cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡ @bewketuseyoum19 Buy ads: https://telega.io/c/bewketuseyoum19 For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot Thank you!

Mostrar más
Advertising posts
129 198Suscriptores
-8924 hours
-9097 days
-4 05430 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

...........ሳቅሽ....... ሳቅሽ  ለመተብተብ ብቻ ሚቃጣው የሸረሪት ድር ነው  ሸማ የማይወጣው ሳቅሽ የተንኮል ፈገግታ  የተንኮል ወትብትብ የዘመን ማዘሎ  ማይቆረጥ ማተብ ሳቅሽ የማያልቅ ፈትል  የማይጠፋ እሳት የሳቅሽ ሚስጥር ነው እሳትን ማስነሳት       By kerim 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Mostrar todo...
9👍 4🥰 1
❤️❤️‍🔥💔የልቤን ብታዪ❤️❤️‍🔥💔 አይኔ እንደ ቆራጥ አንቺን ባያይሽም      ሞልቶት ትንሽ ኩራት አፌም ጀነን ብሎ አሻፈረኝ ቢልም       ስምሽን ለመጥራት ጆሮዬም ቢያስመስል ከቶ እንደማይሰማ       አንቺን የሚል ወሬ በሄድሽበት መሄድ ሁሌ መከተሉን        ባይሞክረው እግሬ           በይ ልንገርሽ ዛሬ ሞኝ ልብ እንዳለኝ ማያውቅ ማስመሰል ጠዋትና ማታ ስራው አድርጎታል          አንቺን ማሰላሰል። 📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝      ✍ በግጥም እናውጋ( @gitim101) 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Mostrar todo...
10🥰 3👍 2
🔴Dot Coin ማይን በማድረግ ገንዘብ መስራት እንደምትችሉ ያውቃሉ? 💸💵Dot Coin active ሆነው ማይን ለሚያደርጉ ሰዎች 0.5 ton = $3.5 እየሰጠ ይገኛል። 🤑🤑🤑🤑🤑 ታዲያ ምን እየጠበቃቹ ነው ጊዜው ሳያልቅ አሁኑኑ ተቀላቀሉ። Click here ሚለውን በመጫን መቀላቀል ትችላላችሁ ይመቻችሁ። ✌️ 👇👇👇👇 Dot Coin click here
Mostrar todo...
ቀጣዩ ‘ስቴፕ” (በእውቀቱ ስዩም) እንደ ቀነኒሳ አይነት ልእለ-ሰብ ሰዎችን ስታይ የእድሜ መገስገስ አያስፈራህም፤ እድሜ ሆይ መውጊያህ ወዴት አለ? ብለህ ትፎክራለህ ፤ “ ቀነኒሳ አንበሳ “ ይላል ጀግና አሞጋሹ ጀግና ቴዲ አፍሮ፤ አንበሳ በምን እድሉ ነው ቀነኒሳን የሚስተካከለው ? አንድን አንበሳ በሀያ አመቱ በአጸደ ስጋ አታገኘውም፤ ካገኘኸው ጭርጭስ ብሎ፥ ጎብጦ ቁርበቱን እየላሰ ተኝቷል፤ ቀነኒሳ ግን በአርባ ሁለት አመቱ ማራቶን ያሸንፋል፤ ዋናው ጥያቄ- ለእድሜ ትገብራለህ ወይስ እድሜን ታስገብራለህ?” የሚል ነው፤ ርግጥ ነው እኔ በዚህ እድሜየ እንኳን ማራቶን ልሮጥ ውድድሩን በቲቪ ጨርሶ ለማየት ራሱ አቅምና ትግስት የለኝም፤ አንዳንድ ቀን፥ ከባለንጀሮቼ ጋር ኳስ ለማየት እቀመጣለሁ፤ በተቀመጥኩበት ሶፋ ላይ አራት ዙር ግልገል እንቅልፍ (ናፕ ) እተኛለሁ፤ በቀደም ከስንት ጊዜ በሁዋላ ጂም ሄድኩ፤ አሰልጣኙ ተቀብሎ ገና የስነልቦና ምክር እንኳ ሳይሰጠኝ “ ሀያ ጊዜ ቁጭ ብድግ ስራ “ አለኝ ፤” ቁጭ ማለቱ ላይ ችግር የለብኝም ብሮ ! ብድግ ማለቱ ላይ ግን እገዛህን እሻለሁ “ ብየው ፥ ትንሽ ወልመጥ ወልመጥ አልሁ ፤ ቀጠለና አስር ፑሽ አፕ አዘዘልኝ፤ አምስቱን ወገቡን እንደተመታ እባብ እየተቅመደምድሁ ሰራሁ፤ በተረፈች፥ ጉልበቴ ምንጣፉን እየሳምኩ ተነሳሁ፤ በመጨረሻ ሳልፈልግ ፥በርከክ ብየ ለወጫጫ ተራራ ሰገድሁ፤ ማጠቃለያው ላይ፥ አምስት ኪሎ ድምቤል አሸከመኝ፤ ከዚያ መስታውት ፊት ቆሜ ፥ ከክርኔ በላይ ያለውን ክንዴን ክፍል እየዳበስኩ ገመገምኩት፤ ብዙም ሳይቆይ አሰልጣኙ ከተፍ አለና፥ “አሁን አሟሙቀሀል፤ ቀጣዩ ስቴፕ ምን እንደሆነ ታውቃለህ? ” ሲል ጠየቀኝ፥ “ ቀጣዩ “ ስቴፕ”ማ ንቅሳት እሚሰሩ ሰዎችን ማፈላለግ ነው ዠለስ“ 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Mostrar todo...
