cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

Gulele inspection Directorate

Gulele inspection directorate

Mostrar más
Advertising posts
1 352Suscriptores
-124 hours
-37 days
+1530 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

ለአዲስ ቅድመ አንደኛ ተቋማት የማመልከቻ ቅጽ 2016
Mostrar todo...
Photo from Fikiru Gebissa
Mostrar todo...
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2016 ዓ.ም የቴ/ሙያ ማስልጠኛ ተቋማት የስታንዳርድ ኢንሰፔክሽን ውጤት ትንተና ግኝት ሪፖርት አቀረበ፡፡ (መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬከቶሬት በ2016 ዓ.ም በጀት አመት በተካሄደው የቴ/ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ትንተና ግኝት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ በመክፈቻ ንግግራቸው የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ተቋማቱ በግብዓት፣ በሂደት እና በውጤት በእያንዳንዱ ስታንዳርዶችና አመልካቾች ያሉበትን ደረጃ እና የታዩ ጥንካሬዎችና ክፍተቶችን እንዲሁም የመፍትሄ ሀሳቦችን በማመላከትና ክትትል ቁጥጥር እና ድጋፍ በማድረግ ጥሩ የሰሩትን እውቅና በመስጠት ድክመት ያለባቸውን ደግሞ ክትትል ድጋፍ አላማ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ከዛ ካለፈ ደግሞ ተጠያቂ በማድረግ ብቁና ተወዳዳሪ የቴ/ ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋም እና የሰው ሀይል ልንፈጥር ይገባል ብለዋል፡፡
Mostrar todo...
የቅ/ፅ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬከቶሬት ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ አለሙ ግኝት ሪፖርቱን ያቀረቡ ሲሆን የትንተናው ዋና አላማ፣ የቴ/ሙ ትምህርትና ስልጠና ኢንስፔክሽን አላማዎች፣ የኢንስፔክሽን ስነድ ትንተና አስፈላጊነት፣ የኢንስፔክሽን ትኩረት መስኮች መለኪያ ክብደትና አመልካች ብዛት የሚያሳይ መረጃ፣ የቴ/ሙ ትምህርት ስልጠና ኢንስፔክሽን አፈፃፀም ደረጃዎች ፣ ተቋማት ኢንስፔክሽን ከትምህርት ፖሊሲ፣የ2016ዓ.ም በኢንስፔክሽን ትግበራ ሂደት የታዩ ጥንካሬዎች ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ መፍትሄዎች እና ዋና ዋና ግኝቶች ላይ ዝርዝር መረጃ አቅርበዋል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ በጉለሌ፣ አራዳና ቂርቆስ ክ/ከተማ በሚገኙ ህጋዊ እውቅና ፍቃድ ባላቸው 56 አጫጭር ቴ/ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ የተካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡ በመጨረሻም በኢንስፔክሽ ግኝት የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ የቴ/ሙያ ተቋማት የምስክር ወረቀት ተበርክቷል፡፡ #ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302 #ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F #ድረ_ገጽ; educoc.gov.et #ቴሌግራም https://t.me/AAEQOCAA
Mostrar todo...
የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን. 2,688 likes · 7 talking about this. Education website

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የ2016 ዓ.ም የቴ/ሙያ ማስልጠኛ ተቋማት የስታንዳርድ ኢንሰፔክሽን ውጤት ትንተና ግኝት ሪፖርት አቀረበ፡፡ (መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት በትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬከቶሬት በ2016 ዓ.ም በጀት አመት በተካሄደው የቴ/ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ትንተና ግኝት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍቅሩ ገቢሳ በመክፈቻ ንግግራቸው የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ተቋማቱ በግብዓት፣ በሂደት እና በውጤት በእያንዳንዱ ስታንዳርዶችና አመልካቾች ያሉበትን ደረጃ እና የታዩ ጥንካሬዎችና ክፍተቶችን እንዲሁም የመፍትሄ ሀሳቦችን በማመላከትና ክትትል ቁጥጥር እና ድጋፍ በማድረግ ጥሩ የሰሩትን እውቅና በመስጠት ድክመት ያለባቸውን ደግሞ ክትትል ድጋፍ አላማ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ከዛ ካለፈ ደግሞ ተጠያቂ በማድረግ ብቁና ተወዳዳሪ የቴ/ ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋም እና የሰው ሀይል ልንፈጥር ይገባል ብለዋል፡፡
Mostrar todo...
የስብሰባ ጥሪ በጉለሌ ፣ አራዳ እና ቂርቆስ ክ/ከተማ ለምትገኙ ህጋዊ የዕውቅና ፍቃድ ያላችሁ የአጫጭር ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት በሙሉ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ትም/ስ/ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት በ2016 ዓ.ም የተካሄደውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ውጤት ትንተና ግኝት ሐሙስ መጋቢት 19/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ስለሚካሄድ የተቋሙ ባለቤት እና ሀላፊ(ዲን) የጉለሌ ፣ አራዳ እና ቂርቆስ ክ/ከተማ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የአራዳና ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት ቅ/ጽቤት ስራ አስኪያጅ ፣ የዕውቅና ፍቃድ ዳይሬክተርና ቡድን መሪ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሠዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አራዳና ቂርቆስ ቅ/ጽ/ቤት 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን ፡፡ ሰዓት ይከበር!! የስብሰባው ቦታ አድራሻ ፡ - አራት ኪሎ ከብርሀንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት ድንቅ ስራ ህንጻ 8ኛ ፎቅ ፡፡
Mostrar todo...