cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የልቤን ለእናንተ

እንኳን ወደ ቻናላችን በደህና መጡ! በዚህ ቻናል:- * አጫጭር ልቦለዶች * ረጅም ልቦለዶች *አጫጭር ታሪኮች *ግጥሞች * የጉዞ ማስታወሻዎች *እንዲሁም ኢትዮጵያዊነትን በሰፊው የሚዳስሱ ፅሁፎች! * መፅሐፍትን በpdf ስለተቀላቀሉን ከ❤ እናመሰግናለን!! t.me/yelbenlenante

Show more
Advertising posts
626Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-730 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ከተማሩ ሰዎች ይልቅ በመከራ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ አልማዝ የሚሆነው የድንጋይ ከሰል ነው ! አልማዝ በተፈጥሮ መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ልንገራችሁ። አልማዝ የሚሰራው HPHT በሚባል Process ነው። HPHT ማለት High Pressure High Temperature ማለት ነው። አንድ አልማዝ አልማዝ ከመሆኑ በፊት አራት ደራጃዎችን ማለፍ ይኖርበታል። አንደኛ ከምድር በታች ከ300 እስከ 600 ኪሎ ሜትር ዝቅ ብሎ መቀመጥ። ሁለተኛ ከፍተኛ ሙቀት መታደል፣ ከ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬት ቃጠሎ ውስጥ መቀመጥ። ሶስተኛ ከፍተኛ ጭነት ማግኘት። አራተኛ ለረዥም ጊዜ ውስጥ በነዚህ ሁኔታ ውስጥ መቆየት ! እንግዲህ አንድን የድንጋይ ከሰል ወስዳችሁ ከምድር በታች 600 ኪሎ ሜትር ብታወርዱት፣ 1200 ዲግሬ ስንቲ ግሬት ቃጦሎ ውስጥ ብታኖሩት፣ በከፍተኛ ፕሬዠር ውስጥ ብታስቀምጡት እና ለረዥም ጊዚያት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብትተዉት። ከሱሉ አልማዝ ይሆናል ! ከሰሉ ወደ ዳይመንድ ይለወጣል። አንዳንዶቻችሁ በህይወታችሁ ግራ ይገባችኋል፣ በጣም የሚወዳችሁ አምላካችሁ ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር አውርዷችሁ ይሆናል። በማይገባችሁ ፈተና 1200 degree cent great ቃጠሎ ውስጥ አስቀምጧችሁ ፤ በማጣት፣ በመገለል፣ በመገፋት ለረዥም ጊዚያት እየፈተናችሁ "ምንድነው እየተካሄደ ያለው" ብላችሁ እስክትጠይቁ ድረስ ለአምስት አመት፣ ለአስር አመት ከሰው፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ፣ ከጓደኛ ዝቅ አድርጓችሁ ይሆናል። .... "ምን ማለት ነው የሚወደኝ አምላክ ይሄን የሚፈቅደው" ስትሉ .... አልማዝ አድርጎ ሊሰራችሁ፣ ውብ አድርጎ፣ ሊሰራችሁ፣ የምታበሩ አድርጎ ሊያበጃችሁ፣ እንቁ፣ ዳይመንድ፣ አልማዝ ሊያደርጋችሁ ስላሰበ ነው ! አልማዝ ሰባት ባህሪዎች አሉት። አንደኛ ጠንካራ ነው። ወስዳችሁ በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልመዝ ግን ብረት ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል። አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው። ሁለተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው። refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ አለው። ያንጸባርቃል። ሶስተኛው የአልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው። አራተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። እጅግ በጣም ንጹህ ነው። አልማዝ የሚታወቀው በነጹህነቱ ነው። አምስተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። አልማዝ በእሳት አይቃጠልም። አንድ ቤት ውስጥ አልማዝ አለ እንበል ያ አልማዝ ያለበት ቤት ሙሉ ለሙሉ ቢቃጠል አልማዙ ምንም አይሆንም። ምንም። በነበረው ቅርጹ፣ በነበረው ንጽህናው እናገኘዋለን። የሚያስገርመኝን ስድስተኛውን የአልማዝን ባህሪ ልንገራችሁ። ወርቅ ላይ አሲድ ድፉበት ወርቁ ይበላሻል። አልማዝ ላይ አሲድ አፍስሱበት ምንም አይሆንም። አይበላሽም። የመጨረሻው እና ሰባተኛው የአልማዝ ባህሪ በጣም ውድ ነው። በጣም ውድ ነው። የአውራጣትህን ራስ የምታክል ዳይመንድ አንድ ትልቅ ፎቅ ይገዛል። በጣም ውድ ነው። ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር ወርዳችሁ ፣ በ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬት ስቃይ ውስጥ ያለፋችሁ፣ በፕሬዠር ውስጥ ለበርካታ አመታት ያለፋችሁ እናንተ አልማዝ ሁናችሁ የተሰራችሁ ሰዎች ናችሁ። ሰዎች ጠጠር ብትመስሏቸውም አልማዞች ናችሁ። ዋጋችሁ በጣም ውድ ነው። ... ከተማሩ ሰዎች ይልቅ፣ ብዙ ድግሪ ከተሳካላቸው ሰዎች ይልቅ፤ በመከራ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ዋጋ የከፈሉ ሰዎችን አከብራለሁ። በስቃይ ውስጥ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ። ምክንያቱም ዋጋቸው በጣም ውድ ነው። መልካም ምሽት (የዶክተር ወዳጀነህ ንግግርን ለንባብ እንዲመች አድርጋ አሳጥሬ አሰናደሁላችሁ 😃)
Show all...
