cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

የኛን #You_Tube ቻናል ለማግኝት ይሄን ይጫኑ⬇️👇 http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube ጥያቄ ወይም አስተተያየት ካላቹ በቦት @ZEKR_MENZUMA_bot ተጠቅመዉ ያድርሱን✍️ የመውሊድ ሀድራ ቪዲዮ በድምፅ የተቀዳ መንዙማ ያላቹ ላኩልን { @ZEKR_MENZUMA_bot }

Mostrar más
Advertising posts
14 428Suscriptores
-3624 hours
-1217 days
+17730 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ትላንት የሆነ ቦታ በአጋጣሚ አንዲት ደስ የምትል የ10 ዓመት ልጅ ከእናቷ ጋር ሆና አጠገቤ ተቀምጠዋሉ። ሙስሊም ናቸው። ልጅቷ በጣም ቀልጣፋ ነች። አይን አይኔን ስታየኝ ወሬ ጀመርኩ። 'ትምህርት እንዴት ነው ?' ስላት ፣ በትምህርቷ ጎበዝ እንደሆነች'ና እስከአሁን አንደኛ ብቻ እየወጣች እንደሆነ ነገረቺኝ። እናቷ በፈገግታ የምናወራውን ትሰማለች። 'እና ስታድጊ ምን መሆን ነው የምትፈልጊው ?' ስላት ፣ ድንገት እናቷ ፊቷ ቅይርይር አለ። ልጅቷ ላይ ተኮሰታተረችባት። ግራ ገባኝ። ልጅቷም እያፈራረቀችን በፍርሃት ውስጥ ሆና እኔ'ና እናቷን ታየን ጀመር። 'ምነው ?' አልኳት ለህፃኗ ቀስ ብዬ። 'እናቴ እኔ መሆን የምፈልገውን ነገር አትደግፈኝም...' አለቺኝ ለንቦጯን እየጣለች። የልጅቷ አይን በእንባ ሲሞላ 'ችግር የለውም ንገሪው በቃ እኔኮ ለአንቺው ብዬ ነው...' አለች እናቷን የግዷን ፈገግ ለማለት እየሞከረች። 'እኔ ሳድግ ፓይለት ወይም ሆስተስ መሆን ነው የምፈልገው...' አለች ህፃኗ ፍንድቅድቅ እያለች። ያልጠበኩት ነገር ስለነበር እኔም ወደ እናቷ እየዞርኩ 'አሪፍ ነገር እኮ ነው የተመኘችው። እኔኮ እንደማንኛውም ህፃን የማይሆን ነገር እየጠራች አስቸግራችሁ መስሎኝ ነበር...' ስላት ፣ 'እኔም ሆንን አባቷ እኮ የምትፈልገው ብትሆን ደስታችን ነበር። ግን ደግሞ ከአሁኑ ተስፋ አድርጋ አድጋ ወደፊት ፓይለትም ሆነ ሆስተስ ለመሆን በአየር መንገዱ ሂጃብሽን ካላወለቅሽ ፣ ሱሪ ወይም አጭር ቀሚስ ካለበስሽ አይሆንም ስትባል ምን ልትሆን ነው ብለን ስለምናስብ ነው ከአሁን የምንከለክላት....' አለቺኝ የንዴት ሳቅ እየሳቀች ! ከዚህ በፊት በብዙ ሙስሊም እህቶቻችን ይሄ ቅሬታ ሲነሳ ብሰማም እንደዚህ ግን ተረብሼ አላውቅም። ቁጭ ብዬ የአንዲት ጎበዝ ተማሪ ሙስሊም ህፃን መብቷ ሲነፈግ ፣ ምኞቷን ገና ከአሁኑ ስትነጠቅ ማየት ያናዳል። ያሳዝናል። ልብ ያደማል። ሴኩላር ነው በሚባል ሀገር ላይ ሙስሊም እህቶቻችንን በአለባበሳቸው ብቻ መቀጠር የማይችሉበት አየር መንገድ የሚያህል ትልቅ ተቋም መኖሩ ያሳፍራል። አውሮፕላን ውስጥ ለማስተናገድ በየቱ አስገዳጅ ምክንያት ነው ፀጉር መልቀቅ ግዴታ ሆኖ ሂጃብ ማድረግ ሊያስከለክል የቻለው ? ሱሪና አጭር ቀሚስ ተፈቅዶ ረዥምም ቀሚስ የተከለከለው ተሳፋሪው ላይ ምን እንዳይጎልበት ነው ? አየር መንገዱ እንደ ገላ ሻጭ በሆስተሶቹ ሰውነት'ና ፀጉር መራቆት ምንድን ነው የተለየ የሚያገኘው ጥቅም ? የሙስሊሙም ጭምር የህዝብ ተቋም የሆነው አየር መንገድ ውስጥ ተቀጥሮ ለመስራት እህቶቻችን መማር እንጂ ሰውነታቸውን አጋልጠው ማሳየት ግዴታ ሊሆንባቸው አይገባም ! በአሁን ሰዓት ሙስሊሙ ህብረተሰብም ሆነ እስላማዊ ተቋማቶች ከምንም በላይ ጊዜ ሳንሰጥ ልንታገለው የሚገባ አድሎዊ ተቋም ይሄንኑ አየር መንገድ ይመስለኛል። ይሄ ተቋም በማይረባ ቢሮክራሲው ትላንት የብዙ እህቶቻችንን ተስፋ መቀማቱ ሳያንሰው ዛሬም የልጆቻችንን ህልም ጭምር እየነጠቀ ነው። ይሄን የተቋሙ አግላይ የሆነ አካሄድ በጊዜ በቃ ልንለው ይገባል። እኛ ታግለን መብታችንን ባለማስከበራችን ልጆቻችን ስርአት ባለው ሃይማኖታዊ አለባበሳቸው ሊያፍሩ'ና ሊሸማቀቁ አይገባም ! ሂጃብ ፣ እንዲሁም ያላጠረ'ና ያልተወጠረ ቀሚስ ያደረገች ሙስሊም ሴት ፓይለትም ሆነ ሆስተስ የመሆን መብት አላት ! ትሆናለችም ! ሃሳቡ ካስማማችሁ ሼር አድርጉት ለሚመለከታቸው አካሎች እንዲዳረስ ! በዚህ ቻናል⬇️👇 ✔ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን። ✔ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤ ✔ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤ ✔ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን። ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇 Youtube http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube Facebook page⬇️ https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886 ቴሌግራም⬇️👇 https://t.me/ZEKR_MENZUMA
Mostrar todo...
Zekr Menzuma & Neshida | Addis Ababa

Zekr Menzuma & Neshida, Addis Ababa, Ethiopia. 1,152 likes · 21 talking about this. የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማ

ትላንት የሆነ ቦታ በአጋጣሚ አንዲት ደስ የምትል የ10 ዓመት ልጅ ከእናቷ ጋር ሆና አጠገቤ ተቀምጠዋሉ። ሙስሊም ናቸው። ልጅቷ በጣም ቀልጣፋ ነች። አይን አይኔን ስታየኝ ወሬ ጀመርኩ።👇👇👇
Mostrar todo...
