cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Ethio ግጥም

@Messifun Send your personal or any poem you want to be posted Link https://t.me/joinchat/AAAAAFATKJuzWIXHGZ_AYQ For any comments use this bot @shortethiopoemBot You can also send your poem and anything feel free.

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
202Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

እንባ እንባ ይለኛል ይተናነቀኛል... እንባ የት አባቱ ደርቆል ከረጢቱ ሳቅ ሳቅም ይለኛል ስቆ ላይስቅ ጥርሴ ስቃ እየነደደች መከረኛ ነፋሴ
Mostrar todo...
ምን አልባት ከዚ በፊት ብዙ ገንዘብ የማግኛ መንገድ ሰምተው እንዲሁም ሞክረው ሊሆን ይችላል ነገር ግን አሁን የምነግራቹ 100% እርግጥ የሆነ ነው። 6731 ላይ ok ብለው ይላኩ ከዛም 02m6 ብለው መላክ ብቻ። ሞክሩት ቀልድ አይደለም.
Mostrar todo...
✍✍ግጥም✍✍ ..........ብርቅርቅታ........ ብርቅርቅታ ያላት እንቁ መሳይ ቆንጆ፣ ሁሉ አንጋጦ የሚያያት ከላይኛው ጎጆ። ምን ግዜም ተወዳጅ ሁልጊዜ አብረቅራቂ፣ ሁሉን አማካሪ ሁሉን አነቃቂ። ብርሀንሽ ምሉዕ... ወዳጅሽ ብዙ ነዉ፣ ሁሌም አመሻሹን አድማቂው መልክሽ ነዉ። አዬ..ዕፁብ ድንቅኮ ነው የፈጣሪ ሥራ፣ አስዉቦ አስቀምጧል ሁሉን በየተራ። ያንቺ ግን ተለየ ውብ ነሽ መልከመልካም፣ ሁሌም አይሻለሁ ስበሺኛል በጣም። .................... ከላዬ ላይ ሆና ሁልጊዜ ስታየኝ፣ በዚያ ዉብ ብርሀኗ አቅሌን ስታስተኝ፤ በራሴ እስቅ ጀመር አኳኋኔን ሳየዉ፣ ከሷ ጋር ሳወራ ስነጋገር ቆየዉ። .................. ጥያቄ ጠየኳት አውጥቼ የልቤን፣ እንድትመልስልኝ እያየሁ አይን አይኗን። አፏ ሳይላወስ በልቤ አወጋችኝ፣ ሁሉን አንድበአንድ በግልጽ አዋየችኝ። ታድያ ምን ይሉታል ይህ አይነቱን ነገር፣ ግዑዟ አካል ሰውን እንዲህ ስታማክር። ህ..ጉድ እኮ ነው!!...... ገረመኝ እንዳዲስ ተደነቅሁኝ ከቶ፣ እንዲህ አይነት ፍጡርስ ከወዴት ተገኝቶ። ................... ቀርቤ አያት ዘንድ በጣም ናፈቀቺኝ፣ በአኳኋኗ ሁሉ ስላስገረመቺኝ። ይህች ባለመልኳ ባለብዙ ዝና፣ ጨረቃ የልቤ.. ናት የኔ ብራና። ቀለሟ ተወዳጅ ሁሌም አብረቅራቂ፣ ጨረቃኮ ውብ ነች ሁሌም ተደናቂ፤ ክብሯን ጠባቂ ናት መልከ ተናፋቂ! 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ⚜ገጣሚ፦ ገብሬላ ⚜⚜⚜❕
Mostrar todo...
​​የዋርካ ስር ጤዛ በእለተ ከተራ ፥ በበዓል ዋዜማ፣ አደባባይ ሳይሽ ፥ ደምቀሽ በሃገር ሸማ ፣ ወርውር ወርውር አለኝ ፥ ሎሚውን ግዛና፣ ሎሚ ሻጭ ፈለግኩኝ...... ጎዳናውን ሙሉ ፥ ስዞር አመሸሁኝ። በጥምቀተ ባህር ፥ ህዝብ ሁሉ በሆታ ፣ እያጨበጨበ ፥ ታቦቱን አጅቦ ሲገባ በእልልታ፣ ማጨብጨብ ተስኖኝ ... እልልታ ጠፍቶብኝ... ሎሚ ፈልጋለሁ ፥ ከአይኔ ሳትጠፊብኝ። ይኸውልሽ ውዴ .... አትታደል ሲለኝ ፥ ቢጠፋ ነው እንጂ .. እድሌ ባይቀና ፥ ብኩን ብሆን እንጂ.. ከአስራ አምስት ቀን በፊት ፥ ለጨዋታ ብዬ ፣ ለገና ጨዋታ ፥ ለአሲና ገናዬ ፣ ዱላ እየፈለግኩኝ ፥ ከጫካ ገብቼ ፥ ሎሚ ጨፍጭፌያለሁ ፥ ዛፉን ተመኝቼ ። እድል እንደዚህ ናት ፥ የዋርካ ስር ጤዛ ፣ ይኸው እኔ ዛሬ ፥ በዋዛ ፈዛዛ፣ እልፍ የሎሚ ዛፍ ፥ ጨፍጭፌ ሳበቃ፣ አንድ ሎሚ አጣው ፥ ለአንቺ የሚበቃ ። አዬ እድል እያልኩኝ ፥ ከወደ አመሻሽ ፥ ከቤቴ ገብቼ ፣ ሎሚ ዛፍ ተከልኩኝ ፥ ለዓመቱ አስልቼ ። እስከዛ ግን አንቺ ..... ሎሚ ወርዋሪዎች ፥ በሌሉበት መንገድ ሂጂልኝ ግድ የለም፣ ዘንድሮን ያለፍኩት ፥ ሎሚ ቢጠፋ እንጂ... ፈርቼስ አይደለም። ወርውር ያለኝ ልቤ ..... ተግቶ ተሰናድቶ ፥ ዓመቱን ጠብቆ፥ በእለተ ከተራ ፣እመጣለሁ ብሏል ፥ ከአስር ሎሚ ጋራ። 🍋🍋🍋🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋🍋🍋 ከሲራክ ወንድሙ @siraaq ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢ አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu @Daniel_bewketu ➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟
Mostrar todo...

