cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ግጥም እና አባባል

╭─┅─┅──┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅─╮ እንኳን :¨·.·¨: ወደ `·.🇪🇹ግጥም እና አባባል ቻናል መጡ ╰─┅─┅──┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅─╯ ━ ━━━━━━•●✠ተ✠●•━━━━━━ ━ 「❝ ዓለሙን፡ሁሉ፡ቢገዛ ነፍሱን፡ግን፡ቢያጠፋ ለሰው፡ምን፡ይጠቅመዋል? ሰው፡ለነፍሱ፡ቤዛ፡ምን፡ይሰጣል? ❞」 ━ ━━━━━━•●✠ተ✠●•━━━━━━ ━ ማር ፰፥፴፮።

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
4 049Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🇪🇹ቅዳሜ ጳጉሜ ፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም ╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮ 「❝ ሶስት፡ነገሮች በጣም፡ያስደንቁኛል። ፩ አባቱ፡የማይቀድመው፡ልጅ ፪ እናቱን፡የፈጠረ፡ልጅ ፫ የፈጠራትን፡የወለደች፡እናት ❞」 ╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯ 🗣 አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለመቀላቀል 👉🏽 @poemandquote አስተያየት 👉🏽 @poemandquotebot ┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓ ❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘ ┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
Mostrar todo...
🇪🇹 ቅዳሜ ጳጉሜ ፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም ━━━━━━━━━━━━━✠━━━━━━━━━━━━━ ┈┈┈┈•◦●✠ተ✠●••┈┈┈ ╭─┅┅──┅──┅─═┅❀┅═─┅──┅──┅┅─╮ 「❝ ቀደም፡ብዬ በቅዳሜ፡ቀን ሐምሌ ፯ ፳፻፲፬ ዓ.ም በዚህ፡ቻናል፡ላይ ከ ፳፻፲፬ ዓ.ም በኋላ ለሀገሬ፡ኢትዮጵያ፡በጎው፡ዘመን እስኪመጣላት፡ድረስ ምንም፡አይነት፡አዲስ፡መልዕክት እንደማይለቀቅ፡ባሳወቁት፡መሠረት በሚቀጥለው፡አባባል፡ተሰነባብተን አገልግሎት፡መስጠቱን፡ያቆማል። ፍቃዳችሁ፡ሆኖ አብራችሁኝ፡ስለቆያችሁ እግዚአብሔር፡ያክብርልኝ። ❞」 ╰─┅┅──┅──┅─═┅❀┅═─┅──┅──┅┅─╯ ┈┈┈┈•◦●✠ተ✠●••┈┈┈ ━━━━━━━━━━━━━✠━━━━━━━━━━━━━ እግዚአብሔር፡ይመስገን!!! ┈┈┈┈┈┈•◦●፲፪ ፳፩ ፲፱●••┈┈┈┈┈┈
Mostrar todo...
🇪🇹ቅዳሜ ጳጉሜ ፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም ╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮ 「❝ እስኪ፡የሰማሃውን ለማሰላሰል፡ጊዜ፡ይኑርህ። ❞」 ╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯ 🗣 ዓለማየሁ ዋሴ 📔 ሰበዝ ለመቀላቀል 👉🏽 @poemandquote አስተያየት 👉🏽 @poemandquotebot ┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓ ❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘ ┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
