cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Zehabesha

Ethiopian News

Mostrar más
Advertising posts
60 171Suscriptores
+4024 hours
+2757 days
+83530 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሠጠ መግለጫ! የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ምላሽ ሰጥቷል። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር በተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች ላይ ትንኮሳ መጀመሩንም አስታውቋል። የመግለጫው ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል፦ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻሕፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት መግለጫ ተመልክተናል፡፡ ጊዜያዊ አሥተዳደሩ የአማራ ክልል የትምህርት ሥርዓትን በማጣቀስ የተሳሳተ ካርታ ተሠርቷል ሲል ያወጣው መግለጫ በተሳሳተ ካርታ ወደ አማራ ክልል ተካተዋል ያላቸውን አካባቢ ሕዝቦች ታሪካዊ እውነታን፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችን እና ነባራዊ ሐቅን የካደ፣ አሳሳች እና የጠብ አጫሪነት ፍላጎትን የተሸከመ መግለጫ በመኾኑ እና በትናንትናው እለት ማለትም መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ከነበረበት አካባቢ በመንቀሳቀስ የራያ አላማጣ ወረዳ ቀበሌዎችን በመያዝ ነዋሪዎችን በመግደል እና በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ ስለኾነም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ መግለጫ መስጠት ተገቢ ኾኖ አግኝቶታል፡፡ ጊዜያዊ አሥተዳደሩ የአማራ ክልል የተማሪዎች የመማሪያ መጻሕፍ ውስጥ የተሳሳተ ካርታ ተሠርቷል ሲል ባወጣው መግለጫ ሊያመላክታቸው የተፈለጉት አካባቢዎች ካለፉት 30 ዓመታት በፊት ጀምሮ የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያሉባቸው ወረዳዎች የማንነት እና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን ሲያቀርቡባቸው በነበሩ ቦታዎች ላይ መኾኑ ግልጽ ነው፡፡ አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በተስተዋሉት የአሥተዳደራዊ መዋቅሮች እና አደረጃጀት ቅመራ ጅማሬ አንስቶ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ አሰቃቂ ጥቃት በመፈጸሙ ምክንያት ጦርነት እስከተቀሰቀሰበት ጊዜ ድረስ የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች በወቅቱ ለነበረው መንግሥት የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መኾኑን በበርካታ ታሪካዊ ሁነቶችና ተጨባጭ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ ሕዝቦች እና አካባቢዎችን ለበርካታ ዘመናት በኃይል ሲገዛ የነበው የቀድሞው የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ላነሱት ታሪካዊና ሕጋዊ ጥያቄዎች ሕጋዊ አሠራርን የተከተለ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የአካባበው ተወላጆችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ የማንነትና የአሥተዳደር ጥያቄ አስተባባሪዎችን በማሰር፣ በማሰደድ እና በመግደል የሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ እስከ ሰሜኑ የሕግ ማስከበር ጊዜ ድረስ እንዲገፋ አድርጎታል፡፡ የማንነት እና የአሥተዳደር መብት ዙሪያ ላነሳቸው ጥቄዎች የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ትግል በተፋፋመበትና ከፍተኛ መሥዋዕትነት ጭምር እየከፈለ በሚገኝበት ወቅት ህወሓት የሠሜን ዕዝ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን አሰቃቂ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ሁሉንም ኢትዮጵያዊያንን በማቀናጀት ለሁለት ዓመታት የቆየ የሕግ ማስከበር እርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ሁኔታ መፈጠሩ ይታወሳል፡፡ የማንነትና የአሥተዳደር ጥያቄዎቹ ለዘመናት የታፈኑበት ሕዝብም ከማዕከላዊው መንግሥት ጎን ተሰልፎ በህ.ወ.ሓ.ት የክህደት ተግባር በኢትዮጵያ ሕልውና እና ሉአላዊነትት ላይ የተጋረጠውን ግልጽ አደጋ እንዲቀለበስ የበኩሉን አስተዋጽዖ ከማበርከቱ ባሻገር በሂደቱ ህወሓት በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረውን የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማሥተዳደር ነጻነት የተቀዳጁበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በዚህም ምክንያት የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ሕዝብ እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል በመኾኑ በቀድሞው የህ.ወ.ኃ.ት እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግሥት መካከል የፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም በትምህርቱም መስክ ተጠቃሚ እንዲኾኑ አድርጓል፡፡ አካባቢዎቹን በተመለከተ የነበረው፣ ያለው እና የሚኖረው እውነታ ይሄ ኾኖ ሳለ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም ከፕሪቶሪያው ስምምነት ከመፈረሙ በፊት በሥራ ላይ የዋሉ የአማራ ክልል ተማሪዎች እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማራ መብታቸው እንዲከበር የአማራ ክልል መንግሥት ግዴታውን መወጣቱን ሰበብ በማድረግ በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መኾኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ ማውጣቱ ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ የተፈጠሩ ችግሮችን በሕግ አግባብ እንዲፈታ እየተደረገ ያለውን ጥረት የአማራ ክልል መንግሥት የራሱን ድርሻ እየተወጣ ባለበት ሁኔታ በሕዝብ መጎሳቆልና በወጣቶች እልቂት ትምህርት አለመወሰዱና የተለመደ ትንኮሳ በማድረግ ላይ መኾኑ እጅጉን አሳዝኖናል፡፡ ስለሆነም የትግራይ ክልል ግዜያዊ አሥተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ፣ ሀገራችንንና ሁለቱን ክልሎች ወደ ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የሕዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላም እና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መጋቢት18-2016 ዓ/ም ባሕር ዳር
Mostrar todo...
