cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

⚜ World 9 ⚜ 📚🎵📸💾🎞

ማንበብ የምቶዱ ይህንን ቻናል ተቀላቀሉ።

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Advertising posts
189Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ያልታየው ጀርባ ክፍል 1 ሁሉም ሰው ቀኑ ስለጨላለመ የስራ ቦታውን እንዲሁም የቤቶችም በሮች እየዘጋጋ ነው። አየለ ግን ቀኑን ሙሉ ተኝቶ ስለዋለ ለእሱ ገና እየነጋለት ነው የሁል ጊዜም ልማዱ ሌሊቱን ሙሉ ሱጠጣ አድሮ ሊነጋጋ ሲል ነው የሚተኛው ለምን እንደሚጠጣ እንኳን በቅጡ አያቀውም ለምን ትጠጣለህ ? ብሎ የሚጠይቀው ሰው ካለ በጭንቅላቱ ፈርዷል ማለት ነው። ምክንያቱም ጥያቄውን ለራሱ እንኳን መልስ ያጣለት ስለሆነ በአቅራቢያው ባገኘው ድንጋይ አንስቶ ነው የሚፈነክተው በዙሪያውም ቢሆን የኔ የሚለው ወዳጅ ዘመድ የለውም ጓደኞቹ እራሱ ቢሆኑ እንደማይለወጥ ስለገባቸው አንድ አንድ እያሉ ከዳንኤል በስተቀር ሸሽተውታል ከአባቱ በውርስ ባገኛት አንዲት ልትወድቅ ትንሽ ጊዜ የቀራት ቤት ውስጥ ነው የሚኖረው እርግጥ አየለ ይሄ ባህሪው የመጣው በጣም የሚወዳት የሚያፈቅራት የወደፊት የትዳር አጋሬ ትሆናለች ብሎ ከሚያስባት ፍቅረኛው ከውጭ የመጣ ሰው ተጋብታ ጥላው ከሀገር ስለወጣች ነው እሷም ብትሆን ልትለየው አትፈልግም በጣም ነው የምትወደው። ነገር ግን ቤተሰቦቿ እሱን አግብታ ሄዳ ህይወታቸውን እንድትለውጥላቸው ጫና ስለሚያደርጉባት እንጂ ይሄን ሁሉ ነገር ግን እሱ አያቅም ምክንያቱም ይህን እንኳን የማስረዳት ጊዜ ስላልነበራት ቢሆንም ግን እሷ ደብዶቤ ፅፋ እንዲደርሰው ልካ ሳይደርሰው ቀርቷል። ምግብ ቢሆንም አንዳንዴ ጎረቤቶቹ በሀዘኔታ ትንሽ ነገር ጣል ካረጉለት እሷን በልቶ ይውላል እንጂ በቅጥ እራሱ ምግብ አይበላም ብዙውን ጊዜም ጠጥቶ ስለሚያድር ሲነሳ ጨጓራው ስለሚላጥ ብር ካገኘ ወተት ገዝቶ ጠጥቶ ይውላል። ብርም ቢሆን በወር አንዴ ዳንኤል የሚባለው ጓደኛው ትንሽም ብትሆን ይሰጠዋል እንጂ ቆሚ የሆነ የገንዘብ ምንጭ የለውም።
Mostrar todo...
