cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የስነ ልቦና ልዕቀት

Posetiv tinker መሆን ይፈልጋሉ እግዳውስ join and shere

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
852Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🌿የረቀቁ ሀሳቦች (osho views) 🔱ምን ይዞ እንደሚመጣ ለማይታወቀው መጪው ጊዜ መፈንጠዝና በምኞት ፈረስ መጋለብ ካላቆማችሁና፣ ትናንትናንና ነገን ትታችሁ ዛሬን መኖር ካልጀመራችሁ ነፃ አትወጡም። ነፃነት አሁን እዚህ ናት። ያለህበት ጊዜ ብቻ ናት እውነት ህልውና ያላት። መጪው ጊዜ ምኞትህ፣ ያለፈውም ጊዜ ትዝታህ ነው። ህልውና የላቸውም። የአሁኑን ጊዜ በንቃት ማሳለፍ ንቃተ ሂሊናህና ካለፈውና ከመጪው ጊዜ ሰብስበህ በአሁኑ ጊዜ ላይ ማትኮር ማለት የነፃነትን ጣዕም ማወቅ ነው። 🔱ብዙ ጊዜ ትወድቃላችሁ። ይህ ለክፉ አይሰጥም። እንደገና ተነስታችሁ ቁሙና ዳግም ያለመውደቅን ተማሩ። የበለጠ ንቁ። ስህተት መስራታችሁ አይቀርም ፣ ግን አንድ ስሄተት ደግማችሁ አትስሩ። ይህን የምላችሁ ሰው ጥበብን የሚያገኘው በዚህ መልኩ ነው። አጭር ሆናችሁ አትቅሩ። የምትችሉት ርቀት ላይ ለመድረስ ሞክሩ። ሊያኮራ የሚችለውን ብቃት ይዞ ያልተፈጠረ ማንም ሰው የለም። አንድን አዲስና ውብ ነገር የመውለድ፣ህላዊን የበለጠ የማበልፀግ ብቃትን ሳይዝ የተፈጠረ ሰው የለም። 🔱አንተ ትክክል መሆን አለመሆንህን ለማወቅየህሊናህ እና የድርጊትህ እንጂ የሌሎች ሰዎች ድጋፍና ምስክርነት አያሻህም ። ትክክለኛውን እንጂ አብዛኛውን ለመሆን አልተፈጠርክም። ትክክል ባትሆን እንኳን መቶ በመቶ የሌላ ሰው ቅጂ አትሁን።" ውስጣዊ ማንነቱ የተከፋፈለ ግለሰብ በአብሮነት የማይስማማ ማህበረሰብን ይፈጥራል፤ንቃተ-ህሊና ያለው ግለሰብ ያልተከፋፈለ ውስጣዊ ማንነት ሲኖረው የተዋሃደ ማህበረሰብንም ይፈጥራል።ንቃት የሌለው ማንነት ለዘላለማዊ ሙት ነውና ንቁ!!!!** 🔱አንድን ሰው የግል ንብረት አድርጎ እንደማሰብ መርዘኛ ነገር የለም ሰውን የግል የማድረግ መሻት የውሸት ፍቅር ነው ከእንዲህ አይነቱ ስሜት ቢያንስ ጥላቻ ይሻላል በጥላቻ ውስጥ ውሸት የለም ከዚያ በላይም ጥላቻ አንድ ቀን ፍቅር ሆኖ ሊቀየር ይችላል የሰውን ልጅ ግን የግል የማድረግ ፍላጎት ፈጽሞ ወደ ፍቅር ሊቀየር አይችልም ፍቅር ማለት በምትወደው ሰው ነፍስ ውስጥ ራስህን መግደል ነው ፍቅር ማለት ሞት ነው። 🔱መላው አለም እኔን መቃወሙ አያስጨንቀኝም። ዋናው ነገር ተሞክሮዬ ተቀባይነትን ማግኘቱ ነው። ምን ያህል ሰዎች ከኔ ጋር እንደሆኑ ለማወቅ ቁጥራቸውን አልመለከትም። ትኩረት የማደርገው በተሞክሮዬ ተቀባይነት _ የሌላ ሰው ቃላትን እንደበቀቀን እየደገምኩ መሆን አለመሆኔን ወይም የምናገራቸው ነገሮች ከገዛ ራሴ የመነጩ መሆን አለመሆናቸው ላይ ነው። ንግግሬ በገዜ ራሴ ተሞክሮ ውስጥ ከሆነ፤ የደሜ፣ የአጥንቴና የመቅኔዬ አካል ከሆነ፣ መላው አለም በአንድ ወገን ሊሆን ቢችል እንኳን፣እኔ ትክክል ነኝ። እነሱ ግን ተሳስተዋል። ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም። እኔ ትክክል መሆኔ እችዲሰማኝ የእነሱ የድጋፍ ድምፅ አያስፈልገኝም። የሌሎችን ድጋፍ የሚሹት የሌሎችን አመለካከት የያዙት ብቻ ናቸው። 🔱ፍቅር በራችሁን አንኳኩቶ ያውቃል? በጭራሽ! ምክንያቱም ገና ፍቅር መስጠት አልቻላችሁም። ማስታወስ ያለባችሁ የሰጠነው ሁሉ ወደ እኛው ተመልሶ እንደሚመጣ ነው። ይህም ከህይወት ህጎች አንዱ ነው።መላው ዓለም ከገደል ማሚቶ የተሻለ አይደለም። ጥላቻ እንሰጣለን፣ ጥላቻም ወደኛው ተመልሶ ይመጣል። ሌሎችን እንሳደባለን ከዛም ስድብ ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። እሾህ ስንሰጥ እሾህ ወደኛው ተመልሶ ይመጣል፡፡ የምንሰጠው ሁሉ በተለያዩ መንገዶች ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። ፍቅርን ካካፈልንም እንደዚሁ በተለያዪ መንገዶች ተመልሶ ወደኛው ይመጣል። ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች ፍቅር ወደ እኛ ተመልሶ ካልመጣ ፍቅር እንዳልሰጠን ማወቅ አለብን፡፡ፍቅር የምትሰጠው እንጂ የምትቀበለው አይደለም። ••●◉Join us share◉●•• ═════❥━━━❥═════ 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫 🎖 @cekuaa 🎖
Mostrar todo...
🌿ዓለም በክፉ አስተሳሰብ ልትወድም እየተንደረደረች ነው፡፡ ሕይወት ጥድፊያ ነው፡፡ ኑሮ ድካም ብቻ ሆኗል፡፡ እዚህም እዚያም ግፊያ ነው፡፡ መተረማመሱ፣ መረጋገጡ፣ መገፈታተሩ የሁላችንም ባህሪ ሆኗል፡፡ ተጠባብቆ ጉዞ፣ ተቻችሎ ኑሮ ቀርቷል፡፡ ሩጫው ወዴት እንደሆነ አይታወቅም፡፡ አካሄዱን ቆም ብሎ የሚያስብ፣ ሃሳቡን የሚመረምር፣ ሰውነቱን የሚፈላሰፍ ብዙ የለም፡፡ ማንም ማንንም አይምርም፡፡ ጥቅሙን ለማግኘት ሲል የማይደረገውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ የሕይወት ግቡ በሀብት ማሸብረቅ፣ ሆዱን መሙላት፣ የሚያምር ልብስ መልበስ፣ ቁስ መሰብሰብ፣ በቅንጡ መኪና መሽከርከር፣ በዘናጭ መኖሪያ ቤት ውስጥ መኖር ብቻ ነው፡፡ በሚያምር መንፈስ፣ ደስ በሚያሰኝ አኗኗር፣ ልብን በሚያረካ ምግባርና ተግባር፣ በዕውቀትና በጥበብ ያሸበረቀ ጎጆ ውስጥ ለመኖር የሚሻ ሰው መንምኗል፡፡ ፍላጎቱ ሆድ ብቻ ነው፡፡ ፖለቲካውም የሆድ ነው፡፡ ለጭንቅላቱ የሚያስብ፤ ለነፍሱ የሚቆረቆር፣ ለመንፈሱ የቆመ ጠፍቷል፡፡
👉🏻(እ.ብ.ይ.)