👍 3👎 1
Mostrar todo...
Zehabesha

በዮሐንስ ቧያሌው፣ ክርስቲያን ታደለ፣ ዘመነ ካሴ፣ እስክንድር ነጋና ሌሎችም ላይ ዛሬ ፍትህ ሚኒስቴር የመሰረተውን ክስ ሰማችሁ? በዕለቱ ዜናችን ላይ በዝርዝር ይዘነዋል። ይመልከቱት።

https://youtu.be/QXq045DsGjk?si=6wFEMXg2izSpGPNw

👍 7 1👏 1
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ፤ * የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በፌዴራል መንግስት እና ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ህወሓት ወያኔ/ትሕነግ) እያለ በሚጠራው ቡድን መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም የተደረገውን ድርድር እና በኋላም የተደረሰውን የሰላም ሥምምነት አስመልክቶ በየጊዜው በአንክሮ እየተከታተለ አቋሙን ይፋ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳን በፌዴራል መንግስት እና በወያኔ መካከል የተደረገው ሥምምነትና ትግበራ ላይ እንደ ድርጅት የታዘብናቸው ጉድለቶች ቢኖሩም ለሀገር ሰላምና አብሮነት እድል ይሰጣል፤ ለውይይትና ንግግር በር ይከፍታል በሚል በጎ መሻት የሀገራችንን ብሎም የትግራይን ህዝብ ሰላም መሆን በመፈለግ፤ መንግስት የስምምነቱ አፈጻጸም ላይ የሰራቸውን ስህተቶች ጭምር ለትልቁ ሀገራዊ የጋራ ሰላም ሲባል በትዕግስትና በጥሞና ስንከታተል ቆይተናል፡፡ በፕሪቶሪያው ሥምምነት አንቀጽ 6(F) መሰረት ህወሓት ወያኔ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቀላል መሳሪያን ጨመሮ ጠቅላላ ትጥቅ እንዲፈታ፤ አንቀጽ 3(5) መሰረት ደግሞ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ ገብቶ ጸጥታ የማስከበሩን ሥራ በተሟላ ሁኔታ እንደሚረከብ ሥምምነት የተደረሰ ቢሆንም፣ ወያኔ ትጥቅ ሳይፈታ የሀገር መከላከያ ሠራዊትም ወደ ትግራይ ገብቶ ጸጥታ የማስከበር ሥራውን ሳይረከብ፣ በጦርነት ጉዳትና መልሶ ግንባታ ስም ወያኔ በትግራይ ግዜአዊ አስተዳደር ስም ከፍተኛ የገንዘብ እና የግብዓት ድጋፍ ሲደረግለት የቆየና የፕቶሪያውን የሰላም ሥምምነት አንቀጽ 7(1)(D) በግልፅ እየጣሰ ባለበት ሁኔታ የሰላም ስምምነቱ ይከበር የሚል የምጸት ፕሮፓጋንዳ እና የጦርነት ጉሰማ ላይ በአዲስ መልክ ተጠምዷል፡፡ ወያኔ ሐገራዊ ሀይሉ ተከፋፍሎ የርስበርስ ግጭት ውስጥ ወድቋል ብሎ ባመነ ጊዜ ሁሉ እንደ ሁኔታው እያፈራረቀ አንደኛውን በመጠጋትና ሌላውን በመጋፋት ነጣጥሎ ሁሉንም ለማዳከምና ለማጥቃት ሲያደባና ዝግጅት ሲያደርግ ከርሟል። በተለይም ግልብ የሆነውና ዘወትር በሬ ካራጁ ያደረውን የልሂቅ አካል በደጋፊነት መልምሎ ለማሰለፍ በተለይም ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ በጦርነት ያላገኘውን ድል ሀገራዊውን ጥምረት በመከፋፈል፣ እርስበርሱ እንዳይነጋገርና እንዳይግባባ ብሎም የሴራ ፖለቲካ ሰለባ እንዲሆን እና ግጭት ውስጥ ገብቶ የሃይል ሚዛኑ እንዲዛነፍ ለማድረግ የተደራጀና ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ ስራ በቅጥረኞቹ በኩል በሰፊው