Mostrar todo...
🇪🇹ቅዳሜ ጳጉሜ ፭ ፳፻፲፬ ዓ.ም ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ የለም! የለም! የለም! የለም! ይህ ስንኝ ይህ ግጥም ፥ ፖለቲካ አይደለም! ከተደማመጥን ፥ ተራ ጎጡን ትተን እንዲህ ነው የሚመስለኝ ፥ ሀገር ሲተነተን ትንቢት ፩ የሞተው ወንድምሽ ትንቢት ፪ የገደለው ባልሽ ጥያቄ አንቺን ምን እንበልሽ ? ማን እንበልሽ አንቺን ? የሟች እህት ዘመድ ፥ የገዳይ ባለቤት ከፊት አይታይም ፥ ሀገር የሌለው ቤት? እኔን ይታየኛል ፥ ወንድምሽ ሲቀበር ይኸውልሽ እንግዲህ! የገደለው ባልሽ ፥ ከፊት ቆሞ ነበር የባልን ቃልኪዳን የነፍስን ደም ክዳን የወንድም ከለላ አለች የሚያስብልሽ ፥ የአካልሽ ጥላ ለደሀ እናት ሀገር ፥ ሁለቱንም ማጣት ጥፋት እያሰቡ ፥ ሰርክ መቀጣጣት እንዴት አርጎሽ ይሆን? ፥ ዘመን ምስቅልቅሉ ቀራኒዮሽ የት ነው? ፥ የሚወርደው መስቀሉ እንዴት አርጎሽ ይሆን? የት ሄድሽ? እስከወዴት? ያገር ጌታ ሲሞት ፥ በአንድ ባርያ ንዴት እንዴት አርጎሽ ይሆን? የነደደው ሲገድል ፥ የሞተው ሲሆን ገል ዘመድሽ ሲጋደል ዘመንሽ ሲነደል ፥ ነፍስሽን ሲያደማት እንደው ምን ተሰማሽ? ፥ እንደው ምን ተሰማት? ብቻ... በዚህ በወንድሟ ፥ በዚህም በባሏ ከሁለት እሳት መሐል ፥ የቆመች አካሏ የጦቢያን እናት ፥ ይመስለኛል ምስሏ ያቺ ምስኪንዬ... ያቺ ምስኪንዬ ፥ በልጇ ሆድ በልታ ያቺ ምስኪንዬ ከሳር ፍራሿ ላይ ወርቅ ከምትለው ፥ ከአብራኳ ተኝታ የምትጽናናውን የምትረካውን የዚያችን ምስኪን ሴት ፥ የእምዬን ገላ እሷን ነው የረሳን ድንጋይ ስንወረውር ፥ አንገቴን ስትቀላ እሷን ነው የረሳን ፥ እናቴን ከእናትህ ከገላዬም ያልፋል ተስፋዋን ይገላል ፥ የያዝከው ጥይትህ። የለም! የለም! የለም! የለም! ይህ ስንኝ ይህ ግጥም ፥ ፓለቲካ አይደለም! ፖለቲካ ስም ነው ፖለቲካ ቃል ነው ፥ ከሥልጣንም በታች የአንዲት እናት ስም ነው ፥ ገመናህን ከታች። ፖለቲካ ሆሄ የዓለማት ጸሎት ፥ የዘመን ኤሎሄ ፖለቲካ ፍዳ ፥ የመከራ ድርድር የራስ ሰማይ መስራት ፥ ማጥፋት የሰው ምድር ! ትንቢት ፩ የገደለው ባልሽ ትንቢት ፪ የሞተው ወንድምሽ ጦቢያ አንቺን ምን እንበልሽ ? የጠፋው ወንድምሽ ያጠፋው ያ ባልሽ የሚሞተው እሱ ፥ ስጋዋ ወንድሟ ገዳዩዋ ባሏ ነው ፥ የሌሊት ሰው ደሟ ዘመድሽ ሲጋደል ዘመንሽ ሲነደል ከማን መሬት ገባሽ? ፥ ከምን አፈር ጉድጓድ? ምን ጥግ አስከለለሽ? ፥ ሓሳብ ልጅሽ ሲናድ ምን ጫካ ላይ ከተምሽ? ፥ ከወዴት ውጥንቅጥ? መጋደል ንዳድ ነው ፥ ነፍስ የሚሰነጥቅ ወንድምን በሬሳ ፥ ወዲያ እየሸኙ የአብራክን ክፋይ ፥ በሞት እየሸኙ ትዳር እንዴት ይቁም ፥ ከጉዳይ ከተኙ ? የለም! የለም! የለም! የለም! ይህ ስንኝ ይህ ግጥም ፥ ፖለቲካ አይደለም! ብቻ... ስንወረውር ፥ ልብህን ሳደማው ባሩድ ስትተኩስ ፥ ነፍሴን ስትቀማው ጉድጓድ ስምስልህ ፥ አንተም ቃታ ስትስብ እናቴን አስታውሳት! ፥ እናትህን ላስብ! ብቻ... ዘሬ በአንተ ዘር ላይ ፥ ሳላድበሰብሰው ወላድህን አስብ ፥ በቂ ነው መባል ሰው! እሷን ማሰብ በቂ ፥ ከማለቅ ያግዳል ካርታማ ሞኝ ነው ፥ ሲያሰምሩት ይሄዳል ካርታ ስናሰምር እኔም ይቅር አልሙት ፥ አንተም ይቅር አትሙት የትኛውም ስሜት ፥ ሞኝ ነው ከሰሙት እኔም አልቀበር ፥ ደሜን አላሙቀው ቀልብ እኮ መንጋ ነው ፥ አረኛ ከራቀው እናም... ቀልባችን ሲከተት ጠንካራ እንደብረት ፥ ንጹሕ እንደወተት ጠንካራ ስትሆን ፥ ዋርካ ነህ መጽናኛ ጠንካራ ሕዝብማ ፥ እርሱ ራሱ እረኛ ጠንካራ ሕዝብማ መሪ በሌለበት ፥ ጠላቱን አዋርዷል ጠንካራ ሕዝብማ ንጉሥ በሌለበት ፥ ዙፋኑን ጠብቋል ጠንካራ ሕዝብማ ሀገር ያሻግራል ፥ ንግሥና ሳይቀማ! ጠንካራ ሕዝብማ ፥ ዕምነቱ ብዙ ነው ድንጋይ እና ጥይት እንኳን ከጭንቅላት ፥ ከእግር በታች ነው በጣልነው ስንዋስ... በናቅነው ስናለቅስ... ከሬሳችን እኩል ፥ ዕንባ ሚታበስ ይሄ... ይሄ... ለሺህ ዘመን ሙሉ ፥ እረኛ ሚከሰው ለሺህ ዘመን ሙሉ ፥ እረኛ ሚወቅሰው ደግ መሪ ስጠኝ ፥ ብሎ የሚያለቅሰው ይህ ሁሉ ምስኪን ሰው ፥ ጸሎቱ የደመነ የመሪዎቹ ምንጭ ፥ እርሱ ስለሆነ። መሪ ንጉሥ ማለት ፥ ከአብራክህ የወጣ እኛው የፈጠርነው ፥ ወልደነው የመጣ ! ጨካኙም ከእኛው ነው። አጥፊውም ከእኛው ነው። ሰናዩም ከእኛው ነው። ካሌብም ከእኛው ነው። ቴዎድሮስ ከእኛ ነው። ምኒልክ ከእኛ ነው። ዮሐንስ ከእኛው ነው። አሉላም ከእኛው ነው። ተፈሪም ከእኛው ነው። መንግሥቱም ከእኛው ነው። መለስም ከእኛው ነው። ግፈኛው ከእኛው ነው። ከእኛው ነው ሁሉም ከሀዲውም ከኛ ፥ ከቋጥኝ የሚከብድ አንተ የኔ ወገን ከመሪዎች በፊት ፥ ሕዝብህን ነው መውለድ። የለም! የለም! የለም! የለም! ይህ ስንኝ ይህ ግጥም ፥ ፖለቲካ አይደለም! እውነት ነው ማወራህ ፥ ዘላለም ያኖረን ከኪዳን የቀረን... ከእማማ የቀረን... ከአባባ የቀረን... ይሄ ነው የሚያኖረን። ይሄ ነው ያኖረን። ስንሰቃይ ኖርን ፥ በመከራ ታንኳ አንተ የሀገሬ ሰው ዝም ብለህ አትክፈት ፥ ማንም ሰው ሲያንኳኳ ያ ነው የሚያኖረን ፥ ትንቢት እንዳንፈራ ለጤፍ እያረስን ፥ እንዴት ቂም እናፍራ ? የቂም በቀል መንገድ መድረሻው ግራ ነው ፥ ጉዞው ማይለካ መንጋነት ያስንቃል ፥ በእረኛ ሲለካ ለዘመን መመዘን ፥ ለችጋር መንጋጋ ይበቃሻል ጦቢያ! በሞትሽ አይጨልም ፥ በሞትሽ አይንጋ "ያፅናሽ!" ብል አልፀናም ፥ አታውቂም ስሜቴን ብቻ... ማንም ሞተ ሲሉኝ ፥ አይሻለው አንቺን አያለሁ እናቴን አያለሁ... አያለሁ... አያለሁ... ብቻ ማሰብም ከእኛ ነው አለማሰብ ከእኛ ፥ ከቋጥኝ የሚከብድ አንተ የኔ ወገን ከመሪዎች በፊት ፥ ሕዝብህን ነው መውለድ። ልባችን ልብ ይግዛ በነገር... በሐሜት በሆሄ ፥ በጦር ስም አትምቱት! እስቲ ነጻ ይውጣ ፥ አሳሪውን ፍቱት ሁሉም ነጻ ይውጣ! ሁሉም ነጻ ይሁን! ፥ የተፈታ ወጥቶ ሁሉም ነጻ ይሁን! ፥ የአጠፋ ተቀጥቶ! ታድያ እኔ እና አንተ ዘርን ወዲያ ቀብረን ፥ ትንቢትን አንፍተል ! ዘርን ወዲያ ቀብረን ፥ ትንቢትን አንፍተል ! ወይ ደግ ቀን አምጣ ወይ ባለደግ ቀን ፥ ፈልገህ ተከተል ! ​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ ✍🏽© ኤልያስ ሽታኹን ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ ለመቀላቀል 👉🏽 @poemandquote አስተያየት 👉🏽 @poemandquotebot ┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓ ❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘ ┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
Mostrar todo...