ሼር
ለበእውቀቱ ስዩም እና ሌሎችም
​​አዳምና ሚስቱ አዳም የትላንቱ የጥንት የጠዋቱ ሳይለፋ ሳይታክት ተኝቶ ባደረ ውኃ አጣጭ አቻውን ተጎኑ ተቸረ ይብላኝ ላሁኑ አዳም ለታካች ምስኪኑ ምነው በተኛና በሸሸሁ ከጎኑ ለምትል ሄዋኑ ። ከበእውቀቱ ስዪም ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
Mostrar todo...
ሀገሬ (ገብረ ክርስቶስ ደስታ) አገሬ ውበት ነው ለምለምና ነፋስ የሚጫወትበት ጸሃይ የሞላበት፣ ቀለም የሞላበት። አገሬ ቆላ ነው፣ ደጋ ወይና ደጋ እዚያ ብርሃን አለ ሌሊቱ ሲነጋ። አገሬ ተራራ ሸለቆ ረባዳ አገሬ ጅረት ነው ገደልና ሜዳ። ውሸት ነው በበጋ ጸሃይ አትፋጅም ክረምቱም አይበርድም፣ አይበርድም፣ አይበርድም። አገሬ ጫካ ነው እንሰሳት አራዊት የሚፈነጩበት በወጥመድ ሳይገቡ ሳይነካቸው ጠላት። እዚያ አለ ነጻነት። በሃገር መመካት፣ በተወላጅነት፣ በባለቤትነት፣ እዚያ አለ ነጻነት። አገሬ ሃብት ነው። ጎመኑ ስብ ጮማ፣ ቆሎ ክትፎ ስጋ ድርቆሹ ፍትፍት ነው፣ ቃሪያው ሙክት ሠንጋ። ጠጁ ነው ወለላ ከኮኛክ ይነጥቃል የመንደሩ ጠላ። እህሉ ጣዕም አለው እንጀራው ያጠግባል በዓሉ ይደምቃል፣ ሙዚቃው ያረካል፣ጭፈራው ዘፈኑ ችግርን ያስረሳል። እዚያ ዘመድ አለ። ሁሉም የናት ልጅ ነው፣ ሁሉም ያባት ልጅ ነው፣ ጠላትም አንዳንዴ ይመጣል መቃብር ባለጋራም ቸር ነው “ያገር ልጅ ሲቸገር” ። ገነት ነው አገሬ። ምነው ምን ሲደረግ ! ምነው ! ለምን ! እንዴት ! ዘራፊ ቀማኛ ምቀኛ ወንበዴ ጥርኝ አፈር በጁ ስንዝር ወሰን አልፎ የተቀደሰውን ያፍሪቃ ላይ ደሴት ባያገኝ ለማርከስ ጠላት ይመኝ እንዴት። እምቢኝ አሻፈረኝ ! አሻፈረኝ እምቢ ! መቅደስ ነው አገሬ፣ አድባር ነው አገሬ። እናትና አባት ድኸው ያደጉበት ካያት ከቅደመ አያት የተረካከቡት አፈር የፈጩበት፣ ጥርስ የነቀሉበት። አገሬ ዓርማ ነው የነጻነት ዋንጫ በቀይ የተጌጠ ባረንጓዴ ብጫ። እሾህ ነው አገሬ፣ በጀግናው ልጅ አጥንት የተከሰከሰ ጠላት ያሳፈረ አጥቂን የመለሰ። አገሬ ታቦት ነው መቅደስ የሃይማኖት ዘመን የፈተነው በጠበል በጸሎት። ለምለም ነው አገሬ፣ ውበት ነው አገሬ፣ ገነት ነው አገሬ። ብሞት እሄዳለሁ ከመሬት ብገባ እዚያ ነው አፈሩ የማማ ያባባ። ስሳብ እሔዳለሁ ቢሰበርም እግሬ አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ። አለብኝ ቀጠሮ ከትውልድ አገሬ ካሳደገኝ ጓሮ። ኮሎኝ ጀርመን 1959 ዓ.ም
Mostrar todo...
​​ድምጽ አልባ ፊደላት ፀጉሩን አንጨብሮ ፂሙን አጎፍሮ ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት ሂድና ታዘዘው ስጠው አንድ ድራፍት ቅዳለት ደብል ጂን ሃሳቡን ይርሳበት በፂሙ መጎፈር በፀጉሩ መንጨብረር ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ነገር እዛም ከጨለማው ብቸኝነት ውጧት ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችው ወጣት ሂድና ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት ምጋ በተፋችው በጭሶቹ መሃል ሴትነት ሲበደል እህትነት ሲጣል እናትነት ሲጎድል ይታየኛል ቋንቃ ይታየኛል ፊደል። ➮ከኤፍሬም ስዩም ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢ Join https://t.me/joinchat/AAAAAFATKJuzWIXHGZ_AYQ
Mostrar todo...
Ethio ግጥም