ትላንት የሆነ ቦታ በአጋጣሚ አንዲት ደስ የምትል የ10 ዓመት ልጅ ከእናቷ ጋር ሆና አጠገቤ ተቀምጠዋሉ። ሙስሊም ናቸው። ልጅቷ በጣም ቀልጣፋ ነች። አይን አይኔን ስታየኝ ወሬ ጀመርኩ። 'ትምህርት እንዴት ነው ?' ስላት ፣ በትምህርቷ ጎበዝ እንደሆነች'ና እስከአሁን አንደኛ ብቻ እየወጣች እንደሆነ ነገረቺኝ። እናቷ በፈገግታ የምናወራውን ትሰማለች። 'እና ስታድጊ ምን መሆን ነው የምትፈልጊው ?' ስላት ፣ ድንገት እናቷ ፊቷ ቅይርይር አለ። ልጅቷ ላይ ተኮሰታተረችባት። ግራ ገባኝ። ልጅቷም እያፈራረቀችን በፍርሃት ውስጥ ሆና እኔ'ና እናቷን ታየን ጀመር። 'ምነው ?' አልኳት ለህፃኗ ቀስ ብዬ። 'እናቴ እኔ መሆን የምፈልገውን ነገር አትደግፈኝም...' አለቺኝ ለንቦጯን እየጣለች። የልጅቷ አይን በእንባ ሲሞላ 'ችግር የለውም ንገሪው በቃ እኔኮ ለአንቺው ብዬ ነው...' አለች እናቷን የግዷን ፈገግ ለማለት እየሞከረች። 'እኔ ሳድግ ፓይለት ወይም ሆስተስ መሆን ነው የምፈልገው...' አለች ህፃኗ ፍንድቅድቅ እያለች። ያልጠበኩት ነገር ስለነበር እኔም ወደ እናቷ እየዞርኩ 'አሪፍ ነገር እኮ ነው የተመኘችው። እኔኮ እንደማንኛውም ህፃን የማይሆን ነገር እየጠራች አስቸግራችሁ መስሎኝ ነበር...' ስላት ፣ 'እኔም ሆንን አባቷ እኮ የምትፈልገው ብትሆን ደስታችን ነበር። ግን ደግሞ ከአሁኑ ተስፋ አድርጋ አድጋ ወደፊት ፓይለትም ሆነ ሆስተስ ለመሆን በአየር መንገዱ ሂጃብሽን ካላወለቅሽ ፣ ሱሪ ወይም አጭር ቀሚስ ካለበስሽ አይሆንም ስትባል ምን ልትሆን ነው ብለን ስለምናስብ ነው ከአሁን የምንከለክላት....' አለቺኝ የንዴት ሳቅ እየሳቀች ! ከዚህ በፊት በብዙ ሙስሊም እህቶቻችን ይሄ ቅሬታ ሲነሳ ብሰማም እንደዚህ ግን ተረብሼ አላውቅም። ቁጭ ብዬ የአንዲት ጎበዝ ተማሪ ሙስሊም ህፃን መብቷ ሲነፈግ ፣ ምኞቷን ገና ከአሁኑ ስትነጠቅ ማየት ያናዳል። ያሳዝናል። ልብ ያደማል። ሴኩላር ነው በሚባል ሀገር ላይ ሙስሊም እህቶቻችንን በአለባበሳቸው ብቻ መቀጠር የማይችሉበት አየር መንገድ የሚያህል ትልቅ ተቋም መኖሩ ያሳፍራል። አውሮፕላን ውስጥ ለማስተናገድ በየቱ አስገዳጅ ምክንያት ነው ፀጉር መልቀቅ ግዴታ ሆኖ ሂጃብ ማድረግ ሊያስከለክል የቻለው ? ሱሪና አጭር ቀሚስ ተፈቅዶ ረዥምም ቀሚስ የተከለከለው ተሳፋሪው ላይ ምን እንዳይጎልበት ነው ? አየር መንገዱ እንደ ገላ ሻጭ በሆስተሶቹ ሰውነት'ና ፀጉር መራቆት ምንድን ነው የተለየ የሚያገኘው ጥቅም ? የሙስሊሙም ጭምር የህዝብ ተቋም የሆነው አየር መንገድ ውስጥ ተቀጥሮ ለመስራት እህቶቻችን መማር እንጂ ሰውነታቸውን አጋልጠው ማሳየት ግዴታ ሊሆንባቸው አይገባም ! በአሁን ሰዓት ሙስሊሙ ህብረተሰብም ሆነ እስላማዊ ተቋማቶች ከምንም በላይ ጊዜ ሳንሰጥ ልንታገለው የሚገባ አድሎዊ ተቋም ይሄንኑ አየር መንገድ ይመስለኛል። ይሄ ተቋም በማይረባ ቢሮክራሲው ትላንት የብዙ እህቶቻችንን ተስፋ መቀማቱ ሳያንሰው ዛሬም የልጆቻችንን ህልም ጭምር እየነጠቀ ነው። ይሄን የተቋሙ አግላይ የሆነ አካሄድ በጊዜ በቃ ልንለው ይገባል። እኛ ታግለን መብታችንን ባለማስከበራችን ልጆቻችን ስርአት ባለው ሃይማኖታዊ አለባበሳቸው ሊያፍሩ'ና ሊሸማቀቁ አይገባም ! ሂጃብ ፣ እንዲሁም ያላጠረ'ና ያልተወጠረ ቀሚስ ያደረገች ሙስሊም ሴት ፓይለትም ሆነ ሆስተስ የመሆን መብት አላት ! ትሆናለችም ! ሃሳቡ ካስማማችሁ ሼር አድርጉት ለሚመለከታቸው አካሎች እንዲዳረስ ! በዚህ ቻናል⬇️👇 ✔ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን። ✔ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤ ✔ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤ ✔ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን። ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ⬇️👇 Youtube http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube Facebook page⬇️ https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886 ቴሌግራም⬇️👇 https://t.me/ZEKR_MENZUMA
Mostrar todo...

