cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

FANOS BOOKS

፨፨ Fanos BOOKS ፨፨ ሰላም ፣ጤና ፍቅር ከናንተ ጋር ይሁን ውድ የFanos BOOKS የቴሌግራም ቻናል ቤተሰቦች| በዚህ ቴሌግራም ቻናል መፅሀፍትን በpdf እና በትረካ በቀላሉ ፈልገው ያገኛሉ እንዲሁም ፣የደራሲያን ታሪኮች ፣ግጥሞች ፣ወጎች ፣ልብወለዶች ፣ምክሮች ፣ድንቃድንቆች ፣አዝናኝ እና አስተማሪ ፅሁፎች ይቀርባሉ ::

Show more
Advertising posts
986Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✅ #ይነበብ ✅      ••••••••••• በተሳፋሪዎች የተሞላዉ አዉቶብስ ጉዞ ላይ ነዉ ወዲያዉ የአካባቢዉ የአየር ሁኔታ ተቀያየረና አስፈሪ የነጎድጓድ ድምፅ የመብረቅ ብልጭታ መታየት ጀመረ፡፡ ተሳፋሪዎቹ አዉቶብሱ ከአሁን አሁን በመብረቅ ተመታ እያሉ መጨነቅ ጀመሩ መብረቁ ግን መኪናዉን እያለፈ ይወድቅ ነበር፡፡ እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ ሁለት ሶስቴ እንደቀጠለ ሾፌሩ አዉቶብሱን ከአንድ ዛፍ ሃምሳ ጫማ ርቀት ሲቀረዉ አቆመና ተሳፋሪወቹን "ከእናንተ መሃል ዛሬ መሞቱ ግዴታ የሆነ ሰዉ አለ ከአሁን በኋላ አብሮን ከተጓዘ በእሱ ምክንያት ሌሎቻችንም አብረን ልንጠፋ እንችላለን። ስለዚህ ሁላችሁም በየተራ እየወጣችሁ ያንን ዛፍ እየነካችሁ እንድትመለሱ እፈልጋለሁ መሞት ያለበት ሰዉ ካለም ዛፉን የነካ ጊዜ በመብረቅ ይመታል ሌሎቻችን ግን እንተርፍለን ማለት ነዉ!!" አለ ሁሉም የመጀመሪያዉን ተሳፋሪ ሄዶ ዛፍን እንዲነካ መጎትጎት ጀመሩ እሱም እየጨነቀዉና በፍርሃት ተዉጦ ሄዶ ዛፍን ነክቶ በሰላም ተመለሰ ምንም ሳይሆን በመመለሱም ልቡ በደስታ ጮቤ ረገጠች፡፡ መጨረሻ ላይ የነበረዉ ተሣፋሪ ተራ እንደደረሰ ሁሉም በበደለኛ(ሟቹ እሱ እንደሆነ በማሠብ) አይኑን እያዩት እንዲሄድ ገፋፉት እሱም በመሞት ፍራቻ ተዉጦ ከአዉቶብሱ ወረደ። ከዛፉ ደርሶ እንደነካዉም ሃይለኛ ድምፅ ተሠማ  አስፈሪ የመብረቅ ብልጭታም ታየ....መብረቁ . . . . ግን የመታዉ አዉቶብሱን ነው። ውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችም ሞቱ፡፡ እነዚያ ቀደም ብሎ አዉቶብሱን ያለፉት አደጋዎች ሁሉ ያለፉትም በመጨረሻዉ ተሣፋሪ ምክንያት ነበር፡፡ አንዳንዴ የስኬቶቻችን ሁሉ አድራጊ ፈጣሪዎች ራሳችን ብቻ እንደሆንን እናስብና ሽልማቱን ለራሣችን ብቻ እንሰጣለን ለዚያ ያበቁን ብዙ ባለዉለታወቻችንን ዘንግተን እኮ ነዉ፡፡   ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ       ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ ╔═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╗ ⭐️  @fanos_books_official ⭐️  ╚═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╝
Show all...
