cookie

Utilizamos cookies para mejorar tu experiencia de navegación. Al hacer clic en "Aceptar todo", aceptas el uso de cookies.

avatar

ቅንጭብጭብ

ካየሁት 👀 አስገራሚ ከሠማሁት 👂 መሣጭ ካነበብኩት 📖 አስተማሪ ካሠብኩት ♀🅱 ልዩ ልዩ እነሆ #ቅንጫቢ ፅሁፎቻችሁን በ @bcrAzykid አካፍሉን። ለማንኛውም አስተያየት ጥያቄ እና ጥቆማ @bcrAzykid ይጠቀሙ።

Mostrar más
Publicaciones publicitarias
8 156
Suscriptores
Sin datos24 horas
Sin datos7 días
Sin datos30 días

Carga de datos en curso...

Tasa de crecimiento de suscriptores

Carga de datos en curso...

Mostrar todo...
Ibex Photography

Photography Decor Dj Phone no - 0945965456 Telegram - T.me/ibexet Facebook - m.facebook.com/ibexet

እንኳን ደስ ያለን! የደጋ ዳሞቱ ሙሉ ኢኮሎጅ መገኛ የሆነው የጮቄ ተራራ የ2022 ምርጥ የቱሪዝም መንደር ተብሎ በተባበሩት መንግስታት የዓለም የቱሪዝም ድርጅት ተመርጧል። ጮቄ ተራራ 4100 ሜትር አማካኝ ከፍታ ሲኖረው በተለምዶ የጎጃም ጣራ በመባል ይጠራል፡፡ ቦታው ተራራማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በጣም ቀዝቃዛና ረግረጋማ በመሆኑ ነው ጮቄ የሚል ስያሜ የተሰጠው፡፡ የጮቄ ተራራ ሰፊ ተፋሰስ የሚሸፍን ሲሆን ሰባት የሚሆኑ የምስራቅ ጎጃምና ምዕራብ ጎጃም ወረዳዎችን ያዋስናል። ከ57 አገራት የተመረጡ 136 የቱሪዝም መንደሮች ለውድድር በቀረቡበት የ2022 ምርጥ የቱሪዝም መንደር ዓለምአቀፍ ውድድር ጮቄ ተራራን ለአሸናፊነት ያበቃው በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ የሚገኘው የሙሉ ኢኮ ሎጅ ከፊል ገጽታ ይሄን ይመስላል። Source፦ https://www.unwto.org/news/best-tourism-villages-of-2022-named-by-unwto?utm_source=ssmm&utm_medium=ssmm&utm_campaign=ssmm Join us - t.me/ibexevents Contact us - 0945965456 / 0928412796
Mostrar todo...
ወንጪ | Wenchi የጉዞ ዋጋ - በሰው 1400 ብር ብቻ ለውጭ ዜጋ - 40$ (1700ETB) ⚠️ ከታህሳስ 12 በኋላ - 1550 ብር የክፍያ አማራጮች CBE - 1000162799828 Abyssinia - 46591402 የቦታ ርቀት - ከአዲስ አበባ 160 ኪሎ ሜትር የጉዞ ቀን - እሁድ ታህሳስ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ክፍያው፦ የቁርስ፣ ምሳ፣ የታሸገ ውኃ፣ የመግቢያ ክፍያዎች፣ የአስጎብኚ፣ የፎቶግራፍ የጀልባ ላይ ጉዞ... ክፍያዎችን ያጠቃለለ ነው። ክፍያው በግል የሚደረጉ ፍላጎቶችን ለምሳሌ - ለስላሳ እና አልኮል መጠጦችን እንዲሁም የፈረስ ግልቢያን ወጪ አያካትትም። Ibex Events & Hiking'ን ስለመረጡ እናመሰግናለን። የከፈሉበትን ደረሰኝ በፎቶ @ibexet / @yoti27 ላይ ይላኩልን ለጉዞ ሲመጡ ደረሰኝ መያዝዎን አይርሱ። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን የምንልክ ይሆናል። በ Telegram t.me/ibexevents በ facebook m./facebook.com/ibexevent ይቀላቀሉን። ለበለጠ መረጃ - 0928274196 / 0945965456 ይደውሉ።
Mostrar todo...
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ #ከማስታዎሻየ_ማህደር!! . . . #ህይወት_የመኖር_እዳ!! . . .. ከተወለድኩ ጀምሮ እድሜዬ በጨመረ ቁጥር ወደ ህይወት እየመጣሁ ይሆን ወይስ ወደ ሞት እየሄድኩ እንደሆን አላዉቅም! ስለ ህይወት እያወኩ ለመኖር እየጀመርኩ ግን ወደ ሞት እየሄድኩ ይመስለኛል! መኖር ታዲያ እንዴት ስጦታ ሊሆን ይችላል?? ሐይማኖተኛ ሰዎች አንደበት ላይ እማይጠፋ ቃል "በህይወት ስላለህ ብቻ አመስግን!!" እሚለው ነው!! ግን ለኔ አይታየኝም! መፈጠሬን እንደስጦታ አይቼ ለማመስገን ህይወት በቃኝ እስክል መኖር አለብኝ! ካልሆናማ እንዲሁ ወደ ህይወት እየመጣሁ ወደ ሞት ከሄድኩ ስጦታነቱ ቀርቶ ኑሮ እዳ ይሆንብኛል!! ሳልሞት በፊት ተሽቀዳድሜ መኖር ያለብኝ እዳ ሁኖ ይሰማኛል። ሰው ሳይኖርም ይሞታል!    ህይወት ከፈጣሪ እምትሰጠን ብድር ትመስለኛለች ብድራችን ለመክፈል ስንፈጋ ስንታገል የተሰጠን የክፍያ የቀን ገደብ አልቆ እኛም በነፃነት ሳንኖር እምንነጠቃት ናት። የሰው ልጅ ሁሉ "የህይወት ግብ ደስተኛ መሆን ነው!" በምትለው ህግ ይተዳደራል! ይሄን ህግ ሐይማኖተኞች ቢያጥላሉትም በነሱ ልብ እንደማያምኑበት ቢናገሩም እነሱም በሆነ የህይወት ዘመናቸው ይከተሉታል። ሁሉም ሰው በራሱ ዛቢያ ኑሮን ለማሸነፍ ይሽከረከራል፤ ኑሮን ማሸነፍ ያው ሀፍታም መሆን ነው! ብሎ አዕምሮው ላይ በሰቀለው ሃሳብ ይነዳል። መፈጠሩን እንደ እዳ ለማየት ወይንም እንደ ስጦታ ለመቀበል በቀላሉ በአኗኗር ዘይቤው ይወስናል፤ ብዙዉን ጊዜ ሀፍትን ካካበተ ስጦተነቱን በተቃራኒው በድህነት ከተሰቃየ ደግሞ እዳነቱን ይቀበላል፤ እዚህ ላይ አንዳንድ ነገረኛ አንባቢ "ታዲያ አንተ በድህነት ተሰቃይተህ ነው! ህይወት የመኖር እዳ ናት የምትል" ይል ይሆናል! ግን ህይወት እንዳለህ ሀብት ወይም እዉቀት የምትወሰን ናት በሚለው አልስማማም!! ምክኒያቱም ህይወት አወቅንም አላወቅን ሀፍታም ሆን ወይ ፀደቅን እስክንሞት ድረስ እዳ ናት!! አዋቂው ህይወትን ተረዳኋት ባላት መጠን ሲያብራራና ሲያወጣ ሲያወርዳት ትንሽ በተጠጋት ቁጥር እማያዉቀው እልፍ መሆኑን እየተረዳ አለማወቁን አዉቆ እንኳ እረፍት ሳያገኝ የእዉቀት