cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

መልካምነት ለራስ ነው!!!🌹🌹🌹

ይህ 🌹🌹🌹መልካምነት ለራስ ነው!!!🌹🌹🌹 ቻናል የተለያዩ ስለ መልካምነት እና በጎነት የሚሰብኩ ታሪኮችና ጽሁፎች ይቀርብበታል ይወያያል የዚህ ቻናል ዋና አላማ መልካምነት በመጥፋት ላይ ያለና ብርቅዬ እየሆነ ስለሆነ በተቻለ መጠን እንዳይጠፋና በሰዎች አእምሮ ውስጥ ቦታ እንዲኖረውና እንዳይረሳ መስራት ነው¡¡¡¡¡¡¡¡ ሃሳብዎን በግሩፕ ለመወያየት @melkaminetlerasnew join ይበሉ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
569Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🎈 የግብፅ ስልታዊ ኘሮፓጋንዳ ሰልፈኞች ከመሆን እንጠንቀቅ 🔹 የወቅቱ ውዥንብር ~~
Mostrar todo...
🎈 የግብፅ ስልታዊ ኘሮፓጋንዳ ሰልፈኞች ከመሆን እንጠንቀቅ የወቅቱ ውዥንብር ~~ ከሁለት ዓመት በፊት ግድባችን የመጀመሪያ ዙር ዉሃን መያዙ እውን ሲሆን ታሪክ ላይመለስ ተቀይሯል ብለናል። ዘመናት ግብፅ በውሃው ላይ የነበራት ፍፁም የበላይነት ላይመለስ ባለበት አስቁመነዋል። ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንጂ ተመልካች ፣ ሰጪ እንጂ ተቀባይ ፣ ተፈላጊ እንጂ ተገፊ የማትሆንበት አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል! አዲስ መንገድ ተቀይሷል ፤ የሚድያዎቻችንም በተለይም የማህበራዊ ሚድያ ዘማች እና አዝማቾችም አካሄድ ይህን አውዱን ማዕከል አድርጎ መቃኘት አለበት። በዋናነትም እኛ አጀንዳ ሰጪ እንጂ ተቀባይ አይደለንም። ያ ጊዜ በመሰረታዊነት አብቅቷል። ይህን በዉል ባለመገንዘባችን ዛሬም ከሁለት አመት በፊት ስንከተል በነበረው መንገድ እየተጓዝን ነው። ከሰሞኑ ግብፆውያን እያደረጉት ባለው ስልታዊ ፕሮፓጋንዳ ተስበን ብዙዎቻችን እየገባን ነው። ግብፃውያን የህዳሴ ግድብ ጉዳይን ልክ ላለፉት ሁለት አመታት እንዳደረጉት ሁሉ አሁን ሶስተኛው ሙሌት ከመከናወኑ በፊት አለምአቀፍ አጀንዳ ለማድረግ ጥረቱን ከጀመሩት ሰንብተዋል። ሆኖም ባሰቡት ልክ መሆኑ ይቅርና በትንሹም ጉዳዩን በአለም መድረክ ሊሸጡት አልቻሉም። አለም ይበልጥ ወዳጅ የሚሏቸው ሃገራት በተለያዩ 'የራሳችን' በሚሏቸው ጉዳዮች ( ሩሲያ ዩክሬንን) በመሰሉ እና ሌሎች ጉዳዮች ተወጥረዋል ። ዘንድሮ ሰሚ የለም!! በተወሰነ መጠንም ቢሆን አጀንዳነቱን እንዳያጣ ታዲያ በራሳቸው እና በቅጥረኛ ሚድያዎቻቸው ሁኔታውን ለማጦዝ የተሰለቹ እና ገዢ ያጡ መልዕክቶችን እያሰራጩ የግድቡን ፋይል ለማነቃነቅ እርብርብ ከማድረግ አልቦዘኑም። ይበልጥ የኢትዮጵያን መንግስት እና የማህበራዊ ሚዲያ ማህበረሰቡን ስቦ ወደ ሜዳ ሊያስገቡ ይችላሉ የሚሏቸውን አጀንዳዎች በየእለቱ በተለያዩ ስልቶች እንዲደርሰን እያደረጉ ነው። ይህን የማድረጉ ፋይዳ፤ አጀንዳዎቻቸው በሁለቱ መንግስታት እንዲሁም በሁለቱ ሃገራት የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚ ህዝቦች ምልልስ የሚያገኙ ከሆነ ነገሩን ለማጦዝ ያስችላል። አለም አቀፍ ማህበሰሰብን እንደ አምና እና ካቻምናው ግጭት ሊፈጠር ነው በሚል ፈጠራ ለግድቡ ጉዳይ ጆሮ እንዲሰጡ እና ጫና እንዲያሳርፉ ለማስገደድ እድልን ይፈጥራል። ይህን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ ኢትዮጵያ ሶስተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት አከናውና ሳትጨርስ ነው ። ከጨረሰችማ እንደገና አራተኛውን አመት መጠበቅ ነው !! ስለዚህም ይበልጥ ባለፉት ሶስት ሳምንታት በልዪ ሁኔታ በመደበኛ እና በማህበራዊ ሚድያዎቻቸው በአዲስ መልክ ለዚሁ አላማ እየሰሩ ነው። የእኛ ሰዎችም በአለማወቅ በየዕለቱ የእነርሱን ሚድያዎች በመከተል ለሚያሰራጩት መልዕክት እና