cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ካነበብኩት በጥቂቱ

📖 ማንበባችን እጥፍ ብናተርፍ እንጂ ከቶ አንከስርበትም፡፡ 📚 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል! 📔 ኑ! እያነበብን እራሳችንን እንገንባ፡፡ ☞ ያላችሁን ማንኛውንም አስተያየት በ @Kibu6008 አድርሱን።

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
552Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

😷 Local Disposable Face Mask 🔔 We have in bulk ⚠️ Only real buyers contact us @Kibu6008 or ☎️ call 0965608934, 0936844580
Mostrar todo...
😷 Disposable Face Mask 💸Only 11.50birr (Minimum Order 1,000) 🔔 We have in bulk ⚠️ Only real buyers contact us @Kibu6008
Mostrar todo...
📚 ያለንን ትርፍ ጊዜ መፅሀፍትን እያነበብን በማሳለፍ በምንም የማይተካ የአዕምሮ ሀብት የሆነውን ዕውቀት እንገብይ። መፅሀፍትን በpdf የማንበብ ልምድ ካለዎት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን አብርሆት የኢንተርኔት ላይብረሪ የተሰኘውን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቅለው መፅሀፍትን በነፃ ያንብቡ። በማንበብዎ ዕጥፍ ቢያተርፉ እንጂ ከቶ አይከስሩበትም። 📖 ጋሪሰን ኬይለር እንዳለው መፅሀፍት ሁሌም እንደ አዲስ የምንከፍታቸው የህይወት ዘመን ስጦታዎች ናቸው። ዛሬውኑ ይቀላቀሉንና ያቀርብንልዎትን የህይወት ዘመን ስጦታ የሆኑትን ውድ መጽሐፍት ይቀበሉን። t.me/pdfbookscloud
Mostrar todo...
አብርሆት የኢንተርኔት ቤተመጻሕፍት

📖 እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጡ እዚህ ቻናል ላይ መፅሀፍትን በፒዲኤፍ እና የተለያዩ ትረካዎችን ያገኛሉ። 📚 "መፅሀፍት ሁሌም እንደ አዲስ የምንከፍታቸው የህይወት ዘመን ስጦታዎች ናቸው።" ✏️ ጋሪሰን ኬይለር 🚧 ቻናላችንን ሼር በማድረግ አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት ያግዙ 👉 @pdfbookscloud 📚📚📚📚📚📚📚 📚 #ንባብ_ለአብርሆት 📚

🎉 ከ84 ከአመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የኢትዮጵያ ታላቁ ደራሲ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር ወደዚህች አለም ተቀላቀለ። ክብር የኢትዮጵያን የድርሰት አለም ከፍ ላደረገው ድንቅ ደራሲ። 🙏 መልካም ልደት አቦይ ስብሃት ነፍስህን በገነት ያኑርልን።
Mostrar todo...
📚 ራሳችንን ከሌላው እንነጥል ከአደገኛው የኮሮና ቫይረስም ራሳችንን እንጠብቅ በዛውም ይህን የመነጠል ወቅት መፅሀፍትን እያነበብን በማሳለፍ በምንም የማይተካ የአዕምሮ ሀብት የሆነውን ዕውቀት እንገብይ። መፅሀፍትን በpdf የማንበብ ልምድ ካለዎት ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን አብርሆት የኢንተርኔት ላይብረሪ የተሰኘውን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቅለው መፅሀፍትን በነፃ ያንብቡ። በማንበብዎ ዕጥፍ ቢያተርፉ እንጂ ከቶ አይከስሩበትም። 📖 ጋሪሰን ኬይለር እንዳለው መፅሀፍት ሁሌም እንደ አዲስ የምንከፍታቸው የህይወት ዘመን ስጦታዎች ናቸው። ዛሬውኑ ይቀላቀሉንና ያቀርብንልዎትን የህይወት ዘመን ስጦታ የሆኑትን ውድ መጽሐፍት ይቀበሉን። t.me/pdfbookscloud
Mostrar todo...
አብርሆት የኢንተርኔት ቤተመጻሕፍት

📖 እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጡ እዚህ ቻናል ላይ መፅሀፍትን በፒዲኤፍ እና የተለያዩ ትረካዎችን ያገኛሉ። 📚 "መፅሀፍት ሁሌም እንደ አዲስ የምንከፍታቸው የህይወት ዘመን ስጦታዎች ናቸው።" ✏️ ጋሪሰን ኬይለር 🚧 ቻናላችንን ሼር በማድረግ አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት ያግዙ 👉 @pdfbookscloud 📚📚📚📚📚📚📚 📚 #ንባብ_ለአብርሆት 📚

