cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

DREAMS-Ethiopia

ራስህን ፣ያለህን መቀበል#+መደሰት#+ማመስገን#+በፈጣሪህና በራስ ማመን#+ተግባር/ጥረት#+በአላማህ መፅናት#=ስኬት ለሀሳብና አስተያየት contact👉 @gos11m12

Show more
Ethiopia6 314Amharic6 085The category is not specified
Advertising posts
840Subscribers
No data24 hours
-137 days
-3430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንድ ቀን ህልምህን ታሳካለህ🔥 🔥 ጉዞው ምንም ያህል ከባድ ቢመስልም በህልምህ ተስፋ አትቁረጥ። አንድ ቀን እውን ታደርገዋለህ። ህልምህን እንዳትከተል ማንም ወይም ምንም ነገር እንዲያቆምህ ወይም እንዲያደናቅፍህ አትፍቀድ። በራስህ እና በእይታህ ማመንህን ቀጥል። ያሰብከውን ማንኛውንም ነገር ለማሳካት አቅም እና ፍላጎት አለህ። በራስህ እና በህልምህ እያመንክ ከሆነ እና እየተንቀሳቀሰስክ ከሆነ ህልምህ እውን ህይወትህም ቀና ይሆናል። ድንቅ ህይወት! ድንቅ ምሽት ተመኘሁ! DREAMS-ETHIOPIA ለአዎንታዊ እሳቤና ህይወት! ይቀላቀሉን 🔔👇👇👇        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia                             
Show all...
"ትላንት በህይወትህ ያለፈውን መጥፎ ቀን ማጥፋትም መቀየርም መሰረዝም አትችልም፤ የምትችለው መቀበል ብቻ ነው"፡፡ ትላንትን አምነህ ተቀብለህ ዛሬን በደስታ ኑር፡፡ አስተውል ዛሬ አዲስ ቀን ነው ከቀኑ ጋር አዲስ መሆን ያንተ ፋንታ ነው፡፡ የተወለወለ ቤት በጭቃ እግርህ ብትገባ ቤቱን ታበላሸዋለህ፤ ልክ እንደዛው በትላንት መጥፎ ሀሳብ ዛሬንም ከተቀበልከው እንደዛው ነው!!! ስለዚህ ዛሬን ከቀኑ ጋር አብረን አዲስ እንሁን፡፡ መልካም ቀን በፍቅር ያውለን🙏 DREAMS-ETHIOPIA ለአዎንታዊ እሳቤና ህይወት! ይቀላቀሉን 🔔👇👇👇        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia                             
Show all...
አውሮፕላኑ ደመናን እየሰነጠቀ በመብረር ላይ ነው፡፡ በድንገት ሚዛኑን በመሳት በአስፈሪ ሁኔታ መንገጫገጭ ጀመረ፡፡ ሁሉም ተሳፋሪ ከፍርሀት በመነጨ መልኩ መጮኽ ጀመረ፡፡ ነገር ግን አንድ የ8 አመት ህፃን ምንም ሳይሰማት በአሸንጉሊቷ ትጫወታለች፡፡ ከሰዓት በኀላ አውሮፕላኑ በሰላም አረፈ፡፡ አንድ ሰው ትንሿን ህፃን እንዲ ብሎ ጠየቃት፡፡ "ሁሉም ሰው እንደዛ በድንጋጤ እየጮኽ እንዴት አንቺ በአሸኔጉሊት ትጫወቻለሽ?" ትንሿ ልጅ በፈገግታ እንዲ ስትል መለሰች፡፡ "አብራሪው አባቴ ነው፤ በሰላም እንደሚያሳርፈኝ ስለማውቅ ነው፡፡" ፍቅር እምነት ነው፤ እምነት ደሞ ህይወት፡፡ የተባረከ ምሽት ተመኘሁ። DREAMS-ETHIOPIA ለአዎንታዊ እሳቤና ህይወት! ይቀላቀሉን 🔔👇👇👇        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia                              
Show all...
#ስላልሆነው_አመስግን ጸሎት የምንፈልገውን በረከት ወደ ህይወታችን ማምጫ መንገድ ነው። ጸሎታችን ተሰምቶልን፣ የልባችን ደርሶ በአይናችን ስናይ ልባችን በደስታ፣ አፋችንም በምስጋና ይሞላል። ጸሎት በረከትን ከማምጣት በተጨማሪ ክፉ ነገር እንዳይደርስብን ይጠብቀናል። ያልደረሱብን፣ ልናያቸው እና ልናውቃቸው የማንችለው ብዙ በጸሎት ያመለጥናቸው ወጥመዶች፣ ያለፍናቸው ሞቶች አሉ። እናም ከበረከታችን እኩል ስላልደረሰብን ክፉ ማመስገን አለብን። ስለሆነው ብቻ ሳይሆን ስላልሆነውም ማመስገን አለብን። ©teklu tilahun    ውብ  ቀን❤️ join us👉@dreamsethiopia                 @dreamsethiopia                 @dreamsethiopia  
Show all...
