cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መፅሀፍት እና ትረካ

በዚህ ቻናል ውስጥ የተለያዩ አዲስ ና ቆየት ያሉ መፅሐፍቶችን አስገራሚ እውነታዎች እንዲሁም አጫጭር እና ረዣዥም # ግጥሞች # ወጎች # ልብወለድ # አስተማሪ እና አነቃቂ ፅሁፎች ሚያገኙ ይሆናል!

Show more
Ethiopia10 087The language is not specifiedBooks15 485
Advertising posts
814Subscribers
+524 hours
+277 days
+11630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

➳➳➳ ይቀላቀላሉ! ➢➢➢ @bookandnarriation ~ @bookandnarriation ➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟
Show all...
ከዚ በፊት የተለቀቁትንም ታሪኮች ሙሉ ክፍሉን ምትፈልጉ @bookandnarriation ላይ #ረግሞ_ፈጥሮኝ #ፍቅርና_ትዳር #ያደረ_ፍቅር #ሞርያ #የቤዛዊት_አለሙ_እዉነተኛ_ታሪክ #የባከነች_ነበስ #ተስፋ_ያጣች_ሴት ሁሉንም በነዚ link ላይ ተጠቅማቹ ማንበብ ትችላላቹ😍.
Show all...
#ተስፋ_ያጣች_ሴት ፧ ፧ ( #የመጨረሻው_ክፍል ) ፡ ሀና ነገሮች እስኪጣሩ ተብሎ የታሰረውን ባሏን ቀን በቀን ትጠይቃለች በተፈጠረው ነገር በጣም ከመደንገጧም በላይ የቴድሮስ መሞት ውስጥ የኪሩቤል እጅ አለበት መባሉ እረፍት ነስቷታል እውነት ለመናገር ኪሩቤል ሊያስፈራራው እንጂ ሊገለው እንደማይደፍር እርግጠኛ ነች ... ሀና ልጇን ትምህርት ቤት አድርሳ ባልዋን ትጠይቅና እቤቷ ተቀምጣ ታስባለች ... ቴድሮስ ሲደፍራትና ሲያሰቃያት መኖሩ ከሞት በላይ ቢቀጣም አያሳዝናትም ነገር ግን ቴድሮስ በመጨረሻ ሰአት የተናገረውን አስታወሰች ለዚ ክፋት ያበቃችው አንዲት ክፉ ሴት ናት ... ሀና ይህን ካሰበች ቡሃላ "አይ አይ አይሆንም ምንም ቢሆን ይቅር አልለውም እኔ በእንጀራ አባቴ ስለተበደልኩ ወደፊት ሌላ ሰው ላይ ክፉ መሆን የለብኝም!" አለች... መሽቶ ይነጋል ኪሩቤልና የሀና አባት ሳይፈቱ 35 ቀናትን አስቆጠሩ ሀና የሷ ሳያንስ በሷ ምክንያት ለፍቅር ሲል መስዋዕት እየከፈለ ያለው ባልዋ ያሳዝናታል ያስጨንቃታል ሁሌ ታለቅሳለች በዚ መሀል ያብስራ ሊያገኛት ቢለፋም ሀና ግን ልታየው አፈረች ሁሌም ያብስራ ወንድሟ መሆኑን ስታስብ ከአባቷ ጋር የሰራችው ስህተት እረፍት ይነሳታል... የእናቷን ልጆች እሷ ጋር አምጥታ ከልጇ ጋር እያኖረቻቸው ነው ... እለተ ሀሙስ ሀና በጥዋት ተነስታ ሰራተኛዋን ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት እንድታደርሳቸው ካዘዘቻት ቡሃላ ወደ ቤተ ክርስትያን ሄደች ዛሬ የፍርድ ቀን በመሆኑ ኪሩቤል ነፃ ይወጣ ዘንድ እንባዋን አውጥታ ለአምላኳ ፀለየች ... ከዛም መኪናዋ ውስጥ እረጅም ሰአት ከቆየች ቡሃላ ወደ ፍርድ ቤት ሄደች ሰአቱ ደርሶ ስለነበር ሁሉም ሰው ገብቷል እዛ ያብስራም አለ አቃቢው የክስ ይዘቱን ማስታወስ ጀመረ "... ሟች አቶ ቴድሮስን አቶ ኪሩቤል መስፍንና አቶ ፀጋዬ ገ/ማርያም በግል ፀብ ተነሳስተው ገለዋቸው እንደነበር በማስረጃ አሳይተናል ... በመሆኑም ለዛሬ ፍርድ ሊሰጥ ቀጠሮ በመያዙ ፍርድ ቤቱ ተገቢውን ቅጣት እንዲሰጥልን እንጠይቃለን...!!" አለ ሀና ኪሩቤልን እያየች እንባዋ ይወርልዳ በዚ ጥቂት ቀን ውስጥ እንዲ ከተጎሳቆለ አመታት ቢፈረድበት ምን ሊሆን ነው ትላለች በውስጧ... ዳኛው ንግግራቸውን ቀጠሉ "ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት ተከሳሾች የምትሉት ካለ" አሉ ይሄን ግዜ የሀና አባት ያለምንም መረበሽ ..."ቴድሮስን የገደልኩት እኔ ነኝ ልጅ ኪሩቤል ምንም አያውቅም ልጄን ሲያሰቃይ በመኖሩና ሲዝትባት አናዶኝ ሆን ብዬ እኔ ገደልኩት ስለዚህ ኪሩቤል ነፃ ነው!!!" አለ ሀና ደንግጣ ፈዛ ቀረች ... የሀና ወላጅ አባት 15 አመት እስራት ሲፈረድበት ኪሩቤል ግን ነፃ ወጣ ሀና ፀሎቷ በመስመሩ ፈጣሪዋን አመሰገነች ... አባቷ ለመጀመርያ ግዜ ጥሩ ስራ በመስራቱ እረፍት ይሆነው ዘንድ ይቅር አለችው ። ሀና ሁለተኛዋን ልጇን ነብሰ ጡር እንዳለች ኪሩቤል ፕሮሰስ ጨርሶ እሷንም እህትና ወንድሟንም ወደ ጀርመን ወሰዳቸው በርግጥ ለሀና ከሀገር መውጣቷ ልክ ነበር ብዙ ችግሮቿን ለመርሳት በቅታለች አሁን ጀርመን ላይ ከምታፈቅረው ባልዋ ጋር በደስታ መኖር ከጀመረች አመት አልፏታል። 💫ተፈፀመ💫 ስለነበረን ቆይታ እናመሰግናለን🙏 ማንኛውንም አስተያየት ካላችሁ comment ላይ አድርሱን😍
Show all...
👍 8👏 3
ርዕስ :ሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ 2 #Requested #ሼር #ሼር #ሼር ለተጨማሪ መፅሐፍት ና ትረካ JOIN JOIN @bookandnarriation JOIN @bookandnarriation
Show all...
➳➳➳ ይቀላቀላሉ! ➢➢➢ @bookandnarriation ~ @bookandnarriation ➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟➟
Show all...
