cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

TIKVAH-ETHIOPIA

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። @tikvahuniversity @tikvahethAfaanOromoo @tikvahethmagazine @tikvahethsport @tikvahethiopiatigrigna #ኢትዮጵያ

Mostrar más
Advertising posts
1 340 899Suscriptores
+55824 hours
+3 1737 days
+28 72930 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

300 ቢሊዮን ብር ዕዳ ! የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ብድር #እዳ እንዳለበት ተሰምቷል። ይህ የተሰማው በህ/ተ/ም/ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይልን የ9 ወራት የስራ አፈፃጸም ሪፖርት ባዳመጠበት ወቅት ነው። የተቋሙ የብድር ጫና በጣም ከፍተኛ ነው ተብሏል። የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢ/ር አሸብር ባልቻ  ባቀረቡት ሪፖርት ፤ ተቋማቸው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ብድር እንዳለበት ተናግረዋል። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ አስረድተዋል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው ተቋሙ ካለበት የዕዳ ጫና ለመውጣት ፦ ➡ #የታሪፍ_ማሻሻያዎችን በማድረግ ➡ የውጭ የሃይል ሽያጭ አቅሞችን በማጠናከር ➡ የውስጥ ገቢን በመሳደግ ለዕዳ ቅነሳው ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስቧል። ኢ/ር አሸብር ፥ በቀጣይ ከጅቡቲ፣ ከኬኒያ እና ከሱዳን በተጨማሪ ለታንዛኒያ እና ደቡብ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የዕዳ ጫናውን ለመቀነስ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት በዕቅድ መያዙን  ተናግረዋል። ℹ #HouseofPeoplesRepresentatives #CapitalNewspaper @tikvahethiopia
Mostrar todo...
#ጥንቃቄ🚨 " በተጣሉ ተተኳሾች እና ፈንጂዎች 103 ሰዎች #ሞተዋል ፤ አካላቸው ጎድሏል " - የቆላ ተምቤን ወረዳ በትግራይ ማእከላይ ዞን የቆላ ተምቤን ወረዳ በጦርነቱ ምክንያት በርካታ ተተካሾች እና ፍንጂዎች ይገኛሉ። እጅግ አስከፊውና ደም አፋሳሹን ጦርነት ተከትሎ በአከባቢው የተቀበሩትና የተጣሉት ተተካሾችና ፈንጂዎች በበርካታ ሰዎችና እንስሳት ላይ የሞትና የአካል ጉዳት አደጋ በማድረስ ላይ እንደሆኑ ተነግሯል። በወረዳው በተቀበሩትና በተጣሉት ተተኳሾችና ፈንጂዎች እስካሁን 103 ሰዎች #ሞተዋል ፤ አካላቸው ጎድሏል። አሁን ላይ አደጋውን ለመቀነስ ነዊና ጉያ  በተባሉ የቀበሌ አስተዳደሮች በባለሙያዎች የተደገፈ የማምከን ስራ መጀመሩን የወረዳው አስተዳደር አሳውዋል። ህዝቡ በአከባቢው ከተለመደው የተለየ ብረት ሲያገኝ ከመንካትና ከመቀጥቀጥ ተቆጥቦ ለጸጥታ አካላት እንዲያሳውቅ ማሳሰቢያ ተለልፏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቆላ ተምቤን ወረዳ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያሳያል። #TikvahEthiopiaFamilyMekelle @tikvahethiopia
Mostrar todo...