☞ስለዚህ በውስጣችን ያለውን የጽናት መጠን መፈተሹ እጅግ ወሳኝ ነገር ነው። ~ 9⃣ ጥምር ሃይል-(Power of the master mind)! : ☞No two minds ever come together without thereby creating a third, invisible intangible force, whichmay be likened to a third mind [the master mind]”. “ሁለት ጭንቅላቶች አንድ ላይ ሲሆኑ ሶስተኛ ጭንቅላት ይወለዳል”። አንድ ሰው የራሱ የሆነ ሃሳብ ወይም ግኝት ሊኖረው ይችላል፤ ከሌሎች ሰዎች ሃሳብ ሲደመር ይበልጥ ይሰምራል። : ☞“ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሐኒቱ” እንዲል የሃገራችን ሰው። : ☞በጋራ የመስራትን ልምድ ማዳበር መቻል አለብን። አብሮ መስራት መቻል ትልቅ ክህሎትም ጭምር ነው። ~ 🔟 የምታደርገው ነገር ደስታን ሊስጠህ ይገባል– (Enthusiasm)! : ☞ስቲቭ ጆብስ በህይወት በነበረበት ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር “የምንሰራውን ነገር የማንወደው ከሆነ እስከመጨረሻው ለመሄድ አንችልም፤ የሚሰራውን የማይወድ ማንኛውም ሰው ተስፋ ቢቆርጥ አይፈረድበትም”። ፡ ☞እውነት ነው የምንወደውን ነገር ስናደርግ በቀላሉ ተስፋ አንቆርጥም። ፡ ☞ሙያችን እንዲሆን የምንመርጠው ነገር የምንወደው ነገር ከሆነ በዛ ነገር ላይ እውቀታችንን ለማዳበርም ሆነ ልምድ ለማግኘት ፍላጎት ይኖረናል። ፡ ☞አስቡት ሰውን መርዳት የማይወድ ወይም ለሰ ሰው ምንም ግድ የለለው ሰው የህክምና ባለሙያ ቢሆን፤ በሽተኞቹን እንደ ገንዘብ ማግኛ ከመቁጠር በቀር ለጤንነታቸውም ሆነ ለደስታቸው ዴንታ አይሰጠውም። ፡ ☞ስለዚህ የምንሰራው ነገር ምን ያህል ደስታ ወይም እርካት ይሰጠናል የሚለው ጥያቄ በተሰማራንበት መስክ ሁሉ እራሳችንን ልንጠይቀው የሚገባን ጥያቄ ነው። 🌌 የተባረከ ምሽት ይሆንላችሁ ዘንድ ተመኘን 📚 በማንበባችን እጥፍ ብናተርፍ ነው እንጂ ከቶ አንከስርበትም 📚 ⛔️ ራሳችንን ከአስከፊው ወረርሽኝ እንጠብቅ የኛ ጤና መሆን ለሌላውም ነውና! @SebhatG @SebhatG @SebhatG
Mostrar todo...
✋ ሰላም እንዴት አመሻችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች በአለማችን ላይ ስለስኬት ከተጻፉ መጻሕፍት ውስጥ ቁጥር አንድ እንደሆነ የሚነገርለት የ “Thinkand Grow rich” ደራሲ ናፖሊዮን ሂል፤ ምንም እንኳን የምንፈልጋቸው ነገሮች ቢለያዩም ሁላችንንም ለስኬት የሚያበቁ ድንቅ መመሪያዮችን በመጽሃፉ አስፍሯል። : ☞እናም እኛንም በመረጥነው የህይወት ጉዞ ላይ ከረዳን ብዬ አስሮቹን የስኬት መርህዎች ኸርል ናይቲንጌል ካሰናዳው ላይ እንዲህ አቀናብሬ አቅርቤያቸዋለው። ~ 1⃣ ፍላጎት(Desire)! : ☞የመጀመሪያው ደረጃ ፍላጎት ነው። ከልብ የመነጨ ፍላጎት፤ፍላጎታችንን እንደ ዘር ልናየው እንችላለን። ፍሬ እንደሚያፈራ አምነን የምንዘራው ዘር። ዛሬ ዘርተነው ዛሬውኑ ፍሬ የሚሰጠን ተክል የለም። : ☞ፍላጎታችንም ልክ እንደ በቆሎ ወይም ማንኛውም ዘር ዛሬ ተዘርቶ በቂ ውሃ፤ በቂ ጸሃይ፤ በቂ እንክብካቤ ፤ካገኘ በኋላ በግዜው የሚያሽት ነው። : ☞የምንፈልገውን ነገር ጥርት ባለ መልኩ ማወቁ ይጠቅመናል። : ☞ለመረጥነው ነገር ምን ያህል ፍላጎት