cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

HAKIM Ethio

Telegram Channel፦ t.me/hakimethio1 Telegram Group ፦ t.me/hakimethio2 Facebook Page ፦ https://m.facebook.com/104755325677864/ Website:- www.hakimethio.com

Show more
Ethiopia6 613The language is not specifiedMedicine9 441
Advertising posts
1 892Subscribers
+224 hours
+97 days
+4830 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የአእምሮ ሞት እና የትንፈሳ እጥረት ምርመራ(Brain death and apnea test) ===================== አንድ ሰው ፅኑ ህክምና ክፍል (ICU) ሲታከም ከፍተኛ ክትትል ይደረግለታል በተጨማሪም የሰውነቱ ክፍሎች መስራት የሚገባቸውን ስራ የሚተኩ ማሽኖች ሊኖሩ ይችላሉ። አንድ ሰው አእምሮው ሙሉለሙሉ ሞቶ ነፍሱ ግን ላትወጣ ትችላለች። ሳንባውን አእምሮው ማዘዝ ሲያቆም በማሺን እንዲተነፍስ (Mechanical ventilation) ማድረግ ይቻላል። ልብ ያለ አእምሮ ትእዛዝ መምታት ትችላለች። ስለዚህ ግለሰቡ ልቡ ይመታል፤ ይተነፍሳል ግን አእምሮው ሞቷል። መስተካከል የሚችል ህመም ሳይኖር የአእምሮ ሞት ላይ ከደረሰ በህክምናው እንደሞት ስለሚቆጠር የመተንፈሻ ማሽኑ ሌላ የሚተርፍ ታካሚ እንዲጠቀምበት ይነቀላል። (መስተካከል የሚችል ማንኛውም አይነት ነገር ከመሞከር ግን ወደ ኋላ አይባልም።) ውሳኔው እጅግ ትልቅ ውሳኔ ስለሆነ አእምሮው መሞቱን በሚገባ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ስለዚህ የአእምሮ ሞትን ቢያንስ በሁለት የተለያዩ ሀኪሞች ለየብቻ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው። በተጨማሪም የሚያስፈራ ምርመራ አለው። የትንፈሳ እጥረት ምርመራ (Apnea test)። የትንፋሽ ምርመራውን ለመስራት በቅድሚያ 100% ኦክስጅን በደንብ ለታካሚው በማሽኑ አማካኝነት ይሰጠዋል። ከዛ ማሽኑ ይነቀላል። ግለሰቡ ምንም የመተንፈስ ምልክት ሳያሳይ ለ6-8 ደቂቃዎች ከቆየ በደሙ ውስጥ ያለው የካርቦን ዳይኦክሳይድ ይለካል። ከ60mm Hg በላይ ከሆነ አእምሮው ሞቷል ማለት ነው። አንድ ሰው ትንፋሽን የሚቆጣጠረው ወሳኝ የአእምሮ ክፍል ሳይሞት ግለሰቡ ቢፈልግ እንኳን ትንፋሹን መያዝ አይችልም። የካርቦን ዳይ ኦክሳይድ መጠን ከፍ ሲል ሳይወድ በግድ አእምሮው ያስተነፍሰዋል። ይህን ካላደረገ አእምሮው መሞቱን ማረጋገጥ ይቻላል። ህክምና ከባድ ስራ ነው።  አንዳንዴ እጅግ አስቸጋሪ ውሳኔዎች መወሰን ይጠይቃል። ብዙ ሰው ስለሞት ማውራትም ማሰብም አይፈልግም።  በከፍተኛ ጫና ውስጥ በፅኑ ህክምና ክፍል ውስጥ በየደቂቃው ከሞት ጋር ግብግብ ገጥማችሁ ለምትሰሩ ነርሶች፣ የአንስቴዢያ፣ የል፣ የሳንባ፣ የውስጥ ደዌና የነርቭ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ጭንቀታችሁን  እንረዳለን። ስለ አገልግሎታችሁ እናመሰግናለን። ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!! በዩቲዩብ ተቀላቀሉን https://www.youtube.com/@dryonaslakew3386 ዶ/ር ዮናስ ላቀው Telegram: t.me/HakimEthio1
Show all...
HAKIM Ethio

