cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

✝️📯•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•🍁☪️

ሰላማቹ ይብዛላቹ🙌 ኢሄ ቻናል የተከፈተው #ክርስቲያናዊ፟_አስተምሕሮት ለማስተማር ነው ፣ እና ስለ #እስልምናም ስህተታዊ አስተሳሰብም እና አመለካከት በዚ ቻናል ላይ ለመቀየርና ለማስተማር እንሞክራለን ። 💬አስታየት ካላቹ በዚ ያስቀምጡ https://t.me/ewnet_ewnetun_bot 🪐 ወንጌል ለአለም ሁሉ 🌍 👇ይሄን 1ጊዜ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ👇 🙏ተባረኩ🙏

Mostrar más
Advertising posts
9 853Suscriptores
+4624 hours
+1507 days
+1 14930 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

የኒቅያ የሐይማኖት መግለጫ ሁሉን በሚችል ሰማይንና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ። እርሱ ብቻ የአብ ልጅ በሚሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ በተወለደ፣ ከአምላክ በተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን በተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘ እውነተኛ አምላክ፣ በህልውናው ከአብ ጋር አንድ የሆነ፣ በተፈጠረ ሳይሆን በተወለደ፣ ሁሉ በእርሱ በሆነ፣ ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለ ደህንነታችንም ከሰማይ በወረደ፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ስጋ ነስቶ ሰው በሆነ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ በተሰቀለ፣ መከራ በተቀበለ፣ በሞተ፣ በተቀበረም፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም እንደተጻፈ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በተነሣ፣ ወደ ሰማይም በወጣ፣ በአብ ቀኝ በተቀመጠ፣ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ዳግመኛ በክብር በሚመጣ፣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ በሌለው በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ። ከአብና ከወልድ ጋር በሚሰገድለትና በሚከበር፣ ከአብና ከወልድ በሚሠርጽ፣ በነቢያት በተነገረ፣ የሕይወት ጌታና ሰጪ በሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስም አምናለሁ። የሁሉም በሆነች በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንም አምናለሁ። ለኃጢአት ማስተስረያ በአንዲት ጥምቀትም አምናለሁ። የሙታንን ትንሣኤና ገና የሚመጣውን ዓለም ሕይወትም እጠባበቃለሁ። አሜን።     ✞●▬▬▬▬๑۩✞ ◒ ✞۩๑▬▬▬▬▬●✞ 
╔═════◒◒◒◒◒◒◒◒◒═════╗  ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━       ✞●▬▬▬▬๑۩✞    ✞۩๑▬▬▬▬▬●✞                        ◒◒◒◒◒◒◒                             ◒◒◒◒
Mostrar todo...
10👍 2🙏 2
የኒቅያ የሐይማኖት መግለጫ ሁሉን በሚችል ሰማይንና ምድርን፣ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ። እርሱ ብቻ የአብ ልጅ በሚሆን፣ ዓለም ሳይፈጠር ከአብ በተወለደ፣ ከአምላክ በተገኘ አምላክ፣ ከብርሃን በተገኘ ብርሃን፣ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘ እውነተኛ አምላክ፣ በህልውናው ከአብ ጋር አንድ የሆነ፣ በተፈጠረ ሳይሆን በተወለደ፣ ሁሉ በእርሱ በሆነ፣ ስለ እኛ ስለ ሰዎች ስለ ደህንነታችንም ከሰማይ በወረደ፣ በመንፈስ ቅዱስ ከድንግል ማርያም ስጋ ነስቶ ሰው በሆነ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን ስለ እኛ በተሰቀለ፣ መከራ በተቀበለ፣ በሞተ፣ በተቀበረም፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም እንደተጻፈ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ በተነሣ፣ ወደ ሰማይም በወጣ፣ በአብ ቀኝ በተቀመጠ፣ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ዳግመኛ በክብር በሚመጣ፣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ በሌለው በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ። ከአብና ከወልድ ጋር በሚሰገድለትና በሚከበር፣ ከአብና ከወልድ በሚሠርጽ፣ በነቢያት በተነገረ፣ የሕይወት ጌታና ሰጪ በሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስም አምናለሁ። የሁሉም በሆነች በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያንም አምናለሁ። ለኃጢአት ማስተስረያ በአንዲት ጥምቀትም አምናለሁ። የሙታንን ትንሣኤና ገና የሚመጣውን ዓለም ሕይወትም እጠባበቃለሁ። አሜን።
   ✞●▬▬▬▬๑۩✞ ◒ ✞۩๑▬▬▬▬▬●✞ 
╔═════◒◒◒◒◒◒◒◒◒═════╗  ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━       ✞●▬▬▬▬๑۩✞    ✞۩๑▬▬▬▬▬●✞                        ◒◒◒◒◒◒◒                             ◒◒◒◒
Mostrar todo...
