cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethio flame tutorial class

ይህ ቻናል ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የተከፈተ ድንቅ ቻናል ነው። ❤️ትክክለኛ ትምህርታዊ መረጃዎችን ለተማሪዎች ያደርሳል entrance tricks ለመመዝገብ @entrance_tricks_bot ላይ ይጠቀሙ ወይም በስልክ 0920308061 you tube channel =https://youtube.com/@ethioflametutorial

Show more
Advertising posts
20 013Subscribers
+6624 hours
+2517 days
+63730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የጂኒየስነት ሚስጢር ክፍል አራት...........! 💡 ዛሬ የምነግራችሁ Maths እና Physics እንዴት መነበብ እንዳለባቸው ነው፡፡ ተከተሉኝ ፦ 📚 በመጀመሪያ Maths ፣Physicsን ለማጥናት ራሳችንን በስነልቦና ማዘጋጀት አለብን ፣ማለትም ከባድ አለመሆናቸውን ራሳችንን ማሳመን አለብን ፡፤በመቀጠልም ትምህርቶቹን ስናጠና እነዚህን ማረግ አለብን ፦ ለPhysics  ❓ 📚 concept መያዝ ያስፈልጋል ፡፡ እንዲሁም formula በመሸምደድ ፋንታ proof ማድረግ በጣም ጠቃሚ ናቸው ፡፡ እንዲሁም ዋና ዋና የሚታወቁ የ physics ህጎችን ለምሳሌ ፦ ፡-Newtons law of motion. ፦ Pascal principle ፦ Archemedian principle ወዘተ...ህጎችን መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ለMaths  ❓ 📚 ስናጠና ደግሞ የtopicኡን ህግ እንዲሁም ጥያቄዎቹ የሚሠሩበትን መንገድ step by step በደንብ ለመረዳት መሞከር እንዲሁም ያልገባን ጥያቄ ካለ የተለያዩ አጋዥ መፅሀፍችን( ከላይብረሪ ብትጠቀሙ ብዬ እመክራለሁ )  እና ት/ቱን የሚያስተምረውን አስተማሪ መጠየቅ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ብዙዎች የሚሳሳቱት ነገር ❓ 📚 ደግሞ Maths ፣Physics ማጥናት ያለብን ፈተና ሲደርስ ብቻ አይደለም፡፡ሁልጊዜ ቢያንስ በዚያን ቀን የተማርነውን topic መከለስ አለብን እንዲሁም ቢያንስ በዚያን ቀን ከተማርነው topic 5 ጥያቄ ብንሠራ በጣም ይጠቅመናል ፤  ምክንያቱም እነዚህ ት/ቶች እንደሌሎች የሽምደዳ ት/ቶች ለፈተና concept እንዲሁም formula ሸምድደን በመግባት ብቻ የምንሰራቸው ከመሰለን በጣም ተሳስተናል፣ ይልቁንስ  topicኡን በመረዳት እና የተለያዩ  ጥያቄዎችን  በመለማመድ የምንሠራቸው የት/ት አይነቶች ናቸው፡፡ አሁን ተግባባን አይደል ❓ 💬 ከእነዚህ ት/ቶች ደስ የሚለው ነገር ደግሞ  topicኡን አንዴ በደንብ  ከተረዳነው ከጭንቅላታችን አይጠፉም ስለዚህም ፈተና ሲደርስ በመጨናነቅ ፈንታ ራሳችንን በተለያዩ ጥያቄዎች challenge የማድረግ እድሉን እናገኛለን ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ካለኝ ልምድ በመነሳት ይህንን ፃፍኩላችሁ ፡፡ በሉ ተነሱና ፍለጡት ❓ 🔜 ክፍል 5 ይቀጥላል.........
Show all...
Ethio flame tutorial class

