cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegaciĂłn. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

🥀ሶልያና🇪🇹

•┈•❈••✦✾✦••❈•┈• 👉ምርጥ ምርጥ ግጥሞች ከእውቅ ገጣሚያን በድምፅና🎧 በፅሁፍ📃 👉አዝናኝ፣ አስተማሪና መረጃ ነክ ፅሁፎች👌 😇 😁 •┈•❈••✦✾✦••❈•┈•

Mostrar mĂĄs
El paĂ­s no estĂĄ especificadoEl idioma no estĂĄ especificadoLa categorĂ­a no estĂĄ especificada
Advertising posts
568Suscriptores
Sin datos24 hours
Sin datos7 days
Sin datos30 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

🥀ሶልያና🇪🇹 ይሄ ነው ጎጆችን ፍቅር ሳያንሰን ባህር የከፈለው መፈላለጋችን እመነት ያራራቀው የኔ ፀባይ ሰናይ አመልህ የሰራው ጣራ ግርጊዳውን ድምፅህ ያሳመረው አጥብቆ ያቆመው ንፁ ማንነትህ ብለያይም እንኳ እመነቴና እመነትህ ይሄ ነው ቤታች በንፁ ህሊና ፍቅር የገነባው መሞጋገስ እንጂ መወቀሳ የሌለው አየህ የኔ ትውት !!!❣️ ለቤቴ ድምቀት ነው ፀባህ እና አመልህ ተስፋ እሰነቀ ሁሌ ምያባብልህ የሄ ነው ጎጆችን ባህር የከፈልው አንድ ነገር ብቻ ስሩን ያራራቀው በነፃነት ቡዙና @Soliana9 @Soliana9
Mostrar todo...
የውበት ጀርባው (በእውቀቱ ስዩም) ላንተ የሚታይህ፤ የሚያምር ፈገግታ ያበባ ጉትቻ ላንተ እሚታይህ ውብ ገፅታ ብቻ ጥርሷን ጉራማይሌ፤ የተነቀሰች ቀን ያየቺው መከራ፤ ያየቺው ሰቀቀን የጆሮዋን ጫፉን ፤ በሾህ ስትበሳ የበላችው ፍዳ ፤ ያየቺው አበሳ የዋጠችው ህመም፤ ከሬት የመረረ የቀመሰው ማነው፤ከሷ በስተቀረ? ከያንዳንዱ ታላቅ ፤ ውበት በስተጀርባ ሲንዠቀዠቅ ኑሯል ፤ ብዙ ደምና እንባ ይሄም ታላቅ ዜማ ይሄም ታላቅ ስእል ይሄም ታላቅ ተረት ይሄም ታላቅ ድርሰት ከፊትህ አልቆመም፤ እንደመና ወርዶ ስቃይ ያቃልላል፤ ከስቃይ ተወልዶ። @Soliana9 @Soliana9
Mostrar todo...
የቅኖች ልብ ❣️ የሰማይ ክዋክብት ለጨረቃ ድምቀት የቅኖች ልብ ናት የዝች አለም ውበት ምንግዜም አይቆጭም ስለፍቅር መሞት አይጠቅምም ወዳጄ ሽመገላና ሐሰት ብቻ የምያሳፍረው አንሶ መገኘት ነው ፍቅር ስሜት አይደለም የነብስ ክርነው ልክ እንደ ጭረቃ ልክ እንደ ክዋክብት አንድላይ ስኖሩ ፍቅርና ተስፋ እመነት ጉልተው ይታያሉ ከክዋክብት ህበረት ይች ናት ለኔ ህይወት አምኜ ምኖራት በነፃነት ቡዙና @solian9 @soliana9
Mostrar todo...
ተላለፉ ሲለን ከመረዋው ውግረት ከቃጭሉ ዋይታ እኩል ብንሰማም በአንድ ደውል ድምፅ ግለ ህሊናችን አንድ ላይ ቢደቃም ተላለፉ ሲለን ፊትና ኋላ እንጂ እኩል አንነቃም ። በይስማእከ ወርቁ @soliana9 @soliana9
Mostrar todo...
አይፀለይም!!! ለሁሉም ግዜ አለው ይሉትን ዘንግቼ ያላቅሜ ፀሎት ሱባኤ ገብቼ በፆም ተገቼ ስጠኝ በአንዲት ጀንበር እያልኩኝ ሳስቸግር እርሱም ዝም አላለኝ ልመናዬን ሰምቶ የምፈልገውን አደለኝ አብዝቶ እኔመች አውቄው እንደምሞት ቶሎ ለካ አይፀለይም አታስርበኝ እንጂ ጥጋብ ስጠኝ ተብሎ ። በሜሮን ጌትነት @soliana9 @soliana9
Mostrar todo...
ጩኸት እግዚኦ አቢሲኒያ ቁናሽን የተካድሽ ባለሙያ የስፌትን ጥበብ ከቁናሽ ሊቀዱ ቁናሽን እኮ ከወሰዱ ሺህ ዘመናት ነጎዱ ። በቁናሽ ቀለባችንን ስለሚሰፍሩ አናማርራቸውም ለግዜሩ ። በኑረዲን ኢሳ @soliana9 @soliana9
Mostrar todo...
ነፍሰ ጡር ስንኞች የራስ ቅሉን በኩርኩም ባደባልቀው እንደቃ ፈጥኖ ባይመልስም ቅሉ እያደር ግን ነቃ ። በቴዎድሮስ ፀጋዬ @soliana9 @soliana9
Mostrar todo...
የገሀነም መዝገብ አንድ ጦማር አንድ መዝገብ አምልጦ ወድቆ ከሰማይ ወደ ገሀነም የሚገቡ የሰዎችን ዝርዝር የሚያሳይ አነሳሁት እና ስበር ከራሴ ስም አስቀድሜ የፈለኩት ያንቺን ነበር ። በይስማእከ ወርቁ @Soliana9 @Soliana9
Mostrar todo...
እንደምትወዳት ንገራት! [በእውቀቱ ስዩም] ህይወት -የብድር በሬ፤ መቼ ሁሌ ይጠመዳል? ለጊዜው ብቻ የመጣ ፤ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል የተሰጠህ ፀጋ ሁሉ፤ ደሞ ካንተ ይወሰዳል፤ ቀለበት ፤ አምባር አይደሉም እጅህ ላይ፤ ሁል ጊዜ የሉም- -ቀናት ፤ሳምንታት፤ ወራት ዛሬውኑ ፤ አሁንኑ ፤ እንደምትወዳት ንገራት ፡፡ . አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ ያፀድ በሮች ሳይቆለፉ በንቦች ጎዳና ላይ ፤ተርቦች ሳይሰለፉ በንፋስ ክንፍ ሳይመታ ህይወት- የላምባ መብራት አሁንኑ ዛሬውኑ፤ እንደምትወዳት ንገራት:: . ርቃ ሳትገሰግስ ገና ስንቋን ስትደግስ እንዲሁ እንዳማረባት ቀልብህ እንደቀረባት መቃብር በመዳፉ እንደ ጠጠር ሳይቀልባት አፈሩን ሳትዛመድ ወደ እማትቀባው አመድ ወደ እማትስበው አየር ሳትቀየር አንተም አንደበት ሳለህ ፤ እሷም ጆሮ ሳያጥራት ዛሬውኑ ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት!! . @Soliana9 @Soliana9
Mostrar todo...