cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

የልቤ ትኩሳት ፨ቅንጭብጭብ መጣጥፎች, ግጥሞች ምስልን በ ቃላት አና የምንኖራቸው እውነቶች በጥብ

Advertising posts
422Suscriptores
-124 hours
-17 days
+730 days

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

✨የዛሬ ደስታህ የዛሬ ነው። የነገ ደስታህ የነገ ነው። ፈጣሪ አንተን የሚያስደስትህ ነገር ሊሰጥህ ምንም እጥረት የለበትም። አንተ ብቻ በሆነውም ባለህም በሚሆነውም በሁሉም ተደሰት። ውስጥህ የሚያሳምምህን ሳይሆን የሚያስደስትህን እይ። ውስጥህ የሚያሳዝንህን ሳይሆን የሚያዝናናህን እይ። ውስጤ ያለችውን ትንሽዬ ደስታ አስተውዬ ባየሁ ጊዜ ግን የፈጣሪን መልካምነትና ቸርነት አያለሁ። የፈጣሪን ደግነትና ቅንነት አስተውላለው። ከምንም በላይ የፈጣሪን ፍቅር አያለሁ። በየቀኑ በየሰአቱ በየደቂቃው ከስምንት ቢሊዮን የዓለም ሰው ሁሉ እኔንም አለመርሳቱ ይደንቀኛል። ውስጤ በፈጣሪ የተቀመጠችውም ትንሽዬ የደስታ ቅባትም በአካሌ ውስጥ ካሉትና በላዬ ላይ ከተፈጠሩት አሉታዊ ነገሮች ሁሉ ትልቃለች። 💡ውስጤ ያለችው ሚጢጢዬ የደስታ ፍንጣቂ ካጋጠሙኝ የሂወት መሰናክሎች ሁሉ ትገዝፍብኛለች። ያኔ ላለመሳቅ ምክንያት አጣለሁ። ከውስጤ የተፈጠረው ደስታ በፊቴ ላይ ይደገማል። መጀመሪያ ውስጤ ይስቃል በመቀጠል ጥርሴ። ከዛ ደሞ የኔ ደስታ ከኔ አልፎ በዙሪያዬ ያሉት ላይ ይጋባና እነሱም ይስቃሉ። የእውነት ፈጣሪ እንዴት ድንቅ ነው። በሱ ላይ እምነታችንን በጣልን ጊዜ ልባችንን በደስታ ፊታችንን በፈገግታ ይሞላዋል! በእውነት የፈጣሪን ጥበበኝነት መመስከር ከፈለጋችሁ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ውስጠ ውስጣችሁን ተመልከቱ። ያኔ የምታገኙት የደስታ ጨረር ከከበቧችሁ ችግሮች ሁሉ ይበልጡባችኋል። ያኔ ከልባችሁ ትስቃላችሁ። 📍የበለጠ የፈጣሪን የእውቀት ጥግ ደሞ የምታዩት በምንምና በየትኛውም ጊዜ ለእያንዳንዳችን እደግመዋለሁ ለእያንዳንዳችን የሚሆን ደስታ ሰቶናል! እሱ ጋ ስስት የለም። እሱ ጋ ማዳላት የለም። የተወሰኑትን አስደስቶ የተወሰኑትን የሚያስከፋ ሚዛናዊ ያልሆነ አምላክ አይደለም። ውስጣችንን በደንብ ማየት ስንጀምር በገንዘብ ልንገዛው የማንችለውን ደስታ እናገኛለን። ይህም ደስታ ሳቅን ይፈጥርልናል። ጥርሳችንም ከልብ በመነጨ ደስታ ፈገግ ይላል። 💡ዛሬ ይህንን በውስጣችን ያለውን ደስታ የምናይበትና ፊታችንን በሳቅ የምንሞላበት ቀን ነው። አስተውለን ወደ ውስጥ እንይና ውስጣችን ያለውን ደስታ በፊታችን ላይ እንዲንጸባረቅ እንፍቀድለት!ውስጣችንን ስናይና ፈጣሪ ውስጣችን ያስቀመጠውን ድንቅ ስጦታ ስናስተውል ፤ያኔ አለመሳቅ ይከብደናል። አለመደሰት ታሪክ ይሆናል። ከፈገግታችሁ ጀርባ ያሉትን ብዙ ችግሮች መከራዎችና ማጣቶችን ሳይሆን ትንሿን ጥሩ ተአምር እዩ፤ያኔ ትንሿ ብዙ ትሆናለች። ከውስጥ የተጫረችው ሚጢጢዬም የደስታ ፍንጣቂ ከናንተ አልፋ ለዓለም ሁሉ የምትበቃ ትሆናለች። 🔑 ከውስጥህ ያለው ብዙ ነው። ከውስጥሽ ያለው ድንቅ ነው። ፈጣሪንም ለሰጣችሁ ሁሉ አመስግኑ! እውነቴን ነው ውስጠ ውስጣችሁ ያለውን ስታስተውሉ (ማየት ብቻ አይደለም ማየት ወስጥ ማስተዋል ካልተጨመረበት ትርጉም የለውም) ያኔ ባላችሁ ሁሉ ትገረማላችሁ። ✍ብሩክ የሺጥላ ውብ አሁን❤️ @Ethiohumanity @Ethiohumanity@EthiohumanityBot
Mostrar todo...
