cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የስንኝ ቋጠሮ

የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው። ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!

Mostrar más
Advertising posts
1 988Suscriptores
-124 hours
+117 days
+4430 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ሰላም እንዴት ናችሁ የተለያዩ ቪዲዮችን ለማህበራዊ ሚዲያ ቀርፃችሁ Edit ለማድረግ የጊዜ እጥረት እና የክህሎት ማነስ ላጋጠማችሁ Content Creater መልካም ዜና አለኝ በዝቅተኛ ዋጋ የቀረፃችሁትን Video ለእይታ በሚያምር መልኩ Edit አድርገን የእርሶን Social Media እናሳድጋለን 0932675770 ይደውሉ!!
Mostrar todo...
ሀሳቤም አመሌም አንድ ሆኖ ሳለ ከትዝታ አይተርፍም ፍቅርን ያስተዋለ የልቤ ደጃፉ መች ተዘግቶ አደረ እንዳያጣው እያልኩኝ መልሶ ካልቀረ ስንቱን አያለሁ አንተ እየመሰልከኝ ስላንተ እያለሙ መኖር አይታክተኝ ህይወት እንዳለበት በትዝታ መሀል ልቤ ታገስ እንጂ ለምን ይከብሀል       መንገዱ ቢያርቀው ትዝታ ያመጣዋል     የመለየቱን ቀን ኧረ ማን ያውቀዋል      መችስ ትዝታ እንደ ሰአት ያልፋል       እስከሞት ድረስ በልብ ውስጥ ይኖራል @gitmv
Mostrar todo...
መች እረሳሀለው አልወጣህ ከልቤ❤ ለሰከንድ ለአፍታ አልራክም ከሀሳቤ🧠 ለብቻዬ ስነድናፍቆት አይሎብኝ🙍‍♀️ አታየኝም 👀አባ ፍቅርህ አጓሳቁሎኝ🔗🖇   በእውነት አልተመቸኝአልደላውም ጎኔን ችላ አትበለኝ ባክህ አታሳንስ ፍቅሬን      እኔ ሰበበኛ ሀዘን የማያጣኝ😭   ፍቅርህ አስከንፎ ካንተ ደጅ አመጣኝ🚶‍♀️🚶‍♀️     ተው ✋ይቅርብኝ ተዋብሽ አትበለኝ🥀 ከጎኔ ከሌለህ ምንም አያምርብኝ ባይሆን ስትመጣ አንተ እቅፍ ስታደርገኝ🤗 የነጠፈው ወዜ ዳግም ተመልሶ የዛኔ ያስውበኝ👩   ያንን ቀን ወደድኩት አንተን ያጋመደኝ💏💑 ደስ የሚል ስቃይ😌 በላዬ ሾመኝ 😊 ደሞም ናፈኩት የተስፋውን ቀን አብረን ምንውለው ማንም ሳያሳቀን👫 ለተራበው ልቤ ባክህ ቶሎ ናለት🚶‍♂️ መኖር አቅቶታል ትዝታህ አዳክሞት🙇‍♀️ ወይ አላገኘውህ ወይ ትቼ አልተውኩ እማኝ በሌለበት ልቤን ላንተ ተውኩ 😌😌             ❤❤❤❤ገጣሚ   @gitmv                           ማህሌት
Mostrar todo...
