cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Up & down

አላማችን ክርስትያን የሆነው ማህበረሰብ ሂወቱን በመለወጥ በእውቀት እንዲመራ የሚያስችሉትን የትኛውም አይነት የስነፅሁፍ ስራዎችን እንዲያገኝ መርዳት ነው ። በዚህ የቴሌግራም ቻነል መንፈሳዊ የሆኑ የስነፅሁፍ ስራዎች ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚዳስሱ የስነፅሁፍ ስራዎች ፣ትምህርቶች(መንፈሳዊ እንዲሁም ማህበራዊ) ፣ የሂወት ታሪኮት (biography) ፣ መዝናኛዎች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ይዳሰሱበታል

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
170Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

///ለሰከንድ አልኖርም/// አንድ ጊዜ በቀኝ አንድ ጊዜ በግራ የያዝኩትን ሳሊዝ ያልያዝኩትን ልይዝ መከራ ስበላ ጠዋቴም አለፈ መሸታው ላይ ደረስኩ የምይዘው ጠፍቶኝ እንዲሁ እንደባዘንኩ በዘላለም መሀል ቢጠልቅ እድሜዬ የሚወስደውን እጅ ሳሰላው ቁጭ ብዬ የሰከንዶች ሽርፍራፊ ደቂቃ ማይሞላ መሆኑ ቢገባኝ ደርሶ ትርጉም የለሽ ምንም የማይረባ የአለምን ጋጋታ ላልሰማ ቸል ብዬ ፍለጋዬን ሁሉ ወደ ዃላ ጥዬ ጤዛውን እድሜዬን ለእርሱ ሰዋውለት ሰከንድን ለመኖር ዘላለም እንዳልሞት ግጥም-ምህረት ሻውል(Mሬ) @Davehymi @litratureforall
Mostrar todo...
❤ 4
🙏 2
ፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን።2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:2
Mostrar todo...
በእግዚአብሔር ቃል መሰረት ሰዎች በልዩ ልዩ ሀጢያት ሲወድቁ ከውድቀታቸው የሚነሱበት ብቸኛ መንገድ ንስሃ ብቻ እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ይሁንና ንስሃ ጥቅል ሃሳብ እነደመሆኑ ወደ ዝርዝሩ መግባትና የሃሳቡን ዋና ነገር መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ንስሃ ማለት 1ኛ ሀጢያተኝነትን ማመን (ማወቅ) 2ኛ ሀጢያትን መናዘዝ 3ኛ ከጥፋት መንገድ መመለስና መካስ የሚሉትን ሀሳብ ጠቅልሎ የያዘ ነው፡፡ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:9 በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው። በመሆኑም በመጀመሪያ ወደ ጌታ ከመጣን በኋላ ከዚህ ቀደም እንኖርበት የነበረውን የሃጢያት ህይወት በክርስቶስ ደም ስለታጠበልን ከእንግዲህ ወዲህ እንደማይታሰብብንና ቀድሞ በሰራነው ሀጢያት እንዳይፈረድብን የሃጢያትን ይቅርታ ማግኘታችን የተረጋገጠ ስለሆነ በቀድሞ ስራችን ፈጽሞ ልንከሰስ አይገባም፡፡ ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:8 ይሁንና በጌታ ቤት ውስጥ ሳለን በድፍረት ወይንም ባለማወቅ ሀጢያትን ሰርተህ እንደሆነ መጀመሪያ የሰራኸው ሀጢያት መሆኑን ማመን ይኖርብሃል፡፡ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:10 ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም። ምክኒያቱም አንድ ሰው ሀጢያተ መስራቱን ሳያምን ንስሃ ቢገባ ተመልሶ ወደ ትፋቱ ለመመለሱ ምንም ዋስትና የለውም፡፡ ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ። የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:22 በሀጢያተኝነቱ ሳያምን ንስሃ የሚገባ ሰው ለምን ንስሃ እንደሚገባ እንኳን በቂ ምክኒያት የለውም፡፡ የሰራው ሀጢያት ነው ብሎ ስላላመነም ለይምሰል ለገባው ንስሃ ለመገዛትና ከጥፋቱ ለመራቅ ጉልበት አይኖረውም፡፡ ስለዚህ ሀጢያትን ሰርተህ ከሆነ የሰራኸው ሀጢያት እንደሆነ ማመን ይኖርብሃል፡፡ አለበለዚያ እስኪገባህ ድረስ መቆየት መጠየቅ ይኖርብሃል፡፡ ሁለተኛው ሀሳብ ሀጢያተኝነቱን ያወቀ ሰው የሰራውን ሀጢያት ቢፈልግ በሰው ፊት፤ ካፈረም በእግዚአብሔር ፊት መናዘዝ አለበት፡፡ ኑዛዜው ለሀጢያቱ እውቅና መስጠቱና ከእንግዲህ ወደዚህ ሀጢያት ላለመግባት ቃል እንደመግባት ስለሆነ መጽሀፍ ቅዱስ መናዘዝን ግድ ይለዋል፡፡ እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።የያዕቆብ መልእክት 5:16 ስለሆነም የሰራው ሀጢያት በእርሱና በእግዚአብሔር ፊት ብቻ የታወቀ ከሆነ የግድ አደባባይ መውጣትና ባደባባይ መናገር ላያስፈልገው ይችላል፡፡ ይሁንና ያው ሰው የሰራው ሀጢያት ብዙዎን የበደለና በብዙዎች ዘንድ የታወቀ ከሆነ ኑዛዜውም በበደላቸው ሰዎ ፊትና ባደባባይ ሊሆን የግድ ይሆናል፡፡ የማቴዎስ ወንጌል 5:24 በዚያ በመሠዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፥ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፥ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።ምክኒያቱም በደሉ እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን ወገኖኑንም ጨምሮ የበደለ በመሆኑ ይቅርታ እንዲደረግለት የሚጠብቀው ከእግዚአብሔርና ከሰዎችም መቀበል ይኖርበታል፡፡ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፥ ቢጸጸትም ይቅር በለው።የሉቃስ ወንጌል 17:3 አንዳንዶች ግን ብዙዎችን ከበደሉና ካሳዘኑ በኋላ በእግዚአብሔር ፊት ብቻ ንስሃ ገብተው የበደለሉዋቸውን ሰዎች ችላ ይሏቸዋል፡፡ እንዲህ ያለው ኑዛዜ ፍሬ አልባ የሆነ ንስሃ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ምክኒያቱም እግዚአብሔር ስለእያነንዳንዳችን ግድ የሚለው አምላክ ስለሆነ የበደሉን ሰዎች መጥተው ይቅርታ ካልጠየቁን ወይንም እኛም የበደልነው ሰው ካለ ወደዚያ ሰው ሔደን ካልተናዘዝንና ይቅርታን ካልተቀበልን በእግዚአብሔርም ዘንድ ይቅር አንባልም፡፡ የመጨረሻው እርምጃ የንስሃ ፍሬ የሚታይበት እና የተበደሉትን የሚክስበት ነው፡፡ እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ፤ የማቴዎስ ወንጌል 3:8ንስሃ የገባ ሰው ከንስሃው በኋላ ወደ ቀደመው ትፋቱ እንደማይመለስና በዚያ ፋንታ በጎ ማድረጉን የሚያሳይበት ደረጃ ነው፡፡ ሰርቆ የነበረ ሰው የሰረቀውን ገንዘብ ለባለቤቱ መመለስና አጥፍቶትም ከሆነ በገዛ እጆቹ እየሰራ ለችግረኞች እያካፈለ የበደላቸውን መካስ ይጠበቅበታል፡፡ የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:28 ዝሙት ያደረገ ወይንም ዋሾ ከሆነ ከእንግዲህ ወዲህ በቅድስና በመኖርና እውነትን ብቻ በመናገር ፍሬውበእግዚአብሔር ፊት መታየት ይኖርበታል፡፡ ብዙ ሰዎች ቅድስናቸውም ሆነ እውነተኝነታቸው በሰው ፊት ብቻ እየሆነ ሰውን ሲያዩ ይቀደሳሉ ሰው ዞር ሲል ብዙ እርኩሰትን በማድረግ በስውር የሚያያቸውን ጌታ ንቀውታል፡፡ እንደዚህ ያሉ ሰዎች ፈጽሞ ንስሃ የገቡና በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ያጡ በመዎናቸው እልኸኝነታቸውን በጨመሩ መጠን ቆይተው እንደ ቃየን በሐጢያት ለይ ነግሰው ለማይረባ አይምሮ አሳልፈው ይሰጡና በጣም የሚያሳፍር ነገር ወደ መስራት ይገባሉ ነገር ግን ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።