cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ፅዱ ኢትዮጲያዊ

ውድ ወገን ሆይ ይህ መልእክት ይድረስልህ። በትላንት ባልተዋበ ታሪክ እኛ ቆስለናል፤ ባለፉት ስህተት ያለነው ተጎድተናል። ነገር ግን ክፉት፣ ተንኮል፣ እንድሁም ቂም በቀል ይብቃ ብሎ ወደ እድገት እና አንድ እርምጃ ወደ ፊት የምራመድ ... ክፉት ሀሉ በእኔ ይብቃ የምል ፅዱ ኢትዮያዊ እራሳችንን እንገንባ። ይሄን channel አብራችሁ መስራት የምትፈልጉ በሙሉ በ @hayalJesus ያናግር

Mostrar más
El país no está especificadoEl idioma no está especificadoLa categoría no está especificada
Advertising posts
290Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

በትውልድ ላይ አንቀልድ!! ይድረስ ለትውልድ ለሚገደው!! ይብቃ የዩኒየን አካዳሚ የትውልድ ላይ ጨዋታ!! በሆድ ትግልና ጉዞ ውስጥ ፈፅሞ ነገን አሻግሮ ማየትም ሆነ ከትናንት ከቀደመው ትውልድ ስኬትና ውድቀት ምን ነበር? ብሎ ማሰብም፣ መመርመርም ፈፅሞ የለም፤ ስለሆድ ብቻ የሚያስቡ የነገን ትውልድ አሻግረው ማየት አይችሉም። የነገን ትውልድ ዛሬ ላይ ሆነው በማስታዋል ማየት የተሳናቸው ትውልድን ከመገንባት ይልቅ ለዛሬ ሆድ ተሸንፈው ይኖራሉ። የሃዋሳ ዩኒየን አካዳሚ(#1) የነገን ትውልድ በስብዕና እና በእውቀት ከመገንባት ይልቅ ለሆዳቸው እንጂ ለነገ ለማሰብ ባልፈቀዱ የአስተዳደር አካላት በመልካም ስብዕና ትውልድን ከመቅረፅ ይልቅ፣ ከመልካም መምህራኖች እውቀትን ገብይቶ በራሱ የሚተማመን ዜጋን ከመፍጠር ይልቅ በሌላው ትከሻ ላይ ተንጠልጥሎ የሚኖር ትውልድን ማፍራትን የሥራቸው አካል አድርገውታል፤ በዘንድሮው ማለትም በ2013 ዓ/ም የማጠቃለያ ፈተና ወቅት የሰማሁት ክስተት እንደ አንድ ዜጋ በእጅጉ አሳዝኖኛል። በሁለትና በሦስት መቶ ብር የት/ቤት ፈተናን በማሰረቅ ማስፈተን ፣ ለእራሱም ሆነ ለሀገርም ተስፋ ይሆናል ብሎ ለሚያስተምር ቤተሰብ፣ ነገ ችግር ፈቺ ዜጋ ለሚሆነው ለእራሱ ለተማሪው ጭምር የማይበጅ ነውና ይህን እኩይ ተግባርና ምግባር አጥብቄ እጠየፋለሁ። የትምህርት ሥርዓታችንም እንዲህ ላለ ውድቀት በማንዳረግበት መልኩ የተጠናከረ ቢሆን፣ ሁላችንም "የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው" ከሚል እሳቤ ነፃ ሆነን ዛሬ ነገን መሆኑ አይቀርምና የነገን ትውልድ እየተመለከትን እንሥራ። የሀገር የወደፊት