cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Maddbn እጅጉ ቃሲም ! ✍️

@maddbn & @Poemrs_bot

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
455Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

#አበባ_አየሁ ©ሲራክ ወንድሙ እሩቅ ለሩቅ ሆነን ይጠባል መስከረም ፥ ይታጠናል ህዳር ፀደይ እየዳኸ ክረምት ይጋልባል ፥ ተስፋዬን ሳሳምር አምና በዚህ ሰዓት ፥ ጠበቅኩሽ በውርጩ እስኪያልፍብኝ ሀሩር ፥ ወፎች እስኪንጫጩ ጠበቅኩሽ ፥ ጠበቅኩሽ የሌት ውብ እንቅልፌን ፥ በናፍቆት መጅ ድጬ በመምጣትሽ እርሾ ፥ ልቤን አሳብጬ። የአንቺ ሀገር ወዴት ነው የአድማስሽ አቀበት ? እግሬን ላወላዳ ፥ ይቆምልኝ እንደው የልቤ ትኩሳት ተይ ንገሪኝ ባክሽ ፥ ወዴት ነው ባዕቱ ካቻምና ላይ ቆሜ ፥ መነነ ዘመኑ ከነፈ ጊዜያቱ የተራራው ደረት በአደይ ፂም ጎልምሶ የሀምሌ ጨለማ ባባረረው ብርሃን ፥ ሲሄድ ተለሳልሶ እንደው ለአዲስ ዓመት ፥ ትጋቴን አስታውሰሽ ናፍቆት ፣ ተስፋ ፣ ፍቅርን - አንድ ላይ ታቅፈሽ በሬን ከፍተሽ ግቢ ፥ አበባ - አየሁ ብለሽ .... ©ሲራክ @siraaq https://t.me/maddbn23ethio
Mostrar todo...
Maddbn እጅጉ ቃሲም ! ✍️

@maddbn & @Poemrs_bot

#ትንሣዔ አልባ ሞት አልገባሽም እየሞትኩ እንደሆነ ስተነፍስ፣ ሣወራ፣ ፈገግ ስል፣ .... ከነፍሴ የሚንጠባጠበው ደም አይታይሽም ስጋዬ እየፈራሰ ወደ ውስጥ ሲወድቅ አጥንቴ ቀስ በቀስ ሲበታተን አይታይሽም። እንዴት ይታይሻል ቢታይሽ ነው የሚገርመኝ! ፩ የረገጥኳት ጠጠር በተረከዜ ስትሸሽገኝ ከእኔ ልቃ... ... ፪ ከለኮስኳት ሻማ በመቅረዜ ቀድሜያት ቀልጬ ስጠልቅ እንደ ጨረቃ! እኔስ እንዴት አሳይሻለሁ ፥ ብሞክርስ እንደ ምን ችላሁ ? አብረን ሁነን አብረን ሳለን ሁለት ሁነን ለየብቻ ፤ መሆኔ! እንዴት ይታይሻል ? ከረገጥኳት ጠጠር ስርቻ ! ኢምንት ሆኜ ትቢያ መታቀፌ ፤ ተራምደሽ ከምታልፊያቸው አሸዋዎች መሀል መሠለፌ ፤ እኔም እንዳንቺ እኔኑ እየረገጥኩ አብሬሽ ማለፌ ..... እንዴት ይገባሻል ? አፌስ እንዴት ይነግርሻል ምላሴ ትታው በርራ ፤ ወደ ሌለሽበት ሽሽታ ወደ ሩ..ሩቅ በረሀ ....... ~ ግን እኮ እዛ ነሽ ፥ ዛሬም ስሞት ፣ ነገም ስሞት፤ እዚህ ጎኔ ሁነሽ .... ካልታየሽ ! ~~~ ለነፍስ ምትሆን አንዲት ቅንጣት አስራት የለኝ ወይ በኩራት ፤ ክንፌ ረግፎ በደረቴ እርክጎተት፥ ስከተልሽ እንደ ቢራቢሮ ስንከራተት ወዳ'ንቺ ስባዝን ስቃትት ስዋትት.... በዝብዘሺኝ አቅሙም የለኝ.... ፵ ጅራፍ ፈርደውብኝ ፥ አንዱ እንኳ ቢያርፍብኝ.... ከስርሽ የምፈርስ የዘላለም ሟች ነኝ! ✍🏽maddbn
Mostrar todo...