የሉቃስ ወንጌል 13:5 እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ ሁሉም መንገድ ሲዘጋባውና ከሰውም ከእግዚአብሔርም እንደማያመልጡ ሲያስቡ ለይምሰል በተንኮል የሆነ ንስሃ ይገባሉ፡፡ ነገር ግን የንስሃ ፍሬ አይታይባቸውም፡፡ ምክኒያቱም ከሰው ለማምለጥ ንስሃ ይገቡና በስውር ደግሞ የሀጢያት ቆሻሻ ውስጥ ሲዳክሩ ይታያሉና ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው ደካማ ነውና ዛሬ ጌታ እየረዳው በቅድሰና ቢገኝ አንድ ቀን በስጋው ተሸንፎና ለጊዜአዊ ጥቅም ተሸንፎ ወድቆ ሊገኝ ይችላል፡፡ የወደቀ ቀን እንደ ጴጥሮስ ወይንም እንደ ንጉስ ዳዊት ፈጥኖ በንስሃ ነፍሱን እንዲያጥብና ከእድፉ እንዲጸዳ እውነተኛ ንስሃ መግባት ያፈልጋል፡፡ ለይምሰልና ለተንኮል ንስሃ ቢገባና ሰውን ማታለል ቢችል፡፡ የነፍሳችንን ፈጣሪና ጌታችን እንዴት ማታለል እንደሚል ያስባል? ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ።ወደ ሮሜ ሰዎች 2:5 አንዴ ንስሃ የገባ ሰው እና የንስሃውን ፍሬ በተግባር የሚያሳይ ሰው በሰው ፊት ድፍረት ያገኛል፡፡ ይህ ሰው ከንስሃ በሀኋላ ሰዎች ለሀሜት ቢነሱበት አስቀድሞ ሐጢያተኛ ነበርኩ ብሎ ለመናገር ድፍረት ስለሚኖረው በማንም ሰው ሀሜት አይፈራም፡፡ ለዚህ ነው ብዙ ሰባኪዎች ሌባ ነበርን ውሸታም ነበርን ሴሰኛ ነበርን እያሉ ባደባባይ በኩራት ሲናገሩ የሚያኮራቸው የነበሩበት ሳይሆን አሁን ግን ነጻ ወጥተናል የሚለው እና ተስፋ ያልነበራቸውና የተጣሉ የነበሩ ሰዎች ሆነው ሳለ ዛሬ በክብር በእግዚአብሔር ቤት መድረክ ላይ መቆማቸው ያስደስታቸዋል፡፡ ጳውሎስ እንኳን ሲናገር አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፥1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:13 ግብዝ የሆነ ሰው ግን ሀሜትን በጣም ይፈራል፡፡ ምክኒያቱም የሚታማበት ነገር ትክክል ስለሆነ በግምት እንኳን ሲዋሹበት አይተውት የሚያወሩበት ስለሚመስለው በጣም ይደነግጣል፡፡ ከዚህ ሁሉ ለመላቀቅ እውነተኛ ንስሃ በመግባትና በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ክብር ይሆንልናል፡፡ ነገር ግን የሚያሳ
Mostrar todo...
ልመና መቅደሱ ስር ሆኜ እንባዬን ሳነባ መፈጠሬን ስረግም ሆዴንም ሳባባ አንዱ ጠጋ አለ ከልቡ ሊያወራኝ ላስቸግርህ! አለ ፈቃዴን ጠየቀኝ እሺ! አልኩ ከልቤ ችግሬንም ስማኝ እራትም አልበላዉ ለዛሬም የለኝ ካለህ ላይ ቆንጥረህ እባክህ አካፍለኝ? ድንጋጤ ሞላኝ ልቤም ተሸበረ ላይበቃው በመስጠቴ ውስጤ እያፈረ ...ይበቃል አለ ውስጡ እየፈነደቀ የሱን ደስታ አይቼ ምኔ ተደነቀ ችግር ላይ መሆኔን ልቤም እያወቀ እግዜር ይስጥህ! በወጣው ይተካ! መረቀኝ ከልቡ በጌታው ተመካ! ይስጠኝ መና እሱ ሳይወስድ መልሶ ይምራኝ በመንገዱ ይውሰደኝ ቀልሶ ይህን እያሰብኩኝ! ጭንቀቴን ረሳውኝ! ማማረሬን ተውኩኝ! አዲስ ቀን ጀመርኩኝ! @Davehymi @litratureforall
Mostrar todo...
