cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የተወደዱና የተመረጡ ፅሁፎች Ⓦ👈👈👈

ከራሴ የሆነ ምንም የለም።ደስ ከሚለኝ ቅዱስ ቃል "የወደዳቸውን "እስከ" መጨረሻው ወደዳቸው" እውቀትን ማወቅ ወደ "እውነት" ደጃፍ ያደርሳል እውነትንም ማወቅ ያድናል ለማወቅ ግን ማንበብ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
199Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🔴“And in the end it’s not the years in your life that count; it’s the life in your years.” ~ Abraham Lincoln 🌀የብዙዎቻችን ምኞት ረጅም ዓመት መኖር ነው… ብዙ ዕድሜ ማስቆጠር… ትልቁ ምርቃታችን ‘ዕድሜ ይስጥህ’ አይደል?… ‘ዋናው ጤና’ ስንልም ከደሕንነት በላይ በሚያሳስበን ረጅም ዓመት መኖር ላይ ተመስጠን ነው…  ❤️የኑረት መቆርቆር ቢጠን፣ የደስታ ከረጢት ቢያጥጥ፣ ልብ በበደል ቢጠለሽ፣ ደዌ ከፍቶ ቢያንገሸግሽ… የቀጣዩን ቀን ብርሃን ለማየት መጓጓት ያለ ነው… ‘የምን ተስፋ መቁረጥ’ ይላል ሁሉም… ‘የነገን ማን ያውቃል?’… 🔴ወጣት ስንሆን ደግሞ የሁልጊዜነት ምኞታችን ራሱን በሌላ መልክ ይገልፃል… በሁሌአዊነት… ረጅም ዓመት ለመኖር የመፈለጋችንን ያህል ሳናውቀው ወጣትነትን ለማዝለቅ እንፍጨረጨራለን… ስሜቱ እጅግ ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ ጉልምስናን ዘለን የእርጅናን በር ስናንኳኳም አይለቀንም… ልብህ የወጣትነት ዝማሬዋን አለመተዋ እኮ በጎ ነገር ነው… በእርጅና ውስጥ ያለን ‘እጅ መስጠት’ ለመቋቋም ይረዳሃል… የዕድሜ መግፋት ሥጋት ውርዝናን የሙጥኝ አስብሎህ ሲሆን ግን ይገርማል… 💙ልጅ ወልደው ዘላለማዊነትን መቋደስ የሚሹ አሉ… ታሪክ ሰርተው፣ ዝና ሸምተው፣ በጎ ውለው የመቃብርን የዕድሜ ቁጨት ስንዝር ከጋት ለማሻገር የሚታትሩም አሉ… ማንም ሰው ግን ድርጊቱን ‘ዕድሜ ማርዘሚያ’ ነው ብሎ አያምንም… ውስጡ ግና የስሙን ሕላዌ የማስቀጠል ምኞት ማድፈጧ አይቀርም… 🔵“Do not act as if you were going to live ten thousand years. Death hangs over you. While you live, while it is in your power, be good.” ~ Marcus Aurelius ❤️ለመኖር የመጓጓታችንን ያህል መኖራችን ዋጋ እንዲኖረው እንተጋ ይሆን?… ከውልደት እስከ ሞት የሚዘረጋው የስብዕናችን ተረክ ሁነኛ ልኩስ ምንድነው?… _ 🔴የሆነ ጊዜ ላይ ደርሰህ ከቤተሰብ እስከ ማሕበረሰብ፣ ከመንደር እስከ ሃገር በሚዘረጋው የኑረት ጎዳና ላይ አሻራህን የሚያሳይ አንዳች እውነት ትፈልጋለህ… እናም እንዲህ ብለህ ትጠይቃለህ – ‘በእኔ መኖር ምክንያት ምን ተቀየረ?’… አበርክቶህ ምንም ያህል ቢሆን በተቀበልከው ኖረህ ስታልፍ ለሌሎች የምታቀብለው ተክቶህ እንዲቀጥል ትሻለህና ‘መዋጮዬ ወዴት አለ?’ ማለትህ አይቀርም… 💙ዛሬ የምትኖረውን ኑሮ እንድትኖር ትናንት ዋጋ የከፈሉ ሰዎች ነበሩ… ለነዚህ ሰዎች ወደኋላ ሄደህ ብድር አትመልስ ይሆናል… ወደፊት ሄዶ ዕዳህን የሚከፍል ስንቅ ማኖር ግን ግዴታህ ነው… አልያማ ሰው ኖሮ ካልጠቀመ ሄዶ እኮ አያጎድልም – ባለዕዳነቱን አይሰርዝም እንጂ… አንዳንዱ ግን ይሙት… ምናልባት መኖሩ የከለላት ጸሐይ ለመድመቅ ዕድል ታገኝ ይሆናል… 🔵የመኖር ውሉ በራስ ታዛ መድመቅ ብቻ አይደለም… የሌሎችንም ማገር ማጥበቅ እንጂ… በበጎ ቃል – የታመመ ልብ ትፈውሳለህ፣ የጎበጠ ሞራል ታቀናለህ… በፍቅር ኃይል – ቂም በቀል ትሽራለህ፣ ጥላቻን ትንዳለህ… ሰው ነህና ብዙ የምትሰጠው ይኖርሃል… 💙ብቻ… በራስ ዛቢያ ከጦዙበት እልፍ ዓመት ሌሎችን የቀላቀሉበት ክራሞት፣ ለብቻ ከኖሩት የዕድሜ ብዛት ለትውልድ ያኖሩት ጥቂት ብልሃት የበለጠ ዋጋ አለው… _ 🔴ሞትን ለምን እንደምንፈራ አስበህ ታውቃለህ? – ኖረን ስለማናውቅ ነው!! “Even death is not to be feared by one who has lived wisely.” ~ Gautama Buddha ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ አይኑርባችሁ።❤️ ✍ ደምስ ሰይፉ @Rightinglove @Rightinglove @Rightinglove
Mostrar todo...