ሲሰራ ቆይቷል። የአማራ ህዝብ የግፍና ሰቆቃ ሀተታ ዋና ደራሲ የሆነው ህወሓት ወያኔ ራሱ በቀሰቀሰው ጦርነት ሳይቀር በሀሰት ላይ የተመሰረተ የሞራል የበላይነት እንዲኖረው አንዳንድ የልሂቃን ወገኖችን ሳይቀር የሀይል አሰላለፍ ግምገማና አጠቃላይ ፖለቲካዊ ምልከታቸውን በማዛባት ጭምር "ጅብ በማያውቁት ሀገር" እንደሚባለው ነገ አድሮ በገዛ ህዝባቸው ላይ ለሚፈጸም ወያኔአዊ ጥፋት አጋርነትን ለማበጀት መልምሎ ሲያሰልፋቸው አስተውለናል፡፡ አዲሱ የወያኔ ትህነግ መግለጫና የጦርነት ዛቻም ከዚህ አንፃር መታየት ይኖርበታል። ሆኖም ግን ወያኔ/ትህነግ በምስረታ ሰነዱ የአማራን ሕዝብ በጠላትነት የፈረጀ እና ማኅበራዊ እረፍት መንሳት የሚል ፋሽስታዊ የፖለቲካ ፕሮግራም ቀርጾ እና ከአማራ ዋና ዋና ግዛቶች ውስጥ ለም እና ስትራቴጅካዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ቦታዎች ወደ "ታላቋ ትግራይ" ለማካተት በማወጅ ደደቢት በርሃ መውረዱን ለአፍታም የምንዘነጋው አይሆንም:: የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የህዝባችን የማንነትና ወሰን ጥያቄዎች ከ30 ዓመት በላይ በፈጀ ያልተቋረጠ ትግልና መስዋትነት ታሪካዊና ስነልቦናዊ መፍትሄ አግኝተዋል ብለን እናምናለን፡፡ በዚህም የአማራ ሕዝብ እንኳንስ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ከሚጋራቸው ሕዝቦች ቀርቶ ከጎረቤት ሀገራት ወንድም ሕዝቦች ጋርም በሰላም፣ በፍቅርና በመከባበር መኖር የሁሌጊዜም ምርጫው መሆኑን የሚያረጋግጥበት ከባቢ ፈጥሯል፡፡ ይሁን እንጂ የህዝቦች አንድነትና የሀገር ሰላም የማይመቻቸው ቀውስ ጠማቂዎችና ከዳግም ጥፋታቸው ያልተማሩ የደም ነጋዴዎች ለሌላ ዙር ሀገራዊና ቀጠናዊ ቀውስ መዘጋጀታቸውን በግልፅ መለፈፍ ጀምረዋል፡፡ በመሆኑም፡- የተከበርከው የአማራ ሕዝብ ፤ ምንም እንኳ አሸባሪው እና ተስፋፊው ወያኔ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠላት ቢሆንም ፣ በተለይ የአማራ ህዝብ የቡድኑ ወረራ ቀጥተኛ ሰለባ እና ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ጦርነቱን የመመከት ድርብ ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በሁሉም አካባቢዎች የሚገኝው ሕዝባችን ካለፈው የጥፋት ግዜ በመማር ለታሪካዊ ጠላቱ ፕሮፖጋንዳ ጀሮ ባለመስጠት ራስህን ከአራተኛ ዙር ጥፋት ለመከላከል ከመቸውም ጊዜ በላይ በአንድነት እንድትቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የተከበርከው የትግራይ ሕዝብ ፤ በስምህ የሚነግደው አሸባሪው እና ተስፋፊው ቡድን ፣ ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር ያለህን ትስስር ለመበጠስ እና ከኢትዮጵያዊ ማንነትህ ለመንቀል በማያባራ የጦርነት አዙሪት ውስጥ እንዳስገባህና አምራች ሀይልህን ፍትሀዊ ባልሆነ ጦርነት ማግዶ ማስፈጀቱ ይታወቃል፡፡ ልጆችህን ከጉያህ እየነጠቀ ፣ ጥሪትህን እያሟጠጠ እና አግቶ በመያዝ ከሌሎች ኢትዮጵያውን ጋር በአንድነት እና በሰላም እንዳትኖር ጋሬጣ የሆነብህን ደም-የማይጠግብ የሽብር ቡድን ከራስህ ላይ አሽቀንጥረህ በመጣል ራስህን ነጻ እንድታወጣ ጥሪያችንን እያስተላለፍን ፣ ከሽብር ቡድኑ እገታ ነጻ ለመውጣት በምታደርገው ተጋድሎ ድጋፋችን እንደማይለይህ ከወዲሁ እናስታውቃለን፡፡ የአማራ ክልል መንግስትና የፌዴራል መንግስት፦ ወያኔ ተደጋጋሚ ወረራ በመፈጸም ታሪክ ይቅር የማይለው ሰፊ ጥፋት በሀገርና በህዝብ ላይ የፈጸመ ሆኖ ሳለ ይህ አልበቃው ብሎ አሁንም ሌላ ዙር ጦርነት ቀስቃሽ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ የገባ በመሆኑ ይህንን የወያኔን ጠብ አጫሪነት በትኩረት እንዲከታተሉ በጥብቅ እያሳሰብን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ልዩ ትኩረት ሰጥተው በውይይትና ድርድር ሰላም የማስፈን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሁንም ጥሪ እናቀርባለን። መጋቢት 17/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ!
Mostrar todo...
😁 35👍 28 6🤮 1
👍 1
ሁለት ባለሃብቶች ከሃገር እንዳይወጡ ከኤርፖርት ተመለሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግብር ከፋይ ባለሃብቶችን ባነጋገሩ ከቀናት በኋላ በትናንትናው ዕለት ሁለት የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ወደ ውጭ ሃገር ሊወጡ ሲሉ ከኤርፖርት መመለሳቸውን የደህንነት ምንጮች ለኢትዮጵያ ገለጹ። ስማቸው ለጊዜው እንዳይጠቀስ የተጠየቀው እነዚህ ሁለት ባለሃብቶች አንደኛው ወደ ጀርመን ለህክምና ሌላኛው ደግሞ ልጁን ለመጠየቅ ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ነበሩ። ሆኖም ግን ባለሃብቶቹ ኤርፖርት ላይ በደህንነት ሰዎች ተይዘው ከሃገር መውጣት እንደማይችሉ እንደተነገራቸው፤ ምክንያቱን ሲጠይቁም የደህንነት ሰዎቹ ት ዕዛዙ የመጣው ከኤርፖርቱ የአቪየሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስራት ቀጀላ ነው። ከሃገር እንዳትወጡ የተከለከላችሁበትን ምክንያት ከአቶ አስራት ቀጀላን እና ከምክትላቸው አቶ ማስረሻ ወርቁ ጠይቁ መባላቸውን የደህንነት ምንጮች ነግረውናል። እነዚህ የደህንነት ክትትል አባላት እነዚህን ባለሃብቶችን ከመመለሳቸውም በተጨማሪ በኤርፖርቱ ውስጥ የሚሰሩ የአማራ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችን የፋኖ እና የሸኔ መረጃዎችን ለቲክቶክ ሰዎች የምታሰራጩት እናንተ ናችሁ በሚል ስልካቸውን ከህግ ውጭ እንደሚፈትሹ አስታውቀዋል። በተለይ እንደ ዋትሳፕ እና ቫይበር ያሉ አፖች በግሩፕ የማይታወቁ ሰዎች የሚልኳቸው ፎቶዎች በቀጥታ ወደ ስልክ የፎቶ ማህደር ስለሚገቡ አንዳንድ የኤርፖርቱ ሰራተኞች የፋኖ ወይም የሸኔ ፎቶ በስልክህ ማህደር ተገኝቶብሃል በሚል ከስራ እየታገዱና የታሰሩም እንዳሉ የደህንነት ምንጮቹ አስረድተዋል። ሌሎችም ቢሮ ድረስ እየተጠሩ ስልካቸው እየተፈተሸ በሰቀቀን እንዲኖሩ ለእንግልት እየተዳረጉ መሆናችው ተነግሯል። በቅርቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባለሃብቶችን ሰብስበው ሁላችሁም ብትፈተሹ በህግ የሚያስጠይቅ አንድ ነገር አይጠፋም ማለታቸው አይዘነጋም።
Mostrar todo...