...عييييد المبارك 💐...እንኳን ለ1445ኛው የኢደል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰህ/ሽ..! 🌼🌺🎉🎉🌙 👳....عيد المبارك* علينا وعليكم تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
Mostrar todo...
ሼህ አህመድ ዳለቲ ክፍል አንድ ሼህ አህመድ ዳለቲ በ 1894 በ ኮኪር ገደባኖ ልዩ ሰሙ መጎ አካባቢ በተለምዶ ሸንቆ በሚባል መንደር ተወለዱ ወላጆቻወ ያወጡላቸወ የ መጠሪያ ሰም ገለቱ አዱሼ ነበር ። ሼሁ ( ገለቱ አዱሼ ) አሰራአንድ አመትሲሞላቸው አገምጃይ ወደ ሚገኝወ አጎታቸው ሸህ አወል ሁሴን ዘንድ በመሄድ የሀይማኖት ትምህረት አሊፍ - ባ ብለው ጀመሩ ፣ ሼሁ (ገለቱ አዱሼ) ከጎታቸዉ ጋር አንድ አመት ገደማ እንደቆዩ የመጠሪያ ሰማቻው ከ ገለቱ ወደ የአለማችን ተወዳጁ ስም እና የ ሚሊዮኖች ሙሰሊም መጠሪያ በሆነው በ አህመድ በመለወጥ አህመድ አዱሼ በሚል ሰም እንደተቀየረ ታሪካቸው የናገራል ። አጎታቸው ጋር ሲቀሩ እና ሲማሩ ከቆዩ ቡኃላ ከ ሁለተ አመት ቆይታ ቡኃላ ወደ አዲሰ አበባ ዙሪያ ወደምትገኘው የ እስልምና ማእከል ዳለቲ በ መሄድ ለጥቂት ግዜ ትመህር ተከታትለዋል ። ከደለቲም በ መቀጠል በ ኢትዪጵያ ሙሰሊም ታሪክ በ እሰልምና ትምህርት ማእከልነት በሰፋት ወደ ሚታወቀው ወሎ እና አካባቢው በማቅናት ለከፍተኛ ትመህርት እራሳቸውን አዘጋጁ ፣ ወሎ ወሰጥ ልዩ ሰሙ ዳወዶ በተበለ አካባቢ መቀመጫቸውን በማደረግ የተለያዪ ኪታቦችን እና የዲን ትመህርቶችን ከ እውቁ ሼህ ዑመር ከተባሉ አሊም እና ከሌሎች አሊሞች ዘንድ እየተዘዋወሩ ከ አሰራ አምስት አመት በላይ ቆየታ ከደረጉ ቡኃላ ፣ በ ኡሰታዘቸው ሼህ ዑመር ምክር እና ትእዛዝ አማካኝነት መርቀው እና ዱአድርገውላቻው ወደ ትወልድ ሰፈራቻወ ሄደው ዲንን እንዲያሰፈፉ እና እንዲያተምሩ ተላኩ ። ሼህ አህመድ የ ሀይማኖት ትመህርት ማሰተማር የጀመሩት ከ ጠላት ወረራ በፊት ሁለት አመት ቀደሞ በሎ በ ዳለቲ ነው ፣ ዳለቲ በ አለም ገና እነ በሰበታ መሀል ተገነጥሎ በሚወጣ መንገድ በ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኝ በሸዋ የሙሰሊሞች መአከልነት ሆኖ ያገለግል ነበር ። ሼህ አህመድ ለ ሰባት አመት በዳለቲ በማሰተማር ከቆዩ ቡኃላ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ማሰተማራቸውን የገፈበታል ሲሆን ፣ የራሳቸውን መርከዝ ወይም መሰድረሳ በመመሰረት ከ ገደባኖ፣ወለኔ ፣ሰለጤ ፣ ከ ኦሮሞ አካባቢ እና ከወሎ ጭምር ሼህ አህመድ ጋር ደረሶች ኢልምን ፈለጋ የመጡ ነበር ፣ ይህ ተቋሟቸው ከእሳቸው ህልፈት ቡኃላ እንኳን የ ሼህ መድረስ እየተባለ ኡማውን አገልግሏል ። ሼሁ ሰምሰያሜቸው በተለይም በዳለቲ ቆይታቻው በዳለቲ በሚኖሩ የትገሬወረጂ በሚባሉ የ ኦሮሞበሄረሰቦች ከፍተኛ እወቅና እና ወዴታ ሰለነበራቸው በአዲስ አበባ ቆየታቸው ሰዎች የስም ሰያሜቸውን ሼህ አህመድ ዳለቲ ዩሏቸው ነበር ሆኖም ግን በተለይም የህ መጠሪያ በጣም የሚያከብሯቸው የ ሚወዷቸው የ ሰጋዘምዶች እና የተወለዱበት አካባቢ ተወለጆችን ቅሬታ ሰላሰነሳ ሰም ሰያሜቸው " ሼህ አህመድ ዳለቲ " ወደ " የአም ሼህ " ወደሚል መጠሪያ በ ወዳጆቻው መገለገል ጀመረ ትርጓሜውም የሁሉም ሼህ እንደመለት ነው ። ሼህ አህመድ አዱሼ እንደ ሀይማኖት መምህር ሆነው 40 አመት ያገለገሉ ሲሆን ፣ በህይወት ዘመናቸው 42 ግዜ ሀጅ ያደረጉ ሲሆን አበዘኛውን ማለት የቻላል እንደ አሁኑ አለጋ በአልጋ በልሆነበት ዘመን በ መርከበ ጉዞ ነበር ። ቁርአን ወደ አማርኛ ሲትሮገምበ ሀይለስላሴ ዘመን ፣ እሳቸው የተስራውን ስራ ረቂቅን አይተው እርማት እና እንዲያሻሽሉት ከተመረጡ አምስት ሀገር አቀፍ ታላላቅ ዑለማዋች ውስጥ አንዱ ናቻው ። ይቀጥላል
Mostrar todo...
ሼህ አህመድ ዳለቲ ክፍል አንድ 👇👇👇
Mostrar todo...
ዘካተል ፊጥር ለአዲስ አበባና ለአካባቢዋ ለአንድ ሰው 200 ብር ነው። ወደ ክፍለሀገርሮች ስሌቱ ከዚህ የተለየ ሊሆን ስለሚችል በአካባቢው ያሉ ዐሊሞችን አማክሩ። ሠራተኛንና ዘበኛን ጨምሮ በምታስተዳድሯቸው ቤተሰቦች ልክ ተሰልቶ ዛሬና ነገ በፍጥነት ማውጣት ለተቀባዮች ለዒድ ዝግጅት የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል።
Mostrar todo...