👍 3
ጋዝ ለጠጣ ወተት መስጠት ጎጂ ወይስ ጠቃሚ? ዛሬ በስራ ገበታ ከገጠመኝ ጀባ ልበላችሁ። እናትን ጨምሮ የእናት ጎረቤት የሆኑ በመደናገጥ ስሜት እየሮጡ ይመጣሉ። ምን ሆናቹ ነው ብለን ስንጠይቅ የሁለት አመት ልጅ ነጭ ጋዝ ጠጥቶ ነው አሉን። ወዲያውም ወተት እንደሰጡት ሁለት ጊዜ እንዳስመለሰው ነገሩን። እኔም ካነበብኩት ጀባ ልበላችሁ። ሃይድሮካርቦኖች ሃይድሮጂን እና የካርቦን አተሞችን የያዙ ሰፊ የኬሚካሎች ቡድን ናቸው፡፡  በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ቤንዚን ፣ ኬሮሴን ፣ የመብራት ዘይትና የቤት እቃ ዘይት ሁሉም የሃይድሮካርቦን ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ፔትሮሊየም ወይም ክሩድ ዘይት በተፈጥሮ ከመሬት በታች የሚገኝ የተቀጣጣይነት ጸባይ ያለው ፈሳሽ ነው። የተገነባው ከውስብስብ የሀይድሮካርቦን እና ሌሎች ውህዶች ጥምረት ነው።ከነዚህም የተለያዩ ግልጋሎቶች መካከል ፤ እንደየተጥቃሚው ፍላጎት ፣ከምግብ ማብሰያ ኬሮሲን እስከ መኪና ቤንዚን እና የጭነት መኪና ናፍጣ እንዲሁም የአውሮፕላን ማብረሪያ ልዩ ቤንዚን ፣ የሞተር ዘይትና የፋብሪካ ማሺን ማንቀሳቀሻ ጠቀሜታው ያለው ሲሆን። በተለምዶ ከምናገኛቸው የተጣራ ነዳጅ ዘይት አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፦ጋዞሊን ፥ ዲዝል ጄት ፊዩል፥ አስፋልት እና ፔትሮ ኬሚካል የተጣራ ዘይት ምርት ውጤቶች ወይንም ሪፋይንድ ክሩድ ኦይል መደብ ውስጥ የሚገኙት ውስጥ ፦ ጋዞሊን - ቤንዚን ፥ ሂቲንግ ኦይል - ፥ የማሞቂያ የማብሰያ ጋዝ ፥ ዲዝል - ናፍጣ ፥ ኬሮሲን - የኩራዝ ጋዝ ፥ አውቶሞቢል ሉብሪኬቲንግ ኦይል - የመኪና ሞተር ዘይት ፥ፕሮፔይን - ቡቴን ጋዝ ፥ ፔትሮኬሚካል - ከዘይት የሚገኙና ክተለያዩ የዘይት ዓይነቶርች ጋር ለመቀመሚያና መደባለቂያ የሚያስችሉ የዘይት ክፍሎች ፥ አስፋልት - የመንገድ መስሪያ ሬንጅ በአሜሪካ ውስጥ በየአመቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከሚሆኑት መመረዞች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከስድስት አመት በታች በሆኑ ህፃናት ላይ የሚከሰት ሲሆን፡፡ ከእነዚህ መርዛማዎች ውስጥ ከ55,000 በላይ የሚሆኑት ትናንሽ ልጆች ሃይድሮካርቦኖችን መዋጥ ያካትታሉ ፡፡ አንድ ሰው በአጋጣሚ የሃይድሮካርቦን ምርትን ከጠጣ እና ወደ ሳንባ ውስጥ ከገባ የመተንፈስ ችግር ሊፈጠር ይችላል፡፡ ከከባድ ጉዳት አለፍ ካለም  እስከ ሞት አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሃይድሮካርቦኖች ዘይት ፈሳሾች ናቸው፡፡ ዘይት ያለው ፈሳሽ ወደ ሳንባ ውስጥ ካልገባ በስተቀር ብዙዎች ጎጂ አይደሉም፡፡ ሃይድሮካርቦን ወደ ሳንባ ሲገባ ምልክቶቹ በተለምዶ እንደ ሳል እና / ወይም የትንፋሽ እጥረት ናቸው፡፡ ሃይድሮካርቦን ወደ ወደ ሆድ ሲገባ ብዙውን ጊዜ ከማስገሳት  እስከ ተቅማጥ ማምጣት እንዲሁም የጨጓራ ግድጊዳ መላጥ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ሆኖም ወደ ሳንባዎች ውስጥ ከገባ የሳንባ ምች የመሰለ ሁኔታ ሊያስከትል ይችላል- የማይመለስ ፣ ቋሚ የሳንባ ጉዳት ፣ አልፎ ተርፎም ሞት ሊያስከትል ይችላል፡፡ አንዳንድ ሃይድሮካርቦኖች እራስ መሳት ፣ እራስ ስቶ መንቀጥቀጥ ፣ የተዛባ የልብ ምት ወይም በኩላሊት ወይም በጉበት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ጨምሮ ሌሎች ጉዳቶች ሊያስከትሉ ይችላሉ ፡፡ አደገኛ ሃይድሮካርቦኖችን የያዙ ምርቶች ምሳሌዎች በቀለሞች እና በደረቅ ጽዳት እና በቤት ውስጥ ማጽዳት ኬሚካሎች ውስጥ የሚያገለግሉ አንዳንድ ፈሳሾችን ያካትታሉ፡፡ ብዙ የሃይድሮካርቦን ምርቶች ልጅን የሚቋቋም ማሸጊያ የላቸውም፡፡ ይህ ልጆች ሊጠጧቸው የሚችሉትን አደጋ ከፍ ያደርገዋል። እ.