cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

طَلَعَ الْبَدْرُ عَلَىْنَا

ሙስሊም ነኝ እኔ (ሙስሊም ሁናችሁ እንጅ እንዳትሞቱ)al emran ማንኛውንም ኢስላማዊና አዳዲስ መረጃዎችን ያገኙበታል። ለአስተያየትዎ @ISLAMFORUS

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
165Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

👇👇👇👇👇👇👇👇👇 አንብበው ለሌሎችም ማካፈል አይዘንጉ!! ረሱል ሰ.ዐ.ወ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም ስለሚዎዷቸው ነገሮች አየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ አቡበክርን "ያ አባ በከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት። አቡበክርም "3 ነገሮችን እወዳለሁ:- 1.ከአንተ ጋር መቀመጥ፣ 2.አንተን ማየት፣ 3.አንተ ባዘዝካቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ። ° ዑመርን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?" "በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ 1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣ 2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣ 3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ። ° ዑስማንን ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን? በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:- 1.ሰዎችን ማብላት፣ 2.ሰላምታን ማብዛት፣ 3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣ ° አልይን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?" "በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:- 1.እንግዳን ማክበር፣ 2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣ 3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣ ° አባ ዘርን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?" "በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :- 1.እርሃብን እወዳለሁ፣ 2.በሽታን እወዳለሁ፣ 3.ሞትን እወዳለሁ፣ ነብዩም "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?" አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣ በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣ ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ። ° ነብዩ ሰለላሁ አለየሂ ወሰለም " እኔም በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:- 1.ሽቶን እወዳለሁ፣ 2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣ 3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣ በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ "አንቱ የአላህ መልዕክተኛ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም "ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት። 1.መልዕክትን ማድረስ፣ 2. አማናን አደራን መጠበቅ፣ 3.ሚስኪኖችን መውደድ፣ ጅብሪል ተመልሶ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ ረሱልና ሱሃቦቻቸው ከመቀመጫቸው ሳይነሱ ተመልሶ ወደ መሬት ዱብ አለ አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:- "አላህም ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም እንዲህ ብሏል:- በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:- 1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣ 2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣ 3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ። አላህ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ሱሃቦች የወደዱትን ያስወድደን! ° ይህን ጣፋጭ ሐዲስ በማንበባችሁ ከፍ ያለ አጅር ታገኛላችሁ -ኢንሻ አሏህ። ሼር በማድረግ ለሌሎች ብታካፍሉ ግን እነሱ ባነበቡት ልክ ለናንተም ሀሰናት ይፃፍላችኋል! ኢንሻ አሏህ!! አላህ አንብበው ከመጠቀሙት ያድርገን!!!
Mostrar todo...
አርኖድ ቫንዶርን 💎💎💎💎💎 ዘረኛና በተለይም በሙስሊሞች ላይ ስር የሰደደ ጥላቻ በሚያራምደው በጊርት ዊልደርስ በሚመራው የሆላንድ ቀኝ ክንፍ የነፃነት ፓርቲ አባል እንደነበር የሚታወስ ነው። ከስራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን የነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) ስብዕና የሚያጎድፍ ፊልም አዘጋጀ። ይህን ተከትሎ በሙስሊሙ ዓለም ቁጣን ቀሰቀሰ። አርኖድ ቫንዶርንም ሙስሊሞች ባሳዩት አጸፋዊ ምላሽ ተገረመ። ውሎ ሳያድር የእስልምና ኃይማኖትን ለማጥናት ወሰነ። ይህ አጋጣሚ የሰው ልጆች ፈርጥ ከሆኑት ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር እንዲተዋወቅ በር ከፈተ። በማግኔታዊ ባህሪያቸው ተሳበ። በፍቅራቸው ልቡ ተሰለበ። ወደ እስልምና አጸድ ኮበለለ። ስማቸውን ባጎደፈው አንደበቱ እውነተኛ ነብይ ለመሆናቸው የምስክርነት ቃሉን ሳይሰስት ሰጠ። «እስልምና ቅጥፈት ነው ፤ ቁርኣን መርዝ ነው» እያለ በተደጋጋሚ ሲሰብክ በነበረበት ምላሱ ከአላህ ሌላ በእውነት የሚገዙት ፍጹም አምላክ እንደሌለ መሰከረ። የነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) መልዕክተኛነት ከልቡ ተቀበለ። የእስልምናን ዘለበት ከጨበጠ ከአንድ አመት በኋላም የአብራኩ ክፋይ የሆነው ልጁ ዱካውን ተከትሎ እስልምናን ተቀበለ። አርኖድ ቫንዶርን «በሰራነው ፊልም ምክኒያት በአለም የሚገኙ ሙስሊሞች በቁጣና በሀዘን ስሜት ተውጠው ያሳዩትን አጸፋ ስከታተል ትልቅ ስህተት እንደፈጸምኩ ታወቀኝ። በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን ስሜት እየጎዳህ የሰራሁት ተግባር ልክ ነው ማለት ልክ አይደለም። እስልምናን በተመለከተ በአውሮፓ ውስጥ በሰዎች ዘንድ የተቀረጸው ምስል መገናኛ ብዙኋን እና ፖለቲከኞች የሚሹት እንጂ እውነተኛው ምስል አይደለም» በማለት ተናግሯል። አርኖድ ቫንዶርን ወደ ተፈጥሯዊ ኃይማኖቱ ከተመለሰ በኋላ በቀጥታ ወደ መዲና አቀና። የታላቁ ነብይ ክቡር አካል ካረፈበት ቀብር አቅራቢያ ፈንጠር ብሎ ቆመ። ነብዩ ሙሐመድን (ሰ.ዐ.ወ) በለሆሳስ ይቅርታ ጠየቀ። እናቱ ገበያ ለመሄድ ከቤት ውስጥ እንደጣለችው ህጻን በለቅሶ ነፈረቀ። በሰራው ጸያፍ ተግባር ተጸጽቶ ክፉኛ ተንሰቀሰቀ። ይኸው ዛሬ ደግሞ ሙስሊሞች በፈረንሳይ ምርቶች ላይ ያለመጠቀም አድማ እንዲያደርጉ ድምጹን አሰማ። እርሱን አምርረው የሚጠሉትን አካላት በፍቅር አንበርክኮ ወዳጅ ማድረግ የሚያስችል ስብዕና የተላበሰ ነብይ ተከታይ በመሆኔ ሁሌም ደስታ ይሰማኛል !!! Telegram 👉 http://t.me/abuafnanmoh
Mostrar todo...
ጦለዓል በድሩ ዓለይና! https://t.me/tolealbedru
Mostrar todo...
#ጥቆማ የዘንድሮ (የ1442ዓ.ሂ) ዓሹራ የሚሆነው የፊታችን ቅዳሜ ሙሐረም 10እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ነሀሴ 23 /2012 ወይም ኦገስት 29/2020 ሲሆን ከፊቱ ጁሙዓን ወይም ከኋላ እሁድን መጾም ተገቢ ነው። አላህ ይወፍቀን! @ImamAhmedcom
Mostrar todo...