Telegram Channel፦ t.me/hakimethio1 Telegram Group ፦ t.me/hakimethio2 Facebook Page ፦

https://m.facebook.com/104755325677864/

Website:- www.hakimethio.com

👍 7
Congratulations to the sixth batch graduates of Pediatric and Child Health specialists of Tibebe Ghion Specialized Hospital, Bahir Dar University, 2024. Telegram: t.me/HakimEthio1
Show all...
ኪንታሮት | ሄሞሮይድስ | Hemorrhoids ➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️➖〰️ 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 ✅ ኪንታሮት ምንድን ነው? 🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️ ኪንታሮት ወይም ሄሞሮይድስ በፊንጢጣ አካባቢ ያበጡ የደም ስሮች ናቸው። እነዚህ እብጠቶች ውስጣዊ ወይም ውጫዊ ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም ሕመም፣ ማሳከክ እና የደም መፍሰስን ወይም መድማት ሊያስከትሉ ይችላሉ። ኪንታሮት እንዳለብዎት ከተጠራጠሩ ትክክለኛ ምርመራ እና ተገቢ የሕክምና አማራጮችን ለማግኘት፤ የጤና ባለሙያን ማነጋገር ወይም ማማከር በጣም አስፈላጊ ነው። 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 ✅ የኪንታሮት ዓይነቶች | Types of Hemorrhoids 🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️ 1️⃣ ውስጣዊ ኪንታሮት | Internal Hemorrhoids! 🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤 እነዚህ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ማየትም ሆነ ስሜት ማግኘት አይቻልም። አብዛኛውን ጊዜ ከአንጀት እንቅስቃሴ (ሽንት ቤት ከተጠቀሙ) በኋላ ደማቅ ቀይ ደም ያስከትላሉ። 2️⃣ ውጫዊ ኪንታሮት | External Hemorrhoids! 🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤 እነዚህ በፊንጢጣ አካባቢ ባለው ቆዳ ስር ይገኛሉ። ስንዳስሳቸው እብጠት ያላቸው ሲሆን፤ ህመም፣ ማሳከክ እና ደም መፍሰስ ወይም መድማት ሊያስከትሉ ይችላሉ። 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 ✅ መንስኤዎች | Causes 🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️ 🍓 በአንጀት እንቅስቃሴ ወቅት መወጠር፡- ይህ በሆድ ድርቀት ወይም በተቅማጥ ምክንያት የሚከሰት የተለመደ ምክንያት ነው። 🍓 ለረጅም ጊዜ መቀመጥ:- በተለይ ሽንት ቤት። 🍓 እርግዝና:- በደም ሥሮች ላይ ያለው ጫና እየጨመረ ይሄዳል። 🍓 ከመጠን በላይ መወፈር፡- ከመጠን በላይ ክብደት የፊንጢጣ አካባቢን እንዲወጠር ሊያደርግ ይችላል። 🍓 እድሜ፡- ሰዎች እያረጁ ሲሄዱ (ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ) የደም ሥሮችን የሚደግፉ ሕብረ-ሕዋሳት ይዳከማሉ። 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 ✅ ምልክቶች | Symptoms 🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️ 🍋 በአንጀት እንቅስቃሴ ወቅት ህመም የሌለው ደም መፍሰስ:- ይህ በጣም የተለመደው ምልክት ነው። 🍋 በፊንጢጣ አካባቢ ማሳከክ ወይም መቆጣት:- በተለይ በውጫዊ ኪንታሮት ጊዜ። 