❥..........🦋⚘🦋.............❥ ••●◉Join us share◉●•• ═════❥━━━❥═════ 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫 🎖 @cekuaa 🎖
Mostrar todo...
ሰውና ~ ፍልስፍናው

☞የዕውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ነው፠ ~ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል✔️ #የፍልስፍና_ስራ_ሰውን ለተፈጠረበትየሰውነትአላማ ማብቃትነው ❖ ጥንታዊ ፍልስፍናዎች< ❖ አስገራሚ አውነታዎች< ❖ ሳይኮሎጂ< ❖ አስደማሚ ታሪኮች< ❖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተንትኖት< ☞ጠቅልሎ የያዘ ለነፍስና ለስጋ የሚበጁ ለሰላማዊ ህይወትም ሆነ ለምድራዊ ቆይታ መሠረት የሚሆኑ አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ያደርሳል

"መጀመሪያ የራስህን ድክመትና ጥንካሬ ተቀበል፤ ከዛ ራስህን ውደድ በመጨረሻ ሁሌም ወደፊት ተጓዝ! መብረር የምትፈልግ ከሆነ ወደታች የሚጎትቱህን ነገሮች ሁሉ ማራገፍ አለብህ" ይለናል ሮይ ቲ ቤኔት የተባለ ደራሲ።

በዚህ አለም አስደሳቹ ነገር የራሳችንን እጣ ፋንታ መወሰን የምንችለው ራሳችን ነን። ፈጣሪማ በራሱ አምሳል ፈጥሮ ለማንም ፍጥረት ያልሰጠውን ነፃ ፍቃድ ሰጠን። ምርጫው በእጃችን ነው!


••●◉Join us share◉●•• ═════❥━━━❥═════ 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫 🎖 @cekuaa 🎖
Mostrar todo...
ሰውና ~ ፍልስፍናው

☞የዕውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ነው፠ ~ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል✔️ #የፍልስፍና_ስራ_ሰውን ለተፈጠረበትየሰውነትአላማ ማብቃትነው ❖ ጥንታዊ ፍልስፍናዎች< ❖ አስገራሚ አውነታዎች< ❖ ሳይኮሎጂ< ❖ አስደማሚ ታሪኮች< ❖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተንትኖት< ☞ጠቅልሎ የያዘ ለነፍስና ለስጋ የሚበጁ ለሰላማዊ ህይወትም ሆነ ለምድራዊ ቆይታ መሠረት የሚሆኑ አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ያደርሳል

🌿ተስፋ እና እምነት የእምነት የቅርብ ወዳጁ እና ጓደኛው ተስፋ ነው። ተስፋ ነገ ሲሆን እምነት ደግሞ ዛሬ ነው። ተስፋ ነገን አይቶ ሰው እንዲደሰት የማድረግ አቅም ሲኖረው እምነት ደግሞ ተስፋውን ሄዶ ያመጣውና ዛሬ ላይ ያደርገዋል። ተስፋ ነገ ላይ ሆኖ መደሰት ሲሆን እምነት ደግሞ ዛሬ ላይ ሆኖ መደሰት ነዉ ። 📘ሬማ እና ሎጎስ ❥..........🦋⚘🦋.............❥ ••●◉Join us share◉●•• ═════❥━━━❥═════ 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫 🎖 @cekuaa 🎖
Mostrar todo...
ሰውና ~ ፍልስፍናው

☞የዕውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ነው፠ ~ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል✔️ #የፍልስፍና_ስራ_ሰውን ለተፈጠረበትየሰውነትአላማ ማብቃትነው ❖ ጥንታዊ ፍልስፍናዎች< ❖ አስገራሚ አውነታዎች< ❖ ሳይኮሎጂ< ❖ አስደማሚ ታሪኮች< ❖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተንትኖት< ☞ጠቅልሎ የያዘ ለነፍስና ለስጋ የሚበጁ ለሰላማዊ ህይወትም ሆነ ለምድራዊ ቆይታ መሠረት የሚሆኑ አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ያደርሳል

🌿#እኔ_የምፈራው. . .
እኔ የምፈራው. . .
"ምን አለኝ?" ከሚል ጥያቄ ይልቅ "ሰው ምን ይላል?!" በሚል ስጋት ተውርሮ ሕልምን ማጨናገፍ! አድገው ጽጌረዳ ሳይሆኑ በለጋነት መርገፍ!
ዓለም በፈጠረችው ሕግጋት ታስሮ የራስን ዓለም ሳይፈጥሩ ማለፍ!

