cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

Show more
EthiopiaAmharicThe category is not specified
Advertising posts
860Subscribers
No data24 hours
-37 days
-2130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የገጠር ልጅ Vs የከተማ ልጅ‼ ===================== (የብሔር ክፍፍሉ ሳያንሰን አንድ ወንድማችን የገጠርና የከተማ ልጅ ብሎ ከፋፍሎ ይህን ጽፏል። በነገራችን ላይ ጸሐፊው የዚሁ የአዲስ አበባ ልጅ ይመስለኛል። ጠቅላይ ድምዳሜ መስጠት ባይቻልም ይህ ነባራዊ ሐቅ ስለሚመስል የተወሰኑ ቆቅ የከተማና ጀንፈል የገጠር ልጆች መኖራቸው ሳይረሳ፤ ከገጠሩም ከከተማውም ልጅ ጠንካራ ጎናቸውን ወስደን አሪፍ የእኛ hybrid መፍጠር ሳይሻል አይቀርም። ጽሑፉ እንደወረደ እንዲህ ይላል፦ «በስራ ጉዳይ የከተማ ልጅና የገጠር ልጅ ለንፅፅር የቀረበ - ድምዳሜ አይደለም። 1ኛ. የገጠር ልጅ ስራ አይንቅም። ያገኘውን ይሰራል። እየሰራ ስራ ይፈልጋል። የከተማ ልጅ ስራ ሳይኖረው ስራ ያማርጣል። ገቢ ይንቃል። ስራ ፈትቶ ስራ ይፈልጋል። 2ኛ. የገጠር ልጅ ለአላማው መሳካት የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ይከፍላል። ይራባል፣ ይጠማል፣ ይታረዛል፣ እንቅልፍ ያጣል  . . . የከተማ ልጅ ነገን የተሻለ ለማድረግ ሳይሆን ዛሬን ለመኖር ይጥራል። በጊዜያዊ ብልጭልጭ ይሸወዳል።  3ኛ. የገጠር ልጅ ለአሰሪው ታዛዥ፣ አለቃውን አክባሪ ነው።  የከተማ ልጅ አለቃ ስር መስራት እንደ ሽንፈት፣ አሰሪ ስር መሆን እንደ ክሽፈት ስለሚያይ ምግባረ-ጎደሎ ነው። ለመታዘዝ ሳይሆን ለመሸወድ፣ ለማክበር ሳይሆን ለመናቅ ይሞክራል። 4ኛ. የገጠር ልጅ በትርፍ ሰአት ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ ስራ ፈልጎ ሲሰራ የከተማ ልጅ ያገኛትን ገቢ የሚያጠፋበት/የሚያባክንበት መንገድ ይፈልጋል። 5ኛ. የገጠር ልጅ አላማውን የሚደግፍ፣ ለግቡ የሚያግዘው ጓደኛ ሲይዝ የከተማ ልጅ ካለፈና ካገደመ ጋር እየዋለ ከአላማው ይዘናጋል፣ ግቡን ይረሳል። 6ኛ. የገጠር ልጅ የስራ ባህሉን እያሻሻለ፣ የስራ ሰአት አጠባበቁን እያረመ፣ የስራ እድገት እያገኘ ሲሄድ የከተማ ልጅ የስራ ባህሉ እያሽቆለቆለ፣ የስራ ሰአት እየቀሸበ፣ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ይሄዳል። አንዳንዴም ይባረራል! 7ኛ. የከተማ ልጅ ብዙ የሚያወራ፣ ሩቅ የሚመኝ፣ ትንሽ የሚተገብር ሲሆን የገጠር ልጅ ትንሽ የሚያወራ፣ ብዙ የሚተገብር የተግባር ሰው ነው። 8ኛ. የከተማ ልጅ ከነፈሰው ሲነፍስ፣ ያዋጣል የተባለ ሁሉ ላይ ሲዘፈቅ፣ ያበላል የተባለን በሙሉ ሲማር/ሲሰለጥን ይከርማል የገጠር ልጅ የያዛትን አንዷን አድምቶ ይሰራል። ያለበትን በደንብ ነክሶ ይዞ ይዘልቅበታል። ለዘርፉ የሚጠቅመውን እየተማረና እየሰለጠነ ወደ professional ያድጋል። 9ኛ. የገጠር ልጅ ወጪውንና ገቢውን አመጣጥኖ ቤተሰቡን ሲረዳ የከተማ ልጅ እስከ 40 መባቻ ከቤተሰቡ/ከእናቱ ጓያ አይወጣም። አሊያ ገቢውንና ወጪውን ማመጣጠን ከብዶት እየሰራ ከቤተሰብ ይዶገማል። 10ኛ. በመጨረሻም የገጠር ልጅ የልፋቱን ውጤት አግኝቶ ከተማ ላይ ቅንጡ መኖርያ፣ ምቹ መኪና፣ ምርጥ ድርጅት ሲመሰርት የከተማ ልጅ የገጠር ልጁን ቤት background አድርጎ አጥር ስር ነፃ wifi እየተጠቀመ ስለገጠሩ ልጅ ውድ መኪና በቲክቶክ ማብራሪያ ይሰጣል።» የአድስ አበባ ልጆች ሀሳብ ስጡበት እስኪ እኔ አላልኩም ደሞ!! https://t.me/Mohammedhassen1
Show all...
Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር

https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

በህይወታችን ለሚያጋጥሙን መልካም ያልሆኑ ነገሮች በሶስት መንገዶች ምላሽ መስጠት እንችላለን። የመጀመሪያው ራሳችንን መቀየር ነው።ይህም እኛ ጋር ትክክል ያልሆነ ባህሪ፣አመለካከት፣የግንኙነት ደረጃ፣የጊዜ አጠቃቀም እና ሌሎችም ካሉ እነሱን ማስተካከል ማለት ነው። ሁለተኛው ተፅዕኖ መፍጠር ነው።ይህ ማለት በዙሪያችን ያሉ ሁኔታዎች እንድቀየሩ ጥረት ማድረግ ነው።ይህም የተሳሳተ የስራ ዘይቤ፣ጎጅ ማህበራዊ ልማዶች፣የቤተሰብ አባላት እና የመሳሰሉት ሁኔታዎችን ያካትታል። ሦስተኛው ምንም ነገር አለማድረግ ነው።ማለትም ከሁኔታዎች ጋር ራሳችንን አስማምተን እና ተላምደን መኖር ማለት ነው።ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች፣የጅኦ ፖለቲካዊ ሁኔታ፣የኢኮኖሚ ሁኔታወች እኛ በግለሰብ ደረጃ ምንም አይነት ምላሽ የማንሰጥባቸው ነገሮች ናቸው። ሶስቱን መንገዶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ቀጥተኛ ተፅዕኖ፣ተዘዋዋሪ ተፅዕኖ እና ዝምታ ናቸው። https://t.me/Mohammedhassen1 https://t.me/Mohammedhassen1
Show all...
Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር

https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

👌 2
በወር 5 ፐርሰንት (5%)የመሻሻል ጥበብ ኢኮኖሚያዊ አቅማችሁን ለማሳደግ የአሁኑን ገቢያችሁን ቢያንስ አምስት በመቶ የሚያሳድግ ስራ ስሩ፤እንድሁም አሁን ከምትቆጥቡት የገንዘብ መጠን አምስት በመቶ ጨምራችሁ ቆጥቡ እውቀታችሁን ለማሻሻል አሁን ከምታነቡት መጠን አምስት በመቶ እየጨመራችሁ አንብቡ መንፈሳዊ መሻሻል ለማድረግ አሁን ከምትሰሯቸው መንፈሳዊ ስራዎች በተጨማሪ አምስት በመቶ መንፈሳዊ ስራዎችን ስሩ የአካል ብቃታችሁን ለማሻሻል አሁን ከምትሰሩት አምስት በመቶ ተጨማሪ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጉ ከላይ ያለውን መርህ በየወሩ እየገመገማችሁ ለአንድ አመት ያህል ተግባራዊ አድርጉት።በእርግጠኛነት አሁን ካላችሁበት አጠቃላይ ሁኔታ ቢያንስ በአርባ ወይም ሀምሳ በመቶ እድገት ታገኙበታላችሁ። https://t.me/Mohammedhassen1 https://t.me/Mohammedhassen1
Show all...
Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር

https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

1
ተሰጥኦህን አውጣው እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ እውቀት እና ችሎታ/ተሰጥኦ/አለው።ያንተ ተሰጥኦህ ምንድን ነው?መምህር ሆኖ ትውልድን መገንባት ወይስ ሀኪም ሆኖ በህመም የሚሰቃዩትን መፈወስ፤ግብርና ነው ውትድርና?እያንዳንዱ ሰው ተሰጥኦ ካለው አንተም የራስህን መፈለግ አለብህ፤እንዴት?የተለያዩ ስራዎችን በመሞከር እና በመስራት።አንድ ቦታ ተቀምጠህ አንድ አይነት ስራ እየሰራህ ኑሮ ከበደኝ አትበል።መንቀሳቀስ መቻል አለብህ!አሁን የምትሰራውን ስራ ካልወደድከው ሌላ ስራ ቀይር፤ያም ካልተመቸህ አሁንም ቀይር። "ሚስቴ አልጋ ላይ ሰነፍ ነች ብለህ ከፈታሃት ስህተቱ ያንተ ነው፤ምክንያቱም ሶፋ ላይ ወይም ወንበር ላይ መሞከር ትችል ነበር።"ብሏል አንድ ከቀድሞዎቹ የሆነ የአፍሪካ መሪ ህይወትን እየቀያዬርክ መሞከር መቻል አለብህ ወዳጄ!! https://t.me/Mohammedhassen1 https://t.me/Mohammedhassen1
Show all...
Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር

https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

👌 1
የሰው ልጅ አካሉ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ፣አእምሮው በንባብ እንድሁም አካሉ በዱዓ/ፀሎት/ይንቃቃል።በህይወታችሁ መነቃቃትን ካጣችሁ ወይም አሁን ያላችሁን መነነቃቃት ጠብቃችሁ ለማስቀጠል ከፈለጋችሁ፤    1.አዘውትራችሁ ስፖርት ስሩ 2.ንባብ የዘወትር ስራችሁ ይሁን 3.ሁልጊዜም ዱዓ አድርጉ፣አላህን ተማፀኑ https://t.me/Mohammedhassen1 https://t.me/Mohammedhassen1
Show all...
Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር

https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

👍 4🙏 1
ከመቶ ክፉዎች መሃል አንዱን መልካም ማየት የሚችል መነፀር ይኑርህ። አንድ እና ሁለት ሰዎች ክፉ ስለሆኑብህ በጅምላ ሰዎች ክፉ ናቸው የሚል  ፍርድ አትስጥ። ከክፉዎች መሃል ጥቂትም ቢሆኑ ደጋጎች አሉና… https://t.me/Mohammedhassen1 https://t.me/Mohammedhassen1
Show all...
Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር

https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

👍 3
#በላጭ_ዱዓእ "ረበና አቲና ፊ'ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዐዛበ'ናር" *አላህ ሆይ በዱንያም* *መልካሙን ሁሉ ስጠን፤* *በቀጣዩ ዐለምም መልካሙን ሁሉ ስጠን፤* *ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን። https://t.me/Mohammedhassen1 https://t.me/Mohammedhassen1
Show all...
Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር

https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐ “አራት አይነት ሰዎች የላቀው አላህ ይቆጣባቸዋል። በመሀላ የሚሸጥ፣ የድሃ ኩራተኛ፣ የሽማግሌ ዝሙተኛና በዳይ መሪ ናቸው።” https://t.me/Mohammedhassen1 https://t.me/Mohammedhassen1
Show all...
Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር

https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

ከፍጥረታት በሙሉ፣ጥበብ የተሰጠው ለሰው ልጅ ነው።የአደም ልጅ የተላቀበት አንዱ ነገር ጥበብ መሰጠቱ ነው።የተሰጠውን ጥበብ መጠቀም ያለመጠቀም የሱ ፈንታ ይሆንና። ጠቢቦች በእውቀት እና በእውነት ላይ ሆነው የሚያስቡ ናቸው። Copied https://t.me/Mohammedhassen1 https://t.me/Mohammedhassen1
Show all...
Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር

https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

👍 4 1
እቅድህ ሰባት ነገሮችን ከግምት ያስገባ እንድሆን እመክርሃለሁ፤ እነዚህን ሰባት ነገሮች ቀጥዬ እዘረዝርልሃለሁ። በእርጋታ አንብበህ በሚገባ ተረዳቸውና እቅድ ስታወጣ ተጠቀምባቸው። 1. መጣጣም;  እቅድህ በህይወትህ ካለው ነበራዊ ሁኔታ ጋር የተጣጣመ መሆን ይገባዋል። ራዕይህ እና ተልዕኮህ፤ ፕርግራምህ እና ቅድሚያ የምትሰጣቸው ነገሮች፤እንድሁም ልማዶችህ እና ፍላጎቶችህ መጣጣም አለባቸው ማለት ነው። 2. መመጣጠን; እቅድህ በህይወትህ ላይ መመጣጠንን የሚፈጥርልህ መሆን ይገበዋል።ማለትም የምታወጣው እቅድ በስራህ፣ከቤተሰብ እና ጓደኛ ጋር በሚኖርህ ግንኙነት፣በህልምህ/ራዕይህ/ እንድሁም በመንፈሳዊ ህይወትህ መካካል የተመጣጠነ ስኬት ሊያጎናፅፍህ የሚችል መሆን አለበት ማለት ነው። 3.አስፈላጊ ጉዳዮችን ብቻ የያዘ ይሁን; በእቅድህ ውስጥ የሚካተቱ ነገሮች ለዋናው አላማህ የሚያግዙ ብቻ መሆን አለባቸው።ዋናውን አላማህን ለማሳካት የማይጠቅሙህን ጉዳዮች በእቅድህ ውስጥ አታካትት። 4. ሰው ተኮር ይሁን; እቅድህን ለመተግበር የሌሎች ሰዎች እገዛ ያስፈልግሃል። የሌሎችን እገዛ ለማግኘት ደግሞ እቅድ ስታውጣ በዙሪያህ ያሉ ሰዎችን ከግምት ውሰጥ ማስገባት አለብህ። የራስህን ፍላጎት ብቻ ማሰብ የለብህም። 5. ተቀያያሪ; እቅድህ አገልጋይህ እንጂ ተቆጣጣሪህ መሆን የለበትም።ስለዚህ ዛሬ ላይ የምታወጣው እቅድ ወደፊት ሊከሰቱ በሚችሉ ሁኔታዎች ማሻሻል ቢያስፈልግህ በቀላሉ ልታሻሽለው የምትችለው መሆን አለበት። 6. ተንቀሳቃሽ;  እቅድህን በቀላሉ ይዘኸው ልታንቀሳቅሰው በምትችልበት መልኩ ማዘጋጀት አለብህ። ይህም በየጊዜው እንድታየው እና እያንዳንዱን እርምጃህን በእቅድህ ለመገምገም ይረዳሃል። 7.የአላህን ውደታ ለማግኘት የሚረዳህ መሆን አለበት: ምድራዊ ስኬት ብቻውን በቂ አይደለም።የምታወጣው እቅድ በደ አኼራ መሸጋገሪያ ሊሆንህ ይገባል። https://t.me/Mohammedhassen1 https://t.me/Mohammedhassen1
Show all...
Mohammed Hassen

መንገደኛ ነኝ ሩቅ ተጓዥ ቢጥሉኝ የማልሰበር ቢገፉኝ ከመንገዴ የማልወጣ ለመማር የምጓጓ ለህልሜ የምተጋ ጥያቄ ካላችሁ @moasya ተጠቀሙ የእናንተው የስኬት አጋር

https://t.me/BIGDREAMETHIOPIA00

5