cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የበርለዓሙ የሺዋስ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
183Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ወጣት መነኩሴ ወደ አባ እንጦንዮስ መጣ። እየተማረረ እንዲህ አለ "አባቴ ሆይ ከመነኮስሁ ዓሥር ዓመታት አለፉኝ። ነገር ግን የዲያቢሎስን ፈተናውን መታገስ አቃተኝ ፣ እጅግ እየታገለኝ ነው" አባ እንጦንስም ለዚህ መነኩሴ የሚገባውን ምክርና ተግሣፅ ሠጥቶ አሰናበተው። መነኩሴው ከወጣ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ አባ እንጦንስ ቀርቦ እንዲህ አለ። "በሕያው እግዚአብሔር እምላለሁ ፣ ይኼ ሰው መመንኮሱንም አላውቅም" እኛ በዲያቢሎስ ተፈተንሁ ለማለት ራሱ ገና ነን ፣ ምክንያቱም የራሳችንን ድካምና ምኞት ገና ድል አልነሣንም። "ምንም እንደ መቅደሱ መንጻት ባይነጻ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልቡን የሚያቀናውን ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው" (2 ዜና 30: 19)
Mostrar todo...
ሕልሜን ተርጉሚልኝ ከዕለታት አንድ ቀን ወይዘሮ ፋጡማ የሚገርም ሕልም ታያቸው፣ ደንግጠው ከመኝታቸው ተነሡ፡፡ ምን እንደሚያደርጉ ግራው ገባቸው፡፡ ሌላ የሚያማክሩት ሰው በቅርብ ስለሌላቸው ወደ ወይዘሮ ብዙነሽ ሔዱ፡፡ ደኅና አደራቹ ብዙነህ አሉ ወይዘሮ ፋጡማ፡፡ ብዙነሽም ደኅና አደርሽ ፋጡማ ግቢ አሏቸው፡፡ ፋጡማም “ዛ…ሬ…የሚ..ያ.ስ.ፈራ ሕልም አይቷል” በማለት ፋጡማ ግራ እንደገባቸው እና መረጋጋት እንዳቃታቸው ነገሯቸው፡፡ ምንድነው ፋጡማ? አሉ ብዙነሽ፡፡ ሌሊት “በሕልሜ አንድ ቀይ ሰው ወደ ቤቱ ጊቢ፣ ወደ ቤቱ ጊቢ፣ ወደ ቤቱ ጊቢ አለኝ” አሏቸው፡፡ ለመሆኑ የሕልሜ ትርጉም ምንድነው? በማለት ጥያቄያቸውን አስከተሉ፡፡ ወይዘሮ ብዙነሽም ወደ ቤት ግቢ ማለቱ ክርስትና ተነሽ ማለት ነው በማለት መለሱላቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ፋጡማ ተናደዱ፡፡ ሃይማኖት ያለሽ አንቺ ብቻ ነሽ፡፡ እኔ ሃይማኖት የለኝም ማለት ነው፡፡ እኔም እብድነኝ ላንቺ ማማከሬ በማለት ተሳድበው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ ወይዘሮ ብዙነሽም ስቀው አንቺው ፍችልኝ ብትይኝ ነገርኩሽ እንጂ መቺ አስገደድኩሽ ብለው ዝም አሉ፡፡ ፋጡማ ከቤታቸው ቢሔዱም የሕልሙ ነገር እየደጋገመ እየታሰባቸው ዕረፍት ነሣቸው፡፡ የሚያደርጉት ግራ ቢገባቸውም የሚያማክሩት ሌላ ሰው የላቸውም እና ደግመው ወደ ብዙነሽ ምክር ለመቀበል ሔዱ፡፡ ብዙነሽን ሲያማክሯቸው መልሳቸው ባያስደስታቸውም ጭንቀታቸውን ማማከሩ አማራጭ የለውም፡፡ ብቻቸውን መነጋገር የዕለት ከዕለት ተግባራቸው ሲሆን ወይዘሮ ብዙነሽን ማመኑንስ ልመን ለመሆኑ ማነው የሚያስተምረኝ እና ክርስትና የሚያነሣኝ በማለት ጠየቋቸው፡፡ ወይዘሮ ብዙነሽም መምህሬ ሙሉነህ ያስተምሩሻል በማለት መለሱላቸው፡፡ መምህሬ ሙሉነህ ዕድሜያቸው በደንብ የማይታወቅ ቢሆንም አንዳንዶች 110፣ ሌሎች 115፣ ደግሞ ሌሎች 120 ዓመታቸው ነው ይሉ ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ ገበዝ ናቸው፡፡ ወይዘሮ ፋጡማ ክርስቲያን ለመሆን ፈቃደኛ በመሆናቸው ወይዘሮ ብዙነሽ ይዘዋቸው ወደ መምህሬ ሙሉነህ ሔደው አጫወቷቸው፡፡ መምህሬ ሙሉነህም አስተምረው አስተምረው አጠመቋቸው፡፡ የድሮዎቹ መምህራን እንደ ዘመናችን ሰባኪዎች አቀላጥፈው መናገር ባይችሉም ፍጹም መንፈሳዊ ስለነበሩ የሚናገሩት ጥቂት ነገር መልካም ፍሬ ያስገኝ ነበር፡፡ የወይዘሮ ፋጡማ ስመ ጥምቀታቸው ወለተ ሥላሴ ተብሎ የሥላሴ ልጅነትን አገኙ፡፡ ልጆቻቸውም ከእናታቸው ጋር አብረው ተጠመቁ፡፡ ፋጡማ ከመጠመቃቸው ከሁለት ወይም ከሦስት ዓመት በፊት አንድ ሰው ድብኝት ነገር አምጥቶ እንካ ይህን ወደ ቤቱ ለሚመጡ ሰዎች ስጣቸው በማለት ለመምህሬ ሙሉነህ ሰጥቷቸው ዕቃ ቤት አስቀምጠውት ይኖር ነበር፡፡ ወይዘሮ ፋጡማ ተጠምቀው የሥላሴ ልጅነትን ካገኙ በኋላ መምህሬ ሙሉነህ ወለተ ሥላሴ ብለው ጠርተው ከሁለት ይሁን ከሦስት ዓመት በፊት አንድ የማላውቀው ሰው ወደ ቤቱ ለሚመጡ ሰዎች ስጣቸው ብሎ አንድ ድብኝት ሰጥቶኝ ነበር፡፡ ምን እንደሆነ አላውቅም፤ እንግዲህ ወደ ቤቱ የመጣሽው አንቺ ከነልጆችሽ ነሽ፡፡ ምን እንደሆነ ባላውቅም አደራ በላ እንዳታደርጊኝ እባክሽ ይህን ድብኝት ውሰጅልኝ በማለት አውጥተው ሰጧቸው፡፡ ድብኝቱ መያዣ መጨበጫ ጀሮም፣ አፍም የለውም፡፡ ቢያንከባልሉት፣ ቢያገላብጡት ሰንጥቅም የለውም። ምን እንደያዘም አይታወቅም፡፡ ወይዘሮ ፋጡማ ከቤታቸው ወስደው ቢያገላብጡ አፉን ማግኘት ስላልቻሉ እያገላበጡ ሲመለከቱ ከእጃቸው አምልጦ መሬት ላይ ሲወድቅ ለካ በውስጡ ሦስት መቶ ጠገራ ብር ነበረበት ወለሉ ላይ ፎጭ አለ፡፡ ፋጡማም በጣም ደንግጠው እየሮጡ ወደ መምህሬ ሙሉነህ ሔዱ። በድብኝቱ ውስጥ ሦስት መቶ ጠገራ ብር እንደ ነበረበትም ለመምህሬ ሙሉነህ ነገሯቸው፡፡ መምህሬ ሙሉነህ የእግዚአብሔርን ሥራ አደነቁ፡፡ ለልጆቹ እና ለሚያምኑበት በረከተ ሥጋ፣ በረከተ ነፋስ በመስጠቱ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ፋጡማም