cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Zena Tube ዜና ቲዩብ🇪🇹🇪🇹🇹🇷💯

አለምላይ ያለው እውነታ ይሔነው hi የ channale ተከታታዮች ✋ ይህ የናንተው የሆነ ከየአቅጣጫው የሚለቀቁ ዜናዎችን ያቀርብላችኋል 😘 #እናም በ channalu ላይ ያላችሁን ማንኛውም ሀሳብና አስተያየት በዚህ ላኩልን 👉👉👉👉 @Mame_Salah

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
651Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰበር ዜና‼️ #Ethiopia : የአፋር ክልል ልዩ ሀይልና ሚኒሻዎች በአብአላ በኩል ወደ ትግራይ ክልል ዘልቆ በመግባት 4 የትግራይ ከተማዎችን መቆጣጠራቸው ተነገረ ይህ በኢንዲህ እንዳለ በአሁን ሰአትም ከመቀሌ በ30ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኘውና ለመቀሌና ለጁንታው ሀይል ቁልፍና እስትራቴጂክ ከተማ የሆነችውን ምላዛት የምትባል ከተማን በአፋር ሀይሎች ቁጥጥር ስር መሆኖ ተረጋግጦል፡፡
Show all...
"የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከ አብዬ_ግዛት መውጣታቸውን እንደማትቀበል ደቡብ ሱዳን አስታወቀች" በሚል ዜና "Sudans Post"  ያወጣው ዘገባ ሀሰተኛ መሆኑን በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒ ሞርጋን ገልፀዋል። አምባሳደሩ ይህንን ያሳወቁት ለኢትዮጵያ ቼክ የመረጃ አጣሪ ድረገፅ ነው። ከዚሁ  "SUDAN POST"  ዘገባ ጋር በተያያዘ ፣ ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪዎች ከአብይ ግዛት መውጣታቸውን እንደማትቀበል አስታወቀች ብለን መዘገባችን ይታወሳል ። ነገር ግን አምባሳደሩ   " SUDAN POST " የተባለው ድረገፅ ሁልግዜ ሀሰተኛ መረጃ  ነው ፤ እንደዚህ አይነት ነገር አልተባለም" ብለዋል። @zena_tubee
Show all...
ጌታቸው ረዳ በግብፅ ሚዲያ ላይ እንግዳው ሆኖ ቀርቧል። ሚዲያው የፕሬዝዳንት ሲሲ ሚዲያ ነው። ያቋቋመው እሱ ነው። እዚህ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ሰዎች እንግዳ ሆነው የሚቀርቡ ሰዎች በግብፅ የደህንነት መስሪያ ቤት እውቅናና ተልዕኮ ነው። በዚህ ሚዲያ ላይ ማንኛውም የፖለቲካ ሰው ወይም የኔ ቢጤ ቀርቦ ትንታኔ አይሰጠም። ሚዲያው የፕሬዝዳንት ሲሲ ትልቁ ተወንጫፊ ሚሳኤሉና የተልዕኮ ማስፈፀሚያ መሳሪያው ነው። . ጌታቸው በዚህ ሚዲያ ላይ እንዴት ቀረበ ብሎ መጠየቅ አያስፈልግም። ከላይ እንዳልኳችሁ በዚህ ሚዲያ ላይ የሚቀርቡ ሰዎችን የሚመርጠው፤ እውቅናና ፍቃድ የሚሰጠው የግብፅ የደህንነት መስሪያቤት ነው። ጌቾን በቀላሉ ወደዛ ያስገቧትም ደህንነቶ ናቸው። ወያኔና ግብፅ ምን ያህል ፍቅር ላይ እንዳሉ ከዚህ በላይ ሌላ ማስረጃ የለም። ጌታቸው ከጋዜጠኛው የቀረበለትን ጥያቄ በሚገባ መልሷል። ተዋግተን አዲስ አበባ ከገባን በህዝብና በክልሉ መንግስት ድምፅ መሰረት ትግራ የምትባል አገር እንመሰርታለን ብሏል። እኛ ብቻ ሳንሆን ኦሮሞውም ጉምዙም ሶማሌውም ጋቤላውም አገር መሆን ይፈልጋል ለዚህም አሁን ተጣምረን እየተዋጋን ነው። አሁን