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) ? በፎቶው የምትመለከቱት ዶ/ር ታዘባቸው ውዴ ይባላል። በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪውን ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል። ሁለት አመት ካገለገለ በኃላም ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) በመቀላቀል ትምህርቱን እየተከታተለ ይገኛል። (የማህፀንና ፅንስ ስፔሻላይዜሽን) ዶ/ር ታዘባቸው በአንደኛው አይኑ ላይ ከልጅነት ጀምሮ መሸዋረር ያለበት ሲሆን በዚህ ምክንያት 4 ዓመታት የደከመበት ትምህርቱን እንዲያቋርጥ እንደተነገረው አመልክቷል። ዶ/ር ታዘባቸው ትምህርት ለማጠናቀቅ እጅግ ጥቂት ጊዜ ቢቀረውም ባላሰበውና ባልጠበቀው ሁኔታ ትምህርት እንዲያቆም እንደተነገረው አስረድቷል። ለ4 ዓመታት አንድም ነገር ሳይጠየቅ የቆየው ዶ/ር ታዘባቸው በድንገት ሊመረቅ ጥቂት ጊዜ ሲቀረው የአይን ምርመረ እንዲያደርግ ወረቀት እንደተሰጠው፤ በኃላም ምርመራ አድርጎ ውጤቱን እንደተነገረው ምንም እንኳን ለስራው እንቅፋት ባይሆንም ከአሁን በኃላ ትምህርት መቀጠል አትችልም / አልያም ዲፓርትመት ትቀይራለህ መባሉን ገልጿል። ላለፉት 4 ዓመታት የቀዶ ጥገና ስራዎችን ሲሰራ የነበረው ዶ/ር ታዘባቸው ውጤቱ ለህክምና ስራው ችግር ያመጣል ወይ ? እስከ ዛሬ ሰርቻለሁ አሁን ምን ችግር መጣናነው የማልቀጥለው እያለ ቢጠይቅም ምላሽ አላገኘም። በሂደቱ ብዙ ውጣ ውረዶች የነበሩ ሲሆን እስካሁን መፍትሄ እንዳላገኘ ገልጾ ዩኒቨርሲቲው ውሳኔውን በድጋሚ አጢኖ ትምህርቱን አስጨርሶ እንዲያስመርቀው አልያ ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስደው ገልጿል። ያንብቡ : https://telegra.ph/Dr-Tazebachew-Wudie-07-17 @tikvahethiopia
Mostrar todo...
#MoH ሚሊኒየም አዳራሽ ለሚድሮክ ተመለሰ። 2 ዓመታት የኮቪድ -19 የህክምና እና የድንገተኛ ምላሽ ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል የቆየውን አዲስ ፓርክ /የሚሊኒየም አዳራሽ/ ለባለቤቱ ተመለሰ። ጤና ሚኒስቴር ሚሊኒየም አዳራሽን ከምስጋና ጋር ለባለቤቱ ለሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አስረክቧል። የጤና ሚኒሰቴር ሚኒስትር ዶከተር ሊያ ታደሰ ማዕከሉን ለሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባስረከቡበት ወቅት ምስጋና አቅርበዋል። በተጨማሪ ፦ " ዛሬ የኮቪድ-19 የህክምና እና የድንገተኛ ምላሽ ማዕከሉን ዘግተን ወደነበረበት የምንመልሰው ኮቪድ ስለጠፋ ሳይሆን አገልግሎቱን በሌሎች የጤና ተቋማት ለማቅረብ የምንችልበት አቅም ስለፈጠርንና በመላ ሀገሪቱ የክትባት ሽፋንን በማድረስና የበሽታውን ጉዳት መቀነስ በመቻሉ ነው " ብለዋል፡፡ በቀጣይም ክትባቱን ያልወሰዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዲወስዱና ጥንቃቄያቸውን ሳይዘናጉ እንዲተገብሩ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
" ... ከወቅቱ የዋጋ ንረት ጋር ሊሄድ የሚችል አዲስ ታሪፍ ለማውጣት ጥናት እያደረኩ ነው " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፤ አሁን በሥራ ላይ ያለውን ታሪፍ በማሻሻል ከወቅቱ የዋጋ ንረት ጋር ሊሄድ የሚችል አዲስ ታሪፍ ለማውጣት ጥናት እያካሄደ መሆኑን ገልጿል። በ2010 ዓ/ም የፀደቀውና አሁንም በሥራ ላይ ያለው የኤሌክትሪክ ታሪፍ መጀመሪያ ላይ ሲወጣ በወቅቱ ከነበረው የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነት ጋር ታሳቢ በማድረግ የተደረገ ጭማሪ ቢሆንም አሁን ገበያ ላይ ያለው የግብዓት የዋጋ ንረት በታሪፍ ላይ ማስተካከያ ለማድረግ እንዳስገደደ ገልጿል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብዙወርቅ ደምሴ ፤ በ2010 ዓ.