cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

🇪🇹AbuchuTech Village 🇪🇹🔐

ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! The channel is all about technology ideas, digital marketing, SEO, tech talk, interviews ideas are discussed here. Please Join us.

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Advertising posts
137Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ኢትዮጵያ በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ መሆኗ ተገለጸ ************************************ ኢትዮጵያ በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ከምስራቅ አፍሪካ አንደኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚትገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ገልጿል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ በአማካይ 50 በመቶ በማደግ ላይ ሲሆን፣ በ2010 ዓ.ም 4.1 ቢሊዮን ዶላር ከፍታ መድረሱ ተገልጿል፡፡ ካለፈው ዓመት ጀምሮ የአገሪቱን የንግድና የኢንቨስትመንት ከባቢ ሁኔታን ለማሻሻል የታቀዱ ተከታታይ ኢኮኖሚያዊ መሻሻዎች ወደ ትግበራ መግባታቸውን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡ በተያዘው ዓመት የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ሊጨምር እንደሚችል ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም፣ በኮቪድ-19 ምክንያት የተስተጓጎለውን የዓለም አቀፍ ንግድና ዓለም ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ተከትሎ ፍሰቱ ከሚጠበቀው በታች እንደሚሆን ይገመታል ተብሏል፡፡ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ትንተና መሰረት በ2012-13 ዓ.ም ዓለም አቀፍ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከ30 እስከ 40 በመቶ እንደሚቀንስ እንደሚገመት የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት እና አገሪቱ ከወጪ ንግድ እንቅስቃሴዎች አንፃር ያስቀመጠቻቸው ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል ተብሏል፡፡
Mostrar todo...
“ከአዲስ አበባ የሚነሳ መልካም ሐሳብ ሁሉንም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያዳርሳል” - ኢንጂነር ታከለ ኡማ ******************** የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቀን 2 ሚሊየን ዳቦ የሚያመርተው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፣ ከአዲስ አበባ የሚነሳ መልካም ሐሳብ ሁሉንም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያዳርሳል። የሸገር ዳቦ ፋብሪካ መገንባቱ የከተማውን ነዋሪዎች የኑሮ ጫና እንደሚቀንስ ም/ከንቲባው ተናግረዋል፡፡ አዲስ አበባ ላይ የአዲስ አበባ እናቶችን፣ ወጣቶችን እና የኅብረተሰቡን ጥያቄ የሚመልሱ ሥራዎችን አቅደን ወደ ሥራ ገብተናል ብለዋል ኢንጂነር ታከለ፡፡ ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌት ተቀን አግዘውናል ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። እንደ አሁኑ ከተጋገዝን ለሚቀጥሉት ዓመታት መንግሥት የያዘቸውን ሥራዎች በፍጥነት ማሳካት እንደሚቻል ኢንጂነር ታከለ ገልጸዋል፡፡ ምክትል ከንቲባው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የሚያመርታቸውን ዳቦዎች ለማከፋፈል ከ400 በላይ አውቶብሶች ለአዲስ አበባ እና ለአጎራባች ከተማዎች መዘጋጀታቸውን በፌስቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል። ሥራ አጥ ወጣቶች በምርቱ ሽያጭ ላይ እንደሚሰማሩም ጠቁመዋል። "የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ፕሮጀክት የሕልማችን ተሻጋሪነት፣ ሀሳባችንም መሬት የሚወርድ መሆኑን ቋሚ ምስክር ነው!" ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው በሥራው ላይ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
Mostrar todo...
