cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

አማርኛ ቅኔ

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
827Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Gojo ጎጆ News የፍቅር ደብዳቤ የኔ ፍቅር ከህወሃት ሴራ የገዘፈ ሰላምታዬ ይድረስሽ። ካየሁሽ እለት ጀምሮ ሀሳቤን እንደ ሜቴክ ሰርቀሽ፤ ልቤን እንደ ጌታቸዉ አሰፋ በቀዝቃዛ እስር ቤት አስረሽ እያሰቃየሽኝ ነዉ። የኔ ማር በተለይ ደግሞ እንደ ዶክተር አቢይ የሚማርከዉ ንግግርሽ፣ እንደ ህወሃት አገዛዝ በማንአለብኝነት የሚንጎማለለዉ ዳሌሽ፣እና አባይ ፀሀየ ከሰረቀዉ ስኳር በላይ የነጣዉ ጥርስሽ እኔን እንደ ክንፈ ዳኘዉ እጅ በፍቅር ካቴና አስሮኛል። የኔ ፍቅር እኔ ያላንቺ መኖር እንደማልችል እያወቅሽ አንቺ ግን እንደ ዶክተር ደብረጽዮን መጣሽ ሰልሽ መሄድ፣ ሄድሽ ስልሽ ደግሞ መምጣት የዘወትር አመልሽ ሆኗል። ዉዴ በፍቅርሽ እንደ ያሬድ ዘሪሁን አንገቴን ብታስደፊኝም አንቺን እንደ ህዳሴዉ ግድብ በተስፋ መጠበቅ ሳይታክተኝ፤ እንደ በረከት ስምዖን በስጋት ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ በተስፋ ዉጭ ዉጭዉን አያለሁ። የኔ ስጋት ግን እንደጠፋዉ አዉሮፕላን እስከመጨረሻዉ ተሰዉረሽ ልቤን እንደ ተሰረቀችዉ መርከብ በባህር ላይ አንሳፍፈሽ እንዳታጉላዪዉ ነዉ። በተረፈ እንደ ኢትዮ-ኤርትራ በፍቅር ተደምረን እንደ ኢሳያስና አቢይ ዘወትር ለመገናኘት ያብቃን እላለሁኝ የኔ ብርቱካን። አፍቃሪሽ ተደማሪዉ ~ይመቻችሁ~ የተመቸው ሼር ያድርጋል መልካም ምሽት
Mostrar todo...
Mostrar todo...
_____ | _| | |__ | ID | |____ |_________| |'''''\_/'''''| | |\_/| UBARAK |__| |__| 4 u & ur family!! Takabelellahu min weminkum!
Mostrar todo...
🇪🇹ሐሙስ ሚያዝያ ፳፰ ፳፻፲፫ ዓ.ም ━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━ #ክረምት_እና_ህይወት መታመን ያቃተው ማመን ያቃተተው ፥ የወዳጅ ልቡና ሸኝቶ ሰው መርሳት ፥ ከቶ አይችልምና በተሰናበትሽው ፥ በሄድሽ በማግስቱ ይህንን ከተበ ፥ ትዝ ብሎት የጥንቱ ብታገላብጭው ፥ የልቤን ማህደር ዞረሽ ብትጎበኚ ፥ በህሊናዬ በር እንቡጥ ለጋ ፍቅር ፥ ከሄደ ሰው ጋራ ያልተነካካ እምነት ፥ ከክህደት ጋራ የሴት ልጅ ድንቅ ውበት ፥ ከጭካኔ ጋራ ከማህደሩ ግርጌ ፥ በስተመጨረሻ ያንቺው መንገድ አለ ፥ እንደ ማስታወሻ ወትሮም የተኛሽው ፥ የሳሳ አንጀት