🇪🇹አርብ ጳጉሜ ፬ ፳፻፲፬ ዓ.ም ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ መቼም... የጠቢብ ሀገር ነው! ሁሉ በየመልኩ ሁሉ በየልኩ ሁሉ በአቋሙ ሁሉ በአቅሙ የሚቀጣጥለው ፥ የሚያቀጣጥለው የሚያንጠለጥለው ፥ የሚያብጠለጥለው የሚበታትነው ፥ የሚተነትነው ጊዜው ተምታቶ እንጂ ፥ ሀገሩስ ጠቢብ ነው! አታይም?! በምሁራን መንደር ፈውስ ሽባ ሆኖ ፥ ደዌ ሲንደረደር አትሰማም?! በጠቢባን ሀገር መሲሁ ተቀምጦ ፥ መጻጉእ ሲናገር ተምታቶ ነው እንጂ ፥ ሀገሩስ ጠቢብ ነው! ምጸትና ጸጸት ፥ የተቀላቀለው! ተምታቶ ነው እንጂ ፥ ሀገሩስ ሀገር ነው! ምጸትና ጸጸት ፥ የተቀላቀለው! ምጸትና ጸጸት ሰው የሚሉት ፍጥረት ፥ ክብሩ እንዳይገባው ዓይኑን አሳወረው ፥ ተንኮልና ደባው የጅራፍ አመሉ ፥ ለጅራፉ ተርፎ ራሱ ይጮሃል ፥ ራሱ ተጋርፎ እኛን አይመስልም ? ወደራስ ነው መጮህ ፥ ወደገዛ ልብህ ቀለብህን ትተህ ፥ መሠብሠብ በቀልብህ ወገን! ወደቤትህ ግባ ወደጓዳህ ግባ ወደውስጥህ ግባ ፥ የሚል ደዌ ካለ? ከህማሙ ጀርባ ፥ አንዳች ትርጉም አለ! አንዳች ትርጉም ሀ ሁሉም ከበር ወዲያ... ሀገሬው መንደሩ ከራሱ ጋር ሽሽት ፥ ስለተላመደ ወደቤትህ ግባ! ፥ የሚል ሞት ወለደ። ወደራስህ ግባ ወደቤትህ ግባ ፥ የመባልህ ነገር ትርጉሙ ይሰፋል ፥ ለሕይወት ለሀገር። ለእኛማ ሌላ ነው... ለእኛማ ሌላ ነው... የቤት ግቡ ቅኔ ፥ የትርጉሙ ሚዛን ነጭን አሸንፈን ፥ በነጭ የተገዛን ለእኛማ ሌላ ነው... በዙፋን ላጠፋ ፥ ዙፋን የምንቀጣ ነጻነትን እንኳን ፥ ነጻ ምናወጣ አጀብ! ለእኛማ ሌላ ነው... ልባችን ተከደቶ ክራችን ተፈቶ ፥ ማህተባችን ላልቶ አለማመን እውቀት ፥ ማመን ተሸልቶ ለምንነዋወጥ! ፥ ለማንደማመጥ! ለእኛማ ሌላ ነው ፥ ከእኛ ጋር መቀመጥ።   ቤት ማለት ገመና! ፥ ገመና ምሥጢርህ ምሥጢርህ ራስህ ልብህ ሰውን ይርሳ ፥ አንተን እንዲከስህ። የመዋቀስ ልማድ ከገዛ ራሳችን ፥ ሊላምደን ሽቶ አፋችን ተዘጋ ፥ ከሰው ጆሮ ሸሽቶ ወደቤትህ ግባ... ወደጓዳህ ግባ... ወደውስጥህ ግባ ፥ የሚል ደዌ ካለ? ከህማሙ ጀርባ ፥ አንዳች ትርጉም አለ! አንዳች ትርጉም ለ ላንቺማ ሌላ ነው ፥ ውጪውጪ ላልሽው በቀልብም በልብም በመንፈስ በሃሳብ ለምትሰደጂው ፥ ለምታሳድጂው ሽል ይበልጣል ብለሽ የገዛ ልጅሽን ፥ ለምታሶርጂው ላንቺማ ሌላ ነው... ከሊቅ እስከደቂቅ ፥ ለሚተነትንሽ ዘርሽን በትነሽ ፥ ዘር ለሚበትንሽ ላንቺማ ሌላ ነው... ስም እየቀያየርሽ ፥ ጠሪ የሚከፋ በእውቀት በሙቀት ፥ ጨለማሽ ሚሰፋ ላንቺማ ሌላ ነው... የለመድሺው እደጅ የለመድሺው በራፍ ፥ የለመድሺው አጥር ጎበዝሽን ሁሉ ፥ ለሞት የሚቀጥር። ላንቺማ ሌላ ነው... በእግዜር ተጠብቀሽ እግዜርን ለረሳሽ ፥ እምነትን ላነሳሽ ! በተለይም ላንቺ የታይታ ሆኖ ፥ ያፈራሺው ሁሉ አስከበሩኝ ብለሽ ፥ በዘመን ቢቀሉ ላንቺማ ሌላ ነው... ሃሳብና ነፍስሽ ፥ ስለተቃጠረ ተመስገን በይ አንቺ! ስምሽን አስቀምጦ ፥ ሰሚሽን ፈጠረ ተመስገን በይ አንቺስ... ተመስገን በይ አንቺስ... ዛሬም ተስፋሽ ቆሟል መዳንሽ ባይቀርም ፥ መንፈስሽ ግን ታሟል። ወደቤትህ ግባ ወደውስጥህ ግባ ወደጓዳህ ግባ ፥ የሚል ደዌ ካለ? ከህማሙ ጀርባ ፥ አንዳች ትርጉም አለ! አንዳች ትርጉም ሐ በጊዜ ታሪክ ላይ... በሕይወት ታሪክ ላይ... በሀገር ታሪክ ላይ ፥ ደም ከሞት የሚኩል አንዳንድ ማለፍ አለ ፥ ከአለማለፍ እኩል። ምሑር ሊቃውንትሽ ይኼም ጊዜም ያልፋል! ፥ እያሉ ሲያቀሉት የማለፍን ትርጉም ፥ ወዴት ነው ያጠኑት? ከመሰበር ወዲያ... ከማለቅም ወዲያ.... ማለፍ ነው እያለ ፥ አስኳላሽ ያሾፋል! የማይቀብሩት ዘመድ ፥ በስንት ዕምባ ያልፋል? በስንት ዕምባ ያርፋል? በጦርነት ሁሉ... በረሀቡ ሁሉ... በህማሙ ሁሉ... ያልፋል ባልነው ሁሉ... ሰው እየገበርን ፥ ሰው እየቀበርን "ግድየለም!" እያልን ፥ ግድየለሽ የሆንን! ሰውን እያሳለፍን "ያልፋል" እንደማለት ፥ ለኮሮጆ ቁማር መቼም የማንማር ! ወገን! ፥ ረሀቡ ቢያልፍም የረሀብ ሀገር ናት ፥ ከመባል አንተርፍም። ጦርነቱ ቢያልቅም ልብሳችን ነው እንጂ ፥ ልባችን አይለቅም። ቸነፈር ቢታለፍ ከጠላት አፍ ምላስ ፥ ዘላለም አያተርፍ። ዛሬም ቁስል አለ ፥ ደነነዋል ያልነው በወሬ በምላስ ፥ አልፈን ያላለፍነው ወትሮም... ሰው ገብረንብት የምንሻገረው ፥ እያንዳንዱ መቅሰፍት አለፍን አይባልም ፥ ሞት ከተጻፈበት!   ወትሮም... ወትሮም... ሰው ገብረንበት የምንሻገረው ፥ እያንዳንዱ መቅሰፍት አለፍን አይባልም ፥ ሞት ከተጻፈበት! በጊዜ ታሪክ ላይ... በሕይወት ታሪክ ላይ... በሀገር ታሪክ ላይ ፥ ደም ከሞት የሚኩል አንዳንድ ማለፍ አለ ፥ ከአለማለፍ እኩል። ሁሉም ከበር ወዲያ... ሁሉም ከአጥር ወዲያ... ሁሉም ቤቱን ትቶ ሁሉም ከራስ ሽሽት ፥ ስለተላመደ ወደራስህ ግባ ፥ የሚል ሞት ወለደ። እንጂማ የጠቢብ ሀገር ነው! ሁሉ በየመልኩ ሁሉ በየልኩ ሁሉ በአቋሙ ሁሉ በአቅሙ የሚቀጣጥለው ፥ የሚያቀጣጥለው የሚያንጠለጥለው ፥ የሚያብጠለጥለው የሚበታትነው ፥ የሚተነትነው ጊዜው ተምታቶ እንጂ ፥ ሀገሩስ ጠቢብ ነው! አላስተውል ስንል ፥ ማስተዋል ቢያነሳን ሁሉን እንድናስብ ፥ ሁሉን ነገር ነሳን። ​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ ✍🏽© ኤልያስ ሽታኹን ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ ለመቀላቀል 👉🏽 @poemandquote አስተያየት 👉🏽 @poemandquotebot ┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓ ❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘ ┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
Mostrar todo...
🇪🇹አርብ ጳጉሜ ፬ ፳፻፲፬ ዓ.ም ╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮ 「❝ ጌታ፡ሆይ የአንተ፡አምላክነት ለእኔ፡ያስፈልገኛል፡እንጂ የእኔ፡ፍጡርነት ለአንተ፡አያስፈልግህም። ❞」 ╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯ 🗣 ቅዱስ ባስልዮስ ምንጭ ➸ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ለመቀላቀል 👉🏽 @poemandquote አስተያየት 👉🏽 @poemandquotebot ┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓ ❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘ ┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
Mostrar todo...