ሥላሴ አንድም ሦስትም ናቸው የሥላሴ አንድነት* በሥልጣን በመለኮት ዓለምን በመፍጠር በአነዋወር በአኗኗር) በአገዛዝ በሕልውና በማሰብና በመናገር ፍፁም አንድ ናቸው፡፡ የሥላሴ ማለትም የአብ፣ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ የአንድነት መጠሪያቸው ‹‹እግዚአብሔር›› ይባላል ‹‹እግዚአብሔር›› የሚለው ቃል የተገኘው፡ ‹‹‹እግዚእ››› ‹‹‹አብ››› ‹‹‹ሔር››› ከሚለው ሦስት የግዕዝ ቃላት ነው፡፡ ‹‹‹እግዚእ››› ማለት (ኢየሱስ ክርስቶስ) ‹‹‹አብ››› ማለት (እግዚአብሔር አብ) ‹‹‹ሔር››› ማለት ደግሞ ጠባቂ፣ ቸር፣ ሩህሩህ (መንፈስ ቅዱስ) ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት፡- አብ እግዚአብሔር ነው ወልድም እግዚአብሔር ነው መንፈስ ቅዱስም እግዚአብሔር ነው ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ብሎ ተናግሮ ይህን ቃል ለአብ ብቻ ነው ማለት በጣም ትልቅ ስህተት ነው ምክንያቱም ቃሉ የሦስቱም ፍጹም አካላት የአንድነት መጠርያ ነውና፡፡ የብዙዎችም የውድቀት መነሻም የእግዚአብሔርን ሥምና ትርጓሜን ያለማስተዋል ነው፡፡ ለምሳሌ ዓለምን ሲፈጠር አብ ብቻውን አልፈጠረም ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንጂ ማስረጃ፡- “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ” ዘፍ 1÷1 በዚህ አስተምህሮ ሥላሴ በአንድነት ዓለማትን እንደፈጠሩ በግልፅ ታውቋል፡፡ ምንጭ ____________________ ተስፋዬ ሮበሌ፤ የአስተምህሮተ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት
📯“እነሆ፤ ቶሎ እመጣለሁ፤ ዋጋዬ በእኔ ዘንድ አለ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍለዋለሁ።”📯
🕯 ራእይ 22፥12 (አዲሱ መ.ት)🕯
      🪔ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል!🪐 🍂Jesus is Coming soon
🌍        SHARE 𝙖𝙣𝙙 JOIN     ✞●▬▬▬▬๑۩✞ ◒ ✞۩๑▬▬▬▬▬●✞  ╔═════◒◒◒◒◒◒◒◒◒═════╗  ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━       ✞●▬▬▬▬๑۩✞    ✞۩๑▬▬▬▬▬●✞                        ◒◒◒◒◒◒◒                             ◒◒◒◒                   🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺                              🎯     ♡         ❍ㅤ      ⎙ㅤ  ⌲          ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃ🔺
Mostrar todo...
4👍 2🤝 2👏 1
Mostrar todo...
ጉባኤ ዘሐዋርያት እቅበተ እምነት

አጭር መልእክት ለመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ(Sola Scriptura) ተቃዋሚዎች። ➠ መጽሐፍ ቅዱስ አፊዎተ መለኮት ወይም θεόπνευστος ቴዎፊኒስቶስ ነው። ቴዎፌኒስቶስ የሚለው ቃል theós  «አምላክ» እና pnéō «እስትንፋስ» የሚሉ ቃላት ውቅር ነው። በተዋቅሮ እና በተዛምዶ ሲየበብ የአምላክ እስትንፋስ እንለዋለን። ይህም ማለት እስትንፋሰ መለኮት የሆነ በመለኮታዊ ተመሥጦ የተጻፈ ሕያውና መለኮታዊ ቃል ይባላል። ➠ልዩ መገለጥ እግዚአብሔር አምላክ ለፍጥረቱ ራሱን በልዩ ልዩ መንገዶች ገልጧል። ስለ አምላክ መገለጥ ወይም መታየት ስናነሳ በሥነ መለኮቱ አስተምህሮ እግዚአብሔር በታሪክ ራሱን የገለጠበት መንገድ ፩፦ ጥቅልል አስተርዮት ይህም ስለ አምላክ ሕላዌ በጥቂቱ ይዳስሳል ጥቆማን ይሰጣል የአምላክን ባሕርይ እና እቅድ በሰፊው አይተነትንም ፪፦ልዩ አስተርዮት ወይም ልዩ መገለጥ ይባላል ይህም አምላክ ለፍጥረቱ ስላለው ዘላለማዊ እቅድ ፍጥረቱ ሊያውቀው የሚያገባውን እውነት እምነትን እና ምግባርን በበቂ ሁኔታ ያትታል። መጽሐፍ ቅዱስ የልዩ አስተርዩት መጽሐፍ ነው። ➠ከዚህም ጋር አያይዘን መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መዳናችን