ላይ ነው የተገላበጥሽው ፥ ቁስል ልቤ ላይ ነው የዳበስሽው ደረት ፥ የተኛሽበቱ በሂያጅ መንገደኛ ፥ ተሰብሯል አጥንቱ የተበደለ ነው ፥ ልቤ ቂም የያዘ በእልፍ ቢላዋ ፥ የተገዘገዘ የተኛሽበት ክንድ ፥ የነካሽው ገላ ጡንቻው የዛለ ነው ፥ ደም-ስሩ የላላ በሄድሽበት ይቅናሽ ፥ ያብዛልሽ ምህረቱን ለምጄዋለሁኝ ፥ በጋ እና ክረምቱን ገና አንድ ብዬ ፥ ፍቅርን ስጀምረው የህይወቴ ፀደይ ፥ ስስ ሙቀት ነበረው ከውበትሽ ጋራ ፥ ከተሽሞነሞነ ብራ ቀን ጀመረ ፥ ፍቅር መኸር ሆነ ሙቀትሽ አሳስቶኝ ፥ ከገላሽ ስጠጋ ግለቱ አቃጠለኝ ፥ አብሮ ገባ በጋ ከዚያማ ቀጥሎ ትርጉሙ ሲጠፋኝ ፥ ግዜ ጥንቡን ጥሎ ከሰማዩ ጋራ ፥ ፊትሽ ተቀየረ ከፀሀይዋ ጋራ ፥ ልብሽ ተሻገረ ከክረምቱ ጋራ ፥ ልቤ ብቻ ቀረ ዝናብ ነፋስ በረድ ድምፁ የሚያስጨንቅ ፥ ሀይለኛ ነጎድጓድ በዚያ በነሀሴ ፥ በዚያ በጨለማ አረቄ እየጠጣሁ ፥ ጉበቴ እስኪደማ ዝናብ እየዘነበ ፥ ጎርፍ እየወረደ እየተብሰለሰልኩ ፥ በመጣ በሄደ እናም... ትላንት በሞቅሽበት ፥ በደመቅሽበት ቤት ይህ ነው ፥ ህይወት ማለት ፀደይ መኸር በጋ የማያልቅ ክረምት ​​ ┈┈┈┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ ✍🏽© ምልዕቲ ኪሮስ ╰══•••┈ ┈ ┈•◦●◉❖◉●••┈┈ ┈ ምንጭ ➸ ባላንባራስ ለመቀላቀል 👉🏽 @yefkrmenged 👉🏽 @yefkrmenged ┏─━─━─━─━≪♡≫━─━─━─━─┓ ❘ ❝ ሰው፡ከሆኑ፡በቂያችን፡ነው። ❞ ᴀ ❘
Mostrar todo...
የፍቅር መድረሻው! (አኑ) ሂድ ስትለው መጣ፣ ውረድ ሲባል ወጣ፣ ውጣ ሲባል ሲወርድ፣ አንዴ እሷን ሲጠላ ፣ አንዴ ደግሞ ሲወድ፣ ከራሱ ተጣልቶ፣ ከራሱ ተኳርፎ፣ ነብሱን ይረግማታል በአንዲት ሴት ተለክፎ (ያቺ ሴት) የሆነ ዘመን ላይ ፍቅረኛው ነበረች በፍቅሩ የከነፈች፣ ስለሱ የምትኖር፣ ስለሱ የምትሞት! እሱም የሚያፈቅራት ከጎና ማይጠፋ ፍቅር እንደማግኔት ከሷ ጋር አጣብቆት! አንድ'ዜ በሀይቅ አንድ'ዜ በየብሱ አንድ'ዜ በአየር ፍቅርን ሸክፈው ሲንሳፈፉ ነበር። (ዛሬ) ተጣልተው ተኳርፈው ደግሞም ተለያየተው አንድ ፍቅራቸውን ሁለት ቦታ ከፍለው ጎጆውን አፍርሰው ተነጣጥለው አሉ ትላንትን ታቅፈው እንዲኹ ይኖራሉ። (እሱ) ጎዳና ዳር ካለ አንድ ካፌ ገብቶ ለካፌ አሳላፊው ፣ አዞ ማኪያቶ ( ሁለት ነው ያዘዘው) አንደኛው ለራሱ ሁለተኛው ደግሞ ለሄደች ፍቅሩ እርግጥ ነው የለችም በምዕናብ ሊያኖራት ከባዶ ወንበሩ (እንዲኽ ነው ሀሳቡ) ትዕዛዙ እስኪመጣ ጋዜጣ ያነባል የጋዜጣው ርዕስ ጥያቄ ይጠይቃል (ጥያቄው) ከአላህ እና ከእግዜር የቱ ነው ትክክል? ከርዕሱ በታች የቄስና የሼኽ የፈገግታ ምስል ፣ (እዚህ ጋር) ቄሱም