🔴“And in the end it’s not the years in your life that count; it’s the life in your years.” ~ Abraham Lincoln 🌀የብዙዎቻችን ምኞት ረጅም ዓመት መኖር ነው… ብዙ ዕድሜ ማስቆጠር… ትልቁ ምርቃታችን ‘ዕድሜ ይስጥህ’ አይደል?… ‘ዋናው ጤና’ ስንልም ከደሕንነት በላይ በሚያሳስበን ረጅም ዓመት መኖር ላይ ተመስጠን ነው…  ❤️የኑረት መቆርቆር ቢጠን፣ የደስታ ከረጢት ቢያጥጥ፣ ልብ በበደል ቢጠለሽ፣ ደዌ ከፍቶ ቢያንገሸግሽ… የቀጣዩን ቀን ብርሃን ለማየት መጓጓት ያለ ነው… ‘የምን ተስፋ መቁረጥ’ ይላል ሁሉም… ‘የነገን ማን ያውቃል?’… 🔴ወጣት ስንሆን ደግሞ የሁልጊዜነት ምኞታችን ራሱን በሌላ መልክ ይገልፃል… በሁሌአዊነት… ረጅም ዓመት ለመኖር የመፈለጋችንን ያህል ሳናውቀው ወጣትነትን ለማዝለቅ እንፍጨረጨራለን… ስሜቱ እጅግ ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ ጉልምስናን ዘለን የእርጅናን በር ስናንኳኳም አይለቀንም… ልብህ የወጣትነት ዝማሬዋን አለመተዋ እኮ በጎ ነገር ነው… በእርጅና ውስጥ ያለን ‘እጅ መስጠት’ ለመቋቋም ይረዳሃል… የዕድሜ መግፋት ሥጋት ውርዝናን የሙጥኝ አስብሎህ ሲሆን ግን ይገርማል… 💙ልጅ ወልደው ዘላለማዊነትን መቋደስ የሚሹ አሉ… ታሪክ ሰርተው፣ ዝና ሸምተው፣ በጎ ውለው የመቃብርን የዕድሜ ቁጨት ስንዝር ከጋት ለማሻገር የሚታትሩም አሉ… ማንም ሰው ግን ድርጊቱን ‘ዕድሜ ማርዘሚያ’ ነው ብሎ አያምንም… ውስጡ ግና የስሙን ሕላዌ የማስቀጠል ምኞት ማድፈጧ አይቀርም… 🔵“Do not act as if you were going to live ten thousand years. Death hangs over you. While you live, while it is in your power, be good.” ~ Marcus Aurelius ❤️ለመኖር የመጓጓታችንን ያህል መኖራችን ዋጋ እንዲኖረው እንተጋ ይሆን?… ከውልደት እስከ ሞት የሚዘረጋው የስብዕናችን ተረክ ሁነኛ ልኩስ ምንድነው?… _ 🔴የሆነ ጊዜ ላይ ደርሰህ ከቤተሰብ እስከ ማሕበረሰብ፣ ከመንደር እስከ ሃገር በሚዘረጋው የኑረት ጎዳና ላይ አሻራህን የሚያሳይ አንዳች እውነት ትፈልጋለህ… እናም እንዲህ ብለህ ትጠይቃለህ – ‘በእኔ መኖር ምክንያት ምን ተቀየረ?’… አበርክቶህ ምንም ያህል ቢሆን በተቀበልከው ኖረህ ስታልፍ ለሌሎች የምታቀብለው ተክቶህ እንዲቀጥል ትሻለህና ‘መዋጮዬ ወዴት አለ?’ ማለትህ አይቀርም… 💙ዛሬ የምትኖረውን ኑሮ እንድትኖር ትናንት ዋጋ የከፈሉ ሰዎች ነበሩ… ለነዚህ ሰዎች ወደኋላ ሄደህ ብድር አትመልስ ይሆናል… ወደፊት ሄዶ ዕዳህን የሚከፍል ስንቅ ማኖር ግን ግዴታህ ነው… አልያማ ሰው ኖሮ ካልጠቀመ ሄዶ እኮ አያጎድልም – ባለዕዳነቱን አይሰርዝም እንጂ… አንዳንዱ ግን ይሙት… ምናልባት መኖሩ የከለላት ጸሐይ ለመድመቅ ዕድል ታገኝ ይሆናል… 🔵የመኖር ውሉ በራስ ታዛ መድመቅ ብቻ አይደለም… የሌሎችንም ማገር ማጥበቅ እንጂ… በበጎ ቃል – የታመመ ልብ ትፈውሳለህ፣ የጎበጠ ሞራል ታቀናለህ… በፍቅር ኃይል – ቂም በቀል ትሽራለህ፣ ጥላቻን ትንዳለህ… ሰው ነህና ብዙ የምትሰጠው ይኖርሃል… 💙ብቻ… በራስ ዛቢያ ከጦዙበት እልፍ ዓመት ሌሎችን የቀላቀሉበት ክራሞት፣ ለብቻ ከኖሩት የዕድሜ ብዛት ለትውልድ ያኖሩት ጥቂት ብልሃት የበለጠ ዋጋ አለው… _ 🔴ሞትን ለምን እንደምንፈራ አስበህ ታውቃለህ? – ኖረን ስለማናውቅ ነው!! “Even death is not to be feared by one who has lived wisely.” ~ Gautama Buddha ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ አይኑርባችሁ።❤️ ✍ ደምስ ሰይፉ @Rightinglove @Rightinglove @Rightinglove
Mostrar todo...
ሰውዬው ከውሻው ጋር • ሰውዬው ከውሻው ጋር እየተጓዘ ነው። የአካባቢውን ውበት በተመስጦ እያደነቀ። ድንገት ግን አንድ ነገር ተከሰተለት። ለካንስ ሞቷል። አዎ! ለካንስ እሱም ሆነ ይሄ እግሩ ስር ኩስ ኩስ የሚለው ውሻ ከሞቱ ሰነባብተዋልና። መሞቱን መዘንጋቱ ደንቆታል። ምናልባትም ገና በቅርቡ በመሞቱ ይሆን? ይሆናል። ብቻ እሱና ውሻው ጉዞዋቸውን ቀጥለዋል። እናም ከአንድ ካማረ ቤተመንግስት ከሚመስል፣ የተሰራበት እብነ በረድ ከሚያንፀባርቅ ትልቅ ህንፃ አጠገብ ሲደርስ ቆመ። በትልቅ ኮረብታ አናት ላይ በታላቅ ግርማ ሞገስ ጉብ ያለው ሕንፃ ከፊቱ በአንፀባራቂ ቅስት አሸብርቋል። በቅስቱ ስር የሚያምር መግቢያ ተመለከተ። ወደ መግቢው የሚወስደው መተላለፊያ በወርቅ ተለብጧል። "እንዴት ያለ ቅጥር ነው" ሲል አሰበ። በመተላለፊያው ወደ በሩ ሲጠጋ የቅጥሩ ጠባቂ የመሰለ ሰው ተመለከተ። "ይቅርታ! ይህ ቦታ ምን የሚሉት ቦታ ይሆን?" ጠየቀ ሰውዬው። "መንግስተ-ሰማያት ነው ጌታው" ሲል መለሰ ጠባቂው። "ግሩም ነው" አለ ሰውያችን። "ጥቂት ውኃ ማግኘት እንችላለን? እኔና ውሻዬ በውኃ ጥም ጉሮሮዐችን እንዴት ተቃጥሏል መሰለህ።" "ምን ችግር አለ" አለ ጠባቂው። "አሁኑኑ ጥም ቆራጭ ቀዝቃዛ ውኃ ይቀርብላችኋል" ጠባቂው ይሄን ብሎ በሩን እየከፈተ "ግን ጌታው" አለ "ወደዚህ ወደ መንግስተ-ሰማያት ገብተህ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ ሳይሆን ሁሉንም በረከት መቋደስ ትችላለህ። ግን ወደዚህ መግባት ምትችለው ብቻህን ነው። የቤት እንሰሳትም ሆነ ሌላ ተቀጥላ ጓደኛ ይዞ መግባት አይቻልም" አለ፣ ሰውዬው እግር ስር ኩስ ኩስ እያለ የሚከተለውን ውሻ እየተመለከተ። ሰውዬው እጢው ዱብ አለ። ትንሽ አመነታ። ግን ወሰነ። ጓደኛዬን፣ ውሻዬንማ ጥዬ አልገባም ብሎ ጉሮሮው በውኃ ጥም እየነደደ ጀርባውን ለሚያምረው ህንፃ ሰጥቶ ጉዞውን ቀጠለ። ከረጅምና አድካሚ ጉዞ በኋላ ደግሞ ሰውዬውና ውሻው ከአንድ ኮረብታ ላይ ደረሱ። ከረብታው ስር ወደ አንዳች ቅጥር ግቢ የሚያመራ በጫቃ የላቆጠ መንገድ ይታያል። መንገዱ በእርሻው ውስጥ የሚያልፍ ሆኖ መላው ቅጥሩ አንዳችም አጥር የለውም። በሩ መቼም ተዘግቶ የሚያውቅ አይመስልም። መቼም ተዘግቶ ወደ ማያውቀው በር ሲጠጋ ዛፍ ስር ደገፍ ብሎ መጻሕፍ የሚያነብ አንድ ሰው ተመለከተ። "ይቅርታ የኔ ወንድም! ጥቂት ውኃ ይኖርሃል? በውኃ ጥም…" ከማለቱ በቅጥር ግቢ ውስጥ ያለው ሰውዬ "እንዴታ! እዛ ጋር ቧንቧ አለልህ። ሄደህ የፈለከውን ያክል መጠጣት ትችላለህ" ሰውዬው ቀጠለና ጠየቀ "ይሄ ጓደኛዬ" ብሎ ወደ ውሻው እየጠቆመ "ውኃ ጥሙ ክፉኛ በርትቶበታል። እሱም ገብቶ መጠጣት ይችል ይሆን?" "ይችላል!" አለ ሰውዬው። "እንዳውም ከቧንቧው አጠገብ መጠጫ አለልህ" ሰውዬውና ውሻው ተደስተው ወደ ቅጥሩ ገብተው፤ ጥማቸው እስኪ ቆርጥ ከጠጡ በኋላ ወደ ሰውዬው ተመልሰው መጡና ሰውዬው እንዲ ሲል ጠየቀ "ለመሆኑ ይሄ ቦታ ምን የሚሉት ቦታ ይሆን?" "መንግስተ-ሰማያት ነው" ሲል መለሰ ሰውዬው። አይኖቹን እንኳን ከሚያነበው መጻሕፍ ላይ ሳይነቅል በታላቅ የረፍት ስሜት ዛፍ ስር ደገፍ ብሎ በተቀመጠበት። "ይሄማ እንዴት ሊሆን ይችላል?" አለ ሰውዬው ግራ ተጋብቶ። "ቅድም ያጋጠመኝ ያማረ ሕንፃም መንግስተ-ሰማያት ነው ብለውኛል። እንዴት ሊሆን ይችላል?" "እም!" አለ ዛፉ ስር የተቀመጠው ሰውዬ መጻሕፉን እልባት አሲዞ እያጠፈ። "ያ ታላቅ ቅስጥ ያለው ባለእምነበረዱ ሕንፃ? መንገዱ በወርቅ የተለበጠው? ከእሱ ሕንፃ በማምለጥህ ደስታ ሊሰማህ ይገባሃል። እሱ ሕንፃ አላወቅከውም እንጂ፣ ንፅህና አዳነህ እንጂ ገሐነብ ነው" አለ። "እንዴት" አለ ሰውዬ በጉዳዩ ይበልጥ ግራ ተጋብቶ። "እሺ ይሁን! ይሄ መንግስተ-ሰማያት ይሁን ግን እንዴት በስማችሁ ሲነግዱ ዝም አላችሁ?" "እንዴት ዝም አላችሁ ነው ያልከኝ?" አለ ሰውዬው። "ዝም ማለት ብቻ አይደለም፥ እንዳውም በጉዳዩ ደስቶኞች ነን። አየህ" አለ ሰውዬው "ያ ላዩን ያማረ ሕንፃ፣ ያ ገሃነብ፤ ጓደኞቻቸውን ጥለው የሚሄዱ፣ ወዳጆቻቸውን በቁርጥ ቀን ጥለው የሚሄዱ፤ ሰዎችን አጣርቶ ስለሚወስድልን ደስተኞች ነን። ሸገር ሼልፍ @Rightinglove @Rightinglove @Rightinglove
Mostrar todo...