ልናውቀው እና ልንረዳው የምንችለውን ሁሉ በበቂነት እና በግልጽነት ይዟል እንላለን። ይህም "Sufficiency Content"(በቂ ይዘት) Sufficiency Clarity (በቂ ግልዘኝነትን አካቷል። ➠ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ ግልጽ በሆነ መልኩ ስለ ድነታችን እና እግዚአብሔር ልንረዳው የሚወደውን ነገር ሁሉ ግልጽ እና በቂ በሆነ መንገድ አስቀምጦልናል ማለት ነው ይህም በመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ አብርሆት የሚፈጸም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ባይኖር...? በቤተክርስቲያን ታሪክ ከጥንት ጀምሮ መናፍቃን የቤተክርስቲያንን መሠረት ለማናጋት ይፈልቁ ነበር። ኖስቲዝም ዶሴቲዝም ኢቦናውያን ሰባልዮስ አርዮስ…

6
ለዚህም እንደ ማስረጃ ቢጤ ይሆኑኛል ያላቸውንም ክፍሎች አብሮ አጋምዶ እናገኘዋለን። በመጀመሪያ አብዱሉ "ፕሮስ(πρὸς)" ወይም "ዘንድ" የሚለውን ቃል ሁለት የተለያዩ ማንነቶች ሲያመለክት እና ግንኙነታቸውን ሲያሳይ የሚናገር ክፍል በተንጻራሪው ከመጽሐፍ ቅዱስ አለማውጣቱ እውነታውን ለመደበቅ የሚታገለውን ትግል ያሳየናል። እስቲ መጽሐፍ ቅዱሱን ገለጥ አድርገን አብዱሉ የደበቀውን እውነታ እንመልከት፦ 🔖“አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ #ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።” — ዮሐንስ 17፥5 ☝️አብዱሉ ከላይ ሲተርክልን እንደነበረው በዮሐንስ ወንጌል 1:1 ላይ ያለው "ቃልም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበር" በሚለው ክፍል ውስጥ ዘንድ የምትለው መስተዋድዳዊ ቃል ባህሪይን ከባለበቱ ያለውን መሰረት ሲያመለክት ይሄም ማለት መስተጋብርን የሚያሳይ እንዳልሆነ የዮሐንስ ምእራፍ 17 ቁጥር 5ን ስንመለከት ግልጽ ይሆንልናል። ምክንያቱም ዮሐንስ 17፥5 ላይ ይህ የእግዚአብሔር ቃል ሎጎስ/λόγος የተባለው(ራዕይ 19:13) ደግሞም ስጋ የሆነው(ዮሐ 1:14) ማለትም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ " #ዓለም_ሳይፈጠር" ሲል በዮሐ 1:1 " #በመጀመሪያ_ቃል_ነበር..." ከሚለው ጋር የተያያዘ ነው። ምክንያቱም ምንም ነገር ሳይፈጠር በፊት እርሱ እንደነበር የሚናገር ክፍል ነው። በዚህ ስልጣን ማንም ፍጡር ተናግሮ አያውቅም። ደግሞም " #በአንተ_ዘንድ_በነበረኝ #ክብር..." ሲል ደግሞ በዮሐ 1:1 ላይ "... #ቃልም_በእግዚአብሔር_ዘንድ_ነበር ..." ከሚለው ክፍል ጋር የሚገናኝ ነው። ይሄም ደግሞ የሁለቱን አካላት ማለትም የአብን እና የወልድን የማንነት ግንኙነት አመልካች ክፍል ነው። ነገር ግን አብዱሉ ከላይ የጠቀሳቸው ክፍሎች በሙሉ(ምሳ 8:30፤ ኢዮ12:16፤ ምሳ2:6፤ ምሳ 3:19፤ ኤር 10:12) እግዚአብሔር አምላክ ከባህሪው ያለውን መስተጋብር የሚያሳዩ ናቸው። "ቃልም ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበር" ማለት ግን ከአንዱ አምላክ ጋር ሌላ ተጨማሪ ፈጣሪ ወይም አምላክ እንደነበር የሚናገር ሳይሆን አንዱ አምላክ በሶስትነት መገለጡን ማለትም አንዱ መለኮት በአካል፣በግብር በስም በሶስትነት እና በስልጣን፤ በአገዛዝ፤ በባህሪ፤ በህልውና በመፍጠር በፍቃድ በአንድነት የሚኖር አምላክ መሆኑን የሚያመለክት ክፍል ነው። አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ሌላ ተጨማሪ አምላክ አለመሆኑን ማወቅ ይኖርብናል። 