#ጊብሰን #GibsonSchool የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በጊብሰን ትምህርት ቤት የሚማሩ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ከተማ አቀፉን የሚኒስትሪ ፈተና ትምህርት ቤቱ ማስፈተን እንደማይችል እንዳሳወቀው ት/ቤቱ ገልጿል። ጊብሰን ትምህርት ቤት " ባጠፋቸው ጥፋቶች ምክንያት እግድ ስለተጣለበት ተማሪዎችን ማስፈተን አይችልም " የተባለ ሲሆን ትምህርት ቢሮው ተማሪዎችን ሌላ ትምህርት ቤት ወስዶ በማስፈተን የሚኒስትሪ ካርዱ ላይም " በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ስር " የሚል እንደሚፃፍበት ተገልጿል። ይህን ውሳኔ ወላጆች እንደማይቀበሉት ገልጸዋል። ወላጆች ምን አሉ ? - ልጆቻችን በተማሩበት ት/ቤት ስር ነው መፈተን ያለባቸው - የተነገርን ነገር የለም - ባለቀ ሰዓት ነው ይህን የሰማነው - በተቀመጠው ካሪኩለም እንደሚማሩ ነው እኛ የምናውቀው - ልጆቻን ካሪኩለሙ የሚፈቅደውን ነው የሚማሩት - ቋንቋ ችግር አለ ወይ ? የለም - ሌሎች ት/ቤት የሚተገበረው ነው እዚህም ያለው - ከሌሎች የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚለየው ሳይንስ እና ሂሳብን በተጨማሪ እንግሊዘኛ ቋንቋ ያንኑ ካሪኩለም ጠብቆ ማስተማሩ ነው። እኛ ትምህርት ቤቱን የመረጥነው ተጨማሪ ቋንቋ ስለሚያስተምር ነው። - በተቀመጠው አማራጭ ሁለት ቋንቋ እያስተማረ ነው። አፋን ኦሮሞ እና አማርኛ በትምህርት አይነት ደረጃ እየተማሩ ነው። የቀረ ነገር የለም። - በመደበኛው ፕሮግራም ምንም የተጣሰ ነገር የለም። የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ትምህርት ቤቱ ብዙ ጥሰት ፈጽሟል ብለዋል። አቶ አድማሱ ደቻሳ ምን አሉ ? ° የትምህርት አይነት ጨምሮ ማስተማር ° የክፍለ ጊዜ ጥሰት ° የትምህርት ቋንቋ አለማክበር ° የአፍ መፍቻ ቋንቋ የሀገራችን " እንግሊዘኛ ነው " ብሎ ስታንዳርድ እስከመያዝ መድረስ፤ ° በእንግሊዝኛ አፋቸውን የፈቱ ካሉ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት አለ እዛ መማር ይችላሉ ግን በከተማው ፍቃድ የወሰደ ት/ቤት " የአፍ መፍቻ ቋንቋው እንግሊዝኛ ነው " በሚል ማስተማር አይችልም። ° የሀገር በቀል ቋንቋ ጠል መሆን ተገቢ አይደለም። ° ተጨማሪ ቋንቋ በጥናት የተመለሰ ነው ይህንም እንዲታወቅ ብዙ ተሰርቷል ይህ ሆኖ እያለ ' አናውቅም፣ አልሰማንም ፣የሚመጣ ነገር የለም ' የማለት ነገር አለ። አንድ ወር ለቀረው የትምህርት ጊዜ ይህን ውሳኔ ለምን አሳለፋችሁ ? ለምን አልታገሳችሁም ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፦ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፦ " እኛ እልህ እየተጋባን አይደለም። የተወሰደው እርምጃ ከ4 ወር በፊት ነው። ነገር ግን ት/ቤቱ ተማሪና ወላጆችን መጠቀሚያ ለማድረግ ጥረት አድርጓል። እርምጃው ከተወሰደ ግን ቆይቷል። ከፈተና ጋር ተያይዞ ግልጽ ነው አንድ የትህምህርት ተቋም እውቅና ፍቃድ ኖሮት ወደ ፈተና ስርዓት ሲገባ ኮድ ይሰጠዋል ይህ የትምህርት ተቋም የእውቅና ፍቃዱ ቀድሞ የተነሳ ስለሆነ ኮድ ሊሰጠው አይችልም። ኮድ ባልተሰጠበት ትምህርት ተቋም ተማሪዎች ይፈተኑ ቢባል ፈተናቸው ሊታረም አይችልም። ስለዚህ ኮድ ወዳለው ትምህርት ተቋም ወስደን ነው የምናስፈትናቸው።  " ሲሉ መልሰዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 መሆኑን ይገልጻል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...