ጮሃለሁ! ========= አባቴ ተሰቅሎ፣ ወንድሜ ተቃጥሎ። እህቴ ታግታ፣ እናቴ ተቀልታ። አያቴ ተሰ'ዶ ህፃን ልጄ ታርዶ... አሞኛል! ወገን ሞቶብኛል! ሰው ተገ'ሎብኛል በማያውቀው ጉዳይ ባልገባው ጨዋታ፣ በሌለበት ግንባር ባልዋለበት ሜዳ ቀድሞ እየተመታ፣ ተጨምቆ ተጨምቆ ጠብ ላይልለት የድላቸው ፋይዳ፣ መከራ የሚገፋው እየወደቀበት የማያውቀው እዳ...። ሞት እያንዣበበ... ደክሞት ካረፈበት ከደሳሳ ቤቱ፣ ለማይሞላ ኑሮው ለማይነጋው ሌቱ። ዛች ጥርስ እያፋጨ፣ ጥይት እያፏጨ። ካራ እየተሳለ፣ ቀስት እየተሾለ... አለ! ከተፈጥሮ ታግላ፣ ጎታች ባህል ጥላ፣ ልትማር የተጋች ቀን ይወጣል ብላ። መድረሻ ተነፍጋ መንገድ ላይ የቀረች እህቴ.... የታለች? አሞኛል! ሰው ተገድሎብኛል! ሰው ተሳዶብኛል! ተፈናቅሎብኛል! ከኖርበት ቀዬ፣ የአቅሜን እጮሃለሁ ... "የሰላም፣ ፍትህ፣ የህግ ያለህ!" ... ብዬ። "የኔ አቅም ለቅሶ ነው ድምፅ ልሁናቸው ልጩህላቸው" ስል ይመጣል ሳይፈራ አሳ'ቆ ሊያፍነኝ ቃላቱን የሚስል "ምንድነሽ?" ይለኛል "ለእገሌ ለእንትና" ጉዳቴ ሳይገደው "የሟች ወገኑ ነኝ!" ንፁህ ሆኖ ሳለ ለሞት 'ሚማገደው። "የት ነበርሽ?" ይለኛል "ለምን ዛሬ?" ይለኛል... ይሳለቅብኛል ድምፄን እየለካ ስጮህም ዝምም ስል ለ'ሱ ፖለቲካ "መርጠሽ ነው" ይለኛል... መርጦ ገዳይ ካለ በየአደባባዩ፣ መርጬስ ባለቅስ ማን ይሆን ከልካዩ? መርጬ አለቅሳለሁ ለተገፋው ህዝቤ ለሞተው ወገኔ ቡድኑን አንተ አብጀው ንፁህ መሆኑ ነው የሚያገባኝ እኔ። በፈለግኩት ጊዜ በፈለግኩት ቦታ ስችል አለቅሳለሁ ሳልችል በዝምታ ፈቃጅ አልፈልግም ለራሴ ስብራት ሀዘን አስተማሪ አስታዋሽ አልሻም ላጣሁት ወገኔ የ'ጩሂለት' ጥሪ በፈለግኩት ጊዜ በፈለግኩት ቦታ ስችል አለቅሳለሁ ሳልችል በዝምታ "የማን ነሽ? ምንድነሽ? ከየት ነሽ?" ይለኛል ከየትስ ብመጣ? ገድዬ አልፎከርኩኝ ሞቶብኝ ነው እንጂ አቅሌን የማጣ ገዳይ ንፁህ ፈጅቶ በኮራበት ሀገር ለተገፋ ማልቀስ ለምነው 'ሚያስወግር? ገድሎም አይበቃውም "እሰይ" ብሎ አይረካ እንባዬን አድርቆ ሀዘኔን መቀማት አዲስ ፖለቲካ እጮህለታለሁ... ንፁሁ ሲጎዳ ባልመረጠው ደሙ ባልመረጠው መልኩ ክርስቲያንም ሙስሊም ጥፋት ከሆነበት በምርጫ ማምለኩ ለአማራ እጮሃለሁ በጅምላ ለሚያልቀው ለሚፈሰው ደሙ ለትግራይ እጮሃለሁ ጦርነት ሲጎሰም በልቶት ሰቀቀኑ፣ ስደት ለመረጠው ከገዛ ሀገሩ፣ ከገዛ ወገኑ። ለተደፈረችው፣ ለተሰበረችው እንግልት እህቴ፣ ላዘነች እናቴ ለኦሮሞ ወንድሜ፣ ለደቡብ አባቴ፣ ለሀረሪ፣ ሱማሌ፣ ቤኑሻንጉል፣ አፋር፣ ድሬደዋ ላለው ወይ አዲስ አበቤ። ለተበዳይ ህዝቤ፣ ለሞተ ወገኔ... እጮህለታለሁ! ቡድኑን አንተ አብጀው ንፁህ መሆኑ ነው የሚያገባኝ እኔ። ትናንት ጮኼያለሁ፣ እጮሃለሁ ዛሬ፣ እጮሃለሁ ነገ ሁሉም ወገኔ ነው ድምፅ የተነፈገ። እጮህለታለሁ! ... እጮሃለሁ! ©✍በአርቲስት ሜሮን ጌትነት =ጥር 2013 ዓ.ም @Rightinglove @Rightinglove @Rightinglove
Mostrar todo...
ውሃ በተሞላ ድስት ውስጥ አንዲት እንቁራሪት ብንጨምርና ከዚያም ውሃውን ማፍላት ብንጀምር፤ ውሃው እየፈላ በሄደ ቁጥር እንቁራሪቷም የሰውነት ሙቀቷን ማስተካከል ትጀምራለች፡፡ ☞ የውሃው ሙቀት ከፍተኛ እየሆነ ሲሄድ እሷም የሰውነቷን ሙቀት በዛው ልክ ማስተካከሉን ትቀጥላለች፡፡ የውሃው ሙቀት ጨምሮ የመፍላት ነጥብ (boiling point) ላይ ሲደርስ ግን ማስተካከል የማትችልበት ደረጃ ስለደረሰ እሯሷን ለማዳን ከድስቱ ዘላ ለመውጣት ትፈልጋለች ትሞክራለች፤ ግን ዘላ መውጣት አቅም አይኖራትም አትችልም፡፡ ምክንያቱም ያላትን አቅም ሁሉ ሙቀቷን በማስተካከል የውሃውን ቃጠሎ ለመከላከልና ለመላመድ ባደረገችው ተጋድሎ ጨርሳዋለችና፤ ወዲያው ትሞታለች፡፡ እንቁራሪቷን ምን ገደላት? አብዛኞቻቸችን የፈላ ውሃ እንል ይሆናል፤ እውነታው ግን ይህ አይደለም ፡፡ እንቁራሪቷን የገደላት የፈላው ውሃ ሳይሆን መች መዝለል እንዳለባት የመወሰን አቅም ማጣቷ ነው፡፡ አብዛኞቻችን ከሰዎችም ይሁን ከነገሮች ጋር ያለንን ነገር ለማስተካከልና ለመላመድ እንሞክር ይሆናል፤ ግን እስከ መቼ ማስተካከል እንዳለብንና መች መወሰን እንዳለብን ማወቅ ይሳነናል፡፡ አንዳንዴ ነገሮችን የለመድናቸውና ለኛ የማይጎዱ መስለው ይታዩናል፤ በመጨረሻው ቅፅበት ግን እንዳልለመድናቸው ቢገባንም ማምለጥና መውጣት የማይቻለን ሰአት ይሆናል፡፡ በጥፋት/ወንጀል/ መንገድ ውስጥም ስንሆን እንዲሁ ነው፤ ትንሹን ወንጀል እንለምደዋለን የሚጎዳን አይመስለንም፤ ደስታ ውስጥ ያለን ይመስለናል፤ ደስታው ሙቀት ይፈጥርልናል፡፡ ሙቀቱ ወደ እሳት የተቀየረ ጊዜ ግን . . .!!!?? ከሙቀቱ መውጣት ካልቻልን ከእሳት እንደማንወጣ እውን ነው! ሙሉ አቅም ባለን ጊዜ እንዝለል!!! @Rightinglove @Rightinglove @Rightinglove
Mostrar todo...
