cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አደይ

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
5 319
Suscriptores
Sin datos24 horas
-417 días
-22830 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️           🛡 የድሀ ፍቅር💚 🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣         በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ::    ዛሬ ማታ 2️⃣ሰዓት ላይ ይጠብቁን like😀 share⬅️ ማድረግ እንዳትርሱ
Mostrar todo...
👍 27💔 3
❤️ይቅጥል የምትሉ?  like 👍
Mostrar todo...
👍 15 3
ሜላት ስራ አቁማለች ምንም አትሰራም እኛ ድሮ ከምንኖርበት ቤት ለቀው ሌላ ቦታ ተከራይተው ነው የሚኖሩም ምክንያቱም ወንድሟ ቤታችንን ያውቀው ስለነበር እንዳያገኛት በማሰብ ነበር .የሜላት እናት ለሜላት እባቷ ሳያውቅ ብርም አንዳንድ ነገር ያደርጉላታል እባቷ ግን ደውለው አያውቁም .የት እንደምትኖርም ለማጣራት አልፈለጉም ብር ስትጨርስ ተመልሳ ትመጣለች ብለው አስበዋል.እሷ ግን ወደ ቤት አልተመለሰችም ነበር.., ማታ ሳጠና አምሽቼ ጠዋት ተነስቼ ሻወር ወስጄ ወደ ላይብረሪ ሄድኩኝ ትንሽ አጠናሁና ተመልሼ ወደ ዶርም ገባሁ .ሜላቴ ደወለች በጣም እያለቀሰች ነው እባቷ የመኪና አደጋ ደርሶባቸው ሆስፖታል ገብተዋል ተብሎ ተነግሯት ወደ ሆስፖታል እየሄደች መሆኑን ነገረችኝ ደነገጥኩ ምንም አባቷ ሊለያዬን ቢፈልጉም ምንም እንዲሆኑ ግን አልፈልግም ነበር .በቃ አይዞሽ ተረጋግተሽ ሂጂ አልኳት .በቃ ደረስኩ ብላኝ ስልኩ ተዘጋ እኔም ቆሜ ቀረሁ
Mostrar todo...
👍 5
⚡️⚡️ ⚡️ የድሀ ፍቅር⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️                                  በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ                                                             🔺ክፍል 🔫🔫 የመጨረሻ አመት ተመራቂ ስለሆንኩ በጣም ተወጥሬ እያጠናሁ ነው አንደኛው ሲሚስተር አልቆ ሁለተኛው ሲሚስተር ላይ ነን አጋጣሚ ላይብረሪ ከምሄድ ማንም ዶርም ውስጥ ስለሌለ እዚሁ ላጥና ብዬ እያጠናሁ ነበር .ድንገት ስልኬ ጮኸ ሜላት ነበረች.ስልኩን አነሳሁት የኔ ፍቅር እንዴት ነሽልኝ አልኳት ድምፃ ደስ አይልም ነበር.አለውልህ እንዴት ነህልኝ ውዴ አለችኝ. ሜላቴ የሆነ ነገር ካልሆነች በስተቀር እንደዚህ ፍዝዝ ብላ አታወራኝም.ደግሞ ምን ተፈጠረ ወይ አምላኬ አልኩ በልቤ.ምነው የኔ ፍቅር ምን ሆንሽብኝ ድምፀሽ ትክክል አይደለም አልኳት.ውዴ ግራ ገብቶኛል ብላ ማልቀስ ጀመረች ምንድነው ምን ተፈጠረ ንገሪኝ አልኳት .አባቴ መልስሽ ከዛሬ እንዳያልፍ ወይ እሽ ወይም እንቢ ብለሽ አታስጠብቂኝ መልሱን ማታ እንድትነግርትኝ ብሎኛል አለችኝ እያለቀሰች .ደነገጥኩ በጣም ምን ትበላቸው., የኔ ፍቅር ተረጋጊ መፍትሄ አናጣም አልኳት ""እሽ በይ እንዳትለኝ ብቻ ""አለችኝ በጩኸት አላደርገውም የኔ ፍቅር አልኳት .