እውነት እየዘቀጠ ስፍራን እያጣ ሀጥዕ እየለመለመ እና ስፍራን እያገኘ በመጣበት በዚህ አለም የህይወት ፍርድ ተገማድሎበት መንገደኛው በሙሉ ብቻውን ቢያወራ እና እብዱን ከ ጤነኛው መለየት ቢያዳግት ተአምር አይደለም ሰው ሁሉ አብዷል! ነገር ግን የሚያስደንቀው ነገር የሰው የእብደት ምክኒያት በሙሉ ምድራዊ መሆኑ ነው! አዳሜው ሄዋኔው በሙሉ ትኩረቱን አፈር ላይ ሰፍቶታል ማበድ ብርቅ ባይሆንም ያበደበት ምክኒያት ግን እብደቱን ልዩ ያደርገዋል! ንጉስ ዳዊት በንግስናው ወራት እርቃኑን ሲዘምር መቼስ ንጉስ ነው ሁሉ በ እጁ ሁሉ በደጁ የሆነለት ሚፈልገውን ነገር ሳይንቀሳቀስ አዞ ማስመጣት የሚችል በኑሮ ቀውስ ነው ጨርቁን የጣለው ብንል ውሃ የማያነሳ ብይን ይሆንብናል። ጨርቅ መጣል የ እብደት መገለጫ መሆኑ አያከራክርም ሆኖም የዳዊት ጨርቅ መጣል ግን መንሰኤው ከላይ ነው። ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኛው ሰው የሆነ % አብዷል ኑሮ በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ ሁላችንም ማበዳችን አይቀርም። የኔ ጥያቄ ግን ማበዳችን ካልቀረ ለምን እብደትን አንቀድመውም? የሚል ነው! ለዳዊት የአቻ ነገስታቶች ስጋት ሳይበግረው የሚስቱ ማፈር ሳይበግረው አንድ አንድ ትኩረቱን የሳበ አምላክ ነበረው! ከ አምላኩ አንፃር ሌሎች ጉዳዮች በሙሉ ቀለሉበት ዘመን ሲከፋ ነገር ሲቀያየር ሁኔውታዎች ሲለወጡ የማይናጋ መሰረት እንዲኖረን ትኩረታችንን እርሱ ብቻ ይውሰደው ተባረኩ! ወንድማችሁ ሞገስ ነኝ! @gitmv
Mostrar todo...
#3_ሰአት_ሙሉ_የ_ቲክቶክ_ተንቀሳቃሽ_ምስል_እያየን_3_ደቂቃ_መፃፍ_ማንበብ_ተራራን_የመግፋት_ያክል__ሚከብደን_ለኛ_ለዘመኑ ወጣቶች አጭር መጣጥፍ መፃፍ ራሱ ድንጋይ ላይ ውሃን እንደማፍሰስ የሚቆጠር ቢሆንም ድሮ ልጆች እያለን አምሳ ሳንቲም ይዘን ዘፈኑን፣ ኮሌክሽኑን፣ እና ሙሉ የ ህንድ ፊልም ከ 3-4 ሰአት የሚያህል ቁጭ ብለን ለማየት የነበረን #ትዕግስት አሁን ስም ብቻ ሆኖ መቅረቱን ሳስብ ይገርመኛል። አሁን ላይ ላለን ወጣቶች አንድ ነገር ላይ ረጅም ሰአት መቆየት የንገፈግፈናል ቤተክርስቲየን ገብተን 20 ደቂቃ ስንቀመጥ የሚያፍሽገን መፅሃፍ ቅዱስን ወይም ሌሎች መፅሃፍትን ለማንበብ ስንቀመጥ ከሶስተኛው ገፅ በሁአላ የሚያቁነጠንጠን ትምህርት ለማጥናት ስንቀመጥ አይናችን ውሃ የሚቋጥረው ነገር ለምን ይሆን? አሁን ላይ በ ሃገራችን ሆነ በ አፍሪካ ብሎም በ አለም ላይ ለተጋረጠብን ድቅድቅ ጨለማ ብርሃን መሆን የምንችለው በ አንድ ነገር ላይ ጥልቅ የሆነ እውቀት እና መረዳት ሲኖረን ለዛ ነገር ፈላጊ(demand) አቅርቦት(supply) እንሆናለን። ለ አንድ ነገር ጥልቅ የሆነ መረዳት ሊኖረን የሚችለው በዛ ነገር ላይ መቆየት ስንችል ብቻ ነው። ስለዚህ እዚህም እዚያም እየረገጥን ወደ ጎን ከምናሰፋ የተወሰነ ቦታ መርጠን ወደ ጥልቅ ብንቆፍር ምንጭ እናገኛለን ተገፍተን የማንወድቅ ስር የሰደድን እንሆናለን። እንታገስ! እንቆይበት! ወንድማችሁ ሞገስ ነኝ። ከታዘብኩት @gitmv
Mostrar todo...
