cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ባለራዕዮች ቤተ-መጻሕፍት

-አስገራሚ ታሪኮችን -አስተማሪ መልዕክቶችን -አባባሎችን -ትረካዎችንና -በ PDF የተዘጋጁ መጽሐፍቶችእኛ ጋ ያገኛሉ Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100087196406622 Personal contact @samirebel Invite Link t.me/Bale_Raiyoch

Show more
Advertising posts
1 846Subscribers
+124 hours
-87 days
-730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በዚ ፎቶ ላይ የምትመለከቷት ተማሪ አስቴር ፋንቱ ስትባል በሀዋሳ ዮንቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት ተማሪ ስትሆን ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው ማክሰኞ መጋቢት 10 ነው። በማንኛውም አጋጣሚ አህታችን ልትገኝበት የምትችልበትን ቦታ መጠቆም የምትችሉ ሁሉ ከዚህ በታች ባለው ስልክ ቁጥር መደወል ትችላላቹ። Phone no +25164938850 +251921632467
Show all...
👍 3
ነገ አዲስ ቀን ነው! እውቀት ኖረህም አልኖረህም፣ ባለ ስልጣን ሆንክም አልሆንክም፣ ሃብት ኖረህም አልኖረህም፣ ዝነኛ ሆንክም አልሆንክም፣ ከተማ ውስጥ ሆንክም ገጠር ውስጥ፣ በእድሜ ገና ሆንክም የገፋህ፣ ስህተትህ ጠሊቅም ሆነ ቀላል . . . . በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሁን፣ ፈጣሪ ለሁላችንም የሰጠን አስገራሚ ስጦታ ለአንተም ተሰጥጦሃል፡፡ ይህ ስጦታ ዛሬ አንቀላፍተህ ነገ ስትነሳ ሁሉንም ነገር እንደ አዲስ የመጀመር ስጦታህና ብቃትህ ነው፡፡ ነገን በአዲስ መልኩ ለመጀመር የሚረዱህ ሃሳቦች፡- 1. አዲስ ጅማሬ ለመጀመር መወሰን 2. ይቅርታ መጠየቅ ያለብህን ሰው ይቅርታን መጠየቅ 3. ራስህን ይቅር ማለት 4. ነገ ስትነሳ ራስህን በአዲስ መልኩ በማየት አዲስ ልምምድን መጀመር ዶ/ር እዮብ ማሞ መልካም ቀን
Show all...
👍 10 2
"አለማወቅ መነሻ ነው። ማወቅ ባለማወቅ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ከማናውቀው ህይወት፣ ማንነት፣ ኑሮ፣ እውቀት ላይ በትንሽ በትንሹ እየቀነስን ነው የምናውቀው። ስለዚህ የማወቅ ፍላጎት እስካለህ ድረስ ብዙውን የራስህን ጥያቄ መመለስ ትችላለህ። ስለ አንተ ከአንተ በላይ፥ ማንም ሊያውቅ አይችልም" አለማወቅ ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ
Show all...
👍 12 1
 ይሉኝታ “ይሉኝታ” ማለት የምናደርገውን ወይም የማናደርገውን ነገር ለመወሰን “ሰው ምን ይለኛል?” በሚለው የመነሻ ሃሳብ መገደድ ማለት ነው፡፡ ይህ የመነሻ ሃሳብ ከሁሉም በፊት ሰዎች በእኛ ላይ ላላቸው አመለካከር ከልክ ባለፈ ሁኔታ ከመጨነቅ ጋር ይገናኛል፡፡ ይህንን ሁኔታ ሚዛናዊ ለማድረግ በመጀመሪያ በራሳችን ላይ ያለንን አመለካከት መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡ 1. የምታደርገው ነገር ትክክለኛ መሆኑን በሚገባ አስበህ ማድረግ 2. በምታደርገው ነገር ምክንያት ደስ የሚለውም ሆነ የማይለው ሰው የመኖሩን እውነታ መቀበል 3. ቢቻል የምታደርገው ነገር ይነካቸዋል ለምትላቸው ሰዎች ነገሩን ያደረክበትን ምክንያት ግልጽ ለማድረግ መሞከር 4. ተግባርህ ይመለከታቸዋል ብለህ ለምታስባቸው ሰዎች ምክንያትህን ከገለጽክ በኋላ የራሳቸውን ሃሳብ እንዲያስቡ ጉዳዩን ለእነሱ መተው 5. ጉዳዩ ስለማይመለከታቸው ሰዎች መጨነቅ ማቆምና የፈለጉትን እንዲያስቡ ነገሩን ለራሳቸው መተው 6. ሰዎች በአንተ ላይ የሚያስቡት መሰረተ ቢስ ሃሳብ የሚያንጸባርቀው የአንተን ሁኔታ ሳይሆን የእነሱን የአመለካከት ደረጃ እንደሆነ ራስህን ማሳመን 7. ሰዎች ምንም አሰቡብህ ምንም አንተ ግን ሙሉ ሰው ሆነህ የራስህ ኑሮ መኖር እንደምትችል ራስህን ማሳመን    ዶ/ር እዮብ ማሞ
Show all...
