cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቤተ መፅሀፍ

አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደ አንተ ይመጣሉ 😁ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና ብቻ ነው😊።✔✔✔✔📖📖📖📖📖📖📖📖📖 ☞https://telegram.me/ChefawoloEthiopia

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
627Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

- ፕሮፍ መስፍን (ዋርካው) ተሸኝተዋል - ለዚህች ሀገር ላበረከቱት ሁሉ በሳይቴክ ቤተሰቦች ስም ሳናመሰግን አናልፍም! ነፍስዎት በገነት ትኑር!
Mostrar todo...
የማለዳ ራእይ! (በእውቀቱ ስዩም) ናፍቆትሽ ፀናብኝ ብየ ስልክልሽ ‘አይዞህ ' አይባልም መከሰት ነው እንጂ በገሀድ ወይ በህልም ! ካጨሽ አሰናብቺ ትዳር ካለሽ ፍቺ ለኔ ለምመኝሽ ሁሉን ነገር ስጪ የህሊና ቀጪ የልቦና ስሜት ይሉንታና ሀሜት ያገር ሰው ሽሙጥም ከምኞቴ አይበልጥም :: ተሊቀመላኩ ክንፍ ተበድረሽ ነፋስ ቀድመሽ በረሽ ባለሁበት አገር እንደ ሸዋዚንገር ብረት ለበስ ጡንቻ ባንድ ርግጫ ብቻ የቤቴን በር ሰብረሽ ዐይነ ርግብሽ ወድያ ቀሚስሽ ወደ ላይ ወደኔ በጥድፍያ ወዳልጋው በዝላይ በጀርባየ ሁኘ ከእግሮቼ መካከል የጠላ ምልክት አንቺ ጆሮ ሆነሽ እኔ ሎቲ ሆኘ-ተጣጥሞ ስክት ! እንዲህ እያሰበ ገላየ ሲቸገር መጣሁ ትያለሽ ስል “አይዞህ “ ብሎ ነገር፤ የማለዳ ራእይ፤ ምኞቴን በማመን በገሀድም ይሁን፤ ወይም በሰመመን አሳትፊኝ አልሁ እንጂ ከገላሽ በረከት፤ ከሙቀት ከለዛው የቃል ምፅዋትማ ሞልቷል በየታዛው!
Mostrar todo...
ፍቅር እና ግጥም
የኢሰመኮ ጋዜጣዊ መግለጫ ******************** የፍርድ ቤት ውሳኔ አለመከበር ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አደጋ ነው! **************************************************** አላስፈላጊ እስር ማስቀረትና የዋስትና መብት ማክበር ያስፈልጋል! *********************************************** (አዲስ አበባ፤ መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም.) የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በአንድ መቶ ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፤ እስካሁን ድረስ አለመፈታታቸውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የሚከተለውን ብለዋል ፡፡ ‹‹የሰብዓዊ መብቶች መከበር ዋና ዋስትናው የፍርድ ቤት ውሳኔ መከበር በመሆኑ፤ አቶ ልደቱ አያሌውን ጨምሮ በፍርድ ቤት የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸውና የዋሰትና ሁኔታውን አሟልተው ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሰጠላቸው ታሳሪዎች በሙሉ በአስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊፈቱ ይገባል››
Mostrar todo...