🇪🇹አርብ ጳጉሜ ፬ ፳፻፲፬ ዓ.ም ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ #ጠያቂ_ነኝ_እኔ ያስቀየምኩት ካለ ፥ በስካሁን ቆይታ ያስከፋሁት ካለ ፥ ልቡ በኔ ደምታ በአምላክ ስም በሉኝ ፥ ከልባቹ ይቅርታ። ደካማ ፍጡር ነኝ ፥ በስራዬም ዘንጊ በማላውቀው ነገር ፥ የሰው ስሜት ወጊ ይሆናል ባላልኩት ፥ ጭራሽ ባልገመትኩት ጎድቼ ይሆናል ፥ የአንዳችሁን ስሜት ግና... አስቤም ባይሆንም ፥ ክፋትም አስቤ ይቅር በሉኝና ፥ ይሰብሰብ ሃሳቤ ለፈጣሪ ብዬ ፥ ሁሉን እወዳለሁ ያስቀየምኩት ካለ ፥ ይቅርታ ብያለሁ ቅርን ያሰኘሁት ፥ በምሰራው ስራ ያበገንኩት ካለ ፥ ሊነግረኝ የፈራ ይቅር እንድትሉኝ ፥ እላለሁ አደራ። ማንን እንዳስቆጣሁ ፥ ከቶ አላውቅም እኔ እንደው በደፈናው ይቅር በሉኝና ፥ ይረፍልኝ ጎኔ። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ ​​ ለመቀላቀል 👉🏽 @poemandquote አስተያየት 👉🏽 @poemandquotebot ┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓ ❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘ ┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
Mostrar todo...
🇪🇹ኀሙስ ጳጉሜ ፫ ፳፻፲፬ ዓ.ም ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ #ነገረ_ማድያት ከድፍርስ አይኖቿ... ከድፍርስ አይኖቿ ፥ ከፍ ብሎ ወደላይ ማኃል ፥ ግንባሯ ላይ ጽሑፍ ስለሌለ ጠባዋን ለማወቅ ፥ ምን ቢከብድም እንኳን እንደሚከተለው እነግራቹሃለሁ ማድያት ያጠቃው ፥ ያ ደም መልኳን። እነሆ ታሪኳን ከዘመናት በፊት... ከዘመናት በፊት... ይችህን የቀይ ዳማ ታፍረው ያስከበሯት ፥ ሦስት ባሎች ነበሯት። የቀደመው ባሏ የእግዜር አበጋዙ ፥ ካህን ሰው ነበረ ለስምንት ዘመናት ፥ አብሮ ፈቅዷት ኖረ በነዚህ ዘመናት ሁለት ልጅ አፍርቶ ፥ በአብሮነት ከረመ ከወራት ኋላ ግን ፍም ፀሐይ ገላዋን ፥ መሞቁን አቆመ "ወቅቱ በረድ ሣለ ፥ ለምን ተውከኝ?!" አለች እቅፍ ሠንሠለቷ እንደአገዳ ሲሆን ፥ እያንሰላሰለች ምክንያቱን ነገራት "እህቴ ውዴ ሆይ" አላት "እህቴ ውዴ ሆይ እንዴት ደስ እንዳሰኝ ስላንቺ እያሰብኩኝ በፍጹም ልብና በፍጹም መንፈስህ አምላክህን ውደድ ፥ የሚል ህግን ጣስኩኝ በርግጥ እመቤቴ በርግጥ አስቀድሞ የትዳር ምኝታው ንጹሕ እንደሆነ ፥ ወንጌል ቢናገርም መንኩስና መልካም ፥ መሆኑን አይሽርም።" ደግሞ ሌላ ምክንያት... ሐሳቡን ሳይጨርስ ፥ ሳጓ ገፍቶ አስቆማት ሐዘኗን ለመግለጽ ፥ መቻሏ ጠቀማት ቃል ሐይሉ ጨነቃት ፥ ሁኔታው ከበዳት ዕንባ ውኃ ሲሆን ፥ በአፏ መጮህ ዳዳት ክፉ ድንጋጤ ፥ ፍርሃት ከበባት ውላ ያደረችው በደመና ጎጆ ፥ እንደሆነ ገባት! ሕይወት... ሕይወት አልወርድ ብሎ እንደኮረት ድንጋይ ፥ አንገቷን አነቃት ሐሳቡን ተፋቺው "አይሆንም!" አለችው "አይሆንም!" ስትለው ፥ ፈታት! ጠላት! ናቃት! አሁንን መረጠች ፥ ነገ ስለራቃት። ሁለተኛው ባሏ... ሁለተኛው ባሏ ፥ ዛፍ ቆራጭ ነበረ ለስድስት ዓመታት በአንድ ጎጆ ኖሮ እድሜዋን ቆጠረ ፥ እድሜውን ቆጠረ በነዚህ ዓመታት... በነዚህ ዓመታት... ወንድ ልጅን ወልዶ የሴት አባት መሆን ፥ ልቦናውን ሲያምረው እንደቆረጠው ዛፍ ስል የሞት ገጀራ ፥ ድንገት መነጠረው። እንዴት ያሳዝናል ? እንዴት ያሳዝናል? ፥ ቅስሟን ሰባበረው! ሌላ ሦስተኛ ባል ሌላ ሦስተኛ ባል የባል መጨረሻው ፥ የውድቀት መነሻው ሁሉን አውቃለሁ ባይ ፥ አንዳች ግን የሌለው! ያልታሠበ ንክ ቀን ፥ ደጇ ላይ የጣለው ሰው ነበር! ይከውልህ ደሴ... የሚገርምህ ነገር እብድ ቀን ያመጣው ፥ ወፈፌ ሰውዬ ሰባት ወር ያህል ነው ፥ በአብሮነት የቆዬ በነዚህም ወራት ፈቃደ ሥጋውን ከመፈጸም በቀር አንዳች አዲስ ነገር የፈጠረው የለም በባዶው እንደመጣ ባዶውን ተለየ ባዶነት ምክንያቱ... መሰልቸት ያለበት ፥ ታካች ማንነቱ እንግዲህ ወዳጄ ታይቷት ከጠፋት ሰው ፥ ከዚያን ቀን በኃላ ትንከራተት ጀመር... ትንቀዋለል ጀመር... ልጆቿን የኔ የሚል እሷን የሚጠብቅ ፥ አገኝ እንደው ብላ አዎ... አዎ ከዚህ በኃላ ነው ሱሪ የለበሰ የታጠቀው ሁሉ ፥ ወንድ እየመሰላት ከእመቤትነቷ ወደ ገረድነት ቁልቁል እየነዳ ፥ በቁም የገደላት። አዎ ምልክት ያይደለ በሽታን ያይደለ ከዓይኗ ሥር ፥ ጉድ በታች የመጣችበትን ፥ መንገድ አመላካች ምስል የተወላት! አዎ ከዚህ በኃላ ነው በስተመጨረሻ... በስተመጨረሻ... የዚችን ሴት ጉዳይ ፥ ስናጠቃልለው ይህቺን የቀይ ዳማ አሁን ካለችበት ፥ ጎትቶ ሚያወጣት ከእድሜ ምዕራፍ ስጋት ልክ እንደበፊቱ ማለት እንደነበረችው ፥ መልካም የሚያደርጋት እሷ ሰውን ሳይሆን ፥ ሰው እንዲፈልጋት የሚያስችል መጠቀም ከቻለች ፥ ሁለት እድል አላት። አንድ የራስ ክብሯን ትታ የአብራኳን ክፋዮች ተጠንቅቃ መያዝ ለማዕረግ ማብቃት ተስፋ ይሆናታል ሁለት ሁሉም ነገር ቀርቶ ከዓለም ጋር ተጣልቶ ከዓለም ተለያይቶ ለነፍሷ መመነን ክብር ያሰጣታል ከነዚህ ከሁለቱ ፥ የቱ ይሸላታል? ​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ ✍🏽© በቃሉ ሙሉ ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ ለመቀላቀል 👉🏽 @poemandquote አስተያየት 👉🏽 @poemandquotebot ┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓ ❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘ ┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
Mostrar todo...
🇪🇹ኀሙስ ጳጉሜ ፫ ፳፻፲፬ ዓ.ም ╭─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╮ 「❝ የማይነጋ፡መስሎት ቁርሱን፡ማታ፡በላ። ❞」 ╰─┅┅─┅─┅─═┅❀┅═─┅─┅─┅┅─╯ ለመቀላቀል 👉🏽 @poemandquote አስተያየት 👉🏽 @poemandquotebot ┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓ ❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘ ┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
Mostrar todo...