አፈቅርሻለው ላጣሽ አልፈልግም አልኳት .እሷም አፈቅርሀለው.እሽ መቼም አልለይህም ሁሌም አብሬህ ነኝ .ለማንኛውም በቃ በኃላ አወራሀለው ብላኝ ስልኩ ተዘጋ ተረበሽኩ ግን ምን ላድርግ ምንም .ማጥናት እንኳን አልቻልኩም ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ ከሜላቴ ጋር ሆኜ ያሳለፍኳቸው እያንዳንዶ ጊዜና ሰአት ድቅን ብለው በትዝታ ወሰዱኝ., ሜላት ስልኩን ዘግታ ባንክ ሄዳ ያላትን ብር እንዲሁም ሌላ ብር ጨምራ ወደ እኔ አካወንት ውስጥ ታስገባዋለች እኔ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም.ሜላት ይሄንን ያደረገችው .አባቷ ጨክነው ከቤት ብትባረር እንኳን ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ይሆናል ብላ አስባ ነበረ .ወደ ቤቷ ከመሄዷ በፊት ደወለችልኝ አባቷን በፍፁም ማሳመን ስለማትችል በቃ አልፈልገውም ማግባት አልፈልግም ብላ መልስ ለመስጠት እንደተዘጋጀችና ወደ ቤት መግባቷን ነግራኝ ስልኩ ተዘጋ., እኔም ፀሎቴን ቀጠልኩ ምንም እንዳይፈጠር አምላኬ ሆይ አደራህን አልኩት,በቃ ግራ ስለገባኝ ለእናቴ ደወልኩላት , ሰላም ካልኳት በኃላ ድምፄ ስለተቀየረባት ምን ሆንክ ብላ ጠየቀችኝ መቼም የእናት አንጀት ሆኖባት ምነው ልጄ እራበህ ጠማህ ምንድነው ድምፅእህ አለችኝ .እኔም ሁሉንም ነገር ነገርኳት ጨንቆኛል አልኳት አይዞህ አምላክ ያውቃል ልጄ አለችኝ እሽ .,እማ ምን አደርጋለው በፀጋ መቀበል ነው ብዬ አሰብኩ ,ልጄ አላማህን እንዳትረሳ ይቺ ልጅ ያንተ ከሆነች የትም አትሄድም እሽ በትምህርትህ በርትተህ እኔንም እሷንም ማስደሰት ይኖርብሀል አለችኝ ,እናቴ እውነቷን ነው እሽ እማ በቃ ሰላም እደሩ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት , እናቴ ያለችኝን ነገር እያሰብኩ ደብተሬን ማገላበጥ ጀመርኩ ግን ጥናት ማጥናት አልቻልኩም.ወዲያው ሜላት ደወለች ምን !ምን!ተፈጠረ አልኳት በፍጥነት.ተረጋጋ ምንም አልተፈጠረም አባቴ ድንገት ስራ ተብሎ ነገ ከከተማ ስለሚወጣ በጊዜ ተኝቷል ከሳምንት በኃላ ፈጣሪ ያውቃል አለችኝ .ተመስገን ጌታዬ አልኩ ደስ አለኝ .ትንሽ ተሳስቀን ደህና እደሪ ደህና እደር ተባብለን ስልኩ ተዘጋ.ከዚህ በኃላ ማጥናት አለብኝ ብዬ ማጥናት ጀመርኩኝ., በማግስቱ ጠዋት ስልኬት ትቼ ወደ ትምህርት ገብቼ ስለነበር ስልኬ ሲደወል ማወቅ አልችልም .በደንብ በጥሩ መንፈስ ተማርኩኝ .ላይብረሪም ገብቼ ሳጠና ቆየሁ .ከዛ ሜላቴ ትዝ ስትለኝ ልደውልላት ብዬ ወደ ዶርማችን ሄድኩ ስልኬን ሳነሳው ያየሁት missed call ከሁለት መቶ በላይ ነበር እናቴና ሜላት ነበሩ ደነገጥኩ.,ስልኬን አንስቼ በመጀመርያ እናቴ ጋ ደወልኩ ግን አታነሳም ለሜላትም ስደውል ስልኳ አይሰራም., ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻልኩም ግራ ገባኝ .