ጥሙን ሳያረካ ያርፋል!! አላዋቂዉም መኖር ባለማወቅ የሰጠችዉን ሰላም ተቀብሎ መኖሩ ሳይታወቅ በሚራመድበት መሬት የሆነ መስመር የእግሩ አሻራ ሳይታይ ይሞታል!! ሀፍታሙ ሃፍቱን የደከመበትን ያህል ሳያጣጥመው ወይ ደግሞ በሀፍቱ ልክ ደስተኛነቱ የወረደ ሲሆንበት! ወይ ሀፍቱ እረፍት እንደነሳው ሌላ አስደሳች ግብ ወይ ምላሽ ሲፈልግ ያልፋል!! ፃዲቁ ደግሞ የፈጣሪው ፍርድ እያስፈራው በአካባቢው ያሉ ሰዎች ኑሯቸዉን በሐጢያታቸው እየለካ የመኖር ጣእሙን እርግፍ አድርጎ ትቶ ሞቱ እንዲቀርብለት እየፀለየ ይኖራል!? መፈጠሩ ስጦታ ነው ብሎ ግን መኖሩን ከመሞት በላይ አይወደዉም! ስጦታ ብሎ የተቀበለዉን ህይወት በሞት መነጠቅን ይናፍቃል እንደናፈቀዉም አይቀርምና ያገኘዉና ይቀበላል!!    በነዚህ ሁሉ መሃል እኛ "ሁሉን ቀመስ!" እምንባል አይነት ሰዎች አለን!! የማህል ዳኛ ማለት ነን፤ ሌሎች በተለያየ አቅጣጫ የመኖራችን ግብ ብለው ያመኑበትን ሲያስቆጥሩ እምናጨበጭብ አንዳንዶች ደግሞ ሲደናቀፉም (ፋዎል) ሲሰሩ እምንታዘብ!! አለን። ለኛ ህይወት ጥያቄ እንጅ መልስ ሁና እማታዉቅ!! ህይወት የመኖር እዳ እንጂ ስጦታ ሁና እማትታየን!! ብዙ የገባን ይመስለናል ግን አንዳች ነገር አንፈታም! እምናምን ግን ደግሞ እማናምን! ወደ ህይወት እንመጣል ግን ደግሞ እማንደርስ! ወደ ሞት እምንሄድ!! እዉቁ ፈላስፋ.. "ያልተመረመረ ህይወት ለመኖር ያልተገባ ነው!" እንዳለው የኛ እዳ ጥያቄ የሆነ ነን። የናንተስ የመኖር እዳ ምንድን ነው?? እዳ ካልሆነ ስጦታነቱን በምን አመናቹህ? ስጦታነቱ ምኑ ላይ ነው? ተሰቶ እሚነጠቅ ስጦታ መሆኑንስ እንዴት ታዩታላቹህ? ወደ ህይወት እየመጣቹህ ነው ወይስ ወደ ሞት እየሄዳቹህ?? . . . ህዳር 28/2015 ዓ.ም ✍️Aman😑 YTZ @amanYTZ23 join 👇👇👇 @YelbeDrset @YelbeDrset ✍✍✍✍✍ inbox me @amanYTZ23 ✍✍✍✍✍ @kinchebchabi @kinchebchabi
Mostrar todo...
እወዳታለሁ ገራሚ ናት ደስስስ ትለኛለች። ብዙ ግሩም ጊዜ አሳልፈናል አብረን ስንሆን ሰአቱ ይበርብኛል አብረን ውለን ከመቼው መሸ ትለኛለች ቶሎ ቶሎ ትናፍቀኛለች። ቀልድ ይገባታል ኮስተር ብዬ ስኮምክ ታሽካካልኛለች፣ ነፍሳችን ይናበባል ፣ ሳናወራ እንግባባለን ። ከስምንት ወር በፊት <<አግባኝ>> አለችኝ አልተዘጋጀሁም አልኳት፣ ጊዜ ስጪኝ ፣ ትንሽ ታገሺኝ አልኳት <<አልችልም >>አለችኝ። የመንደሩ ሰዎች ሽሙጥ ፤ የቤተሰቦቿ ጭቅጭቅ እና እድሜዋ አስጨነቃት ። እኔ ደግሞ ባልተዘጋጀሁም አቋም ፀናው። ከህይወቴ መስመር መሰስ እያለች ሄደች። እየደበረኝ ቅር እያለኝ በአቆሜ ፀናው። አልፎ አልፎ ከአንገት በላይ ሃይ እንባባላለን። ባለፈው ሳምንት እንገናኝ አለችኝ። ተገናኘን ፤ አይኗ ውስጥ ጉጉት፣ ተስፋ እና ደስታ ምንም አላየሁም። <<በነገራችን ላይ ቅዳሜ ሰርጌ ነው ከቻልክ ልጠራህ ነው የመጣሁት>> አለችኝ። ትኩር ብዬ አየኋት ቅናቴን ለመደበቅ የደረቀ ፈገግታ ፈገግኩ (ደስስስ የማይል ስሜት ወረረኝ) ያሳዝናል አመለጥሺኝ አልኳት። <<ብሽቅ ስለሆንክ ተፈላሰፍክ መጠበቅ ፈልጌ አልቻልኩም>>አለችኝ እኔን የምትወደኝን ያህል የምታገባውን ልጅ እንደማትወደው ገብቶኛል። ያዘዘችውን ቢራ ተጎነጨች እና መጨዋወታችንን ቀጠልን። <<በእድሜህ ማሳካት የምትፈልገው ነገርን ዛሬ ካልጀመርከው መሽቶ በነጋ ቁጥር ጭንቀትህ ይበረታል ። ትልቅ ለመምሰል እንዳልጣርን ፤ አንድ ፍሬ ለመባል እንባክናለን። መንደርተኞች ሳይታወቃቸው ጫና ውስጥ ይከቱሃል ። ባገኙህ ቁጥር ጨዋታ ለመፍጠር ይሆን አሳስቧቸው ይሆን ብቻ ምንጩ ባልታወቀ ምክንያት እንደቀልድ ምንድን ነው መፍዘዝ አግቢ እና ሰርግ አብይን እንጂ ይሉኛል ። ቤተሰቦቼ ተጠርተው ስለበሉት ሰርግ ከሰርግ ሲመለሱ ይተነትናሉ ይገባኛል መልእክት እያስተላለፉ ነው ተረድቼሃለሁ ችስታ ነህ ብታገባ ድህነት ፓራላይዝ የሚያደርግህ ይመስልሃል በልጅነት እየራበህ እንዳደክ የነገርከኝን አልረሳሁም ። አሁን ካገባሁ የትላንት ህይወቴን እደግመዋለሁ ብለህ ትሰጋለህ። ሁኔታህ እና የኔ ፍላጎት አራምባ እና ቆቦ ሆነ ። እንደሁኔታ በቅርቡ በቀላሉ ትዳር የሚባል ስብጥር ውስጥ እንደማትገባ እርግጠኛ ነኝ ጌታ ይሁንህ ፤ እህቴ እንዴት ቆማ እንደቀረች አውቃለሁ .. . .. . ዘግይቶ ማግባት ለወንድም ምቾት እንደማይሰጥ ከልጅህ ጋ እየተንከባለልክ መጫወት ሲሳንህ ይገባሃል። ብልጥ ነኝ ባዮች ቆመው የሚቀሩት እየተመራመሩ ነው ፤ ህይወት በስሌት እና በምርምር ብቻ የሚሳካ እየመሰላቹ ነው>> ዝም አልኳት ንግግሬ ከዝምታዬ ካነሰ ለምን እናገራለሁ ። ያወራችው የቱ ነው ስህተት ?! ከነፍ ዝምታ በኃላ አይኖን ትክ ብዬ እያየሁ ትዳርሽ የተባረከ ይሁን አልኳት ። ፈጥኖ ከመሳሳት ዘግይቷ ትክክል መሆን በእጅጉ ይሻላል ደሞ ያልተሳካ ትዳር ቆሜ ቀረው የሚል ጥድፍያ ውጤት ነው ብዬ ተፅናናው። © Adhanom Mitiku @kinchebchabi @kinchebchabi
Mostrar todo...
#ቅንጭብጭብ_ኢትዮጵያ . . #ከማስታዎሻየ_ማህደር!! . . #ሌላ_ዓለም!! (ክፍል አንድ) . . .. ትናንት ህዳር 8/2015 ዓ.ም "አርባተንሳ" ክብረ በዓልን ልታደም ወደ ገጠራማው መንደር ካ'ንድ ወዳጄ በቀረበልኝ ጥሪ መሰረት ወርጀ ነበር። ወዳጀ ካለኝ ቦታ ደርሸ ካገኘሁት በኋላ ያው እንደተለመደው 'ቅርብ ነው ደርሰናል!' እያለ ሰፈር ለሰፈር ትንሽ ተጉዘን ከቤታቸው ደረስን የቤቱ ግቢ በላም በጥጃዎችና በእርሻ የተከበበ ነው። ግቢው በር ላይ የተቀመጡ ሰዎችን ሰላምታ ሰተን ወደ ቤቱ ዘለቅን.. የቤቱ አባወራ ከሳሎኑ ጥግ ይዘው ተቀምጠዋል..ቅድሚያ እርሳቸዉን ሰላምታ ሰተን በቤቱ ያሉ እንግዶችንም ጨበጥናቸው እና የበግ ቆዳ ከተጎዘጎዘበት መደብ ቁጭ አልን። ወዳጄ ቀልጠፍ አለና ወደ ኩሽናው ዘልቆ እህቱን ምግብ እንድታመጣ አዘዛትና "ክቡር ዘበኛ" እሚባለዉን ብርጭቆና በጆክ ጠላ ይዞ መቶ ከፊቴ ቆመ.. እኔም ከቤቴ እንደበላሁና ያው ጠላም እንደማልጠጣ በመናገር አስቤ የመጣሁት "ወተት ለመጠጣት!" እንደሆነ አስታወስኩት!