ሆነ ሼኹ የፃፉትን ፅህፈት፣ የሰበኩት ስብከት፣ ካነበበ ኋላ ደረሰ ከእውነት! (እውነቱ) የቄሱም የሼኹም የኣላህም የእግዜሩም ቃሎች ሲመረመር ፍቅር ነው መነሻው፣ ፍቅር ነው መድረሻው፣ ከፍቅር ለራቀ የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣ ( ያዘዘው ማኪያቶ ከመጣ ቆይቷል ጋዜጣ ሲያነብ ረስቶት ቀዝቅዟል) ሳይጠጣው ተነሳ ጋዜጣውን ይዞ መንገዱን ጀመረ ሚጓዝበት መንገድ ማይሽር ፣ የማይጠፋ ከአንዲት ፍቅሩ ጋራ ትዝታ ነበረ። እርምጃው ፈጠነ ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፣ ይሄዳል ፍቅሩ ቤት ደረሰ ፣ በሯን ደበደበ፣ እየሮጠች ወጣች፣ የበፊት ህይወቷ ፊትለፊቷ ቆሟል የምትለው ጠፋት ፍርሀት ነብሷን ዋጣት እ ሱ ተንበርክኳል እግሯ ስር ተገኝቷል በስስት ፣ በፍቅር ሽቅብ አይኗን ያያል ይቅርታ የሚል ቃል ከአንደበቱ ይፈልቃል እ ሷ አለቀሰች አይኗን እንባ ወረሰው፣ አካላቷን ሙሉ ደስታ አንቀጠቀጠው፣ ተነሳ አቀፈቹ ሲያያት ሳመቹ አ ፈ ቅ ር ሀ ለ ው አለች እየሳቀች ጋዜጣውን አየ ፍቅር ነው መነሻው ፣ ፍቅር ነው መድረሻው ፣ ከፍቅር ለራቀ የይቅርታ ቃል ነው መምጫ መመለሻው፣ ይኽን አስታውሶ ፊቱን ብርሀን ሞላው። ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ @yefkrmenged @yefkrmenged
Mostrar todo...
አማርኛ ቅኔ : : ዛሬ ሌቱ ረዝሞ መሆን ባልቻልሽበት ፣ የክፉ ቀን ደራሽ ጨረቃ ፊት ቆሜ ፣ ያየሁትን ላውራሽ ፤ ይኸውልሽ ዓለሜ... ያቺ የምሽቷ ከዓይን ቢርቅ ቤቷ ከልብም ርቃ ከነፍስም ርቃ ማቅ ለብሳ የተኛች ፣ መልክ አልባ ጨረቃ ልክ እንደ ሰው ሁላ እሷም ካልጋው ውላ የመውደድን ደዌ ፣ ፍቅርን ታማ ብትሞት ደመናውን ምሼ ፣ አልቅሼ ቀበርኳት፤ በሰማይ ዶፍ እንባ ፣ በሌት ለሞት ዳርኳት ፤ እናማ ከዚህ ማጥ ፣ ከማይነጋ ተስፋ ምናል የማይጨልም ፣ ምን አል የማይከፋ ፤ ከጽልመት ተጋብተው ፣ ፍካት አልባ ቀናት ንጋት እንደሁ ቀርቷል ፣ ጸሀይ የሌሎች ናት ፤ ከቀንሽ ልትቀርቢ ፣ በሌቱ ስትርቂኝ ካጣሁት እልፍ ይልቅ ፣ ያለኝን ጠይቂኝ ፤ ከሞላው አዱኛ ፣ ሳለሽ ከነበረኝ ከመውደድሽ በቀር ፣ ምን ይሆን የቀረኝ፤ ተስፋ ይሉት ተረት ብርሃን የሌለበት ከህይወት ተኳርፏል ተፋቷል ከውበት ፤ ደግሞም ፍካትን ልንሸምት ከተስፋ ጎጇችን ፣ ሲመሽ እንደወጣን ቁልቁል ብቅ እያለች ፣ ፍቅር ምታጣጣን ያቺ የምሽቷ... ያንቺን ምሽት ዘርፋ ፣ የኔንም ቀን ሰርቃ በመቅረትሽ ብሶት ፣ ሞታለች ጨረቃ በቃ፡፡ ★ኢዛና መስፍን @amaregn @amaregn @amaregn
Mostrar todo...