3️⃣🔒የአብዱሉ ምናባዊ ሀሳብ ነጥብ ሶስት Θεὸς ἦν ὁ Λόγος እግዚአብሔርም ቃል ነበረ ግሪኩ እግዚአብሔርም ቃል ነበረ Θεὸς ἦν ὁ Λόγος ነው የሚለው፥ እግዚአብሔር ፕሮፎሪኮስ ሎጎስ ማለት ተናጋሪ ቃል*speaker* ነው፥ እርሱ ተናጋሪ ነው ንግግር የእርሱ ባህርይ ነው፥ እግዚአብሔር ቃል*speaker* ነው፥ ቃልም*speech* በእርሱ ዘንድ ነው፦ ♦️እግዚአብሔር የኃይል ቃል ነው፥ የእርሱ ባህርይ የሆነውን ቃል ይሰጣል መዝሙረ ዳዊት 68፥38 ♦️እግዚአብሔር ብርሃን ነው(1ዮሐ.1:5) ብርሃንም በእርሱ ዘንድ ነው(ዳን.2:22) το φως είναι μαζί του the light is with him. እግዚአብሔር ብርሃን ነው ሲል ኣብሪ ነው ማለት ሲሆን ብርሃንም ከእርሱ ዘንድ ነው ማለት ደግሞ ብርሃን የእርሱ ባህርይ ነው ማለት ነው፥ ♦️እግዚአብሔር መድሃኒት ነው፣መድሃኒትም በእርሱ ዘንድ ነው (መዝ.62:1-2 ) እግዚአብሔር መድሃኒት ነው ሲል ኣዳኝ ነው ማለት ሲሆን መድሃኒትም ከእርሱ ዘንድ ነው ማለት ደግሞ መድሃኒት የእርሱ ባህርይ ነው ማለት ነው፥ ♦️እግዚአብሔር ረዳት ነው(ዳዊ118፥7 )ረዳትም በእርሱ ዘንድ ነው(መዝ121፥2) 🔑መልስ 👉አብዱሉ በዚህኛው ነጥቡ የግሪኩን ሰዋስዋዊ አተረጓጎም ቅጂዎችን በማረም መጣጥፉን ጀምሮ እናገኘዋለን። ይሄ አብዱል የግሪክ ሰዋሰው ሰነጣጠኩ ተረጎምኩ ምናምን እያለ ሲናገር ይስተዋላል። ነገር ግን እዚህ ክፍል ላይ ሲደርስ እውቀቱን ምን እንደያዘው ፈጣሪ ይወቀው ወይም ደግሞ እያወቀ እውነቱን ለመደበቅ ፈልጎ ይሆን? ለማንኛውም ወደ ክፍሉ የአተረጓጎም ስርዓት መጀመሪያ ልውሰዳችሁ፦ በዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 1:1 👉"θεὸς ἦν ὁ λόγος" የሚለው አረፍተ ነገር ሲተረጎም 🔖"ቃልም እግዚአብሔር ነበር" 🔖" the Word was God.” John 1:1 (KJV) ☝️ይህ አተረጓጎም በሰዋሰዋዊ (Grammatical) ስርዓት ትክክለኛ አተረጓጎም ነው። ምክንያቱም በግሪኩ ክፍል ላይ የአረፍተ-ነገሩን ባለቤት (Subject) የምንለየው በDefinite Article(the,a) ማለትም በግሪኩ "ሆ(ὁ)" በሚለው አርቲክል ነው። በግሪኩ ላይ Definite Article(ὁ) ያለበት ቃል ".... #ὁ λόγος....# ሎጎስ/λόγος በሚለው ላይ እንጂ ቴዎስ/θεὸς በሚለው ላይ አይደለም። በዚህም መሰረት የአረፍተ-ነገሩ ባለቤት (Subject) ሎጎስ/λόγος ተሳቢው ደግሞ ቴዎስ/θεὸς ነው። ስለዚህ ይሄን የቋንቋ ሙህራን ሲተረጉሙት የአረፍተ-ነገሩ ባለቤት(Subject) ማለትም "ሎጎስ/λόγος" የሚውል በማስቀደም " the Word was God” ወይም "ቃልም እግዚአብሔር ነበር" ተብሎ ተተረጎመ። ለምሳሌ ያክል፦ 🔖“እግዚአብሔር መንፈስ ነው...” — ዮሐንስ 4፥24 🔖John 4:24"....πνεῦμα ὁ θεός." ☝️በዚህ ክፍል ላይ እንደ አብዱሉ አተረጓጎም ከሆነ፦ ❌መንፈስ እግዚአብሄር ነው❌ ብሎ ሰዋስዋዊውን ስርዓት ያልጠበቀ አተረጓጎም ሊሰጠን ነው። ነገር ግን ክፍሉም የሚያወራው በተጨማሪም "ሆ(ὁ)" የሚለው Definite Article ያለው ቴዎስ ላይ ስለሆነ በስርዓቱ ሲተረጎም “እግዚአብሔር መንፈስ ነው" ተብሎ ተተርጉሟል። አብዱሉ የራሱን የአተረጓጎም ስርዓት ሲያወጣ የአረፍተ-ነገሩ ባለቤት(Subject) የትኛው እንደሆነ እንዴት መለየት አቃተው??? ደግሞስ እየተወራ ያለው ስለቃል አልነበረም??? ቃል ቃል....እያልን እየሄድን በመጨረሻም "እግዚአብሔርም ቃል ነበር ብሎ መተርጎሙ sense የሚሰጥ አተረጓጎም ይሆናል??? ስለዚህ ክፍሉ በትክክል subject object verb (sov) agreement /የአረፍተ ነገሩ ባለቤት፣ ተሳቢ እና ድርጊቱን ባማከለ መልኩ ተተርጉሟል። 🔖“በመጀመሪያው #ቃል ነበረ፥ #ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ #ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” ☝️ስለዚህ ከላይ ባየነው መልኩ አብዱሉ ያቀረባቸውን ክፍሎች ስንመለከት፦ "እግዚአብሔር መድሃኒት ነው" ሲል፤ "እግዚአብሔር ብርሃን ነው" ሲል፤ "እግዚአብሔር የሐይል ቃል ነው" ሲል በእነዚህ ክፍሎች በሙሉ የአረፍተ ነገሩ ባለቤት እግዚአብሔር እንጂ እንደ ዮሐ1:1 ላይ እንደተጠቀሰው ቃል እነብርሃን፣ እነመድሃኒት፣ እነየሐይል ቃል አይደሉም። ስለዚህ ይሄም የሚያሳየው በእግዚአብሔር እና በእግዚአብሔር ባህሪያት መካከል ያለውን መስተጋብር ማለትም የባህሪውን መገለጫዎች እየተናገረ ነው። ይህም ደግሞ ከዮሐንስ ወንጌል ጋር የሚያያይዘው አንዳች ነገር የለም። በሚቀጥለው ክፍል በሌላ ጥያቄዎች ምላሽ እስገምንገናኝ ቸረ ሰንብቱ🙏 🙏ክብር ምስጋና ለልዑል አምላክ 🙏 ለኢየሱስ ክርስቶስ( #ያህዌיְהֹוָה) ይሁን!!!አሜን ✍️Jonathan (جوناثان)
Mostrar todo...