መምህሬ ይህንን ያህል ገንዘብ እኔ በሌለሁበት አንዱ መጥቶ ይወስድብኛል እና ከብት ይገዛበት አሏቸው፡፡ በዘመኑ ከብት ርካሽ ነው፡፡ ጊደር በሽልንግም፣ በአንድ ጠገራ ብርም በአጠቃላይ ወደ ሦስት መቶ ቁም ከብት ገዙበት፡፡ ክርስትና በመነሣታቸው ሀብተ ሥጋ፣ ሀብተ ነፍስ ሲመጣ ለልጅቱ ባል መጣ፡፡ የመጣው ባል አምሳ ቁም ከብት ያለው ነበር፡፡ ወይዘሮ ፋጡማም ለልጃቸው አምሳ ቁም ከብት ሰጡ፤ ልጃቸው ትዳር መሠረተች፡፡ ወለተ ሥላሴ ገበያ ለገበያ ተንከራትተው ከመኖር ቤተ ክርስቲያን እየተሳለሙ ወደ መኖር ተሸጋገሩ፡፡ የወይዘሮ ብዙነሽ ብርሃን መሆን ፋጡማን ወደ ክርስትና አመጣቸው፡፡ ወደ ክርስትና ማምጣት ብቻ ሳይሆን ከድህነትም አወጣቸው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚወዱት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን እንዳለው ሐዋርያው። የክርስትና እምነት ሀብተ ሥጋ ከማግኘት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባይኖረውም ላመኑበት እንኳን የዚህን ዓለም ሀብት ሰማያዊውንም ያስገኛል። ለበለጠው እንትጋ በማለት ታስተምራለች።ይህም ፍጽምት ሕግ መሆኗን ያስረዳል።
Mostrar todo...
ክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ የሴቶች አንድነት ገዳም ክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ አንድነት ገዳም ቅዱስ ላሊበላ ከመንገሡ በፊት ከዘመዶቹ ተጣልቶ በተሰደደ ጊዜ በቆየበት አካባቢ የተመሠረተ ገዳም ነው። ቦታው ምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት በደቡብ ሜጫ ወረዳ ይገኛል። ከገዳሙ ትንሽ ከፍ ብሎ ዓፄ ፋሲለደስ የመሠረቷት ናዳ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ትገኛለች። ቀበሌው ደብሯም ናዳ የተባሉበት ምክንያት አባ ናዳ የተባሉ መነኲሴ ከቤተ ክርስቲያኑ ጣራ ላይ ወጥተው ሲሠሩ ተንከባልለው ምንም ሳይሆኑ በመቅረታቸው ለዚያ መታሰቢያ ነው። ቤተ ክርስቲያኗ ጥንታዊት እና ታሪካዊ ናት። ከዚች ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ ትንሽ ራቅ ብሎ ክብረ ደናግል ናዳ ቅዱስ ላሊበላ የሴቶች አንድነት ገዳም ይገኛል። ገዳሙ የተመሠረተው ለሊቀ ብርሃናት ቆሞስ የኔታ ይባቤ በላይ አባታቸው በሰጧቸው መሬት ነው። በቦታው የቅኔ፣ የትርጓሜ መጻሕፍት፣ የፍትሐ ነገሥት እና የአቡሻከር መምህር የሆኑት የኔታ ይባቤ በላይ ለማስተማር ቢፈልጉም ተማሪ በመጥፋቱ ምክንያት ቅኔ እና ትርጓሜ መጻሕፍት በማስተማር ተወስነዋል። ጉባኤ ቤቱን የእኔ የሚለው በመጥፋቱ በደኅና ጊዜ የተሠራው የተማሪዎች መኖሪያ ሊፈርስ ተቃርቧል። በዚህ አካባቢ ጻድቁ ቅዱስ ላሊበላ ከቡግና ተሰዶ መጥቶ ብሉያትን እና ሐዲሳትን እንደተማረ የኔታ ይባቤ ይናገራሉ። በአካባቢው ጻድቁ ንጉሥ መቆየቱን ለማዘከር በክብረ ደናግል ናዳ ላሊበላ አንድነት ገዳም የተሠራው አዲሱ ቤተ ክርስቲያን ትውፊቱን ጠብቆ ምድር ቤቱ የመድኃኔዓለም ታቦት፣ ከላይ የቅዱስ ላሊበላ ታቦት ሊገባበት ሥራው ተጠናቋል። የቤተ ክርስቲያኑ ኮርኔስ በበሬ ቆዳ ተሠርቷል። የፈጀውም የ1400 በሬ ቆዳ ነው። ለምን በበሬ ቆዳ ተሠራ ብዬ ለጠየቅኳቸው ጥያቄ የኔታ ይባቤ ቅዱሱ አባት ከበሬ ቆዳ በተሸረበ ጅራፍ ስለተገረፈ ነው ብለውኛል። ቤተ ክርስቲያኑ በ28 ጌጅ ቆርቆሮ ተሠርቷል። የዚህ ምክንያትም የቅዱሱ አባት ክብረ በዓል ዋዜማው ታኅሣሥ 28 ቀን ስለሆነ እና በዓለ ልደት ከአራት ዓመት አንድ ጊዜ በ28 ስለሚከበር ነው ብለውኛል። በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ ከውጭ 12፣ ከውስጥ ደግሞ 8 ዋሻዎች ተፈልፍለዋል። ዋሻዎቹ የተፈለፈሉበት ምክንያትም በቦታው የሚያርፉ አባቶች ጸሎት አድርገው፣ ሱባኤ ይዘው እንዲሔዱ ነው። ቤተ ክርስቲያኑ በገዳሙ መነኰሳት እና በአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን ትብብር ተሠርቶ በመጠናቀቁ ጥር 30 ቀን ቅዱሳን ፓትርያርኮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ ከቅርብም ከሩቅም የሚመጡ ክርስቲያኖች በተገኙበት ሊመረቅ ቀን ተቆርጦለታል። ቤተ ክርስቲያኑ በአንድ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ባሠሯት ጊሼን ደብረ ከርቤ አምሳል የተሠራው በመስቀል ቅርፅ ነው። የቤተ መቅደሱ አሠራር ብሉይንና ሐዲስን አጣምሮ የያዘ ነው።ይህም አገራችን ኢትዮጵያ ብሉያትንም፣ ሐዲሳትንም አንድ አድርጋ የመያዟ ምሳሌ ነው። ቦታው ገዳማውያን ለሥራ አርአያ መሆናቸውን የሚያስገነዝብ እና ከሥራ የለገመ መጥቶ ከመነኰሳቱ ተምሮ ቢሔድ በሥጋውም፣በነፍሱም የሚጠቀምበት ቦታ ነው። በዚህ ገዳም የሚኖሩ መነኰሳት 24 ሰዓት ሙሉ ዕረፍት አያውቁም። ይህም ክርስቲያኖች ገዳም የሚገቡት ከሥራ ለመሸሽ ለሚመስላቸው ስሑታን ትምህርት የሚሰጥ ነው። በቦታው ልዩ ልዩ አገር በቀል ዕፅዋት ይገኙበታል። ዕፅዋት ብቻ ሳይሆኑ ልዩ ልዩ የዱር አራዊትም ይገኙበታል። ይህም ቤተ ክርስቲያናችን በብዝኃ ሕይወት ጥበቃ ቀዳሚ ለመሆኗ ምሥክር ነው።
Mostrar todo...