በኢትዩጵያ ላይ ጦርነት የተከፈተው በትግራይ አቅጣጫ ብቻ አይደለም በኦሮሚያም ቤንሻንጉልም በሶማሌ ክልልም በጋምቤላም በኩልም ነው። እኛም ከነሱ ጋር አብረን እየሰራን ነው በቅርቡ የአብይ አሕመድን መግንሥት በውጊያው እናሸንፋለን፤ ይሄንንም ማሳካት የሚያስችሉ ስራዎች ተሰርተው እየተጠናቀቁ ነው ትንሽ ነው የቀረን ብሏል። . ጋዜጠኛው ዋና ዋና ጥያቄዎችን ያደረገው የህወሓትን የወደፊት እቅድ ምንም እንደሆነ መለየት ላይ ነበር። እሱንም አለሳልሶ ጠይቆ ከጌታቸው ረዳ በቂ መልስ አግኜቷል። ተዋግተን ካሸነፍን ህዝብና የትግራይ መንግስት ተመካክረው አገር እንሆናለን እኛም ብቻ ሳንሆን ኦሮሞ ጉምዝ ሱማሌ ጋቤላው ከኛ ጋር ተመሳሳይ ፍላገት ኖሮት አብሮን እየሰራ ነው ብሎ ለጋዜጣጠኛው ጥያቄ ተጊቢውን መልስ ሰቶታል። በርግጥ ጌታቸው በግብፅ መንግስት ሚዲያ ላይ የቀረበው እንዲሁ አይደለም። ሰዎቹ አብረው በጋራ አገሪቱን ለማፍረስ እየሰሩ ስለሆነ ምን ያህል የጋራ አላማ ቢኖሯቸውም ነው እንዲህ በዚህ በተመረጠ ሚዲያ ላይ ቀርቦ እንግዳ የሆነው ማለትም አያስፈልግም። ህወሓት አሁን ላይ የሚያደርገው ውጊያና አንዳንድ አለማቀፍ ድርጅቶችና የተወሰኑ አገራት በኢትዮጵያ ላይ ለምን ጫና እንደሚያደርጉ ከዚህ ጀርባ ማን ምን እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል። ጌታቸውም ዛሬ በትክክለኛው ሚዲያ ትክክለኛው ማንነቱን ይዞ ከነስሙ ለኢትዮጵያውያን አሳውቋል። @zena_tubee
Show all...
ኢትዮጲያ አምስት ሚሊዮን ደብዳቤ ለጆ ባይደን ልትልክ ነው! የጆ ባይደን አስተዳደር በሰሜን ኢትዮጲያ ባለው ጦርነት ላይ የያዘውን ፖሊሲ ለማውገዝ አምስት ሚሊዮን ደብዳቤ ለጆ ባይደን ይላካል።ደብዳቤዎች መላክ የጀመሩ ሲሆን ለቀጣዮቹ 10 ቀናት ቀጣይነት ይኖረዋል። የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጲያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ማቆም አለበት፤ ከአፍጋኒስታን ፣ ፓኪስታን እና ሊቢያ መማር ይኖርበታል ሲሉ የኢትዮጵያ ወጣቶች ማጎልበት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ሰይፉ ተናግረዋል
Show all...
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የጀነሬተር አንቀሳቃሽ አካል( Rotar) የማስቀመጥ ሥራ ዛሬ በስኬት ተከናወነ! በቅርቡ ኃይል እንደሚያመነጭ ከሚጠበቁት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለት ዩኒቶች መካከል በዩኒት 10 ላይ የተርባይን ጀነሬተር ተሽከርካሪ አካል (Rotar) በቦታው ላይ የማስቀመጥ ሥራ ዛሬ በስኬት ተከናውኗል።ሮታሩና አብረው ያሉት አካላት 840 ቶን ክብደት ያላቸው ሲሆን ሮተሩ ብቻውን 780 ቶን ይመዝናል።ሮተሩ ከአንድ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ድረስ ያለው አጋማሽ ርዝመት ወይም ዳያሜትር 11 ነጥብ 7 ሜትር ነው።የሮተሩና የተርባይን አካላቶች በአግባቡ መገጠም የኃይል ማመንጨት የሙከራ ስራ ለመጀመር መቃረቡ አመላካች ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። Zena_tubee
Show all...