በዛው ደቂቃ ትንሽ ቆይ መልሼ እደውላለው የሚል ሜሴጅ በሜላት ስልክ ተላከልኝ....... ⚡️⚡️ ⚡️ የድሀ ፍቅር⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️                                  በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ                                                             🔺ክፍል 🔫🔫 ፈተና ስለደረስብኝ ለማጥናት ላይብረሪ ቆይቼ ስመጣ በጣም ብዙ miss call አገኝው እናቴም ሜላትም ደውለው ነበር በጣም ደነገጥኩ ደግሜ ስደውል ስልካቸውን አያነሱም ግራ ገባኝ .በሜላት ስልክ ትንሽ ታገስኝ እሰውላለው የሚል ሜሴጅ ደረሰኝ... ትንሽ ተረጋጋሁ... ከትንሽ ቆይታ በኃላ ሜላት ደወለች .በፍጥነት አነሳሁት ምንድነው ምን ተፈጠረ ሜላቴ አልኳት ተረጋጋ ምንም አልተፈጠረም አለችኝ እና ለምን ይሄን ያክል ጊዜ ደጋግማችሁ ደወላችሁ አልኳት የኔ ውድ እንዳትደነግጥ በጥሞና አዳምጠኝ ,አለችኝ እሽ አልኳት ግን ምንድነው አልኳት ልቤ ፍራት ፍራት እያለው .ካልተረጋጋህ ልነግርህ አልችልም አለችኝ እሽ !እሽ ! ንገሪኝ አልኳት ለመረጋጋት እየሞከርኩ.. እየውልህ የኔ ፍቅር ዛሬ ትንሽ ችግር የፈጥሯል አንተ ትምህርት ልትጨርስ አንድ ወር ነው የቀረህ አይደል እኛ ደግሞ ይቺን አንድ ወር በዘዴ ማለፍ ይኖርብናል አለችኝ ምንድነው ግራ ገባኝ እኮ ንገሪኝ አልኳት,.ውስጤ ግን ይበልጥ ፍርሀት ውስጥ ገብቷል.ምን መሰለህ የኔ ውድ ማታ እንደነገርኩህ አባቴ ሌላ ቦታ ለስራ ሊሄድ ነበር, ነገር ግን ጠዋት ትንሽ ችግር ተፈጥሮ እኔ ከቤት ወጥቻለው አለችኝ .,ደነገጥኩ ለምን እንዴት ብዬ ጥያቄየን አፋጠንኩት.ተረጋጋ አባቴ ውሳኔየን ሲጠይቀኝ የማላውቀውን የማልወደውን ሰው ማግባት እንደማልችልና እንደማልፈልግ ስነግረው ከቤት አባረረኝ አሁን እናንተ ቤት ነኝ አለችኝ .. ብደነግጥም ድንጋጤዬን ዋጥ አድርጌው,.ወይኔ በጌታ እሽ በቃ እሱው ጋ ሁኚ ግን ተጠንቀቁ አልኳት ችግር የለውም እኔ ግን የደወልኩት ዋነኛው ምክንያት ይሄ አይደለም አባቴ ምናልባት የት ዮኒቨርሲቲ እንደደረሰህና ያለህበትን ካወቀ ችግር እንዳያደርስብ እንድትጠነቀቅ ልነግርህ ነው ምክንያቱም በጣም ሲዝት ነበር አለችኝ.አይ ችግር የለም እዚህ ምንም አይፈጠርም አታስቢ አልኳት . አባቷ እኔን ምንም ማድርግ አይችሉም የፈራሁት ለወንድሜና ለእናቴ ነው ምንም እንዲሆኑብኝ አልፈልግም .ሜላቴንም ማጣት አልፈልግም .,እሷ ሀብታም እኔ ድሀ ሆነኜ ያለን ፍቅር እሷም እንደኔ ድሀ ስትሆን ይዘልቅ ይሆን ?አላውቅም ብቻ ግን አሁን ላይ አፈቅራታለው ሁሉም ምንም አይሁኑብኝ .,የሚገርመው እኔ ሳላውቅ ሜላቴ ብር በእኔ አካወንት ማስገባቷን ስትነግረኝ ደነገጥኩ ብዙ ብር ነው ስፈልግ ስፈልግ ትልክልኛለህ ይቀመጥ ለጊዜው ትንሽ ብር እጄ ላይ አለ አለችኝ እሽ አልኳት., ሜላት እኛ ቤት መኖር ከጀመረች ሳምንት ሆኗቷል እኔም ፈተና ስለደረሰብኝ በጥናት ተወጥሪያለው በቃ ብቻ ስለ ወደፊቱም አስባለው .አንዳንዴ የነገን አምላክ ያውቃል ብዬ እተወዋለው ሜላት እኔ ጋ መምጣት ፈልጋ ነበር እኔ ግን የፈተና ሰአት ስለደረስ አትምጪ አልኳት ምክንያቱም እሷን ትቼ ማጥናት አልችልም ግዴታ አብሪያት መዝናናት ይኖርብኛል .እሷም ስለተረዳችኝ ምንም አላለችኝም እሽ ብላ ቀረች., 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 አደይ
Mostrar todo...