🌼 " ዓሹራ" 🌼 ቡኻሪይ እንደዘገቡት ዐብዱሏህ ኢብን ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የዓሹራን ጾም አስመልክተው ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል (ነቢዩም ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለ እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር ሆን ብለው <በጉጉት ጠብቀው> ሲጾሙ አይቻቸው አላውቅም! ) ብለዋል ነቢዩም፥ ( የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል(ያስሰርዛል) ብዬ አሏህ ላይ ተስፋ አደርጋለሁ ) ብለዋል, አንድን ቀን በመጾም የዓመት ወንጀል መማር ለሙእሚኖች ታላቅ የአሏህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስጦታ ነው እድሉም ለሁሉም ክፍት ነው መሽቀዳደም እና መወዳደር ያማረው ሰው በሙሉ እንዲህ አይነቱ የኸይር ስራ ሜዳ ላይ ይሽቀዳደም! የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል ያስምራል ያስሰርዛል በቀላል ስራ ይህን የሚያህል ምንዳ የሚገኝ ሆኖ ሳለ ብዙ ለአኼራቸው ግድ የለሽ የሆኑ ሰዎች እድሉን ችላ ሲሉ እንመለከታለን, አዱኒያዊ ጥቅም ቢሆን ግን አይዘናጉም ነበር አልፎም እድሉ ላይ በመሻማት ይፋጁ ነበር ግን {አብዛኞችየሰው ልጆች አያውቁም} አርሩም 6 👉👉የዓሹራእ ጾም ሙሐረም ስንተኛው ቀን ላይ ነው ?... የዓሹራእ ጾም ማለት የሙሐረም ወር 10ኛው ቀን ላይ ሲሆን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድ ቀን (9ኛውን ወይም 11ኛውን) ቀን ጨምሮ መጾም ይመረጣል,ምክኒያቱም ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ዓሹራን ሲጾሙና ሷሓባዎችም እንዲጾሙት በመከሯቸው ጊዜ አይሁዶች የሚያከብሩት ቀን እንደሆነ ለነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲነግራቸው የሚከተለውን ብለዋል, ( አሏህ ካለ የሚመጣው ዓመት ላይ 9ኛውንም ቀን እንጾማለን ) ብለዋል ከዚህም በመነሳት ዑለማዎች ዘጠነኛውንም ቀን መጾም ሱና ነው ብለዋል። ከዓሹራ ጋር 9ኛውን ቀን መጾም ምክኒያቶች አሉት ከነዚህም መሀል አንዱ 10ኛውን ቀን ብቻ መጾም ከአይሁዶች ጋር መመሳሰልን ስለሚያመጣ አንድ ቀን ጨምሮ መጾሙ ከነሱ ጋር መለያየትን ያስገኛል ከጠመሙ ህዝቦች ጋር መመሳሰል በዲናችን ክልክል ከመሆኑ አንጻር እነሱን ለመቃረን ተብሎ ሸሪዓችን አንድን ነገር ማድረግ ሲከለክል ወይም ደግሞ ስያዝ ሁሉ እናያለን ይህም ሆኖ ሳለ ግን ብዙ ሙስሊሞች አይሁድና ነሳራ ያደረጉትን ለማድረግ ሲሽቀዳደሙ እንመለከታለንል! ይህ በንዲህ እንዳለ ምናልባት የቀን አቆጣጠር ላይ ስህተት ቢፈጠር እና የወሩ መግቢያ አሻሚ ቢሆን ሁለቱን ቀናት መጾም የዓሹራን ቀን ማግኘት ላይ እርግጠኛ ያደርጋል, በላጩ 9 እና 10ኛውን ቀን መጾሙ ሲሆን ያልተመቸው ሰው 10 እና 11ኛውን ቀን መጾም ይችላል።እንዲሁ ዋናውን የዓሹራን ቀን ብቻ እንጂ ሌላ ተጨማሪ ቀን መጾም ያልቻለ ሰው ብቻውን መጾም እንደማይከለከል ዑለማዎች ገልጸዋል። @ImamAhmedcom
Mostrar todo...
🔵🔵🔵🔵የሚገርም የኸይር ሳምንት🔴🔴🔴🔴 ማለትም ስምንት ተከታታይ ቀኖች ፆም የሚወደድባቼው። 1 ሀሙስ 8 ሙሀረም ስራዎች የሚወጡበት ቀን 2 ጁምአ 9 ሙሀረም ታሱአ ወይም የአሹራእ አጃቢ 3 ቅዳሜ 10 ሙሀረም አሹራእ የአንድ አመት ወንጀል የሚያሳብስ 4 እሁድ 11 ሙሀረም የአሹራእ አጃቢ صومويوما قبله ويوما بعده 5 ሰኞ 12 ሙሀረም ስራዎች የሚወጡበት 6 ማግሰኞ 13 ሙሀረም من ايام البيض 7 እሮብ 14 ሙሀረም من ايام البيض 8 ሀሙስ 15 ሙሀረም من ايام البيض እና ስራዎች የሚወጡበት ❀━┈╔═════════╗┈━❀ @iqrae_network ❀━┈╚═════════╝┈━❀
Mostrar todo...
ታላቁ ዛሂዱ ሱሀቢ አቡደርዳእ ረዲየላሁዓንህ ጦለዓል በድሩ ዓለይና! https://t.me/tolealbedru
Mostrar todo...
የድሮ የቀጥባሪ ሀድራ። ጦለዓል በድሩ ዓለይና! https://t.me/tolealbedru
Mostrar todo...
ፕሮፋይል ፒክቸሮን በቁርአን ያድምቁ። ጦለዓል በድሩ ዓለይና! https://t.me/tolealbedru
Mostrar todo...