#⃣ መስተ ውበት❕ ✍maddbn እጅጉ ቀጭን ለግላጋ ..... ..እርጥብ ቄጤማ። ቅጥነቷ ደስ የሚል ቁመቷም የሰጠ....ደም ግባታም የሆነች ቆንጆ ናት። ሞቫይሉ ላይ የሞላው የእሷ ምስልና ቪዲዮ ነው። አሁንም አሁንም እየመራረጠ ያሳየኛል በፍለጋው መሀል ያዳንቃል በተኛበት ሆኖ እያፏጨ ምስሏን 'ቀረብ ረብ' አርጎ ያየውና፤ በእግሩ አየር ላይ እንደመሮጥ አይነት በፍጥነት አወራጭቶ ከብለል ይላል። እንሳሳቃለን በሁኔታው። "እየው በናትህ!" ብሎ ፊቴ ላይ ደቀነው የከፈተውን ቪዲዮ። ከአገጬ ወደ ደረቴ ጠጋ አድርጌ ማየት ጀመርኩ... ታምራለች ስትደንስ የቡጊ ውጊ ሴት አማልክት ትመስላለች። አንገቷ ላይ በሀብል ያንጠለጠለችው ከዚህ በፊት አይቸው የማላውቀው ጠልሰም ቢጤ አብሯት እየተወዛወዘ ዳንሷን ያዳምቃል። የሆነ ነገር እንድጠረጥር ፮ተኛው ስሜቴ ሹክ ብሎኝ አለፈ....። እየዘፈነች ሌላ ቪዲዮ አሳየኝ፤ ያምራል ድምጿ ለጉድ!! ጉሮሮዋ ንፁህ ነው ድምጿ ከምንም ሳይላተም ምንም ሳይንገጫገጭ እንደ እንባ ኩልልል ብሎ ይወርዳል። ያለ ማጋነን በዚህ መረዋ ክርስትናን ብትሰብከው ዲያቢሎስ ጌታን ይቀበላል። እቺ ገነት ገብታ ሁሉ እንጆሪ ለመልቀም ቅርጫቷን ይዛ በዱር በጫካው በአትክልት ቦታው እየዞረች ብትዘምር አንበሳው " ነይ እኔን ጋልቢኝ !" ንስሩ "ተይው እሱን ጎፈሬው ቀምሎዋል ነይ እኔ ይዤሽ ልብረር ...?" እያሏት ሲፎካከሩ ቆማ እያየች ሳታስበው ቅርጫቷ በየፍራፍሬው ተሞልቶ፤ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል "እነሆኝ እመቤቴ ሆይ እኛ ለቅመንልሻል" ብሎ ዘወር ሲል፤ አሻግራ ስታይ ሁሉም መላዕክት ከአንገቱ ሰበር ብሎ እጅ ይነሳል። " ያ አንተ ያለህ ገብሬል ሰይፋን የት ጣለው ባክህ?" ነብሮች ያንሾካሽካሉ..........። ለምን የ፩ሚሊዮን ሴት ውበት ባከነባት፤ ወይስ አካብደናት ነው? ራሴን ጠየኩኝ። እንከን ስፈልግባት ፊቷ ማንኪያ ቢጤ ነው በደንብ ያልተለመጠ አፍንጫዋ አከባቢ ከላይኛው ከንፈሯ እስከ ስረኛው አይኗ ሩብ ጉዳይ ሰመጥ ይላል ፊቷ ሰመጥ እንኳን ይበዛል ትን...ሽ ትንሽ በጣም ገባ ብሎዋል ቢሆንም ልንቀበለው አንፈልግም ያን እንከን። ለምን ? ለምን ጉድለቷ ላይ ደበዘዘብን አይናችን? <አስማት ይሆን እንዴ?> "ይሄ ምንድነው?" አልኩት አንገቷ ላይ ያለውን ነገር። "የቱ?" አለ ቆጣ ብሎ አቃቂር ሳወጣ እንደቆየሁ ገብቶታል። "ይሄ ነዋ አንገቷ ላይ ያለው መስተ ውበት ነው?" እንዳይናደድ ሳቅ ብዬ። "መስተ ውበት ደግሞ ምንድነው?" "እንደ መስተ ፋቅር ነዋ" "መስተ ውበት ሚባል ነገር የለም ባክህ ምንድን ምትዘባርቀው" "ነው እንጂ ለሁሉም በጣም ቆንጆ ሆና እንድትታይ የሚያደርግ" "ኦ ሰውዬ አትበድብኝ እዛው ሂደህ ተፈላሰፍ መስተ ውበት ይላል እንዴ ግም" "ካ ካ ካ" አልቻልኩም ሳቅሁ። "ምንድን የሚያናድድህ ደሞ ልትደበድበኝ ነው እንዴ?" እጁን አወራጨና "ኤጭ ወደዛ በል ባክህ" አለ። " ጥናዣም ስትፈልግ በሻይ ብላት " አልኩ የምር ተናድጄ። መጨቃጨቁ ስለማያዛልቀን ትቼው ማሰላሰል ጀመርኩ <እውነት ቆይ እንደ መስተ ፋቅር መስተ ውበት ቢኖርስ?> <ያ ለመወደድ ወይም መወደጃ ነው ይሄ ደግሞ ውብ ሆኖ መታያ በመልክ ብቻ መማረኪያ ከፍቅር ውጪ .... ግን ይቀራረባሉ መስተ ውበት የአይን ፍቅር ጋ ግንኙነት አለው ኮ....> <በቃ አንድም ሁለትም ናቸው ።> እንዲህ እያልኩ ከራሴ ጋር ብዙ ዘባረቅኩ፤ እውነት ግን መስተ ውበት ሚባል የለም እንዴ ? ካለ አለ ከሌለም እንደ ደብተራ መድገም ባልችልም እነሆ የአዲስ ድግምት ሀሳብ ባለቤት ነኝ። \\ ✍maddbn ፳፩ ታህሳስ ፪፻፲፫
Mostrar todo...
🤝
👍
👎
👤 የባተሌው ዜና መዋዕል ! ረመጥ አቅፌ የምሰቃይ ስጉም፤ ላላመልጠው ምሸሽ የራሴን ተንከተም ። ነፍሴን ለመሸጥ ያቀናሁ ገበያ። ነፍሴን ልሸምት የወጣሁ ገበያ ። ሹም በላዬ የራሴ ባሪያ ! ባዶ ባዶ.......... ባዶ ብዘዙዙ ሚሊዮን ባዶ አቻ የሌላቸው .......... ኮኮቦች ቢረግፉ ጥንድ ማይሆኗቸው እልፍ አእላፍ ባዶ ቀልጦ ማያጠፋቸው የአትላንቲክ በረዶ ..... .... .. ነፋስ ማይበትነው ወደዚም ወደ እዛ፤ እሰከ ተሲዓት ድረስ የማይጠፋ ጤዛ። የደብተራ ክህነት የሺ እግዜር ቤዛነት፥ ተመን የማይሆነው የማይወዳደረው .....። ** ብዙ ጎዶሎነት ፥ ፲ሺ ከንቱነት በ፳ ዓመት እድሜ ፥ ፺ አፈር ድሜ ። ..... ................... .................................. ! ✍🏽maddbn
Mostrar todo...
👍
👎
😢
👤 የባተሌው ዜና መዋዕል ! ረመጥ አቅፌ የምሰቃይ ስጉም፤ ላላመልጠው ምሸሽ የራሴን ተንከተም ። ነፍሴን ለመሸጥ ያቀናሁ ገበያ። ነፍሴን ልሸምት የወጣሁ ገበያ ። ሹም በላዬ የራሴ ባሪያ ! ባዶ ባዶ.......... ባዶ ብዘዙዙ ሚሊዮን ባዶ አቻ የሌላቸው .......... ኮኮቦች ቢረግፉ ጥንድ ማይሆኗቸው እልፍ አእላፍ ባዶ ቀልጦ ማያጠፋቸው የአትላንቲክ በረዶ ..... .... .. ነፋስ ማይበትነው ወደዚም ወደ እዛ፤ እሰከ ተሲዓት ድረስ የማይጠፋ ጤዛ። የደብተራ ክህነት የሺ እግዜር ቤዛነት፥ ተመን የማይሆነው የማይወዳደረው .....። ** ብዙ ጎዶሎነት ፥ ፲ሺ ከንቱነት በ፳ ዓመት እድሜ ፥ ፺ አፈር ድሜ ። ..... ................... .................................. ! ✍🏽maddbn
Mostrar todo...