😋 ቢሆንም 'ካልበላህ ወተት የለም!'😑 እሚል እይታ አሳይቶኝ ለራሱ ጠላዉን ቀድቶ ቁጭ አለ። በልቤም አንድ ቁርጥ አንስቼ እበላና ወተቴን እጠጣለሁ ብየ መጠበቅ ያዝኩ ታዲያ የወዳጄ እህት በሰሃን(ባቲ) የሰማይ ስባሪ እሚያክል እንጀራ በድንች በስጋ ወጥ ይዛ መታ አስረከበችኝ!! 'ኧረ በዝቷል ይተርፋል!' ብልም ሰሚ ስላላገኘሁ ወደ ወዳጄ አባት ፊቴን መልሸ 'አባት ይባርኩልኝ?' አላኳቸው(አክባሪ ለመባል) ምን ዋጋ አለው! 'ለወንድ አይባረክም! ዝም ብለህ ብላ!' ብለው ጨነገፉኝ።😬 ኩርኩሜን ተቀብየ ከወዳጀ ጋር የቀረበልኝን ምግብ መብላት ጀመርኩ.. ወዳጄ ምግቡን አቋርጦ ወደ ኩሽናው ተወነጨፈና በግራም ሰሃን እርጎ ይዞ መጣና እንጀራዉን መሸከም ያቃታት ሰሃን(ባቲ) ላይ እርጎዉን አጥለቀለቀው..😇 በላየላይ የወረደዉን መና እያጣጣምኩ በላሁ..😋 ታዲያ በየ መሃሉ አባወራው በመገረም ለምን ጠላ እንደማልጠጣ እየደጋገሙ ይጠይቁኛል! እኔም የተለያዩ መልሶችን እነግራቸዋለሁ.. ወዳጄና እህቱም እንጀራና ወጥ እያመጡ ጨምር እያሉ ከድንች በስጋው ወጥም ከእርጎና ከንጀራዉም ይከምሩብኛል..🙄'ኧረ በቃኝ!' ብልም የቤቱ አባዎራ ጨምሮ እንግዳቹ ሁሉ 'ትንሽ ብላ እንጅ!' እያሉ አጨናነቁኝ እኔ ግን ተሎ መሃላ ዉስጥ ገብቼ ድርቅ በማለት እጄን ታጠብኩና ቁጭ አልኩ..መቼም የገጠር ሰዎች እማይበላ እማይጠጣ አይወዱም። . . ይቀጥላል.. ✍️Aman😑 YTZ @amanYTZ23 join and share @YelbeDrset @YelbeDrset ✍✍✍✍✍✍ inbox me @amanYTZ23 ✍️✍️✍️✍️✍️✍️
Mostrar todo...
ወደ ቡልጋ - የለኝ ገደል የምናደርገው ጉዞ 4 ቀናት ብቻ ቀሩት እሁድ - ሕዳር 18 ክፍያው ምንን ያጠቃልላል? የቁርስ፣ ምሳ፣ የታሸገ ውኃ፣ የመግቢያ ክፍያዎች፣ የአስጎብኚ፣ የፎቶግራፍ የሻይ ቡና መጠጥ... ክፍያዎችን በሙሉ በዚህ ጉዞ ለመሳተፍ እርግጠኛ ሲሆኑ በ telegram @ibexet , @yoti27 "አለሁ" ይበሉ ወይም 0945965456 / 0928412796 ይደውሉልን። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን በውስጥ መስመር የምንልክ ይሆናል በ Telegram t.me/ibexevents በ facebook m./facebook.com/ibexevent ይቀላቀሉን። መልካም ቀን! ሰላም ለኢትዮጽያ! 💚💛❤ #Ethiopia #LandOfOrigins #hikinglovers #VisitAmhara #Bulga #Travel
Mostrar todo...
የታላቁ ሩጫ ቲሸርቶች አሉን 1 ፍሬ 1500 2 እና ከዛ በላይ1300 0945965456 ይደውሉ
Mostrar todo...