🍋 ህመም ወይም የምቾት ማጣት:- በተለይም በአንጀት እንቅስቃሴ ወቅት። 🍋 በፊንጢጣ አካባቢ እብጠት ወይም መጠጠር:- በተለይ በውጫዊ ኪንታሮት ጊዜ። 🍋 የሰገራ ማምለጥ (መውጣት)፡- ይህ ከውስጣዊ ኪንታሮት ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል። 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 ✅ ሕክምና | Treatment 🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️ 👉👉 የቤት ውስጥ መፍትሄዎች! 🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤 🍎 ሙቅ መታጠቢያዎች፡- በሞቀ መታጠቢያ ገንዳ ውስጥ መታጠጥ የሕመም ምልክቶችን ለማስታገስ ይረዳል። 🍎 ያለ ሐኪም ማዘዣ የሚገዙ ክሬሞች ወይም ቅባቶች፡- እነዚህ ከማሳከክ እና ከህመም እፎይታን ያስገኛሉ። 🍎 የፋይበር ሰፕሊመንትች:- ሰገራን ለማለስለስ እና መወጠርን ለመቀነስ ይረዳሉ። 🍎 እርጥበት፡- ብዙ ውሃ መጠጣት ሰገራን ለማለስለስ ይረዳል። 👉👉 የኪንታሮት ሕክምናዎች፡- 🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤🚤 🍏 የረበር ባንድ ማሰሪያ | Rubber band ligation:- የደም አቅርቦቱን ለመቀነስ የረበር ባንድ በኪንታሮት ስር የሚቀመጥበት ሂደት ነው። 🍏 ስክሌሮቴራፒ | Sclerotherapy:- ኪንታሮትን ወይም ሄሞሮይድን ለመቀነስ ፈሳሽ ኬሚካል በመርፌ መወጋት። 🍏 ሄሞሮይድክቶሚ | Hemorrhoidectomy:- በቀዶ-ጥገና ሕክምና ኪንታሮትን ማስወገድ። 🍏 ሄሞሮይድ ስቴፕሊንግ | Hemorrhoid stapling:- ወደ ሄሞሮይድል ቲሹ የደም ፍሰትን ለመግታት የሚደረግ የአሰራር ዘዴ ነው። 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 ✅ መከላከያ መንገዶች | Prevention 🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️🚣🏿‍♂️ 🍊 ከፍተኛ የፋይበር ይዘት ያላቸውን ምግቦች ይመገቡ፡- ይህ በሆድ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት የሆድ ድርቀት እና መወጠርን ይከላከላል። 🍊 እርጥበትዎን ይጠብቁ:- ብዙ ውሃ ይጠጡ። 🍊 መወጠርን ያስወግዱ፡- የአንጀት እንቅስቃሴን በተሰማዎት ጊዜ (ሠገራ ሲመጣዎት) ሳይዘገዩ ፈጥነው ወደ መጸዳጃ ቤት ይሂዱ። እንዲሁም መጸዳጃ ቤት ሲጠቀሙ አያምጡ። 🍊 አዘውትረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ:- መደበኛ የአንጀት እንቅስቃሴን ያበረታታል። 🍊 ለረጅም ጊዜ ከመቀመጥ ይቆጠቡ:- እረፍት ይውሰዱ እና ይንቀሳቀሱ። 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 የኪንታሮት ወይም የሄሞሮይድ ምልክቶች ካጋጠምዎት ትክክለኛ ምርመራ እና ተገቢውን ህክምና ለማግኘት የጤና ባለሙያ ማማከር ወሳኝና  በጣም አስፈላጊ ነው። 🟪 ጠቃሚ መረጃ ነውና ለወዳጆችዎ ያካፍሉ 🟪 👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉👉 ➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️ ምንጮች:- Mayo Clinic, American Academy of Family Physicians (AAFP), National Institute of Diabetes and Digestive and Kidney Diseases (NIDDK), WebMD, MedlinePlus. ➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️➖➖〰️〰️ ©️FHCSH Telegram: t.me/HakimEthio1
Show all...
HAKIM Ethio