👍 1
𝕊ℍ𝔸ℝ𝔼
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️           🛡 የድሀ ፍቅር💚 🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣         በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ::    ዛሬ ማታ 2️⃣ሰዓት ላይ ይጠብቁን like😀 share⬅️ ማድረግ እንዳትርሱ
Mostrar todo...
👍 12
❤️ይቅጥል የምትሉ?  like 👍
Mostrar todo...
👍 17 4
⚡️⚡️ ⚡️ የድሀ ፍቅር⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️                                  በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ                                                             🔺ክፍል 🔫 ሜላቴ እቤት መጥታ ተጠምጥማ ሰላም አለችን ከድሮዋ ተለውጣብኛለች ፈገግታዋ የለም እንዲያውም እንባዋ ቅርር ብሏል ,ሜላቴ የኔ ፍቅር ምን ሆነሻል አልኳት ,ከመቀመጫዋ ተነስታ ተጠመጠመችብኝ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ግራ ገባኝ ,ሜላቴ ለመጀመርያ ጊዜ ከአይኗ እንባ ሲወርድ አየሁ በሳቅና በደስታዋ ነው እኔ የማውቃት,. በጣም ግራ ገባች ምን ሆነሽ ነው ይሄን ያክል ናፍቄሻለው እንዴ አልኳት እየቀለድኩ ,ማልቀሷን አላቆመችም ምን ሆንሽብኝ ብዬ እንባዋን ጠራረግሁላት እስኪ ንገሪኝ ምንድነው የተፈጠረው?አስከፋሁሽ?ያስከፋሽ ሰው አለ ምን ሆንሽ የኔ ፍቅር አልኳት እንባዋን ለማስቆም እየሞከርኩ,. ሜላቴም እንባዋን ለማስቆም እየታገለች በሚያሳዝን ድምፅ እወድሀለው! አፈቅርሀለው! ካንተ ተለይቼ መኖር አልችልም አለችኝ ,እንዴ የኔ ፍቅር ምን ሆነሽ ነው ምን ተፈጠረ አልኳት ,ሜላቴም ከልብ አዝና እንደዚህ ብላ የተፈጠረውን ነገረችኝ., በጣም እያዘነች አባቷ ሊድሯት እንደሆነ ነገረችኝ, ከአባቷ ጋር አብሮ የሚሰራ አንድ ሀብታም ልጁ ከአሜሪካ ተመልሶ ሀገሩ ተመልሶ መኖር ስለሚፈልግ እኔን እንዲድርለት ሲጠይቅ አባቴ እሽ አላቸው ግራ ገብቶኛል አይሆንም ካልሽ ልጄ አይደለሽም አላውቅሽም አታውቂኝም ብሎ አስፈራርቶኛል አለችኝ እንባዋ እየወረደ,. የምላት ስለጠፋብኝ ዝም አልኩ እኔ እሷን የኔ ማድርግ የምችለው በፍቅር ብቻ ነው .በሌላ ነገር በምንም የኔ ማድርግ እንደማልችል አውቃለው... በተለይ አባቷን በምንም ነገር ማሳመን እንደማልችል ሲገባኝ ተሰፋ የመቁረጥ ስሜት ተሰማኝ ግን እሷን ይበልጥ ማሳዘን ስላልፈለግሁ አይዞሽ በቃ አታልቅሺ አልኳት ስሜቴን እየደበቅሁ,. እኔም አንድ አመት ነው የቀረኝ ለመመረቅ ስለዚህ አብረን እንሆናለን እስከዛ ግን ጠንካራ መሆን ይኖርብናል አልኳት እሽ ግን ያገባሻል የተባልኩት ልጅ አመት ያክል የሚቆይ አይመስለኝም አለችኝ .አይዞሽ ተሰፋ አለን ግን አባትሽን እሽ እንዳትያቸው ቆይ እያልሽ ትንሽ እንዲቆይ አድርጊ,ሜላቴ የኔ ፍቅር አፈቅርሻለው ላጣሽ አልፈልግም አልኳት,.