cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

FELEG ETHIOPIA

Social links ዩቲዩብ - youtube.com/@felegethiopia ፌስቡክ - facebook.com/groups/felegethiopia ሙዚቃ - youtube.com/@timelessmuzika ቲክቶክ - tiktok.com/@zethiojoys

Show more
The country is not specifiedAmharic5 164The category is not specified
Advertising posts
1 314Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

​ዋናዋና ዜናዎች ! 1፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትና የፋኖ ሚሊሻዎች በደቡብ ጎንደር ዞን ዋና ከተማ ደብረ ታቦር አቅራቢያ ትናንትና ዛሬ ውጊያ ማካሄዳቸውን ሮይተርስ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የከተማዋን ሐኪምና ፖሊስ ጠቅሶ ዘግቧል። ሐኪሙ፣ በጥይትና በከባድ መሳሪያ በከባድ ኹኔታ የቆሰሉ ሦስት ሰዎችና ቀላል የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሌሎች 10 ሰዎች በከተማዋ ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ ማግኘታቸውን እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። ዜና ምንጩ፣ ውጊው ዛሬም እንደቀጠለ መኾኑን፣ ወደ ከተማዋ የሚያስገቡ መንገዶች መዘጋታቸውንና ቁስለኞች ከሆስፒታሉ የሚደርሱት በእግር ጉዞ መኾኑን ሐኪሙ ነግረውኛል ብሏል። 2፤ በአማራ ክልል የፋኖ ታጣቂዎች በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አካባቢ ዛሬም በመንግሥት ኃይሎች ጋር መጋጨታቸውን ዋዜማ ከአካባቢው ምንጮች ሰምታለች። ትናንትም በላሊበላ ከተማ አቅራቢያ በፋኖ ታጣቂዎችና ከመንግሥት ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የዋዜማ ምንጮች ገልጸዋል። የስፔን ኢምባሲ፣ በከተማዋ የሚገኙ ስፔናዊያን ከቤታቸውና ሆቴላቸው እንዳይወጡ ዛሬ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ መልዕክት አስተላልፏል። 3፤ የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ መንግሥታቸው በክልሉ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በውይይት ለመፍታት ዝግጁ መኾኑን ለክልሉ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። ይልቃል ውይይት የሚፈልጉ አካላት ነፍጣቸውን አስቀምጠው ለውይይት እንዲቀርቡ ጥሪ አድርገዋል። መከላከያ ሠራዊት በክልሉ እያካሄደ ያለው "የሕግ ማስከበር" እንቅስቃሴ መኾኑን ይልቃል በድጋሚ ገልጸዋል። 4፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ በትግራይ ክልል አክሱም ጺዮን ማርያም ቤተክርስቲያን ሰሞኑን የኤጲስ ጳጳሳት ሹመት የሰጡ አራት ጳጳሳት "ከዲቁና ጀምሮ ያለውን ሙሉ ሥልጣነ ክህነታቸውን" መሻሩን አስታውቋል። ሲኖዶሱ ጳጳሳቱ በቤተክርስቲያኗ ላይ "የክህደት" እና "ኑፋቄ" ተግባር ፈጽመዋል በማለት፣ በውግዘት ከቤተክርስቲያኗ እንዲለዩና በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ መወሰኑን ገልጧል። ኾኖም ጳጳሳቱ፣ በድርጊታቸው ተጸጽተው ይቅርታ ከጠየቁ ቤተክርስቲያኗ የምኅረት በሯን እንደምትከፍትላቸው ሲኖዶሱ ገልጧል። ከቀኖና ውጭ የተሾሙ ዘጠኝ ኤጲስ ጳጳሳትም፣ በተመሳሳይ ተወግዘው የክህነት ማዕረጋቸው ተገፏል። 