ማን አመነኰሳት? ዲ/ን አሻግሬ አምጤ አንድ ቀን አንድ ወዳጄ እንዲህ አለኝ፡፡ በአካባቢዬ አንድ ደግ ሴት ነበሩ፡፡ የእስልመና እምነት ተከታይ ናቸው፡፡ በእንተ ስማ ለማርያም ያለ የቆሎ ተማሪ ከእሳቸው ሳይዘከር አያልፍም ነበር፡፡ ከቤታቸው ሳይለምን ያለፈን ተማሪ ከእመቤቴ በረከት ልትለየኝ ነው ይሉ ነበር አሉ። በተለይ ቤተሰቦቻቸው በአካባቢው ከሌሉ ጨዋታቸው በክርስቲያናዊ ትውፊት የተቀመመ ነበር አሉ፡፡ አጠገባቸው ሰው ካለ ብዙ አይናገሩም፤ ለለመነ ሁሉ ሙሉ እንጀራ አጥፈው ይሰጣሉ፡፡ አቤት የጐረቤት ሰው ሲወዳቸው፡፡ ልጆቹማ ቢታሰሩም ከቤታቸው አይቀሩም፡፡ የሚሰጡት ሁሉ የሚጣፍጥላቸው፣ የነኩት ሁሉ ብሉኝ ብሉኝ የሚልላቸው ደግ ሴት ነበሩ፡፡ ልጆች ከወላጆቻቸው በላይ ይወዷቸዋል፤ ታመው ሲተኙ እንዴት አልጋቸውን ከበው ዓይን ዓይናቸውን ይመለከቷቸው እንደ ነበር አጫውቶኛል። ኑሮዋቸው ከእጅ ወደ አፍ ቢሆንም ቸግሯቸው የሰው እጅ አይተው አያውቁም፡፡ በአንድ ወቅት ታመው ጎናቸው ምንጣፍ ነካ። ከዛሬ ነገ ይሻላቸዋል ሲባል ከመኝታቸው መነሣት ተሳናቸው። ሰውነታቸው ቢደክምም ሁል ጊዜ ከፊታቸው የሚነበበው ደስታ ነበር፡፡ ጥቂት ታመው ዐረፉ፡፡ ሲሞቱ የልጆቼን ነገር አደራ ብለው ለማንም አልሰጡም፡፡ ሴትዮዋ ልጆቻቸውን ለማን አደራ እንደሰጧቸው ያውቁ ኖሯል፡፡ ሲያርፉ ዘመዶቻቸው በሃይማኖታቸው መሠረት የሚፈጽሙትን ሊያደርጉ ሲያዩ ሴትዮዋ ወገባቸውን በሐብል ጥብቅ አድርገው አስረውታል፡፡ ሐብሉ ትንንሽ መስቀሎች አሉበት፤ ዘመዶቻቸው ደንግጠው ወደ ክርስቲያን ጐረቤቶቻቸው ሔደው አማከሯቸው፡፡ ክርስቲያኖችም ፈጥነው ወደ ደጓ ሴት ቤት ሔዱ፤ ሴትዮዋ ለካ መንኲሰዋል፡፡ መቼ የት ከማን? እንደመነኮሱ አይታወቅም፡፡ መጨረሻ ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን ይቀበሩ በማለት አሳብ አቀረቡ፡፡ ሙስሊሞች ደግሞ የለም የአገር መሳቂያ አንሆንም ከእስላም መቃብር ትቀበራለች አሉ፡፡ ሽማግሌ መከረ ቄስ ተጠራ፡፡ ስምምነት ሲጠፋ አንድ ካህን ሴትዮዋ እንደሆነ ገነት ገብተዋል፡፡ ዘመዶቻቸው ከፈለጉበት ቦታ ይቅበሯቸው ብለው ተናገሩ፡፡ በቄሱ አሳብ ስምምነት ላይ ደርሰው ሙስሊሞች ከፈለጉበት ቦታ ሙስሊሞችም ክርስቲያኖችም ተገኝተው አልቅሰው ቀበሩዋቸው ብሎኛል፡፡ እንዲህ ዓይነት ስንት ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ከእግዚአብሔር በቀር የሚያውቅ የለም፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ከእኒህ ደግ ሴት በረከት ይክፈለን። አሜን! መልእክቶቻችሁን በ @eotcmkidusan እንድታደርሱን በትሕትና እንጠይቃለን።
Mostrar todo...
#AbiyAhemedAli የETRSS1 ሳተላይት መምጠቅን በማስመልከት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አሊ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Mostrar todo...