አቀፈችኝ አፈቅርሀለው እኔም ላጣህ አልፈልግም አለችኝ., ሜላት ድንገት ስልኳ ጮኸ አባቷ ነበሩ ስልኳን አነሳችው የት ነሽ የሚል ጥያቄ አቀርብላት ሰላምም ሳይሏት አለው እዚሁ ቢሮ አካባቢ ነኝ አለቻቸው የት እንዳለሽ አውቃለው እዛ የድሀ ልጅ ጋ ነሽ አይደል ሲሉ እኔና ሜላት አይን ለአይን ተያየን,........ ⚡️⚡️ ⚡️ የድሀ ፍቅር⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️                                  በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ                                                             🔺ክፍል 🔫🔫  እኔና ሜላቴ አብረን እየተነጋገርን ማልቀስ እንደሌለባት እየመከርኳት እያለ ድንገት የሜላት ስልክ ጮኸ አባቷ ነበሩ ስልኩን እንዳነሳችው ሰላም እንኳን ሳይሏት የት ነሽ አልዋት .ሜላትም እረጋ ብላ አባቢ እዚሁ ቢሮ አካባቢ ነኝ መጣሁ አለች በትህትና .አትዋሽ ውሽታም ከዛ ከድሀ ልጅ ጋ ነሽ አይደል ብለው ጮሁ እኔና ሜላት አይን ለአይን ግጥምጥም አልን ደነገጠች .እሽ መጣሁ ብላ ስልኩን ዘጋችው., ሜላት አይኔን ለማየት አቅም አጣች እንደአቀረቀረች ይቅርታ ውዴ አለችኝ። የአባቷ አባባል ምንም ቢያበሳጨኝም እሷን ግን ማስከፋት አልፈለግሁም.ተጠግቼ አቀፍኳት ካቀረቀረችበት ቀና አድርጌ ግንባሯን ሳምኳት በቃ ችግር የለውም አትጨነቂ እሽ የኔ ፍቅር አልኳት .አዝናለው የአባቴን ይሄንን መጥፎ ባህሪ መቀየር አልቻልኩም አለች ችግር የለውም አትዘኚ ይበልጥ እንዳይቆጡ ሂጂ አልኳት እሽ ብላኝ ተነስታ ሄደች., እኔም ከሄደች በኃላ ብዙ ነገር አሰብኩ .እኔና ሜላት ስንለያይ ቻው ብላኝ ስትሄድ አንገቷን ግንባሯን ከንፈሯን ሳልስማት ሄዳ አታውቅም ዛሬ ግን ቻው ብቻ ብላኝ ነው የወጣችው .ግራ ገብቶኛል በጣምም ጨንቆኛል .እንዳላጣት በጣም ፍርቻለው ሌላው ቢቀር ውለታዋን በፍቅር መመለስ ነበር ምኞቼ ግን ዛሬ ላይ ልቤ በፍረሀት ተውጧል.አምላኬ አንተ እርዳኝ አልኩ በልቤ። እቤት ውስጥ የነበርኩት እኔ ብቻ ነበርኩ እናቴም ወንድሜም የሉም ስለዚህ ሲመጡ የሚበሉት ምግብ ማዘጋጀት ፈለግሁ ተነስቼ ቤቱን አስተካክዬ ምግብ ሰራሁ ቡና አቀራረብኩ.. ከዛ እናቴን መጠበቅ ጀመርኩ ሜላቴ ግን ከአባቷ ጋር ምን እንደተፈጠረ ምንም አልነገርችኝም አልደወለችልኝም ጨንቆኛል,.. ለሜላቴ ልደውልላት ስልኬን አነሳውና አስቀምጠዋለሁ.. ምናልባት አባቷ አብረዋት ቢሆኑስ ብዬ አስብና እተወዋለው.,ዝም ብዬ በሀሳብ እየተብሰለሰልኩ እናቴና ወንድሜ መጡ እናቴ ቤቱን ስታይ ደስ አላት ዮኒቨርሲቲ ከመሄዴ በፊት ቀድሜ እቤት ከገባሁ ምግብ ሰርቼ ቤት አስተካክዬ ነበር የምጠብቃት., ዛሬም ያንን ስታይ በጣም ደስ አላት ,. የእናቴ ደስታ እኔንም አስደሰተኝ., የእናቴን ደስታ እያየው ድንገት ስልኬ ጮኸ ሜላቴ ነበረች ስልኩን አነሳሁት በር ላይ ነኝ ውጣ አለችኝ ደንግጬ ተንደርድሬ ወጣሁ ከመኪናዋ አልወረደችም መኪናውን ከፍታልኝ ገባሁ .