cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

𝓱𝓲𝓴𝓾𝓽𝓲𝓷𝓪😘💋😍

Mostrar mĂĄs
Publicaciones publicitarias
196
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 dĂ­as
Sin datos30 dĂ­as

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓ ". #ሚራሃ❤️ ". ✎ፀሐፊ፦ ተውሒዳ ┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛ ┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒ . በ @mame_islamic_post የተዘጋጀ . . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ. ┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚ ┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯ #ክፍል_ሃያ_ሁለት ❷❷ ┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷ "አሰላሙ አለይኩም" ለመመለሾ ሁለቱም ካጎነበሱት ቀና አሉ። ሚራሃ ሳታስበው ከመቀመጫዋ ተስፈንጥራ ተነሳች። በድንጋጤ ፍጥጥ ብላ ከላይ እስከ ታች አየችው። መልሳ ወደ ለይላ ስትዞር ለይላ ፈገግ ታያታለች። አሁንም ወደ እሱ አየች እና አፏን ይዛ እንደህፃን ተንሰቅስቃ ማልቀስ ጀመረች። በድንጋጤ ለይላ ወደሚራሃ ሄዳ "ሚራሃዬ ምን ሆነሽ ነው የኔውድ" ሚራሃ እጇን ጭምቅ አድርጋ ይዛ እያለቀሰች በተማፅኖ "ኢኢምራን አይደለም በይኝ በቃ እሱ አይደለማ በይኝ የታለ ምትጠብቂው ልጅ እእ የታል " ለይላ ግን ምትላት ነገር ግራ ገብቷት ዝም ብላ ታያታለች። ሚራሃ ወደ መፀዳጃ ቤት ፈጠን ፈጠን እያለች ሄደች። ለይላ ልትከተላት ስትል "ቆይ ለይላ እኔ ሄዳለሁ" አላት እና ወደ መፀዳጃ ቤቱ አመራ። ሚራሃ ፊቷ ላይ ውሃ እየረጨች "እሱ አይደለም፣ እሱ አይሆንም" ትላለች እያለቀሰች። ቀስ ብሎ እየተጠጋት "ሚራሃ" አላት። በድንጋጤ ዞረች። "እይኝ በደንብ እይኝ ኢምራን እኮ ነኝ ያንቺ ለምን እንደዚህ ደነገጥሽ? አልናፈኩሽም እእ ሚራሃዬ ከመች ጀምሮ ነው እንዲህ አልቃሻ የሆንሽው፣ አታናግሪኝም" አላት እየተጠጋት። አይኖቿ ተርገበገቡ፣ የድሮው ጊዜ ትዝ አላት የናፈቃት ኢምራን አጠገቧ ቆሟል። ናፍቆቷን ምትወጣበት ነገር አጣች። ወይ አታቅፈው ነገር ብቻ በአይኗ እሱም ላያረካት። "የት ጠፍተህብኝ ነው፤ የት ሄደህብኝ ነው ንገረኝ ባንተ ጉዳይ ተጨንቄ ራሴን አጥቻለሁ፣ አሁን መጥተህ አልናፈኩሽም ወይ ትለኛለህ? አንተን እያሰብኩ ራሴን ወቅሻለሁ፣ ጠልቻለሁ እሱንስ ታውቃለህ? እእ" "እሽሽ አውቃለሁ ሚራሀ እባክሽ አታልቅሽ መምጣቴ እንዲቆጨኝ አታድርጊ እሺ ተረጋጊ ፊትሽን ታጠቢ በዚህ አይነት ሁኔታ መቼም አንግባባም ተረጋጊ እና አብረን ቁጭ ብለን እናወራለን.... እስክትረጋጋ ነገሩ እንዳይጋነን እና የሴቶች መፀዳጃ ቦታ  ስለሆነ ወጣ ብሎ ጠበቃት። ልክ ጨርሳ ስትወጣ አያት እና በፈገግታ ተሞልቶ "አሁን ተረጋጋሽ" አላት። "አዎ ቅድም ድንጋጤው ነው መሰለኝ" "ድንጋጤ ብቻ" "ማለት" "ደስታስ አልተሰማሽም እእ" አላት እየሄደ "እንደውም ዋናው እሱ ነው እንጂ" ለይላ ቅድም እንደዛ ስትሆን የነበረች ልጅ አሁን እየሳቀች ስትመጣ ግራ ገብቷት ታያቸዋለች። አብረው እየተጫወቱ ምሳቸውን ከበሉ በኋላ ማውራት ጀመሩ። ሚራሃ አይኗን ከሱ መንቀል አቅቷቷል። ፀጉሩን በእስታይል ይቆረጥ የነበረው ልጅ አሁን ኖርማል ተቆርጧል፣ ፊቱ ላይ ያለው ፂም እና ኑር ሳይናገር ሙስሊም እንደሆነ ያሳብቃል፣ ሱሪውም አጥሯል። በመሀል የአረብኛ ቃላቶች ጣል ያደርጋል፣ አይኑን ቶሎ ይሰብራል። ከዚህም በላይ ብዙ ለውጦች አሉት። ሚራሃ ሳይታወቃት ፈዛበት ስለነበረ ምንነው? በሚለው አስተያየት ፈገግ ብሎ ቅንድቡን ከፍ ዝቅ አደረገ። እሷም "ምንድነው ይሄ ሁሉ ለውጥ የት ከርመህ ነው የመጣሀው በዛ ላይ ምንም ሳትለን" አለችው "አረ ይሄ ጉደኛ ብታይ" "ለይላ አንዴ እሱን ነው የጠየኩት እሱ ይመልስልኝ ንገረኝ" "እሺ አንዴ መጣሁ" ብላ ተነስታ ወጣች። ╬╬═════════════╬╬ #ክፍል_ሃያ_ሶስት ❷❸ || ይቀጥላል..... ╬╬═════════════╬╬ ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሟር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤ @mame_islamic_post @mame_islamic_post ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤ .↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴. የኛን ግሩፕ ለመቀላቀል👇 . @mamediscussion . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ይቀላቀሉን⇊ ይቀላቀሉን⇊ https://t.me/+U3TA8aXXRwT-Tpoa https://t.me/+U3TA8aXXRwT-Tpoa . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴. For any comment👇
Mostrar todo...
┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓ ". #ሚራሃ❤️ ". ✎ፀሐፊ፦ ተውሒዳ ┗─━─━─━∞◆∞━─━─━─┛ ┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒ . በ @mame_islamic_post የተዘጋጀ . . ልብ አንጠልጣይ ታሪክ. ┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚ ┯━━━━━▧▣▧━━━━━┯ #ክፍል_ሃያ_አንድ ❷❶ ┷━━━━━▧▣▧━━━━━┷ ነገራቶች በዝግታ መሄዳቸውን ቀጥለዋል። ከሀሰን ጋር የተገናኙ ጊዜ ስልክ ቁጥር ስለተለዋወጡ ማታ ማታ በዕለት ተዕለት ይደውልልታል። ይህንን ነገር አትወደውም። ፍላጎት ኖሯት ሳይሆን ግዴታዋ ስለሆነ ነው ምታዋራው። ቆንጅናውን፤ ሀብቱን፤አንዳን አንድ ነገሮች ቢያጓድልም ኢማኑን አትክድም፣ ነገር ግን ይሄ መስፈርት ለሡ በቂ አይደለም። የሷ መስፈርትን ኢምራን ይዞት ሄዶ በራሱ ላይ አጥር ሰርቷል። የሀሰን እና የሚራሃ ሰርግ ማለትም አንድ ላይ  ለመኖር ከመደገሳቸው በፊት ሀሰን ከአባቷ ጋር ተነጋጋግረው አንዳንድ ነገሮችን እስከማስተካከል 1 አመት ብቻ ትጠብቀኝ ብሎ ለምኗል። ይሄ ሚራሃን ቢያስደስታትም ከወር በኋላ ግን ኒካህ ለማሰር እንደተስማሙ ሲነገሯት ነገሩ ታጥቦ ጭቃ ሆነባት። ይሄን ያህል ከራሷ ጋር ተራርቃለች። የሷ ህይወት ልክ እንደ ዲም ላይት ሆኗል። ማብሪያ፣ ማጥፋያውን ሰው ይዞት ሲያበሩባት ደስተኛ እየሆነች ሲያጠፉባት እያዘነች መኖር ጀምራለች። ማብሪያ ማጥፊያውን ለመቀበል አንድ እርምጃ እንኳን አልተራመደችም። በገመዱ ተተብትባ ምትወድቅ ይመስላታል። "ሚራሃ.......