5፤ የደቡብ ክልል ምክር ምክር ቤት ከመጭው ዓርብ ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ጉባኤውን እንደሚያካሂድ አስታውቋል። የምክር ቤቱ ጉባኤ፣ ባለፈው የካቲትና ሰኔ በተካሄዱ ሕዝበ ውሳኔዎች መሠረት ለሚቋቋመውና "የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች" ክልል ተብሎ እንደሚሰየም ለሚጠበቀው አዲሱ ክልል ሥልጣን እንደሚያስረክብ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ፋጤ ሰርመሎ ለክልሉ ቴሌቪዥን ተናግረዋል። 6፤ በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ለኹለት ዓመታት የመማር ማስተማር ሥራውን አቋርጦ የቆየው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል። ዩኒቨርስቲው ዛሬ መቀበል የጀመረው፣ የጦርነቱን መቀስቀስ ተከትሎ የመማር ማስተማር ሥራውን ባቋረጠበት ዓመት ዕጩ ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎችን ነው። በትግራይ ክልል ከሚገኙት የፌደራል ዩሚቨርስቲዎች መካከል፣ አዲግራትና አክሱም ዩኒቨርስቲዎች ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቀደም ብለው የመማር ማስተማር ሥራቸውን ጀምረዋል። 7፤ ትናንት ምሽት 2:15 ገደማ ከአሥመራ ደቡባዊ ምሥራቅ 55 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ 5 ነጥብ 6 የተለካ ርዕደ መሬት መከሰቱን የአሜሪካው ጅዖሎጂካል ጥናት ተቋም አስታውቋል። የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል፣ ርዕደ መሬተ መከሰቱን በትዊተር ገጻቸው አረጋግጠዋል። ርዕደ መሬቱ የተከሰተው፣ ከከርሰ ምድር በታች 10 ኪሎ ሜትር ላይ እንደኾነ የተቋሙ መረጃ አመልክቷል። ይህንኑ ተከትሎ፣ በትግራይ ክልል በመቀሌ፣ አክሱም፣ አድዋና አዱግራት ከተሞች የመሬት ንዝረት ተከስቷል። በርዕደ መሬቱና በንዝረቱ የደረሰ ጉዳት የለም ተብሏል። 8፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ7879 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ8837 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 66 ብር ከ7582 ሳንቲምና መሸጫው 68 ብር ከ0934 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ60 ከ0475 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ61 ብር ከ3485 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል።(ዋዜማ) ዩቲዩብ - youtube.com/@felegethiopia ቴሌግራም - t.me/felegethiopia ፌስቡክ - facebook.com/groups/felegethiopia ሙዚቃ - youtube.com/@timelessmuzika ቲክቶክ - tiktok.com/@zethiojoys
Show all...
­