🇪🇹ኀሙስ ጳጉሜ ፫ ፳፻፲፬ ዓ.ም ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ #ተመስገን_ለማለት ማነሽ ባለ ስቃይ? ፥ ማነሽ ባለ ቁስል? እዚህ ያመጣኝን ፥ ሲቃዬን አይተሻል? ከፊቴ ስታልፊ በእምነትሽ ተቋጥሮ ፥ እልፍ አእላፍ እምባ ካይኖቼ ኮብልሎ ካይኖችሽ ኮሮጆ ፥ ምናልባት ከገባ? እስኪ ፈልጊልኝ? የእንባዬን ዘለላ ፥ ነጠላ ሃዘኔን ድንገት ያንቺ መስሎሽ ከ'ንባሽ ጋር ጠቅልለሽ ፥ ወስደሽው እንዳይሆን? ላለው ይጨመራል ነውና አንቀፁ ፥ የፈለቅንበት ህግ ለልቅሶሽ ሊደረብ ለእንባሽ ሊጨመር ፥ ካይኔ ሲምዘገዘግ አገኘው እንደኾን ካይኖችሽ ባህር ውስጥ ፥ እንባዬን ልፈልግ። እንጃ ግራ ገባኝ... የመረረኝ ሁሉ ፥ ልቤን ያቆሰለ በፊቴ ስታልፊ ቀንበርሽን ሳየው ፥ ቀንበሬ ቀለለ መከራዬ ካልኩት ላፍታ ያጮለቅሁት ፥ መከራሽ ቢከፋ ችግር የመሰለኝ ለፀሎት ያመጣኝ ፥ ኡኡታዬ ጠፋ። እንጃ ግራ ገባኝ... በፊቴ ስታልፊ ፥ እንባዬ ተነነ ከአዉደምህረቱ ለፀሎት ያመጣኝ ፥ ችግሬ በነነ ከመቅደሱ ቆሜ ምን ጎደለኝ ልበል? ፥ ጠፍቶኛል ማጣቴ "ስጠኝ!" "ስጠኝ! "እንጂ " ተመስገን!" መች አዉቆ ፥ ሰዋዊ ስስቴ። አንቺ ባለቁስሏ አሁን ፊቴ መጥተሽ ፥ ጸልየሽ የሄድሽው አለቅሰው ቸገረኝ ተከትሎሽ እንደሁ ፥ እምባዬን መልሽው አንቺ ባለ ሲቃ ፥ አንቺ ባለ ስቃይ ከፊት ለፊት ቆመሽ ፥ ላምላክሽ ስትጸልይ የምስጋናሽ ብዛት ፥ እምባሽን ሲያለብሰው የኔ ጠፍቶብኛል ፥ ያንቺን ነው የማውቀው እንዲህ ነበር ያልሽው.... "ተመስገን አምላኬ ጎህ ቀዶ እስኪመሽ ፥ መሽቶ እስኪነጋ አራቱን ልጆቼን አርብ የወሰድክብኝ ፥ በመኪና አደጋ ለካስ ለኔው ነበር ምንይበሉ ይሆን ፥ ብዬ እንዳልሰጋ" አዎ ባለቁስሏ ከመቅደሱ ቆመሽ ፥ "ተመስገን" ስትይው የኔ በኖ ጠፍቶ ያንቺ ነው የቀረው ፥ እንዲህ የጸለዪሽው "ተመስገን አምላኬ ስለሆነው ሁሉ ፥ ስለምንሆነው ባሌን ኀሙስ እለት አዝለህ ያሳረግኸው ፥ በአክናፈ መብረቅ ለካስ አስበህ ነው ልጆቹ ሲሞቱ ፥ አይቶ እንዳይሳቀቅ" አንቺ ባለ እምባ ፥ አንቺ ባለ ሲቃ ተመስገን የጮህሽው ፥ ጉሮሮሽ እስኪነቃ ያንቺን ተመስገን ነው በቃሌ የማውቀው ፥ ሲቃዬ ሲከዳኝ እንባዬ ሲሰወር እንዲህ ነበር ያልሽው ፥ ቃልሽ መች ሊጠፋኝ? "ዛሬ ቅዳሜ 'ለት ሆስፒታል ደርሼ ፥ ሃኪሞች ነገሩኝ ምድርን መልቀቂያ ያንድ ሳምንት እድሜ ፥ እንደጨመርክልኝ ተመስገን አምላኬ ፥ ጌታዬ ተመስገን ቤተሰቤን ወስደህ ፥ ያልተውከኝ ብቻዬን" አንቺ ባለ እምባ ኧረ የኔ ጩኸት ፥ የት አባቱ ገባ? ምን ስጠኝ ልል ነበር? ስሮጥ አመጣጤ ፥ እንዲያ ያስጨነቀኝ "ገንዘብ አጣሁ" ልል ነው ? ፥ ወይስ "ትዳር ስጠኝ"? ስራዬ ያስጠላል? ቪላ ቤት ሰለቸኝ ? ፥ ባክህ ፎቅ ቤት ልስራ! እስኪ ካገር ልውጣ? ፥ ቪዛዬን አደራ? ሁሉም ቀለለብኝ ፥ ከአመድ ደቀቀ ከቁስልሽ ተያይቶ ፥ ቁስሌ ተሳቀቀ ለካስ እምባ ከእምባ ፥ አመዛዝኖ ማየት "ተመስገን! "ያለምዳል ፥ "ተው ስጠኝ?" ከማለት። ​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ ✍🏽© ረድኤት አሰፋ ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ ምንጭ ➸ አስተማሪ ታሪኮች ለመቀላቀል 👉🏽 @poemandquote አስተያየት 👉🏽 @poemandquotebot ┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓ ❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘ ┗─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┛
Mostrar todo...