#AddisAbaba ምንም አይነት የገቢ ምንጭ ለሌላቸው 1,051 ሴቶች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የቴክኖሎጂ እቃዎች ድጋፍ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል። ድጋፉ የተደረገላቸው በቤት ለቤት በተካሄደ ልየት ነው ተብሏል። ቢሮው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣  " ሴቶችን ኢኮኖሚ ላይ ስናያቸው ከ153 አገራት 153ኛ ደረጃ ላይ ናት ኢትዮጵያ። ይሄ ማለት ከግማሽ በመቶ በላይ ሴቶች የኢኮኖሚ ተደራሽነታቸው በጣም ዝቅተኛ ነው " ሲል ገልጿል። ይህን ታሳቢ ተደርጎ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑና በቢሮው ካፒታል አማካኝነት በተሸፈነ በጀት ከአኗኗራቸው ጋር ይስማማል ብለው ሴቶች የመረጧቸውን ኦቨን፣ የኤሌክትሪክ ምጣድና ሌሎች እቃዎችን ለ1,051 ሴቶች ድጋፍ መደረጉ አሳውቋል። በቀጣይ 2,000 ያህል ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን ለሴቶች ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን አመልክቷል። ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ ከ400ዐ በላይ ለሚሆኑ ሴቶች ድጋፍ መደረጉን፣ ድጋፉ የሚደረገው የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያ ላላቸው፣ ምንም አይነት ገቢ ለሌላቸው፣ ለአካል ጉዳተኞች ነው ተብሏል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Mostrar todo...
#SamiTech አዳዲስ ላፕቶፕች  ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!! @samcomptech በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና  በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ  ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን። ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን። የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ። @sww2844 0928442662 / 0940141114 https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
Mostrar todo...
4😢 2
Addis Ababa University- Cisco Networking Academy @CiscoExams www.netacad.com www.cisco.com Online Live class - Cybersecurity Training & Certification Preparation. Registration Date: April 22 to May 26, 2024 Class start date: May 27, 2024. Course Recognitions:- Trainees will receive 4 certificates of training completion; 4 digital badges & 32% discount for LPI Linux Essentials and 58% discount for CyberOps Associate Certification exam voucher. Mobile 0902-340070/ 0935-602563/ 0945-039478 Office : 011-1-260194 Follow our telegram channel: @CiscoExams
Mostrar todo...
8😱 2🥰 1
" ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት " - አቶ ጌታቸው ረዳ በማህበራዊ ሚዲያ " ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ሊዋሃድ ድርድር እየተካሄደ ነው " የሚሉት መረጃዎች ፍጹም ሐሰተኛ ናቸው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ለ ' ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ' ተናግረዋል። ብልፅግና እና ህወሓት ንግግር ማድረግ መጀመራቸውን የገለጹት አቶ ጌታቸው "  እነዚህ ንግግሮች ከውህደት ጋር የተያያዙ አይደሉም " ብለዋል። " የቅርብ ጊዜው ንግግራችን የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ስለማድረግ ነው። ውህደት አጀንዳም ሆኖ አያውቅም " ሲሉ ገልጸዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር ስላላቸው የስራ ግኝኑት በተመለከተ ፥ " ጥሩ የሥራ ግንኙነት ነው ያለን። የራሳችን የሆነ ልዩነት አለን። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ አመለካከቶች አሉን " ብለዋል። " የፕሪቶሪያው ስምምነት #አብረን_እንድንሠራ ዕድል ስለሰጠን፤ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ልዩነቶቻችን ምንም ይሁኑ ምን አብረን እንድንሠራ አስችሎናል። ይህም ወደፊት ይቀጥላል ብዬ አስባለሁ " ሲሉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ፤ አቶ ጌታቸው በጦርነቱ ወቅት የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ በሙሉ ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል። " ማንም ሰው ቢሆን፤ እኔን ጨምሮ መጠየቅ አለብን። ማንም ነጻ እንዲሆን መፈቀድ የለበትም። ሰላም እና ፍትህ ለማስፈን ያጠፋ መጠየቅ አለበት " ሲሉ ገልጸዋል። #BBC #FocusonAfrica @tikvahethiopia
Mostrar todo...
