cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቅ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ አርማ

በ1928 የተመሠረተ ፩ ክለብ ፩ ቤተሰብ ሁሌም ስለ ሳንጃው እንዘግባለን✌️ @SAINTGEORGEFC የመወያያ ግሩፑኑን ለመቀላቀል @talksanjaw ለአስተያየት እና ለጥያቄ ⬇️ @SAINTGEORGEFCV_bot

Mostrar más
Advertising posts
12 125Suscriptores
-124 hours
-207 days
-12130 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

✌️ ቅ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ አርማ✌️ 🟡 የድል ቀን 🔴 ድል ለታላቁ ክለባችን ✌️❤ 88 ዓመታት የድል ጉዞ!     ምንግዜም ጊዮርጊስ! 🏆✌️ ታላቁ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ✌️🏆 #ምንጊዜም_ጊዮርጊስ 💛❤️ 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 ፩ ክለብ  ፩ ቤተሰብ ሁሌም ስለ ሳንጃው እንዘግባለን...✌️
Mostrar todo...
3🔥 2
✌️ ቅ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ አርማ✌️ 🟡 ዛሬ የጨዋታ ቀን ነው 🔴 🔴 ዛሬ የድል ቀን ነው 🟡 ፥ 🔸Match Day✌️ 🔸Victory Day🏆 🔸St George Day❤️ ወላይታ ዲቻ 🆚 ቅዱስ ጊዮርጊስ  📆  ቅዳሜ ሚያዝያ 12/2016 🕗 ከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት 🏟  በድሬደዋ ኢንተርናሽናል  ስታዲየም ድል ለታላቁ ክለባችን ✌️❤ 88 ዓመታት የድል ጉዞ!     ምንግዜም ጊዮርጊስ! 🏆✌️ ታላቁ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ✌️🏆 #ምንጊዜም_ጊዮርጊስ 💛❤️ 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 ፩ ክለብ  ፩ ቤተሰብ ሁሌም ስለ ሳንጃው እንዘግባለን...✌️
Mostrar todo...
🏆 7 1
እናስታውሳችሁ ይህ ክለብ ባለቤቱ ደጋፊው ነው ። የሳንጃው ደጋፊን በብልጣብልጥነት ለማሞኘት በተንኮል አትነካካው እሳት ነው ይፋጃል 💪 👉"መተዳደርያ ደንባችንን የጣሰ አመራር በኛ ዘንድ ተቀባይነት የለውም" 👉"መተዳደርያ ደንባችን ለኛ ለጊዮርጊሳውያን ህገ መንግስታችን ነው"። ምንጊዜም ቅዱስ ጊዮርጊስ✌️
Mostrar todo...
🔥 24👍 4
የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ ሆኖ የጊዮርጊስ ጠላት የለም በማልያው ስር የተሰበሰበ ሁሉም ደጋፊ ለክለቡ ፍቅር አለው ይሄ የማይካድ ሀቅ ነው ያያ የምትወደውን ክለብ ከገባበት ችግር ለማውጣት እንደ አንድ የሳንጃው አባል ደጋፊ የምታደርገውን ጥረት ሁሉ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ከፍታ ነውና ሀሳብህን ደጋፍህን ተቃውሞህን በነፃነት በድጋሚ የምትገልፅበት ቀን ቅርብ ነው ፈጣሪ በሰላም ከቤተሰቦችህ ጋር ያገናኝህ ያሬድ መላኩ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ማዕከላዊ) እስረኞች ማቆያ ውስጥ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ #ምንጊዜም_ጊዮርጊስ ✌️❤️✌️ 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 ፩ ክለብ  ፩ ቤተሰብ ሁሌም ስለ ሳንጃው እንዘግባለን...✌️
Mostrar todo...