👍 9 2👏 2🎉 1🙏 1
📖ቃል(ሎጎስ/λόγος)📖 #ክፍል_ሁለት ✟በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ✟ አሐዱ አምላክ *ዮሐንስ 1፥1 “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” *John 1:1   Ἐν ἀρχῇ ἦν ὁ λόγος καὶ ὁ λόγος ἦν πρὸς τὸν θεόν καὶ θεὸς ἦν ὁ λόγος 👉ሻሎም ሻሎም የተባረካችሁ ያባቴ ብሩካኖች እንዲሁም ሙስሊም ወገኖቻችን በክፍል አንድ ስለቃል(ሎጎስ/λόγος) ምንነት በተወሰነ መልኩ ለመዳሰስ ሞክረናል በክፍል ሁለት ደግሞ ስለቃል(ሎጎስ/λόγος) ዙሪያ በሚነሱ ጥያቄዎች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽ በመስጠት እንቀጥላለን። እስቲ አንዱ የሙስሊም ሚሺነሪዎች ጦማሪ የሆነው አብዱል ስለቃል(ሎጎስ/λόγος) የፈሰረውን መጣጥፍ አንድ በአንድ እያበጠርን እንደተለመደው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽ እንስጠው፦ 1️⃣🔒የአብዱሉ ምናባዊ ሀሳብ ነጥብ አንድ Ἐν archē ἦν ὁ Λόγος በመጀመሪያው ቃል ነበረ ፈጣሪ ሁሉን ነገር የፈጠረው በቃሉ ነው፦ ዘፍጥረት 1.3 እግዚአብሔርም፦ ብርሃን ይሁን አለ ብርሃንም ሆነ። መዝ.33:9 እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም። መዝ.148:5 እርሱ ብሎአልና፥ ሆኑም፤ እርሱም አዝዞአልና፥ ተፈጠሩም፤ ዮሐ.1:3 ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። ኢሳ.55:11፤ ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል፥ ፦ፈጣሪ ከአፉ በሚወጣ ቃል የሚሻውን አድርጓል ፤ቃል ንግግር እንደመሆኑ መጠን፣ ንግግር ከተናጋሪው እንደማይለይ ሁሉ ቃልም የፈጣሪ ባህርይ ነው፤ ባህርይ ከህላዌ ተነጥሎ እንደማይኖር ቃልም በመጀመሪያ ነበረ፤ ይህም ስፐርማቲኮስ ሎጎስ ማለት የንግግር ቃል*speech* ቃል ነው። 🔑መልስ 👉አብዱሉ በመጣጥፉ ውስጥ እግዚአብሔር አምላክ በቃሉ ሁሉን ነገር እንደፈጠረ ከተናገረ በኋላ ቃል(ሎጎስ/λόγος) የእግዚአብሔር ባህሪ ባህርይ ከህላዌ ተነጥሎ እንደማይኖር ቃልም በመጀመሪያ ነበረ እንደተባለ ተናግሯል። ነገር ግን ይሄ የግሪክ ሰዋሰው ተንታኝ ነኝ ባይ አንድ ያልተረዳው ነጥብ እንዳለ ከንግግሩ እንረዳለን። "ቃል(word)" የሚለው ቃል ትርጉማዊ አገባብ እንዳለው አብዱሉ ተናግሮ ነበር። ነገር ግን ለየትኛው ንግግር እንደሚገባ አልተረዳውም። በዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ 1 በቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ቃል ማለትም ሎጎስ/λόγος የሚለው ስፐርማቲኮስ ሎጎስ ወይም ሬማ(ῥῆμα) የሚለውን ሳይሆን መለኮታዊ፣ የሁሉ ነገር ፈጣሪ እና ዘላለማዊ የሆነውን ፕሮፎሪኮስ ሎጎስ ወይም ተናጋሪ ቃልን የሚወክል ነው። ሬማ(ῥῆμα) ግን አምላክ ወይም ፈጣሪ ሊባል ፈጽሞ አይችልም። ነገር ግን በክፍሉ ላይ ያለው "ቃል(word)" የተባለው ፈጣሪ፤ ከፈጣሪ ዘንድ የነበረ፤ ራሱ ደግሞ ፈጣሪ የሆነ አካል(personality) ወይም አንተ(you) የሚል መደብ አመልካች ያለው ራሱን ችሎ የሚቆም ጥገኛ ያልሆነ ማንነት ያለው ተናጋሪ ሎጎስ/λόγος ነው። ለዚህም ምሳሌ እንዲሆነን የዮሐንስ ራዕይ ምእራፍ 19 ቁጥር 13ን እንመልከት፦ 🔖Revelation19:13  καὶ περιβεβλημένος ἱμάτιον βεβαμμένον αἵματι καὶ καλεῖται τὸ ὄνομα αὐτοῦ ὁ λόγος τοῦ θεοῦ 🔖ራእይ 19፥13 “በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።” ☝️በዚህ ክፍል ላይ" #በደምም_የተረጨ #ልብስ_ተጐናጽፎአል" የሚለን የእግዚአብሔር ንግግር(speech) ነው?የእግዚአብሔር ንግግር(speech) ነው ካልንስ ደግሞ እንዴት በደምም የተረጨ ልብስን ለብሷል ይለናል? ስለዚህ በዚህ ክፍል ላይ የእግዚአብሔር ቃል ወይም ሎጎስ/λόγος የተባለው ስጋ የለበሰው ማለትም ሰው የሆነው ስለብዙዎች ሲል መከራን የተቀበለው ስለ ሐጢያት ስርዬት ደሙንም ያፈሰሰው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስለዚህ በዚህ ክፍል ላይ ራሱን ችሎ የሚቆም "አንተነት" ወይም personality ያለው አካል እደሆነ ግልጽ ነው። ነገር ግን አብዱሉ ከላይ የጠቀሳቸው ክፍሎች(ዘፍ 1:3፣ መዝ33:9፣ መዝ148:5፣ ኢሳ 55:11) ሁሉም የእግዚአብሔርን የንግግር(speech) ሎጎስን/λόγος የሚያሳዩ ክፍሎች ናቸው። ለምሳሌ ትንቢተ ኢሳያስ ምእራፍ 55 ቁጥር 11ን ብንመለከት፦ 🔖Isaiah55:11   οὕτως ἔσται τὸ #ῥῆμά μου ὃ ἐὰν ἐξέλθῃ ἐκ τοῦ στόματός μου οὐ μὴ ἀποστραφῇ ἕως ἂν συντελεσθῇ ὅσα ἠθέλησα καὶ εὐοδώσω τὰς ὁδούς σου καὶ τὰ ἐντάλματά μου 🔖ኢሳይያስ 55፥11 “ከአፌ የሚወጣ #ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።” ☝️በዚህ ክፍል ላይ ሬማ(ῥῆμα) ወይም ከእግዚአብሔር አንደበት የሚወጣ ቃል(speech) ወይም የንግግር ቃል እንጅ የእግዚአብሔር ሎጎስን/λόγος ማለትም ተናጋሪ ቃል(speaker) ፕሮፎሪኮስ ሎጎስ የሚወክል ፈጽሞ አይደለም። ደግሞም በኢሳ 55:11 ላይ ያለው ሬማ(ῥῆμα) እና ከዮሐንስ ወንጌል 1:1 ላይ ካለው ፕሮፎሪኮስ ሎጎስ/λόγος መቼም አንድ የማይሆኑ ሁለት የተለያየ ትርጓሜን ያዘሉ ሆድና ጀርባ የሆኑ ቃላቶች ናቸው። 2️⃣🔒የአብዱሉ ምናባዊ ሀሳብ ነጥብ ሁለት ὁ Λόγος ἦν πρὸς τὸν Θεόν ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ πρὸς ዘንድ የሚለው መስተዋድድ ሁለት የተለያዩ ማንነቶች ሲያመለክት ግንኙነትን ያሳያል፣ ነገር ግን ባህሪይን ከባለበቱ ያለውን መሰረት ሲያመለክት ደግሞ መስተጋብርን ያሳያል፣ እስቲ ይህን እንመልከት፦ ምሳ.8:30 የዚያን ጊዜ እኔ በእርሱ ዘንድ ዋና ሠራተኛ ነበርሁ Τότε ήμουν μαζί του Then I was with him ኢዮ.12:16፤ ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ ኃይል፣ጥበብ፣ማስተዋል፦እውቀት የፈጣሪ ባህሪያት ናቸው፤ ፈጣሪ ሁሉን ነገር የፈጠረው በእነርሱ ነው፦ ምሳ.2:6 እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤ ምሳ.3:19 እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና። በእውቀቱ ቀላያት ተቀደዱ፥ ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ። ኤርምያስ 10.12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው። ታዲያ ከአፉ የሚወጣ ኃይል፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፤ እውቀት በእርሱ ዘንድ ነበሩ ስለተባሉ እየሸነሸንን አካላት እንስጣቸው እንዴ ? አንዱ አምላክ አንድ ቅዋሜ-ማንነት ሲሆን ኣጠገቡ ምንም ኣምላክ እንደሌለ ተናግሮ የለም እንዴ? ኢሳይያስ 44.24 ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ከእኔ ጋር ማን ነበረ? ዘዳ.32:39፤ አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም ጋር አምላክ እንደሌለ እዩ 🔑መልስ 👉አብዱሉ "ፕሮስ(πρὸς)" በአማርኛው ደግሞ "ዘንድ" የሚል ፍች የያዘውን መስተዋድዳዊ ቃል ሁለት የተለያዩ ማንነቶች እንደሚያመለክት እና ግንኙነታቸውንም እንደሚያሳይ ከተናገረ በኋላ "ነገር ግን" ብሎ የዮሐንስን ወንጌል 1:1 ላይ ባህሪይን ከባለበቱ ያለውን መሰረት የሚያመለክትና ይህም ደግሞ መስተጋብርን እንደሚያሳይ በመናገር የራሱ ልብ ወለዳዊ ምደባውን ሰንዝሯል።
Mostrar todo...