👍 17🤩 11
🔴Range for sell Grade 60/70 Year. 2023 Origin. Iran Quantity 5000 Barrel Test. Tested Location legally Imported Price 21,000 / barrel 📲0913295326
Mostrar todo...
👍 7
/ ለምን ጠላሻለሁ/ መቼ ተለወጥኩኝ እንደዛው ነኝ እኔ ተለዉጧል እርሱ አይደለም እንደ ያኔ፤ እያልሽ የሌለኝን ማንነት አትስጪኝ ከመሬት አንስተሽ ከሰው አፍ አታውጪኝ፤ ደሞስ መች ሊጨክን ልቤስ ሊደነድን በሕይወት ሳለሁኝ ከቶ ሳልሆን በድን፤ የኔ የዋነቴን የልቤንም አይተሽ ዛሬ ምን ሲል ታየሽ ያኔ የሄድሽው ትተሽ፤ እርግጥ ሰው ባጠፋው ፀፀቱ ባይቀርም ወደሽኝ ቢሆን ኖሮ በኔና አንቺ አይከርም፤ ታዲያ መች እንደዛ ሆኖ ያንቺ ቀረቤታ ፌዝ አዘል ነበረ የጥርስሽ ፈገግታ፤ ያኔ ማፍቀርን ጠግቤው መፈቀር ቢርበኝ ያንቺ ልብ በፍቅር መች አምኖ ቀረበኝ፤ አሁን ላይ ጥያቄሽ ለይቅር ከሆነ ጥፋት እንዳጠፋሽ ልብሽ ይህን ካመነ፤ በሰው ቂም አሊዝም ይቅር ብዬሻለሁ ዳግም ባልወድሽም ለምን ጠላሻለሁ; #መሳይ ግርማ 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Mostrar todo...
👍 11👏 4 2
ዘርተሽብኝ ሄደሽ አምነትና ተስፋ በረሃው ነቃ አለ በማግስቱ አካ`ፋ! ጠረንሽ ሲያልፍበት መዐዛሽ ሲያልፍበት እንኳንስ ዘንቦበት በረሃው ይድናል ተስፋ ካካፋበት። ሲያሳሳኝ የነበር በሰው መደነቄ በሰዎች መናቄ ዛሬ ገና ገባኝ በረሃ እንደነበርኩ ከቶ አለማወቄ። ይህ ከንቱ ድንበሬ በተስፋሽ ተለካ እራስን ማወቅ ነው ሌላን ማፍቀር ለካ። By Yadel Tizazu 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Mostrar todo...
👍 24 3👏 2
💗❤️ወድሻለው💗❤️ - ወደኔ ተራምደሽ ቆመሽ ካጠገቤ - ድንገት አይኔ አይቶሽ ሲደነግጥ ልቤ - ሻል እንዳለኝ ወዲያው ከጎንሽ እንዳለው - ለመናገር ሀቁን አይንሽን እያየው - ውስጤን አሳወኩሽ ብዬ ወድሻለው።          :          : 🎈 ወንዶች ለምትወዷት ሴት ላኩላት   📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝      ✍ በግጥም እናውጋ( @gitim101) 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Mostrar todo...
🥰 12👍 8
💗❤️ወድሀለው💗❤️ - ወደኔ ተራምደህ ቆመህ ካጠገቤ - ድንገት አይኔ አይቶህ ሲደነግጥ ልቤ - ሀሳቤን ሰብስቤ ከጎንህ እንዳለው - ለመናገር ሀቁን አይንህን እያየው - ውስጤን አሳወኩህ ብዬ ወድሀለው።          :          : 🎈 ሴቶች ለምትወዱት ወንድ ላኩለት      📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝📝      ✍ በግጥም እናውጋ( @gitim101) 📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱 @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19
Mostrar todo...
17👍 8💔 4
መርጌታ ዮሐንስ የባህል መድህኒት እና ጥበብ ይፈልጋሉን? የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች በጥቂቱ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋ  በቴሌግራም ወይም በኢሞ ማውራት ይችላሉ። - ለመፍትሔ ስራይ - ለህማም -ጋኔን ለያዘው ሰው -ቡዳ ለበላው - ለቁራኛ - የዛር ውላጅ ለተዋረሰው - ነገረ ሚስጥራት (ሚስጥር የሚነግር) - ነገረ ራዕይ (ራዕይ የሚያሳይ) - ለዓቃቤ ርዕስ - ለቀለም(ለትምህርት) - ሰላቢ የማያስጠጋ - ለመፍትሔ ሀብት (ሀብት ለማግኘት) - ለመስተፋቅር - ለሁሉ ሠናይ - ለገብያ - ለአምፅኦ ብእሲት (ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች     የሚሰራ) - ለመድፍነ ፀር - ለበረከት - ለከብት መስተሐድር (ከብት እንዲረባልኝ) - ለአፍዝዝ ለአደንግዝ - ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ6 የሚያደርግ) - ለግርማ ሞገስ - መርበቡተ ሰለሞን - ለዓይነ ጥላ - ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ - ለሁሉ መስተፋቅር - ጸሎተ ዕለታት - ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ - ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ) - ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ - ድምፅህ ያማረ እንዲሆን - ለኤች አይ ቪ  በሽታ መድኃኒት  - ምናልባት ያለ ኮከባቸው የተጋቡ ካሉ አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት - ለኪንታሮት መድሀኒት - ለስኳር በሽታ መድኃኒት - ጥይት እንዳይመታህ      ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል ይደውሉ  📞☎️    0933266868                           አልያም በቴሌግራም አካውንታችን 👇👇👇👇👇👇👇👇@yohanis33        ያግኙን
Mostrar todo...
👍 3😢 1