19👍 4
የቅርብ ጓደኛ Dawit Fesiha በገፁ ስለ ያያ ወቅታዊ ሀኔታ እንደፃፈው 👇 የያሬድ መላኩ እስር ከምን ጋር ይገናኛል? ያያ መላኩ ወንድማችን ነው፡፡ ቤተሰብ ነን፡፡ ውሎ እና አዳራችንን እንተዋወቃለን፡፡ የምንበላ የምንጠጣውን ቀርቶ የምናስበውን እንተዋወቃለን፡፡ ከዚህ እውነታ በመነሳት አንድ አንድ ጉዳዮችን እናንሳ፡፡ ያያ ከታሰረ 3 ቀናቶችን ተቆጥሯል፡፡ የተያዘበት መንገድ እና አሁን እስሩ ላይ እየሆነ ያለው ሁኔታ ተመጋጋቢ አይደለም፡፡ ሲታሰር አጀብ አልነበረም፡፡ ከስራ ወጥቶ ትንሿ ልጁን ይዞ ወደ ቤት ለመሄድ በመንገድ ላይ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ ሁለት ሲቪል ፖሊሶች መጥው እንደሚፈለግ ነገሩት፡፡ ልጁን ቤት ማድረስ እንዳለበት ነገራቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ራይድ ጠራ፡፡ ልጁን ጨምረው ሁለቱ ፖሊሶች ራይድ ውስጥ ገቡ፡፡ ልጁን ቤት አደረሰና ያያ በያዘው ራይድ ወደ ማዕከላዊ ተጓዙ፡፡ ማዕከላዊ ሲደርሱ ያያ የራይድ ከፍሎ ወረደ፡፡ ከፖሊሶቹ ጋር አብረው ወደ ማዕከላዊ ገቡ፡፡ በዚህም የራይድ ከፍሎ የታሰረ ቀዳሚው ሰው ሳይሆንም አይቀር! ማዕከላዊ ከገባ በኋላ ግን ሌላ ታሪክ ተፈጠረ፡፡ ያለ ፓትሮል፣ ያለ ግርግር እና ራሱ የራይድ ከፍሎ የታሰረው እስረኛ እስከ እዚህ ሰዓት ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረበም፡፡ ከቤተሰብ፣ ከወዳጅ እንዲሁም ከጠበቃ ጋር እንዲገናኝ አልተፈቀደለትም፡፡ የታሰረው ለብቻው በጨለማ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ስለ እስሩም ሆነ አሁን ስላለበት ሁኔታ ብንጠይቅም ጠለቅ ብሎ መልስ የሚሰጠን አካል የለም፡፡ ለመሆኑ እስሩ ፖለቲካዊ ይሆናል? በፍጹም! ያያ ከማንኛውም ፖለቲካ ነክ እንቅስቃሴ ጋር ትስስር የለውም፡፡ ተሳታፊም ሆነ ሃሳብ ሰጪ አይደለም፡፡ ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ ሲያሰማ ተሰምቶ አያውቅም፡፡ ለዚህም ምስክሮቹ እኛ የቅርብ ወዳጆቹ ነን፡፡ ያያ በፖለቲካ ነክ ነገር ከታሰረ መታሰር ያለበት "ስለምን በሀገሪቲ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ላይ አትሳተፍም?" ተብሎ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ እስሩ ከማህበራዊ እንቅስቃሴ ጋር ይገናኝ ይሆን? ያሬድ መላኩ በማህበራዊ ህይወቱ የሚቀናበት ሰው ነው፡፡ ጸብ እና ግጭት ውስጥ አይገባም፡፡ ከትልቅ ከትንሹ ጋር በትህትና ተሳስሮ የሚኖር ሰው ነው፡፡ ጸብ ቢገጥመው እንኳ ጸቡን የሚያልፍበት ጥበብ የሚያስቀና ነው፡፡ ሁሉን እንደ ጸባዩና ባህሪው አሳስቆ መኖር ተክኖበታል፡፡ ከግል ሥራው ጋር የተገናኘ ነገር ይኖር ይሆን? በፍጹም! ከግል ስራው የተገኛኘ አንዳችም ክፍተት የለም፡፡ ከያያ ጋር ከሚሰራው ልጅ ጋር በዚህ ጉይ አውርተናል፡፡ ምንም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም፡፡ ለእስር በተዳረገበት ቀን እንኳ የዋለው ስራ ቦታው ላይ ነው፡፡ በዚያ ቀንም ሆነ ከዚያ ቀናት አስቀድሞ በሥራው ላይ የተፈጠረ እና ለእስር የሚዳርግ አንዳችም አዲስ ነገር የለም፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ጋር በተገኘስ ይኖር ይሆን? ያለፉትን ረጅም ወራት አንስቶ ሰፊ ጊዜውን የሚሰጠው ለዚህ ጉዳይ ነው፡፡ "ክለቡ ለውጥ ያስፈልገዋል!" ብሎ በአደባባይ ያወራል፡፡ ከበርካታ ደጋፊዎች ጋር ይገናኛል፡፡ በሳምንት ቀላል ለማይባሉ ቀናቶች እስከ ለሊት 7 ወይም 8 ሰዓት ድረስ የቪዲዮ ስብሰባዎችን ያደርጋል፡፡ በአካል ከተለያዩ ደጋፊዎች ጋር ይገናኛል፡፡ ቀኑን ሙሉ ስልኩ አያርፍም፡፡ በርካታ ደጋፊዎች ይደውሉለታል፡፡ ለሚደውሉለት ሁሉ መልስ ይሳጣል፡፡ ከደጋፊዎች ጋር በሃሳብ ለመግባባት ይጥራል፡፡ ከስራው፣ ከቤተሰቡ እና ከግል ህይወቱ በላይ ሙሉ ጊዜውን የሰጠው ለክለቡ ነው፡፡ በፌስቡክ እና በሜሴንጀር ከደጋፊዎች ጋር ይጻጻፋል፡፡ በሀሳብ ከሚመስሉት ጋር ይመካከራል፡፡ በሀሳብ ከሚለያዩት ጋር ይከራከራል፡፡ ተቀራርበን እንስራ ይላል፡፡ ክለባችን የእኔም ሆነ የእናንተ ሀሳብ ያስፈልገዋል ይላል፡፡ በዚህ ሁሉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ብዙ ነገሮች ይገጥሙት ነበር፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ዋናው ማስፈራሪያዎች ናቸው፡፡ ከተለያዩ ማንነታቸው ከማይታወቁ ሰዎች ስልክ ይደወል እና ይዛትበታል፡፡ ዘለፋ እና ስድቡ ቀላል የማይባል ነው፡፡ በክለቡ ዙሪያ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ እንዲያቆም የሚያስፈራሩት ሰዎች ቀላል አልነበሩም፡፡ ይህ ሲደርስበት እኛም ወዳጆቹ ሰምተናል፡፡ አብረን በሆንበት ወቅት ተደውሎ ሲዛትበት ስልኩን ስፒከር ላይ አድርገን ሰምተናል፡፡ ዛሬ ወንድማችን በማዕከላዊ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ከተዘጋበት ቀናት እየተቆጠሩ ይገኛል፡፡ እስከዚህ ሰዓት ድረስ ስለ እስሩም ሆነ ስላለበት ሁኔታ ምላሽ የሚሰጠን አካል አላገኘንም፡፡
Mostrar todo...
😭 11👍 8
በራይድ ወደ እስር ቤት የሄደው ምስኪን ታሳሪ ማክሰኞ ዕለት ያሬድ መላኩ (ያያ) ሀገር አማን ብሎ ልጁን ከትምህር ቤት አውጥቶ ወደ ቤቱ እየሄደ ነበረ። ሁለት ሰዎች «ለጥያቄ እንፈልግሃለን» ብለውት ከመንገድ አስቆሙት። ያሬድም ያለማንገራገር እሺታውን ገልፆ ራይድ ጠርቶ ወደ አዲስ አባባ ፖሊስ ኮሚሽን ከአሳሪዎቹ ጋር ሄደ። የተጓዘበትን የራይድ ክፍያም ከፍሎ ወደ እስር ቤት ገባ። ያሬድ ከተያዘ 48 ሰዓታት ቢያልፉትም እስከ አሁን ፍርድ ቤት አልቀረበም። በእነዚህ ቀናት ቤተሰቦቹንም ለማግኘት አልተፈቀደለትም። በቀን ውስጥ ሁለት ጊዜ ምግብ ይገባለታል። ነገር ግን እሱ ስለማይቀበል ይድረሰው አይድረሰው አይታወቅም። ያሬድ በ48 ሰዓት የመከሰስ መብቱን ተነፍጓል። በቤተሰብና ወዳጆቹ የመጠየቅ መብቱ ተነፍጓል። ቤተሰቦቹ በምን ወንጀል ተጠርጥሮ እንደተያዘ የማወቅ መብታቸው ተነፍገዋል። ያሬድ መላኩ ከሁሉም ተግባቢ ፣ የተቸገረ የሚረዳ ፣ በሀይማኖቱ ጠንካራ ሰው አክባሪ መልካም ዜጋ መሆኑን መመስከር እችላለሁ። ፖሊስ የያሬድን ህገ መንግስታዊ መብት እንዲያከብር እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ እጠይቃለሁ። Via Ermias
Mostrar todo...