👍 22😢 10🔥 4🤬 2 1🤔 1
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ኢሉ ወረዳ የአስጎሪ ርጳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። ************************************************************* ታጣቂዎች የካቲት 17 ቀን 2016 ዓ.ም እሁድ ንጋት ላይ ካህናቱ ጸሎተ ኪዳን አድርሰው ቅዳሴ ሊገቡ ሲሉ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት ኦርቶዶክሳውያንን አግተው የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 5ቱ ካህናት ሲሆኑ ቀሪዎቹ 8ቱ ደግሞ ምእመናን ናቸው። ከእነዚህ ውስጥ ስምንቱን ምእመናን እና አስተዳዳሪውን የጠየቁት ገንዘብ ተከፍሎዋቸው የለቀቋዋቸው ሲሆን የተቀሩትን አገልጋይ ካህናት ገንዘብ ቢከፈልም ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋቸዋል። በታጣቂዎች የተገደሉት አገልጋዮች ስም:- 1.ቀሲስ ቸርነት ብዙወርቅ ቄሰ ገበዝ 2.ቀሲስ ሳሙኤል ወደጆ ቀዳሽ ካህን 3.መሪጌታ ያሬድ የደብሩ መሪጌታ እንዲሁም 4.ዲ/ን ቤዛ ባዬ የደብሩ ጠቅላላ አገልግሎት ናቸው። በተለይም የደብሩን መሪጌታ መጀመሪያ እጃቸውን ቆርጠው ለውሻ በመስጠት ከዚያ በኋም እያንዳንዱን አካላቸውን በገጀራ በመቆራረጥ እንደገደሏቸው የዐይን እማኞች ገልጸዋል። ሌሎችም አገልጋዮች በተመሳሳይ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል። በተጨማሪም በቾ ወረዳ ሶየማ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ቀሲስ መልአኩ የተባሉ አንድ ካህን መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ታግተው ተወስደዋል። ቶሌ ወረዳ ላይ እንዲሁ አንድ ዲያቆን በመውሰድ ለመልቀቅ አንድ ሚልዮን ብር እንደጠየቁ ለማወቅ ተችሏል። በመላው ሃገሪቱ ባለው ጦርነትምም ይሁን በታጣቂዎች በሚደረጉ ጥቃቶች አገልጋይ ካህናትና ምእመናን በተለየ መልኩ ጥቃት እየደረሰባቸው ሲሆን ችግሩን ለማስቆምም ይሁን ታግተው ያሉ ካህናትና ምእመናንን ለማስለቀቅ የሚደረግ መንግስታዊ ጥረት አለመኖሩ መንግስት ራሱ ከአጥቂዎች ወገን መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው። ስለሆነም ምእመናን የተከበረችና የታፈረች ቤተ ክስርቲያንን ለትውልድ ለማሻገር ይቻል ዘንድ ለሰማዕነት ልንዘጋጅና ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ልንነሣ ይገባል። ©ስምዕ ተዋህዶ
Mostrar todo...
😭 65👍 22 2🔥 1🤯 1
በተለይ ለሾፌሮች፣ ለኡበርና ሊፍት አሽከርካሪዎች ምግብዎን ለማሞቅ የግድ ማክሮዌቭ ፍለጋ መሄድ አይኖርባችሁም። ይህ የምሳ ቦርሳ እንደማክሮዌቭም ያገለግላል። መኪናዎ ውስጥ ማሞቅ ይችላሉ። አማዞን ላይ ቼክ አድርጉት። https://amzn.to/4aymPmi
Mostrar todo...

👍 13 1
በአዲስ አበባ አፈሳ እንዳለ ምንጮች አድርሰውናል::
Mostrar todo...
👍 31💩 4👎 2😁 1
Inicia sesión y accede a información detallada

Te revelaremos estos tesoros después de la autorización. ¡Prometemos que será rápido!