🔴 ጠቃሚ የህይወት ስንቅ ወዳጄ ሆይ 🔵ያለፈ ነገር አይቀዪርም ፣ ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው ፣ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር ፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነትአይገልፅም ፣ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው ፣ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና ለሁሉም ጊዜ አለው ። 🔴መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘ፕሌን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞም እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ ? ተወው በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው ።በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት አይደለም ። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋሁን ፣ አስተውል ። 🔵ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው ፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ምንድነው? ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው ፣ የድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን) እየሰሩ መኖር ነው ፣ ምንድነው ??? እባክህ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው ። 🔴አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ። መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው ፣ መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም ። 🔵የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን ስታውስ ፣ ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ ። 🔴ለራስህ ስትል መልካም ሁን ፣ በጎውንም አስብ። ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም ። አትፍረድ ፣ የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም ። ፍርድ የፈጣሪ ነው፣ ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል ፣ ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት ። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል ። 🔵ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣ አበረታታው ፣ እንደማይጠቅም አትንገረው ፣ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን ። መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ ነው ። መልካም ጓደኛ ፣ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል ታድለሃል ። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ። 🔴ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን ያስከትላል ።ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ ፣መመለስ በማትችለው ነገር ላይ አትወጠር ፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ። አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ ። 🔵 ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር ።ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው ፣ "ያስከፍላል"ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ ። ደግ ሁኑ ፣ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ በረከታቸው ሰላማቸው ልክ የለውም ። 🔴ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ ፣ ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ ሲርቅ ወይም ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል ። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ ናቸው ። በራስህ በአፈጣጠርህ ደስ ይበልህ ፣ውለህ በመግባትህ ደስ ይበልህ ። በአለህ ትንሽ ነገር ደስ ይበልህ ። 🔵ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም። እድሜህን በተመለከተ ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው ። ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳዪኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው። 🔴የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ። ሰላምና ጤና ፣ ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ። ከስብናችን ተወዶ የተቀዳ @Rightinglove @Rightinglove @Rightinglove(join)