ወዳጄ! አንተነትህን በሌሎች ሰዎች ሚዛን አትመዝነው!። ራስህን በሌሎች ሚዛን የምትለካ ከሆነ የተሻልክ ሲመስልህ ኩራትና ስንፍናን ትጋብዛለህ፤ያነስክ በመሰለህ ጊዜ ደግሞ የበታችነትንና ተስፋ መቁረጥን የምልከታ ገንዘብህ ታደርጋለህ። አየህ የምታገኘው ውጤት ምንም ሆነ ምንም በአንተነህ ላይ መውረዱን እንጂ ከፍታን አያተርፍልህም። አስተውል የአንተነህ ዋጋ የሚለካው በአንተ ሚዛን እንጂ በሌሎች አይደለም። የአንተ ችሎታ(ተሰጥዖ) ያለው አንተ ጋር ብቻ ነው። ራስህን መመዘን ካስፈለገህ በራስህ ሚዛን ብቻ ለካው፤ አስቀድመህ ግን ራስህን አወቀው። 🦅ንስርን ብቃቱ  የሚለካው በመብረር ችሎታው እንጂ  ከ አቦሸማኔ ጋር አወዳድረን ባለው የሩጫ ችሎታው አይደለምና።የእንሰሳት ችሎታ በዚህ ልክ ከተለየ የአንተማ እንዴት አይለይ ወዳጄ!:: መልካሙን ሁሉ ተመኘሁ🙏 DREAMS-ETHIOPIA ለአዎንታዊ እሳቤና ህይወት! ይቀላቀሉን 🔔👇👇👇        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia                              
Show all...
ብልህ ሰው በትናንሽ ነገሮች አይወሰንም ➪ብልህ ሰው የትም ቢሆን መፍትሔ አያጣም!"𑁍𑁍 በአንድ ከተማ የሚኖር አንድ በእድሜ የገፋ ሰው ነበር፡፡ በጓሮው በሚገኘውን ማሳ ቆፍሮ ድንች መትከል ፈልጎ እርጅና ተጫጭኖታልና አቅሙ አልፈቀደለትም፡፡ ሊረዳው የሚችለው ብቸኛ ልጁ ደሞ እስር ቤት ነው የሚገኘው፡፡ እናም አባት ለልጅ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፈ፡፡ "ውዱ ልጄ ምንም ጥሩ ስሜት አሸየተሰማኝ አይደለም፤ ምክንያቱም የድንቹን ማሳ መቆፈር አልቻልኩም፡፡ አለመቆፈሬን አልወደድኩትም፤ ምክንያቱም እናተህ አትክልት በጣም ነበር የምትወደው፡፡ አንተ እስር ቤት ባትሆን አውቃለሁ ትቆፍርልኝ ነበር ፤ አባትህ" በቀጣዩ ቀን አባት አጠር ያለ ፁሁፍ ደረሳቸው፡፡ "በፈጣሪ ስም ይዤካለው አባ ጓሮውን እንዳትቆፍረው፤ ሽጉጡን የቀበርኩት እዚያ ነው" ከሰዓታት በኀላ በደርዘን የሚቆጠሩ የFBI መርማሪዎችና ፖሊሶች የሽማግሊውን ጓሮ በሙሉ በቁፋሮ ምስቅልቅሉን አወጡት፤ ነገር ግን ምንም ሽጉጥ እዛ አልነበረም፡፡ አባት በጣም ግራ በመጋባት አጠር አድርገው ለልጃቸው ምን እንደተፈጠረ እና ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ፃፉለት፡፡ ልጅ "አሁን ድንችህን ትከል አባ፤ ከዚህ ሁኜ ላደርግልህ የምችለው ነገር ቢኖር ይህን ብቻ ነው" ብሎ ፃፈላቸው፡፡ ሁሉም ችግር የራሱ መፍትሄ አለው። ሁልጊዜም ከዚህ ታሪክ ይህን ውሰድ ስለገጠመህ ችግር (ጨለማው) ሳይሆን ስለ መፍትሄው (ብርሃኑ) አስብ ያኔ  ብርሃኑን ከጨለማው መፍትሄውን ከችግሩ እንደምታገኘው። ያለንበህት ነባራዊ ሁኔታ አንተን ሊወስኑህ አይገባም!   መልካም ሁሉ ተመኘሁ። DREAMS-ETHIOPIA ለአዎንታዊ እሳቤና ህይወት! ይቀላቀሉን 🔔👇👇👇        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia                              
Show all...