#እኔ_የምፈራው. . .
ደስታዬን በሰዎች ላይ መገንባት!
ከሰው ሲስማሙ ጮቤ መርገጥ፣ሰው አለኝ ብሎ ደረትን መንፋት! ሰው የጠፋ ቀን ማንነትን ፈልጎ ማጣት፣እውነትን መካድ፣መንገድ አልባ ሆኖ ከንፋስ ጋ መጥፋት! 
 .
#እኔ_የምፈራው. . .
በሚተኩኝ ሰዎች ዙሪያ ማንዣበብ!
"አይተኬ ነኝ" ብለው ሲደነቁ ከርመው፣ ከታች ተወርውሮ አፈር ድሜ መብላት፣እንደ ዘበት. .. እንደ ዋዛ ተዘንግተው መና ሆኖ መቅረት!
.
#እኔ_የምፈራው. . . 
ባልተፈጠሩበት መስክ ዕድሜን ማሟጠጥ!
የሚወዱትን ሰውተው፣የኔ በማይሉት መስክ ላይ ያለ ሰበብ መረገጥ! በሕሊና ጩኸት፣በፀፀት ረመጥ እየታቀጠሉ በሞት ሽረት ህመም ዕድሜ-ዘመን መራወጥ!
.
#እኔ_የምፈራው. . .
በሰው እጅ መውደቅ!
እኔ የምፈራው. . 
ፍርሃቴን ብቻ እየቆጠርኩ፣ፍርሃቴን ብቻ እየፈራሁ፣!ፍርሃቴን ብቻ እየተመንኩ መኖር!

••●◉Join us share◉●•• ═════❥━━━❥═════ 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾 💫 https://t.me/philoso_phy 💫 🎖 @cekuaa 🎖
Mostrar todo...
ሰውና ~ ፍልስፍናው

☞የዕውቀት መጀመሪያ አለማወቅን ማወቅ ነው፠ ~ማወቅ ደግሞ ከማሰብ ይጀምራል✔️ #የፍልስፍና_ስራ_ሰውን ለተፈጠረበትየሰውነትአላማ ማብቃትነው ❖ ጥንታዊ ፍልስፍናዎች< ❖ አስገራሚ አውነታዎች< ❖ ሳይኮሎጂ< ❖ አስደማሚ ታሪኮች< ❖ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተንትኖት< ☞ጠቅልሎ የያዘ ለነፍስና ለስጋ የሚበጁ ለሰላማዊ ህይወትም ሆነ ለምድራዊ ቆይታ መሠረት የሚሆኑ አጅግ በረካታ ሀሳቦችን ለናንተ ያደርሳል

Manuhe Christian literature ✍️ የስነ ፅሁፍ ስራዎቻችሁን እና አስተያየቶቻቹን ለመላክ @manuhecl ያግኙን። Let's praise the Lord with all we have🙏 https://t.me/manuheta
Mostrar todo...
(ማኑሄ ስነ-ፅሁፍ)Manuhe Christian literature ✍️

በስነ-ፅሁፍ ፦ ወንጌል ይሰራል ፦ ክርስቶስ ይገናል ፦ መንፈስ ይታደሳል ፦ ጌታ ይከብራል ኑ አብረን ጌታን እናገልግል የስነ ፅሁፍ ስራዎቻችሁን እና አስተያየቶቻቹን ለመላክ @manuhecl ያግኙን።