ም. የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ በኑሮ ውድነቱ እየተዋጠ በመሆኑ በቀጣይ ለሚታሰቡ የመልሶ ግንባታ ሥራዎች የታሪፍ ማሻሻያው በጣም አስፈላጊ ነው ሲሉ መናገራቸውን ሪፖርተር ፅፏል። ተቋሙ እየሰጠ ባለው አገልግሎት ዙርያ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ያግዘኛል በማለት በአራት ዙር በአራት ዓመታት እንዲጠናቀቅ ተደርጎ በ2010 ዓ.ም ይፋ ያደረገው የታሪፍ ማስተካከያ በታኅሳስ 2014 ዓ.ም. የመጨረሻ ዙር የሆነውን ጭማሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ በተለይም በ2013 ዓ.ም. እየተገባደደ ባለው በ2014 እየታየ ያለው ዋጋ ንረት የሚገመት እንደነበር አለመሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ለጋዜጣው ተናግረዋል። በአገር ውስጥ ሆነ በዓለም አቀፍ ገበያ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ በመኖሩ ምክንያት የኃይል ቆጣቢና መቆጣጠሪያ መሣሪያዎችን ወደ አገር ውስጥ ገዝቶ ለማስገባት ብዙ ሚሊዮን ዶላሮች በማስፈለጉ የታሪፍ ማስተካከያ በከፍተኛ ሁኔታ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል። በመሆኑም በዓለም ካለው የፖለቲካ እንዲሁም የገበያ አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ የዋጋ ንረት በመፈጠሩና ከኤሌክትሪክ ከደንበኞች የሚሰበሰበው ወርኃዊ ታሪፍ አገልግሎቱን አሻሽሎ ለማቅረብ በቂ ባለመሆኑ፣ ወቅቱን የጠበቀ የታሪፍ ማሻሻያ በማድረግ የግብዓት ዕቃዎችን በመግዛት ለኅብረተሰቡ መብራት እንዳይቆራረጥ የመልሶ ግንባታና የማስፋፊያ ሥራዎች አሉብን ብለዋል፡፡ ነዳጅ ዋጋ ላይ በየወሩ የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚደረገው ሁሉ፣ በኤሌክትሪክ አገልግሎትም ወቅቱን የጠበቀ ማሻሻያ በማድረግ የመልሶ ግንባታና ማስፋፊያ ሥራን ማከናወን እንደሚያስፈልግ አክለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በዋጋ ንረቱ ምክንያት ወቅቱን የጠበቀ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ አዲስ የታሪፍ ፕሮፖዛል እየተዘጋጀ እንደሆነ የገለጹት አቶ ብዙወርቅ፣ በቀጣይ ፕሮፖዛሉ እንደተጠናቀቀ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ የታሪፍ ማስተካከያው ወደ ሥራ ይገባል ብለዋል፡፡ #ሪፖርተር @tikvahethiopia

#Sudan በጎረቤት ሀገር ሱዳን ፤ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በሚቀርበው ብሉናይል ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 31 ሰዎች ሲገደሉ 39 ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው በርካቶችም ሰላም ፍለጋ መሸሻቸው ተሰምቷል። ግጭቱ የጎሳ ግጭት እንደሆነ ተገልጿል። በበርቲ እና ሃውሳ ጎሳዎች መካከል በተነሳ የመሬት ውዝግብ ምክንያት በሮሰሪስ ከተማ ውስጥ ከትናንት በስቲያ በተፈጠረው ግጭት ቢያንስ 31 ሰዎች ሲገደሉ፣ 39 ሰዎች ቆስለዋል በርካታ ሱቆች ተቃጥለዋል። በሁለት ግለሰቦች መካከል የተነሳ አለመግባባት ሳቢያ አንድ ሰው (በግብርና ስራ የሚተዳደር) ከተገደለ በኃላ ግጭቱ ወደ ጎሳ ግጭት ተቀይሮ ነው የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈው ተብሏል። ምንም እንኳን ሱዳን በአካባቢው ተጨማሪ ወታደሮችን ብታሰማራም ግጭቱ እስከ ትላንት ከሰአት በኋላ ቀጥሎ መዋሉ ታውቋል። መንግስት ደም አፋሳሹን ግጭት ለማስቆም ችግር ባለባቸው ቦታዎች ላይ የምሽት ሰዓት እላፊ አውጇል። #CGTNAFRICA #AlJazeera #AP @tikvahethiopia
Mostrar todo...