Mostrar todo...
☯ሕሊናህን ጥለቅበት፤ አዕምሮህን ስመጥበት! ሰው’ነትህን እንድታወጣበት፣ ምንነትህን እንድታውቅበት፣ ሰው ሆነህ እንድትበቃበት፡፡ 🔑ሕሊና ለሰው ልጅ የተሰጠ ክቡር ድንቅ ስጦታ ነው፡፡ ይሄን ድንቅ ስጦታውን ለበጎ የሚጠቀመው ግን በጣም ኢምንት ነው፡፡ አንዳንዱ የሕሊናውን ሃይል ባለመረዳቱ በሆነ ባልሆነው ትርኪምርኪ ነገር ያባክነዋል፡፡ ጭንቅላቱን በማይረባ ነገር እየሞላ ሚሞሪውን የሚያጨናንቅ ቀላል ቁጥር የለውም፡፡ በትርኪምርኪና በግብስብስ ሕይወት ነፍሱን ያጨናነቀ ሺ ነው፡፡ መንፈሱን አጉድሎ፣ ነፍሱን አጎሳቁሎ፣ ስጋውን አደልቦ ውስጠቱን ዘንግቶ፣ ሕሊናውን ረስቶ ከራሱ ጋር ተኮራርፎ የሚኖር፤ ለራሱ እንኳን የማይበጅ ዓመለ ቢስ ቤት ይቁጠረው፡፡ ⚜አንዳንዱ ያላደለው ደግሞ ማሰቢያውን ለክፉ ነገር ብቻ ይጠቀምበታል፤ አዕምሮውን የተንኮል ፋብሪካ የሚያደርግ፤ ከገዛ አዕምሮው ክፋትን ብቻ የሚያመርት እጅግ ብዙ ነው፡፡ አብዛኛው ደግሞ ከማሰቢያው ጋር ሳይተዋወቅና አዕምሮውን ምንም ሳይጠቀምበት ከእናቱ ማህፀን ይዞት እንደወጣ ይዞት መቃብር ይወርዳል፡፡ ሕሊናው ሸክም ሆኖበት ከሸክሙ ያልተገላገለ ጭንቅላቱን በራሱ፤ አዕምሮውን በጫንቃው ተሸክሞ ይዞት የሚዞርም እልፍ ነው፡፡ ✨ሰው አዕምሮ ባይኖረው ምን ይሆን ነበር? ከዚህ በላይ ሊከፋ ይችል ይሆን? አዕምሮ እያለው እንኳን አዕምሮውን የማይጠቀምበት በበዛበት ዓለም ሕሊና ባይኖረው ደግሞ ምን እንደሚሆን ለመገመት እጅግ ይከብዳል፡፡ አይ…. ሰው ማሰቢያ ባይኖረው እንደዚህ ሊከፋ አይችልም ብሎ የሚያስብ አይጠፋም፡፡ አሃ ሰው ማሰቡ ነው ክፉ እንዲሆን ያደረገው እንዴ? ብለን ብንጠይቅስ ምን ይሆን የምናገኘው መልስ፡፡ 💫አንድ ጀርመናዊ ፈላስፋ፡- ‹‹ማሰብ ያማል›› ብሏል፡፡ ምን ማሰብ ይሆን የሚያሳምመው? ደግ ማሰብ ወይስ ክፉ ማሰብ? ነው ወይስ ማሰብ በጠቅላላ ራስ ያዞራል? ፈላስፋው ማለት የፈለገው እንደገባኝ ከሆነ መልካም ማሰብ ከባድ ነው፤ ክፉ ማሰብ ግን ቀላል ነው፡፡ አዕምሮ የሚጠይቀው ለሰው ሁሉ የሚጠቅመውን ማሰብ መቻል ነው፡፡ ሰውን የሚጎዳ ነገር ማሰብ እጅግ ቀላል እንደሆነ አፅንኦት ለመስጠት ይመስለኛል ‹‹ማሰብ ያማል›› ያለው፡፡ ☯አዎ ሰውን እንደራስ ለመውደድ ቅን አዕምሮ፤ ደግ ልብ ይፈልጋል፡፡ ቅንነትም ሆነ ደግነት እንዲህ በቀላሉ የሚገኝ አይደለም፡፡ ደግነትን ለመውለድ፤ ቅንነትን ለመገላገል በእውነትና በፍቅር ማማጥ ግድ ይላል፡፡ ምጥ ደግሞ ህመም አለው፡፡ ሕመሙ ግን ከወሊድ በኋላ የሚቆምና በደስታ የሚለወጥ ነው፡፡ ✨ቅንነት ዕውቀት፤ ፍቅር ጥበብ፣ ደግነት ችሎታ መሆኑ የማይገባቸው ሰዎች ግን መልካም ነገር ሲያስቡ ያማቸዋል፡፡ ሕመማቸው እንደምጡ ሲወልዱ የሚገላገሉት አይደለም፡፡ የነሱ ጤንነት መታመም ነው፡፡ ጤንነት የሚሰማቸው ክፉውን ሲዘሩ ብቻ ነው፡፡ አዎ በሱስ ለሚሰቃይ ሰው ህመሙ የሚሰማውና የሚብስበት የሱሱን ምሱን ሲያጣ ነው፡፡ ጤነኛ የሚሆነው የለመደውን ሲያገኝ ነውና፡፡ የሰው መበደል ደስ የሚያሰኛቸው፤ የወገን መሳደድ፣ የደሃ መታረድ፣ የምስኪኖች መጎሳቆል ነፍሳቸውን የሚያረካው ደግ ማሰብ የማይችሉና በጎ ማየትም ሆነ መስማት የማይሹ በተንኮል ወረርሽኝ የተያዙ፣ በዘረኝነት የታመሙ፣ በጎጥ የተለከፉ፣ ሕሊናቸውን የሸጡ እርኩሳን ሰዎች ናቸው፡፡ 💫አዎ የዚህ ሁሉ መግፍኤ መነሻው አዕምሮን ሙሉ በሙሉ መጠቀም ያለመቻል ነው፡፡ ትክክለኛውን ሰውነቱን ፈልጎ ያላገኘ የማይጠቅመውን አውሬነቱን ይወዳጀዋል፡፡ ሰውነቱን የተረዳ የሌላውን ሰውነት ይረዳል፡፡ በራሱ ሕይወት ውስጥ የጠለቀ በሌላ ሰው ሕይወት ውስጥ ጥልቅ ማለት እንደሌለበት ዕውቀት ያገኛል፡፡ ሌላው ወደራሱ ሕይወት ይሰምጥ ዘንድ ነፃ ፈቃድ እንዳለው ይረዳል እንጂ በማያገባው በሌላ ሰው ሕይወት ባህር ውስጥ ዘው ብሎ አይገባም፡፡ 💫 ከአዕምሮው ጋር የተግባባ አዕምሮውን ይስላል፤ በሣለው አዕምሮ ባህሪውን ይሞርዳል፣ ስሜቱን ይገራል፡፡ የሚቀርፅ ሕሊና በራሱ ተሰርቶ የተዘጋጀ (Ready-made) አይደለም፡፡ ገንቢ ሕሊና ቀድሞውኑ በመልካም አስተሳሰብ የታነፀ ነው፡፡ አንተ ሕሊናህን በወጉ ካልሰራኸው አንተን እንደአዲስ አይሰራህም፡፡ እንዲሰራህ ልትሰራው ይገባል፡፡ እንዲያውቅህ ልታውቀው ግድ ይላል፡፡ ወደውስጡ ስትጠልቅ ይዘህ የምትወጣው ራስህን ነው፡፡ ወደባህሩ አንተነትህ ስትሰምጥ የምታገኘው ሰውነትህን ነው፡፡ ብልህ ሰው አዕምሮውን ይሠራል፤ በሰራው ሕሊና እየተመራ የሕይወት ኮምፓሱን ያስተካክላል፡፡ 🔑ወዳጄ ሆይ…… ወደሕሊናህ እልፍኝ ጎራ በል፡፡ ውስጣዊው ዓለምህን ብቅ በልና ጎብኘው፡፡ ያልተጎበኘ ማንነት፣ ያልተስተናገደ ምንነት ትርጉም የለውም፤ ማን ይሁን፣ ምን ይሁን አይታወቅም፡፡ የሌሎች ባሪያ ይሆናል እንጂ የራሱ ተገልጋይ አይሆንም፡፡ ከራስ ጋር መጠፋፋት እውን የሚሆነው ከራስ ጋር በወጉ ባለመተዋወቅ ነው፡፡ የደግነት፣ የፍቅርና የቅንነት ባላንጣ፤ የመተባበርና የአንድነት ጠላት የሚሆኑ ሰዎች ከራሳቸው ጋር የተጠፋፉ፤ ሰውነታቸውን የዘነጉና መልካሙን ሁሉ ከሕሊናቸው ጓዳ አውጥተው በክፉ የተኩ ናቸውና፡፡ ለማንናውም በስንኝ ልሰናበትህ………… ………………. 💎ሰው መሆንን አስተምረው! (እ.ብ.ይ.) ሕሊናህን ጥለቅበት፤ አዕምሮህን ስመጥበት! ሰው’ነትህን እንድታወጣበት፣ ምንነትህን እንድታውቅበት፣ ማንነትህን እንድትሰራበት፣ ሰው ሆነህ እንድትበቃበት፡፡ ልቦናህን ዝለቅበት፤ መንፈስህን ርቀቅበት፣ ስሜትህን እንድትገዛበት፤ ዓለምህን ተመራምረህ፤ አንተነትህን ዝመትበት፣ ኖረህ እንድትረካበት፤ መልካም ፍሬ እንድታፈራበት፤ አውቀህ እንድትፀድቅበት፡፡ ነፍስያህን አነጋግረው፣ ውስጠትህን መርምረው፣ ጭንቅላትህን አማክረው፣ አንተነትህን ንገረው፣ ሰው መሆንን አስተምረው፡፡ ✍እሸቱ ብሩ ይትባረክ
Mostrar todo...