እቅፍ አድርጋ ሳመችኝ ትንፋሽ እስኪያጥረን ድረስ ተሳሳምን ቅድም ሳልስምህ የወጣሁት በአባቴ ተበሳጭቼ ነው ይቅርታ አለችኝ.. ሄዳም ምንም እንዳልተፈጠረና ዋሽታ አባቷን እንዳሳመነቻቸው ነገረችኝ. ሜላቴ ቶሎ መሄድ አለባት ለዛም ነው ከመኪና ሳትወርድ የጠራችኝ በቃ አባቷን ማሳመኗ በጣም ስላስደስተኝ አቅፌ ሳምኳት በቃ መሄድ አለብኝ ብላኝ ከንፈሬን ጉንጫን አይኔን ግንባሬን ስማኝ ሄደች.እኔ ተመልሼ እቤቴ ገባሁ.እራት በልተን ቡናችንን እየጠጣን ለእናቴ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኳት በጣም አዘነች እናቴ አንድ ነገር ማለት ትወዳለች"ሁን ያለው ይሆናል"ሁን ያለው ይሆናል ልጄ አይዞህ ሁሉም ለበጎ ነው አለችኝ እሽ አልኳት., ሜላት አባቷን ቆይ ትንሽ ብላቸዋለች የጋብቻውን ነገር አንስተውባት አያውቁም እኔም ዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ አመት ተመራቂ ነኝ አባቷ ትንሽ ዝም ካሉ የሚያገባትም ትንሽ ከቆየ አሪፍ ነው ብዬ አሰብኩኝ .,ትምህርቴን ጀምሬ በጥሩ ሁኔታ እየተማርኩ ነው ሙሉ ትኩረቴ ትምህርቴ ላይ ነው ,.ምክንያቱም የእናቴን gደስታ ለማየት ነው ድካሜ.,ከክላስ ውጥቼ ዶርማችን ውስጥ ቁጭ ብዬ እያጠናሁ እያለ ስልኬ ጮኸ ሜላት ነበረች🫥 ክፊል 11 ይቀጥላል🫥 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 አደይ
Mostrar todo...
👍 11
𝕊ℍ𝔸ℝ𝔼
❤️ይቅጥል የምትሉ?  like 👍
Mostrar todo...
⚡️⚡️ ⚡️ የድሀ ፍቅር⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️                                  በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ                                                             🔺ክፍል 🔫 ... የማትሪክ ፈተና መጥቶ እኔና ሜላት ውጤት ለመቀበል ትምህርት ቤት ተገናኝን። የማትሪክ ውጤት ቅድሚያ የኔ ወጣ ደስ የሚል ውጤት አምጥቼ አለፍኩ በጣም ደስ እለኝ ሜላትም ደስ አላት። ከቆይታ በሁዋላ የሜላትም ውጤት መጣ.. በሚያሳዝን ሁኔታ ሜላት ግን አላለፈችም ነበር... በጣም ያሳዝናል! አዘንኩ! አብረን እንደምንቀጥል ነበር የማስበው በቃ ግን አልሆነም፤ ሜላት በውጤቷ ብዙም አልተበሳጨችም ይልቅስ የኔ ማለፍ አስደስቷታል። እኔ ግን አዝኛለው። ውዴ አለችኝ እንደከፋኝ አውቃ ወዬ አልኳት.. አየህ የእኔ መውደቅ አሪፍ ነው ምንክያቱም ባልፍ እንኳን አንድ ዮኒቨርሲቲ ላይደርሰን ይችል ነበር... እኔ እዚህ ከሆንኩ ግን ቢያንስ አንተጋ እየመጣሁ እጠይቅሀለው የፈረደበት የአባቴ ድርጅት አለ እዛ መቀጠር እችላለው ለእናትህና ለወንድምህም እኔ ቅርብ ሆኜ እንከባከባቸዋለው አለችኝ። ከሜላት ያልጠበኩትን ነገር ስሰማ በጣም ደነገጥኩ ይከፋታል ብዬ አስቤ ነበር በተቃራኒው ግን አልከፋትም። እሽ! ብያት ተያይዘን እኛ ቤት ሄድን ለእናቴ የኔ ማለፍ አስደሰታት ሜላት እንዳላለፈች ስታውቅ አዘነች ግን ሁሉም ለበጎ ነው። እናቴ እንደተለመደው ነጠላዋን አንጠልጥላ ወደ ቤተክርስቲያን ሄደች። እኔና ሜላትም ያበጠው ይፈንዳ ብለን