👍 10 3
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ ኤጲድ ቆጶሳት ሹመት ጉዳይ ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በኃላ ውሳኔዎችን አሳለፈ። ቅዱስ ሲኖዶስ ፦ 1. ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ የመቀሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የእንቅስቃሴው ሰብሳቢ 2. ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በክልል ትግራይ የማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 3. ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ 4. ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ   መሪነት እጅግ አሳዛኝ ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ አስነዋሪ፣ ሕገ-ወጥ፣ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት በመፈጸም 10 መነኮሳትን በእጩነት በመምረጥና ለዘጠኙ ህገወጥ ሲመት ፈፅመዋል ብሏል።   ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ድርጊታቸው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር ፈፅመዋል ሲል ገልጿል። በዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ እንደለያቸው ገልጿል። ሥልጣነ ክህነታቸውና የማዕረግ ስማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ የተነሣ ስለሆነ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ ውሳኔ ተላልፏል። በቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያም በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን እንደለያቸው ተገልጿል። በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽተው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት በመሆናቸው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት እንቀበላቸዋለን ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል። የኤጲስ ቆጶስነት ሹመት አግኝተናል፤ ተሹመናል እያሉ የሚገኙ 9 መነኮሳት ፦ - አባ ዘሥላሴ ማርቆስ - አባ ኃይለ ሚካኤል አረጋይ - አባ እስጢፋኖስ ገብረ ጊዮርጊስ - አባ መሓሪ ሀብቶ - አባ ኤልያስ ታደሰ ገብረ ኪዳን - አባ ጽጌ ገነት ኪዳነ ወልድ - አባ ዘርአ ዳዊት ብርሃነ - አባ ዮሐንስ ከበደ - አባ የማነ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በሕገ ወጥ መንገድ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንን ጥሰው የተገኙ በመሆኑ አስቀድሞ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ተሽሮ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያ በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን ለይቷቸዋል፡፡    ቅዱስ ሲኖዶስ ህገወጥ ሢመቱ እንዲፈጸም ከመጀመሪያው ጽንሰ ሀሳብ ጀምሮ መሪ ተዋናይና ቀስቃሽ ነበሩ ያላቸው አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤልና ሂደቱን በዋና አስፈጻሚነት በመምራትና መግለጫ በመስጠት ላይ ያሉት መ/ር ተስፋዬ ሐደራ ከዛሬ ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተወግዘው ከቤተክርስቲያን ተለይተዋል ብሏል። ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " መንበረ ሰላማ "  የሚለው ስያሜ ሕገወጥ መሆኑን ገልጾ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትውፊትም ሆነ በቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ትውፊት የማይታወቅ፣ ሃይማኖታዊ መሠረት የሌለው፣ ከቀኖና የወጣ፣ አስተዳደራዊ መዋቅርን የሚያዛባ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም ብሏል። (ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል) ዩቲዩብ - youtube.com/@felegethiopia ቴሌግራም - t.me/felegethiopia ፌስቡክ - facebook.com/groups/felegethiopia ሙዚቃ - youtube.com/@timelessmuzika ቲክቶክ - tiktok.com/@zethiojoys
Show all...
FELEG ETHIOPIA