ስድስተኛ ክፍል ተማሪ እያለው አባቴ ቃል ገባልኝ፡፡ "በትምህርትህ ጥሩ ውጤት ካመጣህ አዲስ አበባን ክረምት ላይ ትጎበኛታለህ!" አለኝ፡፡ አደረኩት፡፡ጥሩ ውጤት አመጣው፡፡ክረምት ሲመጣ ግን አዲስ አበባ ለመሄድ የነበረኝ ጉጉት ዜሮ ሆነ፡፡ "እሽዬ ከአርባምንጭ አዲስ አበባ ለደርሶ መልስ በምትከፍልልኝ ገንዘብ መጽሐፍ ግዛልኝ፡፡" አልኩት፡፡አባቴ ተደሰተ፡፡ተስማማን፡፡አብረን ወደ መጽሐፍ መደብር ሄድን፡፡ ለሰባተኛ እና ለስምንተኛ ክፍል የሚሆኑ አጋዥ መጽሐፍት ተገዙልኝ፡፡ነገር ግን የሆነ ብር ሲተርፍ አባቴ፡ "ማኔ በተረፈው ብር ምን ትፈልጋለህ?" ሲል ጠየቀኝ፡፡ሶስት መቶ ስልሳ ድግሪ የመጽሐፍ መደበሩን ስቃኝ አንድ መጽሐፍ አይኔ ላይ ወደቀ፡፡ "you can win" ይላል፡፡የሆነ ህንዳዊ የሚመስል ሰው ፎቶ የመጽሐፍ ገጹ ላይ አለ፡፡ "Win ማድረግ የማይፈልግ ማን ነው?" አልኩኝ በውስጤ፡፡በተረፈው ብር መጽሐፉ ተገዛልኝ፡፡ከዛ መጽሐፍ ላይ መቼም የማይረሳኝ አንድ ታሪክ አለ፡፡ + መንታ ወንድማማቾች ናቸው፡፡አንዱ የለየለት አስቸጋሪ ነው፡፡ትዳሩ፣ የባንክ አካውንቱ፣ ከሰዎች ጋር የነበረው ግንኙነቱ፣ መንፈሳዊነቱ፣ ጤናውና በአጠቃላይ ሁሉም የህይወቱ ክፍሎች ተበላሽተውበታል፡፡ + ሌላኛው ወንድሙ ደግሞ የሚያስቀና ህይወት የሚኖር ስኬታማ ሰው ነው፡፡መንደሩ ውስጥ ተጽኖ የፈጠረ፣ ልጆቹን በስነስርዓት የሚያሳድግ፣ ከአምላኩ ጋር ያለውን ህይወት ያቃና በሁሉም የህይወት ክፍሎች ገራሚ ውጤት ያስመዘገበ ሰው ነው፡፡ + እነዚህ ሁለት ሰዎች በአንድ እናት ማህፀን ኖረው፡ በአንድ ቤትና በአንድ አይነት ሁኔታ ውስጥ አድገው : ለምን የተለያዩ ሰዎች ሁኑ???? የብዙ ሰዎች ጥያቂ ነበር፡፡ሰዎች ታሪካቸውን ለማወቅ ጉጉት አደረባቸው፡፡ + መጀመርያ ስኬታማ ያልሆነው ሰው ጋ ሄደው ጠየቁት፡፡እሱም ስኬታማ ሊሆን ያልቻለበትን ምንክንያት ነገራቸው፡፡ " እኔ በህይወቴ ላስመዘገብኳቸው ውድቀቶች ሁሉ መጠየቅ ያለበት አባቴ ነው፡፡አባቴ ሰከራም፣ ሐላፊነት የማይሰማው፣ ልጆቹን አዝረክርኮ ያሳደገ፣ ራሱን የማያከብር የወደቀ ሰው ነበር፡፡እኔም የእሱን መንገድ ተከትዬ ነው የወደቀ ሰው የሆንኩት፡፡እባካችሁ እኔ ላይ አትፍረዱ፡፡እኔ የሆነ ጊዜ ህጻን የነበርኩኝ ጨቅላ ልጅ ነበርኩኝ፡፡እንዲህ አይነት ተራ ህይወት ልኖር የቻልኩት በአባቴ ምክንያት ነው፡፡" አላቸው እንባው ቅርር እያለ፡፡አዘኑለት፡፡ ጥለውት ወደ ስኬታማው ወንድሙም ሄዱ፡፡ + የውንድሙን ምላሽ ለመስማት ሲበዛ ጓጉተዋል፡፡ወደ ቤቱም ገብተው ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየቁት፡፡ስኬታማው ወንድሙም፡ " ለእኔ ስኬት ተጠያቂ መሆን ያለበት አባቴ ነው፡፡" አላቸው፡፡ሰዎች ግራ ተጋብተው "እንዴት?" ብለው ጠየቁ፡፡ "አባቴ ጥሩ ሰው አልነበረም፡፡ሐላፊነት የማይሰማው፣ለቤተሰቦቹ የማይጨነቅ፣ በአምላክ ህግ የማይኖር፣ ጠንክሮ የማይሰራና ሰካራም አባት ነበር፡፡ሙሉ የቤተሰቡን ህይወት በስራው ስህተት አጨለመው፡፡ልጅነታችንን ስቃይ አደረገው፡፡እያደኩ ስመጣ ግን በፍጹም እንደ አባቴ አይነት ሰው መሆን እንደሌለብኝ ለራሴ ቃል ገባው፡፡ 'አባቴ የሚያደርጋቸውን ነገሮች ባደርግ መጨረሻዬ ምን ይሆን?' በማለት ራሴን ጠየኩኝ፡፡ መጨረሻዬን ሳስብ አስፈራኝና አባቴ የሚያደርጋቸውን ተቃራኒ ነገሮች ማድረግ ጀመርኩኝ፡፡ ውሎ አድሮም እሱ ያልኖረውን ልዩ ህይወት ፈጠርኩኝ፡፡" አላቸው፡፡ሰዎቹም ተገረሙ፡፡ ታሪኩን አንብቤ ሳበቃም እኔም ተገረምኩኝ፡፡ወንድማማቾቹ አንድ አይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑም ነገር ግን ለሁኔታው የሰጡት የተለየ ምላሽ ህይወታቸውን ለውጦታል፡፡ + የህይወታችን መመርያ ልናደርገው የሚገባ አንድ በጣም ሐይለኛ ጥቅስ አለ፡፡ + "ህይወት 10% የሚያጋጥመን ሁኔታ ሲሆን 90% ደግሞ ለሁኔታው የምንሰጠው ምላሽ ነው፡፡" + ዛፍ አይደለንም፡፡እግር አለን፡፡ከመጥፎ ሁኔታ መሸሽ እንችለላለን፡፡በመሸሽ የማናመልጠው አይነት ሁኔታ ከሆነም jackie chan እንዳለው እጃችንን ተጠቅመን ሁኔታውን መለወጥ እንችላለን፡፡እጅ የሚያቃጥል መጥፎ አይነት ሁኔታ ከሆነም ስለሁኔታው ያለንን አመለካከት እንለውጥ፡፡ለሁኔታው የምንሰጠውን ምላሽ እናስተካክል፡፡ + ከአቅማችን በላይ ከሆነም ሁኔታውን 100% እንቀበለው፡፡መስተዋት እንሁን፡፡የውስጣችንን ሰላም ሳይበርዘው እናሳልፈው፡፡አናማርር፣ አንበሳጭ፣ አንፍራ፣ አንጨነቅ፡፡የምንችለውን ሁሉ እናድርግ፡፡የማንችለውን ለፈጣሪ እንስጥ፡፡በእምነት ፈታ በለን እንኑር፡፡ #ምንጭ:- ማንያዘዋል እንደሻው @Rightinglove @Rightinglove @Rightinglove
Mostrar todo...