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል። የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ።  የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፤ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል ብለዋል። የመፈተኛ ወይም የአድሚሽን ካርድ ከመስከረም 24 እስከ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ለተማሪዎች እንደሚሰጥም ገልፀዋል።
Show all...
አዲሱ ዓመት ለ30 ዓመታት ኢትዮጵያን የተጣባትን ፈተና” ተገላግለን “አዲስ መንግሥት የምንመሠርትበት እንደሚሆን እምነቴ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ። ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ አዲሱን ዓመት በማስመልከት ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አዲሱ ዓመት በወሳኝ ሀገራዊ ፈተናና ተስፋ መካከል ሆኖ የሚከበር መሆኑን ገልጸዋል ይህ ሲሆን የመጀመሪያም የመጨረሻም እንዳይደለ በመጠቆም፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የገጠሟትን ፈተናዎች እንደየ አመጣጣቸው “አሸንፋ” ሺ ዘመናትን በነጻነት መኖሯንም አስታውሰዋል። “ታሪካችንን ሳያውቁ የሚገጥሙንን ታሪካችንን ዐውቀን እንጠብቃቸዋለን። ለወዳጃችን ወተት፣ ለጠላታችን ዕሬት መስጠት እንችልበታለን። ከቶም ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከማሸነፍ እንጂ ከመሸነፍ ጋራ ተጠርቶ አያውቅም። ከነጻነት እንጂ ከባርነት ጋራ ዝምድና የለውም። ኢትዮጵያ ተፈትና ታውቃለች። ተሸንፋ ግን አታውቅም። ቀጥና ታውቃለች፤ ተበጥሳ ግን አታውቅም። የዘመመች መስላ ታውቃለች፤ ወድቃ ግን አታውቅም” ሲሉም አስቀምጠዋል። “ይህ አዲሱ ዓመት ለ30 ዓመታት ኢትዮጵያን የተጣባትን ፈተና የምንገላገልበት፣ አዲስ መንግሥት የምንመሠርትበት፣ ከደረሰብን ፈተና የምናገግምበትና ፊታችንን ወደ ኢትዮጵያ ብልጽግና የምናዞርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው” ያሉም ሲሆን “አዲሱ ዓመት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን የሚጸናበት፣ ዴሞክራሲያዊ ዕሴቶቻችን የሚጎለብቱበት፣ የጀመርነው ሪፎርም መልክ የሚይዝበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል። በማንነቱ የሚኮራ እና የሚሰራ አዲስ ትውልድ እየተፈጠረ ነው ባሉበት መልዕክታቸው በሀገር ጉዳይ ጣት ከመጠቆም ይልቅ “ከእኔስ ምን ይጠበቃል?” ማለት መጀመር እንዳለበትም ነው የገለጹት፡፡ወደ አዲሱ ዘመን የሚደረገው ሽግግር “እንደ ሀገር የሚጎዱንን አሮጌ ማንነቶች በመጣልና በአዲስ ጠቃሚ ማንነቶች በመተካት መሆን” አለበትም ብለዋል ጠ/ሚ ዐቢይ። “ዕንቅፋቶቻችን እየተወገዱ ነው፤ ወደረኞቻችን ሁሉ ድል እየሆኑ ነው። ዘመኑ የኢትዮጵያ ነው። አዲሱ ዓመት የአዲሲቱ ኢትዮጵያ ነው። ኢትዮጵያ በአዲሱ የዘመን መጽሐፍ ላይ አዲሱን የብልጽግና ጉዞዋን ትጽፍበታለች። ድሏንና አሸናፊነቷን ትጽፍበታለች። ክብሯንና ታላቅነቷን ትጽፍበታለ ” ሲሉም ነው ያስቀመጡት።ኢትዮጵያውያን ተደጋግፈው በጋራ ለማደግ እንዲነሱና እርስ በእርስ እንዲተሳሰቡም ጠይቀዋል፡፡ጠ/ሚ ዐቢይ ዛሬ "ስለ ኢትዮጵያ" እና "Biyya koo" የተሰኙ ሁለት አልበሞችን ሠርተው ያቀረቡ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን ማመስገናቸው የሚታወስ ነው፡፡ Zena_tubee
Show all...
አሸባሪው ህወሃት ማንም ያልፈፀመውን ግፍ እና በደል ፈፅሟል ! ሆስፒታሎችን አውድሟል ! እንደ ሃይሌ ገብረስላሴ አይነት ሀገር ወዳዶች የሰሯቸውን ትምህርት ቤቶች አውድሟል ። ከጦርነት ሸሽተው የተጠለሉ ንፁሃንን በጅምላ ከባድ መሳሪያ ጨፍጭፏል ። በአፋር ፣ በወሎ እንዲሁም በጎንደር እጅግ ሰቅጣጭ የሆኑ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ፈፅሟል ። ይህ አረመኔያዊ አሸባሪ ድርጅት ዛሬ ወገቡን ተቆርጦ አከርካሪው ተሰብሮ ፍፃሜው እየቀረበ መሆኑን ሲያውቅ አሸማግሉኝ እያለ ከ 50 በላይ ሀገራትን ተማፅኗል ። የህወሃት ጦር በማሸነፍ ላይ ባለበት ጊዜ ያን ሁሉ ግፍና በደል ሲፈፅም ሰምተው እንዳልሰሙ አይተው እንዳላዩ ፀጥ ያሉት የነፍስ አባቶቹ ዛሬ ግብአተ መሬቱ እየተፈፀመ መሆኑን ሲያዩ ተደራደሩ የሚል ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ !! " በዳይን ይቅር ማለት ተበዳይን እጥፍ ድርብ አድርጎ መበደል ነው " እንዲሉ ቱርኮች መንግስት ከዚህ አረመኔ ጋር ተቀምጦ የሚደራደር ከሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ በተለይም የአማራን እና የአፋርን ህዝብ እንደካደ ነው የምንቆጥረው !! ይህን ጭራቅ ወራሪ ሃይል ለፈፀመው ሊነግሩት የሚዘግንን ግፍና በደል ተገቢውን ቅጣት ሊቀጣ ይገባል እንጅ ድርድር የሚባል ሽልማት ሊሰጠው አይገባም !! ሽፍታ ጋር ድርድር የለም ! ያ ቢሆን ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ያዝናል !! በዚህ ቡድን ሰለባ የሆኑት ኢትዮጵያዊያን አንጀታቸው ሊርስ የማችለው ይህ ቡድን ተጠራርጎ ሲጠፋ ብቻ ነው !!
Show all...
የፌደራል ፖሊስ አባላት ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ አሸባሪው ህወሓት በሀገር ላይ የከፈተውን ጦርነት በብቃት እየመከቱ ነው ተባለ! የፌደራል ፖሊስ አባላት ከመከላከያ ሠራዊትና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር አሸባሪው ህወሓት በሀገር ላይ የከፈተውን ጦርነት በብቃት እየመከቱ መሆኑ ተገለፀ፡፡ አባላቱ በአፋር፣ በወሎ እና በሁመራ ግንባሮች ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረጋቸውን የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል፡፡ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ የፖሊስ አባላቱ አሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ በእምነቶችና በብሄሮች መካከል ግጭት እንዲፈጠር በተለያየ መንገድ የሚያደርጉትን ጥረት ለመከላከል እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዚህም ከ700 በላይ በሚሆኑ የሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የጦር መሳሪያዎች መማረካቸውን እና በርካታ የቡድኑን አባላት በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልፀዋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መከተልና በደቡብ ክልል ጉራፋርዳ አካባቢ በሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ላይም ከክልሉ ፖሊስና ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድባቸው እየተሰራ መሆኑንም ጨምረው መግለፃቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Show all...
ሰበር ዜና‼️ #Ethiopia : የአፋር ክልል ልዩ ሀይል ሚሊሻ እንዲሁም መከላክያ ሰራዊታችን ጁንታውን በመደምሰስ ማምሻውን ያሎን ሙሉ በሙሉ ተቋጣጥሮታል::
Show all...