ኤ.አ. በ2002 የዩኤስ የሸማቾች ምርት ደህንነት ኮሚሽን (ሲፒሲሲ) አሥር በመቶ ወይም ከዚያ በላይ ሃይድሮካርቦኖችን በያዙ ምርቶች ላይ ሕፃናትን የማይቋቋሙ ማሸጊያዎች እንዲቀመጡ አፀደቀ ፡፡ አዲስ የማሸጊያ መስፈርቶች ኩባንያዎች አሥራ ሁለት ወራትን ማሸጊያቸውን እንዲለውጡ ያስችላቸዋል ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ምርቶች ያለ ልጅ-ተከላካይ እሽግ በቤታችን ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሃይድሮካርቦን የያዙ ምርቶች አንዳንድ ምሳሌዎች- ይህ የሃይድሮካርቦን ምርቶች በከፊል ዝርዝር ነው። መዋቢያዎች - የሕፃን ፣ የፀጉር እና የመታጠቢያ ዘይቶች; የፀሐይ መከላከያ; የጥፍር ኢሜል ማድረቂያዎች እና የመዋቢያ ማስወገጃዎች። የጽዳት ምርቶች - ማጽጃዎች (ለምሳሌ-የእንጨት ዘይት ፣ ብረት ፣ ማጣበቂያ እና ጥድ) ፣ የቦታ ማስወገጃ እና የፈሳሽ የቤት ውስጥ እቃዎች ፡፡ አውቶሞቲቭ - ቤንዚን ፣ ኬሮሴን ፣ ቤንዚን ተጨማሪዎች ፣ የነዳጅ መርፌ ማጽጃዎች እና የካርበሬተር ማጽጃዎች፡፡ በምልክት ህመምተኛው ውስጥ የሃይድሮካርቦን መጋለጥ በተለምዶ ሶስት መንገዶች ይከሰታል፡፡ በመጀመሪያ ፣ ሳያስበው የቤት ውስጥ ምርቶችን በልጆች መመገብ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ፣ የቆዳ ወይም እስትንፋስ የሙያ መጋለጥ፡፡ በመጨረሻም ፣ በጉርምስና ዕድሜዎች እና ጎልማሶች ሆን ተብሎ የሃይድሮካርቦኖችን ለመዝነኛነት በሚጠቀሙ ጊዜ፡፡ ድንገተኛ ሁኔታ ሲከሰት ምን ማድረግ አለብዎት? - ማስታወክን አያስገድዱ. - ለተጠቂው ወተት አይስጡ ምክንያቱም በሚያስመልስበት ጊዜ ተጨማሪ ሃይድሮካርቦን ወደ ሳንባ ገብቶ የከፋ ጉዳት ስለሚያስከትል እራሱን ለሳተ ተጎጂ ምንም ፈሳሽ  በአፋ አይስጡ ፡፡ - ሁኔታውን እራስዎ ለማስተካከል አይሞክሩ ፡፡ መጀመሪያ ሁል ጊዜ ለእርዳታ ይደውሉ ወይም ወደ እክምና ተቋም ይውሰዱ፡፡ የሃይድሮካርቦኖች መመረዝ ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች ልጆችን ገና በልጅነታቸው ስለ መርዝ ያስተምሯቸው፡፡ ምርቶችን በምግብ ወይም በመጠጥ መያዣዎች ውስጥ ሳይሆን በመነሻ መያዣዎች ውስጥ ያቆዩ፡፡ (እንደ ቤንዚን እና የመብራት ዘይቶች ያሉ ምርቶች በጋራጅ ወይም በክምችት ስፍራዎች ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ መያዣዎች ውጭ ባሉ ጠርሙሶች ውስጥ በብዛት ይገኛሉ) ከተጠቀሙ በኋላ ወዲያውኑ ምርቶችን ያስቀምጡ፡፡ የፅዳት ሰራተኞችን ፣ ቀለሞችን ፣ ፀረ-ተባዮችን እና ሌሎች አደገኛ ምርቶችን ከህፃናት በማይደርሱበት እና በተዘጋ ካቢኔ ውስጥ ያከማቹ፡፡ የመርዝ መቆጣጠሪያ ማዕከል ቁጥር በስልኩ ላይ ወይም በአጠገብ ይለጥፉ፡፡ ምልክቶች እስኪከሰቱ ድረስ አይጠብቁ፡፡ ጥሩ መመሪያ; አንድ ሰው አንድ ነገር ከጠጣ እና መርዛማ መሆኑን እርግጠኛ ካልሆኑ; ወዲያውኑ ወደ መርዝ ማእከል ይደውሉ ወይም ህክምና ማህከል ይዉሰዱ። አንባቢዎቼ መልዕክቴም ወደ ብዙዎች ትደርስ ዘንድ … እንድታቋድሷት (ሼር እና ላይክ እንድታደርጓት) በትህትና እጠይቃለሁ፡፡ ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤ የህፃናት ሐኪም ©HakimEthio @fanos_books_official
Show all...