Social links ዩቲዩብ - youtube.com/@felegethiopia ፌስቡክ - facebook.com/groups/felegethiopia ሙዚቃ - youtube.com/@timelessmuzika ቲክቶክ - tiktok.com/@zethiojoys

1
በትግራይ ክልል ትላንት እና ዛሬ ለሶስት ጊዜ ያህል የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው ንዝረት መከሰቱ ተገለጸ በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ትላንት ምሽት እና ዛሬ ጠዋት፤ ለሶስት ጊዜ ያህል የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለው ንዝረት መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦፊዚክስ፣ ህዋ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በክልሉ ዋና ከተማ መቐለ እና በሌሎች አራት ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች ንዝረቱ በአካባቢያቸው ማጋጠሙን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል። ይህን ንዝረት ያስከተለው የመጀመሪያው እና ዋናው የመሬት መንቀጥቀጥ ትላንት ማክሰኞ ሐምሌ 25፤ 2015 የተከሰተው፤ በኤርትራ ባህር ዳርቻ ዳህላክ ደሴት አካባቢ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሶሲሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። በሬክተር ስኬል 5.4 ሆኖ የተለካው ይህ የመሬት መንቀጥቀጥ የተመዘገበው፤ ትላንት ምሽት ሁለት ሰዓት ከ15 ደቂቃ ላይ እንደነበር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስር ባለ ኢንስቲትዩት የመሬት መንቀጥቀጥን የሚያጠናውን የትምህርት ክፍል የሚመሩት ፕሮፌሰር አታላይ አስረድተዋል። የትላንቱ የመሬት መንቀጥቀጥ “መለስተኛ” (moderate) የሚባል ምድብ ውስጥ የሚወድቅ ቢሆንም “የሚናቅ” እንዳልሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ ተመራማሪ እና ባለሙያው ተናግረዋል። “ይህንን ያህል መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባ [ከተማ ውስጥ] ቢፈጠር ብዙ ህንጻዎች ይወድማሉ” ሲሉ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ፕሮፌሰር አታላይ አነጻጽረዋል። በኤርትራ የተከሰተው መንቀጥቀጥ፤ በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ትላንት ምሽት እና ዛሬ ጠዋት “ንዝረት” (shock) ማስከተሉን ፕሮፌሰር አታላይ ተናግረዋል። የትላንቱ የመሬት መንቀጥቀጥ በተመዘገበበት ዳህላክ ደሴት አካባቢ፤ ዛሬ ንጋት 12፡37 አካባቢ እና ጠዋት 2፡10 ላይ ተጨማሪ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የዘርፉ ባለሙያ አክለዋል። ሆኖም የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል ምን ያህል እንደሆነ በተቋማቸው ገና ስሌቱ አለመሰራቱንም አመልክተዋል። በኤርትራ የባህር ዳርቻ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ምን ያህል ቦታ እንደሸፈነ መረጃው ገና እየተጠናቀረ ቢሆንም፤ በትላንናው ዕለት የተከሰተው ግን ሀገሪቱን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስኑ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ድረስ የተሰማ እንደሆነ ገልጸዋል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የሽሬ፣ አዲግራት፣ አድዋ፣ አክሱም እና መቐለ ከተማ ነዋሪዎች የመሬት መንቀጥቀጡ ያስከተለው ንዝረት በአካባቢያቸው አጋጥሞ እንደነበር ማረጋገጫ ሰጥተዋል። የአምስቱም ከተሞች ነዋሪዎች የትላንቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት የተከሰተው ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ እንደነበር ተናግረዋል። ንዝረቱ ሲጀምር በቤት እቃዎች እና ቆርቆሮዎች ላይ ንቅናቄዎች መስማታቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፤ በመጀመሪያ የሁኔታውን ምንነት ወዲያውኑ ለመረዳት ተቸግረው እንደነበር ጠቁመዋል። የአዲግራት፣ አክሱም እና ሽሬ ነዋሪዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ በተከሰተበት ሰዓት “ከፍተኛ ድምጽ” መሰማቱን ገልጸዋል። አንዲት የሽሬ ከተማ ነዋሪ የተሰማውን ድምጽ “የከባድ መሳሪያ” አይነት ሲሉ ገልጸውታል። ሌላ የአዲግራት ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው፤ “የማታው በጣም ኃይለኛ ነበር። የቤት እቃዎች ሁሉ፣ በርም ሲንገጫገጭ [ነበር]። ድምጽም ሁሉም ነበረው” ሲሉ የሽሬ ከተማ ነዋሪዋን ገለጻ አስተጋብተዋል። እኚሁ የአዲግራት ከተማ ነዋሪ፤ ዛሬ ንጋት 12 ሰዓት ገደማ ላይም በድጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት መስማታቸውን ጠቅሰው፤ ከትላንቱ ጋር ሲነጻጸር የዛሬው “ቀለል ያለ” እንደነበር ጠቅሰዋል። በዚህም ምክንያት “ብዙም ሰው ላይሰማው ይችላል” ሲሉም አክለዋል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የመቐለ፣ አድዋ፣ አክሱም እና ሽሬ ከተሞች ነዋሪዎች፤ ከትላንት ምሽት የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት በኋላ ሌላ ተመሳሳይ ክስተት አለማስተዋላቸውን አስረድተዋል።  በትግራይ ክልል ያሉ የአምስት ከተማ ነዋሪዎች፤ በመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ምክንያት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች “በሰዎች ላይ ጉዳት አልደረሰም” ብለዋል። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በዚሁ ክስተት የደረሰ ጉዳት መኖር አለመኖሩን ለማጣራት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊዎች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪዎች በታደርግም ምላሽ ማግኘት አልቻለችም። ጉዳዩን በተመለከተ ከመቐለ እና አክሱም ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረትም አልተሳካም።(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) ዩቲዩብ - youtube.com/@felegethiopia ቴሌግራም - t.me/felegethiopia ፌስቡክ - facebook.com/groups/felegethiopia ሙዚቃ - youtube.com/@timelessmuzika ቲክቶክ - tiktok.com/@zethiojoys
Show all...
FELEG ETHIOPIA