ዘገባ በበጎነት ምላሽ በመስጠት በሚፈልጉት መልኩ የህዳሴ ግድብ አጀንዳን ከፍ እያረግንላቸው ነው። አጀንዳነቱ ህይወት የሚኖረው ሶስተኛው ሙሌት ከመጠናቀቁ በፊት በመሆኑ ሆንብለው ስልታዊ በሆነ ኘሮፓጋንዳ ሙሌቱ ተጠናቀቀ የሚል መረጃ በስፋት እንዲሰራጭ አድርገዋል። ይህንንም የእኛ ሰዎች ተቀብለው አንዳች የሚመለከተው የመንግስት አካል መረጃ ሳይሰጥ ግብፃውያኑ ባሰቡት መልኩ አጀንዳውን ወደ ከፍታ እንዲወጣ እየሆነ ነው። በዝምታ ውስጥ በብርቱ ስራ ለዚያውም በፈተና ወቅት ባለድል እየሆን ባለንበት ወቅት እውነተኛ ባልሆነ እና እኛን በማይጠቅም መልኩ አደባባይ መውጣት ተገቢ አይደለም። በእርግጥ የሙሌቱ መጠናቀቅ ሃገር ወዳዶች ሁሉ መስማት የምንፈልገው ዜና ቢሆንም የሚነግረን ባለቤት፣ የሚነገርበትም ጊዜ አለው። ሙሌቱ ሳይጠናቀቅ ተጠናቀቀ ተብሎ የተሰራጨው ስልታዊው የግብፃውያን መረጃ አጀንዳውን በዚህ አመት ከነበረው መቀዛቀዝ ከፍ ስለሚያደርገው አጯጩሆ ከወዲሁ አለም አቀፍ ማህበረሰቡ በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ጫና እንዲያሳርፍ ለማድረግ ነው። አሁን ግድባችን በተቻለ መጠን የሚድያ አጀንዳ እንዳይሆን ማድረግ ነው ከእኛ የሚጠበቀው፤ ለሃገራችን የሚጠቅመውም እርሱ ነው። አለምአቀፍ ሁኔታውም ቢሆን ጊዜ ከግብፅ ጋር እንዳይሆን አድርጓል ፤ የታላላቅ ሃገራት መንግስታትም ይሁኑ ሚዲያዎቻቸው በብዙ ክስተቶች ተወጥረዋል። ይህ ለእኛ ዕድል ነው። ግድባችን ሆነ ድርድሩ አሁን ባለበት ሁኔታ እኛ እነርሱን ልንከተል አይገባም። አጀንዳም ካስፈለገ ሰጪዎች እንጂ አጀንዳ ተቀባዮች የመሆኛ ጊዜያችን አብቅቷል!! ሶስተኛ ዙር ሙሌት ላይ ደርሰን ሳለ ድሮ የጣልናቸውን አጀንዳዎች ሰጥተው ወደ ኋላ ሲስቡን አንሳብ። ወደ ፊት የሚያራምዱን ይበልጥ አሸናፊ የሚያደርጉንን የሚድያ ስልቶች መከተል አለብን። ትላንት የተጓዝንበት የሁልጊዜ መንገዳችን ሊሆን እንደማይችል መገንዘብ ያስፈልጋል !!
Mostrar todo...
የሩሲያና የአሜሪካ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ፍጥጫ ወዴት፡ አንድ‼️ *** “ሥጋ ለጥጋብ አጥንት ለትካዜ” መጪው ጊዜ ከወዲሁ ውል ካልተበጀለት በቀር የዝሆኖቹ ልፊያ ከእነርሱ አልፎ ሳሩን ፍዳውን እንደሚያሳየው ቁልጭ ያለ እውነታ ነው፡፡ ሀያላን አገራት በጠመቁት የሞት ድግስ አንዲት ቴክኖሎጂ፣ አንዲት መስመር ጥበብ፣ አንዲት አንቀጽ ሀሳብ ያላዋጣው የተቀረው የአለም ህዝብም በግፍ የመታደሙ ነገር አይቀሬ ይመስላል፡፡ ምስራቅ ፈነዳ ምዕራብ፣ ሰሜንን ቀድሞ ረገጠ አልያም ምዕራብ እምበዛም ለውጥ የለውም፡፡ ምክንያቱም እምናወራው ስለ ኑክሌር የጦር መሳሪያ ነው፡፡ ታሪክ የሁለቱ አገራት የኑክሌር ፍጥጫ ይበልጥ እየተካረረ የመጣው እ.አ.አ ከ2007 ጀምሮ ነው ይለናል፡፡ ሩሲያና አሜሪካ፡፡ ውድ የሰዋስው ቤተሰቦች በ2007 ምን ሆነ መሰላችሁ፣ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘደንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ 2007ን ባከበሩ ማግስት ለአውሮጳዊያን ያበረከቱት የአዲስ ዓመት ስጦታ ፖላንድና ቼክ ውስጥ የሚሳኤል መከላከያ ሚሳኤል የመትከል ውሳኔያቸውን ነበር። ይሄኔ የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ለአፀፋ እንደማይሰንፉ ዛቱ። እ.አ.