እናት በገንዘብ እጦት ምክንያት ታክሞ መዳን የሚችለውን ልጇን ስታጣ እንደማየት የሚጎዳ የለም። ድህነት ጥሩ ኑሮ ላለመኖራችን ጥፋቱ የራሳችን ይመስለናል፣ ግን አይደለም የስርዓቱ ችግር ነው። ስርዓቱ እኛን ለመጣል የተገነባ ነው። ምክንያቱም ስርዓቱ የተገነባው በእኛ ውድቀት ላይ ስለሆነ። ስለዚህ የመደብ፣ የዘር፣ የሐይማኖት እና የፖለትካ ጥያቄውን ትተን የሰብዓዊነት ጥያቄ እናንሳ። ምናልባትም ያኔ ለችግሮቻችን መፍትሄ እናገኝ ይሆናል። ኤርኔስቶ ‘ቼ’ - ጉቬራ
Mostrar todo...
"የሞት መድኀኒት" ሦስተኛ ዕትም በሁሉም የመጽሐፍ መደብር! #ሂትለር ጨካኝ ነበር አይሁዶችን ያለ ርህራሄ የገደለ ሞት ፊት ሲቆም ግን እጅግ ፈሪ! #ላቬርኒቲ ቬሪ የእስታሊን ቀኝ እጅ በጣም ጨካኝ ገዳይ ነበር ሞት ያስለቀሰው! #ሳዳም ላለመሞት በማይመጥነው ጉድጓድ ለስምንት ወር የተደበቀው ሞትን ፈርቶ ነበር! #መንግስቱ ከሀገር የሸሸው እንዳይሞት ፈርቶ ነው፡፡ #የዓለም ጠበብት ሞትን ከመፍራታቸው የተነሳ ለማስቀረት ለፍተዋል ደክመዋል አልሆነላቸውም! #የዓለም ሀብታሞች እንዳይሞቱ ስንት ገንዘብ አውጥተዋል ወጥተው ወረዱ አልሆነም! #በየትኛውም እምነት ያሉ ቅዱሳን ስለ ሞታቸው ቀን ተጨንቀዋል፡፡ ሞት ቅዱሱንም እርኩስ የምንለውንም የሚያስጨንቅ አስፈሪ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም ሞት በራስ ላይ ሲሆን ሰዎችን ያለ እርህራሄ በዘራቸው፣ በሐይማኖታቸው፣ ወይ በግል ፍላጎታችን እንደ መግደል ቀላል አይደለም፡፡ እጅግ ያስጨንቃል... ከ "ሞት መድኀኒት"
Mostrar todo...