👍 5 1
📖ቃል(ሎጎስ/λόγος)📖 #ክፍል_አንድ ✟በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ✟ አሐዱ አምላክ *ዮሐንስ 1፥1 “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” *John 1:1   Ἐν ἀρχῇ ἦν ὁ λόγος καὶ ὁ λόγος ἦν πρὸς τὸν θεόν καὶ θεὸς ἦν ὁ λόγος 👉ሻሎም ሻሎም የተባረካችሁ ያባቴ ብሩካኖች እንዲሁም ሙስሊም ወገኖቻችን ጌታ ቢፈቅድ በተከታታይ ክፍሎች ስለቃል(ሎጎስ/λόγος) ምንነትና በእርሱ ዙሪያ በሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠን እንቀጥላለን። 👉ቃል(ሎጎስ/λόγος)፦ ማለት ሌጎ λέγω (ተናገረ፣አለ፣ቃል ከአፉ አወጣ) ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን "ንግግር" የሚለውን ስምን(መጠሪያን) የሚወክል ቃል ነው። ይህም ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለሁለት ተግባራት ውሎ እናገኘዋለን። ⓵አንደኛ የእግዚአብሔር ንግግር(ስፐርማቲኮስ ሎጎስ) ወይም የንግግር ቃል ለምሳሌ፦ “ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።” — ኢሳይያስ 55፥11 ⓶ሁለተኛው ስጋ የለበሰው ቃል(ፕሮፎሪኮስ ሎጎስ) ተናጋሪ ቃል ወይም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መጠሪያ ቃል ነው። ዮሐንስ 1፥1 ♦️“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” ♦️“በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።” — ራእይ 19፥13 📍እስቲ የዮሐንስን ወንጌል ምእራፍ 1 ቁጥር 1ን በሀይለቃል እየነጣጠልን እንመልከት፦ 1️⃣ #ነጥብ_አንድ 🔑 #በመጀመሪያው_ቃል_ነበረ (Ἐν ἀρχῇ ἦν ὁ λόγος) 👉በመጀመሪያ(Ἐν ἀρχῇ) የሚለው ቃል ለጅማሬው ወሰን የለሽ(infinite) የሆነን ጊዜ አመልካች ቃል ነው። ይሄ ጅማሬ ከሌሎቹ "ጅማሬዎች" የሚለየው የአምላክን ሀልዎት ወይም መገኘት ገደብ አልባ ወይም ለጅማሬው መነሻ ጊዜ እደሌለው የሚያሳይ ቃል ነው። ለምሳሌ በዘፍጥረት ምእራፍ 1 ቁጥር 1 ላይ "በረሺት ኤሎሂም......." /በመጀመሪያ እግዚአብሔር ወይም ደግሞ በግሪኩ ሰፕቱጀንት ላይ እንደተተረግመው "en arche…ho Theos’ " *Gen1:1 בְּרֵאשִׁית בָּרָא אֱלֹהִים אֵת הַשָּׁמַיִם וְאֵת הָאָֽרֶץ׃ *ዘፍጥረት 1፥1 “*በመጀመሪያ* እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።” *Gen1:1 *ἐν ἀρχῇ* ἐποίησεν ὁ θεὸς τὸν οὐρανὸν καὶ τὴν γῆν ☝️በዘፍጥረት ላይ "በመጀመሪያ (ἐν ἀρχῇ)" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ቅድመ ስራውን ወይም ሰማይ እና ምድር መፍጠር የመጀመሪያ የእግዚአብሔር የእጁ ስራዎች መሆናቸውን ነው። ከዚህ ክፍል አንድ ማስተዋል የሚጠበቅብን ነገር ሰማይ እና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት እግዚአብሔር(ኤሎሂም) መኖሩን ማወቅ ይኖርብናል። ወደ ዮሐንስ ወንጌል ስንመለስ ደግሞ "በመጀመሪያ (ἐν ἀρχῇ)" ሲል ከቃል(ሎጎስ/λόγος) በፊት ምንም አይነት ፍጥረት ሆነ ፈጣሪ እንደሌለ ያመላክተናል። 2️⃣ #ነጥብ_ሁለት 🔑 #ቃልም_በእግዚአብሔር_ዘንድ #ነበረ(ὁ λόγος ἦν πρὸς τὸν θεόν)👉የዮሐንስ ወንጌል ከሶስቱ ወንጌላት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት እና ወልድ ከስላሴ አካል አንዱ እንደሆነ በይበልጥ እና በስፋት ገልጾልናል። ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ (ὁ λόγος ἦν πρὸς τὸν θεόν) በሚለው ሀይለቃል ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ወይም ወልድ ከስላሴ አካል አንዱ እንደሆነና እርሱም በመጀመሪያም ከእግዚአብሔር ጋር እንደነበር ይነግረናል። በእግዚአብሔር ዘንድ (πρὸς τὸν θεόν) በሚለው ሐረግ ውስጥ "ዘንድ(ፕሮስ/πρὸς)" የሚለው መስተዋድድ ከእግዚአብሔር ጋር ሌላ አካል(person) እንዳለና ያላቸውን ግንኙነት ያሳየናል። ለምሳሌ፦ ♦️“አሁንም፥ አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ።” — ዮሐንስ 17፥5 ይህም ማለት ግን ከእግዚአብሔር ተጨማሪ አምላክ ከእርሱ ጋር እንደነበር የሚናገር ሳይሆን አንዱ አምላክ በሶስትነት መገለጡን ማለትም አንዱ መለኮት በአካል፣በግብር በስም በሶስትነት እና በስልጣን፤ በአገዛዝ፤ በባህሪ፤ በህልውና በመፍጠር በፍቃድ በአንድነት የሚኖር አምላክ መሆኑን የሚያመለክት ክፍል ነው። አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ሌላ ተጨማሪ አምላክ አለመሆኑን ማወቅ ይኖርብናል። 3️⃣ #ነጥብ_ሶስት 🔑 #ቃልም_እግዚአብሔር_ነበረ (θεὸς ἦν ὁ λόγος) 👉በዮሐንስ 1:1 ስለ ቃል(ሎጎስ/λόγος) ዘላለማዊነት፤ ከአምላክ እግዚአብሔር ዘንድ እንደነበር በመጨረሻም ቃል(ሎጎስ/λόγος) ራሱ እግዚአብሔር እንደነበር ይህ የዮሐንስ ወንጌል ምእራፍ አንድ ቁጥር አንድ የወንጌልን ጅማሬ ከቃል አምላክነት መገለጥ በመጀመር ስለ ቃል(ሎጎስ/λόγος) ምንነት ይነግረናል። የዮሐንስ ወንጌል የተጻፈው ለአህዛቦች ስለነበር በክርስቶስ አምላክነት ላይ ያተኮረ ወንጌል ነበር። ይህ ዘላለማዊ እና አምላክ የነበረው ቃል ስጋ እንደለበሰ ወይም እንደሆነ ይነግረናል(ቁጥር 14)። "ቃልም እግዚአብሔር ነበረ" ሲል እርሱ እንደሆነ ማለትም በአምላክ መልክ(ፊልጵ 2፥6) የነበረ አምላክ እርሱ ፈጣሪ(ቁጥር 3) እና መለኮት እንደሆነ ያስረዳናል። አንዳንድ ጸረ ክርስቶስ የክርስቶስ አምላክነትን የሚክዱ ሚሽነራውያን "ቴዎስ ኢን ሆ ሎጎስ" (θεὸς ἦν ὁ λόγος)"ቃልም እግዚአብሔር ነበረ" የሚለው የአተረጓጎም ችግር እንዳለ ለማስመሰል በማጭበርበር የተለመደውን ወሬያቸውን ይነዛሉ። በሚቀጥለው ክፍል በጥያቄያቸው እና በቅጥፈታቸው ላይ በስፋት ምላሽ በመስጠት እንቃኛለን እስከዛው ቸር ሰንብቱ🙏 🙏ክብር ምስጋና ለልዑል አምላክ 🙏 ለኢየሱስ ክርስቶስ( #ያህዌיְהֹוָה) ይሁን!!!አሜን ✍️Jonathan (جوناثان)
Mostrar todo...
👍 15👏 2 1
ኢየሱስ #እመጣለሁ ብሎ #ከመጣ ኢየሱስ #እወለዳለሁ ብሎ #ከተወለደ ኢየሱስ #እሰቀላለሁ ብሎ #ከተሰቀለ ኢየሱስ #እሞታለሁ ብሎ #ከሞተ ኢየሱስ #እነሳለሁ ብሎ #ከተነሳ ኢየሱስ #እሄዳለሁ ብሎ #ከሄደ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።። ኢየሱስ እመጣለሁ ብሏልና ይመጣል ማራናታ አሜን ጌታ ሆይ ቶሎ ና! 👉@seleslamenwk
📯“እነሆ፤ ቶሎ እመጣለሁ፤ ዋጋዬ በእኔ ዘንድ አለ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍለዋለሁ።”📯
🕯 ራእይ 22፥12 (አዲሱ መ.ት)🕯
🪔ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል!🚀 💮Jesus is Coming soon📍     ✞●▬▬▬▬๑۩✞ ◒ ✞۩๑▬▬▬▬▬●✞  ╔═════◒◒◒◒◒◒◒◒◒═════╗  ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━ ━━━⊱📯✞•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•✞🍁⊰━━━       ✞●▬▬▬▬๑۩✞    ✞۩๑▬▬▬▬▬●✞                        ◒◒◒◒◒◒◒                             ◒◒◒◒                   🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉን🔺                              🎯     ♡         ❍ㅤ      ⎙ㅤ  ⌲          ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃ
Mostrar todo...
19👍 4🥰 4
የሃጅ እውነታ ወይም ከጀርባው ያለው ሚስጥር || The Truth about the Hajj || David Wood Amharic
Mostrar todo...
👍 6 3🥰 1
🕌የሃጅ እውነታ ወይም ከጀርባው ያለው ሚስጥር 🕋
✝️📯•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•🍁☪️