አ በወርሃ የካቲት 2007 የዋሽግተንና የሞስኮዎች ዕቅድና ዛቻ ዓለምን ዳግም ወደ ኑክሌር ጦር መሳሪያ ሥጋት እንደሚዶላት ባለሙያዎች መክሩ፣ ይሄ ነገር ዳግም ቢታይ ሲሉ አሳስቡም። የፖላንድና የቼክ ሕዝብ በበኩሉ ያቺው ጎመን በጤና ይሻለኛል ሲል በይፋ ተቃወመው። ዳሩ ፀሀፊው “ለሕዝብ የመናገር ነጻነት ብቻውን ምንም አያደርግለትም፡፡ የመደመጥ መብት ከሌለው በቀር” እንዲል የህዝቡን ተቃውሞ የሰማ እንጂ የተቀበለ አልነበረም። ውሳኔ እና ዛቻ ለ11 ዓመት የገዘገዘውን የጎርቫቾቭ-ሬገንን ውል ትራምፕ ብጥስጥሱን አወጡት፣ ፑቲን ከጠረንጴዛቸው ላይ ፈነገሉት። የአሜሪካኖችን የሚሳኤል መከላከያ ሚሳኤል ጀርመኖች አስተከሉት። እዚህ ላይ ለወቅቱ የጀርመን መሪዎች “አያበሬ ሆይ ሳሩን እንጂ ገደሉን መች አየህ” የሚለውን ጆሮ ጠገብ አባባል አድርሰን ታሪካችንን እንቀጥል፡፡ የማታ የማታ ግን ጀርመኖች በተተከለው የኑክሌር መሳሪያ ምክንያት ሊከተል የሚችለውን ከባድ አደጋ አስተዋሉት መሰል ኡኡ አሉ፡፡ ሚሳኤሉ ካልተነቀለልን ብለው ተቃወሙ፡፡ አስነቀሉትም። ነገርየው እንዲህ ነበር፣ እ.አ.አ መጋቢት 1976 ሶቭየት ሕብረት SS-20 የተባለውን ኑክሌር አስወንጫፊ ሚሳኤል ለምዕራብ አውሮጳ እሚቀርበው ግዛትዋ ውስጥ አጠመደች። ኑክሌር ተሸክሞ 5000 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ የትኛውን ኢላማውን በቅጽበት ከመኖር ወደአለመኖር የሚያሸጋግረውን ሚሳኤል መተከሉ ዩናይትድ ስቴትስ ስትሰማ ነጠላዋን ዘቅዝቃ አገር ይያዝልኝ አለች፡፡ የያኔው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት የጂሚ ካርተር መስተዳድር በፍጥነት የማይንቀሳቀሰውን የሶቬቶች የሚሳኤል ጣቢያ ስልታዊ በተባለው የኑክሌር ቦምብና ቦምቡን መጣል በሚችሉት ፈጣን አውሮፕላኖች ማጋየት «አይገድም» በሚል አፀፋ እርምጃ ለመውሰድ አልፈለገም ነበር። የያኔው የምዕራብ ጀርመን መራሔ መንግስት ሔልሙት ሽሚት እ.አ.አ በ1977 ባደረጉት ንግግር ግን የሶቭየቶች ሚሳኤል ምዕራብ አውሮጳን እንደሚያሰጋ አስታውቀው ዩናይትድ ስቴትስ አፀፋ እርምጃ እንድትወሰድ አሳሰቡ። ማሰሰቢያው የምዕራብ አውሮጳ መንግስታትን አሳድሞ፣አሜሪካኖችንና መላው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) አባል መንግስታትን አሳመነ። የድርጅቱ ሚንስትሮች እ.አ.አ በ1979 ባደረጉት ስብሰባ ባንድ በኩል፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከሶቭየት ሕብረት ጋር እንድትደራደር በሌላ በኩል ደግሞ Pershing II የተባለው የዩናይትድ ስቴትስ ኑክሌር አስወንጫፊ ሚሳኤል ምዕራብ ጀርመን፣ ቤልጂየም፣ ኢጣሊያ፣ ሆላንድና ብሪታንያ ውስጥ እንዲጠመድ «መንታ-ጎዳና» የተባለውን ወሰኑ። የጂሚ ካርተር መስተዳድር ሁለቱንም ውሳኔዎች ገቢር ለማድረግ አንድ ሁለት ማለት እንደጀመረ ካርተር እ.አ.አ የ1980ውን ምርጫ በወግአጥባቂው ፖለቲከኛ በሮናልድ ሬጋን ተሸንፈው ከስልጣን ወረዱ። ሬገን ግን እ.አ.አ በ1981 ማብቂያ «ዜሮ-ዜሮ» ባሉት መርህ መሠረት እስከዚያ ጊዜ ድረስ ከተጠመዱት ሌላ ተጨማሪ የአሜሪካ ሚሳዬሎች አውሮጳ ውስጥ መጠመዳቸውን አስቁመው፣ ሊዮንድ ብሬዥኔቭ ከሚመሩት የሶቭየት ሕብረት መንግስት ጋር ይደራደሩ ገቡ። ዳሩ ድርድሩ በውዝግብ፣ ፉክክር፣ ጥርጣሬ፣ ዳተኝነት፣ በሶቭየቶች መዳከምም እየተደነቃቀፈ ደንበር ገተር በሚልበት መሐል-ምዕራብ ጀርመኒቱ ከተማ ሐይልብሮን አጠገብ በሚገኘው የአሜሪካኖች የሚሳኤል ጣቢያ እንዲህ ሆነ፣ «አስደጋጭ» ይሉታል ያኔ የሚሳኤል ጣቢያውን ይጠብቁ ከነበሩት የአሜሪካ ወታደሮች አንዱ ላሪ ኒኮላስ። ይቀጥላል! .. https://am.sewasew.com/p/የሩሲያና-የአሜሪካ-የኑክሌር-ጦር-መሳሪያ-ፍጥጫ-ወዴት-አንድ ..
Mostrar todo...
ሰዋስው | የሩሲያና የአሜሪካ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ፍጥጫ ወዴት፡ አንድ

[ጠቅላላ እውቀት][ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ] “ሥጋ ለጥጋብ አጥንት ለትካዜ” መጪው ጊዜ ከወዲሁ ውል ካልተበጀለት በቀር የዝሆኖቹ ልፊያ ከእነርሱ አልፎ ሳሩን ፍዳውን እንደሚያሳየው ቁልጭ ያለ እውነታ ነው፡፡ ሀያላን አገራት በጠመቁት የሞት ድግስ አንዲት ቴክኖሎጂ፣ አንዲት መስመር ጥበብ፣ አንዲት አንቀጽ ሀሳብ ያላዋ...