#ራስን እንዴት መቀየር ይቻላል# ሕይወት በድንገተኛ አጋጣሚዎች ታጅባ መጓዟ የተፈጥሮ ግዴታ በመሆኑ በድንገት ሁሉም ነገር ቦታውን ሊለቅ ይችላል። በአጋጣሚዎች ሕይወት የመመሳቀሏን ያህል ቀን ጠብቆ ነገሮች የሚለወጡበት አጋጣሚ ይፈጠራል። ዘመኑን ሙሉ የተረጋጋና ሰላም የሰፈነበት ኑሮ ሲመራ የነበረ ሰው ድንገት ሕይወቱ ተዘበራርቆ የማያውቀው ዓለም ውስጥ ሊገባ ይችላል። ታዲያ ከገባበት የችግር አዘቅት ለመውጣት የሚፈልግ ሰው ችግሩ በተከሰተባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ ማሰብና መፍትሔ ማፈላለግ ሰላማዊው ኑሮውን ለመመለስ ይጣጣራል። ከገባበት ችግር ለመውጣት ቀዳዳውን ማግኘት የተሳነው ሰው ደግሞ በሚወስዳቸው የተሳሳቱ እርምጃዎች ከዕለት ዕለት ችግሩን እያወሳሰበው ይሄዳል። «ዊኪ ሃው» የተባለ ድረ ገጽ በሕይወት አጋጣሚ ከገቡበት ጥሩ ያልሆነ መስመር ለመውጣትና ራስን ለመቀየር የሚረዱ ነጥቦች ብሎ ያስቀመጣቸው እንደሚከተለው ቀርበዋል። 1 #ችግሮችን መለየት# ችግሮችን መለየት እራስን ለመለወጥ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ቀዳሚውን ቦታ ይይዛል። ችግሩ ከታወቀ በኋላ «ለምን ሆነ፣ መቼ ሆነ፣ እንዴት ሆነ?» ለሚሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ይቻላል። የመፍትሔ ሰበብ ተገኝቶ ለውጥ እስኪመጣ የተፈጠሩ ችግሮችን መለየት ወሳኝ ነው። የችግሮቹ ምክንያት በግልፅ ከታወቀ መፍትሔ ይገኝለታል። 2 #ለራስ ሃሳብ ቅድሚያ መስጠት# አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ችግር በሚያጋጥማ ቸው ወቅት ራሳቸው የሚያፈልቁትን ሃሳብ ከመከተል ይልቅ በሰዎች ሃሳብ መመራት ያዘወትራሉ። ራስን በመቀየር ሂደት ውስጥ ግን ከሰው ሃሳብ ይልቅ የራስን አእምሮ ተጠቅሞ የለውጥ መንገድ መፈለግ ይደገፋል። 3 #ሁኔታዎች መቀያየር እንደሚችሉ ማመን# እራሱን መለወጥ የሚፈልግ ሰው በነገሮች ቦታቸውን መልቀቅና መያዝ ያምናል። አሁን የተረጋጋ የሚመስል ነገር ከቀናት በኋላ እንዳልነበር ሊሆን ይችላል። ሁሉም ነገር ሊመጣ እንደሚችል፣ እንደሚያጋጥም የሚያምን ሰው ጊዜው ሲደርስ በሚከሰተው ነገር ካለመሸበሩ በተጨማሪ ሕይወቱ አይናጋም። ምክንያቱም ቀድሞ ሊመጣ እንደሚችል ያውቅ ነበርና። 4 .#ታጋሽ መሆን# የታጋሽነት ጥበብ እራስን ለመቀየር ከሚያስፈልጉ ጥበቦች አንዱ ነው። ራሱን መለወጥ የሚፈልግ ሰው ሁሉንም እንዳመጣጡ መመለስና ሁሉንም መቻ6ል አለበት። የሚያጋጥሙትን ችግሮች በፊት ከሚፈታበት በተሻለና ማስተዋል በተሞላበት መንገድ መፍታት ይጠበቅበታል። ለዚህ ደግሞ ትዕግስተኛ መሆን የግድ ነው። #ከሁሉ_ጥረታችን_በፊት ፣ በኋላ ፣ በመንገዳችን ሁሉ ፈጣሪን መለመን ፀሎት = ዱአ ከልብ ማድረግ እንዳንዘነጋ መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ ። @Rightinglove @Rightinglove @Rightinglove
Mostrar todo...
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ ደመና ሲያይ መስሎት የጨለመ አለ ቂል ሰው 'ሁሉም አከተመ' ደቂቅ ተስፋን ካየናት አርቀን ነገ ሌላ ይሆናል ጥሩ ቀን! ጨለማው በብርሀን ይለወጣል! ሕይወት በብርሀን ጊዜ ብቻ የምንደሰትባትና የምንፈነጥዝባት አይደለችም። ይልቁኑም በጨለማውና ግራ በገባን ጊዜ ጭምር ከጨለማውና ከውጥንቅጡ ለመውጣት በምናደርገው ጥረት ይበልጥ ህይወታችንን ወደ በለጠ ደስታ ውስጥ እንጨምረዋለን። በጨለማው ጊዜ በውጥንቅጡ ጊዜ በችግሩ ጊዜ ተስፋ የቆረጡ፣ህይወታችን አበቃላት ብለው ጉዟቸውን ያቆሙና ህመሙ በዛብኝ ብለው ህልማቸውን ያቋረጡት ሁሉ አስደናቂዋን የብርሀን ፍንጣቂ ለማየት አይታደሉም። የብርሀኗን ፍንጣቂ ለማየት በህመሙ ጊዜ መጠንከር፣ በስቃዩ ጊዜ መበርታት በጨለማው ጊዜ መታገስ ያስፈልጋል፤ ያኔ ህመሙ ወደ መዳን፣ ማጣቱ ወደ ማግኘት፣ ጨለማውም ወደ ብርሀን ይለወጣል! በጨለማው ጊዜ ጥርስህን ንከስና ጉዞህን ቀጥል ወደ ስኬትህ መጨረሻ የሚያደርስህን ትግል በፍጹም አታቁም። አዎ ፈተናው ምን ያህል ቢበዛና ሊጥልህ ቢያንገዳግድህም አንተ ግን በፍጹም አትውደቅ። ብትወድቅም እንኳ እየተንፏቀቅ መሄድህን ቀጥል። ያኔ ብርሀን ከፊትህ ይመጣል! ይፈትናል እንጂ ድሉ ያንተ ነው! አስተውል! አበቃ የሚባል ነገር የለም ሕይወት ይቀጥላል... @Rightinglove @Rightinglove @Rightinglove
Mostrar todo...
Inicia sesión y accede a información detallada

Te revelaremos estos tesoros después de la autorización. ¡Prometemos que será rápido!