👍 26😭 6 1💔 1😡 1
በዚህ እስር ላይ የክለባችን አመራሮች እጃችሁ ካለበት ከደጋፊው ጋር ያላችሁን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ችግር ውስጥ ነው የምትከቱት ማንም ደጋፊ የፈለገውን ሀሳብ የማቅረብ የመቃወም የመደገፍ መፍት አለው እኛ ልዩነትን በዚህ ልክ እንዲቀጥል አንፈቅድም አንድ ክለብ አንድ ቤተሰብ በወሬ ሳይሆን በተግባር ይሁን ክሱ ምንም ይሁን ምንም ያያ የታሰረው በክለባችን ጉዳይ ከሆነ ዝም አንልም በዚህ የእስር ጉዳይ የትኛውም የቅዱስ ጊዮርጊስ አመራር እጃችሁ ካለበት ፀባችሁ ከደጋፊው ጋር ነው በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጽ እና መገናኛ ዘዴዎች የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ላይ ያለውን ተቃውሞ በመግለፅ የራሱን ኃሳብ፣ አመለካከት እና ጥቆማ በአደባባይ በመግለፅ የሚታወቀው ወንድማችን ያሬድ መላኩ (Yaya Melaku) በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ያሬድ መላኩ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ማዕከላዊ) እስረኞች ማቆያ ውስጥ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ #ምንጊዜም_ጊዮርጊስ ✌️❤️✌️ 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 👉 @SAINTGEORGEFC 👈 ፩ ክለብ  ፩ ቤተሰብ ሁሌም ስለ ሳንጃው እንዘግባለን...✌️
Mostrar todo...
👍 45 3🔥 1
በተለያዩ የማህበራዊ ድረ ገጽ እና መገናኛ ዘዴዎች የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ላይ ያለውን ተቃውሞ በመግለፅ የራሱን ኃሳብ፣ አመለካከት እና ጥቆማ በአደባባይ በመግለፅ የሚታወቀው ወንድማችን ያሬድ መላኩ (Yaya Melaku) በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ያሬድ መላኩ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ማዕከላዊ) እስረኞች ማቆያ ውስጥ በእስር ላይ ይገኛል፡፡
Mostrar todo...
💔 27👍 1😡 1
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር _ሊግ _21ኛ  ሳምንት  ጨዋታ ውጤት #Ethiopia_ premier_  League ባህርዳር ከተማ  1 - 1 ቅዱስ ጊዮርጊስ  ⚽️ቸርነት ጉግሳ 30'      ⚽️አማኑኤል ኤርቦ 95'
Mostrar todo...
💔 38🔥 12🏆 4👎 2🤣 2😡 2👍 1 1
👉የጨዋታ ቀን # Match  day የኢትዮጵያ ፕሪሚየር _ሊግ _21ኛ  ሳምንት  ጨዋታ #Ethiopia_ premier_  League ባህርዳር ከተማ  🆚 ቅዱስ ጊዮርጊስ  📆  አርብ  ሚያዝያ 4/2016 🕗 ከምሽቱ 1:00 ስዓት 🏟  በድሬደዋ ኢንተርናሽናል  ስታዲየም 💛❤️ድል -ለታላቁ ቅዱስ ጊዮርጊስ 💛❤️
Mostrar todo...
👍 20🏆 12