#የዘመኑ_ተማሪ “እ....ሺ ተማሪዎች” አሉ መምህሩ በክፍለጊዜያቸው ተሜ'ን ሊያስተምሩ፡- “እ....ሺ ተማሪዎች ዛሬ ምንማረው ስለ ድንቅነሽ ነው፡፡ ድንቅነሽ አፅም ናት እስትንፋስ የሌላት፤ ድንቅነሽ ህያው ናት ዘመን የማይገላት፤ ድንቅነሽ ታሪክ ናት ጥንትን የምትዘክር፤ ድንቅነሽ እውነት ናት ነገን ምትመሰክር፡፡ የኛዋን ድንቅነሽ ፈረንጆች ሲጠሯት ሉሲ ነው የሚሏት፡፡ ሉሲ አሮጊት ነች ድሮን የምታሳይ ፤ ሉሲ ኮረዳ ነች የዘመኑ አማላይ ፤ ሉሲ የዓለም ነች የሰው ዘር ሁሉ እናት፧ ሉሲ የአገር ልጅ ነች የኢትዮጵያ ኩራት፡፡ ቅርስ ነች፣ ውርስ ነች የተፈላጊ ሐብታም፤ ውበት ነች፣ ቆንጆ ነች የአጥንት ደም ግባታም፡፡ በ'ርግጥ ተማሪዎች ስለ ሉሲ ታሪክ ስለ ህያዋ አፅም እንኳን በዚች ሰዓት በአርባ ደቂቃ አቅም ዘመናትን ሙሉ ቢነገር፣ ቢነገር፣ ቢነገር አያልቅም:: ምክንያቱም በግልፅ እያየናት ድንቅነሽ ሚስጥር ናት፤ በእጅ እየነካናት ድንቅነሽ ሩቅ ናት፤ በአጭሩ ድንቅነሽ ድንቅ ናት፡፡” ( ስለ ሉሲ ታሪክ - ስለ ሉሲ ጥቅም - ስለ ሉሲ ገላ በሚችሉት መጠን - በአርባ ደቂቃ ውስጥ ካስረዱ በኋላ ) “መልካም ተማሪዎች በዛሬው ገለፃ (በድንቅነሽ ዙሪያ) ግልፅ ያልሆነላችሁ ከመውጣቴ በፊት ጥያቄ ካላችሁ?” አሉ መምህሩ ወደ ተማሪ እጆች በዓይን እያማተሩ፡፡ አንዱ እጁን አወጣ ጸጉሩን እያሻሸ “እዛጋ!” አሉ ጋሼ (ተማሪው ቀጠለ ከርዳዳውን ፀጉሩን እየጠቀለለ)፡- "ቴንኪው ቲቸርየ! እውነት ለመናገር የድንቅነሽ ታሪክ በጣም ፀድቶብኛል የርስዎ ገለፃም እንደተለመደው ግልፅ አድርጎልኛል፤ ግን ያልገባኝ ነገር ይህች ተዓምረኛ ሉሲ 'ምትባለው የአለምን ሳይንቲስት በሐሳብ ከፋፍላ ምታወዛግበው የሰው ዘር ሁሉ እናት ፤ የኢትዮጵያ ኩራት፤ የአለም ልዩ ፍጡር፤ የእኛነት ምስክር ፤ ወዘተ ወዘተ...... ተብላ እየተጠራች የምትወደሰው የኛዋ ድንቅነሽ ብሔሯ ምንድን ነው???” 🔘ሙሉቀን ሰለሞን🔘 @amaregn @amaregn
Mostrar todo...