💚💛❤️
ስለ አዲሱ የመቶ ብር ኖት ጥቂት ነገሮች ♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️ በአሁኑ ሰዓት አዲሱ የመቶ ብር ኖት ላይ አንዳንድ የተሳሳቱ ወሬዎች በዚሁ በማህበራዊ ሚዲያ ምህዳር ላይ እየተሰራጩ መሆኑን በማስመልከት ትክክለኛውን መረጃ ከሚመለከታቸው የብሄራዊ ባንክ አመራር አካላት ጋር ለማጣራት ሞክረናል፡፡ ስለሆነም አዲሱ የመቶ ብር ኖት ላይ የተሰመረው የደህንነት መስመር ወይም ምልክት በተመሳሳይ መልኩ የተሰመረ ካለመሆኑ እና መስመሩ አንበሳው ላይ ወጣገባ ብሎ የተሰመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አንዳንንዶችን የተሳሳተ ግንዛቤን እንዲይዙ አድርጓል፡፡ በመሆኑም ይህ በቀይ መስመር ውስጥ የምትመለከቱት የደህንነት ምልክት ብሩን ወደ ብርሀን አቅጣጫ አዙራችሁ ስትመለከቱት በስውር አንድ ሙሉ መስመር ታያላችሁ፡፡ ትክክለኛው መቶ ብር በዚህ መስመር ላይ የ100፣ የኢብባ፣NBE እንዲሁም በግዕዝ የመቶ ቁጥር ይታያችኋል:: ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች የደህንነት ምልክቶች እንደተጠበቁ ሆነው ወደ ብርሀን አቅጣጣጭ አድርጋችሁ ስትመለከቱ መስመሩ ያልተቆራረጠ እና ያልተዛነፈ ቀጥ ያለ መስመር መሆኑን ካረጋገጣችሁ ብሩ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ ትችላላችሁ፡፡ መረጃውን ለሁሉም ያጋሩ!
Mostrar todo...
💚💛❤️
ዘ ዊኬንድ ከ15 በላይ እውቅ የጥበብ ሰዎች የተዘረዙ ሲሆን ከትውልደ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰብ የተገኘው 'ዘ ዊኬንድ' አቤል ተስፋዬ ከዝርዝሩ አናት ላይ ተቀምጧል። ጥቁር አሜሪካውያኑ ተዋናያኖች ገብርኤላ ዩኒየን እና ቴይለር ፔሪ በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት [2019] የታይም መጽሔት 100 ተጽእኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተው እንደነበረ ይታወሳል። ከፍተኛ ተከፋይዋ ሴት ስፖርተኛ የሆነችው ጃፓናዊቷ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቿ ናኦሚ ኦሳካ የታይም የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መካተት ችላለች። ካረቢያን ውስጥ በምትገኘው ሄይቲ ከተወለዱት አባቷ እና ከጃፓናዊት እናቷ የተገኘችው ናኦሚ በቅርቡ የዩኤስ ኦፕን የሜዳ ቴኒስ ውድድርን ማሸነፏ ይታወሳል። የፎርሙላ ዋነ (Formula 1) ተወዳዳሪ የሆነው እንግሊዛዊው ሉዊስ ሃሚልተን በዝርዝሩ ውስጥ ተካቷል። ሉዊስ ሃሚልተን 'የብላክ ላይቭስ ማተር' እንቅስቃሴን በፎርሙላ ዋን ወድድሮች እና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ አጉልቶ በማውጣት እንቅስቃሴው በርካቶች ጋር እንዲደርስ ምክንያት ሆኗል። የመብት ተሟጋቹ ናታን ሎው የዓመቱ ተጽአኖ ፈጣሪ ግለበሶች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል። የዴሞክራሲ መብቶች አቀንቃኙ ናታን ምንም እንኳ በስደት ከሆንግ ኮንግ እርቆ ቢገኝም፤ የቤይጂንግ መንግሥት የሆንግ ኮንግን የራስ ገዝ ነጻነት እምኖ እንዲቀበል ጥረት ያደርጋል።
Mostrar todo...