ተያይዘን ዘና ለማለት ሄድን። ያን ጊዜ ግን ብር ስለነበረኝ እኔ ልክፍል አልኩ ሜላት አልፈቀደችልኝም! እኔና ሜላት ስንዝናና ውለን መሽቶ ልንለያይ ስንል የባንክ አካወንት መክፈት እንዳለብኝና አንዳንድ ነገሮችን ማስተካከል መጀመር እንዳለብኝ ነገረችኝ። ብዙም ሳይቆይ በሜላት ሀሳብ አመንጪነት ተያይዘን ለመዝናናት ከከተማ ወጣን። በሕይወቴ የማልረሳቸዉ ሁለት ድንቅ ቀናት ካሳለፍን በኧላ ወደ አዲስ አበባ ተመለስን። ነገ ማታ እቤት እመጣለው ብላኝ ተለያየን... በማግስቱ ማታ ሜላት እቤት6 መጣች በእጆቿ ፊስታል አንጠልጥላለች ተቀብያት ገብታ ተቀመጠች ገና ከመቀመጧ ምንም እንዳትለኝ አለችኝ በፍረሀት ምንድነው አልኳት። ፌስታሉን ፈትታ ለቢጃማ የሚሆን ቱታ የውጪ ቲሽርት ጅንስ ሱሪ ጫማ ቦርሳ ስልክ ሳይቀራት ገዝታ ነበር የመጣችው ምን ልበል ምንም እንዳትል ብላ አስጠንቅቃኛለች ዝም አልኩ6 አመስግናለው! ከማለት ውጪ... ሜላት ለኔ ከምንም በላይ ነች! በርትተህ ተማር እኔም እየመጣሁ እጠይቅሀለው እነ ማዘር ከናፈቁህ አንተም በእረፍት ጊዜ መጥተህ ታያቸዋለህ ብቻ ትኩረትህ ትምህርትህ ላይ ይሁን አለችኝ። እሽ ማሬ አልኳት! እናቴም ተባረኪ ልጄ አለቻት በርታ እሽ ልጄ አለችኝ በስስት እያየች የእናት እንጀት ሆኖባታል። ወንድሜም ስማ ለኛ እንዳታስብ እሽ እኔ እንዳንተ ጎበዝ እሆናለው አለኝ። እሽ እልኳቸው ሁላችንም እንባ ተናንቆናል! ትንሽ አምሽተን ሜላትን ሸኘኃት። የተለመደውን ግንባሯን አንገቷን ከንፈሯን ስሜ ተለየኃት። ዝግጅቴን አጠናቅቄ የዮኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ ስለነበር ለመሄድ ወሰንኩ። ሜላትም እናቴና ወንድሜ ሆነው ሸኙኝ። እንደምወዳቸው! ነገርኳቸው ሜላቴ አፈቅርሻለው! አልኳት በቃ ቻው ብዬ ተለየኃቸው። የሚያስፈልገኝን ሁሉ ይዤ ጉዞ ጀመርኩ የብቸኝነት ህይወት አንድ ተብሎ ተጀመረ። እኔና ሜላት እንደዋወላለን ሜላቴ እዛው አባቷ መስሪያ ቤት መስራት ጀምራለች። እኔም ትምህርቴን የመጀመርያ አመት የኢንጅነሪንግ ተማሪ ሆኜ ጀምርያለው። ነገር ግን አሁንም አንድ ነገር አስባለው........ ⚡️⚡️ ⚡️ የድሀ ፍቅር⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️                                  በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ                                                             🔺ክፍል 🔫 የአንደኛ እመት የኢንጂነሪንግ ተማሪ ሆኜ ትምህርቴን ጀመርኩ ,ከቤተሰብ ተለይቻለው ሜላቴንም በቀን ሰወስት ጊዜ በስልክ ሰለማወራት እንጂ ናፍቃኛለች ,ለወንድሜ ትንሽዬ ስልክ ገዝታ ሜላት ሰጥታው በሷ ይደውልልኛ በርታ እሽ እኔ ለእናታችን አለውላት ይለኛል የእናቴንም ድምፀ ስስማ ሰላም ይሰማኛል., ትምህርቴን በሚገባ እየተከታታተልኩ ነው ምክንያቱም የእናቴን የወንድሜን የሜላትን ህልም ማሳካት እንዳለብኝና በተራዬ እነሱን ማስደሰት እንዳለብኝ አምናለው ለዛም ነበር በርትቼ የማጠናውና የምማረው.