#RIP አሜሪካኖች #የማታዋ_አበባ ይሏታል ለሚሊዮን ሰዎች ጥንካሬና ብርታት ሆናለች። በካንስር በሽታ ምክንያት ሰሞኑን በተወለደች በ31 ዓመቷ ከዚህ ዓለም ሁላችንም ወደ ማንቀርበትና ሰላማዊ እረፍትን ወደምናገኝበት ቦታ ኤዳለች። ይህች እንስት ትክክለኛ ስሟ #ጄን ይባላል። ከ8 ወር በፊት AGT (America Got Talent) ላይ ቀርባ ስለ ራሷ ህይወት it’s ok እያለች በዘፈን መግለፅዋን እናስታውሳለን። ያ ዘፈንዋ ያ ዜማ በሚሊዮን ህዝብ ልብ ውስጥ ታተመ። ብዙሃን ሳያንገራግር በአንድ ልብ ወደዳት። ቆመውም አጨበጨቡላት። ዳኛው ሳይመን ሳይቀር የወርቃማው ደውል ሰጣትና ወደ ቀጣዩ ዙር በቀጥታ አለፈች ነገር ግን በዶክተሮች: በቅርቡ እንደምትሞትና የመዳን እድሏም ከ 100% 2% እንደሆነ የተነገራት እቺ ጠንካራ ሴት ባላት ትንሽ ጊዜ ተሰፋ ሳትቆርጥ ለሰው ልጆች ይጠቅማል ያለችውን መልካም ነገር ማስተማር ጀመረች። በምድር ላይ እያሉ ሰዎች ለሰዎች ጥሩ ነገር መስራትን እንዳለባቸው ደጋግማ ተናገረች። በየቀኑ ህመሟ እየጠናባት ቢሄድም በተለያያ ቦታ በመገኘት ለሰው ልጅ ይጠቅማል የምትለውን በሙሉ ማስተማሯን ተያያዘች ነገር ግን ጉልበትዋ እየከዳት ሲመጣ ከውድድር ልትሰናበት ተገደደች። ዶክተሮቹ በቃ :- ነገ ትሞቻለሽ ዛሬ ትሞቻለሽ እያሏት እሷ ግን በፈጣሪ እረዳትነት በህይወት የምትቆይበት 8 ወሩ ተጨመረላት። ነገር ግን ሰሞኑን ሳንባዋና ጉበቷ መስራት አቆሙ። ሰውነቷ መንቀሳቀስ አቃታቸው። በስተመጨረሻም እስትንፋስዋ ከዳት.....። It’s Ok #RIP Nan Pictures
Mostrar todo...
በአንድ ወቅት አንዲት ሴት ልጅ ህይወቷ የተመሰቃቀለ እንደሆነ እና አንዱን ችግር ስትፈታ ሌላ ችግር እንደሚገጥማት፤ መኖር እንደከበዳታ እና ከዚህ በላይ ችግሮቿን መቋቋም እንደማትችል አቤቱታዋን ለአባቷ አቀረበች፡፡ አባቷ የምግብ ሰራተኛ ነው፤ እናም ወደ ማብሰያ ክፍል ይዟት ሄደ፡፡ ሶስት ድስቶችን ውሃ ሞልቶ እሳት ላይ ጣዳቸው፡፡ በድስቶቹ ውስጥ ያለው ውሃ መፍላት ሲጀምር በአንዱ ድስት ውስጥ ድንች፤ በሌላኛው ውስጥ እንቁላል፤ በሶስተኛው ውስጥ ደሞ ቡና ጨመረባቸው እና ከደነው፡፡ እናም ምንም ሳይናገር መጠበቅ ጀመረ፡፡ ልጁ መነጫነጭና ትዕግስት በጎደለው መልኩ ምን ሊያረግ እንደሆነ ለማየት መጠበቅ ጀመረች፡፡ ከ20 ደቂቃ በኀላ እሳቱን አጥፍቶ ድንቹን፣ እንቁላሉን አውጥቶ በአንድ ሰሃን አስቀመጠ፡፡ ቡናውን በሲኒ ቀድቶ አስቀመጠ፡፡ "ልጄ አሁን ምን ይታይሻል? በማለት ጠየቃት፡፡ ልጅ በቁጣ ስሜት ሁና "ድንች፣ እንቁላል፣ ቡና" አለች፡፡ "በደንብ ተመልከች፤ ድንቹን ንኪው" አላት፡፡ እንዳላት አድርጋ ድንቹ ጥንካሬውን እንዳጣ ተገነዘበች፡፡ "እንቁላሉንም ስበሪው" አላት፡፡ ሰበረችው ነገር ግን አስኳሉ ሌላ ጠንካራ እና የሚያቃጥል አካል ሰርቷል፡፡ በስተመጨረሻ ከቡናው ፉት እንድትል አዘዛት፡፡ እሷም ቀምሳ ደስ የሚለው ጣዕሙ የፊቷን ፈገግታ ሲቀይረው ታወቃት፡፡ "አባቴ ይህ ምንድን ነው?" አለች፡፡ አባት ማብራራት ጀመረ.... "ድንቹ፣ እንቁላሉ እንዱሁም የቡናው ዱቄት ሁሉም እኩል የፈላ ውሃ ውስጥ ነው የገቡት፡፡ ነገር ግን ሁሉም ለፈላው ውሃ የሰጡት ምላሽ የተለያየ ነበር፡፡ ድንቹ በፊት ጠንካራ ነበር፤ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ጥንካሬውን አጥቶ ልፍስፍስ ሆነ፡፡ እንቁላሉ በፊት በቀላሉ ከተሰበረ ሜዳ ላይ የሚፈስ ልፍስፍስ አስኳል ነበር፡፡ ነገር ግን በፈላ ውሃ ሲፈተን ውስጡን አጠንክሮ መጣ፡፡ ከሁሉም የሚገርመው ግን የቡና ዱቄቱ ነው፡፡ በፈላ ውሃ ሲፈተን እራሱ ውሃውን ወደ ጣፋጭን መልካም ጠረን ቀይሮ አዲስ ነገር ፈጠረ፡፡ አንቺ የትኛው ነሽ?" ችግር ሲገጥማችሁ የእናንተ ምላሽ ምንድን ነው? እንደ ድንቹ መልፈስፈስ? ወይስ እንደ እንቁላሉ ውስጥን ማጠንከር? አልያም ችግሩን ለአዲስ ነገር መፍጠሪያ መጠቀም?" በህይወት ውስጥ ነገሮች በአካባቢያችን ይከናወናሉ፤ ነገሮች በእኛ ላይ ይደርሳሉ፤ ነገር ግን ትልቁና ወሳኙ በእኛ ውስጥ የሚከናወነው ነገር ነው!" የትኛው ነሽ??