ዛሬ ራሴን የማሰላሰል እና የማሰላሰል ቦታ ላይ አገኛለሁ። ምንም ያህል ሀሳቤን ለመግለጽ ብሞክር ማን እንደሆንኩ ወይም ምን እንደምፈልግ በትክክል የማይረዱ ሰዎች ያሉ ይመስላል። በነዚህ አፍታዎች ዝምታ እና ችላ ማለት ምርጥ አማራጮች ይመስላሉ. ያለማቋረጥ አለመረዳት እና ችላ እንደተባሉ መሰማት ተስፋ አስቆራጭ ነው። ሀሳቤ እና ምኞቴ በዙሪያዬ ላሉ ሰዎች የማይታዩ ያህል ነው ። እውነተኛ ማንነቴን መደበቅ ይሻላል ብዬ በማመን ወደ ራሴ መውጣት እና አለምን መዝጋት ያጓጓል። ከስር ግን ዝምታ እና ችላ ማለት መፍትሄ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ጊዜያዊ እፎይታ ሊሰጡ ይችላሉ, ነገር ግን አለመግባባቶችን እና አለመግባባቶችን ያራዝማሉ. ሌሎችን በመዝጋት፣የእድገት፣የግንኙነት እና የመረዳት እድል እራሴን እክዳለሁ። ወደ ዝምታ ከማፈግፈግ ይልቅ ለመናገር እና ፍላጎቶቼን እና ፍላጎቶቼን ለመግለጽ ድፍረት ማግኘት አለብኝ ግን የማይመች ሊሆን ይችላል, እና ውድቅ የማድረግ ወይም ተጨማሪ አለመግባባት አደጋ አለ, ነገር ግን መውሰድ ያለበት አደጋ ነው. ራሴን በትክክል በመግለጽ፣ ለእውነተኛ ግንኙነቶች እድሎችን መፍጠር እና በጋራ መግባባት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት መፍጠር እችላለሁ። በተመሳሳይ ጊዜ ሁሉም ሰው ሊረዳኝ ወይም ሊቀበለኝ እንደማይችል እና ያ ደህና ነገር ነው  እንደ ሰው ያለኝን ዋጋ ወይም ዋጋ የሚያሳይ አይደለም። ሁላችንም አለምን እንዴት እንደምናስተውል የሚቀርፁ የተለያዩ አመለካከቶች እና ልምዶች አሉን። ሁሉንም ሰው ማስደሰት ወይም ሁሉም እንዲረዳ ማድረግ አይቻልም። ከሌሎች ማረጋገጫ ከመፈለግ ይልቅ ራሴን በመቀበል እና በመረዳት ላይ ማተኮር አለብኝ። የእኔ ሀሳቦች፣ ስሜቶች እና ፍላጎቶች ትክክለኛ እና አስፈላጊ መሆናቸውን በመገንዘብ ራስን ርህራሄ እና ራስን መቀበልን ማዳበር በጣም አስፈላጊ ነው። እራሴን በመመዘን፣ በጸጋ እና በትግስት አለመረዳት ፈተናዎችን ማለፍ እችላለሁ። በብስጭት ወይም በተጎዳ ጊዜ፣ እራስን መንከባከብን መለማመድ አስፈላጊ ነው። ደስታን በሚሰጡኝ እንቅስቃሴዎች መሳተፍ፣ ከሚደግፉ ጓደኞቼ ወይም ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ወይም የባለሙያ መመሪያ መፈለግ ሁሉም ለደህንነቴ የበኩሌን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። እራሴን ማዳመጤ ውስብስብ ነገሮች በተሻለ መንገድ እንድመራ እና ፍላጎቶቼን በብቃት እንድገልጽ ይረዳኛል  እኔ ልዩ ሀሳቦች እና ስሜቶች ያሉት ውስብስብ ግለሰብ ነኝ። የእኔን እውነተኛ ማንነት ነው ብለው የሚሰጡኝ ሳይሆን ነው ብለው እንዲያስቡ የፈቀድኩላቸውን ብቻ ነው።
Mostrar todo...