ተጨማሪ 👇👇
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እና ታዋቂው ዘፋኝ 'ዘ ዊኬንድ' በታይም መጽሔት የዓመቱ የዓለማችን 100 ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ። ከኮሮናቫይረስ የዓለምን ሕዝብ ለመታደግ ከፊት መስመር ሆኖ ትግል የሚያደርገውን የዓለም ጤና ድርጅትን የሚመሩት ኢትዮጵያዊው ዶ/ር ቴድሮስ እና ከትውልደ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰብ የተገኘው ካናዳዊው ዘፋኝ አቤል ተስፋዬ በመድረክ መጠሪያው 'ዘዊኬንድ' በዝርዝሩ ውስጥ ይገኛሉ። እውቁ ታይም መጽሔት በየዓመቱ በተለያዩ ዘርፎች የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ ናቸው የሚላቸውን የ100 ሰዎች ስም ዝርዝርን ይዞ ይወጣል። በዚህ ዝርዝር ውስጥ የአገራት እና የድርጅት መሪዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ የእንቅስቃሴ መሪዎች፣ አርቲስቶች እና ስፖርተኞች እንዲሁም ጸሐፊዎች ይካተቱበታል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በታይም መጽሔት የ2020 ተጽእኖ ፈጣሪ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት ሰዎች በእኩልነት የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ባበረከቱት አመራር ነው። "አስቸጋሪ ወቅቶች ማንነታችን ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ። ኮቪድ-19 ለዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ወሳኝ ከስተት ነው። ልምድ ያካበቱት ተመራማሪው እና የሕብረተሰብ ጤና መሪው ዶ/ር ቴድሮስ ለኮቪድ-19 የበለጠ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ካልጠበቅን ሁላችንም ለበሽታው ተጋላጭ እንደሆንን ያውቃሉ" ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ለታይም የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ ዝርዝር ውስጥ እንዲከታቱ ያጩት ናይጄሪያዊቷ ጎዚ ኦኮንጆ-ኢዌላ ጽፈዋል። ዓመቱ ለዶ/ር ቴድሮስ የፈተናና የስጋት ባቻ ሳይሆን ከፍተኛ እውቅናን የተጎናፈፉበት ነው። ከእነዚህም መካከል ትናንት የ2020 "ብሪጅ ሜከር አዋርድ" ሽልማታቸውን ከፈረንሳይ መቀበላቸው ይታወሳል። በዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱት የአገራት መሪዎች መካከል የጀርመኗ መረሂተ መንግሥት አንጌላ መርክል፣ የብራዚሉ ፕሬዝደንት ጄይል ቦልሶናሮ፣ የሕንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ የዲሞክራት የፕሬዝደንት እጩ ጆ ባይደን፣ የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ፣ የፓሪስ ከተማ ከንቲባ አን ሂዳልጎ፣ በአሜሪካ የዩናትድ አረብ ኤሜሬትስ አምባሳደር የሱፍ አል ኦታይባ ተጠቃሽ ናቸው።
Mostrar todo...
👇ተጨማሪ👇
ዶ/ር ቴድሮስ እና ዘ ዊኬንድ በታይም መጽሔት የዓመቱ ተጽእኖ ፈጣሪ ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ
Mostrar todo...
ተጨማሪ 👇👇
አቶ ልደቱ አያሌው ከእስር እንዳልተፈቱ ተገለጸ። የአቶ ልደቱ ጠበቃ አቶ አብዱል ጀባር ሁሴን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት በ100 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ብሩ የተከፈለ ቢሆንም ዛሬ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ብናመራም የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ አልተከበረም ብለዋል። የምርምራ ቡድኑ አቶ ልደቱ እንዲፈቱ ባስተላለፈው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ላይ ምንም ማለት አንችልም መባላቸውን ጠበቃው ነግረውናል። በመሆኑም የፍርድ ቤቱ ትዕዛዙን እንዲያስከብር ለፍርድ ቤት አቤቱታ እናስገባለን ሲሉም ተናግረዋል። (ethiofm)
Mostrar todo...