Mostrar todo...
#ሰውን ከእንሳስ የሚለየው ማሰቡ ሲሆን ሰውን ደግሞ ከሰው የሚለየው ማንበቡ ነው #መልካም ቀን።
Mostrar todo...
ስብሃት ለአብ!! - «ለኔ ከስብሐት ደራሲነት ይልቅ ስብዕናው ጎልቶ ቢነገር የበለጠ ደስ ይለኛል። ምክንያቱም የስብሐት ውበት በስብዕናው፣ በሰውነቱ ይበልጥ ይጎላል» ማስታወሻ ገጽ 393 (ሚያዝያ 2006 እንደ አዲስ የታተመው) ከተማ ገብቼ ስሜ ረዘመብኝ፣ ለእርድና አይመችም ብዬ ከስሜ ላይ «ለአብ» የሚለውን በፈቃዴ ቀንሼ ስብሃት ብቻ ሆንኩ ይላል ስለ ስሙ ሲናገር - ተጫዋቹ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር። የፍስክ ጨዋታ አዋቂነቱ፣ ድፍረቱ እና ራሱን እንደድሮዎቹ ደራሲያን የማይቆልል መሆኑ ታላቅነቱ ላይ ጥላ አጥልቶበታል ብዬ አምናለሁ። ስለሱ ሲወራ አብዛኛው ወጣት የሚመጣለት ጨዋታዎቹ ናቸው። * ከመስታውት አራጋው ጋር በአንድ ስሙን የማላስታውሰው የኢንተርኔት ራዲዮ ላይ ሲጨዋወት «አሪፍ ሰው ምን ዓይነት ነው ላንተ?» ትለዋለች። ጋሽ ስብሃት «አሪፍ ሰው ማለት ብሽቅ ሰው ሲያጋጥመው አፍንጫውን በቡጢ የሚል ነው» ብሏት ያልፋል። ሌላ ጊዜ ደግሞ ጋሽ ስብሃት ወደ ካዛንቺስ ብቅ ባለበት አጋጣሚ አንድ ትልቅ ቢልቦርድ ያያል። ቢልቦርዱ ላይ የወቅቱን «ኤድስን በጋራ እንከላከል» የሚል መፈክር የያዘ ነው አሉ። ጋሽ ስብሃት ዞር ብሎ አጠገቡ ለነበረው ሰውዬ፦ «እንዴት ነዉ ነገሩ? በጋራ ነው የነፋናቸው እንዴ?» ይለዋል። ይሄን ሰምተን ብዙ ስቀናል። * በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ገ/አብ ስለ ስብሃት ሁለት ገጠመኞችን አጋርቷል፦ #አንድ «የእፎይታ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሳለሁ ደራሲ ስብሀት ገብረእግዚአብሔር አንድ ፅሁፍ ይዞልኝ መጥቶ ነበር። ማርያም ህፃኑን እየሱስ አዝላ ከፈርኦን ከሸሸች በኋላ ለሀያ አመታት ያህል ጣና ደሴት ላይ እንደተቀመጠች የሚገልፅ ውብ ልብወለድ ትረካ ነበር። ሳነበው ደስ አላለኝም። ወደ መቀመጫው ሄጄ ጠየቅኩት፣ «ምንድን ነው ይሄ ጋሽ ስብሀት?» «ታሪክ ነዋ» «እንዲህ መቀለድ ከአማኞች ጋር አያጋጨንም?» «እኔ ጽፌያለሁ። መወሰን ያንተ ፈንታ ነው።» አለኝ። ጥቂት አመነታሁ። ከዚያም በወቅቱ ምክትል ዋና አዘጋጅ ከነበረው ከመኩሪያ መካሻ ጋር መከርን። «ቁጣ ቢመጣ ስብሀት ላይ ነው» በሚል ተስማማንና ታሪኩ ታተመ። ትዝ ይለኛል። በነጋታው ከምሳ በፊት ጋዜጣዋ ተሽጣ አለቀች። ከዚያም አልፎ በጥቁር ገበያ እስከ አምስት ብር መሸጥ ጀመረች። ያኔ ዋጋዋ አንድ ብር ነበር። በዚያን እለት ስልክ አጨናነቀን። እንዲህ የሚሉ ቃላት ጎረፉ፣ «እፎይታዎች! ዛሬ አስደስታችሁናል። ታሪካችንን እንዲህ እየጎለጎላችሁ አውጡልን። ጋሽ ስብሀትን አመስግኑንልን! እንዲህ ነው ጋዜጠኝነት!! በርቱ!!» በነጋታው ጋሽ ስብሀት ሲመጣ ለቡና ይዤው ወጣሁና የሆነውን ሳጫውተው አይኑን ጨፍኖ መሳቅ ጀመረ። ስቆ ስቆ ሲያበቃ እንዲህ አለኝ፣ «ህዝቡ ታሪኩን ካመነው ምናልባት ታሪኩ እውነት ሊሆን ይችላል።» በዚህ ጊዜ ግን የመሳቁ ተራ የኔ ሆነ።» #ሁለት «ለጋሽ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር ለስድስት ዓመታት ያህል አለቃዉ ሆኜ ብንሰራም በአንዳንድ ነገሮች ላይ እርሱ ነበር የሚያዘኝ። አንድ ቀን እንዲህ ሲል ጠይቆኛል። «ላማክርህ ነበር የመጣሁት» «እሺ ጋሽ ስብሐት ምን ነበር?» «ገንዘብ ቸግሮኛል» ዝም አልኩ። ምክንያቱም የመጪዎቹን ሁለት ወራት ደመወዙን ከወዲሁ ወስዶ ነበርና ምን እንደማደርግ ግራ ሊገባኝ ጀምሮ ነበር። እሱም ይህንን ተገንዝቦ ኖሮ ፈጥኖ ንግግሩን ቀጠለ። «ደመወዜን ቀድመህ ስጠኝ ልልህ አልችልም። ወስጄዋለሁና። አሁን ሳስብበት ቆየሁና አንድ ሌላ ዘዴ መጣልኝ።» «ምን ዘዴ አገኘህ ጋሽ ስብሃት?» «ታታሪ ሰራተኛ በሚል ለምን ቦነስ አትሰጠኝም?» * * * የአንድ ደራሲ ስራዎች የደራሲው ማንነት