የሰው ልጅ መባል ብርቅ የሆነበት አምላክ መደምደሚያውና አስደማሚው ፍጡር እግዚአብሔር በሰማይና በምድር የሚታየውንም የማይታየውንም ከፈጠረ በሇላ ፍጥረታትን ያስደመመና ዕፁብ ዕፁብ ያሰኘ ዲያብሎስን ያሳፈረና ያስደነገጠ አንድ እጅግ የሚያምር ፍጡር ፈጠረ ሰው በሚል የወል ስም የሚጠራ አዳም የሚባል። ሰውን በፍጥረት ጊዜም ሆነ ከፍጥረት በሇላ ብቸኛ የሚያሰኙ ብዙ ነገሮችን አድርጎለታል። የተወሰኑትን እነሆ። 1ኛ በኀልዮ፣ በነቢብና በገቢር የተፈጠረ ብቸኛ ፍጡር ነው። በእነዚህን በሦስቱ በአንድ ላይ የትኛውንም ፍጡር ሲፈጥር አናገኝም። ሰውን ሲፈጥር ግን አስቦ፣ "ሰውን በመልካችን እንፍጠር" ብሎ ተናግሮ ከዚያም በእጁ አበጃጅቶ ሲፈጥረው እናያለን። 2ኛ በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረ ብቸኛ ፍጡር ነው። "ሰውን በአርአያችንና በአምሳላችን እንፍጠር " እንዲል ዘፍ 1፣26። በዚህም ምክንያት ሰው የእግዚአብሔርን መልክ ስለያዘ ለሚያየው ሁሉ ሰላምንና እረፍትን የሚሰጥ ሆነ ለመላእክትም ጭምር። 3ኛ ገዥ ሁኖ የተፈጠረ ብቸኛ ፍጡር ነው። በዘፍ 1 ቁ26 "የባሕር ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን የሰማይ ወፎችን እንስሳትንና ምድርን ሁሉ በምድርም ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ ይግዛ " ብሎ በሰማይ ከሚበሩ ወፎች ጀምሮ በምድር ያሉትን ምንም ሳያስቀር ገዣቸው እንዲሆን አሰልጥኖ ፈጥሮታል። 4ኛ ልደቱ በፈጣሪው የተከበረለት ብቸኛ ፍጡር ነው። ከአዳም በስተቀር በተፈጠረ ማግስት ልደቱ የተከበረለት ፍጡር አናገኝም። ያች እግዚአብሔር ያረፈባት የተቀደሰች ዕለት ሰንበት ብቻ ሳትሆን ለአዳም ልደቱም ነበረች። እኛም በእውነት እናከብራታለን ልደቱን ማን ይረሳል። 5ኛ ስሙ ለእግዚአብሔርም መጠሪያ የሆነለት ብቸኛ ፍጡር ነው። ጌታችን መድኅነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ራሱን "የሰው ልጅ " እያለ ይጠራ ነበር። እንዲያውም በአንድ ወቅት አለቃ አያሌው ታምሩ " ጌታችን ለምንድነው ራሱን የሰው ልጅ እያለ የሚጠራ" ተብለው ሲጠየቁ አለቃም " እኔ ምን አውቃለሁ የሰው ልጅ መባል ብርቅ ሁኖበት ይሆናላ " ብለው መለሱ ይባላል። እንዴ? ሰው መሆን ይህን ያህል ብርቅ ነው እንዴ? ለዚህ ይሆን ቅዱስ ዳዊት ልጁን " ሰው ሁን " ይለው የነበር? 6ኛ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን ከመላእክትስ እንኳ በጥቂት አነሰ እስኪባል ድረስ እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሁኖ ራሱን ዝቅ አድርጎ ያገለገለው፣ እግሩን ያጠበው፣ የተገረፈለት፣ የተሰቀለለት፣ የሞተለት ብቸኛ ፍጡር ነው። 7ኛ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንዲበላ እንዲጠጣ የፈቀደለት ብቸኛ ፍጡር ነው። መላእክት ስንኳንስ ሊበሉትና ሊጠጡት እንዲነኩት እንኳን አልተፈቀደም። መላእክቱም የእኛን ሥጋ በዘባነ ኪሩብ ተቀምጦ ሲሰለስ ሲቀደስ እያዩ የሚያከብሩን ሁነዋል። ለዚህ እኮ ነው መልአኩ ቅዱስ ዮሐንስን አትስገድልኝ እስኪለው ድረስ ያከበረው። ያኔ አዳም ከገነት ሲባረር እኛ በመላእክቱ መገልገል ብቻ ሳይሆን የቀረብን እነርሱም እኛን እያገለገሉ የሚያገኙትን ፀጋ አስቀርተንባቸው ተቀይመውን ይኖሩ ነበር። አሁን ግን በተደረገልን ታላቅ ነገር እጅግ አድርገው የሚወዱንና የሚያገለግሉን ሁነዋል። " ታላቅ ሥራን ሠርቶልኛልና " እንዳለች እመቤታችን /ሉቃ 1ቁ 49/። 8ኛ ሲፈጥረውም ሲያድነውም መልኩን ያጸናለት ብቸኛ ፍጡር ነው። መጀመሪያ በመልኩ ፈጠረን። ይህን መልኩን አጥፍተን ስንጠፋበትና ስንርቀው በሇለኛው ዘመን መልካችንን ይዞ ባሕሪያችንን ተዋህዶ ቀረበንና ወደርሱ ከፍ ከፍ አደረገን። መልካችንን አደሰልን። "ቀዳሚሰ ወሀበነ አርአያሁ ክብርተ ወደኃሪሰ ነስአ ሥጋነ ኅስርተ" / በመጀመሪያ የከበረች መልኩን ሰጠን በሇላ ግን የእኛን ጉስቁል ሥጋ ገንዘቡ አደረገ/ ተብሎ በሃይማኖተ አበው የተጻፈውን ስናይ እንድንገረምና እንድንደመም እንገደዳለን። ሰው ግን ይህን ሁሉ ክብር ተሸክሞ እየከበደው ነው መሰል ሁሌም ሲወድቅ ይኖራል። እንግዲህ ምን እንላለን ከበሮውን ይዘን ሥጋችንንና ነፍሳችንን ሰብስበን በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እየበላን እየጠጣን " እናመስግነው እናመስግነው /2/ አምላካችን ውለታው ብዙ ነው "/4/ እያልን ከመዘመር ወጭ። ታኅሣሥ 2008 ዓ.ም የሺዋስ መኳንንት ድሬ ዳዋ
Mostrar todo...
+ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ + ‘’ መጽሐፍ ቅዱስ የተለወጡ ሰዎች ታሪክ መጽሐፍ ነው፡፡ አታላዩ ያዕቆብ እስራኤል ተብሎ አባት ሆነ ፣ ነፍስ የገደለው ሙሴ ትሑትና ነጻ አውጪ ሆነ ፣ ስምኦን ጴጥሮስ ሆነ ፣ ሳውልም ጳውሎስ ሆነ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የተለወጡ ሰዎች የታሪክ መጽሐፍ ነው’’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‘የኖኅ መርከብ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ሆኖም ቤተ ክርስቲያን ከኖኅ መርከብ እጅግ ትለያለች፡፡ ወደ መርከቡ የገባ ዶሮ ሲወጣም ዶሮ ነው፡፡ ተኩላውም ከመርከቡ ሲወጣ ተኩላ ነው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ኝ ዶሮ ገብቶ ርግብ ሆኖ ይወጣል፡፡ ተኩላውም በግ ሆኖ ይወጣል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ኃጢአተኞችን ተቀብላ ጻድቃን አድርጋ የምታወጣ መርከብ ናት’’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‘’አልጋ መግዛት ለምትፈልጉ ኑ አልጋ ላሳያችሁ! ይህ አልጋ የተራ ሰው ወይም የወታደር አልጋ አይደለም፡፡ የንጉሥ አልጋ ነው፡፡ ንጉሥም ቢባል ተራ ንጉሥ ሳይሆን በዓለም ሁሉ የሚዘመርለት ታላቅ ንጉሥ አልጋ ነው፡፡ የንጉሥ ዳዊትን አልጋ ላሳያችሁ፡፡ ይህ አልጋ ከወርቅ ወይም ከአልማዝ ወይም ከከበሩ ድንጋዮች የተሠራ አይደለም፡፡ ይህ አልጋ ከዕንባ የተሠራ አልጋ ነው፡፡ እርሱ ‘ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ ፤ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ’ ብሏልና’’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‘’ኃጢአት ከጣለችው ይልቅ ውዳሴ ከንቱ የጣለችው ሰው ይበዛል’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‘‘ደሃው ወደ አንተ ሊለምን ሲመጣ ‘ራቁቱን ሆኖ የሚለምነው ሲያስመስል ነው‘ ትላለህ፡፡ እርሱን አታላይ ያደረገው ግን የአንተ ጭካኔ ነው፡፡ ርኅሩኅ ብትሆንለት ኖሮ አንተን ለማራራት ሲል እንዲህ ባልደከመ ነበር፡፡ እሱ እኮ በየቀኑ እየመጣ ይለምነኛል ብለህ አትበሳጭ በየቀኑ የሚለምንህ እርሱም እንደ አንተ በየቀኑ ስለሚበላ ነው’’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‘’ንግግርህ ምንም ያህል እውነተኛ ቢሆን በቁጣ ከተናገርክ ሁሉንም ነገር ታጠፋዋለህ’ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከየስብከቶቹ የተሰበሰቡ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ታኅሣሥ 9 2012 ዓ ም አዲስ አበባ
Mostrar todo...
የረቡዕ ትርጓሜ መጻሕፍት ሰሞኑን ክብረ ደናግል ናዳ ላሊበላ ገዳም ሊያሳትመው ያዘጋጀውን መጽሐፍ የማየት ዕድል ነበር። እንዲህ የሚል ታሪክ አነበብኩ። በሴት አያቴ ቤት በዕለተ ረቡዕ መጻሕፍት የመተርጎም ትውፊት ነበር ። መጻሕፍት ይተረጎምባት የነበረችው እልፍኝ ሣር የተጎዘጎዘባት፣ ዙሪያዋን የበግ አጎዛ የተነጠፈባት ነበረች። የቤተሰባችን ንስሓ አባት ትርጓሜ መጻሕፍት የተማሩ ስለነበሩ ረቡዕ በጧት ከአያቴ ቤት መጥተው ሲተረጉሙ፣ እኛም ስናዳምጥ እንውላለን። ዘመዶቻችን ከእልፍኟ ገብተው ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ። በዕለቱ የከበደ ችግር ካልገጠመው በስተቀር የሚቀር ሰው የለም። ቄሱ ጸሎት አድርገው መጻሕፍትን መተርጎም ሲጀምሩ የቻለ ቆሞ፣ የተሳነው ተቀምጦ ያዳምጣል። ምን ልጅ ብሆን ትልልቆቹ እኔንም ይዘውኝ ይሔዳሉ። ትርጓሜ ከተጀመረ በኋላ ድምፅ የሚያሰማ ባይኖርም እኔ ስጫወት የሚቆጣኝ አልነበረም። የሚሰማው የመምህሩ ድምፅ ብቻ ነው። በቤታችን ይካሔድ የነበረው ትርጓሜ መጻሕፍት ከመቼ እንደ ጀመረ አላውቅም። እኔ ከአካባቢው እስክለቅ ድረስ አልተቋረጠም ነበር። አያቴ ከሞተችም በኋላ በእኛ ቤት መተርጎሙ ቀጥሎ ነበር። አሁን ድረስ የሚገርመኝ አባቶቻችን እና አያቶቻችን ትርጎሙን የማይሰሙትን የግእዝ ንባብ በተግባር ለመግለጥ የታደሉ፣ እኛ ደግሞ የሰማነውን በተግባር ለመግለጥ የማንችል መሆናችን ነው። በዕለተ ረቡዕ የሚከናውነው መንፈሳዊ ተግባር አሁን ድረስ ቅደም ተከተሉን እንደጠበቀ ይታወሰኛል። ያን ጊዜ ልጅ ብሆንም በአእምሮዬ እንደታተመ ቀርቷል። አሁን ድረስ ከሚያስገርመኝ ጉዳይ አንዱ የአባቶቻችን ጥንቃቄ ነው። ለመንፈሳዊ ነገር ያላቸው ክብር በቃላት ተሳክቶ በመነገር አይጠቀለልም። በቤታችን መጻሕፍት በሚተረጎሙበት አንድ ዕለት እንዲህ ሆነ። ቀትር ሊሆን ትንሽ ሲቀረው ከእኛ ቤት ራቅ ብሎ ከጎረቤታችን ድብልቅልቅ ያለ ጩኸት ተሰማ። ጩኸቱ በጣም እየበረታ በመሔዱም አንድ ሰው ወጥቶ እንዲያጣራ ተደረገ። ከእልፍኟ የወጣው ሰው በፍጥነት ወዳለንበት ተመልሶ ቤት እየተቃጠለ መሆኑን ስለተናገረ ሁሉም በድንጋጤ እሳቱ ወደ ተነሣበት ሮጠ። ቄሱም ትርጓሜያቸውን አቋርጠው እሳት ወደ ተነሣበት ቤት ሔዱ። በዕለቱ የተገኘው ሰው በብዙ ድካም እሳቱ የከፋ ጥፋት ሳያስከትል አጠፋው። እሳቱ በቶሎ በመጥፋቱ ሰዎቹ እግዚአብሔር ንብረታችንን አተረፈልን ብለው ደስ ብሏቸው እሳት ሊያጠፋ የሔደውን ሰው ሁሉ ቤት ካልገባችሁ ብለው ያዙት። እሳቱ እስከሚጠፋ ዘጠኝ ሰዓት ሆኖ ስለነበር ሁሉም ገብቶ መመገብ ጀመረ። እኔም ከታላላቆቹ ጋር አብሬ በላሁ። ቄሱም የጎረቤቶቻችንን ንብረት ስላተረፈላቸው እግዚአብሔርን አመስግነው፣ ጸሎት አድርገው ሁላችንም ከሰዎቹ ቤት ወጥተን ወደ ቤታችን መጣን። ከቤታችን ስንደርስ ጸሎት የሚደረግባት እልፍኝ እንደተከፈተች አገኘናት። እኔ ባይገባኝም ቄሱም፣ ዘመዶቼም በጣም ደነገጡ። ወደ ውስጥ ሲገቡ ሲተረጎም የነበረው መጽሐፍ አትሮንስ ላይ እንደተዘረጋ ነበር። በዚህ ጊዜ ደግሞ ድንጋጤያቸው ጨመረ። መጽሐፉ እንደተዘረጋ ማደሩ አሳሰባቸው። እንዳያጥፉት እህል ቀምሰዋል። ሲያሰስቡ ቆይተው እኔን ጠሩኝ። የጠሩኝ መጽሐፉን እንዳጥፈው ነበር። አንድ ሰው መሸከም የማይችለውን የብራና መጽሐፍ እንኳን እኔ እሳቸውም በመከራ እንደሚያጥፉት እና እንደሚዘጉት ቢያውቁም ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም። እኔ ወደ አትሮንሱ ብጠጋም መጽሐፉን አልደርሰውም። አንድ ነገር ላይ አቆሙኝ እና እኔ መጽሐፉን እንድይዝ አዘዙኝ። እኔ መጽሐፉን ስይዝ እሳቸው ደግሞ የእኔን እጅ ይዘው በእኔ እጅ ተጠቅመው የብራናውን መጽሕፍ አጠፉት። እኔ የተደሰትኩት ቄሱ የሚተረጉሙትን መጽሐፍ በመንካቴ ነበር። እሳቸው የተደሰቱት መጽሐፉን በእጃቸው ሳይነኩት በመታጠፉ ነው። እንዴት በፍርሃት ይንቀጠቀጡ እንደነበር እና አፋቸው ከጸሎት እንዳልተለየ ዛሬም ይታወሰኛል። የአባቶቻችን ጥንቃቄ ይመስለኛል እግዚአብሔርን ሲጠይቁት በቶሎ መልስ እንዲያገኙ ሲያደርጋቸው የኖረው። የዛሬዎችን ክርስቲያኖች መደፋፈር አለማንሣት ይሻላል። እንኳን የአባቶቻችንን ያህል ልንጠነቀቅ እና ለቃለ እግዚአብሔር ክብር ልንሰጥ ጠንቃቃዎችንም የምንተች ከንቱዎች ነን። እግዚአብሔርን ጠይቀነው መልስ ማግኘት የማንችለው በዚህ ምክንያት ይመስለኛል። እኛ የምንጠይቀው የማናከብረውን፣ ቢደረግልንም ወዲያው የምንረሳውን ነው። አባቶቻችን ተጠንቅቀው ይጠይቁታል፤ እንዴት መልስ እንደሚሰጣቸው በአንክሮ ተመልክተው መልሱን ያገኙታል። እኛ እኮ የምንጠይቀውን የማናውቅ ብቻ ሳንሆን የጠየቅነው ሲመለስልን እንኳ ልብ ብለን የማንረዳ ነን። ለዚህም ነው ሁል ጊዜ መጠየቅ እንጂ ማስተዋል የማናውቀው… እያለ ይቀጥላል። ለቃለ እግዚአብሔር ክብር ሰጥተን እንድንጠቀም አምላካችን ይርዳን። አሜን!! መልእክቶቻችሁን በ @eotcmkidusan እንድታደርሱን በትሕትና እንጠይቃለን።
Mostrar todo...
ች፤ ከመብረቅ አደጋና ከድንገተኛ ሞት በቃል ኪዳኗ እንደምትጠብቅ ሲታመን፤ በጣሊያን የባሕር ኀይላችን ጠባቂ (the patron of the Italian Navy.) ይሏታል። ♥❖♥ በቃል ኪዷና በእጅጉ ከመታመን የተነሣ በጊዜያችን ያሉ በርካቶች ኀያላን ሀገራት ብሪታኒያ (Royal Artillery, RAF Armoures, Royal Engineers) በካናዳ (Explosiv Ordance Technicaians) በአውስራሊያ (RNZAF Armourers) በኒውዝላንድ፤ በስፔን፣ በአሜሪካ፣ በግሪክ የቅድስት በርባራን በዓል በዐየር ኀይላቸው፣ በጦር ካምፓቸው፣ በባሕር ኀይላቸው እንደሚያስቡ ጥናቶች በግልጽ ያሳያሉ:: ♥❖♥ ‘Saint Barbara’s Day, December 4, is celebrated by the፦ ✍ British (Royal Artillery, RAF Armourers, Royal Engineers), ✍ Australian (Royal Regiment of Australian Artillery, RAAF Armourers), ✍Canadian (Explosive Ordnance Disposal Technicians (EOD), Canadian Air Force Armourers, Royal Canadian Artillery, Canadian Military Field Engineers, Royal Canadian Navy Weapons Engineering Technicians), ✍New Zealand (RNZAF Armourers, RNZA, RNZN Gunners Branch) armed forces. ✍ Additionally, it is celebrated by Irish Defence Forces Artillery Regiments, ✍Norwegian Armed Forces Artillery Battalion, ✍ United States Army and Marine Corps Field and Air Defense Artillery, many Marine Corps Explosive Ordnance Disposal Technicians, and other artillery formations.’ (https://www.catholic.org/saints/saint.php?saint_id=166) ♥❖♥ ከሎስ አንጀለስ ሰሜን ምዕራብ 100 ማይልስ በሚገመት አግጣጫ ያለችው በስሟ ሳንታ ባርባራ ካሊፎርንያ በሚል ተሠይሞላታል፤ በተመሳሳይ መልኩ በስፔንና ፖርቱጋል ቦታ ላይ በብራዚል፣ በቺሊ፣ በኮሎምቢያ፣ በሆንዱራስ፣ በሜክሲኮ፣ በቬንዝዌላ፣ በፊሊፒንስ በቅድስት በርባራ ስም የተሠየመ አለ (Hammond Atlas of the World.1997.)፡፡ ♥❖♥ በአሜሪካ ዐየር ኀይልም የቅድስት በርባራ ሥዕል ያለበት ኒሻን ይሰጣል (United States Field Artillery Association, fieldartillery.org. retrieved 23 January 2010,) (Cyprus Army notes on Saint Barbara, Army) ♥❖♥ ታላቁ ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ ሊቁ አርከ ሥሉስ ያወደሷት የኾነች በርካቶች ቃል ኪዳናትን የተቀበለች ቃል ኪዳኗም ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው የቅድስት በርባራ በረከት ይደርብን፨ telegram channel https://t.me/joinchat/AAAAAFTyR7tztt08pN9U-w ✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
Mostrar todo...