Social links ዩቲዩብ - youtube.com/@felegethiopia ፌስቡክ - facebook.com/groups/felegethiopia ሙዚቃ - youtube.com/@timelessmuzika ቲክቶክ - tiktok.com/@zethiojoys

👍 2
ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ ስልሳ ሦስት ሰዎች በሸኔ ታጣቂዎች መታገታቸው ተገለጸ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ልዩ ሥሙ ቱሉ ሚልኪ በተባለ አካባቢ ሰኞ ሐምሌ 24/2015 በሸኔ ታጣቂ ቡድን ስልሳ ሦስት ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የደጀን ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አንዳርጌ ዘውዴ፤ ድርጊቱ የተፈጸመው 65 ሰዎችን አሳፍሮ ከባህር ዳር ከተማ በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የታጣቂ ቡድኑ አባላት እገታውን የፈጸሙት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ መሆኑን እንዲሁም አቅመ ደካማ ከሆኑ አንዲት ባልቴት እና አንድ ሽማግሌ በስተቀር ሹፌሩን እና ረዳቱን ጨምሮ በአጠቃላይ 63 ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የደጀን ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊው አክለውም፤ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ በሚጓዙ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችና የጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ መሰል ድጊቶች በተደጋጋሚ እየተፈጸሙ እንደሆነ ጠቅሰዋል። ለአብነትም ባለፈው ሰኔ 10/2015 በገርበ ጉራቻ አካባቢ ከአማራ ክልል ተነስተው ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በማስቆም ከ50 በላይ አሽከርካሪዎችና መንገደኞች በሸኔ ታጣቂዎች መታገታቸውን አስታውሰው፤ የመክፈል አቅም ያላቸውን ሰዎች ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸውን ጠቁመዋል። ተጨማሪ ➣ InstantView from Source @felegethiopia
Show all...
ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ ስልሳ ሦስት ሰዎች በሸኔ ታጣቂዎች መታገታቸው ተገለጸ

ረቡዕ ሐምሌ 26 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ልዩ ሥሙ ቱሉ ሚልኪ በተባለ አካባቢ ሰኞ ሐምሌ 24/2015 በሸኔ ታጣቂ ቡድን ስልሳ ሦስት ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የደጀን ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አንዳርጌ ዘውዴ፤ ድርጊቱ የተፈጸመው 65 ሰዎችን አሳፍሮ ከባህር ዳር ከተማ በመነሳት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ መሆኑን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የታጣቂ ቡድኑ አባላት እገታውን የፈጸሙት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ መሆኑን እንዲሁም አቅመ ደካማ ከሆኑ አንዲት ባልቴት እና አንድ ሽማግሌ በስተቀር ሹፌሩን እና ረዳቱን ጨምሮ በአጠቃላይ 63 ሰዎችን አግተው መውሰዳቸውን በአካባቢው የነበሩ የዓይን እማኞች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የደጀን ከተማ ሰላም እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት…