የሸገር ዳቦ ፋብሪካ መገንባት በምግብ ራሳችንን የመቻል ጉዞ አካል ነው :- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ *************************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የተመረቀው የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፣ የሸገር ዳቦ የዳቦ ፋብሪካ ብቻ ሳይሆን በምግብ ራሳችንን የመቻል ፍላጎታችንን እንዲሁም ከድህነት ለመውጣት እና የተሻለ ሕይወት ለመኖር ያለን ፍላጎታችንን ማሳካት እንደምንችል ያሳየንበት ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ በ10 ወር ውስጥ ፋብሪካ ገንብቶ መጨረስ አይቻልም ነበር ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አሁን ግን ያንን ማሳካት እንደምንችል አሳይተናል ሲሉ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ለማሳካትም በተለያዩ አካባቢዎች ሰፋፊ የስንዴ እርሻዎች መጀመራቸውን እና የተሻለ ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችል ልምድም መቀሰሙን የገለጹት ዶ/ር ዐቢይ፣ “ዓላማችን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ስንዴን ከውጭ ማስገባት ማቆም ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ነገር ግን ስንዴ ማምረት ብቻ ሳይሆን ያንን ስንዴ ወደ ዳቦ መቀየር የሚያስችል ፋብሪካ ማቋቋም ስለሚያስፈልግ ያንን ለማድረግም ከተለያዩ ኩባንያዎች ጋር ውይይት መደረጉን ጠቅሰዋል። የሚዲሮክ ኢትዮጵያ ባለቤት ሼክ አል አሙዲ የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው በፍጥነት ወደ ሥራ በመግባታቸውም ምስጋናቸውን አቀርበውላቸዋል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንም ቀና ምላሽ መስጠቷን እና መለስተኛ የዳቦ ፋብሪካዎችን ለማስገባት በመስማማቷ አመስግነዋል። የዱባዩ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ አልናህያንም በአዲስ አበባ አነስተኛ ፋብሪካዎችን ለማቋቋም ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል። እነዚህ አሁን የተገነባው እና ወደ ፊት የሚገነቡ ፋብሪካዎች በቀን ዳቦ ለማግኘት ለሚያዳግታቸው ሕፃናት ዳቦ እንዲያገኙ የሚያስችሉ መሆናቸውን ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ ካለችበት ድህነት ወጥታ ወደ ብልፅግና እንድትጓዝ ከሁላችንም ወደ ፊት መመልከት ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ጆሯችንን፣ ልባችንን፣ ዓይናችንን ከምንፈልገው ዓላማ ላይ ማንሳት ወደ ኋላ ይመልሰናል እና ያንን ማድረግ አይገባንም ሲሉ አሳስበዋል። ወደ ኋላ የሚመለከት ሕዝብ ወደ ፊት መጓዝ ይሳነዋል ነው ያሉት። ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ኢትዮጵያን ለማስቆም የሚጮኹ ድምፆች ይኖራሉ እንጂ ኢትዮጵያን ከጉዞዋ የሚስያቆሙ ኃይሎች አይኖሩም" ብለዋል። ቻይና ከ20 ዓመት በፊት 1 ትሪሊየን ብቻ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ብቻ ነበራት፣ ወደ ፊት በመመልከቷ ግን ዛሬ ላይ 14 ትሪሊየን አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ያላት ሀገር ሆናለች ሲሉ በምሳሌነት ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ለወደፊቷ ዕድል ይሆናታል እንጂ እንቅፋት አይሆንባትም፤ ሁሉም ተባብሮ ከሠራ የዛሬ 10 ዓመት የምግብ ጉዳይ ዋና አጀንዳ ያልሆነባት ኢትዮጵያን መገንባት እንችላለን ብለዋል።
Mostrar todo...
የትራምፕ ደህንነት አባላት ኮቪድ-19 ተገኘባቸው! ባለፈው ቅዳሜ ቱልሳ ውስጥ የተካሄደው የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ላይ የተገኙ የደኅንነት አባላት ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተሰምቷል። የደህንነት አባላቱ ወደ ለይቶ ማቆያ የገቡት ከመካከላቸው የተወሰኑት የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስለተገኘባቸው መሆኑ ተገልጿል። መረጃውን መጀመሪያ ያወጣው ዋሽንግተን ፖስት ሲሆን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የፖሊስ ባለሥልጣን ደግሞ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት በጣት የሚቆጠሩ አባላት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ከምርጫ ቅስቀሳው በፊት የፕሬዝደንት ትራምፕ የቅስቀሳ ቡድን አባላትና ሁለት የደኅንነት ሰዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተዘግቦ ነበር። ፕሬዝደንት ትራምፕ፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ባልተገታባት ኦክላሆማ ግዛት የምርጫ ቅስቀሳ አደርጋለሁ ሲሉ ብዙ ወቀሳ ገጥሟቸው ነበር። በስብሰባው ቦታ የተገኙት ታዳሚዎችም ሙቀታቸው ተልክቶ እንዲሁም የእጅ ማፅጃ ፈሳሽ ተሰጥቷቸው ቢገቡም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ አልነበረም። የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት አንድ ሚሊዮን ሰዎች ለመታደም ቃል ገብተዋል ብለው የነበረ ቢሆንም 19 ሺህ ሰው በሚይዘው ስታደየም የተገኙት 6,200 ሰዎች ብቻ ነበሩ ሲል #BBC አስነብቧል። @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Mostrar todo...