ግዜ /time/፦ ግዜ አከራክሯል ታላላቅ ሳይንቲስቶችንና የፍልስፍና ሠዎችን ፣አነደነ አይዛክ ኒውተን፣ አልበርት አንስታየንና ካርል ማርክስ ያሉትን። እነዚህ ታላላቅ ሠዎች ግዜን ገልፀውታል፣ በግዜ ተመራምረውበታል፣ ግዜ ቁልቁል ሯጭ መሆኑን አስገንዝበዋል። ለአይዛክ ኒውተን ግዜ ፍፁም ነው፣ ለአልበርት አንስታዬን ግዜ አንፃራዊ ነው፣ ለፈላስፋውና ለምጣኔ ሐብት ተንታኙ ካርል ማርክስ ግዜ ለካምፖንዎች ምርት መሸጫ አገልግሎትን አበርካች ነው። ማንም ሠው ስለ ግዜ በትንሹም ቢሆን ሚስጥራቱን ማወቅ አለበት፣ አለማችን /the universe/ ከግዜ ጋር የተዋሀደና የተገናኘ በመሆኑና ስለ ግዜ የእውቀት ማነስ እውቀታችንን በጣም አናሳ ስለሚያደርገው። ግዜ ለግዜ ዋጋ በሠጡ ታላላቅ ሠዎች አንዲህ ይታወቃል። " ግዜ እንደ ወንዝ ውኃ ተጓዥ ነው፣ ግዜ አቅጣጫ አለው ወደፊት እንጂ ወደኋላ አይጓዝም፣ ግዜ ወቅትንና ተራን ጠብቆ ተጓዥ ነው ቅደም ተከተል አለው፣ ግዜ ተቆጣሪ ነው ከአንድ ድርጊት ወደሌላ የሚሸጋገር። እንደ አይዛክ ኒውተን ግዜ እያንዳንዱን ድርጊት የምንረዳበት በመቁጠሪያ የምናስቀምጠው ነው በቀናት፣ በወራት፣ በአመታት ከፋፍለን፣ ለምሳሌ አስር ሚሊዮን አመታት ፍፁም የሆነ ግዜን አመላካች ሲሆን፣ አሁን ልክ 7:30 ነው ስንልም ትክክለኛውን ግዜ ጠቋሚ ነው። ይህን አልበርት አንስታዬን በንፅፅር ያስቀምጣል። ለምሳሌ አሁን የምሳ ግዜ ነው ስንል ግዜን በምንመገበብት ወቅት አንፃር አስቀመጥነው ማለት ነው ፣ ያው ምሣ የምንበላበት የራሡ የሆነ ሠአት ስላለውና ያም እንዲሁ ግዜን አመላካች በመሆኑ። አለማችን በግዜ አንፃር መች ተገኘች፣ ይህንን ጂኦሎጂስቶች /አለትን አጥኚ ሊቃውንት/ በአለቱ ለውጥ በመነሳት ያረጋግጣሉ።አለም ከተፈጠረች እጅግ ብዙ ዘመናትን አስቆጥራለች ይላሉ የአለት አጥኚ ሊቃውንት፣ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ አመታትን አስቆጥራለች፣ ይህን ማረጋገጫቸውም የአለቶች ከአንዱ አይነት ወደሌላ የሚለወጥበትን የግዜ ብዛት በመተንተን ነው። ምሣሌዎችን መጥቀስ ይቻላል፦ በአለቶች ቅደም