ቃል ነበረ በሰው የተሰበረ እንደ አሞራ ገደል የተሸረሸረ ለሰው የተሰጠ በሰው የተሻረ ቃል ነበረ! እንደ ወርቅ የነፃው ከውሃ እኩል የጠራው ድብልቅልቅ ብሎ ዛሬ ላይ ቢያጣ ከውሸት ሚያጠራው ቃሎች? ክብራን ነበሩ ልክ እንደ እንቁ ዛሬ ላይ ተገፍተው ተጥለው ቢወድቁ ዛሬ ላይ! ሚያነሳቸው አጥተው ቢመስሉ ትቢያውን ውስጣቸው ንፁ ነው አይመስሉም ጣይውን ጣይውን ቢመስሉ ከድሮም አይኖሩ ለኛም አይሰጡን ከላይ ከእግዜሩ                                  ✍️🏽በሰለሞን
Mostrar todo...
ለምን ቀረሽ ሳልኖር ካንቺ ጋር፣ ሳላቀው ስሜቱን ሳልኖር በቅፍሽ ውስጥ፣ ሳለየው ጠረንሽን ሳይቀር ልቤ ውስጥ። ላክሽኝ ተስፋ ሞልተሽ ከማላቀው ሰው ጋር። ጉንጮቼን ደባብሰሽ አቅፈሽ ስትስሚኝ፣ እንባዬን ጠራርገሽ በስስት ስታይኝ፣ መች ገባኝ እማዬ ቻው እንደምትይኝ፣ እመጣለሁ ልጄ መሸት ሲል ቀኑ ነበር እኮ ያልሽኝ። ቀኑም መሸት ሲል ጀንበር አዘቅዝቃ ወደ ቤቷ ገባች፣ ተረኛ ጨረቃም በከዋክብት መሀል አሸብርቃ ወጣች። እኔም ወጣሁ ከቤት መምሸቱን አይቼ፣ ከበራፉ ቆሜ እጠብቅሽ ጀመር እስካይሽ ጓጉቼ፣ አቅፌ ልስምሽ አጆቼን ዘርግቼ።         ግን ግን ግን      አልመጣሽም እማ ለምን እንደቀረሽ ሚነግረኝ አጣሁ፣ የኔንም መጠበቅ ላንቺ የሚነግር ተላላኪም አጣሁ። ታዲያ ለምን ቀረሽ እመጣለሁ ብለሽ? ምን እንቅፋት ያዘሽ ልጅሽ እንዳታይሽ።                                           MW                                     13-07-2015
Mostrar todo...
ቶሎ ና🏃💨 ቆሜያለው ከደጁ 🏠ናፍቆትን አርግዤ😔 ትመጣለህ👣 የሚል ትንሽ ተስፋን ይዤ ከብርዱ እንድሸሸግ እቅፍን ናፍቄ ከጉያዬ ውስጥ ፍቅርን ❤አምቄ          እየጠበኩህ ነው👤            .            .     ብርዱ  ሳይጠናብኝ እባክህ ቶሎ ና      ብቻዬን እንዳልሆን ስጎዝ በጎዳና ትመጣልኛለህ ከቅፍህ እንድኖር ከአለም እርቀን በፍቅር እንድንበር💓                   አሰብከው አለሜ💑                           .                           . አነስ ባለ ጎጆ በእሳት በሞቀ በ'ቅፍህ ውስጥ ሆኜ ፍቅርን ባመቀ ልባችን ታድሞ ከጣፋጩ ዜማ ከእሳቱ ዳር🔥 ሆነን መውደድን ስንሰማ               ለማይደገመው ለዚ ጣፋጭ🍯 ጊዜ               ዝናብ ☔ብርዱን ችለህ ቶሎ ና በጊዜ⏳ Be Mahi
Mostrar todo...