ነፀብራቆች ናቸው። ለጋሽ ስብሐት ስራዎች ምንጭ ደግሞ የጋሽ ስብሐት ስብዕና ነው። ድንቅ ስብዕናን የታደለ ሰው ነው። ሰፌድን ሰፌድ ብሎ ለመጥራት ወኔው ነበረው ፥ በሐሰት ውዳሴ ሰው አያጅልም፥ አድር ባይነት አያውቀውም። የመረጠው መንገድ የሐቀኝነትን መንገድ ነው። ለዚህም ነው «የኤሚል ዞላን የአጻጻፍ ፈለግ ተከተልኩ» የሚለን። ሕይወትን ከነቡግሯ ሳትቀባባ ማስነበብ። እንደዚህ አይነት ጽሁፎች እኛው ራሳችን የምንኖረውን ሕይወት የሚያሳዩን በመሆናቸው ብዙ ላይስቡን ይችላሉ። የምንኖረውን ለምን እናነባለን የሚል ጥያቄ ያስነሳላ!! እውነተኛ ታሪክ የአንባቢውን ትኩረት እንዲያገኝ ልዩ የሆነ የሥነ ጽሁፍ ተሰጥኦ ይጠይቃል። ጋሽ ስብሃት ሁለቱን ነገሮች ተክኖባቸዋል። * አንዳንዶች ጋሽ ስብሐት የሀገራችንን ባህል በጽሁፎቹ ተጋፍቷል፣ አሳንሷል፣ አርክሷል በማለት ሲናገሩ ይስተዋላሉ። ይህ ለኔ የተንሸዋረረ አስተሳሰብ ነው። ከንባባችን ውስጥ የምናገኘው ቁምነገር ለማግኘት የምንፈልገውን ነገር ነው። ስለዚህ እነዚህ አንባቢዎች መልሰው ቢተቹትም የፈለጉትን ነገር ነው ያገኙት እላለሁ። አረዳዳችን ስናነብ የምንጠቀምበት «ሌንስ» ላይ ወይም ደግሞ ስናነብ ለማግኘት እየፈለግን ያለነው ነገር ላይ የተመሰረተ እንደሆነ አምናለሁ። በራሱ አገላለፅ «እኛ በድብቅ ያላደረግነውን ነገር አልጻፈም»። ጋሽ ስብሃትን በዚያ የሚከሱት ሰዎች ግብዞች ናቸው እላለሁ፤ ከአዝሙድና ከከሙን አስራት የሚያወጡ ነገር ግን ዋናውን ነገር የተዉ። ገጣሚ ኑረዲን ኢሳም «ኢሻራ» በተሰኘው መድብሉ አንድ ግጥም ለርሱ መታሰቢያ አድርጓል፣ ርዕሱ «ከ`ዳ ሽሽት» ይላል። ላንተ ለአዛውንቱ የቀለለችው ዳ ለኔ ለወጣቱ እንደመርግ ከብዳ እንዲህ ብዬ ፃፍኩኝ ስዳዳ ስዳዳ፤ “አይቶ የናዘረ ያው አመነዘረ ብሏልና ቄሱ መጽሐፉን ሲያስረዳ ላይቀርልን ዕዳ በይ ነይ እንባ . . . * አንድ የሱ «ማስተርፒስ» ነው የምለውን መጽሀፍ ለአብነት ላንሳ፤ አምስት ስድስት ሰባት። የሀገራችንን ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤ እና ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ያሳየንን «አምስት ስድስት ሰባት»ን መቼም አንዘነጋውም። የዚህ መጽሃፍ ፍልስፍናዊ ይዘቱ የትየለሌ ነው። «በሴት ጉልበት እጦት» የተፈጠረውን የቤታቸውን ችግር «ሌሊት» እየተነሱ አቶ በርሱፈቃድ ወንድ ልጅ የማይሰራውን የእህል መፍጨት ስራ እንደሰሩ ይነግረናል። ነገር ግን አቶ በርሱፈቃድ የተሳሳቱት ነገር ነበር፤ ይህንንም ጋሽ ስብሓት እንዲህ ብሎ ይነግረናል «ሲያስቡት እጄም ወገቤም ሞፈር ለምደዋልና ከእፍረቱ በስተቀር ወፍጮ ምንም አያስቸግርም መስሏቸው ነበር። አልሆነም፤ እንዳሰቡት አልሆነም» ይለናል። ሴቶቹ ችለውት የኖሩትን ሸክም ጋሽ ስብሓት በሌሊት ያስቃኘናል። ከዚህም ባለፈ ያ የገበሬ ቤተሰብ (የአቶ በርሱፈቃድ ቤተሰብ) ከበሬአቸው ከሲሳይ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ከዚህም የዘለለ እንደሆነ ይነግረናል። አንድ ስሙ የተዘነጋኝ የማህበራዊ ሳይንስ ምሁር/ፈላስፋ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ ሶስት አይነት ጥምረቶች አንዳሉ ይነግሩናል። እነዚህም የአሰሪና የሰራተኛ ጥምረት (አንዱ ስራ እንዲሰራለት ሌላው ገንዘብ ለማግኘት የሚያደርጉት ጥምረት)፣ የእኩሎች ጥምረት (ባልና ሚስት ዘር ለመቀጠል የሚያደርጉት ጥምረት) እንዲሁም የሰውና የእንስሳ ጥምረት (ለምሳሌ ገበሬው በሬው እንዲያርስለት እንዲሁም ሲብስበት ሊበላው ይፈልገዋል፣ በሬው ደግሞ ከአውሬ ስለሚጠብቀውና ስለሚቀልበው ገበሬውን ይፈልገዋል) ናቸው። ጋሽ ስብሐት ግን በዚህ ስራው በሃገራችን ያለው የሰውና የእንስሳ ጥምረት ከዚህ ያለፈ እንደሆነ ይነግረናል። አቶ በርሱፈቃድ በሬአቸው ሲሳይ ሲጎዳባቸው ተናደው ከገረፉት በኋላ እንዴት እንዳዘኑለት እና እንደተንሰፈሰፉ እንዲህ ሲል ይገልፅልናል « አቅፈው ሊያባብሉት አሰኛቸው. .