ተከተል /geologic time/ ግዜን ስንተነትን እንደሚከተለው ይቀመጣል በቅደም ተከተል ስናስቀምጣቸው በአምስት ዋና ዋና ግዜን ተንተራሽ ክፍልፋዮች ይቀመጣሉ፣ በአለት አለዋወጥ ቋንቋ ስናስቀምጣቸው eons,eras,periods, epochs, ages በመባል በቅደም ተከተል ይታወቃሉ። እያንዳንዱ ምን ያህል ግዜን አመላካች ይሆኑ? እስቲ እንያቸው፦ eon በቢሊዮኖች አመታት የሚመነዘር እጅግ በጣም የረዘመ ወቅት ነው ከ4.6 ቢሊየን እስከ 542 ሚሊዬን አመታትን በውስጡ የሚያካትት። ተከታዩ ERA በመቶ ሚሊዮኖች የታቀፈቱን አመታት የሚያጠቃልል ሲሆን period በአሥርት ሚሊዬን ተቆጣሪ አመታትን የሚጠቀልል ነው። ሶስቱም እጅግ በጣም ብዙ አመታትን እንደሚያጠቃልሉ ነው የምንረዳው። ወደ ብሊዬኑ ሳንሄድ እስቲ አንድ ሚሊዬን አመታትን አስቡ ሚሊዬን አመት ማለትኮ 1000*1000 አመታትን የሚጠቀልል ነው የትዬሌለ መሥሎ የሚታዬን። የሠውን እድሜ በአንፃሩ ስናይ ሳንኖር የሞትን ያስመሥለናል አጅግ በጣም አናሳ በአሥርቶች የሚቆጠር በሁለት ዲጅቶች። 99አመትን አስቡ ያን የኖረ የታደለ አይደለምን ? 100ና ከዚያ በላይ እድሜን በእድሜ ለታደሉ እንተውና። ይህን ግዜ ከምንከተለው እምነት እንዴት እናስታርቃለን? የቀን ቆጠራ በርግጥ አለም ከተፈጠረች ጀምሮ ነውን ? በትክክል። በእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ ሺህ አመታት አንደ አንድ ሰኮንድ ስለሚቆጠር፣ ከሣይንሱ ያልራቁ የኃይማኖት ሊቃውንትም በዚህ ይስማማሉ። የግዜን ቀመር አሳምሮ የሚያውቀው ቀምሮ የፈጠረው ታላቁ ሣይንቲስት በመሆኑ እርሱ የደረሠበትን ደርሰን አፍ መክፈት አይቻልም። መመራመሩን ግን ስላልከለከለን ክብሩ የሠፋ ይሁን፣ ሶቅራጢስም ታላቁ ፈላስፋ ብዙ ከተመራመረ በኋላ የማይታወቀውን ማወቅ ባለመቻሉ በታላቅ አባባል አለማወቁን አስታወቀን እንዲህ በሚል "እኔ የማውቀው ምንም አለማወቄን ነው ።" What I know is that I know nothing." አወን ይህ ሃቅ ነው ሁላችንም የምናውቀው አለማወቃችንን በመሆኑ።
Show all...
ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ይህንን ተናግረዋል ፦ " ፍልስፍና ያስፈልጋል ስትሉም ትፈላሰፋላችሁ ፤ ፍልስፍና አያስፈልግም ስትሉም ትፈላሰፋላችሁ " አርስቶትልን ጠቅሰው ። ፍልስፍና ምንድን ነው ? የሚለው ጥያቄ በፍልስፍና ውስጥ ወሳኝ ጥያቄ ነው ። ጂኦግራፊ ምንድን ነው የሚለው ጥያቄ የጂኦግራፊ ማዕከላዊ ጥያቄ አይደለም ። (በቀጥታ ስለ ጂኦግራፊ ያጠናል እንጂ )። ህግ ምንድነው የሚለው ጥያቄም የህግ ማዕከላዊ ጥያቄ አይደለም (ስለህግጋት ድንጋጌ ያጠናል እንጂ) ። ሌሎችም ሳይንሶች እንደዛው ። ፍልስፍና ምንድነው ስንል ግን የፍልስፍና መሠረታዊና ማዕከላዊ ጥያቄ ነው ። ምክኒያቱም ፍልስፍና የገዛ ስያሜዋን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ ምትንቀሳቀስ ዲስፕሊን ስለሆነች ነው ። መጀመሪያ ፊሎሶፊያ ያሉት ግሪኮቹ ጥንታዊ እና አዲስ ትርጉም ነው ።ሁልጊዜ እየታደሰ ሚቀጥል ትርጓሜ ነው። የቃሉን አመጣጥ (ethnologyውን) ስናየው ፊሎ (love) ፍቅር ማለት ማለት ሲሆን ሶፊያ ደግሞ ጥበብ ማለት ነው ። እዚህ ጋር ማፍቀርን ምን አመጣው ? ለምን ( Desire ) መሻት አላሉትም ? መሻት የፈለግሽውን ነገር ስታገኚ ያበቃል ። ትረኪያለሽ ። ለምሳሌ ዛሬ ማታ ክትፎ / ላዛኛም ይችላል አግኝተሽ ከበላሽ በኋላ እዛ ላይ ያከትማል ፤ እርካታ ላይ ። ፍቅር ካልን ግን ማብቂያ የለሽ ጉዞ ነው ። እገሌን አፈቀርሁ ስትይ ማብቂያ የሌለው ጉዞ ውስጥ ነሽ ። ሶረን ኪየርኪጋርድ " እገሌን እወደው ነበር ፤ አሁን ጠላሁት አትበሉ ።መጀመሪያም አልወደዳችሁትም ።" ይላል ። ስለዚህ ፊሎሶፊያ Love of wisdom ስንል እርካታ ላይ የማይቆም ማለቂያ የሌለው የጥበብ ፍቅር ማለታቸው ነው ። እንግዲህ ሳርቴር ከመሞቱ በፊት አይኑ ጠፍቶ ነበር እንኳን መፅሐፍ ይነበብለት ነበር ። ሶክራቲስ ክሪይቶ ዲያሎግ ላይ ከነ ክሪቶ ጋር ሲመላለስ ይህንን ግቻ ፍልስፍናህን ተውና ክሱ ይነሳልህ ።አልያም ገንዘብ አሰባስበን እናስመልጥህ ቢሉት እስኪ ለምን ? አንድ ምክኒያት ስጡኝ አሳቤን እንድቀይር እያለ ሲከራከር ነበር ። የሰውየውን አካሄድ ስታይው የጤነኛ አይመስልም ምናልባት ወፈፍ አርጎት ይሆን አይታወቅም ። የኛው ፈላስፋ ዘርዓያዕቆብም ከእንፍራንዝ ናና እዚህ አክሱም በከፍተኛ የክህነት ማዕረግ አገልግል ቢሉት የለም! እዚያ መጥቼ የማለምንበትን ከማስተማር እዚሁ (ከፍልስፍናዬ ጋራ ) ምናምንቴ ሆኜ ብቀር እመርጣለሁ ብሏል ። አንዳዶች አሉ ሳያፈቅሩ ሙዚቃን አርትን ሳያጣጥሙ የሚያረጁ ። ምክንያቱም በቫይረሱ መለከፍ ያስፈልጋል ። በጥበብ መንፈስ መዳሰስ ይጠይቃል ። ሆኖም ማንም በጥቂቱም ከመፈላሰፍ አያመልጥም ። ፍልስፍና አልወድም የሚለው ሰው ለምንድንነው ብሎ ራሱን ቢጠይቅ መፈላሰፍ ጀመረ ማለት ነው ። እንዲሁም የትኛውም የትምህርት ጥናት ዘርፍ ሄዶ ሄዶ መጨረሻው ፍልስፍና ነው ። ለ40አመታት ታሪክ ሲያጠኑ ቆይተው በስተመጨረሻ ዞረው ይጠይቃሉ ።' ታሪክ ራሱ ምንድነው? ምን ማለት ነዉ ?' ብለው። በህግም በማቲማቲክስም PhD ሰራህ ማለት Doctor of philosophy ሆንክ ማለት ነው ።Phd ቃሉም ይህንን እሴት ለመጠበቅ ታስቦ የተፈጠረ ነው ። አላለቀም ...
Show all...
" አራዳ ለመሆን ከፈለግክ ፣ ሁሉን አውቅ ለመሆን ካሰብክ ፣ በአንድ ነፍስ ብዙ ለመኖር ከወሰንክ ፣ ዓለማችንን በንስር ዓይን ለማየት ከቆረጥክ ፣ ወደድክም ጠላህ መፃህፍትን ማንበብ አለብህ፤ ያላነበበ ሁሉ ድብን ያለ ፋራ ነው። ዓይኑ የሩቁን አይደለም ፣ የቅርቡንም አጥርቶ አያይም።"                             መልሕቅ ገፅ 14                               በዘነበ ወላ t.me/yelbenlenante
Show all...

👏 1
"ትንሽ ቦታ" በዚህ አመት: ብንጣላ መታረቂያ: ብንታረቅ ለመጣያ: ትንሽ ቦታ መጠለያ: ትንሽ ቦታ መሰደጃ። ምናለበት: ለምናልባት ብንተውለት ፍጹም መሆን ስለማንችል ትንሽ ቦታ እንዋዋል በልባችን ደግ በኩል። ለአንጎላችን መላወሻ: ትንሽ ቦታ እንተውለት "ምናልባት" የምንልበት!! ልክ እንደአምና ለዚህ አመት። ብንጣላ መታረቂያ: ብንታረቅ ለመጣያ: ብንታሰር ይቅር ማያ ይቅር ብንል መታሰሪያ ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ ጥግ ድረስ የለም ስራ : ጥግ ድረስ የለም ፋታ። በልባችን ደግ በኩል : እንፈልግ ባዶ ቦታ የጷግሜ አይነት ትንሽ ቦታ። ለዘመን መለዋወጫ ። ገጣሚና ጋዜጠኛ ነብይ መኮንን
Show all...
👍 3 1
...ጭንላቴ ውስጥ ምንነቱን ያልተረዳሁት ሀሳብ ይራወጣል። አነባለሁ አይሰምርልኝም። እበላለሁ አልጠረቃም። እጠጣለሁ ጥሜን አልቆርጥም። ከሰዎች ጋር እወራለሁ ፤ እስቃለሁ ነገር ግን ሁሉም ነገር የእውነት አይደለም። ልቤ ላይ እንደ መርግ የከበደኝ ስሜት አለ። በቻልኩና ጉጠት ፈልጌ ባወጣው ደስ ባለኝ። በጣም የህመም ስሜት አለው ነገር ግን ውስጡ ደግሞ የተደበቀ ደስ የሚል ስሜትም ይንጸባረቅበታል። አንዳንድ ጊዜ እናቴ ጉያ ስር ውሽቅ አላለሁ። ፀጉሮቼን ስትደባብሰኝ ከሚሰማኝ ስቃይ እፎይ የምል ይመስለኛል። እጆቿን በፀጉሮቼ መሃል እያርመሰመሰች ሩቅ ስትመለከት ምናልባት ትላንትናዋን እያስታወሰች ይሆን ? ወጣትነቷን ፣ አፍላነቷን እላለሁ። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ብቻዬን ስሆን እርቃኔን መስታወት ፊት እሆንና ሁሉ ነገሬን እቃኛለሁ። እንደጅብራ የተገተሩ ጡቶቼን ፣ ሴቴነት ውልብ ሲለኝ የምሰራው ፀጉሬ ፣ ቀጭን ሽንጥና ዳሌዬን ፣ የእግርና የእጅ ጣቶቼን ፣ ውፍረትና ቅጥነቴን በደንብ አያቸዋለሁ። በእርግጥ ከስንጥር መለስ የምል ይመስለኛል ። እነዚህ ሁሉ ስሜት አይሰጡኝም። አንዳንድ ጊዜ ልቤ ውስጥ ተሸጉሮ የሚያሰቃየኝን ስሜት ለመፃፍ እሞክራለሁ። ነገር ግን ጠብ የሚል ነገር አይኖርም። ወይም እፅፍ እፅፍና መልሼ ሳነበው ተራ ነገር ስሜት አልባ ሆኖ አገኘዋለሁ። ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት አእምሮ ሊደክመው ይገባል። አእምሮ ሲነቃ ስራውን በምንም ብታስተኛው አይተኛም። ስሜትን መግለጽ አለመቻልን የመሰለ ህመም ይኖር ይሆን? ወጣትነት አስቸጋሪ ነው። በተመጠነ አካሄድ ካለመራነው እርምጃችን ወደ አዘቅት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ እያንዳንዱ ወጣት መጠነ ርዕይ ሊኖረው ይገባል። የዚህ ሁሉ መንስኤ ግን አንተ ነህ አንተ !!
Show all...
3