👍 1
በመተከል ዞን ከገዢው ፓርቲ አመራርና አባላት ውጭ በኢንቨስትመንት መሳተፍና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን ማግኘት እንደማይቻል ተገለጸ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ከብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት ውጭ በኢንቨስትመንት ዘርፍ መሳተፍም ሆነ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ማግኘት እንደማይቻል ተገልጿል። በዞኑ በተለይም በቡለን ወረዳ የከበሩ የማዕድን ሃብቶችን ለማውጣት፣ የእርሻ መሬት ወስዶ ለማልማት እና የመንግሥት ሠራተኞች ሆኖ ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት የገዥው ፓርቲ አመራር ወይም አባል መሆን ግድ ይላል ነው የተባለው። በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ካቀረቡ የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ግለሰብ፤ ማንኛውም የገንዘብ አቅም ያለውና መስፈርት የሚያሟላ ሰው በኢንቨስትመንት ዘርፍ ተደራጅቶ ቦታ መጠየቅና መውሰድ ቢችልም፤ በቡለን ወረዳ ውስጥ ግን “የእኛ ፓርቲ አባል ስላለሆናችሁ ማስተናገድ አንችልም” የሚል ምላሽ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ አክለውም፤ በዞኑ የቀበሌ መታወቂያ እንኳ ለማውጣት እና ለማሳደስ የገዢው ፓርቲ አባል መሆንን እንደሚጠይቅ በመጠቆም፣ ገዢውን ፓርቲ የማይደግፉ ሰዎች አገልግሎቱን ለማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን አክለዋል። “ዋና ዋና የኢንቨስትመንት ዘርፎች በብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና በቤተሰቦቻቸው እየተያዙ ነው፡፡” ያሉት ነዋሪዎቹ፤ በቡለን ወረዳ ማሳ፣ ዳንጉርጋ፣ ሞራ፣ ማጣ እንዲሁም ኩየ በተባሉ ቀበሌዎች በብዛት የከበሩ ማዕድናት ያሉባቸው ቦታዎች መሆናቸውን ተከትሎ፤ ከባለስልጣናት ውጭ ሌላው የአካባቢው ማህበረሰብ እየተጠቀመ አይደለም ብለዋል። ተጨማሪ ➣ InstantView from Source @felegethiopia
Show all...
በመተከል ዞን ከገዢው ፓርቲ አመራርና አባላት ውጭ በኢንቨስትመንት መሳተፍና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን ማግኘት እንደማይቻል ተገለጸ

ረቡዕ ሐምሌ 26 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ከብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት ውጭ በኢንቨስትመንት ዘርፍ መሳተፍም ሆነ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ማግኘት እንደማይቻል ተገልጿል። በዞኑ በተለይም በቡለን ወረዳ የከበሩ የማዕድን ሃብቶችን ለማውጣት፣ የእርሻ መሬት ወስዶ ለማልማት እና የመንግሥት ሠራተኞች ሆኖ ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት የገዥው ፓርቲ አመራር ወይም አባል መሆን ግድ ይላል ነው የተባለው። በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ካቀረቡ የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ግለሰብ፤ ማንኛውም የገንዘብ አቅም ያለውና መስፈርት የሚያሟላ ሰው በኢንቨስትመንት ዘርፍ ተደራጅቶ ቦታ መጠየቅና መውሰድ ቢችልም፤ በቡለን ወረዳ ውስጥ ግን “የእኛ ፓርቲ አባል ስላለሆናችሁ ማስተናገድ አንችልም” የሚል ምላሽ እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ አክለውም፤…