ግለሰብ ፣ ማህበረሰብና ሀገር ማለፍ ያለባቸው ተገቢ የሆነ የዕድገት መሰላሎች አሉ፡ እነዚያ መሰላሎች ረጅምና አድካሚ ቢመስሉም ስናልፋቸው በራስ መተማመንን የሚያጎናፅፉ ፣ ጠንካራ መሠረት የሚጥሉ ጥሩ መምህራን ሆነው እናገኛቸዋለን በእርግጥ ዓመታት ቢፈጅም በእምነበረድ ስለሚሠራ ቤት ፣ ምንጣፍ ስላለው ቢሮ ፣ ከረቫት በሙሉ ልብስ ስለ መልበስ አሁን እንግዳ አይደለሁም ። ሀለቱ ጓደኞቼ በትላልቅ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች በከፍተኛ ኤክስፐርትነት ይሠራሉ እኔም ወረዳና ዞንን አልፌ ክልል ደርሻለሁ ከዚያ አልፎ ለመሄድ በራስ መተማመ E ና ዕድሉ አለኝ ለሁሉም ጊዜ አለውና !!!በሰው ልጅ የአካላዊም ፣ የአዕምሯአዊም ሆነ ማህበራዊ ዕድገቶች መታለፍ የሌለባቸው ደረጃዎች አሉ፡ ከታች የነበርከው ድንገት ከላይ ከሆንክ በኋላ ዘመንህ የመካከሉን እንደገና ማለፍ ግዴታህ ይሆናል ። እያንዳንዱ የሕይወት ምዕራፍ ለሚቀጥለው ተገ ግብዓት ነው : በሥነ ሕይወት ትምህርት ( Biology ) ሜታሞርፈስ የሚባል የነፍሳት እድገት አለ፡ እንቁላል- እጭ- ኩብኩባና- ጉልምስ ናቸው : አንዱ አንዱን አይበልጥም አንዱ ከአንዱ አያንስም :: ይልቁንም አንዱ ለሚቀጥለው አስፈላጊ ነው : ከእነዚህ ደረጃዎች አንዱ ከተዘለለ ሙሉ አካል ያለው ነፍሳት ለምሣሌ ንብ አይገኝም :: በሰው ልጅም ፅንስ- ጨቅላ- ህፃን- ታዳጊ- ወጣት- ጐልማሳ- አረጋዊ የተፈጥሮ ቅደም ተከተሎች ናቸው፡ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትም ትርፍ በኪሣራ ፣ ማወቅ ባለማወቅ ይጀመራል ። ስልጣን በመታዘዝ ፣ ከላይም መሆን ከታች በመሆን ይጀመራል ።
Mostrar todo...
አንድ ቀን ታሪክ ሲኖረው የሆነ ጊዜ ነው።ወደኋላና ወደፊት የሚነበብ የታሪክ ገድል በሆነ ቀን ላይ የሆነ ቦታ አለ።የሆነ ጊዜ አለን‥የሆነ ነገር የሆንባቸው ካለፈውና ከሚመጣው የማይደባለቁ፣ የትኛውንም የማይመስሉ የሆኑ ጊዜዎች።ነፍሳችን አብዝታ የምታስታውሰው ቀንና ሰዐት፣ እለትናሳምንት፣ ወርና አመት። ዘመን በአንድ ቀን በአንድ እለት ቢቋጭ ያንን ይመስላል የምንለው እንዲደም እንዲሰለስ የምንመኘው እና ደግሞ ማስታወስ የማንፈልገው። ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ የማይደገሙ ነፍሶች አሉ።ከሄዱ የማይመለሱ ከራቁ የማይደረሱ፣ከጠፉ የማይተኩ፣ ለሕልውናችን እንዲሆኑ በልክና በመጠን የተበጁ። እኚህ ነፍሶች እኛን ሆነው እኛን መስለው በህይወታችን ውስጥ ስለበዙ ምንም ይመስሉናል..ግን አይደሉም የሄዱ ቀን እንድንሞት ሆነን ነው የተሰራንው እኚህ ሰውነቶች ለእኛም ለአለምም አንድ ጊዜ ናቸው።