cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የቡታጅራ ሰለፍዮች ቻናል

Publicaciones publicitarias
1 134
Suscriptores
+624 horas
+317 días
+3230 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

👉 ዓሹራእና ምንዳውዓሹራእ ማለት የሙሐረም ወር 10ኛ ቀን ሲሆን ከነብዩላሂ ሙሳ አስገራሚ ታሪኮች አንዱን የሚያስታውሰን ቀን ነው። ➧ ነብዩላሂ ሙሳ ፊርዓውን ህፃናቶችን በሚያርድበት ዘመን ተወልደው በራሱ ቤት እንዲያድጉ አላህ ያሻውን ሰሪ የሆነው ጌታ አደረገ። ይህም ፊርዓውን በይተል መቅዲስ አካባቢ የተነሳ እሳት የግብፅን ምድር ሲያጠፋ በህልሙ ያይና ለጠንቋዮቹና ድግምተኞቹ ሲነግራቸው ከእስራኤላዊያን የሚወለድ ህፃን የንግስናው  መጥፊያ ሰበብ እንደሚሆን ነግሩት። ፊርዓውንም ከሚወለዱት ህፃናት ሴቶቹ ቀርተው ወንዶቹ እንዲታረዱ አዘዘ።ይህ ነገር አገልጋይ እንዳያሳጣቸው የፈሩት ግብፃዊያን ፊርዓው ዘንድ ሄደው አቤቱታ ሲያቀርቡ አንድ አመት የሚወለደው ተትቶ በሌላኛው አመት የሚወለደው እንዲታረድ አዘዘ። የአላህ ፍላጎት ሆነና ነብዩላሂ ሙሳ ወንድ ህፃናቶች በሚታረዱበት አመት ተወለዱ። የእስራኢላዊያን ህፃናት መወለድ የሚጠባበቁ ሰራዊቶች በመኖራቸው የነብዩላሂ ሙሳ እናት ጊዜዋ በመድረሱና አመቱ ወንድ ህፃናት የሚታረዱበት በመሆኑ ጭንቅ ውስጥ ገባች። የተፈራው አልቀረም ህፃኑ ተወለደ። እናት ምን ይዋጣት!!!? ↪️ አላህ ሁሉን ቻይ መሆኑን ሊያሳያት በሳጥን አድርገሽ ወደ ቀይ ባህር ወርውሪው የሚል መልእክት እንዲመጣላት አደረገ። ወረወረችውም። ወደ አላህም ፍፁም ተማፀነች። አላህም ልጇን እንደሚመልስላት ቃል ገባላት። ባህሩ ሳጥኑን ወደ ፊርዓውን ቤተመንግስት እየነዳ አደረሰው። የፊርዓው አገልጋይ ሴቶች ሳጥኑን አገኙት ሲከፍቱት የሚያምር ህፃን ነው!!!። ወደ ቤተመንግስት ተወሰደ። ኣሲያ የፊርዓው ባለቤት የአይናችን ማረፊያ ይሆናል ልጅ አድርገን እንያዘው አትግደለው አለችው ተቀበላት።     ➲ ረሃብ ይዞት ሲያለቅስ የሚቀርብለት ጡት በሙሉ እንቢ አለ። ምናልባት የሚስማማው ጡት ከተገኘ ብለው ሴቶችን ሲፈለጉ እህታቸው ማንነቷን ደብቃ አንድ ህፃናት በሙሉ ጡቷን የሚጠቡላት ሴት ላመላክታችሁ ወይ ብላ ጠየቀች አው አሉ። እናታቸው ወደ ቤተመንግስት መጣች!!!። ሱብሃናላህ በፊርዓውን ቤተመንግስት በእሱ ተንከባካቢነት በእናታቸው ጡት እንዲያድጉ አላህ አደረገ። በወቅቱ እስራኤላዊያን በቂብጦች የመከራ ገፈት ይጎነጩ ነበር። አላህ በሙሐረም 10ኛ ቀን ፊርዓውንን ከነሰራዊቱ አጥፍቶ እሳቸውንና ህዝቦቻቸውን ነጃ አወጣ። የአላህ መልእክተኛ ነብዩ ሙሐመድ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ወደ መዲና ሲሄዱ አይሁዶች ይህን ቀን ሲፆሙ አገኙዋቸው። ለምንድነው የምትፆሙት ብለው ሲጠይቁዋቸው ይህ ቀንማ አላህ ፊርዓውን አጥፍቶ ሙሳን ያዳነበት ቀን ነው። ለዚህ ነው የምንፆመው አሉዋቸው። እሳቸውም ለሙሳማ እኔ ከናንተ የቀረብኩኝ ነኝ ብለው መፆም ጀመሩ ተከታዮቻቸውንም እንዲፆሙ አዘዙ። ያለውንም ምንዳ ሲናገሩ እንዲህ አሉ:– "صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ وَصِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ"     رواه مسلم   ( 1162). "የዓረፋ ቀንን መፆም ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የዓሹራእ ቀንን መፆም ደግሞ ያለፈውን አመት ወንጀል ያስምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።" ♻️ አዩዶችን ለመኻለፍ አላህ ካቆየኝ የሚመጣውን አመት ዘጠነኛውን የሙሐረም ቀን እፆማለሁ ብለው ነበር። ከዚህ በመነሳት የሙሐረምን ዘጠነኛና አስረኛ ቀን መፆም ይወደዳል። አብዛኛዎች ፉቀሃዎች ዘጠነኛ አስረኛና አስራ አንደኛውን ቀን መፆም ሱና ነው ይላሉ። ነገር ግን ከመረጃ አንፃር ዘጠነኛና አስረኛው ነው። ይህ ካልተቻለ አስረኛና አስራ አንደኛውን በመፆም አይሁዶችን መኻለፍ ይቻላል።         አላህ ይወፍቀን። ከተወሰነ ማስተካከያ ጋር በድጋሚ የተለቀቀ። http://t.me/bahruteka
Mostrar todo...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

ስለዓሹራ ፆም በኡስታዝ አብዱልቃዲር[አቡአብዱረህማን] ሐምሌ 08/11/2016 በእለተ እሁድ በቡታጅራ ኹለፍኡራሺዲን መስጅድ የተደረገ ሙሀደራ https://t.me/butajiraa
Mostrar todo...
ስለ_ዓሹራ_ፆም_በኡስታዝ_አብዱልቃድር_1.m4a11.78 MB
ኡስታዝ በህሩ ተካ ጨርሷል:: 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/butajiraa
Mostrar todo...
የቡታጅራ ሰለፍዮች ቻናል

ዳዕዋ ሰለፊያ

https://t.me/butajiraa

Photo unavailableShow in Telegram
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/butajiraa
Mostrar todo...
ኡስታዝ በህሩ ተካ ጀምሯል
Mostrar todo...
Photo unavailableShow in Telegram
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/butajiraa
Mostrar todo...
ኡስታዝ
Mostrar todo...
የኹለፋኡራሺዲን የዳዕዋ ፕሮግራም ቀጥታ ስርጭት ይተላለፍል
Mostrar todo...
01:24
Video unavailableShow in Telegram
11.09 MB
Elige un Plan Diferente

Tu plan actual sólo permite el análisis de 5 canales. Para obtener más, elige otro plan.