🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂🍂
#ምሳሌ_6_21
#ሁልጊዜም_በልብህ_አኑረው_በአንገትህም_እሰረው። "
♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦
አንዳንድ በልማድ በውስጣችን የተሰገሰጉ ምንም አይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የሌላቸው ነገር ግን መንፈሳዊ መስለው አብረውን አድገው ያረጁ ብዙ ልማዳዊ ነገሮች አሉ
#ትልቁ ስህተት የሚጀምረው ደግሞ እነኚህን
#በዘፈቀደ የተሰገሰጉ ልምምዶችና አስተምሮቶ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማረግ
#መጽሐፍ_ቅዱስን በግድ ጠምዝዞ የምንፈልገውን እንዲል ማስገደድ ከባድ ስህተት ነው ፡፡
#እንደ_አንድ_ክርስቲያን እነኚህን አይነት ማስረጃ የሌላቸው ነገሮች ማጋለጥ እና እውነትን መግለጥ ግዴታዬ ነው ፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በውይይት ወቅት
#መስቀልን_በአንገት ስለማሰር ማስረጃ በማለት የሚያቀርቡት ክፍል ☞ ምሳሌ 6:21 በእርጋታ ለተመለከተው ክፍሉ ፍጹም ከዚ የተለየ ሐሳብ የያዘ ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡
📚 ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድን
#መስመር_ነቅሶ በማውጣት አሰተምሮ አይሰራም ፡፡ ቁጥር 21 ን ከ ቁጥር 20 ገንጥሎ በማውጣት የሌለ ሐሳብ መፍጠርም ስህተት ነው ለዚህ ነው ከፍ ብለን ቁጥሮቹን ከላችና ከታች ማየት የሚገባን እንዲህ ይላል 👇👇
..............,,,,........,,,,.........,,,,,........
(መጽሐፈ ምሳሌ ምዕ. 6)
----------
20፤
#ልጄ_ሆይ_የአባትህን_ትእዛዝ ጠብቅ፥
#የእናትህንም_ሕግ አትተው፤
21፤
#ሁልጊዜም_በልብህ አኑረው፥
#በአንገትህም_እሰረው።
22፤ ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
እንግዲ የክፍሉን ሙሉ ሀሳብ ለማግኘት ከቁጥር 20 ጀምሮ ማንበብ ግድ ይላb ፡፡ ነገር ግን ቁጥር #21 ን ብቻ ገንጥሎ በማውጣት የመጽሐፉን ሙሉ ሐሳብ ማግኘት አይቻልም ስለዚህ ክፍሉ እንዲ ይላል
📌 የአባትህን ትዕዛዝ ጠብቅ
📌 የእናትህን ሕግ አትተው
ይለንና ቁጥር 21 ላይ
🔍 ሁል ጊዜ በልብህ አኑረው በአንገትህም እሰረው ይላል ይህ ማለት ግን እንጨት ወርቅ ነሀስ ወይም ሌላ ነገር በመስቀል ቅርጽ ቀርጸህ አንገትህ ላይ አንጠልጥል ማለት አደለም ፡፡
ስለዚህ የእኔ ሙግቴ መስቀል በአንገት ለማሰር ብላቹ የምታቀርቡት
#ማስረጃ ልክ ያልሆነና የመጽሐፉን ሐሳብ ካለመረዳት የተፈጠረ ስህተት ነው ፡፡ እኔም ልክ ያልሆኑ ሐሰቶችን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መዝኜ አጋልጣለሁ እውነትን
#እሰብካለሁ ፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
⏰
@Henock4 ⏰
⏰
@adiskidanj ⏰
💡💡💡💡💡💡💡💡💡💡
Show more ...