እውቀት ጥበብ ማስተዋላችን ሳይሆን ምናልባት ትልቁ ጸሎታችን ያመጣቸው ደጉ ፈጣሪያችን ያስጠጋቸው የጥሩነታችን ክፍያዎች ናቸው። ነፍስ እውቀት ከሌላት፣ ይወት ጥበብ ከጎደላት ሞቷን ፈጣሪ ናት የሰው ልጅ ባለማወቅ ብዙ ሞቶችን በራሱ ላይ ፈጥሯል አለማወቅ ጎጂ ነው አውቆ አለመጠቀም ደግሞ የበለጠ ጎጂ ነው።የምንሞተው ስላላወቅን ሳይሆን ያወቅንውን ባለመኖራችን ነው።ፍቅር ሽጋ እንደሆነ እናውቃለን ግን ባለማመን አጨቅይተንዋል ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ የክረምት ጀምበር ስትጠልቅ አትታይም ብርሀኗ ሲወር እንጂ ልክ እንደዚህ ሄደው ሲቀሩ እንጂ ሊሄዱ ሲሉ ያላየናቸው ነፍሶች ብዙ ናቸው። ፍቅር ከመትረፍረፉ በላይ እጥረቱ ነው የሚገለን።በፍቅር ሚዛን ሺህ አመት የአንድ መዐልት ያክል ይመዝናል በጥላቻ ሚዛን አንድ ቀን ሺህ ዘመን ነው እናም ፍቅር ገብቶ የወጣበት ሰውነታችን ሺ ዘመን ተሸክመንው የምንኖረው ሞትና ጉስቁልናችን፣ ጸጸትና ቁጭታችን ነው። ትካዜን በፍቅር እስካልገደልንው ድረስ በምንም አይሞትም። ፍቅር ለሁሉም አይነት የሰው ልጅ ደዌ በእመበለቷ እምነት ሀይል እንደወጣበት እንደ እየሱስ ቀሚስ ነው።ከምንም የሚያሽር። ጠላቶቻችሁን ለመሽንቆጥ ዱላና ድንጋይ፣አለንጋና ጅራፍ አትጨብጡ።በወደረኞቻችሁ ላይ ቂምና በቀል አትያዙ።ዱላና ድንጋይ ሳናነሳ አንዳንድ ክፉ ነፍሶችን መውገሪያ መርሳት የተባለ ጥበብ አለ። በአጋጣሚ ተገናኝተን የደራሲውን ሁለት ስራዎች እንዳነብ በመጋበዝ እነዚህን መጽሐፍት አውቅ ዘንድ ምክንያት የሆንከኝን Getu Bekele  ከልብ አመሰግናለሁ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ▣ትርታ  በ Makbel Teshome
Mostrar todo...
"ሁሉም ጥሩ ይሆናል" የጠመመው ይቃናልናል፣ የተበላሸው ይስተካከላል ፣ ጥላቻችን ጊዜ ያሸንፈዋል ፣ የበደለንን ይቅርታ እናደርጋለን ፣ ያቄመብን ይረዳናል፣ የጀመርነውን እንጨርሳለን ፣ያቀድነውን እንተገብራለን ፣ ህልማችን እውን ይሆናል ። አሻግረን ተስፋ እናያለን !! ከባድ ነበር እንላለን ፣ ቁስላችን ይደርቃል ፣ ሃዘናችን ግዜ ይፈውሰዋል ። ድካማችን ፍሬ ያፈራል ፣ጨለማው ይነጋል ፣ "ሁሉም ጥሩ ይሆናል" ስራ እናገኛለን፣ጤናችን ይስተካከላል ፣ ከአምላካችን ጋር እንታረቃለን ፣እራሳችንን ይቅርታ እንላለን ። ሁሉም ጥሩ ይሆናል እንለመልማለን፣ የውነት እንስቃለን ፣ እንወልዳለን፣ ከልጆቻችን ጋር እንላፋለን ፣ ወላጆቻችንን እንጦራለን እንመረቃለንም ስህተታችንን የማይደግሙ፣ አገር የሚሰሩ ፣ በመነጋገር የሚያምኑ ፣ተቋም የሚገነቡ ከዓለም ጋር የሚወዳደሩ ልጆች እናሳድጋለን ። ነገ እንደ ዛሬ አይሆንም !! ሁሉም ጥሩ ይሆናል!!
Mostrar todo...