👍 1
#ተስፋ_ያጣች_ሴት ፧ ፧ #ክፍል_አስራ_ሦስት የሀና አባት እራሱን መሳቱ ለሀና ደስ አላላትም ምክንያቱም እሷ የፈለገችው ለአባቷ ቴድሮስ "ስምህን ሊያጠፋው ነው ሀጥያትክን ለልጆችህ ሊናገርብህ ነው!" ብላ ነግራው አባቷ ደግሞ ቴድሮስን አፉን እንዲያዘጋው ለማድረግ ነበር ግን አባቷ ቀድሞ ራሱን ሳተ ሀናም በፍጥነት አምቡላንስ ጠርታ አባቷን ሀኪም ቤት ካስገባችው ቡሃላ ለኪሩቤል ደወለችለት ኪሩቤልም ያለችበት ድረስ በፍጥነት ደረሰ... ሀናም ልክ ኪሩቤልን ስታይ እሩጣ አቅፋው ማልቀስ ጀመረች ኪሩቤል በሁኔታዋ ግራ ተጋብቶ ምን እንደሆነች ጠየቃት ከዛ ሀና አንድ ባንድ መናገር ጀመረች ... " " ... ቴድሮስ በልጅነቴ ያደረገው ሳያንስ አሁንም ገላዬን ተመኘ እናም የእናቴ ባል እኔ ህሊና ቢስ ስለመሰልኩት ስሜ እንዳይጠፋ ስል አብሬው እንድጋደም ፈለገ እምቢ ካልኩ ቅድሚያ ለአባቴ ልጆች ከዛ ደግሞ መነጋገርያ እንድሆን መፅሄት ላይ ከአባቴ ጋር አብሬ ማደሬን እንደሚያስወራብኝ አስፈራራኝ እኔም አባቴን አግኝቼው እንዲያስቆመው ፈልጌ ነበር ግን ለካ ችግረኛ ሴት በመጨረሻ የምታሸንፈው ፊልም ላይ ብቻ ነው! ለካ የእውነተኛው አለምላይ ይሄ የለም" ... ይህን ስትናገር ሀና በንዴትና በቁጭት እየጮኸች ነበር ኪሩቤል ካወራችው ሁሉ ውስጡ ዘልቆ የገባው ቴድሮስ ሀናን መመኘቱ ነበር ኪሩቤል ደርቆ ቀረ ሀናም "በቃኝ ከዚ ቡሃላ መኖር አልፈልግም እራሴን አጥፍቼ እገላገላለው ተስፋዬ በሙሉ አልቋል ተስፋ ቢስ ሴት ነኝ!!" አለችና ትታው ልትሄድ ስትል እጇን ይዞ ..."ሁለተኛ ይሄን ቃል እንዳትደግሚው ለእኔና ለልጄ እጅግ በጣም ታስፈልጊናለሽ ውዴ እኔ ቅጣት ለሚገባው ቅጣቱን እሰጥልሻለሁ!" አለ ኪሩቤል እንዲ ለበቀል ጥርሱን ሲነክስ የመጀመርያው ነበር... የሀና አባት ተሽሎት እቤቱ ገባ ሀናም ከቤት መውጣት አትፈልግም የፃፈቻቸውን ግጥሞች በሙሉ ቀዳደቻቸው ኪሩቤል በሀና ሁኔታ ያዝናል ! እሁድ ደረሰ ቴድሮስ ያን ቀን ካላገኛት ምን እንደሚፈጠር መገመት ለሀና ቀላል ነበር ጭንቀቷን ያየው ባልዋ ያን ቀን እሱ እስከሚደውል ድረስ ከቤት እንዳትወጣ በማስጠንቀቅ ከቤት ወጣ እህትና ወንድሟ ደግሞ እሷ ቤት ነበሩ ። ኪሩቤል ከቤት እንደወጣ ሳይመለስ ምሽት 4:00 ሞላ ይሄኔ ሀና በጭንቀት ልታብድ ደረሰች ልክ 4፡ 15 ላይ ስልኳ ጠራ አነሳችው ኪሩቤልም ቴድሮስ ቤት ነኝ ቶሎ ነይ አላት ሀናም ምን እንደተፈጠረ እንኳ ለመገመት ግዜ አታ በፍጥነት ደረሰች ኪሩቤል ቴድሮስን በጣም ቀጥቅጦት ነበር ሀና ይሄን ያደረገው ባሏ ባይሆን የቴድሮስን ሞት ለማየት ትቀመጥ ነበር ግን ኪሩቤል ይህን ማድረጉ እጅግ በጣም አስፈራት ቴድሮስም በደም በተለወሰው አፉ "ይቅርታ አርጊልኝ ሀና ክፉ የሆንኩት ወድጄ አይደለም እኔንም የእንጀራ እናት ነበረችኝ ክፉ ቃሉ የማይገልፃት እናም ሁሌም በአባቴ ላይ ትማግጥ ነበር በዛ ላይ ምግብ አትሰጠኝም ግን ቤታችን ውሃ ባለመኖሩ ውሃ ከእሩቅ ቦታ እየቀዳው የማመላልሰው እኔ ነበርኩ ሴት ልጅ እያለቻት እቃ ስታሳጥበኝና ቤት ስታፀዳኝ የምትውለው እኔን ነው እርሃብና መድሎ ተደማምረው ጭካኔዋ ውስጤ ጭካኔን ዘራ...በቃ ክፉ ሆንኩ" አለ ለመጀመርያ ግዜ ቴድሮስ በሀዘን ተውጦ በአይኖቹ እምባ ሲፈስ ሀና በአይኗ ተመለከተች የሰራው ሀጥያት ቢበዛም መሰረቱ ሌላ መሆኑን አወቀች ... በዚ ቅፅበት ከየት መጣ ሳይባል የሀና አባት በሩን በርግዶ ገባ በያዘው መሳርያም ቴድሮስን እዛው ከተንጋለለበት መሬት ሳይነሳ በጥይት ግንባሩን አለው ሀናና ኪሩቤል በድንጋጤ ጮሁ እዛው ባሉበት ደርቀው ቆመው ሳላ አካባቢው በሰው ተሞላ ከደቂቃዎች በኋላም ፖሊስ መጥቶ ሶስቱንም ይዟቸው ወደጣብያ ሄደ ሀና በነጋታው ጠዋት ብትፈታም ባሏና ወላጅ አባቷ ግን እስኪጣራ በሚል ሳይፈቱ ቀሩ.. 💞ይቀጥላል💞 የመጨረሻው ክፍል👉ወደ @metshafit group  አዲስ 100 ሰው አድ ስታረጉ ይለቀቃል ሙሉ ክፍሉን @bookandnarriation ላይ ያገኙታልከ
Show all...
😱 6👍 3
እናም ይህን ለልጆችህ ተናግሬ በሀፍረት ሳትሞት በፊት እኔን ከዚ ታደገኝ ከስቃይ አውጣኝ አለች በምሬት አባት ግን ይህን የሚሰማበት ሞራል አጣ ማንም በሌለበት ጭር ባለው ቦታ እያየችው መሬት ላይ ተዘረረ... 💞ይቀጥላል💞 ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ  👉ወደ @metshafit group  አድ እያረጋቹ ከዛ ክፍል #አስራ_ሶስት ይቀጥላል😁 ሙሉ ክፍሉን @bookandnarriation ላይ ያገኙታል
Show all...
😱 7
#ተስፋ_ያጣች_ሴት ፡ ፡ #አስራ_ሁለት ፡ ሀና ችግሮቿ አሁንም አለመቆማቸው ቢያበሳጫትም የልጇ አባት ኪሩቤል መሆኑን ግን እርግጠኛ ነች። ነገር ግን እንዴት ሀኪሞቹ አባቱ አይደለም አሉ? ይሄ የማይታመን ነው ኩሩቤልም ልጇ ማክቤልም አሁን አልጋ ላይ ናቸው ታመዋል ሁለቱም ደግሞ ለሀና የመኖሯ ዋስትና ናቸው! ለዚም ሁለቱም በፍጥነት መዳን አለባቸው ... ሀና እያለቀሰች "ኪሩ የልጄ አባት ነው እባካቹ አስተውሉ ልጄን ወይ ባሌን ባጣ ዋጋ ትከፍላላቹ!!" እያለች የሀኪም ቤቱን ቢሮ ባንድ እግሩ አቆመችው ዶክተሩም በድጋሚ ለመመርመር ቃል ገብቶላት ሀናን አረጋጋት እሷም ባልዋን ለማየት ወደተኛበት ክፍል አመራች... ኪሩቤል ነቅቷል ስታየው እንባዋን መቆጣጠር አቃታት የኔ ፍቅር አለችና ከተኛበት አልጋ ስር በጉልበቷ ተንበርክካ እጆቹን ያዝ አደረገች ኪሩቤል ግን እጁን