Mostrar todo...
.”ሆድ ብሶኝ ነው ጨንቆኝ ነው ርቦኝ ነው አትቀየመኝ ሲሳይ ወዳጄ፤ የመጨረሻ ወዳጄ” ባሉት፤ የበሬ ቋንቋ ባወቁና የልባቸውን በነገሩት።» ይለናል። በሬና ላም ለአንድ የገበሬ ቤተሰብ የቤተሰቡ አካላት ናቸው፤ ስም ወጥቶላቸው፣ አንክብካቤ ሳይጓደልባቸው ይኖራሉ። ስጋቸው በዚያ ቤተሰብ አባል አይበላም። ያ በሬ ተሽጦ ሌላ ይገዛል ወይ ደግሞ ሌላ ይቀየርበታል እንጂ ፈጽሞ እርሱ አይታረድም። ችግር፣ ረሀብ ግን ይህንን ታሪክ ሲቀይረው ጋሽ ስብሐት በኛው ቋንቋ ይነግረናል። ምናልባት አንድ መርከብ ተገልብጦ በላዩ ላይ ያሉት ሰዎች ደካማውን ሰውዬ በሉት የሚል ዜና ሰምተን ይሆናል። ጋሽ ስብሐት ይሄንን ለአንድ ገበሬ ከዚያ የከፋ ነገር እንዳለ በኛው ሀገር አውድ ያሳየናል። «የማበላቸውን ከልከልለህ ልጆች የሰጠኸኝ ምነው?» እያሉ ፈጣሪን የሚሞግቱትን አቶ በርሱፈቃድን ያሳየናል ጋሽ ስብሐት። «አረድኩት፤ ገፈፍኩት፤ ብልቱን አወጣሁት። ጠብሰን ቀቅለን በላነው ሲሳይን የመጨረሻ ወዳጃችንን። ወጥ እንዳይሆን እንጀራ የለን፤ ቋንጣ እንዳይሆን ቶሎ ጨረስነው። በላሁት ሲሳይ ዘመዴን። ለሆድ ለሰይጣን ሰዋሁት። ታዲያ ይሁዳ ከዳተኛ ነው ይላሉ። የኔን ታሪክ ያላወቁ። ይሁዳ እንኳን ተጸጸተ ተሰቀለ ዕዳውን ከፈለ። እኔ ግን! እኔ ግን! እኔ ግን!» * * * ከዚህ በታች ያለውን ምስክርነት ስለአጎቷ ስለ ጋሽ ስብሃት የፃፈችው Roman Tewolde ነች። ከበርካታ ዓመታት በፊት ስለርሱ በፃፍኩት ጽሁፍ ሥር በኮሜንት መልክ የፃፈችው ነበር፦ «Meet ETV በእንግሊዘኛ ባደረገው ኢንተርቪው (Youtube ላይ አለ) «መፃፍ ላንተ ቀላል ነው ወይ?» ብሎ ሲጠይቀው «ፁሁፍ ጥበብ ነው፣ እንደማንኛውም ጥበብ መታነጽ አለበት [. . .] አዎን ቀላል ነው፣ እንደማወራው ነው የምጽፈው። ያኔ እና አሁን አንድ አይነት ፀሃፊ አይደለሁም" ሲል መልሷል። ይህን ሲል ለኔ እንደሚታየኝ እንደወሬ መፃፍ ማለት ሳይሆን፣ ሃሳብን ለንግግር በሚጠቀምበት ቋንቋ መፃፍ ማለቱ ይመስለኛል። አነጋገሩን በጣም ሳያከብድ፣ ሳያሸበረቀርቀው መፃፍ ማለት ይመስለኛል። ለዚህም ይመስለኛል ፅሁፎቹ እየጣሙን የምናነባቸው (ወሬ አይጠላም መቸም)። እንደዛም ሆኖ ግን ዝም ብሎ ወሬ ማብዛት እና የተንዛዛ ቀደዳ መቅደድ ማለት አይመስለኝም። ሃሳቦቹን በስነስርዓቱ ቅደም ተከል አስይዞ፣ በቅርፅና ይዘትም ማነፅና መፃፉ ነው የሚታየኝ። እናማ እንደዚህ አይነት አፃፃፉ ውስጥ ልክ ለወሬ የምንጠቀምባቸውን ቃላት እና አባባሎች ይጠቀማል፣ "ሙቀጫ"ን "ሙቀጫ" ብሎ እንደመጥራት። ይህ በኔ አስተያየት ብልግና አይደለም - እንቅጩን መናገር/መፃፍ እንጂ። መልክዓ ስብሃት ላይ ከትችት አልፎ ወደ ስድብ ያደላ ወቀሳ ተሰንዝሮበታል። አንዱም የተወቀሰበት ነገር ስድስት ኪሎ ሃውልት ላይ ሽንታችንን ሸናን ብሎ ሌቱም አይነጋልኝም ላይ የፃፈውን ነገር አስመልክቶ ነው። ይህም አገሩን እንደማይወድ፣ ለአገሩም ሆነ ለአድዋ ድል ምንም አክብሮት እንደሌለው ተደርጎ ቀርቧል። ሌቱም አይነጋልኝም ላይ የተፃፈው "ኢትዮጵያውያን ፋሺሲዝንም ሳይሆን ጣልያንን ጠላት አደረጉት" ነው የሚለው። እናማ በዚህ አስተሳሰብ ለማሾፍ ያህል ይመስለኛል የሃውልቱ ነገር የተፃፈው። ሁሉም ጣልያናዊ ፋሽት አይደለም። ጣልያን ሁላ ፋሽት ነው የሚለውን በሕብረተሰባችን አስተሳሰብ ውስጥ የነበረውን አመለካከት ለማሳየት ብሎም የፃፈው ነው የሚመስለኝ። አገሩን የማይወድ ቢሆን ኖሮ ፈረንሳይም ሆነ አሜሪካ በነበረበት ግዜ እዛው መቅረት ይችል ነበር። በሕይወቱ በጣም ፈትኖታል ብዬ የማስበው ነገርም የአገር ፍቅሩ ይመስለኛል። የደርግ አብዮት ሲፈነዳ የሚወዳት ሚስቱና ልጁ አገር ለቀው መሄድ በነበረባቸው ግዜ እንኳን አብሯቸው መሄድ አልቻለም። አዳም ረታ "አገሮች ግን ልጆቻቸውን ከፍቅር መለያያ ጥበብ አላቸው" ብሎ በይወስዳል መንገድ የፃፈው እውነታ እንግዲህ ይሄው ነው! ስብሃት የራሱ አፃፃፍ ዘይቤ መፍጠር