አንድ ሰው በሥልጣን ሳቢያ ሊከፋ ይችላል፤ ሌላው ደግሞ በክብር፣ ሌላኛው ደግሞ በሐብት፡፡ አንዳንዱ ደግሞ የሚከፋው በፍቅር ሳቢያ ይሆናል፡፡ ሌላው ቀርቶ በእግዚአብሔር ጭምር ተስፋ የቆረጠ እና የተከፋ አለ፡፡ እግዜርን ለማግኘት ትፈልጋለህ፡፡ እግዜር በበረከቱ እንዲጎበኝህ ታልማለህ፡፡ ተመስጦ (meditate ማድረግ) ትጀምርና ወዲያው አንዳች ነገር በሕይወትህ ላይ እንዲመጣ ትጠብቃለህ፡፡ እግዜር እንዲወርድልህ፣ እንዲወርድብህ ትጠብቃለህ… አንዳንድ ሰዎች አጋጥመውኛል - በቀን ለ15 ደቂቃ ለሰባት ቀን ተመሰጥን (meditate አደረግን) ብለው ይመጡና፣ “እየተመሰጥን ነበር ግን መለኮት አልተገለፀልንም … ልፋታችን ሁሉ ከንቱ ሳይሆን አይቀርም” ይሉኛል፡፡ ልብ አድርጉ … ለሰባት ቀናት ያህል በቀን 15 ደቂቃ መድበው ሲያበቁ፣ ‘እስካሁን ድረስ ግን እግዚአብሔርን አላየንም’ እያሉ ያጉረመርማሉ - “ይሄን ሁሉ ለፍቼ እግዜር ዘንድ መቅረብ አልቻልኩም … ምን ላድርግ ?” ይሉኛል፡፡ እግዜርን፣ መለኮትን ስንፈልግ እንኳ የሆነ ነገር እንዲሆን የመጠበቃችን ነገር አልቀረም፡፡ የሆነ ነገር እንዲሆን መጠበቅ በራሱ መርዝ ነው፡፡ ለዚህ ነው ተስፋ መቁረጥና ሐዘን የበዛው - መሆንም አለበት፡፡ የጠባቂ አእምሮን ውሸትነት፣ መርዛማነት በመጀመሪያ ደረጃ ተረዱ፡፡ እናም ቀስ በቀስ ነገሩን እየተረዳችሁት፣ ንቁ (Aware) እየሆናችሁ ስትመጡ መጠበቁ በራሱ እየቀረ እየቀረ ይመጣል፤ በዛውም ልክ ሐዘን እና መከፋት የሚባሉት ነገሮች አያገኝዋችሁም... ስለዚህም፣ “ለምንድነው በዓለማችን ተስፋ መቁረጥ፣ መከፋት እና ሐዘን የበዛው ?” ብለህ አትጠይቅ፡፡ ይልቁንም፣ “ለምንድነው እኔ የማዝነው ? የምከፋው ? የምበሳጨው ?” ብለህ ጠይቅ፡፡ ይሄኔ መላው ነገር ዓለሙ ተለውጦ ታገኘዋለህ፡፡ አንድ ሰው … ዓለም ለምንድነው እንዲህ በተስፋ መቁረጥና በሐዘን የተሞላችው ብሎ መጠየቅ ሲጀመር፤ በዓለማችን ላይ ያለው ተስፋ መቁረጥና ሐዘን እንዲቀንስ መጠበቅ ይጀምራል፡፡ ግን ደግሞ መላው ዓለም ተስፋ ይቁረጥ አይቁረጥ፣ ዓለም ይዘን አይዘን - አንተ ግን እንዳዘንክ እንደተከፋህ ነው፡፡ አዎ … መላው ዓለም እንደተከፋ ነው - ይህ እውነት ነው፡፡ እናም ለምንድነው እኔ ሐዘን የተጫነኝ፣ የምከፋው፣ የተከዝኩት፣ የምበሳጨው ብለህ ጠይቅ - መርምር፡፡ በራስሁ መጠበቅ (expectation) ሳቢያ እንደሆነ ትደርስበታለህ፡፡ አዎን ዋናው ፍሬው፣ ሥሩ እሱ ነው፡፡ ወርውረህ ጣለው… ስለዓለም አታስብ፤ ስለራስህ አስብ፡፡ አንተ ራስህ ዓለም ነህ፡፡ አንተ መለወጥ ስትጀምር ዓለምም አብራ መለወጥ ትጀምራለች፡፡ የዓለም አንዱ ክፍል፣ ውስጠኛው ክፍል