ስለሀገራችን #የታላቁ_ህዳሴ_ግድብ የመከሩት የአሜሪካው እና የግብፁ ፕሬዜዳንት ምን አሉ ? የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ። ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የአረብ አገራት ጉባኤ እየተካሄደ ሲሆን ከጉባኤው በተጓዳኝ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ጋር መወያየታቸው ተሰምቷል። ሁለቱ መሪዎች ትላንት ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በተለያዩ ጉዳዮቻቸው ላይ መወያየታቸው ነው የተሰማው። መሪዎቹ ውይይት ካደረጉባቸው ጉዳዮች መካከል ሀገራችን በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የሕህዳሴ ግድብ አንዱ ነበር። ፕሬዝዳንት አል ሲሲ አገራቸው የግድቡን የውሃ ሙሌትና ቀጣይ ሥራ በተመለከተ የግብፅን የውሃ ዋስትና በሚያስከብር ሁኔታ “አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረስ” ያላትን ጽኑ አቋም ለባይደን ገልፀዋል ተብሏል። ፕሬዝዳንት ባይደንም አሜሪካ የግብፅን የውሃ ዋስትና እንደምትደግፍ እንዲሁም ለአካባቢው ሰላምና ብልጽግና አስተዋጽኦ የሚያደርግ፣ የሁሉን ወገኖች ጥቅም የሚያስከብር ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ላይ እንዲደረስ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ሁለቱ መሪዎች ባለፈው ዓመት መስከረም ላይ “በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው እና በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት” በግድቡ ሙሌትና ቀጣይ ሥራ ላይ ሳይዘገይ ከስምምነት የመደረሱን አስፈላጊነት መናገራቸው ተሰምቷል። መረጃውን የአሜሪካ እና ግብፅ ፕ/ት ፅ/ቤቶችን ዋቢ አድርጎ ያስነበበው ቢቢሲ ነው። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
ፎቶ ፦ ትላንትና ለሊት በተካሄደው የሴቶች 1500 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ሁሉም አትሌቶቻችን ወደ ፍፃሜው ማለፍ ችለዋል። 🇪🇹 ጉዳይ ፀጋይ 🇪🇹 ሂሩት መሸሻ 🇪🇹 ፍሬወይኒ ኃይሉ የሴቶች 1,500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ሰኞ ከንጋቱ 11:50 ላይ ይደረጋል ። በወንዶች የ1500 ሜትር ማጣሪያ ደግሞ 🇪🇹 ሳሙኤል ተፈራ 🇪🇹 ታደሰ ለሚ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ ችለዋል። 🇪🇹 ሳሙኤል ዘለቀ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፍ #ሳይችል ቀርቷል ። የወንዶች 1,500 ሜትር የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ዛሬ ከለሊት 11:00 ላይ ይደረጋል። Photo Credit : Gettyimages @tikvahethiopia
Mostrar todo...
ፎቶ ፦ ለተሰንበት ግደይ ለሀገሯ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 በኦሬጎን ዓለም ሻምፒዮና የመጀመሪያውን ወርቅ ካስገኘች በኋላ የተወሰዱ ፎቶዎች። በድጋሚ እንኳን ደስ አለን 🇪🇹 ❤️ ! @tikvahethiopia @tikvahethsport
Mostrar todo...