ሜላት አባቷ መስሪያ ቤት እየሰራች ነው በየ ወሩ ትንሽ ብር በባንክ ታስገባልኛለች በቃ የምታደርግልኝ ነገር ከአይምሮዬ በላይ ነው ,እሷ ለኔ የተሰጠች ልዬ ስጦታ ናት,. በዮኒቨርሲቲው ውስጥ ብዙም ጋደኛ አላፈራሁም ምክንያቱም አንዳንዶቹ ልጆች የከተማ ልጅ መሆኔን ይጠራጠራሉ,በዛ ላይ ለነሱ ስልጣኔ ማለት መጠጣት መቃም ማጨስ ነው ያንን ካላደርግሁ ለነሱ ፋራ ነኝ ስለዚህ ማንንም መቅርብ አልፈልግም .አንዳንዴ ከዶርም ከወጣሁ እንኳን ቤተክርስቲያን እንጂ ሌላ ቦታ የትም አልሄድም መሄድም አልፈልግም,. በዚህ ሁኔታ ግማሽ አመት ሆኖ ለእርፍት ወደ አዲስ አበባ መጣሁ ሜላት ልምጣና ልጠይቅህ ስትለኝ እምቢ ያልኳት እንድትንገላታ ስላልፈለግሁ እንጂ ሳትናፍቀኝ ቀርታ አልነበርም ሁሉም ተሰብስበው አገኝኃቸው ሜላት መኪና ተገዝቶላታል ከከተማ ውጪ ግን አይፈቀድላትም ,ሳገኛቸው ደስ አለኝ አብረን ወደ እኛ ቤት ሄድን ቤት ቀይረዋል ነገሮች ሁሉ ተስተካክለዋል ደስ አለኝ እናቴም በቋሚነት የጉልት ስራ እየሰራች ነው,. የእረፍት ጊዜዬን ከቤትሰቤና ከሜላት ጋ በደንብ አሳለፍኩ ቀኑ አልቆ ወደ ዮኒቨርስቲ አመራሁ በቃ ትምህርቴን በደንብ እየተማርኩ ነው በማህል ሜላት መጣች አብረን ዘና አልን ሁለት ቀን ተቀምጣ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰች ,እኔም ወደ ጥናቴ ተመለስኩ የ አንደኛ አመት በደረጃ ደስ በምይል ውጤት ተጠናቀቀ,እኔም ቤተሰቤም ተደሰትን,. ወደ ቤተሰብ ተመለስኩኝ ሁለት ወር ክረምትን በፍቅር አሳለፍን ሜላቴም አብራኝ ነች ከስራ መልስ መኪናዋን ታቆምና በታክሲ እኛ ቤት ትመጣለች አብረን አምሽተን እሸኛታለው ,በእኔና በሜላት መሀከል ምንም አይነት መጋጨትም ሆነ መኮራረፍ ተፈጥሮ አያውቅም በድህነቴ እወዳታለው ከእነ ድህነቴ ትወደኛለች በቃ ፍቅራችን እዚህ ድረስ ነው,. የሁለት ወር ከርምት አልፎ ወደ ዮኒቨርሲቲ ተመለስኩኝ ትምህርቴን በሚገባ መከታተል ጀመርኩ ,በቃ ሜላት እየመጣች እየጠየቀችኝ እኔም በእረፍት ጊዜ እየሄድኩ እያየኃቸው አመቱ ተጠናቀቀ ክረምት ሆኖ ወደ ቤተሰብ ተመለስኩ ሜላትን ግን አላገኝኃትም ነበር ,. እቤት ሄጄ ሜላቴጋ ደወልኩ እመጣለው እቤት ቅድም ስብስባ ሰለነበረ ነው አለችኝ ልቤ ፈራ ማታ ደርሶ እስከምትመጣ ስጠቃት አመሸሁ መጣች ተጠምጥማብኝ አለቀሰች ይሄን ያክል ናፍቄሻለው ብዬ ቀለድኩባት አይ አይደለም አለችኝ ልትነግርርኝ የፈለገችው ነገር እንዳለ ከአይኗ እነበብኩ እንባዋ በጉንጮቿ ላይ መውረድ ጀመሩ ግራ ገባኝ✍️ ክፊል 9 ይቀጥላል📄 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹 አደይ
Mostrar todo...
👍 8
𝕊ℍ𝔸ℝ𝔼
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️           🛡 የድሀ ፍቅር💚 🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣         በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ::    ዛሬ ማታ 2️⃣ሰዓት ላይ ይጠብቁን like😀 share⬅️ ማድረግ እንዳትርሱ
Mostrar todo...
👍 5