እንዳለን ለማወቅ የምናደርጋቸውን ነገሮች መቃኘት ያስፈልገናል። : ☞ከምንም በላይ በውስጣችን ያለው የትዕግስት መጠን ፍላጎታችን ምን ያህል እንደሆነ ያስረዳናል። : ❀ለምሳሌ ሰዓሊነት ፍላጎቱ የሆነ ሰው ባይከፈለው እንኳን ስዕል መሳሉን አያቆምም። : ☞አላማ ብለን ለመረጥነው ነገር በቀላሉ ሊገደብ የማይችል ፍላጎት ሊኖረን ይገባል። : ☞ጥልቅ ፍላጎት ማለት ወደ ኋላ እንዳናፈገፍግ የመመለሻውን ድልድይ እንደማቃጠል ያህል ነው። ~ 2⃣ እምነት(Faith)! : ☞እምነት አላማችን የሚገነባበት መሰረት ነው። የምንፈልገው ነገር ምንም ይሁን ምን እምነት ከሌለን ነዳጅ የሌለው መኪናን ለመንዳት እንደመሞከር ይሆንብናል። : ☞ደግነቱ እምነት በመጀመሪያ ባይኖረንም፤ በሂደት ልንገነባው የምንችለው ጥበብ ነው። : ☞ለአይምሮዋችን ቀና የሆኑ ነገሮችን በመመገብ እምነትን በሂደት ማዳበር ይቻላል። : ☞የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት እምነት እጅግ ወሳኝነገር መሆኑን መዘንጋት የለብንም። : ☞ማርቲን ሉተር ኪንግ ስለ እምነት ደስ የሚል አባባል አለው ” እምነት ማለት ሙሉውን ደረጃ እስከየት እንደሚደርሰን ባናውቅም እንኳን የመጀመሪያውን ደረጃ መውጣት ነው” ይላል። ~ 3⃣ ራስን ማሳመን-Auto Suggestion (አውቶ ሰጀሽን)! : ☞አይምሮዋችን እውነት ብሎ የሚቀበለው ነገር ደግመን ደጋግመን የምንመግበውን ነው። : ☞እዚህ ላይ ይህንን በደንብ የሚያስረዳ አንድ ታሪክ ትዝ አለኝ። : # ታሪኩ እንዲህ ነው:- : <ሁለት ውሾች የነበሩት አንድ ሰው ነበር።አዘውትሮ እኒህን ውሾች አደባባይ እየወሰደ እንዲደባደቡ ያደርግ ነበር። ታዲያ ተመልካቾቹ የትኛው ውሻ በእለቱ እንደሚያሸንፍ ሲጠይቁት “በደንብ የምመግበው ውሻ ነው” ሲል መለሰላቸው። >> : ☞ሁላችንም ውስጥ ሁለት ዉሾች አሉ:- : ✔ የመልካም እና የክፋት፤ : ✔ የልማት እና የጥፋት፤ : ✔ የእውቀት እና የድንቁርና፤ : ✔ የውድቀት እና የድል ውሾች። : ✔ የበላይ ሆኖ የሚመራን ውሻ ዘወትር የምንመግበው ነው። : ☞ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል “አውቶ ሰጀሽን”ወይም ለራስ መልካም ነገሮችን ደጋግሞ በመንገር አይምሮዋችንን ወደፈለግነው መንገድ መምራት እንደምንችል የሚነግረን።መንገር ብቻም ሳይሆን የሚያሳስበን! ~ 4⃣ በአንድ ነገር ላይ እራስን የተካኑ ማድረግ(Specialized Knowledge)! : <“Mastermind group- associate with men who know what you want to specialize in” ልንሰማራበት በመረጥነው ወይም ፍላጎት ባለን ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መተዋወቁ እና ቅርርብ መፍጠሩ ወሳኝ ነገር ነው።> : ጊዜያችንን የምናሳልፈው ከነማን ጋር ነው? : የምናውቃቸው ሰዎች ወይም ጓደኞቻችን ለምንፈልገው ሙያ የሚያግዙን ናቸው? : ☞ለምሳሌ፦ ፡ ✔ ፕሮፌሰር ለመሆን ፍላጎት ያለው ሰው በተቻለው መጠን ዩንቨርሲቲ አካባቢ ካሉ ሰዎች ጋር ግንኙነቱን ቢያዳብር ይጠቅመዋል። : ✔ ተዋናይ መሆን የሚመኝ ሰው እራሱን ከቲያትር መድረክ አካባቢ ማራቅ የለበትም። : ☞ሁላችንም የምንማረው ቀድመውን ካወቁት ነውና፤ የምንፈልገውን ነገር በቅጡ የሚያውቁ ሰዎችን ማወቁ ይጠቅመናል። ~ 5⃣ ነገሮችን