የመዲናዋ ነዋሪዎች የቤት ጣሪያና ግድግዳ ግብር ክፍያቸውን እስከ ነሐሴ 30 እንዲያጠናቅቁ ማሳሰቢያ ተሰጠ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የመዲናዋ ነዋሪዎች የቤት ጣሪያና ግድግዳ ግብር ክፍያቸውን እስከ ነሐሴ 30/2015 ድረስ እንዲያጠናቅቁ አሳስቧል፡፡ የቢሮው ኃላፊ አደም ኑሪ፤ በቤት ወይም በከተማ ቦታ ኪራይ እና የቤት ግብር አዋጅ መሰረት የጣራ እና ግድግዳ የግብር ክፍያ ሲተገበር መቆየቱን ጠቅሰዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አዲስ የገበያ ጥናት በማድረግ በሚያዝያ ወር ላይ ወቅታዊ የማድረግ ሥራ መሰራቱን አስታውሰዋል። በዚህም መሰረት እንዲከፍሉ ይጠበቅባቸው የነበሩ ሰዎች እስካሁንም በመክፈል ላይ መሆናቸውን ገልጸው፤ ከሚጠበቀው አንጻር በርካቶች ገና መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በአዲሱ ጥናት መሰረት ለመኖሪያ ቤት 50 በመቶ እንዲሁም ለድርጅት 75 በመቶ እንዲከፍሉ መወሰኑን አስታውሰዋል። በጥናቱ መሰረት 800 ሺሕ የሚጠጋ ግብር ከፋይ ይጠበቃል ያሉት ኃላፊው፤ በአዲሱ ስሌት መሰረት እስካሁን 223 ሺሕ ግብር ከፋዮች ብቻ መክፈላቸውን ተናግረዋል። በእዚህም ቁጥሩ ከፍ ያለ ግብር ከፋይ እስካሁን አለመክፈሉን በመጥቀስ፤ ነዋሪዎች የቤት ጣሪያና ግድግዳ ግብር ክፍያቸውን እስከ ነሐሴ 30/2015 እንዲያጠናቅቁ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል። ከተቀመጠው ጊዜ ውጭ የሚመጡ ግብር ከፋዮች በሕጉ መሰረት ባልተከፈለው ግብር መጠን 5 በመቶ ቅጣት የሚጠብቃቸው መሆኑንም ጠቁመዋል። በተለይም የትልልቅ ህንጻ ባለቤቶች ግብር የመክፈል አዝማሚያ እስካሁን ዝቅተኛ ነው ያሉት ሃላፊው፤ በተሰጠው ጊዜ በመክፈል ግዴታቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል። ዩቲዩብ - youtube.com/@felegethiopia ቴሌግራም - t.me/felegethiopia ፌስቡክ - facebook.com/groups/felegethiopia ሙዚቃ - youtube.com/@timelessmuzika ቲክቶክ - tiktok.com/@zethiojoys
Show all...
­

👎 1
በአማራ ክልል ሕግን ለማስከበር በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ሕዝቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያሳይ ተጠየቀ የጸጥታ አካላት በክልሉ ሕግን ለማስከበር በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሁሉ ህዝቡ ድጋፍ በማድረግ የተለመደ ትብብሩን እንዲያሳይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ጥሪ አቀረቡ። ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ በመግለጫቸው ሕግ የማስከበር ሥራ የመንግሥት ሃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ሰላማዊውን ሕዝብ በማወክና መንገድ በመዝጋት ችግር የሚፈጥሩ አካላት የክልሉን ልማትና የሕዝቡን አንድነት እየጎዱ በመሆናቸው ከእዚህ ድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል። የአገር መከላከያ ሠራዊት ሕግን ለማስከበር ወደ ተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የሚደረግ ትንኮሳ መቆም እንዳለበት የገለጹት ዶክተር ይልቃል፤ መላው የክልሉ ሕዝብም ለሠራዊቱ ድጋፍ በማድረግ የተለመደ ትብብሩን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል። በተለይ የኹሉም የአገሪቱ ሕዝቦች ልጅ የሆነውን የመከካከያ ሠራዊት ሥም ማጥፋት ተገቢነት የሌለው መሆኑን መላ ህዝብ ሊገነዘብ እንደሚገባም ተናግረዋል። "የአገር መከላከያ ሠራዊት የአገር ሉአላዊነትን የሚያስጠብቅ የህዝብ መከታ ነው" ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የሠራዊቱን እንቅስቃሴ ለመገደብ የሚደረጉ ጥረቶች መቆም አለባቸው ብለዋል። በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች እየተስተዋለ ያለው ችግር ከመባባሱ በፊት ነፍጥ ማንገብ መቆም አለበት ያሉት ዶክተር ይልቃል፣ በየአካባቢው በሚካሄዱ የውይይት መድረኮች በመሳተፍ ሀሳብን መሞገትና ልዩነቶችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል። የክልሉ መንግሥት ከዚህ ቀደምም ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱ ርዕሰ መስተዳድሩ፤ አሁንም ሰላምን ለማጠናከር በየአካባቢው ከሕዝቡ ጋር እየተወያየ መሆኑን ገልጸዋል። ዩቲዩብ - youtube.com/@felegethiopia ቴሌግራም - t.me/felegethiopia ፌስቡክ - facebook.com/groups/felegethiopia ሙዚቃ - youtube.com/@timelessmuzika ቲክቶክ - tiktok.com/@zethiojoys
Show all...
­