❤ 2
🙏
ኖር (በተስፋ ብዙወርቅ) በፊት በፊት ድሮ ድሮ፣ ድንጋይ ሁሉ ዳቦ ጠጠር ሁሉ ንፍሮ፣ በነበረበቱ ኖር………… በጃንሆይ ኖር ………… በእግዜሩ ነበር ንግግሩ በፊት በፊት ድሮ ድሮ ጭልፊት ሳለች ዶሮ ክንፍ ሳትሰፋ ኖር ሲባል ኖር ኖራ ……… በግዜራ ኖራ ……….. ሆራ ሎን ኩመ ሆራ የሺዎች አባት ሁን እልፍ መንጋ አፍራ በሺህ ሰው ተፈራ ነበር ንግግሩ ዛሬ ዛሬ ተተወ ማክበር ሽበት ኖር ቀረ ሆነ ተረት ነበር ተብሎ የሚተረት ያለውም ሆነ ካንገት ከበደ ብድግ ከተቀመጡበት ወገብ ስራ በዝቶበት፡፡ @litratureforall @Davehymi
Mostrar todo...
👍
❤ 1
ይፍታ መላ ያጣ ላጤ የላጤ ደንቆሮ ውሉ የጠፋበት የመላ ቋጠሮ ድመቱን አልጋው ላይ በገመድ ጠፍሮ አይጥ ያሳድዳል ሊገላት አባሮ ላ'ይጥ ዱላ ይዞ እቃ ከሚመታ ስራዋን ትስራበት ድመቲቱን ይፍታ ፡፡ ከ የአገጭ ጢሞች መድብል (በለው ገበየው) @Davehymi @litratureforall
Mostrar todo...
👍
😂 1
❤ 2
ስንቱስ ከሀገር ወጣ ስንቱስ ተሰደደ ስንቱስ እስር ስቃይ ላንቺ ሲል ፈቀደ ስንቱስ ከዚህች አለም በህይወት አለፈ ላንቺ ሲል ላንቺ ሲል ............. በደምና በአጥንት ታሪክ እየፃፈ። @Davehymi @litratureforall Adem hussen
Mostrar todo...
👍 1
❤ 2
አሳብ ፨፨፨ << የሰው ልጅ አለ ሃሳብ ሊኖር አይችልም ጠቀመም አልጠቀመ የሰው ልጅ በቀናትና በሰአታት ልዩነት ብዙ ነገሮችን ያስባል ልዩነቱ ምንድነው አንዳንዱ ማሰብ እንደሚችል ያውቃል አንዳንዱ ደግሞ ማሰብ እንደሚችል ባያውቅም ያስባል ። አለማሰብ አይቻልም አሳብን እምነት ላይ መጣል ይቻላል ። እምነት የለም ብሎ ማሰብም ይቻላል...እሄንን ስታነብ ሶቅራጥስ ለምን "ማሰብ ስታቆም ማመን ትጀምራለህ" እንዳለ ማሰብህ አይቀርም እያሰብክ ነው ስለዚህ አለህ አየህ ሳያስቡ መኖር አይቻልም... >> / ማንነቱ ያልታወቀ የሶቅራጥስ ተማሪ ከተናገረው / ፨ ይህንን እሳቤ ጋስ ስብሃት ገ/እግዚአብሔርም እንደሚደግፈው "የሆነም ያልሆነ" የሚለው ጽሑፉ ላይ አንፀባርቆታል...! እርሶስ በዚህ እይታ ይስማማሉ? ለምን? ሐሳቦን ማካፈል ከፈለጉ አለን @Nirvana134 @Davehymi @litratureforall
Mostrar todo...
👍
❤ 3
Rediet Aseffa አርምሞ. . . ፍቅርና ህብረት፥ አጥሩን ካልጣሰ . ንስሃና ይቅርታ፥ ተበዳይ ካልካሰ . ፍርጠማና ጡንቻ፥ ማዕበል ካልገታ . ጥበብና ብስለት፥ ቋጠሮ ካልፈታ . ብትነቃም ብታውቅም አቅምህን ሰብቀህ፥ እንደ ናዝሬት ጌታ . ሀቅህን ባደራ የምታኖርበት፥ የምትሰጥበት፥ ለጊዜ ይሁንታ . ሽንፈት እንዳይመስልህ ቀን ቆጥሮ እሚያደባይ አቅም ነው ሃይል ነው ጉልበት ነው ዝምታ። @Davehymi @litratureforall
Mostrar todo...