እንኳን አደረሳችሁ! DREAMS ETHIOPI ለእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም የኢድ-አል አድሃ (አረፋ) በዓል ይመኛል። በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የፍቅር እና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን። Eid Mubarak
Show all...
"በእያንዳንዱ ጠዋት ሁለት ምርጫ አለህ፤ ከህልምህ ጋር እንቅልፍህን መቀጠል ወይም ተነስተህ ህልምህን ማሳደድ። ምርጫው የአንተ ነው።" መልካም ቀንይሁንላችሁ። DREAMS-ETHIOPIA ለአዎንታዊ እሳቤና ህይወት! ይቀላቀሉን 🔔👇👇👇        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia                              
Show all...
🙍‍♂ተራ ሰው ነበሩ! ወዳጄ! ሁሉም በዓለም ላይ ያሉ ስኬታማ ሰዎች መጀመሪያ እንዳንተና እንደ እኔ መደበኛ፤ ማንም የማያውቃቸው ተራ ሰው ነበሩ። ራሳቸው ላይ በመስራት በጊዜያት ሂደት ግን፦ እውቀታቸውን እያዳበሩ፣  አስተሳሰባቸውን እያሰፉ፣ እምነታቸውን እያጠነከሩ፣ ፍልስፍናቸውን እያጎለበቱ፣ አመለካከታቸውን እያቀኑ፣ ራእያቸውን እያገዘፉ፣ ከዛሬ አልፈው ለነገ እየኖሩ፣ ውሳኔያቸውን እያጠነከሩ አሁን ያላቸውን ትልቅ የስኬታማ ሰው ማንነት ፈጠሩ። እንዴት ይመስልሀል እንዲህ ያደረጉት! ራሳቸውን በጥልቀት አወቁ ተረዱ፤ ግብና ራዕያቸውን ለዩ፤ ለራሳቸው የሚገባቸውን ትልቅ ክብርና ቦታ ሰጡ፤ ልምዶቻቸውን ቀና አደረጉ፤ በራሳቸው አመኑ፤ ፍርሀትን ጥለው ተገቢ ድፍረትን ተላበሱ....በመጨረሻም ብዙዎች የሚመኙትን ጥቂቶች የሚደርሱበትን ስኬት አገኙት። አየህ ይህ መርህ ለአንተም ይሰራል ተግብረውና ስኬትን ህይወትህ አድርገው!። አንቺም ውዷ አህቴ። ሸጋ ምሽት ተመኘሁ! DREAMS-ETHIOPIA ለአዎንታዊ እሳቤና ህይወት! ይቀላቀሉን 🔔👇👇👇        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia                              
Show all...
❤ሰው የሀሳቡን ፍሬ ይበላል! Henry ford አንዲህ ስል ድንቅ እውነት ይናገራል። "እችላለሁ ካልክ አዎ ልክ ነህ ትችላለህ፤ አልችልም ካልክም አዎ ልክ ነህ አትችልም" አየህ henry አንዳለው በአሸናፊነት እሳቤ ከተቃኘህ የአሸናፊነትን፤ በተሸናፊነት እሳቤ ስትቃኝ ደግሞ የተሸናፊነት ህይወትን ትኖራለህ። መጽሐፍስ "ሰው በልቡ እንደሚያስበው እንደዚያው ነው" ይል የለ። ወዳጄ ምንአልባት አሁን ህልምህን ለማሳካት የሚረዳህ ሰው አጥተህ፣ የኢኮኖሚ ችግር ይዞህ ወይም እውቀት ጎድሎህ ተስፋ ቆርጠህ ወይም ተስፋ ወደ መቁረጥ እየተቃረብ  ሊሆን ይችላል፤ እስኪ ቆም ብለህ ራስህን ጠይቅ ለራስህ እያልከውና እያሰብክ ያለኸው የቱን ነው? አስቀድመህ ሀሳብህን ወደ ዕምነት ስታሳድገው ነው እምነትህ ምግባር ሆኖ ውጤትን የሚሰጥህ። አስተውል! አሁን ከፊትህ እየገጠመውህ ያሉት ችግሮች ልክ እንደ አቧራ ናቸው፤ አንተ በቃ ብለህ ሳትቆም፤ ከተትንቀሳቀስክ ይራገፋሉ። በሚራገፍ ችግር ከትልቁ ስኬትህ መቅረትን ለራስ አትፍቀድ! ሰው የእንደበቱን ፍሬ ይባላል እንዲሉ አበው ሁልጊዜም ትልቅ አስብ መልካሙን እመን። ሸጋ ምሽት ተመኘሁ🙏 DREAMS-ETHIOPIA ለአዎንታዊ እሳቤና ህይወት! ይቀላቀሉን 🔔👇👇👇        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia        @dreamsethiopia                              
Show all...
Sign in and get access to detailed information

We will reveal these treasures to you after authorization. We promise, it's fast!