እጣፈንታ የሚወሰነው አንዱ ባላት የትምህርት ሥርዓት ነው፤ በትክክል እውቀትንን የሰነቀ፣ ራዕይና ዓላማን ያነገበ ትውልድን በመፍጠርና በመሆን እኛ ተማሪዎችም ለሀገር ተስፋ ለወገን መከታ ሆነን ከዛሬ ይልቅ ነገን መርጠን እንራመድ። የዩኒየን አካዳሚም ነገን አሻግሮ በመመልከት ገንዘብን ከትውልድ፣ ገንዘብን ከሀገር ባለማስቀደም ለትውልድ እና ለሀገር በእውነት፣ በታማኝነት ወደመስራት ወደማገልገልም ልዕቀት ከፍ ማለት ይገባዋል። ???????? ብዙ ነገር ይቸኩላል፤ ቆም ብሎ ማሰብ፣ አስተውሎም መራመድ ድሮ የቀረ ይመስላል፤ እውቀት ወደ መኖር መዝለቅ ተስኖት በስሜት ላይ ተንጠልጥሎ የቀረ ይመስላል። ሁሉም ነገር አሁን፣ ለአሁን ስንል ትንቅንቅ ውስጥ የገባን ይመስላል፤ ስሜትን በስሌት ገቶ ነገን አርቆ ማየት ከሁላችን የተወሰደ ይመስላል። ነገን ማን ልብ ብሎት? ሁሉም በዛሬ ተሸንፎ የማይቀረውንና የሚመጣውን ነገ እያወቀ እንዳላወቀ ሆኖ ማለፍን የወደደ ይመስላል፤ መሆን እና መምሰል ያለብንን አውልቀን ጥለን በማስመሰል መኖርን ኑሯችን ያደረግን ይመስላል። አንዳንዴ ትዕግስት አጥተን በስሜት ታውረን ላየን ጎበዝ ነገ የለም እንዴ? ያስብላል። ዛሬ የፈለግነውን የመምረጥ፣ የመወሰን፣ የመከወን፣የመኖር. . . መብት እና ፍቃድ አለን፤ ነገ ግን ወደን፣ ፈቅደን፣ ወስነን... በመረጥነው ዛሬ ውስጥ የመኖር ግዴታ አለን። ነገ ላይ ብልሹ አሰራርን የሚጠየፍ ሀገሩን የሚወድ ሕዝቡን በዘር፣ በገንዘብ ሚዛን የማይመዝን ተማሪ ሆኖ ትውልድን እናይ ዘንድ ዛሬ ከኩረጃ(ከስርቆት) የፀዳ፣ በመልካም ግብረገብነት የታነፀ ትውልድን ዛሬ ላይ እንገባ። አርቆ ማሰብ፣ አስተውሎም መራመድ ነገን ብቻ ሳይሆን ዛሬን ብሩህ ያደርጋልና በትዕግስት ዛሬን እንለፍ፤ በማስተዋልም ነገን እንመልከት። እንደ ዩኒየን አካዳሚ አይነት ተግባር ላይ ያሉ ጥቂቶች አይደሉምና ሁላችን ኃላፊነታችንን እንወጣ!! ምንተስኖት መኩሪያ የስውር ቁልፎች መጽሐፍ ደራሲ፣ ፀሐፊ፣ የማሕበረሰብ አንቂ፣ የአሼ ታለንት ፕሮሞተርና አጋዥ አስተባባሪ እና ድርጅታዊ አምባሳደር። ሐምሌ 27/2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ-ሃዋሳ
Mostrar todo...
ዝምታችን እኩይ ተግባርን አያስቆምም፤ ዝም ባለማለት አለመደገፋችንን ካሰማን እንኳ በቂ ነው።
Mostrar todo...
ብዙ ወጣቶች ጆሮ ይድረስልኝ
Mostrar todo...
Mostrar todo...
ምንተስኖት መኩሪያ ለሃዋሳ፣ ለኢትዮጵያ እና ለአፍርካ ወጣቶች ያስተላለፈው መልዕክት፡፡