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በሱዳን ጉብኝት እያደረጉ ነው❗️ ⚡️የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ጉብኝት እያደረጉ መሆናቸው የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ዛሬ አስታወቀ። ⚡️የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው እንደገለጹት የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በሁለቱ አገሮች ላይ ያተኩራል። ⚡️በተጨማሪም በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ትብብርና ውህደት ላይ እንደሚወያዩ አመልክተዋል። ⚡️ኤርትራ ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ ጋር በመሆንኢቢሲ በአፍሪካ ቀንድ አገሮች ትብብር በመሥራት ላይ መሆኗ ይታወቃል።
Mostrar todo...
በናይሮቢና ቤጂንግ የሚገኙ ኢትዮጵያ ኢምባሲዎች በግድቡ ዙሪያ ዌቢናር አዘጋጅተዋል! በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ “ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለቀጠናዊ ልማት እና ውህድት ያለው ጠቀሜታ” በሚል ርዕስ ዌቢናር ያካሂዳል። ዌቢናሩ ኬንያ ከሚገኙ የዓለም አቀፍ ሚዲያ ተቋማት ጋር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ለአፍሪካ ቀንድ የበለጠ መተሳሰር ስለሚኖረው ፋይዳ የፓናል ውይይት በ Zoom ያካሄዳል። በተመሳሳይ በነገው ዕለት በቤጂንግ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲም በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ዌቢናር አዘጋጅቷል። @tikvahmagbot @tikvahethmagazine
Mostrar todo...
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። #Ethiopia : በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኛ በረራን ለማቆም የተገደደው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቢዝነስ አማራጮቹን በመጠቀም ላይ መሆኑን አስታውቋል።በአየር መንገዱ የካርጎና ሎጀስቲክስ ማነኔጂንግ ዳሬክተር አቶ ፍፁም አባዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የኮሮና ፈተናዎችን ለመቋቋም ፊቱን ወደ ካርጎ ጭነት አገልግሎት ማዞሩን ተናግረዋል፡፡አቶ ፍፁም እንዳሉት በኢትዮጵያ ሰኔ መጨረሻ በጀት አመቱ የሚዘጋ በመሆኑ አየር መንገዱ ከካርጎ ብቻ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር ያገኛል ብለዋል፡፡ @NatnaelMekonnen7 Via Ethio FM
Mostrar todo...
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የዋና ዋና ስራዎችን ግምገማ በማጠናቀቅ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ #Ethiopia : የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ2012 በጀት ዓመት የታቀዱ ዋና ዋና ስራዎችን በመገምገም ለቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ። የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንደገለጹት፤ ትናንት የጀመረው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ግምገማ ዛሬ ተጠናቋል። በትናንትናው ዕለት የኢኮኖሚ ዘርፍ ስራዎች ተገምግመው ማጠቃለያ እንደተሰጠባቸው ያስታወሱት አቶ ንጉሱ፤ በዛሬው ዕለት የሰላምና ጸጥታ፣ የማህበራዊ እንዲሁም የውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ስራዎች መገምገማቸውን ገልጸዋል። ህግ በማስከበር ሰላምና ጸጥታ በማጎልበት የህብረተሰቡን ተደራሽነት በማረጋገጥ ረገድ ተጠናክረው መሰራት ያለባቸው ተግባራት መለየታቸውን ገልጸዋል። የተገኘው ውጤት በቀጣይ ለህብረተሰቡ የሚደርስ መሆኑን የገለጹት አቶ ንጉሱ፤ በግምገማው ሰፊ ውጤት መምጣቱና እጥረት የታየባቸው ጉዳዮች ተለይተው አቅጣጫ ተቀምጦባቸው ግምገማው መጠናቀቁን አመልክተዋል። ምክር ቤቱ ትናንት በነበረው መድረክ የኢኮኖሚ ዘርፍ ተብለው በተለዩ ዘጠኝ መስሪያ ቤቶች አፈጻጸም ገምግሟል። ግምገማው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ ዋና ዋና ዕቅዶች አፈጻጸም፣ የገጠሟቸው ችግሮች፣ መልካም ተሞክሮዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነበር። ኢዜአ @NatnaelMekonnen7
Mostrar todo...