ብቸኝነቴን ታጫውችኝ ዘንድ ቀድመሽ ጠብቂኝ በላት 😢😢😢 በትንሹ ለ100 ሺህ ዓመታት ቀብርህ ውስጥ ምን ትሰራለህ? ከደጋጎቹ አንዱ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ። "በርግጥ ለደጋጎች ካልሆነ በቀር ቀብር አስፈሪ ነው። ዱንያንና ውስጧን እጅግ የምጠላ ስሆን አሁን እድሜዬ 54 ነው። በትንሹ ቀብሬ ውስጥ ለ100 ሺ ዓመታት ምንድን ነው የምሰራው? ስል አሰብኩ። እናም እንደሚከተለው መስራት ጀመርኩ ። እኔ እንደሆነ እሞታለሁ፣ የሚጠብቀኝም ሙሉ በሙሉ ጨለማና ባዶ የሆነ ቀብር ነው። እናም ይህ ቀብር ጌጣጌጥ ይሻል፣ የማደርጋትን እያንዳንዷን ኢስቲግፋርና አዝካር ብቸኝነቴን ያጫውተኝ ዘንድ ወደ ቀብሬ ቀድሞ እንዲጠብቀኝ እየላኩት ነው ብዬ ማሰብ ጀመርኩ። እውነቴን ነው አልቀለድኩም፣ የቀብሬን ለሕድ በሺዎች በሚቆጠሩ ተስቢሖች ማጌጡን ተያያዝኩት። እዚህ ሳለሁ በትንሹ 300 ጊዜ ቁርአንን ቀርቼ አኸትመዋለሁ፣ እያንዳንዷን የሰላት ረከዐ ለቀብር ሒሳብ አካውንት ላይ ጥሪት አድርጌ አስባታለሁ፣ ሁሉም ጥሎኝ ወደ ቤቱ ይመለሳል፣ ምናልባት ብቻዬን ሚሊዮን ዓመታትን እዛ ነኝ። ቀብሬ የግድ ጨፌ፣ ብርሃናማ እና የምርም ጀነት መሆን ይኖርበታል። እናም ከእያንዳንዷ መልካም ተግባር፣ ከዚክርና ቁርአኔ፣ ከሰደቃና ተሸሁዴ በነርሱ ተከብቤ አብረን ስንስቅና ስንጫወት በእዝነ ህሊናዬ አስባለሁ። በዚህ ጨዋታ መሃል በረሱሉ (ሰዐወ) የተደረገ ሶለዋት ጨዋታውን ሲካፈል አስባለሁ። ከሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወት.... ምድር ላይ ሳለሁ ከሃሜትና ነገር ማዋሰድ፣ ለአላህ ተብሎ ካልተሰራ ስራዬ ውጤት ማለትም ከጭንቀት፣ ከቅጣትና ከጨለማና ቅጣት አይሻለኝም?! ከዛሬ ጀምሮ ለናንተ ያለኝ ምክር ይላሉ ይህ ደግ ሰው ቀብራችሁን ባንክ አድርጉትና ሁሌም ከመልካም ስራዎች ጣል እያደረጋችሁበት ሙሉት። በዒባዳዎች ላይ ጠንክሩ። ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ፣ ከዱንያ ይልቅ ለወዲያኛው ዓለም ተጠበብ። አሁንማ ቤተሰብ መሃል ሆነህ ያሻህን ትለብሳለህ፣ ትመገባለህ እንዲሁም ደስ ብሎህ እንቅልፍህንም ትተኛለህ። ሁሉም ፍላጎቶቻችን ተሟልተው እንኳ ተጨባጫችንን እናማርራለን። ይህ ምቾት ማጣት እስቲ ከምድር ሆድ ውስጥ ቢሆን ብለህ አስበው?! ስለዚህ እያንዳንዷን ተስቢሕ በትኩረት አድርግ፣ መልካም አጫዋችና አቀማማጬ ትሆኝልኝ ዘንድ ቀብር ቀድመሽ ጠብቂኝ በላት።" (ዶክተር ሙስጠፋ ማሕሙድ እንደፃፉት) Behredin Rahmeto ቤት
Mostrar todo...
ብቸኝነቴን ታጫውችኝ ዘንድ ቀድመሽ ጠብቂኝ በላት 😢😢😢 👇👇👇
Mostrar todo...
🥁#ለድቤ_ፈላጊዉች🥁 የተለያየ አይነት መጠን ያላቸውን ድቤዎችን እንሸጣለን መግዛት ለምትፈልጉ በዉስጥ ያናግሩን ወይም ይደዉሉልን👇 @ABD_ABD2 ስልክ👇 📞 #0966807265 ክፍለ ሀገር ላላቹም እንልካለን አድራሻችን👇 አዲስ አበባ #አቶቢስ_ተራ
Mostrar todo...