👏 862😡 314 220🕊 102🤔 72🙏 54😭 28😢 22😱 20
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት  አቶ ጌታቸው ረዳ ከ ' ቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ' ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር። በቃለምልልሱ ፥ ባለፉት ሳምንታት በአማራ እና ትግራይ አዋሳኝ አካባቢዎች የነበረው ግጭት በ " የሚሊሻ አባላት " መካከል እንጂ መደበኛ ኃይሎች የተሳተፉበት አልነበረም ብለዋል። " አማራ ክልል በኩል የነበሩ ሚሊሻዎች የተለያዩ አስጊ እንቅስቃሴያዎችን ሲያደርጉ ነበር። በእኛ በኩል ያሉ የሚሊሻ አባላት ምላሽ ሰጥተዋል " ሲሉ ገልጸዋል። የአማራ ክልል ያወጣውን መግለጫም  " መሬት ላይ ያለውን እውነታ ያላገናዘበ " ብለዋል። የሰላም ስምምነቱ #ተፈጻሚ_እንዳይሆን እያደረገ ያለው " ሕጋዊ የልሆነ የአማራ አስተዳደር ነው " ሲሉ ተደምጠዋል። አቶ ጌታቸው በዚሁ ቃለ ምልልስ ፥ በሰላም ስምምነቱ መሰረት በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉትን ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ከስምምነት መደረሱን አስታውሰዋል። " ሕጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮችን ለማፍረስ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር አብረን እየሠራን ነው። ከአማራ ክልል ጋርም ቢሆን በተወሰነ ደረጃ አብረን እየሠራን ነው " ብለዋል። " የፕሪቶሪያው ስምምነት ተፈጻሚ እንዳይሆን የሚሹ አካላት እንዳሉ ግን በጣም እርግጠኞች ነን " ሲሉ ተደምጠዋል። አቶ ጌታቸው እነዚህ አካላት እነማን እነደሆኑ በግልጽ በስም ጠርተው አልጠቀሱም። #BBC #FocusonAfrica @tikvahethiopia
Mostrar todo...
😡 456 309👏 64🕊 54😭 22😱 10🙏 10🤔 9🥰 7
#Raya እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ሪፖርት መሰረት ከራያ አላማጣ ገጠራማ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺህ በልጧል። 42 ሺህ ዜጎች ቆቦ ፤ 8,300 ሰዎች ሰቆጣ ይገኛሉ። የተፈናቀሉት ከራያ አላማጣ፣ ዛታ፣ ኦፍላ ነው። አብዛኞቹ ህጻናት ፣ ሴቶች ፣ ወጣቶች እና በእድሜ የገፉ አዛውንቶች ናቸው። #UNOCHA @tikvahethiopia
Mostrar todo...
😭 365👏 36😡 33😢 32 25🤔 17🕊 13🙏 9🥰 7😱 4
#Update ባይደን ፊርማቸውን አኑረዋል ፤ ቲክቶክ " ፍርድ ቤት እንተያይ " ብሏል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በባይት ዳንስ ባለቤትነት ያለው " #ቲክቶክ " ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ ተሽጦ ከቻይና ካልተፋታ በመላው አሜሪካ #እንዲታገድ የቀረበላቸው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን በማኖር ሕግ ሆኖ  እንዲወጣ አድርገዋል። " ቲክቶክ " ድርሻው ለአሜሪካ ኩባንያ እንዲሸጥ የተሰጠው ጊዜ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ብቻ ነው። በዚህ ጊዜ ይህንን ካላደረገ #እስከወዲያኛው ከአሜሪካ እንደሚታገድ ተገልጿል። አሁን በአሜሪካ ብቻ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት " ቲክቶክ " ሙሉ በሙሉ የመታገዱ ነገር #እውን ወደ መሆኑ ተቃርቧል። የቲክቶክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ሹ ዚ ቼው ፥ " የትም አንሄድም። ለመብታችን በፍርድ ቤት እንታገላለን። ሀቁ እና ህገ መንግስቱ ከጎናችን ናቸው፣ እናሸንፋለን ብለን እንጠብቃለን " ሲሉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ፤ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን ፣ እስራኤል እና ታይዋን የቀረበው የ95 ቢሊዮን ዶላር የድጋፍ ጥቅል ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል። @tikvahethiopia
Mostrar todo...