ዛሬ አጠር ያለ ሀሳብ ላካፍላቹ ህይወትን እንደ ፒያኖ 🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹🎹ይሄ ፒያኖ እና ህይወት ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው። በህወት መገድ ውስጥ ደስታን ብቻ ሁሌ ማግኘት አንችልም ደግሞም ሁሌ ሀዘን አይሆንም ህይወት ትርገም ሚኖረውም ሁለቱም አንድ ላይ ሲሆኑ ነው።🎹🎹ነጩ key ደስታን ጥቁሩ ደሞ ሀዘንን ያመለክታል ። ግን ፒያኖ ሁለቱንም ከለሮች ሲያሙአላ ነው ውብ ድምጽ ምናገኘው ልክ እንደዚህ ህይወትም ሀዘንም ደስታም ሲቀላቀል ነው ውብ ሚሆነው።።።
Mostrar todo...
የተስፋ እስር ቤት “ሰው ከምግብ ውጪ አርባ ቀን መኖር ይችላል፤ ከውኃ ውጪ ሶስት ቀን ሊኖር ይችላል፤ ከአየር ውጪ ስምንት ደቂቃዎች መኖር ይችላል፤ ከተስፋ ውጪ ግን ከአንዲት ደቂቃ በላይ መኖር አይችልም” – Hal Lindsey በአሁን ሰአት ያለህበትን ወዳጅነት፣ የፍቅር ግንኙነትት፣ ስራ፣ ንግድም ሆነ ማንኛውንም በየእለቱ ጠዋት መንጋቱን የምትጠብቅበትን ነገር ተመልከተው፣ በዚያ ነገር ውስጥ ያለህ ተስፋ ነው እንደዚያ የሚደርግህ፡፡ በአንድ ነገር ላይ ተስፋ እንደሌለህ እንዳሰብክ ወዲያውኑ አቅም የማጣት ስሜት፣ እንቅልፍ መጣትና አንዳንዴም መኖር ያለመፈለግ ስሜት ይጫጫንሃል፡፡ ተስፋ ማለት የነገ መሄጃ ነውና ተስፋ ከሌለ ወደየት ይኬዳል? ተስፋ የጉልበት ምንጭ ነው፡፡ ተስፋ ዛሬ ካለህበት ሁኔታ ወጥተህ ነገ እንዲሆን ከምታስበው ነገር ጋር አጣብቆ የሚያቆይህ ወሳኝ ሂደት ነው፡፡ ሆኖም ተስፋ ለአንዳንድ ሰዎች የሕመም ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምክንያት የማይሞላን ተስፋ ከሰዎች በመጠበቅ ከአመት እስከ አመት ሲኖሩ ነው፡፡ ሰዎች በተለያየ ጊዜ በተስፋ እንድንጠብቃቸው ቃል በመግባት ያስጠብቁናል፡፡ የምንወዳቸውንና የምናምናቸው ሰዎች በተስፋ መጠበቅ የጨዋዎች ምልክት ነው፡፡ ነገር ግን የተገባው ተስፋ ከመጠን ያለፈ ፈተና ውስጥ በሚጨምረን ጊዜና ዝም ብለን የምንጠብቅ ከሆነ፣ የተስፋ እስር ቤት ውስጥ እንዳለን ማወቅ አለብን፡፡ ወይ በተስፋው ምክንያት በጉጉት አንኖር፣ ወይም ደግሞ አንደኛችንን የራሳችንን መንገድ አንከተል፣ እንዲሁ ተስፋውን በመጠበቅ እንደ እስረኛ እንከርማለን፡፡ ሰዎች በማይሞላ ተስፋ ውስጥ አንጠልጥለውን እየኖርን እንደሆነ ከተሰማን ሰዎቹን እውነተኛነት ለመመዘን የሚከተሉት ጥያቄዎች መጠየቅ እንችላለን፡- 1. ተስፋ የሰጡን ሰዎች ጉዳዩን የሚያስታውሱት እኛ ስናነሳላቸው ብቻ ሲሆን 2. ተስፋውን የመጠበቃችን ሁኔታ አመታቶቻችንንና እድሜያችንን የሚበላ ሲሆንና ስጋት ውስጥ ስንገባ 3. ሰዎቹ የሚያደርጉት ነገር ከምንጠብቀው ተስፋ አንጻር ተቃራኒ ሲሆን 4. ስለተሰጠን ተስፋ ለመወያየት ስንፈልግ (ልክ እንደተጠራጠርናቸው በማሳየት) በእኛ ላይ የቁጣና የንዴት ስሜት የሚያሳዩ ከሆነ ከላይ የተጠቀሱትንና መሰል ሁኔታዎች ከተመለከትን መስጠት ከምንችላቸው ምላሾች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል . . . 1. ግልጽ ውይይት የማድረግ ጉዳይ አጽንቶ በመጠየቅ የሚቻለውን ያህል መታገስ 2. ሁኔታዎች ግልጽ ባለመሆን ከቀጠሉ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ አቋምን ግልጽ ማድረግ 3. ልብን ከስብራት ለመጠበቅ መዘጋጀትና ከተገባልን ተስፋ ውጪ መኖር እንደምንችል ራስን ማሳመን 4. የተገባውን ተስፋ በማይጣረስ መልኩ የግል ሕይወትን እቅድ በማውጣት ራስን የመቻል ሂደት መጀመር በማይሞላ ተስፋ ድባብ ውስጥ ለአመታት መኖር አደገኛ የሆነ “የተስፋ እስር ቤት” ነውና ዛሬውኑ ተነሳና ከዚህ እስር ቤት ውጣ!
Mostrar todo...
Positive Thinking  is a mental attitude in wich you expect good and favorable results. In other words, #positive_thinking is the process of creating thoughts that create and transform energy into reality. A positive mind waits for #happiness, #health and a #happy_ending in any situation. @Rastafarian_life
Mostrar todo...
ሁለቱ ክህሎቶች፡- ሁለት አይነት ክህሎቶች አሉ፡- አንደኛው የሞያ ክህሎት ሲሆነ፣ ሌላኛው ግን ማሕበራዊ ክህሎት ነው፡፡ የመጀመሪያው ስራን በስኬታማነት እንድንሰራ ሲያደርገን፣ ሁለተኛው ግን ማሕበራዊ ግንኙታችን የሰመረ እንዲሆን ያግዘናል፡፡ ማንኛውም የሞያ ክህሎት ከማሕበራዊ ክህሎት ውጪ ብዙ ርቀት አያስኬደንም፡፡ ለማብራሪያውና ለግንዛቤው መጽሐፉን ማንበብ ጠቃሚ ነው፡፡ ከመጽሐፉ የተቀነጨበ . . . ምን ዋጋ አለው?! የሕክምና ባለሞያው ምን ያህል አዋቂና “ፈዋሽ” ቢሆን፣ ለሕመምተኞች ካለው ርህራሄ ተነስቶ ሕብረተሰቡን ከማገልገል ይልቅ ለክብሩና ለጥቅሙ ካደረ ምን ዋጋ አለው … የሕግ ባለሞያው ሕግን ጠንቅቆ ቢያውቅ፣ ከፍትህ ይልቅ በጠማማነት የሚገኘውን የግል ጥቅም ካስቀደመ ምን ዋጋ አለው … መሃንዲሱ በፈጠራ ብቃቱና በቅልጥፍናው በሰው ሁሉ ተፈላጊ ቢሆን፣ ከጥራትና ከደህንነት ይልቅ አስተርፎ የሚያተርፈውን ካሳደደ ምን ዋጋ አለው … ሂሳብ አዋቂዋ ቁጥርን ከቁጥር በማጋጨትና በማስማማት ብቃቷ ወደር ባይገኝላት፣ በስንፍናዋና በግድ የለሽነቷ የድርጅቱን ስራ በሰዓቱ የማድረስ ፍላጎትና ዲሲፕሊን ከሌላት ምን ዋጋ አለው … የሕብረተሰቡና የሃገር መሪዎች ምን ያህል ፖለቲካን ቢያውቁ፣ ደጋፊ ቢሰበስቡና በፖለቲካ ሳይንስ ቢራቀቁ፣ እውነተኞች፣ ሕዝብን አስቀዳሚና ሕብረተሰቡን አገልጋይ ለመሆን ራሳቸውን ካላቀረቡ ምን ዋጋ አለው … በእውቀት፣ በብቃትና በሞያ ላይ ብቻ የምናተኩርበት ጊዜ አልፎ የስነ-ምግባር፣ የተግባቦትና የመልካም ዜግነት ጉዳይ እያሳሰበን የመጣበት ዘመን ነው፡፡ አንዱን ይዘን ሌላኛውን ችላ ስንል የሚያስከትለውን ቀውስም እጅ በእጅ እየተቀበልን ስለሆነ መፍትሄውን ፍለጋ በሚገባ ልናስብበት ይገባል፡፡
Mostrar todo...