ፊደላት™
ፊደል ^ ቃል ^ ስሜት = ምንም ይሁን ብቻ ተንፍስ! ° ° °°°°°° ~ በግጥሞቻችን ~ በልቦለዶቻችን ~ በፍቅር ደብዳቤዎቻችን ~ በፎንቃ ክሊኒኮቻችን ፨፨፨ ይዝናኑ ፣ ይማሩ ፣ ይታከሙ ፨፨፨፨ ° ° °°°° አስታየቶቻችሁ + ጥያቄዎቻችሁ > @AB_zlike217 < ይላኩልን።
Mostrar másEl país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
1 503Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days
- Suscriptores
- Cobertura postal
- ER - ratio de compromiso
Carga de datos en curso...
Tasa de crecimiento de suscriptores
Carga de datos en curso...
በሚገባ ያንብቡ
#የበአል ስጦታ
በመጀመሪያ ለመላው ሙስሊም ወገኖቻችን እንኳን ለኢድ አል-አድሃ(አረፋ) በአል በሰላም እደሳችሁ ማለት እንወዳለን ☪
ድርጅታችን ኢትዮቴሌኮም በአሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የካርድና የጥቅል ሽልማቶችን አዘጋጅቷል። ተሸላሚ ለመሆን ቻናላችንን በመቀላቀል ሌሎችን መጋበዝ ብቻ ነው 👇👇
🔗የኢትዮ ቴሌኮም የበዓል ስጦታ ቻናል ይቀላቀሉ 📌
✅ ሽልማቱ በ 3 ደረጃ ነው :
1ኛ. ከ 100 ሰው በላይ ሼር ለሚያደርጉ 5ሺ ብር ጥሬ ገንዘብ በአካውንት እናስገባለን።
2ኛ. ከ 50 ሰው በላይ ሼር ካደረጉ 2500 ብር ገቢ ይደረግሎታል።
3ኛ. ከ 25 ሰው በላይ ሼር ለሚያደርጉ የ 1663 ብር- የአንድ ወር ያልተገደበ የድምፅ እና የኢንተርኔት ጥቅል
( ብሩን ከፈለጉ በአካውንት ይላክሎታል)
ተሸላሚ ለመሆን ይሄን መልዕክት ኮፒ አድርገው ለወዳጅዎ መላክና ፌስቡክ እና ቴሌግራም ግሩፖች ላይ ሼር (#forward) ማድረግ ብቻ ነው ‼️
ማሳሰቢያ! ተሸላሚ ለመሆን የቻናሉ አባል መሆን አለብዎት join ካላረጉ ለምን ያህል ሰው share አንዳደረጋቹ መረጃ ማግኘት አንችልም
@ethio_telecom_holiday_gift
🔗የኢትዮ ቴሌኮም የበዓል ስጦታ ቻናል ይቀላቀሉ 📌
እኔ አልሰክርህም
~~~~~~~~~
(✍ አብርሃም ታደለ አጥራ)
፧
#ነገሩ_ነው_እንጂ
እኔማ አልሰክርም
ሰክሬህም አላውቅም
ደጋግመህ ብትወጋኝ - ሺህ ስለት እየሳልክ
አንዳችም ሳትሰስት
መሬት ብትጎትተው - ስጋዬን እየጣልክ
እመነኝ አለሜ
አቅሉ እንደሳተ - መቼም አልጣላክ፣
መጠጥም ብትሆን - የምጋተው አልኮል
ቢነግሩኝ ክፋትህ - በወሬ በተንኮል
ፈፅሞ እመነኝ - ማንንም አልሰማም
እኔ ስካር እንጂ - መስከርን አልጠላም፤
፡
#እናማ_ስነግርህ
ሺህ ሰሚ እያየሁ - እልፍ ሺህ ሰካራም
ሀገር ሙሉ በርሜል - የአልኮል ጎተራም
ነገሩ ነው እንጂ
ሰው ሲሰክር እንጂ
ሲጠጣ አይደለም - ሚባለው ሰካራም፤
፡
ግን ደሞ አለሜ
ይሄን ሁሉ ግዜ - ያለፉት ዘመናት
ተላውሰን ስንጠጣ - ፍቅርን እያየናት
መች እንሰክር ነበር - ከሞቅታ አልፎ
እጅህና እግሬ - ሽቅብ ተጠላልፎ
መችስ እንደ ጠጪ - ትጠግበኝ ነበረ
ከውስጡ አልቄ
የጨበጥከው - ጠርሙዝ ካልተሰባበረ
ታድያ ያገሬ ሰው
ምን ነገር አገኘው - ምንስ ነካው ዛሬ?