ይህ ቻናል ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የተከፈተ ድንቅ ቻናል ነው። ❤️ትክክለኛ ትምህርታዊ መረጃዎችን ለተማሪዎች ያደርሳል entrance tricks ለመመዝገብ @entrance_tricks_bot ላይ ይጠቀሙ ወይም በስልክ 0920308061 you tube channel =

https://youtube.com/@ethioflametutorial

👍 6👏 1
የ2014 ዓም ሁሉንም የnatural science እና የsocial science entrance ጥያቄዎች መልስ ከሰፊ ማብራሪያ ጋር ትፈልጋላችሁ አንግዲያውስ፤ 👑2014 natural English Ethiopian entrance exam answer and explanation =https://youtu.be/OPiKGRFYHW8 👑2014 natural Mathematics Ethiopian entrance exam answer and explanation =https://youtu.be/qxiqnaTovUM 👑2014 physics Ethiopian entrance exam answer and explanation =https://youtu.be/kPSwODp54Ro 👑2014 Chemistry Ethiopian entrance exam answer and explanation =https://youtu.be/KB-xV1w9Vuw 👑2014 Biology Ethiopian entrance exam answer and explanation =https://youtu.be/bQciZLWgAbw 👑2014 natural aptitude/ sat Ethiopian entrance exam answer and explanation =https://youtu.be/eOgPmOExVXo 👑2014 natural civics Ethiopian entrance exam answer and explanation =https://youtu.be/1ztAL_H4wtQ 👑2014 social English Ethiopian entrance exam answer and explanation =https://youtu.be/5bRV0JubJwY 👑2014 social aptitude/ sat Ethiopian entrance exam answer and explanation =https://youtu.be/VpvRN-GU8p4 👑2014 social civics Ethiopian entrance exam answer and explanation =https://youtu.be/VpvRN-GU8p4 @ethioFlame @ethioFlame @ethioFlame
Show all...
2014/15 English natural students entrance examination with answer and explanation/atc tube/atc maths