ቁዝም . . የዘመን መገለጥ ...የጀምበር ወጋግታ እኩል አይታይም ለእኩል ስጋ ለባሽ ...እኩል ባንድ ቦታ ። እያረፋፈደ የሚገለጥ ሰማይ ሰው እያጋደመ ፥ ሰው እያፋረደ ጨክኖ መጨከን የተለማመደ የቀደመው ነቅቶ ፥ የተኛ እያረደ ነጋ...ነጋ ...ባዩ ሽመሉን ወልውሎ ፥ በነጋው ወረደ ። ወ ረ ደ መአቱ ክንትው ....አለ ስንቱ ሺ ዘመን ቢኖሩ ... ነገ መሰወሩ ያለመገመቱ የትላንትና እሾ ዛሬም መዋጋቱ ለነገ ጠባሳ ሽንቁር ማበጀቱ ክ ፋ ቱ ይገርማል !!! በንዲህ ያለ ግዜ መላ ቅጡን ባጣ ፅልመት ያው....ፅልመት ነው ተገባም ....ተወጣ ሁሉን ይጋርዳል ከነጭ ጥርስ ኋላ የውሸት ቅጥልጥል ፥ በሌት ይገመዳል እውነት የሚመስል ተቀፅላ ሀሰት ፥ ሴረኛው ይወልዳል የተወለደም ዘር ባድርባይ እንኮኮ ፥ ተንፈላሶ ያድጋል ቀመሩ ያልገባው ልቡ የታወረ ኗሪ እንደ ደረጃው ለእግሩ ጧፍ ያነዳል ጉርሱን ቶሎ ጎርሶ ... ፍንጥቅ ላምባ ደፍኖ ፥ ትልቅ ሌት ይለምዳል እንዲ ነው ክፉ ቀን ይሄ ነው ጨለማ ይህ ነው ሰንካላ እድል እግር እየነሳ ፥ ክራንቹን የሚያድል ስጋ የሚያተላ ... ወገን የሚያጋድል ይህ ነው እርኩስ ወራት ይህ ነው ብላሽ እድል ምንም ማለት ማቃት ምንም ማድረግ መሳን ብዙ ጉድ ባለበት ... ባሰቡት ያነዳል ዳሩ ቀን ሲጎድል ቀን ሲጥል ቀን እንጂ ከፈጣሪ በቀር ፥ መች ሰው ይማለዳል ? የት ችሎስ ይፈርዳል !!! (አብርሀም ተክሉ) @amaregn @amaregn @amaregn
Mostrar todo...
ደመናት በሰማይ ቅርፅ እየፈጠሩ አይስሉም ትተዋል ፤ የጓሮ ሰበዞች አበቦች ረግፈዋል ፤ ወፎችም ጠፍተዋል እንደድሮ አይመጡም ፤ ሽማግሌዎች ዛፍ ስር ሸንጎ አይቀመጡም ፤ ያልጠኑ ጥጃዎች እየፈነጠዙ መስክ ላይ አይሮጡም ፤ ልጆች ሲቆጧቸው ቶሎ አይደነግጡም ፤ ህፃናት አውቀዋል እንደ ልጅ አይፈሩም ፤ በእሳት ዙሪያ ከበው ተረት አያወሩም ፤ ከእለታት አንድ ቀን አይባልም ቀረ ፤ ያልኖረውን እድሜ ልጅም እየኖረ ፤ ወንዞችም ደርቀዋል እያሉ አይፈሱም ፤ ወጣቶች ደክመዋል ለሺበት አይደርሱም ፤ ክረምትና በጋም ተናፍቀው አይመጡም ፤ ቀኖቹ ሮጠዋል ምንም ጊዜ አይሰጡም ፤ እየገሰገሰ እንዲህ እየጋለበ ጊዜ በቀን ፈረስ ዘመን ቢያስስም ባመት በዓል ቀን እንኳን አመት በዓል አይደርስም ፤ አሁን እንደ ድሮ አሁን ያለ አይመስልም ፤ ቀብር ይፋጠናል ለቅሶ አይደረስም መርዶ አይተረክክም ሞትም አይፈራ በሰርግ ቤት እንኳን አይሞቅም ጭፈራ ፤ ለአደራ ሚበቃ ሰው አንሷል ባገሩ ጎረቤት አይመጣም ጠንክሯል አጥሩ ፤ እናቶች በፍቅር ቡና አይተጣጡም ምናገባኝ አሉ የሰው ልጅ አይቀጡም ፤ ሁሉም ነገር ቢኖር በቃ ምንም የለም ጥም አይቆርጥም ውሀ አይማርክም ቀለም ፤ ገበታ ላይ ያለም እህል ይዞ መተከዝ አያጣም ይሰከራል ቶሎ በወግ አይጠጣም ፤ በቃ በቃ ደስታ የለም በቃ ምንም የለም ፤ ምኞትም ተመኘ የድሮውን ነገር ጠቅሎ ሄደና ሀገር ከራሱ ሀገር ፤ አብሮ መብላት ቀርቶ ፍቅር የጠፋ ዕለት ደስታም ይጨክናል ተስፋም ይጨፍናል፤ የፊቱ አይታይም ባሁን ይደፈናል ፤ መልኩ አይናገርም ተፈጥሮም ዝም ይላል ሙሉ ህይወት የለም ሁሉም ባዶ ባዶ ባዶ ባዶ ይላል ፤ አሁን የኛም ነገር ይሄንን ይመስላል ፤ ግን ተስፋ አለ ሁሉም ነገር ጥሩ ይሆናል። ©ገጣሚ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)
Mostrar todo...
