ ሰው… የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማየት አይቻለው›› ምሥጢሩ ባይገባው ‹‹ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፡፡ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው›› ብለህ አስረዳኸው፡፡ ‹‹ይህ ሊሆን እንዴት ይቻላል?›› ብሎ ኒቆዲሞስ ቢጠይቅህ ‹‹አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ፤ ነገር ግን እንዴት ይህን አታውቅም?.... ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፤… የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡›› ብለህ አስተማርከው፡፡ አሁንስ ገባው፤ እውነቱንም አውቆ ጌታውን ዘመናት አልፈው ሲደርስ ጠብቆ ተራውን ቢኖርም ተብሎ መምህር፣ በሌላ ሕግ ተደብቆ ያለ አንተ ሲኖር ከአይሁድ ተደባልቆ አሁን ግን ሰጠኸው የእውነት ሕይወት በመስቀል ላይ ገልጸህ ፍጹም አፍቅሮት ክብርንም አገኘ በአንተ ስቅለት ገንዞ እንዲቀብርህ በዓርብ ዕለት! |ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
👍 4
#የእለቱ_መልእክት #ጎደሎን_ማወቅ መምህርም ምሁርም ሆኖ ቁጭ ብሎ መማር ምን ረብ አለው? ይባል ይሆናል፡፡ ኒቆዲሞስ ምሁረ ኦሪት እንጅ ምሁረ ሐዲስ አይደለም ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ዘስጋ እንጅ መምህረ እስራኤል ዘነፍስ አይደለም፡ ክርስትና አለቃና ባሪያን አንድ እንደምታደርግ አያውቅምና የጎደለውን ፍለጋ መጣ ገላ 3÷26፡፡ ያለውን ሳይሆን ያጣውን የሞላለትን ሳይሆን የጎደለውን ፍለጋ መጣ፡፡ዕውቀት ብቻውን ምሉእ አያደርግም፡፡ አለቅነትም ቢሆን ገደብ አለው፡፡የሕይወቱን ክፍተት ሊሞላ የሚችል አንድ ክርስቶስ ብቻ ነውና ጎደሎነቱን አምኖ መጣ፡፡ የሚጎድለኝ ምንድን ነው? ብሎ እንደጠየቀው እንደዚያ ሰው ጎደሎን ማመን ምንኛ ታላቅ ነገር ነው ማቴ 18÷ 21፡፡ በአብዛኞቻችን የሚታየውና ክርስትናችንን አገልግሎታችንን ቤተክርስትያናችንን እየተፈታተነ ያለ ችግር ጎደሎዎቻችንን አለማወቅና ምሉእ ነኝ ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ምንም እንዳልሆኑ አውቆ ራስን ለክርስቶስ፣ ራስን ለመርዐተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አሳልፎ መስጠት ምንኛ መታደል ነው! ሰናይ ቀንን ተመኘን ---------------------------------- ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
👍 8🥰 2🙏 2
የመረጃ ሰዓት ------- "ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ ልዩ ታሪካዊ ዐውደ ርእይ" በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ ጉብኝትና ቡራኬ ተጠናቀቀ። በሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ድርጅት አዘጋጅነት የተሰናደው "ንጹሕ ምንጭ ኢትዮጵያ ልዩ ታሪካዊ ዐውደ ርእይ" በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ ጉብኝትና ቡራኬ ተጠናቀቀ። ዐውደ ርእዩ ከአንድ ሳምንት በላይ በይታ ላይ የቆየ ሲሆን ትናንት ሚያዚያ ፲፫/፳፻፲፮ ዓ/ም በቅዱስነታቸው ጉብኝትና ቡራኬ ፍጻሜው ሆኗል። በሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ድርጅት አማካኝነት ተዘጋጅቶ ለእይታ የበቃው ዐውደ ርእይ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ትውልዳዊ ሀብቶችን በትንናትናዊ ውበታቸው በአሁናዊ ቅኝት የቀረበበት ትውልዱን የሚመጥን ሥራዎች የታዩበት ነው ተብሏል። በመርሐ ግብር ከቅዱስነታቸው ጋር ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሌሎች ብፁዓን አባቶች፣ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሐላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ኦርቶደክሳውያን ተገኝተዋል። | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ -------------------------- ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም
نمایش همه...