@Messifun Send your personal or any poem you want to be posted Link

https://t.me/joinchat/AAAAAFATKJuzWIXHGZ_AYQ

For any comments use this bot @shortethiopoemBot You can also send your poem and anything feel free.

. . ለውጥ ነውጥ ይዞ ከመጣ በኋላ ፣ እንዴት እንተኛ? "ኢትዮጵያ" ሚል ሁሉ ፣ ይባላል "ነፍጠኛ" ፍርድ ቤት ይሾማል ፣ የኳስ ሜዳ ዳኛ ቢረግጡን ቢረግጡን ፣ ኳስ ህዝቦቹ እኛ ዳኛው ምን ሊገደው? ለሚጠልዘን ነው ፣ ግቡን የሚፈርደው። ( በላይ በቀለ ወያ) Join https://t.me/joinchat/AAAAAFATKJuzWIXHGZ_AYQ Send your poem @shortethiopoemBot
Mostrar todo...
Ethio ግጥም

@Messifun Send your personal or any poem you want to be posted Link

https://t.me/joinchat/AAAAAFATKJuzWIXHGZ_AYQ

For any comments use this bot @shortethiopoemBot You can also send your poem and anything feel free.

ለሐያት መዳን ምክንያት እንሁን 🙏 *** ሀያት ኢብራሂም ኡመር ትባላለች:: የ 11ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን እድሜዋ 17 ነው። በደረሰባት ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ህመም ዲያለሲስ እየተደረገላት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ቆይታለች። አሁን ላይ ሁለቱም ኩላሊቶቿ ከጥቅም ውጪ ስለሆኑ ወደ ቀድሞ ጤንነቷ እንድትመለስ ያለው አማራጭ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ብቻ እንደሆነ ከሃኪሞች ተነግሯታል። የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ ወደ ውጪ ሀገር መሄድ የግድ ይኖርባታል። ለዚህም ህክምና ሁሉንም ሂደት (process) ጨምሮ እስከ 2,000,000 (ሁለት ሚሊየን) ብር ያስፈልጋታል!!! ይህን ገንዘብ ለመሸፈን የሀያት ቤተሰቦች ወገኖቻችን እርዱን አግዙን እያሉ ወደ ህብረተሰቡ ጥሪ ያቀርባሉ። ሐያት ወደ ሞት ስትሄድ እያያችሁ ዝም አትበሉኝ ለመዳኔ ምክንያት ሁኑ ትለናለች! ከተረባረብን 2000( ሁለት ሺህ) ሰው ሆነን 1000 (አንድ ሺህ) ብር ብልነግስ ልጃችን፣እህታችን ድና ህልሟን ታሳካ ዘንድ ምክንያት እንሁናታለን። ሀያት ድና ትምህርቷን መቀጠል ትፈልጋለች። ደግሞ ለመዳኗ ሰብብ እንሆናለን። የቻልነውን በሙሉ እህታችንን በገንዘብ እንርዳት፣ በገንዘብ ያልቻልን በፀሎት አብረናት እንሁን ፣ ሌላው ቢቀር መረጃውን ሼር በማድረግ ሊረዷት ወደሚችሉ ሰዎች አንድ እርምጃ እናቅርባት። በገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ👇 የአካውንት ስም:— ሀያት ኢብራሂም ዑመር የኢትዮጲያን ግድ ባንክ:— 1000353443147 አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ:— 01425853981500 ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ :— 1000089014135 የሀያትን ቤተሰቦች በስልክ ለማግኘት👇 0983676776 0920942369 0912823605 ያለችበትን ሁኔታ ለመከታተል 👇👇👇👇 https://t.me/helphayat
Mostrar todo...
አስቾኳይ የእርዳታ ጥሪ ለ እህታችን !! ★ በቅንነት ሼር ሼር ሳያድርጉ እንዳያልፉ የሕይወት አድን ጥሪ ወገን ለወገን ደራሽ ነውና #ETHIOPIAN || ሀያት ኢብራሂም ኡመር ትበላለች የ 11class ተማሪ ነች በ ባሌ ጎባ ነዋሪ ስትሆን በደረሰበት ከፍተኛ በሆነ የኩላሊት ህመም ሁለት #ኩላሊቶቹዋ ከጥቅም ውጪ ሆነው ዲያለሲስ እየተደረገላት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ትገኛልች ። ውድ ወገኖች ለእህታችን በሃኪሞች በተነገረው የቀድሞ ጤንነቱ እንዲመለስ ያለው አማራጭ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ብቻ እንደሆነ #የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ ወደ ውጭ ሃገር መሄድ ይኖርበታል ለህክምና በጠቅላላ 2,000,000(ሁለት ሚሊዮን ብር)ያስፈልጋታል ውድ ወገኖች ወገን ለወገን ደራሽ ነውና ለህታችን #ህይወት ለመታደግ የእርዳታ እጆቻቹ እድትዘረጉለት ዘንዳ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን መርዳት ባትችሉ እንኳን ለሚረዱ ሰው ሼር በማድረግ እድተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን! የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር +251925386501 እንዲሁም ቤተሰቡዋ ጋር 0920942369 0912823605 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ !! በቅንነት ሼር ያድርጉ
Mostrar todo...