ሰክራለች እያለ - የሚነዛው ወሬ፤
፡
ቲሽ! ኤ ... ጭ! - ምድረ አሽቃባጭ
እኔማ አልሰክርም!
ጭራሽ አልሰክርህም!
እንደውም ሚገርምህ ...
አንደኛው ሰከረች
ሌላኛው በፍፁም - ፀንቶ ክርክሩ
ሲከሱኝ በውድቅት - መልሰው ሲመክሩ
አንድ እጄን ሲፈቱ - አንድ እግሬን ሲያስሩ
ቀኝ ግራው ገብቷቸው
ብርጭቆዬን ነጥቀው - ቀድመውኝ ሰከሩ፤
.
.
.
.
#በሰከረ_ሳይሆን_በሰካራም_አለም
ነገሩ ነው እንጂ - ገመድ ሰው አያስርም
አንተ አልኮል ሆነህ - ዘመኔን ስጠጣህ
እድሜዬን ብከርም...
እመነኝ አለሜ፡
አያሰክረኝ ብዬ - በመጠጥ አልኮራም።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ፊደላት_ኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
💐🌷🌾🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌾🌷💐
ልሂድ ያልሽ ለታ
💐እንዴት ነህ ስትዪኝ ያኔ የመለስኩልሽ
🥀ከሌለሽ የለሁም ብዬ የነገርኩሽ
❣እንዳትረሺው ብዬ ዛሬም ልድገምልሽ
🌺እውነቴን ነው ፍቅሬ ከሌለሽ የለሁም
🌼አንቺ ስላለሺኝ አሁን ላይ አልሞትኩም
💝ግን ወዴ ካጣሁሽ በህይወት እያለው
🌸አልቅሰሽ ሳትቀብሪኝ በቁሜ እሞታለው
💐እስኪ አስቢው ውዴ በቁም ከሞትኩብሽ
💋አላቅፍሽ፣ አልስምሽ ግጥም አልፅፍልሽ
💖ባካል አላገኝሽ ወይ አልደውልልሽ
😞ያለሁበት ጠፍቶኝ ስንከራተትልሽ
🙈እናቴ አልቅሳ በቁሜ አትቀብረኝ
😁ወይ ድጋሜ አርግዛ እኔኑ አትወልደኝ
💔ሞትና ቀብሬ ተራርቀውብኝ
😔እውነት ያበደ ሰው ሆኜ እቀራለውኝ😔
💚አንቺ የሄድሽ ጊዜ ገነትንና ሲዖልን እዚው አየዋለው
💙ገነትን በትዝታ ሲዖልን በእብደት ውስጥ እመለከታለው
❤️ልሂድ ያልሽ ጊዜ ቀኑ ይጨልማል
💘ጨረቃ ጠዋት ላይ ፀሀይ ማታ ይወጣል
🤦♂ተፈጥሮ በኔ ላይ ይገለባበጣል
🙇ውዴ ሆይ ልሂድ ያልሽ ለታ
👽ቀን ላይ እየሞትኩኝ እኖራለው ማታ
🙇አንቺን እያሰብኩኝ ሁሌ በትዝታ
💓ስለዚህ ፍቅሬ ሞቴ ያማረሽ ጊዜ ምንም እንዳትዪኝ
💘3 ፊደል ተናግረሽ "ልሂድ"ብቻ በይኝ
#መልካም_ቀን
@Fidelat
@Fidelat
@Fidelat
💐💐💐🌷🌷🌷🌹🌷🌷💐💐💐
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
💐💐🌾#ፊደላት ኢትየጵያ💐🌾💐
እነሆ ተመለስን
እለተ ማከሸሰኞ 18/2/2012 ዓ.ም
💐🌷💐🌸 ፊደላት_ቅምሻ
ማንም ሰው በግዜ ሚዛን ላይ ሲወድቅ ጥሩ ይሁንም መጥፍ አንድ የተለየ ምዕራፍ እንደሚያገኝ እርግጥ ነው። እኛም ያገኘነውን አካፍለን ከናንተም ለመቀበል እነሆ ወደ ተወዳጁ ቻናል #ፊደላት ተመልሰናል፡
🌷🌺🌹 #ትርታዊ_ግጥሞች
🌷💐🌸 #የፍቅር_ልብ_ወለድ
🌺🌹🌝 #ፊደላት_ቅምሻ
🌸🍁🌷 #የፍቅር_ደብዳቤዎቻችሁ ከናንተው ለናንተው ማድረስ ጀምረናል🌷🌷🌷🌝🌺🌝🌝🌝🌝🌷🌷🌷
።።።።።።። እኔኮ እንዳንቺ ።።።።።።
:
እኔኮ እንዳንቺ
ከረሀብ ማያስጥል...