#Frustration / #ተስፋ_መቁረጥ ከየት_ይመጣል ? ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች ሁነው ተስፋ የለኝም ፣ ተስፋዬ ተሟጧል ፣ የመሳሰሉትን ቃላት በቀን ተቀን ሕይወታቸው ይጠቀማሉ ፡፡ ተስፋ መቁረጥ ወደ ግባችን / ፍላጎቶቻችን እንዳንደርስ የሚያረገን ባህሪ ነው ፡፡ በሕይወቱ ብዙ ጊዜ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ወደግቡ/እቅዱ የመድረሱ እድል በጣም አነስተኛ ነው ፡፡ ወደ ጠቃሚ የሕይወት ግባችን አለመድረስ ደግሞ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃት ፣ የበደለኝነት ስሜት ያመጣብናል ፡፡ ሳይኮሎጂ ችግር የመፍቻ ዋና መንገዱ የችግሩን ምክንያት መረዳት እንደሆነ ያትታል ፡፡ስለሆነም የተስፋ መቁረጥ ዋና ዋና ምክንያቶች እንመለከታለን፡፡ ___ 1.Environmental Factor (አካባቢያዊ ምክንያት) በአካባቢያችን ያሉ የተለያዩ ሁኔታዎችና ገጠመኞች ፍላጎቶቻችንንና እቅዳችንን እንዳናሳካ ይከለክሉናል ፡፡ ለምሳሌ ፦ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ማድረግ የምንፈልገውን ነገሮች " አትችለውም ፣ ይከብድሀል ፣ ከዚህ በፊት አልተሞከረም ፣ ሰው ምን ይልሀል" በማለት ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ ፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ያደግንበት ባህል ፣ የምንኖርበት አካባቢ ለማድረግ ያቀድነውን ነገር እንዳናሳካ በራሱ ሊይዘን ይችላል ፡፡ ይሄ በሕይወታችን ተስፋ መቁረጥን ያስከትላል ፡፡ 2.Personal inadequency Factor (ግላዊ ብቃት/ክህሎት ማጠር ) ይህ ደግሞ ፍላጎቶቻችንን እንዳናደርግ የሚገድበን አለመሙላት (ብቃት አልባነት) ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ አንድን እቃ በጣም ወደነው ለመግዛት ስንፈልግ ከተወደደብንና ያለን ገንዘብ አነስተኛ ከሆነ ተስፋ ቆርጠን ላንገዛ እንችላለን ፡፡ እዚህ ጋር ነገሩን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አለመኖር የራሳችን የሆነ ጉድለት ይሆናል፡፡ ሌላው አንድን ነገር ለመስራት አስበን የግል ችሎታ / ብቃት/ ክህሎት ሲያንሰን እሱ " በቃ አልችልም " በማለት ተስፋ ለመቁረጥ መንስኤ ይሆነናል ፡፡ 3. Conflict of interest ( የፍላጎት ግጭት ) የመጨረሻው የግላዊ ፍላጎቶች/ ግቦች እርስ በእርስ ሲፃረሩ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይችላል ፡፡ ተስፋ መቁረጡ የሚመጣዎ ሁለቱንም ግቦቻችንን ልናሳካ ባለመቻላችን ነው ፡፡ አንዱን ግብ ብናሳካ ራሱ ሌላውን ስላላሳካን የመወላወል ተስፋ የመቁረጥ ( የማዘን ) ስሜት ይሰማናል፡፡ ከነዚህ ሶስቱ ዎና ዎና ምክንያቶች እግጅ በጣም ብዙ ሰው የሚያጋጥመው የመጨረሻው (.Conflict of Motives / የፍላጎት ግጭት ) እንደሆነ ሳይኮሎጂ ይጠቁማል፡፡ __ እነዚህ Conflict of motives ( የፍላጎት ግጭት ) ደግሞ በ አራት ይከፈላሉ ፡፡ __ ሀ. Approach - Approach Conflict (ፍላጎት ፥ ፍላጎት ግጭት) ይህ ግጭት ሁለት ነገሮችን በእኩል ፈልገን ነገር ግን መምረጥ የምንችለው አንዱን ብቻ ሲሆን ማለት ነው ፡፡ ለምሳሌ :- ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኅላ Department ሲመርጡ ብዙ ተማሪዎች በሁለት ወይም ከዛ በላይ በሆኑ የdepartment ምርጫዎች ይወጠራሉ ነገር ግን መምረጥ የሚችሉት የወደዱትን ሁሉ ሳይሆን አንዱን ብቻ ስለሚሆን ግጭት ውስጥ ይገባሉ ፡፡ ሌላው ገበያ ሂደን ሁለት ሱሪዎች በጣም ወደናቸው ነገር ግን መግዛት የምንችለው አንዱን ብቻ ከሆነ ይህ አይነት ግጭት ከራሳችን ጋር ይገጥመናል፡፡ ለ. Avoidance - Avoidance Conflict (የማስወገድ ፥ የማስወገድ ግጭት) ይህ ደግሞ ከሁለት የማንፈልጋቸው ነገሮች የግድ አንዱን መምረጥ ግድ ሲለን ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ ልጃችን በሰዎች ታግቶ ብር ካልከፈላችሁ ይገደላል ቢሉን ፤ እዚህ ጋር ልጁ እንዲሞትም አንፈልግም ለአጋቾቹ ብር መክፈልም አንፈልግም ፡፡ ግን አንዱን መምረጥ ግድ ይለናል ፡፡ ሌላ ምሳሌ ፦ ሐ. Approach - Avoidance Conflict (የፍላጎትና ማስወገድ ግጭት) ይህ ደግሞ በአንድ ግብ ላይ የፍላጎትም የማስወገድም ስሜት ሲሰማን ነው ፡፡ መ. Multiple Approach - Avoidance Conflict (ብዙ የፍላጎት ማስወገድ ግጭት) ይህ ሁላችንም በሕይወት ቆይታችን የሚያጋጥመን የለት ተለት ግጭት ነው ፡፡ እያንዳንዱ የሚገጥመን ነገር #ብዙ_አወንታዊና_አሉታዊ ነገሮች ይይዝና እሱን #መምረጥና #አለመምረጥ ችግር ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው መልኩን ፣ ገቢውን ወደን ፀባዩ አመለካከቱ ካላማረን ይሆነኛል አይሆነኝም ብለን ከራሳችን እንጋጫለን ፡፡ሌላው አንድን ስራ ስንሰራ በዉስጡ ያሉ የተለያዩ ጥሩና መጥፎ ነገሮች ስገፉን ሲስቡን እንደዚህ አይነት ግጭት ውስጥ እንገባለን ፡፡ ______ ©Psychoet 👍 @fanos_books_official!
Show all...
👍 1
ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ መጨነቅን ለማቆም ቀላል ዘዴዎች ‘’የማይባል ነገር ተናገርሁ እንዴ? እንዴት እንደዚህ አደርጋለሁ? ሰዎች እኮ መሃይም :ገገማ:የሚያናድድ ሰው ነው/ነች ይሉኝ ይሆናል’’  እያልን ራሳችንን የምናስጨንቅ ስንቶቻችን ነን! ሌሎች ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ በመጨነቅ አእምሯችንን በጨለማ ቦታ እንዲንከራተትና ራሳችንን በመጠራጠር የስጋት ስሜት እንዲሰፍንብንና እንዳንረጋጋ እያደረግን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: ለነገሩ ሁላችንም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው ሃሳብ/አስተያየት ምን ይሆን ብለን መጨነቅ እንደሌለብን እናውቃለን ወደ ተግባር ለመቀየር  ግን ስንቸገር እንታያለን:: ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ብንጠቀምባቸው ይረዱናል! 1. የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ እንደማንችል መረዳት፡- እስኪ ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡትን በእርግጠኛነት ማወቅ እንችላለን? ብዙ ጊዜ ነገራትን ሳናጣራ ይሆናል በማለት ብቻ ማወቅ እንደምንችል ነው የምናስበው ይህ አስተሳሰባችን ደግሞ ለህይወታችን ፀር ወደሆኑ ድምዳሜዎች/ዉሳኔዎች ይመራናል::ስለዚህ እነዛ ሰዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበትን ዕድል አግኝተው ሃሳባቸውን እስካልገለጹልን ድረስ ስለምን እንደሚያስቡ ማወቅ በፍጹም አንችልም፡፡ 2. በቋሚነት ለሚጠቅመን ነገር መስራት:- ከሌሎች  ሰዎች የሚሰነዘሩ  የኩነኔ አስተያየቶች በእርግጥም እኛን ይጎዱናል ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች የሚመጣውን አሉታዊ ምላሽ በመፍራት የምናጣቸው/የምናሳልፋቸው መልካም ዕድሎች ጥለውብን ከሚያልፉት የአእምሮ ጠባሳ አይበልጥም፡፡ እነዚህ የኩነኔ/አሉታዊ አስተያየቶች የሚያደርሱብን ጉዳት ቅጽበታዊ ሲሆን ባጣናቸው/ባመለጡን መልካም ዕድሎች ምክንያት የሚደርስብን ጸጸትና ቁጭት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደና እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ በቋሚነት የሚጠቅመንን ነገር ለማግኘት ጊዜያዊ የሆኑ ተቀባይነት ማጣትን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሁን:: 3. ራስን ከመኮነን/በራስ ላይ ከመፍረድ መቆጠብ:- እስኪ ሰዎች ምን ይሉን ይሆን ብለን የምንጨነቅበትን ሃሳብ ለሰከንድ ቆም ብለን እናስበው! በእርግጠኝነት እኛ ለራሳችን የምናስበውን ነገር ላይ ነው ሌሎችም እንደዚ ያስባሉ ብለን የምንሰጋ፡፡ ስለዚህ በራሳችን ላይ መፍረድን አቁመን(ራስን ከመኮነን ተቆጥበን) እኛነታችንን ከተቀብለነው ወይም ለራሳችን ጥሩ ግምት ከሰጠን ሌሎቹ ስለእኛ ለሚሰጡት/ለሚያስቡት ሃሳብ ፍርሃትና ስጋት አይኖረንም ማለት ነው፡፡ 4. ሌሎች ሰዎችን መኮነንን/በሌሎች ላይ መፍረድን ማቆም፡- ሰዎችን እየገመገምን፡እየኮነንና እየፈረድንባቸው የምንኖር ከሆነ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈርዱብን ነው የምናስበው፤ ስለዚህ በእነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ህይወታችንን ለማሻሻልና ለማደራጀት እንደሚያግዙን ቆጥረን ብናደንቃቸውና ብናበረታታቸው የበለጠ ተጠቃሚዎች መሆን እንችላለን፡፡ 5. ስለእኛ አለመሆኑን መረዳት፡- ሰዎች በራሳቸው እይታ ከደረሰባቸው ክስተት፡ ቁስል፡ ፍራቻና እንከን የተነሳ ለነገሮች የተለያዩ አሉታዊ ምላሾችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነሱ ምላሽ ከእኛ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡ ለምሳሌ የሆነ ቢዝነስ ለመጀመር ብንወስንና አንድ ሰው ”እመነኝ ይህንን ስራ ከጀመርህ በሚቀጥሉት ወራት አሊያም ዓመታት ምንም  ዓይነት የእረፍት ጊዜ አይኖርህም” ቢል ሰውዬው የተናገረው ቢዝነስ መጀመር ላይ ያለውን ሃሳብ/አመለካከት እንጂ እኛን በተመለከተ እንዳልሆነ ለይተን መረዳት ይጠበቅብናል:: 6. በሚያስደስተን ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ:- ይህን ባደርግ ሰዎች ይፈርዱብኛል በማለት የሚያስደስቱንን ተግባራት ከማድረግ የምንገደብ ከሆነ(የማኅበረሰቡን እሴቶች በጠበቀ መልኩ) ጊዜያችንን ምንም ዓይነት ጥቅም በሌለው ጭንቀት እያባከንነው መሆኑን እናስተውል፡፡ ስለዚህ በህይወታችን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ብርቅ የሆነውን አቅምና ኃይላችንን በመሸርሸር ፈንታ እኛን በሚያስደስቱን ነገራት ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡ 7. የሚያውኩንን ነገሮች መለየት፡– ሌሎች ሰዎች አሉታዊ በሆነ መልኩ ይገመግሙናል/ይፈርዱብናል ብለን የምንጨነቀው ምናችንን በተመለከተ ነው? በስራችን ሁኔታ: ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት: ምናልባትም በክህሎታችንና ነገሮችን በመመርመር ባለን አቅም ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በውስጣችን መረጋጋት እንዳይኖር የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መለየትና ማሻሻል ከቻልን ማሻሻል አሊያም እንዳሉ መቀበል ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከሁኔታዎች ጋር ሰላም መፍጠር ከቻልን የሰዎች አጸፋዊ ምላሽ አያስጨንቀንም ማለት ነው:: 8. ራሳችንን መቀበል:– ፍጹም አለመሆናችንን፡ እንከንና ድክመቶች እንዳሉን መቀበል ነገር ግን አቻ የሌለን(ልዩ) በዓለም ላይ እኛን የሚመስል ሰብዕናና ተሰጥኦ የታደለ ሰው እንደሌለና ወደፊትም እንደማይኖር ልናስተውል ይገባል፡፡ 9. አጸፋዊ ምላሾችን መጠበቅ/ተስፋ ማድረግ፡- በሰዎች ዘንድ የሚፈጠረውን አጸፋዊ መልስ በመፍራት ፈንታ ያ ምላሽ ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድመን ተስፋ ማድረግ አለብን(የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ መፍራት የለብንም) ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽ መፍጠር ካልቻልን ምናልባትም ራሳችንን የመሆን ድፍረቱን ልናጣ እንችላለንና፡፡ 10. እየኮነኑን/እየፈረዱብን ነው ብለን ካሰብናቸው ሰዎች ጋር ማውራት፡- እንዲያው ሁኔታዎች ተመቻችተውልን ስለእኛ መጥፎነት ያስባሉ/እየፈረዱብን ነው ብለን ከምናስባቸው ሰዎቸ ጋር ተቀራርበን ብናወራ እስከምንገረም ድረስ ምንም ባለጠበቅነው ሁኔታ አዕምሯቸው በብዙ ጭንቀቶች እንደተሞላ ልናውቅ እንችላለን፡፡ ማን ያውቃል ልክ እኛ እንደምንጨነቀው እነሱም ሌሎች ሰዎች ስለእነሱ ምን ሊያስቡ/ሊሉ በሚችሉት ሃሳብ እየተጨነቁ ሊሆን ይችላል እኮ፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ግልጽ በማድረግ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተቀራርበን ሃሳብ ማንሸራሸር ያስፈልጋል:: በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባረ ከቀየርናቸው እኛም መቀየር እንችላለን! ©Zepsychologist   ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ       ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ ╔═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╗ ⭐️  @fanos_books_official ⭐️  ╚═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╝
Show all...
👍 1 1
ለፈገግታ😂 «ስንት ተምች ሰው አለ መሰለህ¡ አንዱ ገጠሬ ነው አሉ። ህዝቦቹ ተሰብስበው አንድ ትምህርት ሊሆነን ሚችል ነገር ንገረን አሉት። ከዛም መድረክ ላይ ወጥቶ እንዲህ አላቸው👇 √ "እናንተ ሰዎች ሆይ! ስለ ምን እንደ ምነግራችሁ ታውቃላችሁ ኣ❓" ሲላቸው "አናውቅም" አሉት። "እንግዲያውስ ለማያውቁ ሰዎች ማስተማር ድካም ነው።" ብሎ ወረደ! በሌላም ቀን መጥተው "እሺ ዛሬ አስተምረን" አሉት። አሁንም መድረክ ላይ ወጥቶ √ "እናንተ ሰዎች ሆይ! ስለ ምን እንደ ምነግራችሁ ታውቃላችሁ ኣ❓" ሲላቸው በአንድ ድምፅ "አዎን! እናውቃለን" አሉት። "እንግዲያውስ ለሚያውቅ ሰው መናገር ፋይዳ የለውም።" ብሎ ወረደ። ለሶስተኛ ጊዜ መጥተው "እባክህ አስተምረን" አሉት። አሁንም መድረክ ላይ ወጥቶ √ "እናንተ ሰዎች ሆይ! ስለ ምን እንደ ምነግራችሁ ታውቃላችሁ ኣ❓" ሲላቸው ቀድመው ተወያይተው ነበርና ግማሻቸው "አዎን" ሲሉ ግማሻቸው "አናውቅም" አሉ። "እንግዲያውስ ያወቁት ለማያቁት ያሳውቁ!" ብሏቸው እርፍ!!»😂😂 ♥✦_ ፍቅር _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ       ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ ╔═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╗  ⭐️  @fanos_books_official⭐️  ╚═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╝
Show all...
🏝「 ወ ዳ ጄ  ሆ ይ! 」🩶 ▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭ ✅:ዱንያ ላይ ከመሥራትና ከመበርታት ውጭ አማራጭ የለህም። የሚያበረታታህ ብታጣ እንኳን ራስህን አበርታ። ለራስህ ነዳጅ ሁን፤ ራስህን ግፋ፤ ራስህን ሸልም። ሌላውን እንደምትመክረው ሁሉ ራስህንም ምከር -ጎበዝ! በርታ! በል ራስህን።  የሆነ ነገር ጀምረህ ሰዎች አይሳካልህም ቢሉህ እንኳ ያ የራሳቸው ፣ የግላቸው አስተያየታቸው መሆኑን አስብ። እነርሱ የራሳቸው አስተያየት እንዳላቸው ሁሉ አንተም የራስህ አቋም ይኑርህ። ያ አቋምህ የነርሱ አመለካከት ተቃራኒ መሆን አለበት። ንግግራቸውን መስማት የለብህም። መስሚያህን ጥጥ አርገው። ንግግራቸውን ሰማህ ማለት ምኞታቸውን አሳካህ ፣ ፍላጎታቸውን አሟላህ ፣  ለስንፍና እጅ ሠጠህ… ማለት ነው። አስተያየታቸውን ወደ ሕይወትህ አታምጣ ፤  ራስህን አታወናብድ ፣ ራስህን አታወዛግብ። 🔱:ትክክል ከሆነና ራስህ ካላመንክበት በስተቀር በሰዎች አስተያየት መንገድህን #አታቋርጥ። ከአሉታዊ ሃሳባቸው ከፍ በል ፤ ከፍ ብለህም ብረር። መብረሪያ ክንፍህን እንዲቆርጡ ፣ ወደታች እንዲጎትቱህ ዕድል አትስጣቸው። ሃሳባቸውን ካላነሳህ ፣ ንግግራቸውን ካልሰማህ ፣ አስተያየታቸውን ካላዳመጥክ ይሳካልሃል። ማንም ቢናገርህ ፣ ቢያሸማቅቅህና ቢስቅብህ እጅ አትስጥ። ይሳካልኛል በላቸውና ያለድካም ተጓዝ። ትክክለኛው መስመር ላይ እያለህ ተው አይሳካልህም ቢሉህ “አልተውም ፤ ያ የናንተ አስተያየት እንጂ የኔ አቋም አይደለም” በላቸው። 📙 ~~> 📝 ┊  ┊  ┊  ┊ ┊  ┊  ┊  ✿ ┊┊  ❀ 📘 ┊  ✿ 📌 ❀ ✨                                ╠══════╣╔━━━━⎙ ┣@fanos_books_official       ┣━✨━━╗ 📘 ╔━━━━⎙ ╠════•❁❀❁•════╣
Show all...
አይ የሴት ተንኮል 😁😁😁 ባሏ የሞተባት አንዲት ሴት በጥሩ ይዞታ ላይ ያለ ማርቼዲስ መኪና በአንድ ዶላር ብቻ ለሽያጭ ታቀርባለች። ታዲያ ማስታወቂያውን ያየ ሁሉ በዚህ ዋጋ መሆኑ የቀልድ ስለመሰለው ማንም ሊገዛ የመጣ አልነበረም። አንድ በእድሜ ገፋ ያሉ አዛውንት በስልኳ በመደወል መኪናውን ለማየት ይሄዳል እንደተባለው መኪናው በጥሩ ሁኔታ ያለ መሆኑ ይበልጥ ሲመለከት ተገረመ የመጨረሻ ዋጋውን ንገሪኛ  ዋጋው አንድ ዶላር እንደሆነ ደገመችለት። አንድ ዶላሩን ሰጣት ቁልፉን ተቀበለ በነገሩ በጣም የተገረመው ሽማግሌ ምክንቱን ለማወቅ ጓጓ  ለመሆኑ ለምንድነው በዚህ ዋጋ ምትሸጪው?? ባሌ ከኔ ሌላ ሚስት ነበረው ፀሀፊው እንደነበረች አውቂያለሁ እና ባሌ ከመሞቱ በፊት መኪናው ተሸጦ ብሩ ለሷ እንዲሰጥ ተናዟል የባሌን ኑዛዜ እየሞላሁ ነው አለችው😂😂😂😂 ♥✦_ ፍቅር _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ       ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ ╔═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╗ ⭐️  @fanos_books_official ⭐️  ╚═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╝
Show all...
📍በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።   📍መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል።  ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። በአጋጣሚ ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።   📍ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል። 💎ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም። ሁሉንም ክብርና ምስጋና የፈጠረን ይውሰድ።                             📖አርምሞ 🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ ፍቅር _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ       ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ ╔═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╗       @fanos_books_official ╚═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╝
Show all...