St. Barbara - Saints & Angels - Catholic Online

Saint Barbara, also known as the Great Martyr Barbara, was an early Christian Greek martyr born mid-third century in Heliopolis, Phoenicia. Barbara was the daughter to a rich pagan named Dioscorus. After the death of Barbara's mother, Dioscorus dedicated his life to his only daughter. Barbara ...

[ታኅሣሥ 8 በዓሏ የሚከበረው ቃል ኪዳኗ ከድንገተኛ ሞት የሚጠብቀው የቅድስት በርባራ ድንቅ ታሪኳ፤ በኢትዮጵያውያን የቀረበላት ውዳሴ፤ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ያላት ክብር] ✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ♥❖♥ ቃል ኪዳኗ ከድንገተኛ ሞት እንደሚጠብቅ የተነገረላች ቅድስት ሰማዕት በእኛ በርባራ፤ በግሪክ Αγία Βαρβάρα, በቅብጥ Ϯⲁⲅⲓⲁ Ⲃⲁⲣⲃⲁⲣⲁ), በእንግሊዝኛ St Barbara ትባላለች። ♥❖♥ ቅድስት በርባራ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከሓዲው መክስምያኖስ ዘመነ መንግሥት መስፍን የነበረው የዲዮስቆሮስ ልጅ ናት፤ ለርሷም ማረፊያ ታላቅ ሕንፃ አሠርቶ በመታጠቢያ ክፍሏ ላይ ደግሞ ኹለት መስኮቶች እንዲሠሩላት ዐናጺዎችን አዘዘ፤ ርሷ ግን የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በማመኗና በመጠመቋ ሦስተኛ መስኮትን እንዲጨምሩ ዳግመኛም አዳኝ የኾውን የመስቀሉን ምልክት በውሃ መታጠቢያው ላይ እንዲሠሩ ሐናጺዎችን አዘዘቻቸው፡፡ ♥❖♥ አባቷም ወደዚኽ ሕንጻ በገባ ጊዜ ልጁ ያሠራችውን አይቶ ዐናጺዎችን ሲጠይቃቸው፤ ይኽነን እንዲሠሩ ያዘዘቻቸው ልጁ መኾኗን ነገሩትን ርሱም “ለምን እንደዚኽ አደረግሽ” ብሎ ጠየቃት፡፡ “ወትቤሎ አእምር ወለቡ ኦ አቡየ እስመ በሥሉስ ቅዱስ ይትፌጸም ኲሉ ግብር በእንተዝ አግበርኩ ሣልሲተ መስኮተ፤ ወዘንተኒ መስቀለ በአምሳለ ስቅለቱ ለመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ” ይላል ♥❖♥ ርሷም “አባቴ ሆይ አስተውል፤ ልዩ ሦስት በኾነ በሥላሴ ስም ሥራ ኹሉ ይፈጸማልና ስለዚኽ ሦስተኛ መስኮት አሠራኊ፤ ይኽም መስቀል ዓለሙ ኹሉ በርሱ በዳነበት በመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል አምሳል ነው አንተም አባቴ ሆይ ከስሕተትኽ ተመልሰኽ የፈጠረኽን አምላክ አምልከው” በማለት ተናገረችው፡፡ ♥❖♥ አባቷም ከርሷ ይኽነን በሰማ ጊዜ በንዴት ሰይፉን መዝዞ በኋላዋ ሮጠ፤ ያን ጊዜ ሸሽታ በዐለት ውስጥ ገብታ ለጊዜው ብትሸሸግም በኋላ ግን ወደ አባቷ ተመለሰች፤ ርሱም እንድትሠቃይ ለሌላ መኰንን አሳልፎ ሰጣት፤ ርሱም እየገረፈ በጊዜው አሉ በተባሉ በታላላቅ ሥቃይን ቢያሠቃያትም የባሕርይ አምላክ ክርስቶስን ግን አልካደችም፤ ከዚያም ብቻዋን ወደ ወህኒ ተጣለች፤ በዚያም ኾና “ጌታዬ አምላኬ ሆይ አትተወኝ” ብላ ጸለየች፤ በእኩለ ሌሊትም የእስር ቤቱን ደማቅ ብርሃን መላው፤ “ከአንቺ ጋር ነኝና አትፍሪ” የሚለውን የአምላክን ድምፅ ሰማች፤ ከዚያም ጌታችን ቊስሎቿን ኹሉ ፈወሰላት፡፡ ♥❖♥ በነጋታው ቅድስት በርባራን በማርቲያኑስ ፊት አቆሟት፤ ኹሉም ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንደዳነችና ፊቷም እንደ ፀሓይ ጨረር ሲያንጸባርቅ ተመለከቱ፤ መኰንኑም “አማልክቶቻችን ስለፈወሱሽ የምስጋና መሥዋዕትን ሠዊ” አላት፤ ቅድስት በርባራም ለአገረ ገዢው “በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው የዳንኩት” አለችው፡፡ ማርቲያኑስም በቊጣ ኾኖ በአስከፊ ኹኔታ ቅድስት በርባራ እንድትሠቃይ አዘዘ፤ በዙሩያዋ ቆመው ይመለከቱ የነበሩ ሕዝቦች ርሷን ለመከላከል ምንም ቃል አልወጣቸውም፡፡ ♥❖♥ በዚያም ዮልያና የምትባል ሴት ነበረችና ቅድስት በርባራን አይታ የምታጽናናትና የምታረጋጋት ኾነች፤ ክብር ይግባውና ጌታችን ለቅድስት በርባራ ተገልጾ አረጋጋት ቃል ኪዳንም ሰጣት፡፡ በመጨረሻም ጨካኙ መኰንን ምንም ዐይነት ሥቃይ ቢደርስባቸው እነዚኽ ቅዱሳት አንስት በክርስቶስ ላይ ያላቸውን እምነት እንደማይለውጡ ባየ ጊዜ አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘ። ♥❖♥ ከወታደሮቹ መኻከል አንዱ አንገታቸው ለመቊረጥ ሰይፉን መዘዘ፤ በአባቷ ወደተዘጋጀው ወደመግደያው ስፍራ ይዟቸው ኼደ፤ ያን ጊዜ ቅድስት በርባራ እንዲኽ ብላ ጸለየች “ዘላለማዊ እግዚአብሔር ሆይ ከእኔ ሞት በኋላ እኔንና መከራዬን ለሚያስቡ ኹሉ ሥጦታኽን ስጣቸው፤ ድንገተኛ ሕመምና ብርቱ (አስጨናቂ) ሞትን በእነርሱ ላይ ፈጽሞ አታምጣባቸው” አለች፡፡ ♥❖♥ ከዚያም የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ መሻቷን ኹሉ እንደሚፈጽምላት ቃል ኪዳን ሲገባላት በሰጣት ቃል ኪዳን የሚታመኑ ኹሉ ድንገተኛ ሞት እንደማያገኛቸው ቃል ኪዳን ገባላት። ♥❖♥ በመጨረሻም አባቷ የርሷንና የባልንጀራዋ የዮልያና አንገታቸው እንዲቈረጥ አዘዘና ታኅሣሥ 8 አንገታቸው ተቈርጦ የሰማዕትነት አክሊል ሲቀዳጁ፤ ቅድስት ዮልያናንም በኹለት ጡቶቿ በኩላብ ሰቅለው ሰይፈዋታል፡፡ በዚያን ጊዜ ከሰማይ መብረቅ ወርዶ አባቷንና ጓደኛው የኾነ መኰንን መርትያኖስን አቃጠላቸው፤ ከዚኽ የተነሣ በዓለም ባለው ሥዕሏ ላይ የመብረቅ ብልጭታ ይሣላል፡፡ ♥❖♥ ያም በመታጠቢያ ቤት ውስጥ በመስቀል ምልክት ያሠራቸው መታጠቢያ ለታመመ ኹሉ ከርሱ በታጠበ ጊዜ የሚያድን ኾነ፤ ከዚኽም በኋላ የሰማዕታቱን ሥጋቸውን ወስደው ከከተማ ውጪ ባለች ቤተ ክርስቲያን ስሟ ገላልያ በሚባል ቦታ አኖሯቸው፤ ይኽ ሥጋቸውም በቅዱሳን ሰማዕታት በአቡቂርና በዮሐንስ በምስር አገር ባለ ቤተ ክርስቲያን ተቀመጠ፡፡ ♥❖♥ ይኽነን ተጋድሎዋን ለማዘከር በመላው ዓለም በሚሣለው ሥዕሏ ላይ ሦስት መስኮት ያለው ሰገነት፣ ዘንባባ፣ ጽዋ፣ መብረቅ፣ የሰማዕትነት አክሊል ይዛ ይታያል፡፡ በዓለም ላይ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ የታነጹላት ሲኾን በሩሲያ ብዙዎች ቤተ ክርስቲያናት በስሟ ሲሠየሙላት አንደኛው በሞስኮ ከቅዱስ ባስልዮስ ካቴድራል አጠገብ ይገኛል:: ♥❖♥ ቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ቅድስት በርባራን አመስግነው በቃኝ አይሉም ነበር፤ ለምሳሌ ያኽል ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እና ቅዱስ አርከ ሥሉስ እንዴት እንዳመሰገኗት ብናይ፤ አባ ጊዮርጊስ በተአምኆ ቅዱሳን መጽሐፉ ላይ፡- “ሰላም ለበርባራ ወዮልያና በፍኖተ ስምዕ እለ ቆማ፤ በድሮን እለ ፈጸማ እለ ተጋደላ ከመ ሐራ አርዑተ መስቀሉ ለክርስቶስ እለ ጾራ መርዓዊሆን እስከ ረከባ ድንግልናሆን እለ ዓቀባ”፡፡ (ሙሽራቸው ክርስቶስን እስኪያገኙ ድረስ ድንግልናቸውን የጠበቁ፤ የክርስቶስ መከራ መስቀሉን የተሸከሙ፤ እንደ ጭፍሮች የተጋደሉ፤ ሩጫቸውንም የፈጸሙ፤ በምስክርነት ጐዳና የቆሙ ለኾኑ ለበርባራና ለዮልያና ሰላምታ ይገባል) በማለት አወድሷቸዋል፡፡ ♥ኢትዮጵያዊው ሊቅ አርከ ሥሉስም ይኽነን በዐርኬው ላይ፡- “ሰላም ለበርባራ እንተ አግሀደት ሃይማኖታ እንዘ ታርኢ ሥላሴ በመስኮተ ቤታ ኢያፍርሃ መጥባሕት ወሞሠርተ ሐጺን ኢያሕመመታ ወሰላም ካዕበ ለዮልያና ካልዕታ እንተ ሰቀልዋ በክልኤ አጥባታ” (በቤቷ መስኮት የሥላሴን ምሳሌ እያሳየች ሃይማኖቷን የገለጠች ለኾነች ለበርባራ ሰላምታ ይገባል፤ ሰይፍም አላስፈራትም የብረት መጋዝም አላሳመመቻትም፤ ዳግመኛም በኹለት ጡቶቿ የሰቀሏት የርሷ ኹለተኛ ለምትኾን ለዮልያናም ሰላምታ ይገባል) በማለት የተቀበሉትን ጽኑ መከራ ጽፏል፡፡ ♥❖♥ ጳውሎስ የበርያሱስን ዐይን እንዳጨለመ ቅድስት በርበራም እመቤታችንን ለምና የገድሏን መጽሐፍ በሰረቁት ላይ ያደረገችውን የመስከረም 25 ተአምሯን ደግሞ ሊቁ አርከ ሥሉስ፦ "ሰላም ለበርባራ ወለዮልያና አምሳላ በዛቲ ዕለት ዘአስተርአየት ኀይላ በክልኤ ዕደው ዘሰረቁ መጽሐፈ ገድላ ፈደየቶ ለአሐዱ እንባዜ እምኀበ ማርያም ስኢላ ወለዐይነ ቢጹ ካልዕ አጽለመት ጸዳላ" (የገድሏን መጽሐፍ በሠረቁ በሁለት ወንዶች ላይ በዚች ዕለት ኃይሏን በገለጠች ለበርባራና እርሷን ለምትመስላት ለዮልያና ሰላምታ ይገባል። ወደ እመቤታችን ማርያም ለምና አንዱን መቅበዝበዝን፤ ሌላኛው ባልንጀራውን ዳግመኛ ብርሃኑን አጨለመች) ይለዋል በመስከረም 25 ስንክሳር አርኬው ላይ፨ ♥❖♥ በእጅጉ የሚገርመው ከጥንት ዠምሮ በየክፍላተ ዘመናቱ እስከ ዛሬ ድረስ በበርካታ የዓለም ክፍሎች በቅድስት በርባራ ከሚፈነዱ የጦር መሣሪያዎ
Mostrar todo...