"ይነጋል ባልነው ቀን ፣ ጨለማው ገነነ አሻጋሪ ያልነው ፣ አሸባሪ ሆነ እያለ ውስጥ ውስጡን ፣ ህዝብ ያጉረመርማል ይሄ ምን ይገርማል? "ህዝብ እየታረደ የሰላም ሽልማት ፣ እሱ ይሸለማል" እያለ አንዳንዱ ፣ በአሽሙር አንተን ያማል። ይሄ ምን ይደንቃል? እኔም አንድ ሰሞን ፣ በሚያሽኮረምም ቃል እንዲህ ብዬ ነበር በፍቅር ስብከትህ ፣ ልቤ እየራደ "ከእባቦች እንቁላል ፣ እርግብ ተወለደ ።" ብዬ ነበር ያኔ ፣ ምህረት ስትምገኝ ተአምር መሥሎኝ ነበር ከገዳዮች መሀል "መግደል መሸነፍ ነው" ፣ ምትል አንተን ሳገኝ። ።። ይሄ ምን ይገርማል? "በግንቦት ሀያ ላይ ፣ ግንቦት ስላሴ ተቆጣ ደርግ ጥሎን ሲሔድ ፣ ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ፣ሌላ ደርግ መጣ ገዢ መንግስት ወርዶ ፣ ገዢ መንግስት ወጣ ከተገዛች አይቀር ድርሻዬ ይሰጠኝ ፣ ሀገሬ ተሽጣ" ብዬ ነበር ያኔ ዝም በል እያለ ፣ ሲገርፈኝ ወያኔ ዝም አልልም ብዬ ፣ በሀገር ፍቅር ወኔ የታገልኩት እኔ ለቀብሬ አይደለም ፣ ቀን በቀን ለማልቀስ ከሞት መች አዳነን በታረድን ቁጥር ፣ ህወሐትንና ፣ ኦነግ ሸኔን መውቀስ ማነው ከነትጥቁ ወደሀገር ያስገባው ፣ ማነው ያስታጠቀስ?! ፍትህ ስንጠይቅ ሞት የሚፈርድብን ፣ የማን ሹም ነው ዳኛ ማን ነው ስም ሚሰጠን ስንሞት ኢትዮጵያዊ ፣ ስንኖር ነፍጠኛ ብሎ የሚጠራን ፣ በጅምላ ስንረግፍ ጭካኔ ሲበዛ ፣ በደል ሲያገፈግፍ እጥፍ ድርብ ሲሆን ፣ ይቀራል ያልነው ግፍ ትጠብቃለህ ወይ? ህዝብ እየተገፋ ፣ አንተን እንዲደግፍ ። ።። እና ሬሳ ተለቅሞ ፣ ፍትህ ስትቀር ኦና ሰርክ እየታረደ ፣ ሚሞት የለምና ወይ ህዝብህን አስታጥቅ ፣ መይ መንግስት ሆነህ ና ሀገር አይመራም!!! "መግደል መሸነፍ ነው ፣ በሚል ፍልስፍና! ሰው እየፈረሰ ፣ የለም ብልፅግና! By Belay bekele weya
Mostrar todo...