# ህልሜን በህልሜ አየኋት ✍🏽 ማድብን የፍቅር ሙዚቃ <ክሊፕ> እንደሚሰራ ሰው ፩ እግሬን አጠፍ አድርጌ ፣ እጆቼን ኪሴ ውስጥ ከትቼ እያፏጨው ፤... .. ዛፍ ተደግፌ በጆሮዬ ፤ ወፎች ሚያዜሙትን ቅኔ ያዘለ ሙዚቃ... ፣ በአይኔ ከየዛፉ የወዳደቁ ፍሬዎችን ማንጎራጎር የሰለቻቸው ወፎች አሞሮች ሲሻሙት ... ቢራቢሮዎች በውብ አበባ ዙሪያ እየበረሩ አባሮሽ ሲጫወቱ እያየሁ ... ሁሌ እያረፈደች ልቤን ብትሰቅለውም ቀርታ ስለማታውቅ ገሊን ጠብቃታለሁ። ዛሬ ከእሷ ጋር በ11 ሰዓት እዚህ ውብ ስፍራ ቀጠሮ አለኝ ። እንኳን እንደኛ ልባቸው ለተቃቀፈ ፤ ቂም ና ቁርሾ ያለባቸው በደም ሚፈላለጉ ጠበኞች ድንገት ቢገናኙ ተቃቅፈው ሚሳሳሙበት ! ፍቅር ብቻ ሚነፍስበት ገነት ቀረሽ በየብስ ያለ ቦታ ነው። ቦታውን ሰፋ አርጌ ሁሉም የሀበሻ ህዝብ እዚህ እንዲኖር ባደርግ ምኞቴ ነው። "ምነው ዛሬ ደሞ ብዙ ቆየችሳ ? " በሚል የሸሚዜን እጅጌ ሠብስቤ ፣ ሠዓት አይቼ ቀና ስል ፤ በቀስተ ደመና የተነከረ ፣ በዓለም ካሉት ሁሉ እጅግ የተዋበውን ቀሚስ ለብሳ ፣ ለመራመድ እንዲመቻት በግራ እጇ ወደ ላይ ሰብሰብ አድርጋ ይዛው እንደሙሽራ ፣ ወፍራም ጥቁር ወዛም አብረቅራቂ ፀጉሯን ንፋስ እየበተነው ቃላት በማይገልፀው ውብ ቅርፅ ተጠርበው በተደረደሩ በረዶ ጥርሶችዋ ፈገግታዋን ለኩሳ ፣ እንደ " remote control " በተስለመለሙ ቁጥር ስሜቶቼን ሚቀያይሩትን አይኖችዋን ተክላብኝ ፣ ዜማና ሪትም ባለው አረማመድዋ አጠገቤ መጥታ እቅፍ..ፍ አርጋ ስትስመኝ ፣ ፀጉሯ አሁንም በንፉስ ፊቴ ላይ ሲበተን የፀጉሯን ጠረን እየሳብኩ ዘላለም መኖር ስመኝ ፣ የተመኘሁትን ስነግራት ፤ <<አንተ እብድ ብላ ! >> ስትስቅብኝ ፣ እብድ አትበይኝ አላልኩሽም ብዬ ጉንጯን ቆንጠጥ ሳደርግ ፣ የውሸት ስታኮርፍ የቆነጠጥኩት ቦታ ላይ እስማታለሁ .... ። << እሱጋ ብቻ ነው የምትስመኝ ? >> ብላ እነዛ ለደቂቃ ችዬ ማላያቸውን አይኖችዋን በአይኔ ላይ ተክላብኝ ከንፈሯን ፤ ስስ ቀይ ከንፈሯን ! እንድስመው ስታመቻች ፣ ልስማት ስጠጋ ተጠግቼም የ፩ ጣት ግማሽ ከንፋስ ሲቀረኝ ...... 😋 ፊቴ ላይ የተረጨውን ውሀ እየጠራረኩ << መቀስቀስሽ እሺ ይሁን ውሀ መርጨቱን ምን አመጣው ! ደሞ ምን ከመሰለ ህልም መሰለሽ የቀሰቀስሺኝ ምን እንደው እዚ... >> ተነጫነጭኩ! << ብጠራህ ብጠራህ መች ትሰማለህ እንዲሁ እየተገላበጥክ ታንጎላጃለህ እንጂ : ከነጋ ደሞ የት አገር ነው ሚታለመው ባክህ ቀጣፊ በል አሁን ቁርስ ቅመስና ቶሎ ውጣ ሰዓት ሂዶብሀል... >> << አልበላም እንደውም ደህና ዋይ>> ፊቴን ተለቃልቄ እነደነገሩ ለብሼ ወጣሁ ። ✍🏽maddbn
Mostrar todo...