በህሊናችን መሳል (Imagination)! : ☞“Imagination- It’s the workshop, the impulse. men can create what he can imagine. what the mind conceives it achieves”. ሁሉም ነገር ሃሳብ ነበር። ምንም ነገር እውን ሆኖ ከማየታችን በፊት በአንድ ሰው አይምሮ ውስጥ የተጠነሰሰ ሃሳብ ነበር። : ☞የምንፈልገውን ነገር እውን ሆኖ ከማየታችን በፊት በህሊናችን መሳል ትልቁ የስኬት ሚስጥር እንደሆነ ብዙዎች የተስማሙበት ነው። : ☞አላማችን ቁልጭ ብሉ በህሊናችን ከታይን ለጉዞዋችን ትልቅ ጉልበት አገኘን ማለት ነው። ምክንያቱም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እንደሚሳካ አይምሮዋችን እየነገረን ነው። ~ 6⃣ እቅድ ማውጣት (Organized Planning)! : ☞እቅድ ማውጣት ጊዜን በአግባቡ እንድንጠቀም ከማድረጉም በላይ፤ በአንድ ጊዜ አንድ ደረጃ እየወጣን ጉዞዋችን አድካሚ እንዳይሆን ያደርግልናል። ፡ ☞እቅድ ስናውጣ ነገሮች ሳይደራረቡብን ቀስ በቀስ ወደ ግባችን እንደርሳለን። ፡ ☞እቅድ ስናወጣ ግን እራሳችንን በሚያጨናንቅ እና ካልፈጸምነው የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን በሚያደርግ ሁኔታ ሳይሆን፤ ከጊዜያችን ፤ ከባህሪያችን እንዲሁም ከማንነታችን ጋር የሚስማማ እቅድ ነው ማውጣት አለብን። ምክንያቱም ሌላው ያቀደበት መንገድ ለኛ ላይስማማ እና ከግባችን ላያደርሰን ስለሚችል። ~ 7⃣ ውሳኔ (Decision)! : ☞“lack of decision is the top reason for failing. if you make a decision its worth sticking toit. don’t let others opinion to sway you” .የሰው ልጅ ውድቀት አንደኛው መንስዔ የውሳኔ ማጣት ነው። አንድ ሰው ምንም ያህል እምቅ እውቀት ቢኖረው፤ ምንም ይህል የሚያስደንቅ ሃሳቦችን ማመንጨት ቢችልም ውሳኔ መወሰን ካልቻለ ግን አቅሙ ሁሉ ከውስጡ አይወጣም። ፡ ☞ውሳኔ በማጣት የተነሳ ብዙ ሙዚቃዎች ሳይሰሙ፤ ብዙ መጽሐፎች ሳይጻፉ፤ ብዙ ግኝቶች ሳይገኙ፤ ወደ መቃብር ይወርዳሉ። ፡ ☞በሁላችንም ውስጥ ለኛ ብቻ የተሰጠ ስጦታ አለ፤ ይህን ስጦታ ግን አውጠን ሌሎች እንዲያዩት ማድረግ የምንችለው ውሳኔ መወሰን ስንችል ብቻ ነው። ፡ ☞የምንወስነው ምንድን ነው ካላችሁ፤ መልሱ የምንወስነው መሆን የምንፈልገውን ነው። ~ 8⃣ ጽናት (Persistence)! : ☞“the power of will. This quality distinguishes the success from the failure. it’s a state of mind and can be cultivated”. ውሳኔ ብቻውን አቅም የለውም። ውሳኔያችን ባህሩን አቋርጦ ከአላማችን ዳርቻ እንዲደርስ የሚያደርገው ሃይል ጽናት ነው። ብዙዎⶭችን የተለያዩ ውሳኔዎችን እዚህና እዚህ እንወስናለን ነገር ግን ጽናት ኖሮን አንገፋበትም። : ☞ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል የወድቀት እና የስኬት ዋናው መለያ ጽናት ነው ያለው። : ✔ለምሳሌ ከመጠጥ ሱስ መላቀቅ የሚፈልግ ሰው መቶ ጊዜ ለማቆም ቢወስንም ከውሳኔው ጋር ጽናት ካልተደመረበት በቀር ውሳኔው ብቻውን ምንምዋጋ የለውም። :
Mostrar todo...