የእለቱ መልእክት #ከኒቆዲሞስ_ምን_እንማር? ---------------------------- #አትኅቶ_ርእስ በቅዱስ ወንጌል ላይ በተደጋጋሚ የምናገኘው የፈሪሳውያንን ግብዝነትና የጌታችንን ተግሳጽ ነው፡፡ ማቴ 9 10፣ ማቴ 23፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነን የፈሪሳዊውና የቀራጩ ጸሎት ምን ይመስል እንደነበር መመልከት ነው ሉቃ 18 9፡፡ ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፣ የአይሁድ አለቃ ፣መምህረ እስራኤል ፣ምሁረ ኦሪት ቢሆንም ራሱን ዝቅ አድርጎ ከጌታ እግር ስር ቁጭ አለ፡፡ ሕዝብን ከመምራትና ከማስተማር ይልቅ ቁጭ ብሎ መማር ምንኛ መታደል ነው! ጌታስ በትምህርቱ «ማርያምም  መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርሷም አይወሰድባትም » ያለ ለዚህ አይደል ሉቃ 10 42፡፡ ብዙዎቻችን ባለን የኑሮ ደረጃ የዕውቀት ደረጃ የስልጣን ደረጃ ራሳችን ሰቅለን የመማር አቅም አጥተናል፡፡ ቁጭ ብሎ መማር ደረጃችንን የማይመጥን የሚመስለንስ ስንቶች እንሆን? አንድ ወቅት አባ መቃርስ ከህጻናት እንቆቅልሽ ለመማር ቁጭ እንዳሉ በእንቆቅልሹም ልባቸው ተነክቶ እያነቡ ወደ በዐታቸው መመለሳቸውን  እያወቅን የመማር አቅም ያጣን ስንቶች እንሆን? ማን ያውቃል ከአንድ ሰአት ስብከት ውስጥ እግዚአብሔር ሊያስተመረን የፈለገ አንዲት ዐረፍተ ነገር ቢሆንስ? ትሑት የሚያሰኘው ሳያውቁ አላውቅም ማለት ሳይሆን እያወቁ አላውቅም ማለት ነው፡፡ ሳይማሩ ተምሬያለሁ ማለት ሳይሆን ተምረውም ልክ እንደ ኒቆዲሞስ ለመማር ራስን ዝቅ ማድረግ ነው:: ሰናይ ቀንን ተመኘን! ------------------------------- | ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
🥰 7 1
#ኒቆዲሞስ ======================== የዐቢይ ፆም ሰባተኛ ሳምንት ✝ በዕለቱ ቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ መልዕክታት፣ወንጌልና ምስባክ። ሮሜ. ፯፥፩ - ፲፪፤ ፩ ዮሐ. ፬፥፲፰ - ፍ፤ ግብ ሐዋ. ፭፥፴፬ - ፍ፤ የዕለቱ ምስባክ፦ መዝ ፲፮፥፫ ሐወፅከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፤ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፤ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው። ትርጉም፦ በሌሊት ጎበኘኸኝ ልቤንም ፈተንኸው፤ ፈተንኸኝ ዓመፅ አልተገኘብኝም፤ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር። የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፫፥፩ - ፲፪ ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ ማርያም |ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
👍 3
#ማስታወሻ የነገ የጉባኤ ኒቆዲሞስ መርኃግብር በቀጣይ ወር የተሸጋገረ መሆኑን እንገልጻለን ።
نمایش همه...
#የዝማሬ_ሰዓት #ቢፈልግባትም_መልካሙ_ገበሬ ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ፤ … ለስልሶላት ነበር ሃይማኖት መሬቱ፤ ተቀጥሮላት ነበር አጥር ሥርዓቱ፤ ተነቅሎላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ፤ ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ፤ … ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለሆነች፤ ተካይዋን በምግባር ስላላስደሰተች፤ መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ፤ ሌሎች እንዳይጠፉ በእርሷ የተነሳ፤ … ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት፤ ጠባቂ መልአኳ ተማጸነላት፤ ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት፤ ታፈራ እንደሆነ ለዓመት እንያት፤ … ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ፤ ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ፤ ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች፤ ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች፤ ---------------------------------------------------       |ፍኖተ ሰላም ሚዲያ
نمایش همه...
🥰 3🙏 3😢 1