Telegram Channel፦ t.me/hakimethio1 Telegram Group ፦ t.me/hakimethio2 Facebook Page ፦

https://m.facebook.com/104755325677864/

Website:- www.hakimethio.com

👍 5 1
በቅድምያ ምስጋናችን ለእቅፍ በሚያዳግት አበባ ይድረሳቹ እያልን. ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያን መደገፍ እንፈልጋለን ላላቹ እነሆ የንግድ አካውንታችን CBE account: 1000382769523,Healing Valves Ethiopia We deeply appreciate everyone who showed interest to contributes and support Healing Valves Ethiopia (HVE). Your dedication and assistance mean the world to us. Thank you sincerely for all that you do. CBE account: 1000382769523,Healing Valves Ethiopia.
Show all...
📌Vacancy Announcement Telegram: t.me/HakimEthio1
Show all...
*አስፕሪን: ስትሮክን ያክማል ፤ ስትሮክንም ሊያመጣ ይችላል* ======== አንዳንድ ሰዎች አስፕሪን'ን ደም መርጋትን ለመከላከል በሚል ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ሲወስዱ ይታያሉ። መድሐኒቱ ዘመን የተሻገረ ገናና ዝናን ያተረፈ ነው። በተለይ የልብ ህመምን እና ስትሮክን በመከላከል ረገድ ዝናው የናኘለት ነው። ዝነኛ መድሐኒት ነው። አስፕሪን ለቅድመ መከላከል ተግባር እንደማይውል ተረጋግጧል። ያም ማለት ቀድሞ የልብ ህመምን አለያም ስትሮክን አይከላከልም። ችግሩ ከተፈጠረ በሗላ ግን ዳግም እንዳይፈጠር ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መድሐኒት ነው። የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች አስፕሪንን ያለ ትዕዛዝ ዛሬም ይወስዳሉ። ለምን ሲባሉ< ደም እንዳይረጋ > ነው የሚሉት። ደም እንዳይረጋ የማድረግ ስሪት ስላለውና በቀደመው ዘመን ሁሉም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ይውሰዱ ተብሎ ስለነበር ነው። ያ አሁን በነበር ተሽሯል። በቅድመ መከላከል /primary prevention/ ሒደት ጥቅም አይሰጥም። ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። አስፕሪን ስትሮክን ያመጣል። የተፈጥሮ ደም ማርጊያ ስርዓትን በማስተጓጎል ለመድማት ዳርጎ ስትሮክን ይወልዳል። አስፕሪን በሁለት ሰይፍ የተሳለ ነው ማለት እንችላለን። ስትሮክን ያክማል ይከላከላል ፤ በሌላ ጎን ለስትሮክ ይዳርጋል። የዘርፉ ባለሙያዎች የሚያስፈልጉት እዚህ ጋር ነው ! አስፕሪን ለማን እና መቼ ይሰጣል? ለማን የተከለከለ ነው? የሚለውን አጣብቂኝ ውሳኔ ለመበየን ሙያዊ እይታን ይፈልጋል። በኛ ሀገር ብቻ ሳይሆን በሌሎች ሀገርም አስፕሪንን ያለ ሐኪም መውሰድ ባህል ሆኖ ቀጥሏል። መጥፎ ልማድ!! ስትሮክ ፣የደም መርጋት፣ የልብ ህመም ያጋጠማቸው እንደየ ግለሰቦቹ ግለ ታሪክና ህመም መንስኤ አስፕሪን ሊታዘዝ ይችላል። የማይታዘዝላቸው እንዳሉ ይወቁ። ምናልባትም መውሰድ የማይገባቸው ከወሰዱ ለከፋ ችግር ተጋላጭ ስለሚሆኑ ምንጊዜም ቢሆን ሐኪሞን ያማክሩ። በተጨማሪ አስፕሪን ለህመም መስታገሻ ፤ ለብግነት መድሐኒትነት ያገለግላል። ያለ አግባብ ሲወሰድ እና እንደ ጎንዮሽ የሚጠቀሱት የጨጓራ መድማት (ህመም) ፤ ስትሮክ  ናቸው። በዚህ መጣጥፍ እገሌ ውሰድ አትዉሰድ ማለት ይከብዳል። እያንዳንዱ የተለየ ስለሆነ ለእያንዳንዱ ሰዉ ሐኪሙ የሚሰራው የሒሳብ ስሌት ስላለ ቀላሉ መንገድ ሐኪም ማማከር ነው። ያለ ባለሙያ ትዕዛዝ እየወሰዳችሁ ካላችሁ ፈጥናችሁ ሙያዊ ምክር ተቀበሉ። 1)Jankovic J, Mazziotta JC, Pomeroy SL, Newman NJ, Bradley WG (Walter G. Bradley and Daroff’s neurology in clinical practice; eighth edition :P.1389 ዶ/ር መስፍን በኃይሉ (ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል) ©️CHSAAU Telegram: t.me/HakimEthio1
Show all...
HAKIM Ethio

Telegram Channel፦ t.me/hakimethio1 Telegram Group ፦ t.me/hakimethio2 Facebook Page ፦

https://m.facebook.com/104755325677864/

Website:- www.hakimethio.com

👍 8
👍 1
Updates & Attention: ✍️Hayyama Jijjiirraa  Hojjataa Seektaraa Fayyaa Marsaa  2ffaa Bara 2016. Hub:1.Ragaa Jijjiirraa GP ,IESO fi Specialist ragaan qulqulluun unka jijjiirraa akkaataa qajeelfamaan guutameen lakk.telegram.0916365708 fi0966884365 biiroof ergama.👇👇👇 Telegram: t.me/HakimEthio1
Show all...
👍 2