👎 2
ናሳ ከምድራችን 20 ቢሊዮን ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጠፍቶብኝ ነበር ያለውን መንኮረኩር መልሶ ማግኘቱን አስታወቀ። የአሜሪካው ግዙፉ የጠፈር ምርምር ማዕከል ከእአአ 1977 ጀምሮ ጠፈርን ሲያስስ ከነበረው መንኮራኩር ጋር የነበረው ግንኙነት መቋረጡን አስታውቆ ነበር። ባለፈው ወር ቮይጀር-2 ወደተባለው መንኮራኩር በስህተት የተላከ ትዕዛዝ መንኮራኩሩ ከምድራችን በሁለት ዲግሪ አንቴናውን እንዲያዞር በማድረጉ ግንኙነት ተቋርጦ ናሳ መልዕክት መቀበልም ሆነ መላክ ተስኖት ቆይቷል። ይሁን እንጂ ናሳ ትናንት ማክሰኞ በአጽናፈ ሰማይ (ዩኒቨርስ) ላይ የተለመደ ዳሰሳ እያደረገ ሳለ ከመንኮረኩሩ መልዕክት እንደደረሰው አስታውቋል። ቮይጀር-2 አሁን ያለው የት ነው? ከሐምሌ 14/2015 ዓ.ም. ጀምሮ ከናሳ ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋርጦ የነበረው ቮይጀር-2 በአሁን ወቅት በናሳ ኔትወርክ ውስጥ መልሶ መግባቱ ዳግም ከመንኮራኮሩ ጋር ግንኙነት መፍጠር ይቻላል የሚል ተስፋን ፈጥሯል። መንኮራኮሩ ከምድራችን 20 ቢሊዮን ኪሎ ሜትሮችን ርቆ መገኘቱ ከመንኮራኮሩ የወጣው መልዕክት ወደ ምድር እስኪደርስ 18 ሰዓታት ሳይወስድ አይቅርም ተብሏል።ናሳ መልዕክቱን መቀበሉ መንኮራኮሩ አሁንም መረጃ እያሰራጨ እና “በጥሩ ሁኔታ” ላይ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው ብሏል። ናሳ እስካሁን ድረስ ከመንኮራኮሩ ጋር ሙሉ ግንኙነት መፍጠር ባይችልም ቮይገር-2 በቀጣይ አንቴነው ወደ ምድር አቅጣጫ ሲሆን ዳግም ሙሉ ግንኙነት መመሥረት እችላለሁ የሚል ተሰፋን ሰንቋል። እንደ ናሳ ገለጻ ቮይገር-2 በየዓመቱ ለበርካታ ጊዜያት ሥርዓቱን እንደ አዲስ እንዲያስጀምር ቀድሞ ተሞልቷል። ይህ ማለት መንኮራኮሩ የመቆጣጠሪያ ሥርዓቱን እንደ አዲስ ሲያስጀምር አንቴናውን ወደ መሬት አቅጣጫ ያዞራል። መንኮራኮሩ በቀጣይ ሥርዓቱን እንደ አዲስ የሚያስጀምረው ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ነው። ቮይጀር-2 የፀሐይን የውጪያዊ ሥርዓትን እንዲያጠና ነበር እአአ 1977 የተላከው።ይህ መንኮራኩር ከኔፕቱን እና ዩራኑስ ጎን የበረረ ብቸኛው መንኩራኩር ነው። ዩቲዩብ - youtube.com/@felegethiopia ቴሌግራም - t.me/felegethiopia ፌስቡክ - facebook.com/groups/felegethiopia ሙዚቃ - youtube.com/@timelessmuzika ቲክቶክ - tiktok.com/@zethiojoys
Show all...
­