አስለቅቋት ፊቱን አዞረባት ይህን ማየት ለሀና ትልቅ ህመም ነው ኪሩቤል ከነብዙ ጉድለቷ እብዝቶ አፍቅሯት ነበር ዛሬ ግን ኪሩቤል አዝኖባታል ... ሀናም "የኔ ፍቅር በሞተችው እናቴ ስም እምልልሃለው ማክቤል ያንተ ልጅ ነው የኔ ውድ እባክህ እራስህን አረጋጋ !" አለች እሱም አይኑ እምባ አቅርሮ መናገር ጀመረ "ውዴ አፈቅርሻለው ግን ማክቤልን ነጠቅሽኝ ያለፈ ማንነትሽን ባውቅም ልጄ የኔ መስሎኝ ነበር ግን አንቺ ጨካኝ ሴት ነሽና ለኔ ሳልሰስት ለማፈቅርሽ ሰው እንኳ አራራሽም!" አለ ይህን ሲናገር ለመጀመርያ ግዜ ተስፋ መቁረጥ ይነበብበታል... ይህን እይተባባሉ አንዲት ቀጠን ያለች ነርስ በሩን ከፍታ ገባች... ሁለቱም በእንባ ታጅበው ወደነርሷ ተመለከቱ... ነርሷም ረጋ ባለ አነጋገር "ይቅርታ የማክቤል ወላጆች በተሳሳተ መረጃ ነበር የኪሩቤልና የህፃን ማክቤል ደም ያልተመሳሰለው ለዚም ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን አሁን ልጃቹ በሙሉ ጤንነት ላይ ስለሚገኝ ወላጆቹ እንዲያዩት ይፈልጋል!" አለች ኪሩቤል ከተኛበት ተፈናጥሮ ተነሳ ያ ተስፋ የቆረጠውና መነሳት አቅቶት በሆስፒታል አልጋ የተኛው ሰው አሁን ሙሉ ጤነኛ ነው እንዳዲስ የተወለደ መሰለው ሀናን አቀፋት ተቃቅፈው ተላቀሱ .... ኪሩቤል ለልጁ ደም በመለገሱና ራሱስ ስቶ ስለነበር እንዲያርፍ ቢነገረውም እሱ ግን ማንንም ሳይሰማ ልጁን ለማየት ክፍሉን ለቆ ወደ ማክቤል ከሚስቱ ጋር ሄደ ... ሀናም የግጥም መድብሎቿን ይዛ ልታቀርብ ወደተጋበዘችበት ሆቴል ስትሄድ ኪሩቤል አብሯት ነበር ከሰአታት ቡሃላ መድረክ መሪው ሀና ፀጋዬ እባክሽ ወደ መድረክ አለ ሁሉም ሰው እሷን ለማየት የጓጓ ይመስላል ሀና በፈገግታ ወደመድረክ ወጣች ሁሉም ሰው በጭብጨባ ተቀበላት ሀና ልእልት መስላለች ኪሩቤልም በስስት እያያት ግጥሟን ለማዳመጥ ህሊናውን ሰብሰብ አደረገ ይሄኔ ሀና ድምፅ ማጉሊያውን ተቀብላ ... # እማ... እናቴ የት አለሽ ድምፅሽን አሰሚኝ እስቲ ቀና ብለሽ ላፍታ ተመልከቺኝ ያኔ ስትለፊልኝ ስትደክሚ ኖረሻል እድሜሽን ሰውተሽ ህይወት ሆነሽኛል ታድያ ቀና በያ ውጤቱ ደርሶልሻል እማ ተመልከቺ ዘርሽ አፍርቶልሻል ለከፈልሽው ዋጋ ክፍያ ይሁንሽ ብዬ አንቺን ለማስደሰት ይሄው ዛሬ ደረስኩ በሁለት እግሮቼ ተደላድዬ ቆምኩ ግን አንቺ የለሽም የዘራሽውን ዘር ቡቃያ አላየሽም የልጅሽን ስኬት ለማየት አልታደልሽም... ሀና ግጥሙን ሳትጨርስ እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት አቆመችው ሁሉም ሰው በሀና ግጥም ስሜቱ ተነካ ሁሉም ሰው እንባውን አዘነበው ይሄኔ ሀና ለመረጋጋት ውጪ ወጣች ቴድሮስም ከየት መጣ ሳትለው " ሀና" አላት ስታየው እንደመደንገጥ አለች "መድረክ ላይ ወጣሽ ደስ ብሎኛል ግን አንድ ነገር እወቂ እጠላሻለሁ እናም ስምሽን አጠፋዋለሁ ሴተኛ አዳሪ በነበርሽበት ወቅት ከአባትሽ ጋር ስላደረግሽው ነገር አሶርቼ በሀፍረት እራስሽን ታጠፊያለሽ!!!!" አላት ሀና የእንጀራ አባቷን የእውነቷን ፈራችው "ይህን እንዳታደርግ" አለች ድምፅዋ እየተቆራረጠ እሱም እሱን "እንዳላደርግ እብረሽኝ እደሪ" አላት ሀናም በስሜት ንዴቷን መቆጣጠር እያቃታት በጥፊ መታችው የእንጀራ አባቷ አብሯት ማደር መፈለጉ እንኳን ለሀና ለሰሚም ይከብዳል ... ሀና በጥፊ ስትመታው ቴድሮስ ከት ብሎ ሳቀ ይሄኔ ሀና በፍርሃት መንቀጥቀጥ ጀመረች ... ሁለቱ በዚ መልኩ ተፋጠው ሳለ ስታስበው ያብስራ መጣ ባልጠበቀችው ጊዜና ቦታ መገኘቱ ለሀና ትንሽ ግራ ቢገባትም ያብስራ ግን በእንባ ተሞልቶ "እህቴ ሀና ታውቂ ነበር??"... ብሎ እንደ ህፃን ልጅ ጭምቅ አርጎ አቀፋት ... ሀና ግን ሀሳቦቿ ትርምስምስ ስላሉ ያብስራ ያለውን በስትክክል አልሰማችም ... ቴድሮስም "ኦ ያባቷ ልጅ ካካካ..." ብሎ እሷን ለማናደድ የውሸት የሚመስል ሳ ሳቀ ያብስራ ግን ነገራቸው ስላልገባው ንግግሩን ቀጠለ "አዎ ሀናን ከልጅነቴ ጀምሮ ከልቤ እመኛት ነበር እውነት ለመናገር እህቴ መሆኗን ሳላውቅ አፍቅሬአት ብዙ ተሰቃይቼ ነበር ግን እሷ ምክንያቷን ሳላውቀው ሸሸችኝ ግን አሁን ገባኝ ሀኒ እህቴ ናት ..." አለ ያብስራ ይህን ሲናገር ኪሩቤልም ካጠገባቸው ይሰማ ነበር ... ቴድሮስም ሀናን ቀና ብሎ እያየ "የልጄ ወንድም ስለሀናና አባቷ ግንኙነት ታውቃለህ? ወይስ ልንገርህ ?" አለ ኪሩቤል በቴድሮስ ንግግር ግራ ተጋባ እናም ኮስተር ብሎ "ምን ለማለት ፈልገህ ነው?" አለው ሀና ግን ለማንም ምንም መልስ አልሰጠችም! ኪሩቤል ሲመለከታት አንድ ነገር እንዳለ አውቋል ግን ምን እንደሆነ አልገባው አለ ... ቴድሮስም "ሀና አስቢበት እንገናኛለን!" ብሎ ሄደ ሁለቱም ሀናን ተመለከቷት ሀና ተረብሻለች "ያብ ግን ማን ጠራህ እዚ" አለችው እሱም ወደኪሩቤል እየተመለከተ ጥሩ ባል ነው ያለሽ... እህቴ እንደሆንሽ አባቴ ከነገረኝ ወዲ ስፈልግሽ ነበር!" ሲል ሀና አቋርጣው አባቴ? ያውቀኛል እንዴ? አለች አይ ሀኒ አሁን አያውቅሽም የልጅነትሽን ፎቶ ይዞት ስለነበር አሳየኝ እና እኔ አወኩሽ አለና.. .