ምንተስኖት መኩሪያ ለሃዋሳ፣ ለኢትዮጵያ እና ለአፍርካ ወጣቶች ያስተላለፈው መልዕክት፡፡እኔ ማረፊያየ ወንድሜን አፈናቅየ ያስፋፋሁት መሬት ሳይሆን፣ በፍቅር አቅፈው የገዛሁት ልብ ውስጥ ነው፡፡ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ጥያቄያቼው መልካም አስተዳደር፣ ፍት...

#የቀጠለ_3 በፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር ፌብሩአሪ 1984 ዓ/ም ከኢትዮጵያ ወጣሁ ። ዛሬ ከ36 ዓመት በላይ ሆኖኛል ፤ አንድም ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሼ አላውቅም ። በለንደን የኖርኩባቸው አምስት ዓመታት በአልኮሆል መጠጥ የታሠርኩባቸው በአመንዝራነት የተጠመድኩባቸው ዓመታት ነበሩ ። በካሜሩን ኤምባሲ ተቀጥሬ ልዩ ልዩ የአልኮሆል መጠጦችንና ሲጋራዎችን ከቀረጥ ነፃ በሆነ ዋጋ እያዘዝኩ በየዕለቱ እሰክርና አመነዝር ነበር ። የወደዱኝን ሴቶች ልብ እያታለልኩ አልጋ ላይ ካገኘኋቸው በኋላ እተዋቸው ነበር ። በዚያን ጊዜ ሴሰኝነት “ሴክሲ” ተብሎ ይወደሳል ፥ ብዙ ሴት ጋ መድረስም ታላቅ ጀብዱ ነበር - ክብራችን በነውራችን ። እኔና አንዲት ወዳጄ የወላጅነት ኃላፊነት ላለመቀበል ተስማምተን አንድ ልጃችን ከፅንስ እንዲወርድ አስደርገናል ። ታዲያ የሥጋዬ ቁራጭ የአጥንቴ ፍላጭ ዘመዴና ልጄ ገና በእንጭጭነቱ ከማኅፀን ደጅ ተቆርጦ ሲጣል እርሳስ የተጣለ ያህል እንኳን አልተሰማኝም ፥ አላዘንኩም ፤ ልቤ የወፍጮ ድንጋይ ነበር ።... ይቀጥላል @life_of_jesus
Mostrar todo...
#የቀጠለ_2 … በሴቷ ላይ የሚፈርድ ማን ነው? ፅንስ ማስወረድ እጅግ የተለመደ ሆነ ። “ዞሮ ዞሮ ከቤት ኖሮ ኖሮ ከመሬት” ይላሉ አበው ሲተርቱ ፤ እነዚያ ሕፃናት ግን “ኖሮ ኖሮ ከመሬት” የሚል ዕድል አላገኙም ። ተወልደው የዓለምን አየር ሳይተፍሱ ፥ በደስታ እልል ሳይባልላቸው ፥ ዳቦ ተጋግሮ ስም ሳይወጣላቸው ፥ እንደሌሎቹ ሕፃናት ወተት ጠጥተው ሳያቀረሻቸው ፥ የዳዴ ወግ ሳይደርሳቸው ፥ ወፌ ቆመች ሳይባልላቸው ፥ በወላጅ እቅፋት ሳይታቀፉ ፥ በአንቀልባም ሳይታዘሉ ፥ መንግሥት ሳያውቃቸው ፥ በስውር ሲገደሉ ለደማቸው ተፋራጅ ሳያገኙ ፥ ከፅንስነት ወደ ልጅነት የመሻገር መብታቸውን ተነፍገው ፥ በስውር ኖረው በስውር ሞቱ። .... ይቀጥላል .... @life_of_jesus
Mostrar todo...
አንድ ጊዜ አንዲት የማውቃት ልጅ “ታማለች” የሚል ወሬ ሰማሁና ልጠይቃት ሄድሁ ። በርግጥም ታማ ነበር ። ፊቷ ጠቋቁሯል ፥ ሕመም ይሰማታል ፥ ስትናገርም ታቃስት ነበር። “ምነው? ምን ሆንሽ?” ብዬ ጠየቅኋት ። “እባክህ እሱን አዲስ ጫማ አቀብለኝ” አለች ። አልጋዋ ፊት ለፊት የመጽሐፍት መደርደሪያ አለ ፥ ከበላዩ ደግሞ የአዲስ ጫማ ካርቶን ተቀምጦ ነበር ። ካርቶኑን አንስቼ አቀበልኳት ። “ውይ ፥ ክፈትና አቀብለኝ” አለች ። የካርቶኑን ክዳን ከፈትኩት ። በጣም ደንገጥኩ ፥ መላው ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ ፤ እንደዚያ ዓይነት ነገር አይቼ አላውቅም ነበር ። ካርቶኑን አልጋው ላይ ልጥለው ቃጣሁና ወዲያው መለስኩት ። ብዙ ስሜቶች ተፈራረቁብኝ ፦ ሐዘን? ቁጣ? ትዝብት? ስድብ? ፥ ያየሁት ምንጊዜም የሚረሳኝ አይደለም ። ካርቶኑ ውስጥ የሞተ ሕፃን ልጅ ተጋድሞ ነበር ። “ልጅ” የምለው ልጅ ስለሆነ ነው ። ሊወለድ ጥቂት የቀረው ፥ ሙሉ ለሙሉ ሕፃን ልጅ የሚያሰኘው ነበር ። ሕፃኑን አስወርዳው ነበር ። ከናዝሬት ከተማ አለፍ ብሎ ገጠር አካባቢ የታወቀ ፅንስ አስወራጅ በዛገ ብረት ማኅፀኗን ጎርጉሮ ብዙ ደም ከፈሰሳት በኋላ ፅንሱን እንዳወረደላት ነገረችኝ ። ማኅፀኗ ቆስሎ (ኢንፌክትድ ሆኖ) ነበር ። “ምነው? ለምን አስወረድሽው?” አልኳት ። ፈቷን ወደ ግድግዳው አዞረች ። … በሴቷ ላይ የሚፈርድ ማን ነው? ይቀጥላል .... @life_of_jesus
Mostrar todo...
Mostrar todo...
ታላሳ ዘላሜሮስ |ይስሀቅ ክፍያው| NGM| [

#SUBSCRIBE#SHARE#LIKE

በአለማችን በአሸባሪዎች ከሚሞቱ በላይ በውርጃ የሚሞቱት ይበዛሉ። በተለይ በሀገራችን በስፋት እየታየ ነው። ❗️❗️ውርጃ ይቁም ውርጃ ሀጢያት ነው። @tsidu_Ethiopia
Mostrar todo...