ጥቂት ቦታዎች ቀርተውናል ለጀማሪ ተጓዦች የሚሆን ከከተማ ጫጫታና ግርግር ወጣ ብለን ከተፈጥሮ አንነጋገር #ሱባ #አደሬተራራ ኑ! በመላው ኢትዮጵያ አብረን እንድረስ። ✅ Suba is 45km from Adiss and the Hiking covers about 16km. 🗓Hiking Date (nov 6 2022, ጥቅምት 27,2015) 🛑Departure Time-12:30 local time (Mexico Wabi Shebele Hotel) 💵Contributions Per person: 999 birr only ፨ Package Include 🚎Transportation 🍩 Snack 💧 Water 🥙 Lunch ☕️ Coffee 🎟️ Entrances 👨‍💼 Guide የጉዞ ዋጋ - በሰው 999 ብር ብቻ የክፍያ አማራጮች CBE - 1000162799828 Abyssinia - 46591402 ክፍያው በግል የሚደረጉ ፍላጎቶችን ለምሳሌ - ለስላሳ እና አልኮል መጠጦችን አያካትትም። Ibex Events & Hiking'ን ስለመረጡ እናመሰግናለን። የከፈሉበትን ደረሰኝ በፎቶ ይላኩልን፤ ለጉዞ ሲመጡ ደረሰኝ መያዝዎን አይርሱ። በtelegram t.me/IbexEvents ይቀላቀሉን ለበለጠ መረጃ - 0928412796 / 0945965456 ይደውሉ። Telegram @ibexet @yoti27 #hiking #Ethiopia #travel #LandOfOrigins #suba #visitoromia
Mostrar todo...
ኑ - በመላው ኢትዮጵያ አብረን እንድረስ ጉዞዎን ከእኛ ጋር ይጀምሩ፤ ጉዞ ወደ #መናገሻሱባ 🗓የጉዞ ቀን- እሁድ ጥቅምት 27/2015 (Nov 6/2022) 🕓 የቆይታ ጊዜ- ሙሉ ቀን (ደርሶ መልስ) 🛣 የቦታ ርቀት- 55 ኪሜ 🏝 ሱባ ፓርክ የመድረሻ ሰዓት -ጠዋት 2፡00** 🏙 አዲስ አበባ (መነሻ ቦታ) የመድረሻ ሰዓት- ምሽት 1:00** ፨ ሰዓቱ እንደመንገዱ የትራፊክ እንቅስቃሴ ሁኔታ ሊለዋወጥ ይችላል 🏞 የቦታው ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ 2,200 ሜትር ከፍታ ነው:: 🏞 የእግር ጉዞ የሚሸፍነው ርቀት- በሱባ ጥብቅ ደን እና አደሬ ተራራ የምናደርገው የእግር ጉዞ በጠቅላላው ወደ 16 ኪሎ ሜትር ሲሆን ወደ 4:00-4:30 ሰዓታት ገደማ ይወስዳል:: 🏞 የጉዞ አስቸጋሪነት- ለጀማሪ በመጠኑ ከበድ ያለ ሊሆን ይችላል:: ሆኖም ልምድ ላለው/ላላት ተጓዥ ቀላል የሚባል አይነት ነው:: 💵 ጥቅል ዋጋ በሰው - 999 ብር ብቻ ዋጋው ምን ምን ነገሮችን ያካትታል? • የደርሶ መልስ ትራንስፖርት ምቾት ባለው ቱሪስት ባስ (Round trip transport with a tourist bus)🚍 • የመግቢያ ክፍያ (Entrance fee)💵 • አስጎብኝ (Tour Guide)🙎🏿‍♂️ • ቀለል ያለ ቁርስ(Snack) 🍩💧 • ምሳ እና የታሸገ ውኃ (Lunch & - Botteld water) 🥘💧 መገናኛ ቦታ፡ ሜክሲኮ ዋቢ ሸበሌ የመገናኛ ሰዓት: ከንጋቱ 12:00 የመኪና መነሻ ሰዓት: ከንጋቱ 12:30 ለመመዝገብ እንዲሁም ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ቁጥሮች ይደውሉልን:: 📲 0928412796 / 0945965456 Join us - @IbexEvents
Mostrar todo...