ሚራሃ..... አረ ሚራሃ ተነሺ ሱብሂ ደርሷል" አለች የተዘጋውን የሚራሃን ክፍል ለመክፈት እየተቃረበች እየጠራቻት አንድ ሁለቴ ካንኳኳች በኋላ በሩን ስትከፍተው "አኡዙቢላህ ምንሆነሻል የኔ ልጅ እንደዚህ ስጠራሽ እያወቅሽ ነው እንዴ ዝም ምትይኝ" ሚራሃ ሰግዳ፣ ልብሷን ለባብሳ ወንበሯን ከበሩ ፊት ለፊት አድርጋ ተቀምጣ ነበረ ለዛ ነው እናቷ የደነገጠችው። "እማ ሰግጃለሁ ሾል ቦታ ልሂድ" ብላ ተነስታ በሩ ጋር ስትደርስ በደንብ ስትመለከታት የነበረችው እናቷ "በዚህ ሰዐት ሾል ይኬዳል ልጄ ገና አልነጋም እኮ ከሰገድሽ ትንሽ አረፍ በይ እና እንደውም አሪፍ የምትወጂውን ቁርስ እኔ እራሴ እሰራልሻለሁ በይ እረፊ በቃ" ብላት ወጣች። እናትየው ሚራሃን ቀን በቀን ስታያት ያመጣችው ለውጥ ግራ አጋብቷቷል። ወሩ እየተቃረበ ይሀው ቀን ከተቆረጠ ሳምንት ሆነው። ሚራሃ ሾል ቦታ ሆና ሂሳብ እያሰላች ከስልኳ ጥሪ ገባ። ስታየው ለይላ ናት። አነሳችው። "አሰላሙ አለይኩም ሀቢቢቲ" አለች ለይላ "ወአለይኩመ ሰላም የኔ ለፍላፊ እንደምወድሽ ግን ታውቂያለሻ" "ማንን እኔን ስልኩን አላየሽውም መሰለኝ ባልሽ ከመሰልኩሽ ሀሀሀ" "እንዴት ነሽ" "አልሃምዱሊላህ አለውልሽ በአስቸኳይ አሁኑኑ እንድትመጪ" "እንዴ ለምን ምን ተፈጠረ" "ያ ባለፈው የነገርኩሽ ልጅ ከሱ ጋር ዛሬ ቀጠሮ አለብኝ ብቻዬን ደሞ አልሄድም በአላህ ቶሎ ነይ" "እንዴ አሁን እኮ ሾል ቦታ ነኝ መቼ ከሰዐት ነው ምመጣው" "አረ አሁን ነው ምፈልገው" "እሺ ልብሴን እንኳን ልቀየር ጠዋት ዝም ብዬ ለሾል ነው የለበስኩት" "አረ አንቺ ፌስታልም ብትለብሺ ያምርብሻል፣ ችግር የለውም ብቻ አንቺ ቶሎ በይ ከፈለክሽ የራይድ እኔ ከፍላለሁ" "እሺ ቦታው የት ነው" ብዙም ሳትቆይ በተባባሉበት ቦታ ከች አለች። ስትመጣ ነይ ብላ ወደሷ ጠራቻት እና ሚራሃ ለመግቢያው ጀርባዋን ሰጥታ ተቀመጠች። "አንቺ ጅል እሱ ሳይመጣ ነው እንዴ አንቺ ምትመጪው" "ምን ላድርግ ከጨራረስኩ በኋላ መቼስ ቤት ቁጭ አልል" "እሱ ይሻልሽ ነበረ ደግሞ አርፋጅ ነው እንዴ? ተይ አርፋጅ እንኳን ይቅርብሽ" "አረ አሁን ይመጣል 5 ደቂቃ ብሎኛል" "እስከዛ በቃ የሆነ ቦታ እንደበቅ እና ሲመጣ እኛም እንመጣለን አይሻልም" "ምን እስከዛ ይሀው መጣልሽ" አለቻት ወደ መግቢያው እየተመለከች። "አትይው አትይው አውቀሽ ከኔ ጋር በወሬ የተጠመድሽ ነው መሆን ያለብሽ" "አረ ሳቄ መጣ እሱም መጣ" "አንቺ የኔንም አመጣሽው ጥርሽን ይርገፍ" "አሰላሙ አለይኩም" ለመመለሾ ሁለቱም ካጎነበሱበት ቀና አሉ። ╬╬═════════════╬╬ #ክፍል_ሃያ_ሁለት ❷❷ || ይቀጥላል..... ╬╬═════════════╬╬ ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመዶ ሟር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን! ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤ @mame_islamic_post @mame_islamic_post ╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤╧╤ .↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴. የኛን ግሩፕ ለመቀላቀል👇 . @mamediscussion . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴ ይቀላቀሉን⇊ ይቀላቀሉን⇊ https://t.me/+U3TA8aXXRwT-Tpoa https://t.me/+U3TA8aXXRwT-Tpoa . ↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴. For any comment👇
Mostrar todo...
ግን ደሞ ግን ደሞ ዛሬ ነገን ይወልዳል ቀን እንደቀልድ ይነጉዳል እያዘነችም ቢሆን ስቃ ታያታለህ አንድ ቀን ይህ ሰውነቷ ደርቆ ትሞታለች በህመም ታንቃ የእውነት መስሎ የውሸት ስቃ #Elsita @Mapoem2 @Mapoem2
Mostrar todo...
00:37
Video unavailable
Yega jema🤣😂🙄🤦‍♀🫣🤪🤪😘😘😘 Konjeyw new 😛😛😛😛
Mostrar todo...