#english_answer #entrance2015 #entrance2014

👍 1
የስኬት ቁልፎች (The key to success)- ክፍል አንድ ስኬት አንድ የታቀደ እቅድ(ግብ)በትክክል መፈፀም ማለት ነው፡፡ ከዚህ ዐረፍተ ነገረ መረዳት የምችለው ነገር ቢኖር ከስኬት በፊት ምንጊዜም የታቀደ ግብ ሊኖር እንደሚገባ  ነው፡፡ ስኬት ግብ ለሚያቀምጡ ብቻ የተሠጠች ነች ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው “ If you fail to plan, you are planning to fail’ የሚሉት ምሁራን፡፡ ከስኬት ቁልፎች መካከል አንዱ ግብ ማስቀመጥ(Goal setting) ሲሆን ሌሎች ደግሞ የዉስጥ መነሳሳት(Motivation) እና ጽናት (persistence) ናቸዉ:: 1.  ግብ ማስቀመጥ ( Goal setting) ማንኛውም ስኬታማ መሆን የሚፈልግ ሰው እቅድ ማቀድ እንዳለበት ከተስማማን እቅዱስ ምን ምን ማሟላት አለባቸው? የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ ጠቃሚ ነዉ፡፡  ማንኛውም ዓይነት እቅድ “SMART ” መሆን አለበት:: ትርጓሜውም እንደሚከተለው ይተነተናል፡፡ S- Specific ( ግልጽና የተወሠነ) M-Measurable (የሚለካ) A- Achievable (ሊሳካ የሚችል) R- Realistic (እውን ሊሆነ የሚችል) T- Time framed ( በጊዜ የተወሰነ) i)specific ( ግልጽና የተወሠነ) እቅድ (ግብ) በግልፅ የሚታወቅ መሆን ይገባዋል፡፡ ግልጽነት የሚጎድለዉ እቅድ እንዴት እንደምናሳካዉ ለማወቅ ከባድ ነዉ::ብዙ ሰዎች ግባቸውን ሲጠየቁ “የተሻለ” የምትለዋን ቃል በማስቀደም ሌሎችን ፍላጎታቸውን ያስከትላሉ፡፡ የተሻለ ትምህርት፣ የተሻለ ቤት፣ የተሻለ ገቢ ፣የተሻለ የስልጣን ቦታ ወዘተ ይላሉ፡፡ ይህ አይነቱ ግብ ግልጽነትና ዉሱንነት ይጎድለዋል፡፡ ለስኬታማነትም ሊያበቃን አይችልም፡፡ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜያቸው የሚያጠፉት ከአንዱ አንዱ በመንከራተትና በመወዛገብ ነው፡ የተረጋጋ ህይወት ለእነርሱ ተረት ነው፡፡ የተሻለ ገቢ ለማግኜት የሚያቅድ ሰውና የ3000 ብር ደመወዘኛ የ3200 ብር ደመወዝ ያለው የስራ ማስታወቂያ ከወጣ ያለ ጥርጥር ስራውን ይቀይራል፡፡ ምክንያቱም እቅዱ የተሻለ ማግኜት ነውና፡፡ ለዚህም ነው እንዳንድ ሰዎች ከእድሜያቸው በላይ መስሪያ ቤት ሲቀያይሩ የሚኖሩት፡፡ በተመሳሳይ የተሻለ ትምህርት የሚፈልግና ዲግሪ ያለዉ ሰው በአጋጣሚ መንገድ ጠፍቶበት በዩኒቨርሲቲ በር ሲያለፍ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ማስታወቂያ ቢያነብ ትምህርቱ ይጥቀመውም አይጥቀመውም ዘሎ ገብቶ ይመዘገባል፡፡ ተምሮ ሲወጣ ግን በህይወቱ ምንም ዋጋ ላይጨምር ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ግብ በግልጽ ተወስኖ የተቀመጠ መሆን ይገባዋል፡፡ የተሻለ ገቢ በማለት ፈንታ በወር ማግኜት የሚፈልገውን የገንዘብ መጠን ቢያቀምጥ ይመረጣል፡፡ የተሻለ ትምህርት በማለት ፈንታም ዲግሪ፣ ማስተርስወይም ፒ.ኤች. ዲ እና የመሣሰሉትን ቢያቀምጥ ይመረጣል፡፡ ii). Measurable (የሚለካ) ሌላው ግብ ስናስቅምጥ ማስተዋል የሚገባን ነገር ግባችን የሚለካ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰዎችን የሚረዳ ድርጂት ለማቋቋም ያቀደ ሰው ምን ያህል ሰዎችን እንደሚረዳ በግልፅ ማስቀመጥ አለበት፡፡ ቤት ለመሰራት ያቀደም ሰው ቢሆን የቤቱን ስፋት አይነት እና የመሳሰሉትን በግልፅ  ማስቀመጥ አለበት፡፡ አለበለዚያ አንድ ሰው ብቻ የምታሰገባ ቤት ቢሰራም ቤት ቤት ነውና እቅዱን እዳሳሣካ ሊቆጥረው ይችላል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ግብ የሚያስቀምጥ ሰው ግቡ የሚለካ መሆን አለበት፡፡ iii). Achievable (ሊሳካ የሚችል) አሁንም ግብ ስናስቀምጥ ግባችን ሊሳካ የሚል መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ይህን በምሳሌ ለማስረዳትም አንድ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ዛሬ ላይ ሆኖ የዛሬ 10 ዓመት ፒ.ኤች.ዲ ዲግሪዉን እንደሚይዝ ቢያቅድ እቅዱ ሊሳካ የሚችል አይደለም፡፡ ምክንያቱም ስርዓተ-ትምህርቱ ከ7ኛ ክፍል ወደ ፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ በ10 ዓመት ያጠናቅቅ ዘንድ አይፈቅድለትም፡፡ በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ከ7ኛ ክፍል ፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ  ለመያዝ ቢያንስ 14 ዓመታትን ይፈጃል፡፡ ስለሆነም ይህን እቅድ ያቀደ ሠው እቅዱን ሊያሳካ አይችልም፡፡ ስለዚህም ሁጊዜ ግብ ስናስቀምጥ ሊሳካ የሚችል መሆኑንና አለመሆኑን ማሠብ ይኖርብናል፡፡ iv). Realistic  (እውን ሊሆን የሚችል) አራተኛው ግብ ሊያካትተው የሚባው መስፈርት ደግሞ እውን ሊሆን የሚችል መሆኑን ነው፡፡ ይህ ቀጥታ ከተፈጥሮ ጋር የሚያያዝና ልንቀይራቸው የማንችላቸውን ነገሮች ማቀድ እንደሌለብን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ “change the changeable, accept the unchangeable” እንዲሉ ምሁራን በተፈጥሮ እውን ሊሆን የማይችልን ነገር ማቀድ ድካሙ ነው ትርፉ፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው “የዛሬ ዓመት መልዓክ ለመሆን ቢያቅድ እቅዱ እቅድ መሆኑ ቀርቶ ቅዠት ነው የሚሆነው፡፡ ስለሆነም ግባችን በገሃዱ አለም እውን ሊሆን የሚች መሆን አለበት፡ v). Time framed ( በጊዜ የተወሰነ) የመጨረሻውና ግብ ስናስቀምጥ ማካተት ያለብን ነገር ግባችን በጊዜ-የተወሰነ መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ ይህ ችግር ከሌሎች ማሟላት ከሚገቡን ነገሮች የበለጠ ጎልቶ የሚታይ ነው፡፡ “መኪና ሳልገዛማ አልሞትም” ሲል የምንሠማው ሰው መኪና መቼ እንደሚገዛ ግን አያውቀውም፡፡ የዛሬ 20 አመትም ይህንን ሲደግመው እናሠማለን፡፡ ግብ ስናስቀምጥ ምን ጊዜም በጊዜ የተወሰነ መሆን ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ ነገ እሠረዋለሁ እያልን እድሜያችንን መፍጀታችን ነዉ፡፡ ክፍል 2 ይቀጥላል....       📜Via unknown source Share Share👆👆👆🙏 https://t.me/ethioflame https://t.me/ethioflame
Show all...
Ethio flame tutorial class

ይህ ቻናል ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የተከፈተ ድንቅ ቻናል ነው። ❤️ትክክለኛ ትምህርታዊ መረጃዎችን ለተማሪዎች ያደርሳል entrance tricks ለመመዝገብ @entrance_tricks_bot ላይ ይጠቀሙ ወይም በስልክ 0920308061 you tube channel =

https://youtube.com/@ethioflametutorial

👍 5
Repost from Remedial Tricks
እስካሁን ጥሪ ያልተደረገላቸው የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል። ተማሪዎቹ ከታህሳስ ወር ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የአቅም ማሻሻያ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም። ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የጀማሪ መርሐግብር እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ለተከታተሉ ተማሪዎች መጋቢት 14/2016 ዓ.ም ጥሪ ሲያደርግ፤ በ2016 ዓ.ም ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ ሳያደርግ ቀርቷል። እነዚህ ተማሪዎች በቀጣይ ጥሪ ይደረግልናል በሚል በተስፋ ሲጠብቁ ቆይተዋል። ይሁን እንጂ ከአንድ ወር በኋላም ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አላደረገላቸውም። "የትምህርት ጊዚያቸው እየባከነባቸው እንደሆነ"ና "አስቸጋሪ ጊዜያትን እያሳለፉ እንደሚገኙ" ለቲክቫህ አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች፤ መንግሥት መፍትሔ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጠይቀዋል። የሪሚዲያል ፈተናው ይሰጣል ተብሎ በመንግሥት የተቀመጠው ጊዜ 45 ቀናት የቀሩት መሆኑ ሌላው ተማሪዎቹን እያሳሰበ ያለ ጉዳይ ነው። ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎቹ መቼ ጥሪ እንደሚደረግ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችን በስልክ እና በአጭር መልዕክቶች የጠየቀ ቢሆንም ምንም አይነት ምላሽ ማግኘት አልቻለም። ተማሪዎቹ ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተዘዋውረው የሚማሩበት ዕድል ካለ፣ አማራጭ የፈተና ጊዜ የሚዘጋጅላቸው ከሆነ እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ወይም/እና ትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጡትን ምላሽ ወደናንተ እናደርሳለን። https://t.me/remedial_tricks https://t.me/remedial_tricks
Show all...
Remedial Tricks

ለ2016 አም እጩ ፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ቻናል You tube channel

https://youtube.com/@ethioflametutorial.

for registration call us on 0920308061

👍 4
✅8 parts of speech: 🎚1. Noun: A noun is a word that represents a person, place, thing, or idea. ⭐️ Examples include "dog," "house," "car," and "love." 🎚2. Verb: A verb is a word that describes an action, occurrence, or state of being. ✅ Examples include "run," "eat," "sleep," and "be." 🎚3. Adjective: An adjective is a word that describes or modifies a noun or pronoun by providing more information about its qualities or characteristics. ✅Examples include "big," "happy," "green," and "beautiful." 🎚4. Adverb: An adverb is a word that modifies a verb, adjective, or another adverb by providing more information about how, when, where, or to what extent something happens. ✅Examples include "quickly," "happily," "very," and "there." 🎚5. Pronoun: A pronoun is a word that takes the place of a noun in a sentence. Pronouns are used to avoid repetition and to make sentences flow more smoothly. ✅ Examples include "he," "she," "it," "they," and "we." 🎚6. Preposition: A preposition is a word that shows the relationship between a noun (or pronoun) and other words in a sentence. Prepositions usually indicate location, direction, time, or manner. ✅Examples include "in," "on," "at," "under," and "between." 🎚7. Conjunction: A conjunction is a word that connects words, phrases, or clauses in a sentence. Conjunctions are used to show relationships between ideas and to join different parts of a sentence together. ✅Examples include "and," "but," "or," "because," and "although." 🎚8. Interjection: An interjection is a word or phrase that expresses strong emotion or sudden feeling. Interjections are often used to convey surprise, excitement, joy, or other emotions. ✅ Examples include "wow," "ouch," "oh," and "bravo." https://t.me/ethioflame
Show all...
Ethio flame tutorial class

ይህ ቻናል ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የተከፈተ ድንቅ ቻናል ነው። ❤️ትክክለኛ ትምህርታዊ መረጃዎችን ለተማሪዎች ያደርሳል entrance tricks ለመመዝገብ @entrance_tricks_bot ላይ ይጠቀሙ ወይም በስልክ 0920308061 you tube channel =

https://youtube.com/@ethioflametutorial

👍 4
የዘንድሮ ብሄራዊ ፈተናወች ቅደም ተከተል Remedial Exam —> Exist Exam—>Entrance Exam በዚህም የ12ኛ ክፍል ፈተና ሀምሌ ወር መጀመሪያ በ ሁለት ዙር የሚሰጥ ይሆናል !!! ሶስቱንም ሃገር አቀፍ ፈተና የምትፈተኑ ተማሪወች መልካም እድል !!!
Show all...
Ethio flame tutorial class

ይህ ቻናል ለኢትዮጵያ ተማሪዎች የተከፈተ ድንቅ ቻናል ነው። ❤️ትክክለኛ ትምህርታዊ መረጃዎችን ለተማሪዎች ያደርሳል entrance tricks ለመመዝገብ @entrance_tricks_bot ላይ ይጠቀሙ ወይም በስልክ 0920308061 you tube channel =

https://youtube.com/@ethioflametutorial

👍 13 1
Repost from Remedial Tricks
የሪሚዲያል ፈተና የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ፈተና ከሰኔ 3 -14 በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል! #Remedial https://t.me/remedial_tricks
Show all...
Remedial Tricks

ለ2016 አም እጩ ፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ቻናል You tube channel

https://youtube.com/@ethioflametutorial.

for registration call us on 0920308061

👍 3
Repost from Remedial Tricks
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ በየነ ተዘራ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡ ከ70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በኦንላይን፣ በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡ ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ የሪሚዲያል ትምህርት ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም መጨረሻ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ #ኢፕድ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ https://t.me/remedial_tricks https://t.me/remedial_tricks
Show all...
Remedial Tricks

ለ2016 አም እጩ ፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ቻናል You tube channel

https://youtube.com/@ethioflametutorial.

for registration call us on 0920308061

👍 4 1🔥 1