አንድ ቀን መምህሩ ወደ ማስተማሪያ ክፍሉ ከገባ በሁዋላ ተማሪዎቹን ለድንገተኛ ፈተና እንዲዘጋጁ ይነግራቸዋል። ተማሪዎቹ ያልጠበቁት ፈተና ስለሆነ በጭንቀት ጥያቄውን ይጠባበቁ ጀመር። መምህሩ፣ ጥያቄ የሰፈረባቸውን ወረቀቶች ለተማሪዎቹ በጠረጴዛ በጠረጴዛቸው ላይ አስቀመጠላቸው። ከዚያ ወረቀቱን ለሁሉም ተማሪዎች ካዳረሰ በሁዋላ፤ ‹‹አሁን መጀመር ትችላላችሁ›› አላቸው። ሁሉም እየተጣደፉ ወረቀቱን ገልብጠው ሲያዩት አንድም ጥያቄ የለም። ደነገጡ። ከዚያ ልብ ብለው ሲያጤኑ ወረቀቱ መሐል ላይ አንዲት ጥቁር ነጥብ አለች… ከእሷ ውጭ ሌላ ነገር የለም። ዞር ዞር እያሉ እርስ በእርስ ተያዩ። መምህሩ ይሄን ግዜ እንዲህ አላቸው። ‹‹ወረቀቱን ስታዩ እንደተደነቃችሁ እያስተዋልኩ ነው። በሉ ያያችሁትን ጻፉ… ፈተናው ምን እንዳያችሁ በትክክሉ መጻፍ ነው።›› ተማሪዎቹ በድጋሚ ተያዩና ወደ ወረቀቱ አቀርቅረው የመሰላቸውን መሞነጫጨር ጀመሩ። ለፈተናው የተመደበው ጊዜ አለቀና ወረቀቱ ሁሉ ተሰበሰበ። ከዚያ መምህሩ እያንዳንዱን ወረቀት እያነሳ ተማሪዎች የሰጡትን መልስ ጮክ ብሎ ያነብላቸው ጀመር። የሚደንቀው ነገር ሁሉም ተማሪዎች ለማብራራት ሲጣጣሩ የነበረው ስለዚያች ጥቁር ነጥብ እንጂ ስለሌላ ነገር አልነበረም። ነጥቧን በተመለከተ እያንዳንዳቸው፥ ስለ ጥቁረቷ፣ ስላለችበት ቦታ፣ ስለ ግዝፈቷ፣ ስለሌላም ሌላም ጥቁሯን ነጥብ ስለተመለከቱ ጉዳዮች ትንታኔዎችን አቅርበዋል። መምህሩ አንብቦ ሲጨርስ ዐይኑን መለስ ቀለስ እያደረገ የተማሪዎቹን ፊት ሲያስተውል ቆየ። ከዚያም ‹‹ተማሪዎች አንዳችሁም ትክክለኛ መልስ አልሰጣችሁም። ስለዚህ ይሄን ፈተና ውጤት አልሰጥበትም። ነገር ግን አንድ ነገር ላስተምራችሁ እፈልጋለሁ›› አላቸው። ሁሉም ተማሪ መምህሩ የሚናገረውን ለመስማት ጓጉተው መጠበቅ ጀመሩ። መምህሩም ንግግሩ ቀጠለ። ‹‹ከመካከላችሁ አንዳችሁም ስለነጩ ወረቀት አልጻፋችሁም። ሁላችሁም ትንሽዬዋን ነጥብ ዐይታችሁ፥ ትልቁንና ሰፊውን ወረቀት እስከናካቴው ረሳችሁት። በሕይወታችሁም ላይ አንዲት እንከን ስታገኙ በዚህ መልኩ ያላችሁን ጸጋ ሁሉ ጠቅልላችሁ የምትረሱ ከሆነ በጣም ትጎዳላችሁ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ መልካም ስጦታዎች እያላችሁ ስለ አንዲቷ እንከን አብዝታችሁ የምታስቡ ከሆነ እውነቴን ነው የትም አትደርሱም፤ ቆሻሻ ውስጥ ትቀራላችሁ። የገንዘብ ማጣቱ አስጨንቋችሁ ታማርሩ ይሆናል፤ ነገር ግን ከገንዘብ የበለጠ ጥሩ ፍቅር፣ ጥሩ ጤና፣ ጥሩ ሰላም፣ ጥሩ ቤተሰብ ወዘተ ካላችሁ ዓለም ላይ ተዓምር መሥራት ትችላላሁ። ስኬታማ ሕይወት ለመምራት ዋናው ነገር ያላችሁ ዐቅም ስፋት ላይ ማተኮር ስትችሉ እንጂ የጎደላችሁ ኢምንት ነገር ላይ ስታተኩሩ አይደለም። እንዲህ ማሰብ ከጀመራችሁ ያለጥርጥር እንደ እናንተ ደስተኛ ሰው አይኖርም። በተቃራኒው ጉድለት ብቻ ተመልካች ከሆናችሁ ምንም ብታገኙ እርካታ የሚባል አይኖራችሁ።››              እንግዳውስ አመስጋኝ ባሪያ እንሁን 🙏🙏🙏 🪴✨🌹ከወደዱት አጋሩ🌹✨         ♥✦_ ፍቅር _✦♥       ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲                   ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ       ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ ╔═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╗ @fanos_books_official ╚═════✩˚⋆★⋆˚✩═════╝
Show all...
ም ክ ን ያ ት ══✦══ "አዎ ልክ ነህ፤         ድንጉጥ ነኝ። ዐውቃለሁ፤         ፈሪ ነኝ፤ ምክንያቱም ልጅ አለኝ"         አልኩት። እሱ ግን፣         እየሳቀ ነገረኝ፤ "አትሳሳት፣      ልጅ ስለወለድክ አይደለም           ፈሪ የሆንከው፤ ፈሪ ስለሆንክ ነው      ልጅ የወለድከው።" ═══════ 📔 አርነት የወጡ ሐሳቦች 🗓 2003 ዓ.ም. 📖 📖 📖 📖 📖
Show all...