🤝
👍
👎
ፀሎቴን ባሰማ ፥ እንደሰው ዝም አለኝ እሱንም ዘመቻ ፥ ወሰዱት መሰለኝ ....... የእቴሜቴ ጀምበር ©ሲራክ ወንድሙ . እረኛ አይዘምርም ፥ ዝም ነው አድባሩ ፋኖስ ክሩን አጥቷል ፥ መሸ ደህና እደሩ ቡሬ መንደር ራቃት ፥ የለችም ከቤቷ በሌት አልዘመረች ፥ ከፍቷታል ወፊቷ ማልዶ ሌት ሚያነቃኝ ፥ ዶሮ በጉድ ወጣ የሌት ድምፁን ሸጦ ፥ መውዜር ይዞ መጣ ወዲያም ወደ ሰማይ ከጎጆዬ በላይ ፀሎቴን ባሰማ እንደሰው ዝም አለኝ እሱንም ዘመቻ ወሰዱት መሰለኝ . የዛች የእዝነት አርማ ፥ የህዋ ላይ ሰንደቅ እንዴት ቀን ከፍቶባት ፥ ውብ ጀምበሯ ትጥለቅ ከዛች ከገራገር ፥ ከደጊቱ ዳሴ እንደምን ብርቅ ይሁን ፥ ሰላም ለእለት ጉርሴ ኧረ እንደምን በምን ኧረ እንደምን በምን አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን እኔን አፈር ይብላኝ ፥ ለእኔ ቀኑ ይክፋ አንቺን ያሳጣችሽ ፥ ያች አለም ትደፋ እስከ መች አስከ መች ፥ የአረር ሙዳይ ቋጥረን እንደጃኖ ኩታ ፥ ዝናር ጥለት አርገን ሀገር እያጠፋን ፥ ያልፋል እንላለን ? እንዴት ነው መሰንበት ? መውዜር እንደነዶ በሚመዘዝበት? ኧረ እንደምን በምን ኧረ እንደምን በምን አምነን ያነገስነው ብራ ቀን ይዳምን? . ከጩኸትሽ ማዶ ፥ ካኮረፈው ሰማይ ቄራ ከመሰለው ፥ ከአድማስሽ ሸራ ላይ እብሪት ያጠላበት ፥ ምስል ድንገት ካየው ለቸር አንመስለኝም ፥ ያን ጊዜ ፈራለሁ አርብ አርቡን አመሻሽ የሰማዩ ገላ ሲመስል የደም ሻሽ ንትብ የለበሰ ከወደ አንገቱ ዘሞ የተዘለሰ ይሁዳሽን ባላይ ፥ ወድቆ ሲያንሰራራ መስቀል ሆኗል ለሻጭ ፥ ገዢ ራሱን ያኩራ ከክርስቶስ ይልቅ ፥ ይሁዳ ነውና ሚረከብ መከራ ምክኒያቱም ...... ዘመን እያሰፉ ትውልድ ለሚነቅፉ ነገር ጠንቷል ዛሬ ፥ አውቀውት ይረፉ ለሻጭ መስቀል ሊሆን ፥ ምሏልና ዛፉ . በኑረት ቀራንዮ ፥ በህይወት ጎለጎታ ከገዳይሽ ቀዬ ፥ አንቺ ሆነሽ ጌታ በሰማያ አኮርባጅ ፥ ወዲያ ስትላጊ የመከራን መስቀል በሌት ተሸክመሽ ፥ መንገድ ስትፈልጊ ጨረቃዋ ገባች ፥ ከደመና ጉያ ከዋክቶች ሸሽተው ፥ እንደሰደድ ቋያ ጠረንሽን ገፍተው ፥ ከገላሽ ሲርቁ በንቄት ሸምቀው ፥ ሊጥሉሽ ዘለቁ . ዞር ብንል ወዲያ ፥ አራራይ መረዋ ቀና ብንል ኦና ፥ የጠቆረ ህዋ የፀሎትሽ ጩኸት ፥ ካልደረሰው ያ ' ቃል እሱም እንደሰዉ ዘምቶልሽ ይሆናል። ..................... //// .............. ©ሲራክ ወንድሙ @siraaq የእቴሜቴ ጀምበር ህዳር ፳፻፲፬ ዓ.ም https://t.me/maddbn23ethio