የቻለ ፀሃፊ ነው። አይነኬ የሚመስለን የተከበረውን የኢትዮጵያ ስነጽሁፍ በአሁኑ ግዜ ሁላችንም እንዳመጣልን እንድንሞነጭር ድፍረቱን ሰጥኖል ብዬም አምናለሁ። በዚህ ድፍረት ውስጥ ነው ደግሞ ሌሎችም የአፃፃፍ ዘይቤዎች እየተፈጠሩ ጥበቡ የበለጠ እየታነፀና እየበለፀገ የሚጓዘው ብዬም አምናለሁ። ስለ አይነኬ ጉዳዮችም በድረፍት ፅፏል። ይህንንም ድፍረት የሚወስዱ ፀሃፊዎች አሉን/እየተፈጠሩም ነው። የማሕበረሰብን አስተያየት እና አመለካከት የሚከፋፍልም ፀሃፊም ሰውም (ባሕሪያቱ ማለቴ ነው) ነው። የዚህ ጉዳት ምን እንደሆነም አይታየኝም። የተለያዩ አስተያየትና አመለካከቶች እየተፋጩና እየተጋጩ ነው ሌሎች አዳዲስ ሃሳቦችና አመለካከቶችን የሚፈጥረውና።» * * * ጋሽ ስብሃት የዛሬ 10 ዓመት በዛሬዋ ዕልተ ነበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው። ነፍሱ በሰላም ትረፍ!
Mostrar todo...
#ስለማይሰበረው_ኤርሚያስ_አመልጋ_በጥቂቱ በአዳዲስ የቢዝነስና የስራ ፈጠራ ሃሳቦች አፍላቂነታቸውና በፈር-ቀዳጅ ኢንቬስተርነታቸው በሚታወቁት ኢትዮጵያዊው ኢኮኖሚስትና ባለሃብት በአቶ ኤርሚያስ አመልጋ የሕይወት ታሪክና ስራዎች ዙሪያ የሚያጠነጥነውና በደራሲና ጋዜጠኛ አንተነህ ይግዛው የተጻፈው “የማይሰበረው - ኤርሚያስ አመልጋ” የተሰኘው መጽሐፍ በአጠቃላይ ዝግጅቱ ከስድስት አመታት በላይ ፈጅቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ከወላጆቻቸው የበስተጀርባ ታሪክ አንስቶ የአቶ ኤርሚያስ አመልጋን የልጅነት ሕይወትና አስተዳደግ ፣ የወጣትነት ዘመንና የትምህርት ቆይታ እንዲሁም ወደ አሜሪካ አቅንተው ከዘበኝነትና የዩኒቨርሲቲ ተማሪነት እስከ ግዙፉ የአለማችን የፋይናንስ ማዕከል ዎልስትሪት የኢንቨስትመንት ባንኪንግ ስመጥር ባለሙያነት የዘለቁበትን የረጅም አመታት ጉዞ የሚያስቃኝ ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ከ20 አመታት በላይ የተጓዙበትን በስኬትና በውድቀት የታጀበ፣ ፈተናና ውዝግብ ያልተለየው ረጅም የሕይወት ጎዳናም በዝርዝር ይዳስሳል፡፡ ��� አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በተለይም ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ የወጠኗቸውን አዳዲስና ሰፋፊ የፋይናንስ፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕቅዶቻቸውን ከዳር ለማድረስ ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ጉዞ ውስጥ ያጋጠሟቸውን እሾህ አሜካላዎች ፣ የተጋፈጧቸውን ፈተናና እንቅፋቶች በዝርዝር የተረኩበት መጽሐፉ፣ከባለታሪኩ የግልና የስራ ሕይወት ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ተሰምተው የማይታወቁ በርካታ አዳዲስና አነጋጋሪ መረጃዎችን ያካተተ ነው፡፡በሁለት ክፍሎች ተከፋፍሎ የቀረበውና 12 ዋና ዋና ምዕራፎች ያሉት “የማይሰበረው - ኤርሚያስ አመልጋ” የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ፣ “ማረፊያ አንቀጾች” እና “ድህረ-ታሪክ” የሚሉ ተጨማሪ ንዑሳን ክፍሎችን ጨምሮ አጠቃላይ የገጽ ብዛቱ 394 ነው፡፡ ��� በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የታሸገ ውሃ “ሃይላንድ” ለገበያ በማቅረብ እንዲሁም “ዘመን ባንክ” እና “አክሰስ ሪል ስቴት”ን ጨምሮ ባቋቋሟቸው የተለያዩ ኩባንያዎች የሚታወቁት አወዛጋቢው ኢኮኖሚስት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ ከብረታ ብረት ኮርፖሬሽን የሙስና ክስ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው መታሰራቸው ይታወቃል፡፡
Mostrar todo...