13👍 4
ራሳችንን ለመከላከል እንኳን ቢሆን፣ ኃይልን የመጠቀሙ አማራጭ፣ ከሚፈታው ችግር ይልቅ የሚያስከትለው መዘዝ ያመዝናል የሚለው እምነቴ ዛሬም የጸና ነው። ጥላቻ ወይም ሰው መግደልን እምቢ በማለት ብቻ ነው የዓለማችንን ሁከት ድል አድርገን የሰው ልጅ በሙሉ ያለ ስጋት የሚኖርበት ህብረተሰብ ልንገነባ የምንችለው። ግባችን ፍቅር የሞላበት ህብረተሰብ ለመገንባት ነው፤ ይህ ደግሞ የአስተሳሰብና የአኗኗር ለውጥን ይፈልጋል ፡፡ ዶ/ር ማሪትን ሉተር ክንግ 1966 እ.እ.አ
Show all...
👍 8
ከትናንት ዛሬ የተሻለ ነው፡፡ ቀኖቼን በምስጋና ጀምሬ ከቤተሰቦቼና በሕይወቴ ልዩ ቦታ ከምሰጣቸው ወዳጆቼና ጓደኞቼ ጋር አሳልፋለሁ፡፡ የስስት እይታቸውን የፍቅር አመለካከታቸውን፣ አንዳች እንዳይጎድልብኝ የሚያደርጉትን ነገርና ጉድለት እንዳይሰማኝ የሚሆኑልኝን ሁኔታ ስመለከት እንኳንም ኖርኩ እላለሁ፡፡ ተርፎት በገንዘብ የረዳኝ ማንም የለም፡፡ ሁሉም ሰው የሰጠኝ ዋናውን፣ ኑሮውንና ትዳሩን ነው፡፡ ገንዘብ የረዳኝ ቢሆንም ከገንዘቡ በላይ የጠገነኝ ግን የተሰጠኝ ፍቅርና እንክብካቤ ነው፡፡ አሁን ሁሉም ሰው ይወደኛል፤ ይንከባከበኛል። በዚህም ደስተኛ ሆኜ ውዬ አድራለሁ። አንዳንድ ጊዜ ጉዳቴንም ፈጽሞ የምረሳበት ቀን አለ፡፡ ሰዎች ተስፋ ቆርጠውና ተማርረው ወደ እኔ ሲመጡ እኔንም አይተውና ተመካክረን ተጽናንተው ሲሄዱ የመኖር ትርጉሙ ለሌሎች መትረፍ መሆኑን እገነዘባለሁ። በመትረፌም ደስተኛ እሆናለሁ፡፡ ቤተሰቦቼም በተለያዩ ቤተሰባዊ ጉዳዮች ላይ ከእኔ ምክር ሲጠይቁኝና ሃሳቤን ሲቀበሉኝ ከምን ውስጥ ወጥቼ እዚህ እንደደረስኩ እያሰብኩ አምላኬን አመሰግናለሁ፡፡ ሁሌም አሁን ያለሁበት ሁኔታ የሚቀየርበት ቀን እስከሚመጣ ድረስ ባለሁበት ሁኔታ ውስጥ ለራሴና ለሌሎች ማድረግ ስለምችለው ነገር አስባለሁ፡፡ በማልቀስና በማጉረምረም በመበሳጨትና በማማረር የማሳልፈው አንድም ቀን እንዲኖር አልፈልግም፡፡ የሆነውንና ያለሁበትን ሁኔታ ተቀብያለሁ፡፡ አሁን ጥረቴ ቀን እስኪያልፍ በትዕግስት መጠበቅና ትንሿን የራሴን ቀላል ዓለም ፈጥሬ በደስታ መኖር ነው። በሕይወቴ ላይ አንድ ቀን በተጨመረ ቁጥር አንድ ተጨማሪ ዕድል እየተሰጠኝ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ እንዲሁ የሚጨምር ቀን የለም፡፡ እኔ ግን ዕድላኛ ነኝ፡፡ ከተጨማሪ ቀናት አልፎ ተጨማሪ ዓመታት ተሰጥተውኛል። ትኩረቴ ሁሉ ባሉኝ ነገሮች ላይ እንጂ ባጣኋቸው ነገሮች ላይ አይደለም፡፡ አንዱ የደስተኛ ሕይወት ሚስጥር ይሄ ነው።         _ _ _ _ዳግማዊ አሰፋ ባለራዕይዮች  ቤተ-መጻሕፍት t.me/Bale_Raiyoch
Show all...
8👍 1👏 1
ራስህን መጉዳት አቁም! ፀሀይ ስትጨልም ስራ አቁማ አይደለም፤ ሌላኛውን የመሬት ክፍል ልታበራ ዞር ብላ ነው። እናቱ ገበያ የሄደችበት ልጅ እናቱ ከሞተችበት ልጅ እኩል ያለቅሳል፤ ግን እኮ መመለሷ አይቀርም። ህይወትን በቀጥታ እየተረጎምክ ራስህን መጉዳት አቁም! የተወሳሰቡና ግራ ያጋቡህን ነገሮች ተረጋግተህ በተለየ መንገድ ለማሰብ ብትሞክር ብዙ እንቆቅልሽ ትፈታለህ። ኑሮ፣ ስራ፣ የፍቅር ግንኙነት የፈተና ድንጋይ ሲወረውሩብህ አንተ ሰብስበና ተዓምረኛ ቤት ስራበት!
Show all...
👍 12 7
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!