ተጨማሪ መረጃ
በኢትዮጵያ ከ1 ሺህ 300 በላይ የጤና ባለሙያዎች ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል❗️ ⚡️በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ከ1 ሺህ 300 በላይ የጤና ባለሙያዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ⚡️ሚኒስቴሩ በነገው ዕለት የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሕሙማን ደህንነት ቀን አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። ⚡️መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴሩ የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ያዕቆብ ሰማን እንዳሉት ኮሮናቫይረስ በተለይ በሽታውን በመከላከል ሥራ ግንባር ቀደም በሆኑት የሕክምና ባለሙያዎች ላይ መጠነ ሰፊ ችግር አስከትሏል። ⚡️በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 1 ነጥበ 3 ሚሊዮን የሚሆኑት የጤናው ሴክተር ሠራተኞች ናቸው። ⚡️“በኢትዮጵያም ኮቪድ-19 ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 1 ሺህ 311 የሚሆኑ የጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል 700 የሚሆኑት አገግመው ወጥተዋል፤ ቀሪዎቹ በሕክምና ተቋማት ይገኛሉ” ብለዋል አቶ ያዕቆብ። ⚡️ሁለት የሕክምና ባለሙያዎችም ለሞት መዳረጋቸውን ነው ያስታወሱት። ⚡️ነገ ለሁለተኛ ጊዜ በአገሪቱ የሚከበረው የሕሙማን ደህንነት ቀንም ቫይረሱ የተገኘባቸው ወገኖቻቸውን ሌት ተቀን እያገለገሉ ላሉ ባለሙያዎችና አጋሮቻቸው ክብርና ምስጋናን በመስጠት እንደሚከበር ተናግረዋል። ⚡️በዓሉ የጤና ባለሙያዎች በሥራ ላይ የሚገጥማቸውን ችግር በመፍታትና በማገዝ እንዲሁም ራሳቸውን ከበሽታ ጠብቀው ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ በሚያስችሉ ፕሮግራሞች የሚከበር መሆኑንም ነው አቶ ያዕቆብ ያመለከቱት። ⚡️ “በተጨማሪ በዓሉ በቫይረሱ የተጠቁ የሕክምና ባለሙያዎችና ሠራተኞችን በመጠየቅና በማበረታታት ይከበራል” ብለዋል።
Mostrar todo...
እንዴት ነህ አማራ? *★★★* «ዘውድአለም ታደሰ» #Zewdalem_Tadesse #ETHIOPIA | ~ ስለ ዐማራ ለመጮኽ ዐማራ መሆን አይጠበቅብኝም። ሰው መሆን በቂ ነው። [ ዘመድኩን በቀለ ] እንዴት ነህ ግዮኑ - እንዴት ነህ አማራ አንት የታሪክ ዶሴ - አንት የሰሜን ጮራ ተነሳብህ አሉ - የተሳለ ሳንጃ - የጨከነ ካራ እንዴት ነህ አማራ? ገደሉህ ይሉኛል - አረዱህ ይሉኛል ህመምክን ስሰማ - መንፈሴን ያመኛል ደከመ ይሉኛል ፥ መረረው ይሉኛል ላድንህ ባልችልም ፥ የቀመስኩት ሁሉ ይጎመዝዘኛል!! እንዴት ነህ አማራ? አንተ ያገር ካስማ - አንተ ያገር አጥር ግማሽ ጎኔ ሞተ - ሞትህን ስቆጥር ተሸለተ ሲሉኝ - መኖሬን ጠላሁት ሳቅና ደስታዬን - በቅፅበት አጣሁት!! እንዴት ነህ አማራ? ደምህን እረጭተህ - ፈትተህ የለቀቅከው ፊደል ቀርፀህ ሰጥተህ - ቀድመህ ያሳወቅከው ሰላምክን ሲያውከው ... አጥንት ከስክሰህ - ባቀናሀት ሐገር ትገባበት ጨንቆህ - ሰርክ ስትቸገር በነፃ ገበያ ፥ በዘመነ ቁማር ፥ በርካሽ ሲሸጡህ ዘርህን መንዝረው ፥ጎሳህን አስልተው ፥ ከመሃል ሲያወጡህ እርጥብ አፈር ምሰው የቀበሩህ ለታ ሰላሜ እንደዝናር ከነፍሴ ተፈታ!! እንዴት ነህ አማራ? ጀግናማ ጀግና ነህ ፥ ምንሽር ትራስህ ለሐገር የምትተርፍ ፥ እንኳን ላንድ እራስህ ገላህ ቢራቆትም ፥ ክብርህ ሁሌ ሙሉ ካንተ የተጣላ - ፍፃሜው አያምርም - መውደቅ ነው እድሉ!! የተነሳህ ለታ አጥር ላያቆምህ እሳቱ ላይፈጅህ ከሰማየ ሰማይ ተቀብቷል እጅህ!! እንዴት ነህ አማራ?
Mostrar todo...
💚💛❤️ኢትዮጵያ💚💛❤️
Inicia sesión y accede a información detallada

Te revelaremos estos tesoros después de la autorización. ¡Prometemos que será rápido!