Mostrar todo...
ቃል ፡ ሲሆን ፡ ምዕራፍ !።

ውበት ፡ የኪነት ፡ ባንዲራ ፡ ናት። ባንዲራዋም ፤ የስነፅሁፍ ፡ አድባር ፡ ፈገግ ፡ ስትል ፡ ትውለበለባለች...! እነሆ ኪነት በእኛ በልጆችዋ፤ ሰንደቅዋ ከፍ ብሎ ይውለበለብ!፤ ዘንድ የግጥም፣የድርሰት፣ የሌላም ሌላም አርት ዛር የሰፈረባችሁ ኑ በጋራ፤ በብዕራች ቀለም የነተበ ጎኗን እናስውብ🙏 ሀሳብ ካላችሁ @maddbn እና @Poemrs_bot ላይ ልታናግሩን ትችላላችሁ።

ከትቢያ ፥ ተጣብቆ ፥ እንዳል ፥ ነበር ክፉም : ደግም : ሀሳብ : በንፋስ : መልክ : ሽ'ው : ያለው። የቱማታው: ማርፊያውን : እንጃ እየተግተለተለ: ይላወሳል። መፃዕጉነቱ : ቢጠናበት ቀን ቆጥራ : ጅመረ። አዎ ቀኑ #19 ነው የአመቱ ገብርኤል ፥ የባለ : ቀኑን ስም ፍቺ መሰነጣጠቁን : ተያያዘው። ገ ብ ር ኤ ል አምላክ ሰው ሆነ ሰው እምላክ ሆነ በሚል ፥ ፍቺ ፥ ተዋህዶን ፥ እፀናት! የዛር በቆሎ : እንደተጠናወተው : የግንባሩንም : ስጋ መሽሽግ አልፈለገም።የግማሽ ዓለም ጣኦትነቱን : አምኖ ከተቀበል : መክሩሙም አደል.... በገሚስ : ብርሀን :የሞላው : የእዕምሮው ክፍል : የባለ ቀኑን: ስም : ከነፍቺው መርምሮ : አወቀ : አውቆም ፣ ተደሰተ ተደስቶም ፣ ከልቡ አመሰገነ። የቀረው : ገሚሱ : ጨለምተኝነት ከእሱ ዘንድ : ተጣብቶት : ነበርና :ሀኔታው አልዋጥለት : ተብሎ : ነገር ይፈለፍል ፣ ይሰንጣጥቅ: ጀመር። እንዴት ሰው አምላክ ሆን? ጠየቀ...... ጥያቄውንም : በጥርጣሬ: አፀናው!! በቀን : ከ 5 ግዜ በላይ :መርዛማ ፈሳሹን ልምትፋት እንደ ኮብራ : እባብ እንገት : የሚገትር: መቀንዘሪያው ልጓም : ሲበጥስ : ተመለከተው። ጌታም : ሰው : በነበረበት : ግዜ ይህ ነገር : ገጥሞት : እንደነበር : አሰበ :ባሰበበባት : ቅፅብትም : መብርቅ: ከምድረ: ገፅ መቶት አጠፋው። ያኔም እግዜሩ ከላይ ሆኖ ከልቡ ሳቀ¡ የዛ መፃዕጉ ነፍስ የት ገብታ ይሆን? 🦋 ቅዱስ አርዮስ✍ 🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗 ።።።።።👇👇👇👇።።።።። 🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋 🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
Mostrar todo...