የዴክሳሜታሶን (Dexamethasone) ጉዳይ: ዶ/ር ቴዎድሮስ ፀጋዬ ፤ የውስጥ ደዌ ሐኪም #ምንነት ❗️ በዘመናዊ ህክምና ታሪክ ውስጥ ፋና ወጊ (Ground breaking) ከሚባሉ ግኝቶች ውስጥ ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚመደበው ዴክሳሚታዞን (dexamethasone) ንን በአባልነት ያካተተው ኮርቲኮስቴሮይድ (Corticosteroids) ተብለው የሚጠሩ የመድሃኒቶች ስብስብ ወይም ቤተሰብ ጥቅም ላይ መዋል ነው። ይህ ስብስብ ሰፋ ሲል steroids ጠበብ ሲል ደግሞ glucocorticoids የሚል ስያሜ አለው። የመጀመርያው ህክምና ላይ የዋለው በላቦራቶሪ የተመረተ (synthetic) corticosteriod ኮርቲሶን (cortisone) ሲባል ተመርቶ ገበያ ላይ የዋለውም ከ60 አመታት በፊት ነበር። ⚡️በሰውነታችን ውስጥ የሁለቱም ኩላሊቶቻችን አናት ላይ ተፈናጥጠው የሚገኙ የአድሬናል እጢዎች (Adrenal glands) የሚባሉ ሆርሞን አመንጪዎች ይገኛሉ። እነዚህ እጢዎች ከሚያመርቷቸው ሆሮሞኖች መካከል Dexamethasoneንን ጨምሮ የሁሉም glucocorticoids አባት የሆነው ኮርቲሶል (cortisol) የተባለው ሆሮሞን ይገኝበታል። ዛሬ እንደ አዲስ ተአምራዊ ግኝት የአለም ዜና አውታሮች የተቀባበሉት dexamethasone በድንገት ኮሮናን ለማከም የተፈጠረ መድሃኒት ሳይሆን ለብዙ ሚሊዮን አመታት አብሮን የኖረ በእኛው ሰውነት የሚመረት ሆሮሞን ላይ መጠነኛ ማስተካከያ (modification) በማድረግ የተዘጋጀ መድሃኒት ነው። #ታሪክ❗️ የመጀመርያው የcortisone ታካሚ Rheumatoid arthritis የሚባል የመገጣጠሚያ ችግር ተጠቂ ነበር። ይህ ታካሚ በወቅቱ በህክምናው ያሳየው ለውጥ እና መሻሻል ፈጣንና አስደናቂ ነበር። በዚህም የተነሳ በህክምናው ማህበረሰብ ዘንድ በጊዜው የተፈጠረው ጉጉት እና ተነሳሽነት ለሁሉም አይነት በሽታዎች መፍትሔ ሊሆን እንደሚችል እስከከመተንበይ እና ሙከራ እስከማድረግ ዘለቀ። በቀጣይ አመታትም ለበርካታ የጤና ችግሮች አይነተኛ መፍትሔ ሊሆን ይችላል በሚል በሰፊው ጥቅም ላይ ዋለ። የአለም የዜና አውታሮችም በጊዜው "እውነተኛው ምትሀተኛው ፈዋሽ" በማለት አድናቆታቸውን ከጫፍ እስከ ጫፍ አስተጋቡ። #የጎንዮሽ_ጉዳት❗️ ጉድ እና ጅራት ወደኋላ እንዲሉ corticosteroids ላይ የተጣለው ተስፋ እና ግርግር ከጥቂት አመታት መዝለል አልቻለም። በቀጣዮቹ አመታት የመድሃኒቱ የጎንዮሽ ጉዳት እና መዘዝ በብዛት መስተዋል ጀመረ። ይሄው መድሃኒት ጥቅም ላይ መዋል በጀመረ በ10 አመት ጊዜ ውስጥ ተስፋው በስጋት ተተካ። ለሁሉም የሰው ልጅ ደዌዎች ፈውስ ይሆናል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት መድሃኒት ሁሉም የሰውነት ክፍሎች እና ስርዓቶች ላይ በሚያስብል ደረጃ መርገምቱን ያወርደው ጀመረ። ⚡️ ከመርገምቶቹ በጥቂቱ የስኳር በሽታ ፣ ደም ግፊት ፣ የዐይን መታወር ድረስ ሊያደርሱ የሚችሉ Glaucoma እና cataract ፣ ከፍተኛ ውፍረት እና ተያያዥ ጉዳቶቹ ፣ የበሽታ የመከላከል አቅም መቀነስ ፣ የስነ ልቦና ችግር (psychosis) ፣ የአጥንት መሳሳት ፣ ወዘተ ይገኙበታል። በተጨማሪም በጎንዮሽ ጉዳት ምክንያት ወይም በሌላ መድሀኒቱ በድንገት በሚቆምበት ጊዜ በመጀመርያ መሻሻል ያሳዩ ስሜቶች በብዙ እጥፍ ተባብሰው መታየት ጀመሩ። ይባስ ብሎም እነኚህን መድሀኒቶች የጤነኛውን የAdrenal gland ተግባር በማዛባታቸው ምክንያት መድሃኒቱ በድንገት ሲቆም እነዚሁ እጢዎች የሆርሞን ማመንጨት ስራቸውን በአግባቡ ማካሄድ ባለመቻላቸው ብዙዎችን ለህልፈት የዳርገ ጦስ (complication) እስከማስከተል ደረሰ። ⚡️በዓመታት ውስጥ በተገኘው የተሻለ ግንዛቤም በዚህ ዘመን dexamethasone ንን ጨምሮ ሌሎች Glucocorticoids ለበርካታ የበሽታ ዓይነቶች ህክምና ጥቅም ላይ በመዋል ይገኛሉ። አደጋ እና ጥቅማቸውን ባመዛዘነ መልኩ። ከነዚህም ውስጥ የአስም በሽታን ጨምሮ በርከት ያሉ የዓየር ቧንቧ እና የሳንባ በሽታዎች ይገኙበታል። #ኮሮና እና #ዴክሳሚታሶን ❗️ ኮሮና እንደሌሎች በርካታ ተላላፊ በሽታ በሰውነት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ሁለት እጥፍ (two fold) ነው ቀጥተኛ እና ተዘዋዋሪ። ቀጥተኛው በቫይረሱ መራባት ሂደት ውስጥ የሚከሰተው ጉዳት ሲሆን ተዘዋዋሪው ደግሞ ሰውነታችን ራሱን ከበሽታ/ወራሪ ለመከላከል ብሎም ለማጥቃት በሚያደርገው እንቅስቃሴ የሚፈጠር የጎንዮሽ ጉዳት ነው። ግርምት ሊያጭር በሚችል ሁኔታ አብዛኛው ጉዳት የሚደርሰው ከቀጥተኛው ይልቅ በሁለተኛው ተዘዋዋሪ መንገድ መሆኑ ነው። እጄን በእጄ እንዲሉ። ⚡️ከተከሰተ የመንፈቅ ዕድሜ ያስቆጠረው የዘመናችን ወረርሽኝ- ኮሮና ሚሊዮኖችን አዳርሶ መቶ ሺዎችን ወደመቃብር አውርዷል። በዚህ የጭንቅ ጊዜ ውስጥ ይሄ ነው የሚባል ፈዋሽ መድሃኒትም ሆነ መከላከያ ክትባት አልተገኘለትም። በአንዳንዶቹ ሲገለፅ እንደምንሰማውም Dexamethasone የኮሮና ፈዋሽ መድሃኒት አይደለም። በፅኑ የታመሙ የኮሮና ህሙማንን ሞት በመቀነስ ረገድ ግን ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ያልወጣው የጥናት ውጤት ማመላከት ችሏል። #ማሳሰብያ❗️ ዴክሳሚታሶን በጥናት ላይ የዋለው የኮሮናን ቫይረስ ለማጥፋት እና በቫይረሱ ላይ ቀጥተኛ ካለው ተጽዕኖ ሳይሆን የመድሀኒቱን የፀረ-ብግነት ባህሪ ታሳቢ በማድረግ በኮቪደ-19 ላይ ያለውን አስተዋጽኦ ለማጥናት ነው፡፡ እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ይህ መድሀኒት ኦክስጅን በሚፈልጉ ታካሚዎች ላይ ይሞቱ ከነበሩት አምስት ሰዎች አንድ ሰው እንዲሁም በመተንፈሻ አካል መሳርያ ላይ ሆነው ከሚሞቱት ሶስት ሰዎች የአንድ ሰው ሞት መቀነሱ ተስፋ እንዲጣልበት አድርጓል፡፡ ⚡️ሆኖም ግን ዴክሳሜታዞን የኮቪድ-19 መድኃኒት ያለሆነ፣ ለመከላከል የማይጠቅም እና የራሱ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት እንዳለው ከግንዛቤ ሕብረተሰቡ ያለሀኪም ትዕዛዝ መድኃኒቱን እንዳይወስድ እንዲሁም የፋርማሲ እና ሌሎች የጤና ባለሙያዎችም የዴክሳሜታዞን መድኃኒትን ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ለደንበኞቻቸው መሸጥ እንደሌለባቸው በአጽንኦት እናሳስባለን፡፡ ©ጤና ሚኒስቴር 🦁• @ThinkAbyssinia •🦁
Mostrar todo...