ንግግሩን ቀጠለ ከዛ ትላንት ባለቤትሽን አግኝቼው እዚ ዝግጅት ላይ ጋበዘኝ እናም..." አለና ንግግሩን ሳይጨርስ እንባው አስቸግሮት ዝም አለ... ከዛ "እሺ ያብዬ እንገናኛለን " ብላ ወንድሟ ያብስራን ተሰናብታው ኪሩቤልን እጁን ይዛ ወደመኪናዋ ተጣደፈች... ከዛ ቀን ጀምሮ ከያብስራ ጋር ይጠያየቁ ጀመር ከአባቷ ጋር ሊያስተዋውቃት ቢፈልግም እሷ ግን ብቻዋን ሰርፕራይዝ ልታረገው እንደምትፈልግ ነገረችው እሱም በሀሳቧ ተስማማ ... አንድ ቀን ፀጉር ቤቷ ቁጭ ብላ መፅሃፍ ስታነብ ቴድሮስ መልክት ላከ ስልኳን ከፍታ ማንበብ ጀመረች ቴድሮስም ሀኒዬ እንዴት ነሽ ዝም ስልሽ የተውኩት እንዳይመስልሽ ግዜ ልስጥሽ ብዬ ነው ለማንኛውም የፊታችን እሁድ ጥሩ ሆቴል እራት እጋብዝሽና አብረን እናድራለን አይ ካልሽ ግን ለወንድምሽ ከአባትሽ ጋር እንደማገጥሽ እነግረዋለው በዛም አይበቃኝ..." ይላል ይሄኔ ሀና በውስጧ አምላኳን አማረረች ውሳኔ ላይ መድረስ እንዳለባት በማመን "ተስማምቻለው!" ብላ ላከችለት ... ሀና ለባልዋ ሳትነግረው ከያብስራ የአባቷን ስልክ በመቀበል አባቷን እራቅ ያለ ቦታ ቀጠረችው አባቷም በተባለው ሰአት ደረሰ ሀናን ሲያያት ደነገጠ የት እንደሚያውቃት አያውቅም ግን ይህችን ሴት ያውቃታል ልጄ ከዚ በፊት አይቼሽ አውቃለሁ አላት ለማቀፍ እየተጠጋ እሷም እንዳትነካኝ አቶ ፀጋዬ አለች ይቅርታ ይሄን ያክል አመት ልጄ አለማለቴ ጥፋት ነው እናም... ሲል ንግግሩን ሳታስጨርስ አይ አይ አሁን ይቅርታ እንድጠይቀኝ አልመጣሁም ባንተ ሀጥያት ስቀጣ መኖሬ ሳያንስ ባንተ ልክስክስነት ከገዛ ልጅህ ጋር በማደርህ ዛሬም ወደፊትም ስቃይ ላይ ነኝ
Show all...
👍 4 1
በኪሩቤል ግፊት ለ1ወር ሀና ቤቷ አስታመመችው ከዛም ሰራተኛ ቀጥራለት ልጆቹን ይዞ ቤቱ ገባ ሀና ሁሌም ስታየው ክፋቱን ታስታውሳለች ያሳለፈችው ስቃይ በጠቅላላ በሱ ጭካኔ የተመሰረተ ነው ልጇን ሲስመው ብትከለክለው ደስ ይላታል ምክንያቱም ያኔ በሆዷ እያለ ዲቃላ ብሎ ሰድቦባት ስለነበር... ይህ በእንዲህ እንዳለ ሀና ከፀጉር ስራዋ በተጨማሪ የግጥም ተሰጦዋን ለማዳበር ትምህርት ቤት ገብታ መማር ጀመረች ...ብዙ ግጥሞችንም መፃፍ ጀመረች በዚም ሀና የራሷ አስተማሪ የጥበብ ምሽት ላይ ስራዋን እንድታቀርብ ጋበዛት ይህም የህይወቷ ትልቁ እርምጃ ነበርና በደስታ እየቦረቀች ላባልዋ ልትነግረው ስትጣደፍ ከልጇ ትምህርት ቤት ተደወለላት ማክቤል ታሟልና ቶሎ ድረሽ ተባለች ሀናም የልጇ መታመም ከልክ በላይ አስደንግጧት ባልዋ ለልደቷ በሰጣት ቪትስ መኪና ስትበር ደረሰች... ሀኪም ቤት ገብቶ ወላጅ አባቱ ደም እንዲሰጥ ታዘዘ ይሄኔ ማመን የሚከብድ ጣጣ ገጠማት ኪሩቤል የማክቤል ወላጅ አባት አይደለም ኪሩቤል ይህን ሲሰማ ራሱን ሳተ... 💞ይቀጥላል💞 ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ  👉ወደ @metshafit group  አድ እያረጋቹ ከዛ ክፍል #አስራ_ሁለት ይቀጥላል😁 ሙሉ ክፍሉን @bookandnarriation ላይ ያገኙታል
Show all...
😱 9