የስንዴ እንክርዳድ
ዳቦው ያማረለት - የታደለ ምጣድ
አይደለም የምሻው፤
፡
እኔኮ እንዳንቺ
ክብሬን ክብሬን እያልኩ
ነፍሴን አጠልሽቼ - ለስጋ እየማልኩ
ጎኔ ሚያንዣብብ
ቆርቆሮ መኪና
ድክርቲ ቦርከና
አይደለም የምሻው፤
:
እኔ 'ምፈልገው...
አፍቃሪ ልብ ያላት
ታማኝ ነፍስ ያደላት
ሴት የሆነች እንቁ - ጌታ የቀመማት
ስጦታዬን እንጂ
ገንዘብ ማቴርያል - መች ሊታውቀኝ
መሻቴ ታማኝ ነው
ክህደትና በደል - ደጋግሞ ሳያንቀኝ።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
።።።።።። የወደድኩሽ ሰሞን ።።።።።።
፧
የወደድኩሽ ሰሞን - እኔ አልነበርኩም፣
ተዘረፍኩኝ እንጂ - አፈቀርኩ አላልኩም፣
የወደድኩሽ ሰሞን...
ሁሉም ተራ ተራ
ሆኖብኝ አለፈ - ትርፍና ኪሳራ፣
፡
የወደድኩሽ ሰሞን፡
ውሀም ትን ይለኛል - እህልም አልወቃ፣
እንዳረገዘች ሴት - ወደላይ ነው በቃ፣
ወየው ከንቱ ሲቃ!
አቤት ያልታደለ - የማይዳልጥ ጭቃ፣
አዘንኩኝ ላጣኝ ሰው!
እራሱን ሊሞላ - እኔን ለቀነሰው፣
አዘንኩለት እኔ፣
ተስፋው ጨላልሞበት - ሲያቆጠቁጥ ቀኔ፣
የእውነት አዘንኩኝ፤
፡
ግን...
የጠላሁሽ ሰሞን፡
ስክሪፕቱ አለቀ፣
በምዕራብ የወጣው - በምስራቅ ጠለቀ፣
ምላሴ ላይለፍፍ - ከልቤ ተፋቀ፣
አዎ ተፋፋቀ፤
ያስጠላሽኝ ሰሞን፡
የሆነውን ሁሉ - ዞር ብዬ አስቤ፣
ፊልም እንደነበረ - ነገርኩት ለቀልቤ፣
አንቺን እንዳይጠይቅ - ዳግመኛ ስምሽን፣
Cut አድርጌ ጣልኩት - የነበረው Action፣
ብቻ...
ያፈቀርኩሽ ሰሞን፡
የወደድኩሽ ሰሞን፡
ስሜቶቼ ሁሉ - ላንቺ ቢዘምሩም፣
ዛሬ ከጠላሁሽ...
አንድ ካንድ ሲቀነስ - ዜሮ ነው ድምሩ፤
አለቀ።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
💜💜💜💖💖💖💖💜💜💜💜
#የፊደላት_ቤተሰቦች ለረጅም ግዜ
ያቋረጥነው፡
#ፊደላት_ቅምሻ
#ፊደላት_ድርሰት
#ፊደላት_ግጥም
#ፊደላት_ነጥብ
#ፊደላት_ደብዳቤ
ከናንተው ተቀብለን ለናንተው ደርስ ነው፤ ምን ትላላችሁ? ይጀመር እንዴ?
💐💐💐💐💚💛❤💐💐💐💐
💖💖💖💖🌷🌷🌷💖💖💖💖
👌 55
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ፊደላት 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
💐🌷💐 #ፊደላት_ቅምሻ 💐🌷💐
🌹🌷 #የፊደላት_እንቁዎች. ..
ለማስመሰል የምንጠቀማቸው ቀመሮች
ከኛ ጋር ሲዋሀዱ ከፊል ማንነታችን
ለሁሉም ሰው አስመሳይ ሆኖ ይታያል፡
ማስመሰል እራሱን የቻለ ጥበብ ቢሆንም
ዙርያችንን ከቦ ሳያጠበን ነገን እንደዛሬ
በተስፋ ብሩህ አስመስለን.. ከማስመሰል
ጥገኝነት እንውጣ።
💐💐💐 @Fidelat
@AB_zlike217
💜💖💐💐💜💖🌷💖💜💐💐💜
💚💚💚💚💛💛💛💛❤️❤️❤️❤️
🌷💜💓 #መልካም_ቀን 💓💜🌷