👍 1
❤ 3
መስለውኝ ነበረ የበቁ የነቁ ያዉም የረቀቁ የሰው ፍጡሮች ለካ እነሱ ናቸው ጥሬ ጨው .... ጥሬ ጨው ጥሬ ጨዋዎች መፈጨት...መሰለቅ..መደለዝ..መወቀጥ...መታሸት...መቀየጥ ገና ሚቀራቸው እኔ የለሁበትም!> ዘወትር ቋንቋቸዉ፡፡ (( ደበበ ሰይፉ )) ነብስያህን አድምጥ ❤️❤️ ራስህን ሁን!!❤❤❤ ሁላችንም ምን አገባኝ የሚሉት....ፈሊጥ ተጠናውቶናል.. " የምናገባኝ ትውልድ ” ወኔያችንን ምን እንደሰለበብን ባይታወቅም ብዙ ነገራቶች ላይ እጅግ ግድ የለሽ ሆነናል ። ለማንም ምንም የማይመስሉ ነገራቶች እንኳ ሳይቀር የሚቆረቁረን ዜጋዎች ነበርን ። ዛሬስ እገሌ ሞተ ... ከሰውዬው ሞት ይልቅ የኛ ስሜት አልባ መሆን ይደንቃል ረሃብ ሰውን ፈጀው ስንባል ... ዝም!!! አረ ወጣቱ ተሰዶ ሀገር ያለ ተረካቢ ቀረች ... ዝምምም!!! ከተማዋ ቆሸሸች .... ዝምምም መንገድ ላይ የሚሸና ብናይም ... ዝምምም የትራፊክ አደጋ በዛ ... ጉዳያችን ስላልሆነ ዝምምም የእከሌ ቤት ፈረሰ .... የኛ እስካልፈረሰ አያገባንም ጎዳና ተዳዳሪዎች ብርድ ፈጃቸው ... ልጆቻችን አይደሉምና አይመለከተንም ስርቆት በዛ ... ዝምምም እኛ እስካልተሰረቅን ሁሉም ጋቢና ከተቀምጠ መኪናው ከጭቃ አይወጣም! ሰብሰብ ብላችሁ በመኪና ስትሄዱ በጭቃ ከተቀረቀረ የተወሰነው ሰው ወርዶ መግፋት አለበት፡፡ ሁሉም "አይ እኔ ውስጥ ነው የምቀመጠው" "ታየኝ እኮ ጭቃ ሲነካኝ" ካለ ተቀርቅራችሁ መቅረታችሁ ነው፡፡ ሌላው አማራጭ ሌላ መኪና መጥቶ ከጎተተ ብቻ ነው፡፡ አሁን የኢትዮጲያ ሁኔታ ጭቃ ውስጥ እንደተቀረቀረ መኪና ነው፡፡ የተወሰነው ያህል ዜጋ ወርዶ ለመግፋት ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡ ተራ እየወሰድን ልንገፋ እንችላለን፡፡ ግን አንዱ መጀመሪያ ላይ መጀመር አለበት፡፡ ሌላውም መቀጠል አለበት፡፡ በፉክክር ማንም የመጀመሪያ አልሆንም ካለ ጭቃ ውስጥ መሰንበታችን ነው፡፡ --------------------------------------- ሁላችሁንም ለነበረኝ ሸጋ ጊዜዎች አመሰግናለሁ .....ብዙ አስተማሪዎች አሉኝ እዚህ ቻናል ውስጥ...አሁን ከራስ ጋር ስብሰባ የሚገባበት ሰዓት ነው.....አሁን ነብስያን እያደመጡ ራስን በመሆን ገንዳ ከመሆን የሚሆኑበት ሰዓት ነው.......በመጨረሻም ቅዱስ ቁርኣን ምን ይላል መሰለህ...."ከችግር ቦኃላ ምቾት አለ" በብቻነት ኑሮ ብቻ ይወደዳል በብቻነት ኑሮ ብቻ የሚለው ቃል...ብቻ ይወደዳል ... @Davehymi @litratureforall
Mostrar todo...
👍
❤ 2