የሀገሯ ~ ገመገም ከጥርሶቿ ~ ግርግም፣ ሳቋ ~ ሲያፍገመግም ሳልፍና ~ ሳገድም። አማትሬ ~ ባየው: ተሰትረው ~ ኑረው የቅርብ ሩቅ ~ ሆነው። ኩንስንስ አመሏ ጵስጡቂስ ጠረኗ ኑረት አኳኃኗ፣ ዘንጠፍጠፍ እያለ ቀልብ እያዋለለ፣ የገዛ ጥላዋ ብርቅርቅ ገላዋ፣ ውልብ ይልብኛል..... የድምጿ ሲርሲርታ ያቃጭልብኛል። እናማ...... ምናብ ሀሳብ ሲምስ ሲያወጣ ሲመልስ፣ ጣዕሙን ሊያጣጥም ምላስ ሲፈረጥም፣ እፀበሉ ግርጌ ነጠላ አደግድጌ፣ ስለቴን ላስገባ በእግዜሩ ሙሀባ፣ መጣሁ ከአድባርሽ እቤተስኪያን ቅጥርሽ፣ የኔ እንዲያ መዋተት ደርሶ መንከራተት፣ የኔ እንዲያ መውተረተር ካንቺ ለመሰተር። እነሆ አካሏን ጎብኝቶ ጠረኗን በምናቡ ምጎ ካጣጣመ በኃላ በዕውኑ አለም ፍለጋውን ማነፍነፉን ቀጠለ። አንቺ ሆዬ ወዴት አለሽ? ✍ቅዱስ አርዮስ✍ 🌗የግማሽ ዓለም ጣኦት🌗 ።።።።።👇👇👇👇።።።።። 🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋 🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋 🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
Mostrar todo...
#ወዲያ_ሽሽ_ይለኛል! © ሲራክ ወንድሙ @siraaq . ኑረት ሲረክስብኝ ፥ ሲሆን እንደ እቃ 'ቃ ፣ አዎን ያስፈራኛል ፥ የዘመን አታሞ .................... ፥ የዘመን ድለቃ ፤ የድግግሞሽ ሰልፍ ፥ የእሽ ፡ ክርክሪት ምልዓት ፣ ሰው ሆኖ ተኝቶ ፥ ትል ሆኖ እንደመንቃት ። ንጋት አድባር ሆኖ ፥ የሀገር ጌጥ የሀገር ዳስ ፣ ጀምበር በሰረቀ በአመሻሹ ፈለግ ፥ እንደካህን መርከስ ፤ እንደምኩራብ ከብሮ ፥ እንደ እንትን መንኳሰስ ። አዎን ያስፈራኛል... ወዲያ ሽሽ ይለኛል... ወዲህ ግድም እሩጥ ፣ ወዲህ ግድም አምልጥ ፤ ወዲያ ጥግህን ያዝ ፥ ይለኛል ይለኛል ፤ የዘመኑ ቅኔ የዘመኑ መንፈስ ፥ መንን ያሰኘኛል ፤ ወዲያ ሽሽ ይለኛል ። .............. | ። | ............... ነሐሴ ፳፻፲፫ ዓ.ም ⓒሲራክ ።።።።።👇👇👇👇።።።።። 🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋 🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋 🦋🦋 t.me/sufafel 🦋🦋
Mostrar todo...
Inicia sesión y accede a información detallada

Te revelaremos estos tesoros después de la autorización. ¡Prometemos que será rápido!