መለወጥ ሲጀምር - ዓለም መለወጥ ትጀምራለች፡፡ ሁልጊዜ ዓላማችን ዓለምን ለመለወጥ ነው፡፡ ይሄ ከራስ ችግር የማምለጫ መንገድ ነው፡፡ ሁሌም እንደምረዳው፣ ሰዎችን ለመለወጥ የሚሹ፣ ስለሰዎች መለወጥ የሚብሰለሰሉ ሰዎች ከራሳቸው ሐዘን፣ ጭንቀት፣ ከራሳቸው ጋር ከገጠሙት ፀብ ለማመለጥ በሚል የፈጠሩት ማምለጫ ነው… ራሳቸውን ለመለወጥ ፍቃደኛ ስላልሆኑ፣ አእምሯቸው ስለራሳቸው ችግር እንዳያስብ፣ በሌላ ጉዳይ እንዲጠመድ በሚል ነው ስለሌሎች የሚያስቡት - ከራስ ችግር ለመሸሽ በሚል ነው፡፡ ራስን ከመለወጥ ይልቅ፣ ዓለምን ለመለወጥ መሞከር ይቀላል፡፡ ግን ደግሞ ዓለምን መቀየር አይቻልም፡፡ ዓለም ቢቀየርም ራሳችንን ካልቀየርን - ያው የድሮው መከረኛ ሰው ከሆንን ምን ለውጥ አለው ለእኛ ? ምንም !! የራስህን መከፋት መንስዔ፣ የሐዘንህን ሰበብ ማወቅ እንዳለብህ አትዘንጋ !!! እናም በቶሎ ማወቁ ይመረጣል፡፡ ሁኔታዎች ይለያያሉ - ግን የሁሉም መከፋት፣ ሐዘንና የልብ ስብራት ሰበቡ ግን አንድ ነው - መጠበቅ
Mostrar todo...
ይሄ ዓለም በመከፋት ተሞልቷል፡፡ አንድም ያልተከፋና ተስፋ ያልቆረጠ ሰው ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ ፃድቅ ተብዬዎቻችሁ ጭምር ተስፋ ቆርጠዋል፣ አዝነዋል፣ ተከፍተዋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ተከታዮቻቸው ናቸው፡፡ ፃድቅ ተብዬዎቹ ተከታዮቻቸው፣ ደቀ መዛምርቶቻቸው እንዲህ እንዲያደርጉ፣ እንዲያ እንዳያደርጉ ይጠብቃሉ፡፡ የጠበቁት ሳይሆን ሲቀር ደግሞ ተስፋ ይቆርጣሉ - መሆንም አለበት፡፡ አንድ ነገር እንዲሆን ከጠበቅክ ተስፋ መቁረጥና ማዘን አይቀሬ ነገር ነው… ሰራተኛ ተብዬዎቻችሁም እንዲሁ ተስፋ ቆርጠዋል፣ አዝነዋል - ምክንያቱም የሚጠብቁት ነገር አላ፡፡ ምክንያቱም ማህበረሰቡ እንዲከተል የሚፈልጉት ሐሳብ አለ፡፡ ሕዝቡ እሺ ብሎ በዚያ መንገድ እንዲሄድ ይፈልጋሉ፤ ይጠብቃሉ፤ ተስፋ አድርገዋል፡፡ ከመጠን በላይ ተስፋ አድርገው እየጠበቁ ነው፡፡ በእነሱ ቤት መላው የሰው ልጅ አሁኑኑ በእነርሱ መንገድ መሄድ አለበት፡፡ ማህበረሰቡ የእነርሱን ፍልስፍና እንዲከተል ይፈልጋሉ፡፡ ዓለም ግን ለዚህ ጉዳይ ግድም የላት፡፡ ዓለም በራሷ መንገድ ነው የምትሄደው - ስለዚህም ተስፋ ቆርጠዋል፣ ልባቸው ተሰብሯል፣ አዝነዋል፡፡ በዚህ ዓለም ተስፋ ያልቆረጠ፣ ያላዘነና ያልተከፋ ሰው ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ እናም እንዲህ ዓይነት ሰው ካገኛችሁ፣ ይህ ሰው፣ በዕርግጥም፣ መንፈሳዊ ሰው እንደሆነ እወቁ፡፡
Mostrar todo...